ሚዲያና ዕውነታ
===========
ሐሳብን ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ ለአንድ ስራ ቀና ውጤት ትልቁን ሚና ይወጣል፡፡ ለዚህ ይረዳ ዘንድ የዛሬውን የቴክ-ኢን ቤተሰቦች የክሆሎት ግንባታ ውሎ በሳይንስ ግንኙነት (science Communication) ላይ በማድረግ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ስልጠናን ሰጥተዋል፡፡ በሀገራችን የጋዜጠኝነት እና ግንኙነት አስተምሮት ሰፊ ልምድ ያላቸው ዶ/ር ጌታቸው በመሰረታዊ የግንኙነት ምንነት፣ መንገዶቹ፣ ታሪካዊ ዳራውን ብሎም በእይታዎቹ ዙሪያ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጥን አከናውነዋል፡፡ ካነሷቸው ሐሳቦች መካከል ግለሰቦች ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር ባላቸው የግንባር ግንኙነት እንዴት ጥሩ ተናጋሪ መሆን እንደሚችል ሲሆን ሃሳቦቹን በአዝናኝ አቀራረብና አስተማሪ ምሳሌዎች አዋዝተው አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ሚዲያው የህብረተሰብን አስተሳሰብ እና ድርጊት በማነፅ ደረጃ ያለውን ጉልበት እንዲሁም የአቀራረባቸውን እይታዊ እውነተኝነትና የዘገባ አድማስ ተዳሰውበታል፡፡
ሌላው በዛሬው መድረክ ስልጠኛ የተሰጠበት ደረጃዎችን (standard) እና አራተኛውን የኢንዱስትሪ አብዮት አስመልክቶ የተሰጠው ሲሆን ኢትዮጵያ ደረጃዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ እንዳለው መኮንን ነበሩ፡፡ ከደረጃዎች ምንነት አንስቶ በውስጡ ምን ይይዛል፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ መዳቢዎች ብሎም በኢትዮጵያ ያለው የደረጃዎች አሰጣጥ ሁኔታና የአሰጣጥ ሰንሰለት ምን ይመስላል የሚለው ተዳሷል፡፡

የtechin ቤተሰቦች ክህሎት ማዳበሪያ በአስገራሚነቱ ቀጥሏል
==========================
ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የtechin ቤተሰቦች ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና በዛሬው ዕለት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ስልጠና ያቀረቡት የላይትሀውስ ስልጠናና ማማከር መስራች እና ዋና ዳይሬተር አቶ እስክንድር ካሳ ሲሆኑ በመርሀ ግብራቸውም በለውጥ አመራርአሳታፊ (change management) እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊውን ጊዜ በመስጠት በአዝናኝና እንቅስቃሴዎች አጅበው አካሂደዋል፡፡
በስልጠናቸው መካከል አስተማሪውን የሚፈጥረው ተማሪው ነው ያሉየለውጥ እስክንድር ለውጥን በመቀበል ረገድ ስላለው የሰዎች እይታ በዝርዝርእንደሆነና በማስረዳት 70 በመቶ የለውጥ እንቅስቃዎች ሳይሳኩ የሚቀሩት በራሳቸው በሰዎች አማካኝነት ይህንንም ለማስተካከል ይረዳ ዘንድ ቀድሞ እራስን ለለውጥ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ የክህሎት ስልጠናው ከዚህ በተጨማሪ ነገሮችን በበጎ ተርጉሞ ስለመረዳት፣ ስለ ይቅር ባይነት እንዲሁም ችግር አፈታት የዳሰሰ ሲሆን በታዳሚዎቹም ላይ ላቅ ያለ ደስታና መነሳሳትን ፈጥሯል፡፡

ለውጥ ለውጥ ለውጥ !!!
==============
“ወደኋላ መኖር ያብቃ፤ በምናብ ውስጥ መኖር ያብቃ፤ አሻጋሪ የሆነ አመራርን ለሀገራችን የምንሰራበት ጊዜ አሁን ነው”
በግለሰባዊ እድገት እና አመራርነት ማበልፀጊያ ላይ በሚሰራው # ሲነርጎስ የተባለ ተቋም ሪጅናል ዳይሬክተር አቶ
# አበራ # ቶላ የTECHIN ቤተሰቦችን ስልጠና ሰተዋል፡፡
የፕሮጀክት ትግበራን እና ተቋማት ግንባታን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዘርፎች ሰፊ ልምድን ያዳበሩት አቶ አበራ "መሪነት አካታች ነው" ፣ "ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን ቅርፅ ማስያዝ ይገባል" ብለዋል፡፡ ጨምረውም “ኃላፊነት የሚሰማው ህዝብ ማለት ኃላፊነትን የሚሰማው ግለሰብ ነው፤ ኢትዮጵያ እኛ ብቻ ሳትሆን ኢትዮጵያ # እኔም ነች” ብለዋል፡፡

የTECHIN ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል
****************************
ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ የቆየው የተቋማችን ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በመርሀ ግብሩ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ስለ ተቋሙ ህጋዊ ቁመና፣ የተሰጡት ኃላፊነቶች እና ተቋማዊ መዋቅር ላይ ሰፊ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን በሰራተኛው በኩልም ሰፋ ያሉ ጥያቄዎች ተነስተው ለውይይት ቀርበዋል፡፡
በከሰዓቱ መርሀግብርም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዋና አማካሪ የሆኑት ዶክተር እሸቴ አበበ በፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዋናነትም የውጤት አሰጣጥ ሂደቶች ምን መምሰል እንደሚኖርባቸው እና የስትራቴጂክ ግቦች በምን መልኩ መቀረፅ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ እንዳሉትም የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በአዲስ ተስፋ ትልልቅ ሃገራዊ ትሩፋቶች ለማስመዝገብ እንዲችል ለስምንት ተከታታይ ቀናት የተደረጉት የማነቃቂያ ስልጠናዎች ትልቅ ዋጋ እንደነበራቸው ያነሱ ሲሆን እያንዳንዱ ሰራተኛም ጥንካሬ በተሞላበት መንፈስ፣ በእኔነት ስሜት እና የተሰጠውን ስራ በአግባቡ በመወጣት ለተቋሙ ስኬት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡