TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የኩላሊት ጠጠርን ለማሟሟት ዝንጅብልን እንዴት እንጠቀም?
የዛሬው መረጃ የኩላሊት ጠጠርን ለማሟሟት ምን ማድረግ እንዳለብን ይመክራል… እንደተለመደው ሌሎችም እንዲያነብቡ ለማስቻል ቀድመን ሼር እናድርገው እንላለን… ጤና ለሁሉም!!
ከስራ ስር ዘሮች የሚመደበው ዝንጅብል በሻይ መልክ ለጉንፋን እና ተያያዥ ህመሞች ማከሚያ እና ማገገሚያነት ሲውል ይስተዋላል።
ይሁን እንጅ ዝንጅብል ከዚህ ያለፈ ብዙ ጠቀሜታም አለው፤ በመተንፈሻ አካል ላይ ለሚከሰቱ የጤና እክሎች እና በሽታዎች ማከሚያነት በመዋል።
በተፈጥሮው ጥገኛ ህዋሳትን፣ ቫይረስን፣ ባክቴሪያዎችን እና ለሰውነት መቆጣትና ሽፍታ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን መዋጋት የሚችል እና በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት እንደመሆኑ መጠንም በዚህ ዘመን ገበታ ላይ አስፈላጊው ነገር ሆኗል።
በቪታሚን ሲ፣ በማግኒዥየም እና በሌሎች አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገው ዝንጅብል፥ በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳበር፣ ከህመም ቶሎ ለማገገም፣ የምግብ መፈጨትን ለማስተካከል እና አስምን ለመከላከል እና ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊው ነው።
ከዚህ ባለፈም ለተስተካከለ የልብ ስርአት፣ አደገኛ ኢንፍሉዌንዛን ለመዋጋት እና ለመከላከል፣ የጡንቻ ህመምን ለማስወገድ፣ ለስርአተ ምግብ መንሸራሸር እና ሰውነት ለሚያገኘው የተስተካከለ የኦክስጅን ዑደትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
እስካሁን ከተነገሩለት እና ብዙዎቹ ከሚያውቋቸው ጠቀሜታዎቹ ደግሞ ለየት ያለ የጤና ጠቀሜታም አለው።
ይህም የኩላሊት ጠጠርን ማሟሟት፣ ጉበትን ማጥራትና ማጽዳት እንዲሁም ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ ህዋሶችን መግደልም ሌላው የዚህ ተክል ልዩ ጠቀሜታ ነው።
ይህን ጠቀሜታውን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ነገሮች፥
• አንድ ብርጭቆ ውሃ
• ሩብ የሻይ ማንኪያ በደንብ የተፈጨ ዝንጅብል
• ሩብ የሻይ ማንኪያ ተፈጭቶ የደቀቀ እርድ
• የኮኮናት ወተት
• ወለላ ማር
አዘገጃጀት፦ በመጀመሪያ ውሃውን በደንብ ማፍላት ከዛም ዝንጅብል እና እርዱን የፈላው ውሃ ውስጥ መጨመር።
ከ7 እስከ 10 ደቂቃ አብሮ እንዲፈላ ማድረግ እና ከተባለው ጊዜ በኋላ የኮኮናት ወተቱን ጨምሮ ለሰከንዶች ማቆየት እና ከእሳቱ ላይ ማወረድ።
አብሮ የፈላውን ውህድ በብርጭቆ በመቅዳት እላዩ ላይ ትንሽ ወለላ ማር ጠብ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱም ማጣፈጫ ጨምሮ መጠቀም።
ይህን በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትንና ልዩ የሆኑትን የዚህን ተክል ጠቀሜታ ማግኘት እና ጤናን መጠበቅ ይቻላል።
—---------------
source - scitechethiopia
ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
የቦርጭን ችግር ቦርጫሞች ይረዱታል፡፡ ቦርጫም መሆን ማለት ትልቅ ቋጥኝ ተሸክሞ መዋል ማደር ነው፡፡ እንቅስቃሴን ከመገደብ አልፎ አያሌ የጤና ችግሮችን ያስከትላል… ለምሳሌ እንደ ልብ ሕመም፣ የስኳር ሕመም፣ የደም ግፊት መጨመር እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል ክምችትን ይፈጥራል፡፡ እባክዎ… ቦርጫም ባይሆኑ ሼር ያድርጉት፤ ለቦርጫም ወዳጆችዎ ይደርሳቸዋል፡፡
►መንስኤው
በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም በአማርኛው ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
✔️ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
✔️ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ
✔️ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ
✔️ ጭንቀት
✔️ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
✔️ በተፈጥሮ የሚመጣ
► ቦርጭን ለማጥፋት መፍትሄው
✔️ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት
✔️ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፡- በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማስወገድ አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔️ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር
✔️ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር
✔️ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር
✔️ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡
✔️ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ
✔️ እንቅልፍ አለማብዛት
✔️ ጭንቀት ማስወገድ
✔️ ለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር ናቸው፡፡
✔️ አሁኑኑ ይሞክሩት… ሼር ያድርጉት፡፡

ምንጭ - ዶ/ር ሆነሊያት እና ዶ/ር አለ
ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)
(“ሀኪም በሌለበት” ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ)

ኒሞኒያ(የሳንባ ምች) በጣም አጣዳፊ የሆነ የሳንባ ህመም ነው፡፡ ይህ ህመም አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው በመተንፈሻ አካል በሽታዎች ከተጠቃ በኋላ የሚከሰት ነው፡፡ ኩፍኝ፣ ትክትክ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ብሮንካይትስ፣ አስም ወይም ሌላ ከባድ ህመም ለሳንባ ምች በሽታ መንገድ ይጠርጋሉ፡፡ በሽታው በህፃናትና በሽማግሌዎች ላይ ይበረታል፡፡ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ያለበትም ሰው ተጋላጭነቱ ከፍ ይላል፡፡

መለያ ምልክቶች

• በድንገት ብርድ ብርድ ማለትና የትኩሳት ስሜት፡፡
• ከላይ ከላይ መተንፈስ፣ ማቃሰት፣ አንዳንዴም ፉጨት የመሰለ ድምፅ ይሰማል፡፡ የአፍንጫ ቀዳዳዎች ከአተነፋፈስ ጋር መርገብገብ፡፡
• ትኩሳት (አንዳንድ ጊዜ አራስ ልጆች፣ ሽማግሌዎችና ደካማ ሰዎች ትኩሳት ሳይኖራቸው የሳንባ ምች ሊይዛቸው ይችላል፡፡)
• ከሳሉ ጋር ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሽሮ የሚመስል ወይም ደም ለው አክታ ይወጣል፡፡
• የደረት ውጋት (አንዳንድ ጊዜ) ይኖራል፡፡
• የህመምተኛው ጉስቅልና ጎልቶ ይታያል፡፡
• ፊት ላይና ከንፈሮች አካባቢ ሽፍታ ይወጣል፡፡

ህክምና

በሽታው መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በሃኪሙ የታዘዘውን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ ይገባል፡፡ መድሃኒቱን ጨርሶ ባለመውሰድ የበሽታው ደረጃ ከፍ ሊል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

ሼር አድርጉት (Sharing is Happiness)
ስለጨጓራ ሕመም
===”===”

የገጻችን ቤተሰቦች… በመልዕክት መቀበያችን በደረስን ጥያቄ መሰረት ዛሬ ስለጨጓራ ህመም መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል፡፡ በቅድሚያ ሼር አድርጉት፡፡

► መንስኤዎች

የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶች ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

✔️ ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
✔️ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
✔️ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
✔️ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
✔️ ጭንቀት
✔️ ሲጋራ ማጤስ
✔️ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት

► የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡

✔️ የማቅለሽለሽ ስሜት
✔️ የሆድ መንፋት ስሜት
✔️ ማስመለስ
✔️ የምግብ አለመፈጨት
✔️ የማቃጠል ስሜት በተለይ ከምግብ በኋላ
✔️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔️ የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው

ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡

✔️ የማላብ ስሜት
✔️ የልብ ምት መጨመር
✔️ የትንፋሽ ማጠር
✔️ ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
✔️ ደም ማስመለስ
✔️ ደም የቀላቀለና ከወትሮው የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡

እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡

የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡
አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ9 ልምዶች
1- ልንተኛ ስንል መመገብ
(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡)
2- ያልተመጠነ እንቅልፍ
(ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡)
3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ
(በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ )
4- ጭንቀት እና ውጥረት
(አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡)
5- በፍጥነት መመገብ
(በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ )
6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት)
(የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ )
7- ቁርስን መዝለል
(የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡)
8- የበዛ ጨው መጠቀም
(ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ )
9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
(የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው።
ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን እንዴት መክፈት እንችላለን?

አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡

Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡

Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡

Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot). በትክክል ይሰራል…
TechIn2 pinned «ጠቃሚ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን እንዲሁም የጤና ምክሮችን በየቀኑ እናደርሳችኋለን። ወዳጅ ጓደጎቻችሁንም ወደዚህ ቻናል ይጋብዙ።»
የጨጓራ በሽታን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 3 የቤት ውስጥ ውህዶች

ሰሞኑ የበዓል ነው፡፡ አምሮት የሚቀሰቅሱ ቅባታማ እና በርበሬያማ ምግቦቻቻንን ባላየ ማለፍ የምንችልበት አቅም ያለን አይመስልም፡፡ ስለዚህ የልብ አድርሶ የመሸመበት ማደር ነው ብለን እጃችንን ሰብሰብ አድርገን የገባንበት ካለን እንግዲያውስ ለጨጓራችንም መላ እንፈላልግለት፡፡ እነዚህን በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የሚቻሉትን ውህዶች በመጠቀም እርፍ ማለት እንችላለን፡፡

1- የድንች ጭማቂ

(ድንቹን በ ጁስ መፍጫ ከፈጨነው በኋላ ውሃውን በቀን አንዴ 3 ወይንም 4 የሾርባ ማንኪያ መጠጣት ፡፡ ህመማችን ባስ ካለ በ ቀን ሁለቴ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ የጨጓራችንን የ ph መጠን የሚያረጋጋው ሲሆን የጋዝ ምርቱን እንዲቀንስ በማድረግም የማቃጠል ስሜትን ያጠፋል፡፡

2- የሩዝ ውሃ

(ሩዝ የተቀቀለበትን ውሃ ለተለያየ የህክምና ዓላማ መጠቀም አሁን አሁን ዓለማችን ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡ትንሽ ሩዝ በውሃ ከጣድን በኋላ ሩዙ እንደመብሰል ሲል የውሃው ቀለም ነጭ ይሆናል ያኔ ውሃውን አጥልሎ በመጠጣት የማቃጠልን ስሜት ማጥፋት ይቻላል፡፡ )

3- ማር

(2 የሾርባ ማኒኪያ ንፁህ ማርን ለብ ባለ ውሃ በጥበጥ አድርገን በመውሰድ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ልናገኝ እንችላለን፡፡ህመሙ ሊጀምረን አከባቢ ብናደርገውደግሞ የበለጠ ፍቱን እንደሆነ ይታመናል፡፡
መጽሀፍትን በነፃ
ኦንላይን በቀላሉ መጠቀም ለሚፈልጉ (በቅርቡ)

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል፣ ዲጂታል የሆነ ቤተ-መጽሀፍት የገነባ ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይደረጋል፡፡ እዚሁ በአገራችን የተገነባው ዲጂታል ላይብረሪው የሚከተሉትን የላይብረሪ አገልግሎቶችን ያገኙበታል፤ library.stic.et ብለው ይጎብኙ፤

• የመማሪያ መጽሀፍትን፣ በማህበራዊ ሳይንስም በተፈጥሮ ሳይንስም ዘርፍ

• ጥናታዊ ጽሁፎችን፣ ጆርናሎችን

• የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ህጎችን፣ ድንቦችንና መመሪያዎችን

• የሀገር ውስጥ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መረጃን

• አለም አቀፍ የፓተንት መረጃዎችን በአንድ ላይ ያገኙበታል

በዚህ አጋጣ ዌብሳይቱ_በይፋ_ስራ_የሚጀምረው_ጥር_15_እንደሆነ_ልንገልፅላችሁ_እንወዳለን፡፡

library.stic.et በመጎብኘት የዕውቀት አድማስዎን ያስፉ!!
—----------------------------------------------------------------------

• Educational Books For both Natural and Social sciences
• All kind Research papers
• Local and International Law books and Manuals
• Informations about Mega Projects in Ethiopia
• International patent informations
• Visit here: library.stic.et
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ

5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች

በኮምፒዩተር ሳይንስ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ትክክለኛ የድረገጽ ምንጭ ማወቅ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በየግዜው ዓለምን እያጥለቀለቀ ካለው አዳዲስ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤት ጋር እራስን እኩል ለማስኬድም ሆነ ተጨማሪ ክህሎቶችን ለማግኘት ትክክለኛ የኢንተርኔት ድረገጽ ማግኘት እጅጉን ወሳኝ ነው። ለዚህም ሲባል እነዚህን አምስት ምርጥ የኮምፒዩተር ሳይንስ ድረገጾችን እንሆ ብለናል።

1᎐ Stanford Engineering Everywhere(SEE)

ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ሲሆን ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

2᎐ MIT Open Courseware

የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

3᎐ GitHub.com

GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።

4᎐ W3 Schools

ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት የሚሰጥ ይሰጣል። በተጨማሪም በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

5᎐ Codecademy

አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
ምንጭ፡ The Best Master’s Degrees
መረጀውን ሼር ያድርጉ፡