የtechin ቤተሰቦች ክህሎት ማዳበሪያ በአስገራሚነቱ ቀጥሏል
==========================
ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የtechin ቤተሰቦች ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና በዛሬው ዕለት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ስልጠና ያቀረቡት የላይትሀውስ ስልጠናና ማማከር መስራች እና ዋና ዳይሬተር አቶ እስክንድር ካሳ ሲሆኑ በመርሀ ግብራቸውም በለውጥ አመራርአሳታፊ (change management) እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊውን ጊዜ በመስጠት በአዝናኝና እንቅስቃሴዎች አጅበው አካሂደዋል፡፡
በስልጠናቸው መካከል አስተማሪውን የሚፈጥረው ተማሪው ነው ያሉየለውጥ እስክንድር ለውጥን በመቀበል ረገድ ስላለው የሰዎች እይታ በዝርዝርእንደሆነና በማስረዳት 70 በመቶ የለውጥ እንቅስቃዎች ሳይሳኩ የሚቀሩት በራሳቸው በሰዎች አማካኝነት ይህንንም ለማስተካከል ይረዳ ዘንድ ቀድሞ እራስን ለለውጥ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ የክህሎት ስልጠናው ከዚህ በተጨማሪ ነገሮችን በበጎ ተርጉሞ ስለመረዳት፣ ስለ ይቅር ባይነት እንዲሁም ችግር አፈታት የዳሰሰ ሲሆን በታዳሚዎቹም ላይ ላቅ ያለ ደስታና መነሳሳትን ፈጥሯል፡፡

ለውጥ ለውጥ ለውጥ !!!
==============
“ወደኋላ መኖር ያብቃ፤ በምናብ ውስጥ መኖር ያብቃ፤ አሻጋሪ የሆነ አመራርን ለሀገራችን የምንሰራበት ጊዜ አሁን ነው”
በግለሰባዊ እድገት እና አመራርነት ማበልፀጊያ ላይ በሚሰራው # ሲነርጎስ የተባለ ተቋም ሪጅናል ዳይሬክተር አቶ
# አበራ # ቶላ የTECHIN ቤተሰቦችን ስልጠና ሰተዋል፡፡
የፕሮጀክት ትግበራን እና ተቋማት ግንባታን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዘርፎች ሰፊ ልምድን ያዳበሩት አቶ አበራ "መሪነት አካታች ነው" ፣ "ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን ቅርፅ ማስያዝ ይገባል" ብለዋል፡፡ ጨምረውም “ኃላፊነት የሚሰማው ህዝብ ማለት ኃላፊነትን የሚሰማው ግለሰብ ነው፤ ኢትዮጵያ እኛ ብቻ ሳትሆን ኢትዮጵያ # እኔም ነች” ብለዋል፡፡

የTECHIN ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል
****************************
ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ የቆየው የተቋማችን ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በመርሀ ግብሩ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ስለ ተቋሙ ህጋዊ ቁመና፣ የተሰጡት ኃላፊነቶች እና ተቋማዊ መዋቅር ላይ ሰፊ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን በሰራተኛው በኩልም ሰፋ ያሉ ጥያቄዎች ተነስተው ለውይይት ቀርበዋል፡፡
በከሰዓቱ መርሀግብርም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዋና አማካሪ የሆኑት ዶክተር እሸቴ አበበ በፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዋናነትም የውጤት አሰጣጥ ሂደቶች ምን መምሰል እንደሚኖርባቸው እና የስትራቴጂክ ግቦች በምን መልኩ መቀረፅ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ እንዳሉትም የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በአዲስ ተስፋ ትልልቅ ሃገራዊ ትሩፋቶች ለማስመዝገብ እንዲችል ለስምንት ተከታታይ ቀናት የተደረጉት የማነቃቂያ ስልጠናዎች ትልቅ ዋጋ እንደነበራቸው ያነሱ ሲሆን እያንዳንዱ ሰራተኛም ጥንካሬ በተሞላበት መንፈስ፣ በእኔነት ስሜት እና የተሰጠውን ስራ በአግባቡ በመወጣት ለተቋሙ ስኬት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ታዳጊዎቹ የኢትዮጵያ ተስፉዎች የሮቦት ውድድር አድርገው ተሸለሙ
=================
ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ በሮቦቲክስ እና ፕሮግራሚንግ ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ አስመርቋል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉት እድሜያቸው ከ6-18 የሆኑ ታዳጊ ተማሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተከፍለው የተወዳደሩ ሲሆን ከአንድ እስከ ሦስት የወጡትም ከክብር እንግዳው እጅ የምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል፡፡
በክብር እንግድነት የተገኙት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የትምህርት ስርዓታችን ችግር ፈቺ ተማሪዎችን ማውጣት አለመቻሉን ጠቅሰው መሰል ስልጠናዎች ተማሪዎች ወደፊት በምን መስክ መሰማራት እንዳለባቸው የሚለዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በተቋም ደረጃ የስታርታፕ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ያሉት አቶ ሳንዶካን ከኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ጋራም በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ታዳጊዎችን በሮቦቲክስ እና ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ በማሰልጠን ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ተማሪዎችን በመደበኛ እና የክረምት መርሃ ግብር ተቀብሎ በማተናገድ ላይ ነው፡፡ ስልጠናዎቹም ተማሪዎቹን በሮቦቲክስ ዙሪያ ዕውቀትን ከማስጨበጥ ባሻገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ክህሎታቸውን እንደሚያዳብሩ ተደርገው እንደሚሰጡ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰናክሪም መኮንን (ሰናይ) ገልፀውልናል፡፡

መፅሐፍትን ተጋበዙልን
================
የቴክ ሳይንስ መፅሐፋችን አስራ ስድስተኛው ቅፅ ይህን ይመስላል፡፡ በውስጡ ከኢትዮጵያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና አማራጭ ቴክኖሎጂዎች አንስቶ፣ የአረንጓዴ ከተማ ፅንሰ ሃሳብን፣ የባንክን ስራ ስለሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ሌሎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፋፊ ፅሁፎችን ከአጫጭሮች ጋር በማዋሃድ ወጥቷል፡፡ መፅሐፍቶቹን ከታች የተቀመጠውን የዲጂታል ቤተ መፅሐፍታችን ሊንክ በመጠቀም በሶፍት ኮፒ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በሌላ በኩል ህትመቱን በቅርቡ በሐበሻ፣ ጎልደን፣ ገዳ እና ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች፣ እንዲሁም በተለያዩ ቤተ መፅሀፍት እና የመንግስት ተቋማት በኩል ማግኘት ይችላሉ፡፡
http://library.techin.gov.et/web/dl-site/stic-resources/-/document_library/Y9QR0tiVPdYe/
view_file/4926068?_com_liferay_document_l
ibrary_web_portlet_DLPortlet_I
NSTANCE_Y9QR0tiVPdYe_redirect=http%3A%2F%2Flibrary.techin.gov.et%2Fweb%2Fdl-site%2Fstic-resources%2F-%2Fdocument_library
%2FY9QR0tiVPdYe%2Fview%2F67269
7%3F_com_liferay_document_library_web_portlet
_DLPortlet_INSTANCE_Y9QR0tiVPdYe_redirect%3Dhttp%253A%252F%252Flibrary.techin.gov.et%252Fweb%252Fdl-site%252Fstic-resources%253Fp_p_id%253Dcom_liferay_document_libra
ry_web_portlet_DLPortlet_INSTA
NCE_Y9QR0tiVPdYe%2526p_p_lifecycle%253D0%2526p_p_

የዓይን ምርመራ በማካሄድ ብቻ ለአልዛይመር በሽታ ተጋላጭ መሆን አለመሆንዎን ማረጋገጥ ተቻለ፡፡
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሳንዲያጎ የህክምና ት/ቤት በስብቴበር 9/2019 Neurobiology of Aging በተሰኘው የጥናት ዘርፍ ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ የግልሰቡን ብሌን በመመርመር እና ለመለጠጥ የሚወስድበትን ጊዜ በማየት ብቻ ግለሰቡ ለአልዛይመር እንደተጋለጠ ማወቅ ይቻላል ብለዋል፡፡
ይህ የብሌን በፍጥነት ያለመለጠጥ እና ያለመሰብሰብ ችግር የአልዛይመር በሽታ ያለበት ሰው የበሽታውን ምልክት ከሚያስይበት ከ 10 ዓመታት በፊት የሚታይ በመሆኑ ግለሰቡን ከበሽታው በቀላሉ መታደግ እና በቀላል ዋጋም ማከም እንዲቻል ይረዳል ብለዋል፡፡
ከመጠን በላይ በሆነ የፕሮቲን ክምችት ሳቢያ የሚከሰተው ይህ የአልዛይመር በሽታ የዓለም ህዝብን እያስጨነቀ ያለ እና ባለሞያዎችንም እረፍት እየነሳ ያለ ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም በአዕምሮ ውስጥ ያለው የፕሮቲን ክምችት በቅድሚያ የዓይን ብሌንን እንቅስቃሴ በመግታት የሚጀምር በመሆኑ ግለሰቡ ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት የዓይን ምርመራ በማድረግ እና የብሌኑን እንቅስቃሴ ብቻ በመለካት ሊደረስለት ይቻላል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily

የልጅነት ማብቂያ ዕድሜ ስንት ነው?
የ Murdoch Children’s Research Institute የጉርምስና ጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩት ፕሮፌሰር ሱዛን የዓለም የጤና ድርጅት ለጉርምስና ጤና ትኩረት አይሰጥም ሲሉ ተችተዋል፡፡
የልጅነት ማብቂያ ዕድሜ ስንት ነው? የሚለው ጥያቄ በዓለም የጤና ድርጅት በአግባቡ ባለመመለሱ ምክኒያት አገራት የራሳቸው የሆነ የእድሜ ክልል አበጅተው እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ፕሮፌሰሯ አክለውም የህፃናት ህክምና ላይ የሚሰለጥኑ ባለሞያዎችን በጉርምስና ህክምና ላይም ጨምረን ማሰልጠን ካልቻል በልጅነት ማብቂያ እና በጉርምስና መባቻ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ጤና መታደግ አይቻለንም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ምንም እንኳ የዓለም የጤና ድርጅት የጉርምስና እድሜ ክልል ከ 10 – 19 ዓመት ድረስ ያለው ነው ቢልም በህፃናት ህክምና ባለሞያዎች በአሁኑ ሰዓት እየታከሙ የሚገኙት ታካሚዎች ዕድሜ በወል የሚታወቅ ካለመሆኑ ጋር በጉዳዪ ላይም በቂ የሆኑ ጥናቶች እየተደረጉ አይደለም፡፡
የ Murdoch Children’s Research Institute ተመራማሪዎች የኦንላይን ሰርቬይ በመዘርጋትና በ115 አገራት የሚገኙ 1372 የህፃናት ህክምና ባለሞያዎችን (pediatricians) ያሳተፈ ጥናትን ያከናወኑ ሲሆን በስተመጨረሻም `The Age of Paediatrics' የሚል ጥናት ለህትመት አብቅተዋል፡፡
በጥናቱ ላይም አገራት ወጥ የሆነ የእድሜ ጣሪያ የሌላቸው እንደሆነ የተስተዋለ ሲሆን ለምሳሌ ያህል ደቡብ አፍሪካ ትንሹ የዕድሜ ጣርያ ያላት አገር በመባል የተመዘገበች ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የጉርምስና የእድሜ ጣሪያ 11.5 ዓመት ነው፤ በተቃራኒው አሜሪካን ደግሞ ትልቁ የእድሜ ጣሪያን ያስመዘገበች አገር ስትሆን የአሜሪካን የጉርምስና የዕድሜ ጣሪያ 19.5 ዓመት ነው፡፡
ተመራማሪዎች ከየአገራቱ የተገኙትን የጉርምስና