TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የዕፅዋት ተከላን አከናወኑ
******************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስትቲውት ሰተራተኞች በዛሬው እለት የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ በመገኘት ዕፅዋትን ተክለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የክፍያ መንዶች ኢንተርፕራይዝ ጋራ በጋራ የተከወነው ይህ የዕፅዋት ተከላ በዓመቱ አራት ቢሊዮን ዕፅዋትን ለመትከል የተያዘው ሐገራዊ ዕቅድ አካል ነው፡፡
ይህን ተግባር በማስመልከት ቃለ መጠይቅ ያደረግንላቸው የኢንስትቲውታችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ መሰል ክንውኖች ለተቋሙ አዲስ ሁነት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም በተያዩ ጊዜያት ዕፅዋትን የመትከል ስነ ስራ እንደተሰራ ገልፀውልናል፡፡ አያይዘውም የተጀመረውን ሐገር ዓቀፍ እንቅስቃሴ በበጎ በመመልከት ሌሎች አካላትም እንዲሁ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በዓመት ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በአየር መበከል ምክንያት ለህልፈተ ህይወት ሲዳረግ 2.4 ሚሊዮን የሚሆኑትም ደግሞ የዓየር ንብረት መበከልን ተከትሎ በሚመጣ የልብ ህመም ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡
የICT ኤክስፖ ላይ በመገኘት ይጎብኙን
ኢኖቬት ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲከናወን የቆየው 3ኛው ዓለም አቀፍ የICT ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡ በዚህ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ አስመጪዎች፣ አገልግሎት ሰጪ አካላት እና ሌሎች ሐገራዊ እንዲሁም ግዙፍ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
ታድያ በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩትም እንደ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱ ይዘን ከቀረብናቸው ስራዎቻችን መካከል የዲጂታል ቤተ-መፅሐፍት (ከአጠቃቀም ገለፃ ጋር)፣ በወረቀት ላይ የሰፈሩ ፅሁፎችን ወደ ኮምፒውተራችን ገልብጠን ማስተካከል የሚያስችለንን ቴክኖሎጂ እነዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎቻችንን እናስዳስስዎታለን፡፡ በተጨማሪም ተቋማችን በየሶስት ወሩ የሚያሳትመውን የቴክ-ሳይንስ መፅሐፍት እና የሐገራችንን ጠሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽ ሁናቴ የሚቃኙ የዳሰሳ ጥናቶችን በነፃ ያገኛሉ፡፡
ይፍጠኑ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ በማምራት ይጎብኙን!!!
9ኛው ሐገር አቀፍ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሽልማት ተከናውኗል፡፡ በክብር እንግድነት ተገኝተው ሽልማቶችን ያበረከቱት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዓብይ አህመድ ተሸላሚዎቹ ስራዎቻቸው የረጅም ጉዞዋቸው ጅማሬ እንደሆኑና በሐገራችን ያለው የሐብትና ግብዓት እጥረት ሳይገታቸው ወደፊትም ለተሸለ ፈጠራ እንዲተጉ በማሳሰብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሐገራችን ፈጣሪ አዕምሮ ያላቸው ዜጎች እጥረት እንዳለባት ያመላከቱት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም እነዚህን ባለ ብሩክ ተስፋዎች ከመሸለም ባለፈ ከኢንዱስትሪዎች የማስተሳሰር ስራን ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሐገር ዓቀፉ የፈጠራ ሳምንት መዝጊያ ጭምር በነበረው በዚህ በስነ ስርዓት ላይ 177 ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪና መምህራን ብሎም በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ተሸላሚ እንደሆኑበት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ሚኒስትትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም ቴክኖሎጂን ያላማከሉ ማህበራዊም ሆነ ምጣኔ-ሐብታዊ እንቅስቃሴዎች ከስኬት ስለማይደርሱ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙትን ህፃናት ከቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የነገዎቹን ታላላቅ የፈጠራ ባለሙያዎች መፍጠር እንዳለብን አብራርተዋል፡፡
ከ2002 ዓ.ም አንስቶ ሲከናወን በቆየው በዚህ ሽልማት ከ1800 በላይ የፈጠራ ባለሙያዎች ተሸላሚ ሆነውበታል፡፡
የመጀመሪያው የክህሎት ውድድር ተጀመረ
************************************
የመጀመሪያው ሐገር ዓቀፍ የቴክኖሎጂ ክህሎት እና ተግባራዊ ምርምር ውድድር በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ታጅቦ ትናንት ተጀምሯል፡፡ በፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲና በፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስትቲውት በጋራ የሚዘጋጀው ይህ ውድድር “በክህሎትና ስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለሰላምና ልማታችን ዋስትና ናቸው” በሚል መሪ ቃል እስከ ሰኔ 11 የሚዘልቅ ይሆናል፡፡ በተሳታፊነትም የተለያዩ የቴክኒክ እና ሙያ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዝ ኦፕሬተሮች ተካፋይ ያደርጋል፡፡
የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሺዴ መንግስት ትምህርት እና ስልጠና ለሐገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት መሰረታዊ መሆኑን ተረድቶ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት መንቀሳቀሱን ገልፀዋል፡፡ ክቡር ሚንስትሩ “ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ዜጎችንም ያፈራል” ባሉት ቴክኒክ እና ሙያ ተቋም ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመለካከት ለማሻሻል የአተያይና የግንዛቤ ስራዎች መስራት እንደሚገባ አስቀምጠዋል፡፡ በመጨረሻም ዘርፉን ለማጎልበት እና የህብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ስራዎችን በጥናትና ምርምር መደገፍ እንደሚገባ በማሳሰብ በውድድሩ ለተሳተፉ ሰልጣኝ፣ አሰልጣኞች እና እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዝግጅቱ የእንኳን ደህና መጣችው ንግግሩን ያቀረቡት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታው ዶክተር አብዲዋሳ አብዱላሂ ትምህርት ለአንድን ሐገር የልማት መሳሪያና የእድገት ፍትሐዊነት ማረጋገጫ እንደሆነ ሲገልፁ፤ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናም የሰው ልጆችን ድህነትና ስራ አጥትን ለማስወገድ እንዲሁም ሰላምን ለማረገገጥ የቁልፎች ሁሉ ቁልፍ ነው ብለዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና አንዱ ተልዕኮ የቴክሎጂ አቅምን በመገንባት ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪ ማድረግ ቢሆንም ባለው የቅንጅት አሰራር፣ የማበረታቻ ስርዓት፣ የእይታ መድረኮች እና ኢንዱስትሪዎች ላይ መተግበሪያ መንገዶች አለመኖር ሳቢያ ይህ ሚናቸውን በብቃት መወጣት እንዳልቻሉ የተናገሩት ዶክተር አብዲዋሳ እነዚህን ተግዳሮቶች በመፍታት እና መሰል የቴክኖሎጂ ክህሎት እና ተግባራዊ ምርምር ውድድሮችን ከታች ከወረዳ አንስቶ እስከ ሐገር ዓቀፍ ድረስ ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
ውድድሩ የተወዳዳሪዎቹን ስራዎች በዓውደ ርዕይ መልክ በማሳየት እና የዘርፉን አቋም የሚገመግሙ የፓናል ውይይቶች በማካሄድ የሚቀጥል ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ላሳዩ 11 ተወዳዳሪዎችም የሚበረከትላቸው ይሆናል፡፡
“ሐገር የምትገነባው ከታች ጀምሮ ነው !” ክብርት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
************************************
የኢፌድሪ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመጀመሪያው ሐገራዊ የክህሎት ውድድር መቋጫ ላይ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ስኬቶችን ቢመዘገቡም ዘርፉ ላይ የሚታየውን ሰፊ ክፍተት ለመድፈን የሁሉም አካላት ተሳትፎን እንደሚሻ ተናግረዋል፡፡ ሐገር የምትገነባው ከታች ጀምሮ ነው ያሉት ክብርት ፕሬዘዳንቷ ህብረተሰቡ በቴክኒክ እና ሙያ ላይ ያለውን አመለካከት የሚለውጡ የተግባርና ግንዛቤ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
Technology Installation እና Database Administration ጨምሮ በአስራ አንድ ምድቦች ተከፍለው ከተወዳደሩት የቴክኒክ እና ሙያ ሰልጣኝ፣ አሰልጣን እና ኢንተርፕራይዞች መካከል በየምድባቸው ከአንድ እስከ ሶስተኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች እንደየ ደረጃቸው የሜዳሊያ፣ ገንዘብ እና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዕለቱ ክብርት ፕሬዘዳንቷን ጨምሮ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ሚኒስትር ደኤታዎቹ ዶክተር ሂሩት እና ዶክተር አብዲዋሳ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሲገኙ የተሳታፊዎቹን ስራንም ለመጎብኘት ችለዋል፡፡