ትናንት ስለመጠቀችው የኢትዮጵያ ሳተላይት 10 አጫጭር መረጃዎችን ልናካፍላችሁ ወደድን
===================
ሙሉ ስም፡ Ethiopia Remote Sensing Satellite (ETRSS-1)
የአገልግሎት ቆይታ፡ 2.6 ዓመት
Resolution: 13ሜ
የዕይታ ስፋት (Swath)፡ >60 ኪ.ሜ
ክብደት 60+10 ኪ.ግ
የመንሳፈፊያ ከፍታ፡ 645.3 ኪ.ሜ
መረጃ የማከማቸት አቅም ≥256 Gbits
በስራው የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቁጥር፡ 20
አጠቃላይ ወጪ፡ 210 ሚሊዮን ብር (ከቻይና 6 ሚሊዮን ዶላር፣ ከመንግስት 20 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከተለያዩ አካላት 10 ሚሊዮን ብር)
የአገልግሎት መስኮች፡ የድንበር ምርመራ፣ የከተማ ፕላን፣ ካርታ ስራ፣ አካባቢ ጥበቃ….

በስራ ባህል እና ማይንድሴት ላይ ያተኮረ ሴሚናር በመካሄድ ላይ ነው
***********************************
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው የሁለት ቀን ሴሚናር ዋና ትኩረቱን የፕሮጀክት ማኔጅመንት አተገባበር፣ የስራ ባህል ፍልስፍናዎች እና የማይንድሴት እሳቤ ላይ በማድረግ በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል፡፡ በሴሚናሩ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የተወጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በዋናነት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በሚመሩት የተለያዩ አቅርቦቶች እና የእርስ በእርስ ውይይቶች አማካኘነት መርሃ ግብሩ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
ሴሚናሩ በተከፈተበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በመጠቀም ተቋማትን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል እንደዚህ የሰዎችን አስተሳሰብ የሚቃኝ የስልጠና መርሃግብር መዘጋጀቱ ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም የቴክኖሎጂና የአይሲቲ እሳቤዎችን ለአመራሮች፣ ለሰራተኞች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በስፋት ከማስተዋወቅና ከማስረፅ አንጻር መሰል የማይንድሴት እና ውጤታማ የአሰራር ባህሎችን በትኩረት መዳሰስ አስፈላጊ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በሴሚናሩ የተለያዩ ገለፃዎችን ለተሳተፊው በማድረግ መድረኩን የመሩት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ውጤታማ የስራ ባህልን እና የአስተሳሰብ ለውጥን በትክክል ለማምጣት ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል እንደብዝሃነት፣ የአሰራር ስነ ምግባር፣ አካታችነት እና የምልዓት ወይም Integrity እሳቤዎችን በስፋት ያስረዱ ሲሆን፤ አክለውም በየተቋማቱ ሊኖር የሚገባውን የቢሮክራሲ ሁኔታና የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ከተሞክሯቸው አንፃር በጥልቀት ዳሰዋል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ በተለይም የፕሮጀክት ማኔጅመንት አተገበባር ላይ ባደረጉት ሰፊ ገለፃ የፕሮጀክት እቅድ ከማቅረብ አንስቶ በትግበራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ሪፖርት ምን መምሰል አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንተና ሰተዋል፡፡
በሴሚናር መርሃ ግብሩ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ ያደረጉት እና ተሞክሯቸውን ያካፈሉት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በጀርመን በሚገኘው ሜርሴዲስ ቤንዝ ኩባንያ ውስጥ የፕሮጀክት አስተዳደር ባለሙያ ሲሆኑ፤ ከዚህ በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ጁጂትሱ ፌዴሬሽን የስነ ምግባር ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የምስራቅ አፍሪካ ጁጂትሱ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ያሉ አትዮጵያዊም ናቸው፡፡

የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች የዘር መድሎ ያደርጋሉ ተባለ
*************************************
አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች ነጭ የቆዳ ቀለም ካላቸው ሰዎች በላይ ሌላ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች በትክክል ላይለዩ እና ሊያምታቱ እንደሚችሉ የአሜሪካ መንግስት ጥናት ያስታወቀ ሲሆን ይህም በህግ አስፈፃሚ አካላት በስፋት እየተተገበረ ያለውን የዚህን ቴክኖሎጂ ህፀፆች በማጉላት ቴክኖሎጂው ላይ ያሉ ጥርጣሬዎችን ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ጥናቱ የተከናወነባቸው አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ አልጎሪዝሞች አፍሪካ-አሜሪካውያንን እና የኢሲያዊያን ፊቶች ከነጭ ካውኬዢያን ፊቶች ከ10 እስከ 100 ጊዜ በላይ በስህተት የለዩ ሲሆን ኔቲቭ አሜሪካውያንም በትክክል ካልተለዩት ውስጥ እንደሚገኙ ጥናቱን ያከናወነው የአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ገልጿል፡፡ ጥናቱ በወንጀል ምርመራዎች ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ለመለየት በብዛት የሚገለገለው የአልጎሪዝሙ የአንድ ለብዙ አቻ-መለያ በይበልጥ አፍሪካ-አሜሪካውያን ሴቶችን በትክክል እንዳለየ አሳይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ኩባንያዎች የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎቹ ቀደም ሲል የግለሰቦችን ፆታ በአግባቡ የመለየት ችግሮች እንዳሳዩ ሲያመለክቱ እንደነበር የታወሰ ሲሆን የጥናቱ ውጤትም የፊት አቻ-ልየታው በስነ-ህዝብ ልየታ መስክ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት ማረጋገጫ ሆኗል፡፡
የጥናቱ ውጤት በኤርፖርቶች፣ በፖሊስ ዲፓርትመንቶች እና በጠረፍ ፍተሻዎች እየተለመደ የመጣውን የዚህ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂ አስመልክቶ በፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም በወንጀል ፍትህ አክቲቪስቶች ዘንድ ሲደረጉ የነበሩት የማንቂያ ደውል ማስጠንቀቂያዎች ላይ ተጨማሪ ማስረጃ ሆኗል፡፡ የመንግስት ሳይንቲስቶችም በቴክኖሎጂዎቹ ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች እየተጋሩ እንደሆነ በአሜሪካ የሲቪል ነፃነቶች ማህበር ከፍተኛ የፖሊሲ አናሊስት የሆኑት ጄይ ስታንሊ ተናግረዋል፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ አንድ የተሳሳተ የፊት-አቻ ሲያጋጥም በኤርፖርቶች የሰዎችን በረራ ሊያስተጓጉል፣ የተራዘመ ቃለመጠይቆችን ሊያስከትል እና በተጠርጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተትን ሊያመጣ ከመቻሉም በላይ፤ ለጠንካራ የፖሊሲ ምርመራዎች ሰዎች እንዲዳረጉ፣ በስህተት ወደእስር እንዲሄዱ እና ከዛም ለከፉ እርምጃዎች ሊዳርግ እንደሚችል አክለው ተናግረዋል፡፡
በዚህ በአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት የተከናወነው ጥናት ወደ 100 የሚጠጉ የቴክኖሎጂውን አቅራቢዎች እንደ ኢንቴል፣ ማይክሮሶፍት፣ ቶሺባን እንዲሁም ታዋቂ የቻይና ኩባንያዎች የተካተቱ ቢሆንም የፊት-መለያ ሶፍትዌሮችን ለፖሊስ ዲፓርትመንቶች በብዛት የሚያቀርበው የአማዞን ኩባንያ ግን በጥናቱ አልተሳተፈም፡፡
በጣት የሚቆጠሩ የአሜሪካን ከተሞች እንደ ሳን ፍራንሲስኮ፣ ኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ የመሳሰሉት የፊት-አሻራ መለያ እድገትን በቴክኖሎጂው ላይ የተለያዩ እገዳዎችን በማድረግ ሊቆጣጠሩት እየሞከሩ የሚገኙ ሲሆን እንደ ፖርትላንድ እና ኦሪጎን የመሳሰሉ ከተሞች ደግሞ ከዚያ ባለፈ የፊት-አሻራ መለያዎችን ሙሉ በሙሉ ከክልል መንግስት እና ከግል ኩባንያዎች የማስቀረት ሀሳብ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካን የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት የአሜሪካን ዜጎች እና ግሪን ካርድ ያላቸውን ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸውና ከመውጣታቸው በፊት የፊት-አሻራ መለያ ምርመራውን እንዲደረግ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን የሚዲያን ሪፖርቶች እንዲሁም ጠንካራ ህዝባዊ ተቃዎሞዎችን ተከትሎ እቅዱን ገተውታል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን እና ሮይተርስ

TECHIN weekly seminar
*********************
You are invited to join us today @TECHINhall
Issues for this week:
A Multistage Data Mining For Crime Prevention: The Case of Jimma Town Police Office
Dropout among Primary School Students: Reason, Experience and Mitigating Factors
Presenters:
Bikila Mezgebu and Biniam Wendmu
#TECHINtalk
#TECHIN #weeklyseminar

የቴኪኢን ሳምንታዊ ሴሚናር ተካሂዷል
******************************************
የቴክኖሎጂ እና አኖቬሽን ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ ሃሙስ የሚዘጋጀው የቴኪኢን ሳምንታዊ ሴሚናር በትላንው እለትም በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ሁለት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው የሴሚናር መርሃ ግብር በቅድሚያ በተመራማሪ ቢቂላ መዝገቡ የተዘጋጀው A Multistage Data Mining For Crime Prevention: The Case of Jimma Town Police Office የተሰኘው የምርምር ውጤት ለታዳሚዎች የቀረበ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች እና ጠቃሚ አስተያየቶች መሰረትም ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል፡፡ ተመራማሪ ቢቂላ ያቀረበው ይህ የምርምር ውጤት በጅማ ከተማ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ለወንጀል መከላከል ታስቦ የተሰራውን የመረጃ ልየታ እና የዳታ ክላስተሪንግ ፕሮጀክት የሚያሳይ ሲሆን በሂደቱም በወንጀል ተከሰው የሚገኙ ግለሰቦችን የተለያየ መረጃ በመቀመርና በመመንጠር (Mining) እንዴት ለተሻለ ዉሳኔ እናውለዋለን የሚለውን ጉዳይ የሚያሳይ ነበር።
ከሱ በማስቀጠል የምርምር ውጤቱን ያቀረበው ተመራማሪ ቢኒያም ወንድሙ በቤንች ማጂ ዞን በሚገኝ ወረዳ የተደረገውን ፍሬያማ የምርምር ስራ ያስረዳ ሲሆን በዚህም እንዲሁ ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል። ተመራማሪው በዚህ ጥናት እንዳነሳው በተጠቀሰው ቦታ የሚኖሩ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደሌላ ነገር የሚሳቡበት ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ጥናቱን ለማድረግ እንዳነሳሳው ተናግሯል። በዚህም በተደረገው ሰፊ ጥናት ለችግሮቹ መከሰት ዋና መንስኤ የሆኑትን ጉዳዮች በመለየት እንዴት ከችግሩ መውጣት እንደሚቻል እና ማን ምን መሥራት አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ምክረ ሀሳብ የቀረበበት እንደሆነ ገልጿል።

የስኳር መጠንን ለመለካት የሚውለው መነፅር
******************************************
የብራዜል እና የዩኤስ ሳይንቲስቶች የሰውን እንባ በመጠቀም ደም ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን ለመለካት የሚያስችል መነፅር መስራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ተማራማሪዎቹ ይፋ ያረጉት ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት በመነጽሩ እጀታዎች ላይ በሚገጠም ባዮሴንሰር አማካኝነት ውጤቱን ወደ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ የሚልክ ቴክኖሎጂ ሲሆን፤ ለስኳር ህመምተኞች የምርመራ ጊዜን በማሳጠር እና እንግልትን በመቀነስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡
እንደሚታወቀው የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የግሉኮስ መጠናቸው ለማወቅ ዘወትር ክትትል ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በሽታ በአሜሪካ ውስጥ ብቻ 62 ሚሊዮን ሰዎችን ሲያጠቃ፣ በዓለም ዙሪያ ደግሞ 380 ሚሊዮን ሰዎች በዚህ ህመም ይጠቃሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ደግሞ በቅርብ አሥርት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ውስጥ የስኳር በሽታ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን በ2035 ወደ 580 ሚሊዮን ሰዎችን ሊያጠቃ እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
በበሽታው የተያዙ ብዙ ሰዎች የደም ናሙና ለመስጠት ጣታቸውን በመወጋት እንዲሁም የደም ግሉኮስ መጠናቸው ለመለካት ተንቀሳቃሽ የስኳር መለኪያን (glycosometer) ይጠቀማሉ። ይህ ሂደት በቀን ውስጥ ለብዙ ጊዜ ሊደጋገም የሚችል በመሆኑ በህመም እና በበሽታ (infection) የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡
ታዲያ ሳይንቲስቶች የፈጠሩት ይህ የባዮሴንሰር መነፅር ግሉኮስ ኦክሳይድ (glucose oxide) የሚባለውን ኢንዛይም መለየት ከመቻሉም ባላይ በሰውነታችን ውስጥ በፈሳሽ መልክ የሚገኙ ነፃ የሆኑ የግሉኮስ መጠኖችን ለማወቅ የሚያስችል ነው፡፡ ቴክኖሎጂው እንደቀደሙት መሳሪያዎች በየጊዜው ከጣት ላይ የሚወሰድ ደምን ከማስቀረቱም በተጨማሪ ስኳርን፣ ቫይታሚን እና የአልኮል መጠኖችን በአንድ ላይ መለካቱ ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
ባዮሴንሰሮቹ በእንባ አማካኝነት የስኳር መጠኑን መለካት ሲያስፈልጋቸው ላቺማል (lachrymal gland) የተሰኘውን ዕጢ እንባ እንዲመነጭ ማነሳሳት ያስፈልጋል፡፡ ታዲያ ይህ ከአይን የሚወጣው እንባ ከግሉኮስ ኦክሳይድ ጋር ሲገናኝ የኤሌክትሮኖችን ፍሰት በቀላሉ መለወጥ ስለሚችል፤ በዓይን መነፅሮች እጀታ ላይ በተጫነው ባዮሴንሰር ውስጥ የመጣውን መረጃ በመያዝ እና በመተንተን ውጤቱን ወደሚፈለገው ኮምፒውተር እና ስማርት ስልክ ለመላክ ያስችላል፡፡
ባዮሴንሰሮች በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት በተለይ በህክምናው ረገድ የሰው ልጅን ጤንነት ወደተሻለ ሁኔታ ከፍ ለማድረግ ላቅ ያለ ሚናን የሚጫወቱ ሲሆን ወደፊትም በምርምር ደረጃ እነዚህን ባዮሴንሰሮች በመጠቀም ለተለያዩ የህክምና ግልጋሎቶች ማዋል እንደሚቻል ሳይንቲስቶች ይጠቁማሉ፡፡
ምንጭ
https://www.scidev.net/…/brazilian-researchers-eye-biosenso…

SciDev.Net
Home
SciDev.Net: Bringing science & development together through news and analysis.
በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራችው እና በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሚትር በምትጓዘው መኪና ዙሪያ ከፈጠራው ባለቤት ጋራ ያደረግነውን አጭር ቆይታ በዩትዩብ ቻናላችን ይከታተሉት https://www.youtube.com/watch?v=xvaSA6T_N_Q
YouTube
የምስራች ለኢትዮጵያዊያን!!! በሊትር 40 ኪ.ሜ የምትጓዘዋ መኪና በኢትዮጵያዊዉ ታዳጊ
የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማ ፪
====================
በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና ገቢ ማመንጨት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የተሰሩ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ከሰራተኛው ዘንድ ዛሬ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከጠዋት አንስቶ በተከናወነው መርሀግብር 14 የተቋሙ ሰራተኞች ከተለያዩ ፕሮፖዛሎቻቸው ጋራ በመገኘት ገለፃ የተሰጡ ሲሆን ለአህዝቦተ ሳይንስ ግብዓት ከሚሆኑት አንስቶ ከመንገድ ላይ መፀዳዳት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የከተሞች የንፅና ጉድለት የሚፈቱ ሐሳቦች ለመድረኩ ቀርበዋል፡፡
የዛሬው መርሀ ግብር ለሁለተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን ከሳምንታት በፊትም መሰል 16 የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ቀርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቢሮ ውስጥ አቀማመጣችን ሁኔታ
======================
በቢሮዎ ውስጥ ያልዎት አቀማመጥ ምን ይመስላል? በስራ ቦታስ ምን ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያከናውናሉ? እነዚህ ሀሳቦች የተነሱት ጤናማ የሆነ ሰራተኛን እና የስራ ውጤታማነትን ለማሳደግ ያለመው የጤና ግንዛቤና የቢሮ አጠቃቀም ስልት (ergonomics) ስልጠና ዛሬ ለሰራተኞቻችን በተሰጠበት ወቅት ነበረ፡፡ ከአቀማመጥም ባሻገር ኮምፒውተና ሌሎች መሳሪያዎችን ስንጠቀም ልንወስዳቸው በሚገቡን ጥንቃቄዎች ዙሪያም በጥቁር አንበሳ ሰሆስፒታል የፊዚዮ ቴራፒ ሀኪሟ ዶ/ር ዊንታና መኮንን ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ከእርሳቸው በተጨማሪም በስኳር በሽታና መከላከለያ መንገዶቹ ላይ በኢትዮጵያ ስኳር ህመምተኞች ማህበር እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እያገለገሉ ባሉት ዶክተር ቴዎድሮስ አበራ አማካኝነት ስልጠና ሲሰጥ፤ የስኳር በሽታ ምንነት እንዲሁም በሀገር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተፅዕንዖ ተዳሶበታል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የስኳር ህመምተኞች ድርሻ እንደምትወስድ የገለፁት ዶክተር ቴዎድሮስ በሽታው የህይወት ዘይቤ ለውጥን ተከትሎ ከመምጣቱ አኳያ የአመጋገብ ስርዓትን በማስተካከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ እና በቅድመ ምርመራዎች መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሌላዋ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፊዚቴራፒ ሀኪም ዶ/ር ህይወት ዘላለም አማካኝነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አስመልክቶ የተሰጠ ስልጠናም የዛሬው ዝግጅት አካል ነበረ፡፡ በዚህኛው ክፍል ከተዳሰሱት ጉዳዮች መካከልም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረጋችን አስቀድመን ልናሟላቸው በሚገቡን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም ከስኳር በሽታ ጋራ ያለው ትስስር የገኙበታል፡፡ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዙሪያ ያሉ አጓጉል ልማድ እና አስተሳሰቦች አስወግዶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን በአጥንት ጤና፣ የደም ቧንቧዎች ብሎም ድብርትን ከማስወገድ አንፃር የሚያጎናፅፋቸው ጥቅሞቹ ተካፋይ መሆን እንደሚቻል ዶ/ር ህይወት አስረድተዋል፡፡
ከተሳታፊ ሰራተኞች በተወረወሩ ጥያቄዎች እና በአሳታፊ እንቅስቃሴዎች ታጅቦ በተከወነው በዚህ ዝግጅት ለሌሎች ስልጠናዎችም ቃል የተገባ ሲሆን፤ በተለይም በኒውትሬሽን ባለሙያ የታገዘ ትምህርት ለማቅረብ እንደሚሰራ የስፓይን ኦንሰልታንሲ ባለቤት እና ስራ አስኪያጁ አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡