የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከዜናይሲስ ቴክኖሎጂስ ጋር በግዙፍ ዳታ ትንተና|Big Data Analytics| ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
**************************************************************
በግዙፍ የመረጃ ትንተና (big data analysis) እና የቴክኖሎጂ አቅም በመፍጠር ላይ አተኩሮ የሚሰራው አለምአቀፉ የዜናይሲስ (ZENYSIS) ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢነስቲትዩት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
በዛሬው ዕለት የተካሄደው ይህ የፊርማ ስነ ስርዓት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢነስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ እና በዜናይሲስ ቴክኖሎጂስ ሪጂናል ዳይሬክተር አቶ በርናርድ ሎሬንዶ መካከል የተፈፀመ ሲሆን፤ ስምምነቱም በመረጃ ሳይንስና በቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ላይ ሃገራችን እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ለማገዝ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡
በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ስለስምምነቱ አስፈላጊነትና አጠቃላይ የተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ያደረጉት የኢነስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ እንዳሉት አሁን ያለንበት የዲጂታል ዘመን የተደራጀና ጥራት ያለውን መረጃ በመያዝ እና ቀድሞ በማወቅ የሚከናወን በመሆኑ እንደ ቢግ ዳታ አናሊስስ ያሉ የልህቀት መሳሪያዎች እጅግ ወሳኝ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በተለይም እንዳነሱት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢነስቲትዩት የሃገሪቱን የቴክኖሎጂ አቅም በምርምር እና ስርፀት ከመደገፍ ባለፈ ሴክተሮችን የማዘመን እና አቅም የመፍጠር ስራዎችን ለማከናወን የተቋቋመ በመሆኑ እንደ ዜናይሲስ ካሉ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የዜናይሲስ ቴክኖሎጂስ ሪጂናል ዳይሬክተር አቶ በርናርድ ትብብሩን አስመልክተው እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች አፍሪካ ሃገራት መረጃን በጥራት ሰብስቦ እና አደራጅቶ ለፖሊሲ አውጪዎች ማቅረብ ላይ ካለው ክፍተት አኳያ አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸውን መሰል የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ማሳተፍ እና ከእነሱ ጋርም በትብብር መስራት ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
የዜናይሲስ ቴክኖሎጂስ እ.ኤ.አ በ2015 ከጎግል፣ አማዞን እና ናሳ በተወጣጡ የመረጃ እና ሶፍትዌር መሃንዲሶች አማካኝነት የተቋቋመ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን፤ በግዙፍ የመረጃ ትንተና እና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ላይ እየሰራ የሚገኝ ነው፡፡ ኩባንያው ላለፉት ሶስት አመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት አሀጉራት የተለያዩ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም እጅግ ወሳኝ በሆኑ የጤና እና ግብርና ዘርፎች ላይ አተኩሮ ይሰራል፡፡

ችግኝን እንዴት መትከል እና መንከባከብ ዓለብን
============================
ሰኞ ሐምሌ ፳፪ በሐገር ዓቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ሽር ጉድ ውስጥ እንገኛለን፡፡ ሆኖም ከመትከል ባለፈ ዘመቻው ውጤት ያመጣ ዘንድ ችግኞቹን በአግባቡ መትከል እና መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ይረዳ ዘንድ ተከታዮቹን ተግባራት በቅደም ተከተል ማከናወን አለብን፡፡
፩፡ በመጀመሪያ ችግኞቹን የምንተክልበት ጉድጓድ ውስጥ እንደ ድንጋይ እንጨት፣ ቅጠል እና ውሃ ያሉ ባዕድ ነገሮች ካሉ ማውጣት አለብን፤
፪፡ ከጉድጓዱ ተቆፍሮ የወጣውን አፈር ከችግኙ ስሮች ይጣጣም ዘንድ እስከ ጉድጓዱ አጋማሽ ድረስ መልሶ መሙላት ይገባል፤
፫፡ በመቀጠልም ችግኙ ላይ ያለውን ፕላስቴክ አፈሩ ሳይፈስብን በጥንቃቄ በመላጥ ችግኙን እስከ ግንዱ መጀመሪያ ድረስ በጉድጓዱ ማኖር፤
፬፡ ችግኞቹ ተጣመው እንዳይቆሙ በመጠንቀቅ ተቆፍሮ የወጣውን አፈር በፕላስቲክ ተሸፍኖ በነበረው አካል ዙሪያው ጠቅጥቆ መሙላት
፭፡ ከተተከለ በኋላ ውሃ በመጠኑ ማጠጣት (በተለይም አፈሩ ደረቅ ከሆነ)
፮፡ ችግኝ ተሸፍኖባቸው የቆዩትን ፕላስቲኮች በመሰብሰብ በተገቢ ሁኔታ ማስወገድ፡፡
በችግኝ ተከላ ወቅት የሚስተዋሉና መቅረፍ የሚገባን ተደጋጋሚ ስህተቶች
• ችግኝን ከነፕላስቲኩ መትከል፤
• የችግኙ ስር አንዲታይ አድርጎ መትከል፤
• የችግኙን ግንድና ቅጠል ጭምር በጉርጓዱ መቅበር፤
• አፈሩን በትክክል አለመሙላት እና አለመጠቅጠቅ፤
• ችግኙን ሳይተክሉ በጉድጓድ ውስጥ አስቀምጦ ብቻ መሄድ፤
• አጣሞ መትከል፤
• ከአንድ በላይ ችግኝ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ መትከል፤
• የችግኙን ስር አጣሞ መትከል፤
• በውሃ በተሞላ ጉድጓድ ውስጥ መትከል፡፡
ችግኞችንስ ዕንዴት እንንከባከብ?
እንደየ ዝርያ፣ የተተከሉበት አካባቢ እና ወቅት ቢለያይም ችግኞች እስከ ሶስት ዓመታት ድረስ ልዩ እንክብካቤን ይሻሉ፡፡ በዚህም መሰረት ተከታዮቹን መንገዶች ተጠቅመን እንክብካቤን ልንቸራቸው ይገባል፡፡
• ከተተከሉበት ዕለት አንስቶ ችግኞቹን ከሰውና እንስሳት ንክኪ መጠበቅ (ከተቻለ ማጠር)፣ በዙሪያቸው ያለውን አረም፣ ደረቅ ሳር ወዘተ…ማንሳትና ከእሳት መጠበቅ እንዲሁም ከተባይና ነፍሳት ጥቃት በመታደግ ጥበቃ ማድረግ፤
• ብርሃን፣ ውሃና ንጥረ ነገሮችን ስለሚሻሟቸውና ለተባይ መራቢያ ስለሚሆኑ በዙሪያቸው ያለውን አረም ችግኞቹ ከተተከሉ ከሁለተኛው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ ማንሳት፤
• የሞቱ ችግኞች ካሉ ለይቶ መተካት፤
• ከክረምቱ ማብቂያ አንስቶ መኮትኮት፤
• የተተከሉበት አፈር ለምነት የጎደለው ሊሆን ስለሚችል ጉዝጓዝ፣ ቀልዝ፣ ፍግ ወይም ማዳበሪያ ከበጋው ወቅት ጅማሮ አንስቶ ማድረግ፤
• በበጋው ወቅት ሲገባ ወይም የተተከሉት እርጥበት አጠር ቦታ ሲሆን ውሃ ማጠጣት፤
• መመልመልና ማሳሳት፡፡
መልካም የተከላ ጊዜ እንዲሆንልዎ ተመኘን!!!

ተልዕኮው ተሳካ፤ እኛም የድርሻችንን ተወጣን !!!
==============================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒትቲትዩት ሰራተኞች የችግኝ ተከላን በጋራ አከናወነዋል፡፡ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ ሌሎች ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ጨምሮ በተሳተፉበት በዚህ ስነ-ስርዓት ከአዲስ አበባ 75 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የአለልቱ ወረዳ በጠቅላላው 17887 ችግኞች ለመትከል ተችሏል፡፡
አግኝተን ያነጋገርናቸው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታው ዶ/ር ጀማል በሽር ይህ ሐገር ዓቀፍ የችግኝ ተከላተ በጋራ ከተሰራ በሐገር ላይ ዕድገትን ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነ ሲናገሪ የችግኝ ተከላው የተከናወነበት ስፍራም ከመሐል ከተማ መራቁ የገጠሩን ኑሮ ለመገንዘብ ድርብ አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ችግኞቹን ከመትከልም ባለፈ የመንከባከብ ተጋባራት በቀጣይነት አንደሚከናወኑ ጠቁመው አልፈዋል፡፡
ይህ የችግኝ የመትከል ስነ-ስርዓት ከላይ ከተጠቀሱት ተቋማትም በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የተከበረው ምክር ቤታ ዓባላትም ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

የማርጀት ሚስጥር ታወቀ
በሳውዝ ካሊፎርኒያ ኢንጂነሪንግ ዩኒቨርስቲ በሁለት የኬሚካል እና የማቴሪያል ኢንጂነሪን ረዳት ፕሮፌሰሮች የሚመራው ቡድን አማካኝነት የሴሎችን የማርጀት ሚስጥር ለማወቅ ተችሏል፡፡
የማቴሪያል ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰሩ ግራሃም እንዳለው የወጣትንትን ምንጭ ለመቅመስ ወጣትንትን እና ሁኔታውን መመርመር የሚመረጥ በሆንም እኛ ግን በተቃራኒው እርጅናን በመመርመር እርጅናን በትክክለኛ መንገድ ማከም መርጠናል፡፡
ይህም ጥናቱ ሴሌች እንዴት እንደሚያረጁ በመረዳት የሚሰራ ሲሆን ሴሎች በምን ምክኒያት እንደሚያረጁ ከታወቀ ያንን ማስቆም እና የተራዘመ እርጅናን ማምጣት ይቻላል ብለዋል፡፡
ጥናቱ ሴሎች እራሳቸውን መተካት የሚያቆሙበትን እርከን በማጥናት የተጀመረ ሲሆን እዚህ እርከን ላይ እንደ አንጓ ብግነት፣ የአጥንት መሳሳት እና የልብ መድከም የመሳሰሉት የእርጅና ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡
ሴንሴት ሴል በሴል ኡደት ውስጥ የመጨረሻው የሴል ደረጃ ነው፤ ማለትም ሴሎች ሴሎች እራሳቸውን ለመተካት ሲሉ የማይከፈሉበት ደረጃ ማለት ነው፡፡ ይህ የጥናት ቡድን ግን ከዚ አንድ ደረጃ ከፍ በማለት ስለዚህ የሴል ዑደት እርከን አዲስ ነገር ለማወቅ ችሏል እሱም ሴሌች የሴንሴት የሴል ዑደት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ኒውክሎታይድ የተሰኘውን የኬሚካል ዓይነት ማምረት ያቆማሉ፡፡
ኒውክሎታይዶች ለ ዲ.ኤን.ኤ ምስረታ እንደ መሰረተ ዲንጋይ የሚየገለግሉ ኬሚካሎች ናቸው፡፡ስለዚህ ሴል ኒውክሎታይድን ማምረት ሲያቆም ዲኤንኤ መሰራት ስለሚቆም እርጅና ይከሰታል፡፡ ስለዚህ ትላለች የምርምር ቡድኑ ተጠሪ ዴልፋራህ ሴሎች ኒውክሎታይድን ማምረት እንዳያቆሙ ማድረግ ከተቻለ ሰዎች የሚያረጁበትን እድሜ ወደዛ መግፋት ይቻላል፡፡
ይሁንና ሴንሴት ሴል ባለሁለት ስለት ሴል ነው፤ ማለትም በአንድ በኩል ሰውነታችን በካንሰር እንዳይጎዳ የሚረዳ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እርጅና እንዲከሰት ምክኒያት ነው ያሉት ሳይንቲስቶች ሴንሴት ሴል ሳይጎዳ ኒውክሎታይድን ብቻ ማረት የማያቆምበትን መንገድ ለመፍጠር እንድንችል ዘንድ ከባድ የሆነ ምርምር እና ጥናት ልናደርግ ይገባና ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩትን በቴክኖሎጂው መስክ ለማገዝ ቃል ገቡ ***************************************** **********************************
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከአሜሪካ እና ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ከተወጣጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በቴክኖሎጂና መሰል ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስአቶ የሚያስችሉ ውይይቶችን አድርጓል፡፡ በወይይቱ መጀመሪያ ላይ ስለተቋሙ እቅድና አጠቃላይ ዓላማ ገለፃ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ፤ በውጭ ሃገር ኑሮቸውን ካደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር መስራት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ የመንግስትን አሰራር የሚያዘምኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ እየሰራ ከመሆኑ አኳያ እና የጥናትና ምርምር እንዲሁም የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ዋና ስራዎቹ ከመሆኑ አንፃር፤ የትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ድጋፍ እጅግ አስፈላጊ እንደሚሆን አበክረው ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ኢንስቲትዮቱ አቅሙን ለማጎልበት እንዲችል እና ተልኮውን በሚገባ ለማሳካት እንዲችል ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ‘ተስፋ’ የባለሙያውች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ደረጀ ተሰማ (ዶ/ር) በተለዩትመስኮች ድጋፍ ለማድረግ የሚያግዝ የባለሙያዎች ብድን በማቋቋም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርጉ በውይይቱ ላይ ቃል ገብተዋል፡፡

አለምአቀፉን የጠፈር ጣቢያ በጥቂቱ
International Space Station (ISS)
********************************
አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ (ISS) እጅግ ውስብስብ እና በታሪክ የሰው ልጆች የሚገርም የላቀ የአስተሳሰብ ጥበባቸውን ተጠቅመው የሰሩት እጅግ ግዙፍ የምህንድስና ውጤት የሆነ ህዋ ላይ የሚንሳፈፍ የምርምር ማእከል ነው። ይሄ በራሪ ሳተላይት አሁን ላይ ሆነን የምንሰማቸውን አዳዲስ የጠፈር ሳይንስ ግኝቶች ያስገኘ እና እያስገኘም ያለ ላቦራቶሪ እና ጂኦሎጂካል ምርምሮች የሚካሄዱበት ግዙፍ ተቋም ነው። ISS በአማካኝ ከምድራችን በ 400 ኪሎሜትሮች ከፍታ ላይ ይጉዋዛል። ምድርንም አንድ ግዜ ዞሮ ለመጨረስ 90 ደቂቃ ብቻ ይፈጅበታል፤ ይህም የሆነው ISS በሰአት 28,163ኪ.ሜ የመብረር ፍጥነት ስላለው ነው።
ማእከሉ በአንድ ቀን ውስጥ የሚጉዋዘው ርቀት ቢደመር ከምድር እስከ ጨረቃ ደርሶ ለመመለስ የሚፈጀውን ርቀት ይሆናል። ይህ የሚያሳየው ISS ህዋ ላይ እጅግ በጣም ፈጣን ጉዞ እንደሚያደርግ ነው። ISS ጥርት ባለ ጨለማ ሰማይ ላይ ከፕላኔት ቬኑስ ይልቅ ደምቆ ያለማጉያ መነፅር ይታያል። ነገር ግን በፍጥነት ስለሚጉዋዝ ወስን ቦታ አይኖረውም፤ በመሆኑም ISSን ሰማይ ላይ ለማየት የረጅም አመት ልምድ እና መቼ የቱ ጋር ማየት እንዳለብን ማወቅ ያስፈልጋል። ይሄን ግዙፍ ማእከል ለመስራት በስራቸው 15 ሀገራትን ያቀፉ 5 ሀገራት ተሳትፈዋል። የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (NASA)፣ የአውሮፓ፣ የካናዳ፣ የሩሲያ እና የጃፓን የጠፈር ምርምር ተቋማት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ሙሉ ማእከሉን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 100 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር ፈጅቱዋል።
ISS በአጠቃላይ 391ቶን ወይንም 391,000ኪ.ግ ይመዝናል። ይህን የሚያህል ክብደት ያለው ነገር ወደጠፈር ይዞ መውጣት አሁን ባለው ቴክኖሎጂ የማይቻል በመሆኑ ተመራማሪዎች ማእከሉን ወደ 7 ንኡስ በመክፈል ሊወስዱት ችለዋል። በመሆኑም የመጀመሪያውን ንኡስ ማእከል የሆነችውን የሩስያዋን 'ዛራያ' እ.ኤ.አ በ1998 ወደጠፈር እንድትመጥቅ ተደረገ። ዛራያ ለ 2 ሳምንታት ያህል በጠፈር ላይ በምህዋር ስትንሳፈፍ ከቆየች ቡሀላ አሁንም ሩስያ ሰራሹዋ 'የኒቲ' እንድትመጥቅ ተደርጎ ከዛራያ ጋር ጠፈር ላይ በተመራማሪዎች ተገጣጥመው ወጥ ሆኑ። ሁለቱ ብቻ በምህዋር ላይ ለአመት ከመንፈቅ ያክል ሲዞሩ ቆይተው እ.ኤ.አ በ2000 ሌላኛዋ 'ዚቬዝዳ' የተባለችዋ ንኡስ ማእከል ተልካ ተገጥማለች። በመቀጠልም 'ዴስቲኒ' እ.ኤ.አ በ 2001፣ የጃፓን የምርምር ማእከል በ 2009 እና ሌሎችም ንኡሳን ማእከላት ወደጠፈር በመምጠቅ እና እርስ በእርሳቸው በመገጣጠም መሉ ማእከሉ ተሰርቶ ሊያልቅ ችሉዋል።
ማእከሉን በፎቶዎች ስናየው አንሶ ታይቶን ይሆናል። ነገር ግን የፀሀይ ብርሀን መሰብሰቢያ ክንፉን ጨምሮ ስፋቱ አንድ የእግር ኳስ ስታዲየም ይክላል፡፡ ISS በውስጡ ሳሎኖች፣ 2 መታጠቢያ ከፍሎች፣ ጂምናዚየም እና የተመራማሪዎቹ የስራ ቦታ ላቦራቶሪ አለው። ለግዜው በውስጡ መያዝ የሚችለው የተመራማሪዎች ቁጥር 6 ሲሆን ይህ ቁጥር ከግዜ ወደግዜ አዳዲስ ንኡሳን ማእከላት ሲጨመሩ አብሮ ይጨምራል። እነዚህ ንኡሳን ማእከላት በየጊዜው ዘመኑ የደረሰባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይዘው ነው የሚሄዱት። በቅርቡ 3Dprinter፣ የጨረር ግንኙነት መሳሪያ እና ያሉት ማእከሉ ላይ የሚገጠሙ ተወንጫፊ የምርምር ሳተላይቶችን የያዙ ንኡሳን ማእከላት ተልከዋል። እነዚህን ማእከላት በከፊል የሚቆጣጠሩት ISS ላይ ያሉት ተመራማሪዎች ሲሆኑ ገሚሱን ደግሞ ምድር ላይ ያሉ ተመራማሪዎች ይቆጣጠራሉ።
ምንጭ፡ Airtable universe እና E.As

ከቁልቋል ጭማቂ ፕላስቲክ መስራት የቻለቸው ተመራማሪ
*****************************************
**********
አብዛኛውን ጊዜ በቤተ ሙከራ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ምርምሮች በሚሊዮን እና በቢሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ የሚፈስባቸው ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን እጅግ ቀላል በሚባል ወጪ አስገራሚ የምርምር ውጤቶች ሲሰሩ ይታያል፡፡ እነዚህ ምርምሮች ቀላል ወጪ ይውጣበቸው እንጂ እጅግ ከፍተኛ የምርምር ሂደት ተከናውኖባቸው የሚሰሩ ናቸው፡፡
ታዲያ በቅርቡ በሜክሲኮ ሃገር በአንዲት ወጣት ተማራማሪ የተሰራው ሳይንሳዊ ግኝት ካላይ ያነሳነውን ሃሳብ የሚደግፍ ይመስላል፡፡ በሃገሪቱ በሚገኘው ቫሊ ኦፍ አቴማጃክ ዩኒቨርስቲ የኬሚካል ምህንድስና ፕሮፌሰር የሆነቸው ይህች ወጣት ተመራማሪ አስገራሚ ሊባል በሚችል የቤተ ሙከራ ምርምር ከቁልቋል ጭማቂ ባዮዲግሬደብል (biodegradable) የሆነ የፕላስቲክ ቁስ ማውጣት ችላለች፡፡
ሳንድራ ፓስኮይ ኦርቲዝ የተባለችው ይህች ተመራማሪ በሃገሪቱ ታዋቂ የሆነውን የቁልቋል ተክል ጭማቂ በመውሰድ glycerol እና colorants ከተሰኙ ውህዶች ጋር በመቀየጥ ከባዮፕላስቲክ የሚመደብ ቁስ ማግኘት የቻለች ሲሆን ግኝቱም ምንም ተቀጣጣይነት የሌለው እና እንደ ዓሳ ያሉ የውሃ ውስጥ ፍጥረታት ቢመገቡት አንዳች የጎንዮች ጉዳት እንደማይኖረው ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ በአለማችን በስፋት በመተግበር ላይ ያለው ነዳጀን መሰረት ያደረገ የፕላስቲክ ምርት ለውቂያኖሶች እና ለተለያዩ የውሃ አካላት ስነ ምህዳራዊ ሚዛን መናጋት ትልቅ ምከንያት ከመሆኑ አኳያ፣ እንደ ባዮዲግሬደብል ያሉ የፕላስቲክ አይነቶች እጅግ አስፈላጊ መሆናቻውን የሚጠቅሱት የዘርፉ ባለሙያዎች ከቁልቋል ጭማቂ የተገኘው ይህ አዲስ የምርምር ግኝትም እጅግ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፡ Natural Blaze