TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
አርቴፊሻል ቆዳ ተሰራ
************

እንደ ማየት እና ማዳመጥም ሁሉ መዳሰስም ከሰዎች እና ከዓለማችን ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ የማይተካ ሚናን ይጫወታል፡፡የመዳደሰስ ህዋሳችንን መልሶ ሊገነባልን የሚችለው ቴክኖሎጂ haptic feedback በመባል ይወቃል፡፡

በጄሚ ፓይክ የሚመራው የReconfigurable Robotics Lab ሳይንቲስቶች ቡድን ስሜትን የሚለይ እና ለስሜት ምላሽ መስጠት የሚችል ቆዳን መስራት ችለዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ንዝረትን እና ግፊትን የሚለይ እና ለእነሱም ተገቢ ምላሽን የሚሰጥ ሲሆን ከዛ በተጨማሪም ማኛውም አደጋ ቢደርስበት እንደማንኛውም ቆዳ እራሱን የሚተካ እና የሚያክም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሳይቲስቶቹ እንዳሉት ከሆነ እንዲህ ያለ የተቀናጀ ስራን መስራት የሚችል አርቴፊሻል ቆዳ ሲሰራ የመጀመሪያው ከመሆኑም በላይ ጥቅመ ብዙ እና ታላቅ የህክምና አብዮትም ጭምር ነው ሲሉ አስረግጠዋል፡፡ በማከልም በተለይ በህክምና ወቅት ታማሚው እራሱን መግለጥ የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሲሆን የቆዳውን የግፊት እና የንዝረት ሁኔታ በመከታተል ተገቢውን ምላሽ እንድንሰጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡

አርቴፊሻል ቆዳው ከመጀመሪያ አቋሙ እስከ 4 እጥፍ ድረስ መለጥጥ የሚችል ነው ያሉ ሲሆን ይህ ለተጠቃሚው ምቾት እንዲሰጥ ይረዳል ብለዋል፡፡ ምንም እንኳ አሁን ላይ ጣት ላይ ሊጠለቅ የሚችል አርቴፊሻል ቆዳን የሰሩ ቢሆንም በቅርቡ መላ ሰውነት መሸፈን የሚችል የቆዳ ፕሮቶታይፕ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

ምንች፡- ScienceDaily
የኢትዮጵያን ሥነ-ህዝብ ፖሊሲ የሚፈትሽ አዲስ ጥናት ይፋ ሆነ
========================
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን የስነ-ህዝብ ሁናቴ የሚፈትሽ ጥናት ትናንት አመሻሽ ይፋ አድርጓል፡፡ የህዝብ ፖሊሲው ያለበትን ክፍተት ለመሸፈን ታስቦ የተሰራው ይህ ጥናት የሀገራችንን የሥነ-ህዝብ ፖሊሲ አፈፃፀም እንዲሁም የአፈፃፀም ሂደቱን ቅድመ እና ድህረ 2003 በማለት ከፍሎ በመቃኘት ምክረ ሃሳቦችን እንደለገሰ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በምልከታውም ከ2003 አስቀድሞ የነበረው የፖሊሲ አተገባበር መልካም እንደነበር አስቀምጧል፡፡ ሆኖም ከ2003 በኋላ በነበረው አፈፃፀም በርካታ ተግባራት ቢተተገበሩም ዝቅተኛ ውጤት የታየበት እንደነበር አመላክቷል፡፡ ለዚህም የፖለቲካዊ ድጋፍ መመንመን እና በስነ-ህዝብ ተቋማት ያለው ያልጠነከረ ተቋማዊ አደረጃጀትን ጨምሮ አምስት አባይት ምክንያቶች ተቀምጠውበታል፡፡
ሌላው በመድረኩ ይፋ የተደረገው የሥነ-ሕዝብ መዝገበ ቃላት ሲሆን በሀገራችን ያለውን የሥነ-ህዝብ ተኮር ውይቶችን እንዲያግዝ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በመዘዝገበ ቃላት ዝግጅቱም ከሥነ-ሕዝብና ከቋንቋ ዘርፍ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩበት፡፡
ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን በተደረገ የገንዘብና ቴክኒካዊ ድጋፍ የተሰሩት እነዚህ ስራዎች ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን ፈጅተዋል፡፡ በትናንትናው የምረቃ ስነስርዓቱ ማገባደጃም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ እና ወ/ሮ የምሰስራች በላይነህ (ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን) የመዝጊያና ምስጋና ንግግራቸውን አድርሰዋል፡፡

የ2019 3ቱ የፊዚክስ አዋርድ ተሸላሚዎችን አውቀዋቸዋል?
**********************************
የፕሪሴንትን ዩኒቨርስቲው ጀምስ ፒብል ፣ የጄኔቫ ዩኒቨርስቲው ማይክል ማየር እና የካምብሪጅ እና የጄኔቫ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነው ዲዲየር ክዌሎዝ የህዋን አዲስ ሚስጥር በማወቅ በሚል የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ ሁነዋል፡፡
የዘንድሮው የፊዚክስ ኖቤል ሽልማት በሁለት ዋና የአከፋፈል መንገድ ነበር የተሸለመው፡፡ የመጀመሪያው ግማሽ ሽልማት የስዊዲሽ 9 ሚሊዮን ክሮኖር ማለትም 9መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለፕሪሴንትን ዩኒቨርስቲው ጀምስ ፒብል የተሰጠ ሲሆን ይህም ለህዋ ሳይንስ አዲስ የአጠናን መንግድ በመቀየሱ እና አዳዲስ የምርምር አካሄዶችን በማሳየቱ ነው፡፡
ጥናቱ የፍጥረተዓለሙ የብራሀን ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያውን የፍጥረተ ዓለሙን ብርሃ ምንነት የመረመረ ነበር፡፡
ሁለተኛው የፊዚክስ ኖቤል ሽልማት ደግሞ ለጄኔቫ እና ለካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎቹ ለዲዲየር ክዌሎዝ እና ማይክል ማየር የተበረከተ ሲሆን ይህም ከሶላር ሲስተሙ ውጭ ያለ ፕላኔጊዜትን ለመጀመሪያ በማግኘታቸው ምክኒያት ለሳይቲስቶች ፈርቀዳጅ እና መንገድ ጠቋሚ የሆነ ግኝት ሆኗል በሚል ሳቢያ ነበር፡፡
ምንጭ፡- Science News
የወርክሾፕ ጥሪ
**************
October, 15 2019
Foundation of Big Data Analysis and Advanced Computing
# አዲስአበባ #ኢትዮጵያ
# AddisAbeba # Ethiopia
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከዜነሲስ ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር Foundation of Big Data Analysis and Advanced Computing በሚል የአንድ ቀን ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ ወርክሾፑ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ከከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባሉሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም በዚህ ወርክሾፕ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ እንደምትችሉ ማሰወቅ እንወዳለን፡፡ ከአርባዎቹ እድለኛ ተሳታፊዎች መካከል ከሆኑም የ # UDEMY ስልጠናን በነፃ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ቀን፡- ጥቅምት 4 2012 (October 15 2019)
የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://docs.google.com/
forms/d/e/1FAIpQLSe6iJ-htk2LfOHQkRdxBXVc-
5UpG9Vsmj--jd2LwGs5LJ_gfg/viewform
ብሎክቼን ቴክኖሎጂ ለግብርና
*******************************************************************
ብሎክ ቼን ቴክኖሎጂ የብዙ ነገሮችን መልክ እያስቀየረ ያለ ጆከር ነው ሲሉ ይጠሩታል፡፡ ብሎክ ቼን በግብርና ላይም ከባድ የሚባልን ለውጥ እያመጣ ያለ ሲሆን የገበሬዎችን ምርታማነት ከማሳደጉም በላይ በንግዱ ዘርፍ የሚኖረውን ቀጥተኛ ተሳታፊነት እያሳደገ ነው፡፡

ብሎክ ቼን ቴክኖሎጂ ያልተማከለ የመረጃ ቅብብሎሽ እንዲኖር የሚያደርግና ማንኛውንም መረጃ በመረጃ መረብ ውስጥ ለተሳሰረ አካል ክፍት እና ግልፅ አድርጎ የሚያቀብል ተክኖሎጂ ነው፡፡

ብሎክቼን ቴክኖሎጂ ከባድ የሚባል የቴክኖሎጂ ዓይነት አይደለም በዚህ ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚጠበቀው ነገር መረጃዎች ክፍት በሆነ ዳታ ቤዝ ላይ እንዲቀመጡ በማድረግ እና በመረጃ መረብ በማስተሳሰር ለእይታ ክፍት ማድረግ ነው፡፡

ይህ አሰራር በግብርናው ዘርፍ ያለው ፋይዳም ብዙ ነው፡፡ የገበሬዎችን ምርታማነት ማሳደግ ፤ገበያው የሚፈልገውን ምርት ማወቅ፣ የገንዘብ ፍሰቱን መለየት እና የምግብ ዋስታናን እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚሉት በጥቂቱ የሚጠቀሱ ሲሆን ከዛ በተጨማሪም ጥንቃቄ የተሞላው አሰራር እንዲከተሉ በማድረግ የዘመናዊነትን በር እንዲከፍቱ ያስገድዳል፡፡

ምንም እንኳን ይህ ዓይነት አሰራር ለአፍሪካ አዲስ ቢሆንም አሁን ላይ የገበሬዎችን የአሰራር ሁኔታ በመቀየር ገበሬዎች በገያው ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየረዳ ነው፡፡ ይሁንና የብሎክቼን ወርክስፔስ መስራች የሆኑት ሄንክ ቫን ካን እንዳሉት ከሆነ ቴክኖሎጂው ስማርት ስልከ፣ የመብራት ሃይል ፤ የኢንተርኔት ኮኔክሽን እና የተወሰነ የስልክ አጠቃቀም ስልጠና የሚፈልግ በመሆኑ ስራው በአፍሪካ ውስጥ በተቀላጠፈ መልኩ እንዳይከናወን ሆኗል፡፡

በዩጋንዳ ኤቢ አንቤቭ የተሰኘ ቢራ አምራች ድርጅት በዛምቢያ እና በዩጋንዳ ወደ አራት ሺህ የሚጠጉ ገበሬዎች የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ሲሆን ስማርት ስልክን በመጠቀም ብቻ ገበሬዎች ብድር ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታ እና ምርቶቻቸውን በቀጥታ ወደ ገበያ እንዲያስገቡ የሚችሉበትን አሰራር እንዲከተሉ አመቻችቶላቸዋል፡፡

ምንጭ፡- The African Green Revolution Forum
☞ ይህንን ያውቁ ኖሯል?
********************
በፕላኔት ሜርኩሪ ላይ አንድ ቀን ማለት ከመሬት 59 ቀን ጋር እኩል ነው። ይህም ማለት መሬት በራሷ ዛቢያ ላይ አንድ ጊዜ ለመዞር 24 ሰአት ሲፈጅባት ፕላኔት ሜርኩሪ ግን በራሷ ዛቢያ ላይ አንድ ጊዜ ለመዞር 1416 ሰአት ይፈጅባታል።
በሌላ አነጋገር በፕላኔት ሜርኩሪ ላይ አንድ ቀን ማለት 1416 ሰአት ማለት ነው። ይህም ማለት 708 ሰአት ጨለማ፣ 708 ሰአት ብርሐን ማለት ነው። ከስር የምትመለከቱት የሜርኩሪ ፎቶ ነው።
“ወደ ሃብት ሊቀየሩ የሚችሉ ብዙ መረጃዎች ቢኖሩንም አልተጠቀምንባቸውም”
*******************************************************
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዜናይሲስ (ZENYSIS) ቴክኖሎጂስ ጋር በትብብር ያዘጋጀው እና ዋና ትኩረቱን በግዙፍ የመረጃ ትንተና (big data analysis) እና አድቫንስድ ኮምፒዊቲንግ (advanced copmputing) ላይ አድርጎ የተሰናዳው ወርክሾፕ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ጥናትና ምርምሮችን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያከናወኑ ምሁራንም ተሳትፈውበታል፡፡
በፕሮግራሙ መጀመሪያ ላይ የመክፈቻና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ሃገራችን ሌላው ዓለም እየሄደበት ያለውን የመረጃ እና ቴክኖሎጂ ግስጋሴ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን አድራጊ እና ፈጣሪ ልትሆን ቢገባትም የመረጃን ወሳኝነት በሚገባ ካለመረዳታችን እና ካለመገንዘባችን የተነሳ ብዙ ወደ ውጤት ልንቀይራቸው የሚገቡ ሃብቶች ሳንጠቀምባቸው እንደቀሩ አንስተዋል፡፡ መረጃ የቀጣዪ ጊዜ ወርቅ እና ነዳጅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ይህንን መሰረታዊ ሃቅ በመረዳት በግዙፍ የመረጃ ትንተና እና አድቫንስድ ኮምፒውቲንግ ላይ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በግዙፍ መረጃ እና ምጡቅ ትንተና ላይ ሰፊ ንግግር ያደረጉት የዜናይሲስ ቴክኖሎጂስ የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ካሳ የዘርፉን ታሪካዊ አጀማመር ጨምሮ አጠቃላይ ሂደት ካስረዱ በኋላ የግዙፍ መረጃ ትንተና ሊመሰረትባቸው በሚገቡ ወሳኝ ግብዓቶች ላይ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ከእርሳቸው ቀጥለው መድረኩን የተረከቡት የዜናይሲስ ቴክኖሎጂሰ የሃገር ውስጥ ምርትና ቴክኒካል ትግበራ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንተነህ መኩሪያው የቴክኖሎጂ እና የግዙፍ መረጃ ትንተና በመንግስት ተቋማት ውስጥ በሚለው ርዕሳቸው የሃገራችን የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የግዙፍ መረጃ ትንተና በመጠቀም ወሳኝ የሆኑ የፖሊሲ ክፍተቶች ለመሙላት እንደሚችሉ ከድርጅታቸው ተሞክሮ በመነሳት ገልፀዋል፡፡ አቶ አንተነህ በተለይም ድርጅታቸው በተሳተፈበት የጤና ዘርፍ ላይ ዋና ትኩረታቸውን አድረገው በየተቋማቱ የሚገኙትን ብዛት ያላቸው መረጃዎች እንዴት ወደ ውጤት መቀየር እንደሚኖርብን በሰፊው አስረድተዋል፡፡ ወርክሾፑ ከከሳዓትም ሲቀጥል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውቲሽናል ዲፓርትመንት ዋና ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሰለሞን በመረጃ ሳይንስ፣ ሃይ ፐርፎርማንስ ኮምፒዊቲንግ እና በኮምፒውቲሽናል ሳይንስ መሰረታዊ እሳቤዎች ሰፊ ትንተና እና ተሞክሮን አጋርተዋል፡፡
ቢግ ዳታ
************
በዓለማችን ላይ ያለ ነገር ሁሉ ዳታ የማመንጨት ዐቅም አለው፡፡ ሰውነታችን መኪናችን ከባቢያችም ሆነ በዙሪያችን ያለ ቁስ ሁሉ ስለ ብዙ ነገር ብዙ መረጃ ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ እርምጃችን ፣ንግግራችንም ሆነ አኗኗራችን በዘፈቀደ የሚታለፍ አይሆንም ሁሉም ነገር ይቀዳል ይጠራቀማል ትርጉም እንዲሰጥም ይደረጋል፡፡

ይህ ሁኔታ ዓለማችን የተበታተነ ሰውነቷን የሚሰበስብላት የነርቭ ሲስተም ማበጀት እንድትችል የሚረዳት ሲሆን እያንዳንዳችን ደግሞ እንደ ህዋስ በመሆን እናገለግላታለን፤ ይህም ዓለማችን እንደኛው ሁሉ ማስታወስ፣ማጠራቀም እና ማስተንተን እንድትችል ያደርጋታል፡፡ይህ የቢግ ዳታ ቴክኖሎጂ ትልቁ ግብ ነው፡፡

ማንኛውም የምንጠቀመው ማሽን ስልክም ሆነ ኮምፒውተር ትልቁ የመረጃ ምንጭ ነው እያንዳንዱ የጉግል ፍለጋችንም ሆነ ማንኛውም እንቅስቃሴያችን የዲጂታል ፋናን እየጣለ ያልፋል፡፡

ይሁንና ይህ ቁጥር ስፍር የሌለው መረጃ ማለትም ቢግ ዳታ ብቻ ነው፡፡ ጥቅም ላይ መዋል እስካልቻለ እና ትርጉም እንዲሰጥ ተደርጎ ካልተቀናበረ ምንም ነው፡፡ ባለሞያዎቹ እንደተነበዩት ከሆነም በ2020 ዓለም ላይ ያለው መረጃ 40 ዜታባይ ይደርሳል፡፡ ይህም ማለት ዓለማችን ላይ ያለን አሸዋ ሰብስበን በ75 እንማባዛት ነው ሲሉም የመረጃውን ብዛት ይገልጻሉ፡፡

ባለሞያዎቹ እንደሚሉት ከሆነም ባለፉት 3 ዓመታት የተደረገው የዳታ አናላይሲስ ስራ ከዛሬ 3000 ዓመት ገደማ ከተደረገው ይበልጣል፡፡

ታዲያ ቢግ ዳታ ለምን ይጠቅማል;
*****************************************
ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ ብዙ መረጃ በኖረን ቁጥር ብዙ ችግሮችን መፍታት ይቻለናል፤ ይሁንና ምንም ነገር ባለ ሁለት ሰይፍ ነው ችግር መፍታት የሚችለውን ያህል ችግር መፍጠር የማይችል እውነት የለም በመሆኑም መረጃዎችን በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ካልፈቀድን ከባባድ ቀውሶችን መፍጠር እንደምንችለው ሁሉ በተቃራኒው ከግርዶሽ ወዲያ ያሉ የዓለም ችግሮችን እና እንከኖቸን በመዋጋት ባለ ብዙ መፍትሄ የመሆን ዐቅም ይኖረናል፡፡

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ትርጉም እንዲሰጥ ተደርጎ የተተረጎመው መረጃ የአስትሮኖሚ መረጃ ነው ከህዋ የተገኙ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በማቀናበር ስለፍጥረተዓለማችን ብዙ መረዳት እንድንችል የረዳን ሲሆን ከዛም ውስጥ ዛሬ ትንሽ የሚመስለንን ትልቁን እውነት የተዋወቅነው ያኔ ነው ይህም ፀሀይን የምንዞራት እኛ እንጂ እሷ አለመሆኗን መሆኑ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ቀጠለ የሰው ልጅም ማየት ያልቻላቸውን ነገሮች ማየት የሚችልበትን 4ኛ ዓይን አበጀ፤ የማይክሮስኮፕ ግኝት ሴሎች ባክቴሪያዎችን እና ጥቃቅን ነገሮችን በማጋለጥ የሚሊዮኖችን ህይወት ታደገ፡፡ ዓለም በዚህ አላቆመችም ሳይንቲስቶች ወደ ሌላ ክፍታ አሻገሩን በ1650ዎቹ እና በ1660ዎቹ አከባቢ ያገኘናቸው ማይክሮስኮፖች ሊያዩዋቸው የማይችሏቸው ሌላ ረቂቅ እውነታዎች እንዳሉ ታወቀ ያኔም ኤሌክትሮኖች፣ ኒውክለሶች ፣ አተሞችን እና የመሳሰሉትን ታላላቅ ሚስጥሮች በማወቅ የአቶሚክ ዓለም ምዕራፍ ተከፈተ፤ የመብራት እና የኤሌክትሪክ ዘመን መባቻም ተበሰረ፡፡

ቢግዳታን እንደዚህ ያለ ማይክሮስኮፕ እንደሆነ መረዳት እንችላለን ፤በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈጣን መረጃዎችን አጉልቶ የሚያሳየን አጉሊ መነፅር፡፡በምናየው መረጃ ውስጥ እውነትን እና ሚስጥራትን በመፈለግ የሂወትን እከሎች ከስር እና ከጅምሩ መቅጨት ይቻላል፡፡

መረጃዎችን ከማሰባሰብ አልፎ ማቀናበር የሚቻልበት መንገድ ከተበጀ በጤና ፣ በግብርና፣ በኢንደስትሪና በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ የማይታመን ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ዳታ/መረጃ እንደ ተጨማሪ ህዋስ በማገልገል ለብዙ ችግሮች ፈጣን እና ብዙ መፍትሄዎችን እንካችሁ ይላል፡፡

በህክምናው ዘርፍ ብናይ አንድ ሰው ከታመመ በኋላ በመታከም ሊድን ይችላል፡፡ ይህ የህክምና መንገድ ግን ከፍተኛ ለሆነ ለመድሃኒት ወጪ እንዲሁም ከመድሃኒት ጋር ለተያያዙ አላስፈላጊ በሽታዎች ሊያጋልጠን ይችላል ስለዚህ ህክምና ሌላ ተጨማሪ መፍሄ ይዞ መጣ እሱም የቀድሞ መከላከል እና ሳይባባስ በጊዜ ቀላል በሆነ መንገድ የማከም ሂደት ይህም የህብረተሰብ ጤናን አዎንታዊ በሆነ መንገድ ሊረዳ ችሏል፡፡

ነገር ግን አሁንም ትንሽ ከዛ ጠለቅ ብለን እንይ ፋታ የማይሰጡ እና ምልክት የማይተው በሽታዎች ሲከሰቱስ ምን እናደርጋለን? ለምሳሌ ያለጊዜያቸው በመወለዳቸው ምክኒያች ለደቂቃዎች የሚቆይ ኢንፌክሽን ህይወታቸውን ለሚቀጥፋቸው ጨቅላ/አራሶችስ እንዴት እንድረስላቸው? ይሄኔ የቢግዳታ አናላይሲስ ጥቅም ጎልቶ ይወጣል ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በጣም ቀድሞ ያሉ የማይታዩ ስስ ለውጦችን በመዘገብ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ በመሆኑ በሽታው ገና በሽታ የሚል ስያሜ ሳይሰጠው በፊት እንዲቀጭ ይሆናል፡፡

እንግዲህ በዚህ ትንሽዬ የቴሌግራም ግድግዳ ላይ ስለቢግ ዳታ ፋይዳ አውርተን መጨረስ የምንችል ባይሆንም ቢግዳታ በአጠቃላይ ለሰው ልጅ እምርታ ያለውን ታላቅ አስተዋፅዖ በሌላ ጊዜ በሰፊው እንደምናነሳ ቃል እየገባን ለዛሬ በዚህ ላይ እናብቃ፡፡
የአፍሪካ ሶፍትዌር አበልፃጊዎች ጉባዬ እየተካሄደ ነው
*****************************************
AFRICAN DEVELOPERS CONFERENCE በማባል የሚታወቀውና በዋናነት በገበያ (Gebeya) የቴክኖሎጂ ኩባንያ እና በተባባሪነት ደግሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢን ቴክ (Ethiopians in Tech) ጋር የሚዘጋጀው የአፍሪካውያን ደቨሎፐርስ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መካሄድ ጀምሯል፡፡
ለሁለት ቀን የሚዘልቀው ይህ ጉባዬ የዲጂታል ኢንዱስትሪን ዋና ትኩረቱ አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ ሶፍትዌር ኢንጂነሮች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ የSTEM ተማሪዎች እና ስራ ፈጠሪዎች የሚሳተፉበት ነው፡፡
በጉባዬው ላይ ተጽዕኖ ፈጠሪ የሚባሉ እና በዘርፉ ስኬት ያስመዘጉ ድርጅቶች በተወካዮቻቸው በኩል የፓናል ውይይት እና የልምድ ልውውት ያደረጉ ሲሆን በዋናነትም በሳይበር ደህንነት፣ ክላውድ ኮምፒዊቲንግ፣ ዳታ ሳይንስ እና የሞባይል ቴክኖሎጂ በመሳሰሉ የዲጂታል ዘርፎች ላይ ሰፊ ገለፃ እና ምክክር አድርገዋል፡፡
ጉባዬው በነገው ዕለትም በተለያዩ የፓናል ውይይቶች፣ የስልጠና መርሃግብሮች እና የአውደ ርዕይ ትዕይንቶች ሲቀጥል በዘርፉ ስኬታማ ተብለው የሚጠሩት እንደ Orbithealth፣ ዜናይሲስ፣ አይኮ ግላብስ እና ሌሎች መሰል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ልምዳቸውን እና እይታቸውን ለተሳታፊዎች ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡