TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ኩላሊትን የሚጎዱ ነገሮች እና የበሽታው ምልክቶች ሌሎችም ያንብቡት፣ በተን በተን(ሼር) አድርጉት፡፡ ኩላሊትን የሚጎዱ ነገሮች 1. ሽንትን መቋጠር 2.የአልኮል መጠጥ 3.የስጋ አመጋገብን ማብዛት 4.በቂ እረፍት አለማግኘት 5.በቂ ውሃ አለመጠጣት 6. ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ 7. ኢንፌክሽኖችን በተገቢው ሁኔታና በቶሎ አለመታከም 8. በቂ ምግብ አለመመገብ 9. ለሕመም ማስታገሻ ተብለው የተሰሩ መድኃኒቶች አብዝቶ መጠቀም 10. ለብዙ ግዜ የቆየ የኢንሱልን ተጠቃሚነት የኩላሊታችንን ጤንነትን መጠበቅ አቅቶን ለኩላሊት በሽታ ከተጋለጥን በፍጥነት በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል በመሄድ አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ይኖርብናል:: የኩላሊት በሽታ ምልክቶች • የእጅና የእግር እብጠት • መዳከምና አቅም ማጣት • ለመትንፈስ መቸገር • የተደጋገመ ትውከት • የምግብ ፍላጎት መቀነስ • ለነገሮች ትኩረት (concentration) አለመስጠት • አፍችን ውስጥ የብረት ጣዕም(ስሜት) መሰማት ኩላሊታችን ሙሉ ለሙሉ መስራት ካቆመ ያለው መፍትሄ የኩላሊት እጥበት ሲሆን ከዚህ ካለፈ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊያስፈልገን ይችላል:: ከዚህስ አምላክ ይሰውረን፣ እኛም ጥረት አይለየን… ጥንቃቄ ለኩላሊት!! ሌሎችም ያንብቡት፣ በተን በተን(ሼር) አድርጉት፡፡ ምንጭ: ሳይ-ቴክ
አስደናቂ የፓፓዬ የጤና ጥቅሞች

ፓፓዬ በቫይታሚን ሲ እጅግ የበለፀገ የዓለማችን የፍራፍሬ አይነት ነው።
ፓፓዬ ካሉት በርካታ የጤና በረከቶች በጣም የተወሰኑትን ልናካፍልዎ ወደድን
1.በሰውነታችን የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ የጎላ አስተዋኦ ያበረክታል!
ፓፓዬ በፋይበር፣ ቫይታሚን ሲ እና የተለያዩ አንቲኦክሲዳንቶች የበለፀገ በመሆኑ እነዚህ ነገሮች በደምስሮቻችን ውስጥ የኮሌስትሮል ክምችት እንዳይኖር ያደርጋሉ።
በዚህም የስትሮክ ህመም እና ሀይፐርቴንሽን ችግር እናዳይገጥመን የጎላ ሚና አላቸው።
2.ክብደት ለመቀነስ ተመራጭ ነው!
ክብደታቸው እንዲቀንስ የሚፈልጉ ሰዎች ፓፓያን ከምግብ ገበታቸው ማራቅ የለባቸውም፣
ፓፓዬ አንስተኛ ካሎሪ እና ጥሩ የሚባል ፋይበር ያለው በመሆኑ ክብደታችን ባልተፈለገ ሁኔታ እንዳይጨምር ይከላከላል።
3.በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል!
አንድ የፓፓዬ ፍሬ በቀን ከሚያስፈልገን ቫይታሚን ሲ 200 በመቶ ያህሉን በውስጡ ይዟል።
ይህም ኢንፌክሽንን ጨምሮ ሰውነታችን ሊደስበት የሚችለውን ህመም ለመመከት ፓፓዬ እጅግ ተመራጭ የምግብ ዓይነት ያደርገዋል።
4. ፓፓዬ ለስኳር ህመም እንዳንጋለጥ ያግዛል!
ፓፓዬ ምንም እንኳን ጣፋጭ ቢሆንም አንስተኛ የስኳር መጠን በመያዙ የስኳር ህመመተኞች ጨምሮ ለማንኛው ሰው የሚመከር የፍራፍሬ አይነት ነው።
5. ፓፓዬ ለአይን ጤንነት የሚበጅ ነው!
ፓፓዬ በቫይታሚን ኤ የበለፀገ በመሆኑ የተሻለ ዕይታ እንዲኖረን ከማድረጉም ባለፈ ከአይን ጋር ተያያዥ በሆኑ ህመሞች እንዳንጠቃ ይረዳናል።
6. ፓፓዬ በተለይ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ህመም ፍቱን ነው!
በፓፓዬ ውስጥ የምናገኘው ፓፔን የተባለው ኢንዛይም የወር አበባ ፍሰትን ከማስተካከል ባለፈ ተያይዞ የሚከሰትን ህመም በመግታት እፎይታን ያጎናፅፋል።
በመሆኑም በወር አበባ ወቅት ሴቶች ፓፓዬን እንዲያዘወትሩ ይመከራል።
7. ፓፓዬ ካንሰርን ይከላከላል!
ፓፓዬ ፓይቶ ኒውትረንትስ እና ፍላቮኖይድስ በተሰኙ አንቲኦክሲዳነትስ እንደመበልፀጉ መጠን የሰውነታችን ሴሎች እንዳያረጁ፣ እንዳየሞቱ እና ለተለያዩ የካንሰር ህመሞች እንዳየጋለጡ ያደርጋል።
አንዳንድ ጥናቶች በተለይም የፕሮስቴት ካነሰርን በመከላከል ፓፓዬ ወደር እንደሌለው ነው የሚናገሩት።
ምንጭ; Doctor Alle
21 በሳይንስ የተረጋገጡ የማር ጥቅሞች
1.አለርጂን ይከላከላል
2.ሀይል ይሰጣል
3.የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል
4.ሳልን ይከላከላል
5.የዕንቅልፍ እጦትን ያስወግዳል
6.ፎሮፎርን ይከላከላል
7. ቁስልና በቃጠሎ የተጎዳ የሰውነት ክፍል በፍጥነት እንዲያገግም ያደርጋል
8.በሰውነት ላይ የሚወጣን ሽፍታ ያስወግዳል
9.የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል
10.የጨጓራ አሲድ ሾልኮ ወደ ሌላ አካል እንዳይሄድ ይከላከላል
11.የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል
12.ካንሰርን ይከላከላል
13.ሀንግኦቨርን ወይም የዞረድምርን ይከላከላል
14.ብጉርን ያጠፋል
15.ስንፈተ-ወሲብን ይከላከላል
16.ሳይነስና ከሳይነስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህመሞች ይከላከላል
17. የፈንገስ ኢንፌክሽንን ለማከም ያስችላል
18.የድድ ህመምን ለማከም ያገለግላል
19.የሰውነት የቆዳ መቆጥቆጥ ህመምን ያስወግዳል
20.ኮሌስትሮልን ይከላከላል
21.ምርጥ የተፈጥሮ ማጣፈጫ ነው፡፡
غየማስታወስ ችሎታን ለማሻሻል ምርጥ 10 ዘዴዎች
(በቅድሚያ ሼር)

1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ
2. በቂ እንቅልፍ ይውሰዱ
3. ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን ያዘውትሩ
4. ሕይወትዎን በፕሮግራም ይምሩ
5. አዕምሮዎን የሚያነቃቁ ጨዋታዎችን ይጫወቱ
6. ጭንቀትን ይቀንሱ እና በቂ ዕረፍት ያድርጉ
7. የሚያገኙትን መረጃ በምድብ ከፍለው ያስቀምጡ
8. ነገሮችን ከፋፍለው ለማስታወስ ይሞክሩ
9. በቡድን የሚደረጉ ውይይቶች ላይ ተሳታፊ ይሁኑ
10. 10 ለማስታወስ እንዲጠቅምዎ ደጋግመው በአዕምሮ ያመላልሱ
11. ሌላው ማስታወስ ያለብን ለምንወደው ሰው ይሄን መረጃ ሼር ማድረግ ነው!!
ይህን ካነበቡ በኋላ ለሙዝ ያለዎት አመለካከት በእጅጉ ይቀየራል::

ሙዝ ሶስት የተፈጠሮ ስኳሮችን (ማለትም ሱክሮስ፣ ፍሩክቶስ እና ግሉኮስ) ከፋይበር ጋር አጣምሮ ይዟል:: እነዚህም የሰዉነታችንን ኃይል ከፍ የማድረግ አስተዋፅኦ አላቸው::

ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከዘጠና ደቂቃ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ በኋላ 2 ሙዝ የሚመገቡ ስፖርተኞች እንደገና ኃይላቸውን ማደስ ይችላሉ:: ለዚህም ነው - በዓለማችን ታላላቅ ስፖርተኞች ዘንድ ‘ሙዝ’ ተወዳጅ እና ተመራጭ ፍራፍሬ የሆነው::

ይህ ብቻ አይደለም: ሙዝ የሚመገቡ ሰዎች የተለያዩ ህመሞችና ከባድ ሁኔታዎችን የመከላከል አቅማቸው እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው:: ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፤

1. የአንጀት ቁስለትን ይከላልከላል
2. ከሀንግ ኦቨር (HANG OVER) በፍጥነት ያላቅቃል
3. አእምሮ እንዲነቃቃ ያግዛል
4. የደም ማነስ ችግርን ያስዎግዳል
5. የሰዉነት ሙቀትን ለመቆጣጠር ይረዳል
6. የድብርት ስሜትን ያስዎግዳል፤ እንዲሁም ራስን ለማረጋጋት ይጠቅማል
7. ለደም ግፊትን ያስታግሳል
8. የሰገራ ድርቀትን ይከላከላል
9. የወር አበባን ተከትሎ የሚመጣ የስሜት መለዋወጥን ይቀንሳል
10. ቃርን ያስወግዳል
11. ሌላው በጣም የሚገርመው ከወባ ትንኝ ንክሻ ይከላከላል (ቆዳዎትን በልጣጩ ከቀቡት) – ይቺኛዋ መረጃ በተለይ በሞቃታማው የአገራችን ክፍል ለምትገኙ ትሁንልን ብለናል!!

በተጨማሪ:
አንድ ሙዝ ከሌላ ፍራፍሬ ጋር ስናወዳድረው ለምሳሌ ከአንድ አፕል (an apple) ጋር ብናወዳደር:-
አንድ ሙዝ በውስጡ የአፕልን
• 4 እጥፍ ፕሮቲን
• 2 እጥፍ ካርቦሃይድረት
• 3 እጥፍ ፎስፈረስ
• 5 እጥፍ vit A እና ብረት(IRON)
• እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ፖታሽየም የያዘ ነው::
(ለሌሎች share ማድረግዎን እንዳይዘነጉ!)

---------------
source - ወይ ማወቅ ደጉ እና ሳይቴክ
የኩላሊት ጠጠርን ለማሟሟት ዝንጅብልን እንዴት እንጠቀም?
የዛሬው መረጃ የኩላሊት ጠጠርን ለማሟሟት ምን ማድረግ እንዳለብን ይመክራል… እንደተለመደው ሌሎችም እንዲያነብቡ ለማስቻል ቀድመን ሼር እናድርገው እንላለን… ጤና ለሁሉም!!
ከስራ ስር ዘሮች የሚመደበው ዝንጅብል በሻይ መልክ ለጉንፋን እና ተያያዥ ህመሞች ማከሚያ እና ማገገሚያነት ሲውል ይስተዋላል።
ይሁን እንጅ ዝንጅብል ከዚህ ያለፈ ብዙ ጠቀሜታም አለው፤ በመተንፈሻ አካል ላይ ለሚከሰቱ የጤና እክሎች እና በሽታዎች ማከሚያነት በመዋል።
በተፈጥሮው ጥገኛ ህዋሳትን፣ ቫይረስን፣ ባክቴሪያዎችን እና ለሰውነት መቆጣትና ሽፍታ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን መዋጋት የሚችል እና በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት እንደመሆኑ መጠንም በዚህ ዘመን ገበታ ላይ አስፈላጊው ነገር ሆኗል።
በቪታሚን ሲ፣ በማግኒዥየም እና በሌሎች አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገው ዝንጅብል፥ በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳበር፣ ከህመም ቶሎ ለማገገም፣ የምግብ መፈጨትን ለማስተካከል እና አስምን ለመከላከል እና ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊው ነው።
ከዚህ ባለፈም ለተስተካከለ የልብ ስርአት፣ አደገኛ ኢንፍሉዌንዛን ለመዋጋት እና ለመከላከል፣ የጡንቻ ህመምን ለማስወገድ፣ ለስርአተ ምግብ መንሸራሸር እና ሰውነት ለሚያገኘው የተስተካከለ የኦክስጅን ዑደትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
እስካሁን ከተነገሩለት እና ብዙዎቹ ከሚያውቋቸው ጠቀሜታዎቹ ደግሞ ለየት ያለ የጤና ጠቀሜታም አለው።
ይህም የኩላሊት ጠጠርን ማሟሟት፣ ጉበትን ማጥራትና ማጽዳት እንዲሁም ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ ህዋሶችን መግደልም ሌላው የዚህ ተክል ልዩ ጠቀሜታ ነው።
ይህን ጠቀሜታውን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ነገሮች፥
• አንድ ብርጭቆ ውሃ
• ሩብ የሻይ ማንኪያ በደንብ የተፈጨ ዝንጅብል
• ሩብ የሻይ ማንኪያ ተፈጭቶ የደቀቀ እርድ
• የኮኮናት ወተት
• ወለላ ማር
አዘገጃጀት፦ በመጀመሪያ ውሃውን በደንብ ማፍላት ከዛም ዝንጅብል እና እርዱን የፈላው ውሃ ውስጥ መጨመር።
ከ7 እስከ 10 ደቂቃ አብሮ እንዲፈላ ማድረግ እና ከተባለው ጊዜ በኋላ የኮኮናት ወተቱን ጨምሮ ለሰከንዶች ማቆየት እና ከእሳቱ ላይ ማወረድ።
አብሮ የፈላውን ውህድ በብርጭቆ በመቅዳት እላዩ ላይ ትንሽ ወለላ ማር ጠብ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱም ማጣፈጫ ጨምሮ መጠቀም።
ይህን በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትንና ልዩ የሆኑትን የዚህን ተክል ጠቀሜታ ማግኘት እና ጤናን መጠበቅ ይቻላል።
—---------------
source - scitechethiopia
ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
የቦርጭን ችግር ቦርጫሞች ይረዱታል፡፡ ቦርጫም መሆን ማለት ትልቅ ቋጥኝ ተሸክሞ መዋል ማደር ነው፡፡ እንቅስቃሴን ከመገደብ አልፎ አያሌ የጤና ችግሮችን ያስከትላል… ለምሳሌ እንደ ልብ ሕመም፣ የስኳር ሕመም፣ የደም ግፊት መጨመር እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል ክምችትን ይፈጥራል፡፡ እባክዎ… ቦርጫም ባይሆኑ ሼር ያድርጉት፤ ለቦርጫም ወዳጆችዎ ይደርሳቸዋል፡፡
►መንስኤው
በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም በአማርኛው ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
✔️ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
✔️ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ
✔️ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ
✔️ ጭንቀት
✔️ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
✔️ በተፈጥሮ የሚመጣ
► ቦርጭን ለማጥፋት መፍትሄው
✔️ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት
✔️ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፡- በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማስወገድ አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔️ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር
✔️ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር
✔️ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር
✔️ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡
✔️ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ
✔️ እንቅልፍ አለማብዛት
✔️ ጭንቀት ማስወገድ
✔️ ለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር ናቸው፡፡
✔️ አሁኑኑ ይሞክሩት… ሼር ያድርጉት፡፡

ምንጭ - ዶ/ር ሆነሊያት እና ዶ/ር አለ
ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)
(“ሀኪም በሌለበት” ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ)

ኒሞኒያ(የሳንባ ምች) በጣም አጣዳፊ የሆነ የሳንባ ህመም ነው፡፡ ይህ ህመም አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው በመተንፈሻ አካል በሽታዎች ከተጠቃ በኋላ የሚከሰት ነው፡፡ ኩፍኝ፣ ትክትክ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ብሮንካይትስ፣ አስም ወይም ሌላ ከባድ ህመም ለሳንባ ምች በሽታ መንገድ ይጠርጋሉ፡፡ በሽታው በህፃናትና በሽማግሌዎች ላይ ይበረታል፡፡ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ያለበትም ሰው ተጋላጭነቱ ከፍ ይላል፡፡

መለያ ምልክቶች

• በድንገት ብርድ ብርድ ማለትና የትኩሳት ስሜት፡፡
• ከላይ ከላይ መተንፈስ፣ ማቃሰት፣ አንዳንዴም ፉጨት የመሰለ ድምፅ ይሰማል፡፡ የአፍንጫ ቀዳዳዎች ከአተነፋፈስ ጋር መርገብገብ፡፡
• ትኩሳት (አንዳንድ ጊዜ አራስ ልጆች፣ ሽማግሌዎችና ደካማ ሰዎች ትኩሳት ሳይኖራቸው የሳንባ ምች ሊይዛቸው ይችላል፡፡)
• ከሳሉ ጋር ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሽሮ የሚመስል ወይም ደም ለው አክታ ይወጣል፡፡
• የደረት ውጋት (አንዳንድ ጊዜ) ይኖራል፡፡
• የህመምተኛው ጉስቅልና ጎልቶ ይታያል፡፡
• ፊት ላይና ከንፈሮች አካባቢ ሽፍታ ይወጣል፡፡

ህክምና

በሽታው መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በሃኪሙ የታዘዘውን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ ይገባል፡፡ መድሃኒቱን ጨርሶ ባለመውሰድ የበሽታው ደረጃ ከፍ ሊል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

ሼር አድርጉት (Sharing is Happiness)
ስለጨጓራ ሕመም
===”===”

የገጻችን ቤተሰቦች… በመልዕክት መቀበያችን በደረስን ጥያቄ መሰረት ዛሬ ስለጨጓራ ህመም መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል፡፡ በቅድሚያ ሼር አድርጉት፡፡

► መንስኤዎች

የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶች ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

✔️ ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
✔️ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
✔️ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
✔️ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
✔️ ጭንቀት
✔️ ሲጋራ ማጤስ
✔️ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት

► የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡

✔️ የማቅለሽለሽ ስሜት
✔️ የሆድ መንፋት ስሜት
✔️ ማስመለስ
✔️ የምግብ አለመፈጨት
✔️ የማቃጠል ስሜት በተለይ ከምግብ በኋላ
✔️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔️ የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው

ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡

✔️ የማላብ ስሜት
✔️ የልብ ምት መጨመር
✔️ የትንፋሽ ማጠር
✔️ ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
✔️ ደም ማስመለስ
✔️ ደም የቀላቀለና ከወትሮው የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡

እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡

የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡
አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ9 ልምዶች
1- ልንተኛ ስንል መመገብ
(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡)
2- ያልተመጠነ እንቅልፍ
(ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡)
3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ
(በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ )
4- ጭንቀት እና ውጥረት
(አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡)
5- በፍጥነት መመገብ
(በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ )
6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት)
(የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ )
7- ቁርስን መዝለል
(የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡)
8- የበዛ ጨው መጠቀም
(ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ )
9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
(የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው።