የመብረቅ ጥቃት መቼና የት እንደሚፈጠር መተንበይ ተቻለ
የመብረቅ ጥቃት መቼና የት እንደሚፈጠር በሰው ሰራሽ አስተውሎት መተንበይ ተቻለ!
ለመተንበየ ከሚያዳግቱ ተፈጥሯዊ ክስተቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው መብረቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ መብረቅ በየወቅቱ ሰዎችንና አንስሳቶችን ይገድላል፤ ቤቶችንና ደኖችን እሳት በማያያዝ ያወድማል እንዲሁም ብዙ መሰል ውድመቶችን ያስከትላል፡፡
የ EPFL’s School of Engineering ተመራማሪዎች በ 30 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ከ 10 እስከ 30 ደቂቃዎች በኋላ ሊፈጠር የሚችል የመብረቅ ጥቃትን ለመተንበይ የሚያስችል ቀላልና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አዲስ ዘዴ ፈጥረዋል፡፡ ዘዴው በአየር ንብረት ጣቢያዎች የሚገኙ መረጃዎችንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በጋራ በማጣመር ይጠቀማል፡፡
አሁን በስራ ላይ ያለው ዘዴ በጣም ውስብስብና ፍጥነት የሚጎድለው ሲሆን ከ ራዳር አና ከ ሳተላይት የሚገኙ መረጃዎችን መጠቀሙ ወጪውን ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡ አዲሱ ዘዴ በአንፃሩ በማንኛውም የአየር ንብረት ጣቢያ የሚገኝ መረጃን መጠቀሙ ከራዳርና ሳተላይት ውጪ የሆኑና የተግባቦት አውታሮች የሌሉባቸውን የገጠር አከባቢዎችን ለማካተት ያስችላል፡፡
በተጨማሪም ወቅታዊ መረጃን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ በፍጥነት ለመተንበይና አውሎነፋስ ወይም ማእበል ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ የማስጠንቀቂያ ደውል ለማበጀት ያስችላል፡፡
የመረጃው ምንጭ scitechdaily ሲሆን የምርምር ስራውም November 8, 2019 Climate and Atmospheric Science, a Nature Partner Journal ላይ መታተሙ ተገልጿል፡፡

ሐሴትን ከበጎነት !!!
*=*=*=*=*=*=*
የሰው ልጅ በምድር ሲመላለስ ታላቅ የመንፈስ እርካታን ከሚያጎናፅፉት ተግባራት መካከል አንዱ ለተቸገረ መድህን፤ ለወገንም አለኝታ መሆን ሲችል እንደሆነ ብዙዎቻችንን ያስማማል፡፡ ከነዚህ በጎ ተግባራት መካከልም ብዙዎችን ከህልፈት የሚታደገው የደም ልገሳ ተግባር ይጠቀሳል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በ፳፻፲፪ የመጀመሪያቸው የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይም የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ፲፰ የቤተሰብ አባላቶቻችን ተገኝተው ደማቸውን ለግሰዋል፡፡ ታድያ ለበጎ አድራጎት ተግባራት እንግዳ ያልሆኑት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች መሰል የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ሲያከናውኑ የዛሬው ለአስራ አንደኛ ጊዜ ነው፡፡
በቅርቡ ይህን መሰል የደም ልገሳዎች በሀገራችን ኢትዮጵያም ቀስ በቀስ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት አጋማሽ ሀገር ቀን ቆጥሮ ቀጠሮ ይዞ ካከናወነው የደም ልገሳ ዘመቻ በላይም ለዚህ ምስክር የሚሆነን አይገኝም፡፡ በዕለቱም በአርባ የሀገራችን ከተሞች ከአስራ አራት ሺህ በላይ ዜጎች ታላቁን ስጦታ ከአካላቸው ቀንሰው ለወገን አካፍለዋል፡፡

የዲጂታል ፋይናንስን ለማሳደግ የሁሉም ትብብር ወሳኝ አንደሚሆን ተገለፀ
***************************************
‘‘Digitizing Finance: Mobile Payment’’ በሚል የተሰናዳው ይህ የአንድ ቀን ወርክሾፕ አንደሃገር በዲጂታል ኢኮኖሚው ላይ ያለንበትን ደረጃ፤ ያሉ ችግሮች እና የሚታዩ መልካም እድሎች በማንሳት እንዴት እንምራው ወይም እናሳድገው በሚለው አጀንዳ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡
በወርክሾፑ የተለያዩ የባንክ ተቋማት፣ የዩኒቨርስቲ ሙሁራን እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሰማሩ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ በባለሙያዎች በቀረቡ ሰፊ ትንተናዎች እና የፓናል ውይይቶች ሰፊ ጊዜ በመስጠት ተካሂዷል፡፡ በመርሃግብሩ ጅማሬ ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የመድረኩ መዘጋጀት በዘርፉ ለሚንቀሳቀሱ ባለሙያዎችና ሌሎች የንግድ ተቋማት የሚፈጥረውን ወርቃማ እድል አንስተው የዲጂታል ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ የሁሉም ትብብር እጅግ መሰረታዊ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ የኬኒያን የዲጂታል ፋይናንስ እንቅስቀሴ እንደተሞክሮ በመጥቀስ ኢትዮጵያም ከዚህ ትልቅ ትምህርት መውሰድ እንደሚገባት እና ኢኒስቲትዩቱም እንዲህ ያሉ የውውይት መድረኮችን በማዘጋጀት የፕሮጀክት ሃሳቦች የሚያድጉበትንና የግንዛቤ ስራዎች የሚስፋፉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ወርክሾፕ ሰፊ ትንተና ካቀረቡ ባለሙያዎች መካከል ከደቡብ አፍሪካ የመጡት ወ/ሪት አንቶኒያ ኢሰር አንዷ ሲሆኑ የዲጂታል ፋይናንስና ቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ እየተራመዱ ያለበትን ሁኔታ እና ሃገራት በዚህ ዘርፍ ውጤት ለማምጣት እየሄዱበት ያለውን ርቀት በጥልቅት አስረድተዋል፡፡ ከሳቸው በማስቀጠል መድረኩን የተረከቡት የቴኪኢን የቀድሞ የስራ ባልደረባ አቶ ዮዳሂ ዘሚካኤል ነባሩ የፋይናንስ ስርዓት በፖሊሲና በመዋቅር ደረጃ በዲጂታል ዘርፉ ላይ የሚኖረውን ጫና በማስረዳት፤ መንግስት እየሄደባቸው ያሉትን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አብራርተዋል፡፡ አቶ ዮዳሂ በተለይም በመሰራት ላይ የሚገኘውን የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ በምሳሌ በማንሳት ሀገሪቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ሃብት ለመፍጠር የሚያስችል ጥሩ መሰራት እንደሚኖራት ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በማስቀጠል መድረኩን የያዙት የቤልካሽ ቴክኖሎጂ ዋና መስራች አቶ አብርሃም ጉልላት ከድርጅታቸው ተሞክሮ በመነሳት በዲጂታል ፋይናንስ እና የሞባይል ክፍያ ዙሪያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንና መልካም እድሎችን አብራርተዋል፡፡ የውርክሾፑ መርሃ ግብር ከእነዚህ አቅርቦቶች በተጨማሪ እጅግ ፍሬያማ በሆኑ የፓናል ወይይቶች የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊ በኩልም ገንቢ አስተያየቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ተንፀባርቀውበታል፡፡

የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማ
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና ገቢ ማመንጨት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የተሰሩ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ከሰራተኛው ዘንድ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በዕለቱ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች ይሆናል ይበጃል ያሏቸውን አስራ ስድስት(16)የፕሮጀክት ሀሳቦች ወደ መድረክ ያመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የእንቦጭን አረምን ወደ ገቢ ምንጭነት የሚለውጥ እና በአዲስ አበባ ላለው የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሄ የሚሰጡ ስርዓቶች ይገኙበታል፡፡
ቀሪ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች በሚቀጥሉት ቀናት ለውይይት እንደሚቀርቡ ሲጠበቅ ከነዚህ መካከልም የተመረጡት ስራ ላይ የሚውሉ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በጋራ እየሰሩ ነው
*********************************
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ ትኩረት ሰተው እየሰሩ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ራፋዬል ሞራቭ አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደሩ ሰሞኑን ከሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እና እስራኤል በአቮካዶ ምርት ለ13 አመታት ሲሰሩ እንደቆዩ እና በቅርብ ጊዜ ደግሞ የኤክስፖርት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ የአቮካዶ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለአቮካዶ ምርት እጅግ የተስማማ የአየር ፀባይ ያላት ከመሆኑ አኳያ ካለፉት አራት አመታት ጀምሮ የተሻሉ የአመራረት ስልቶችን በተለያዩ አካባቢዎች ለመተግበር መሞከሩን የጠቀሱት አምባሳደሩ በተካሄዱ አዋጭ መርሃግብሮችም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኘውን አርሶ አደር የተሻለ የአመራረት ዘዴን በማስለመድ ወደ መካከለኛ ደረጃ እንዲመጣ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ግብርናው ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተከተለ አዳዲስ መንገዶችን የሚሻ በመሆኑ በሃገራቸው የሚተገበሩትን ልዩ ልዩ የአመራረት ዘዴዎች በቴክኒካልም ይሁን በሌሎች መንገዶች ለማገዝ የመንግስታቸው ሙሉ ፍላጎት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ራፋዬል በተለይም ሃገራቸው አንደቅድ ይዛ እየተገበረች ያለውን፤ የስንዴን ምርት ከከፍተኛ ቦታዎች በተጨማሪ በዝቅተኛ ቦታዎች የማምረት ፕሮግራም በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሰፊው እየተሰራበት እንደሚገኝ የተናገሩ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ ሃገራት የንግድ ልውውጥ ላይ ተለዋጭ የምርት ውጤቶችን ከማምጣቱም ባለፈ ተጨማሪ እሴቶችን እንደሚያክል የሚጠበቅ ነው፡፡
መርሃግብሩ ዝቅተኛ በሆነው የእስራኤል መልካምድር የተሻሻለ የመስኖ ስርዓትን በመተግበር እጅግ ስኬታማ ከሆኑ የግብርና ልማት አይነቶች አንዱ ከመሆኑ አኳያ ለኢትዮጵያም የተሻለ ለውጥን ሊያመጣ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
The Ethiopian Herald