የኪሎግራም ልኬት ተለወጠ
===============
ለ130 ዓመታት ገደማ የኪሎግራምን ክብደት ይወስን የነበረው ልኬት (Standard) ከትናንትናው ዕለት አንስቶ ተቀይሯል፡፡ በፓሪስ አቅራቢያ በሚገኘ ስፍራ የተቀመጠውና እስከትናንትናው ዕለት ድረስ የኪሎግራም ልኬት ሆኖ ያገለገለው የብረት ሲሊንደር ከስራው በጡረታ ሊሰናበት ግድ ሆኗል፡፡ በምትኩም ፕላንክ ኮንስታንት በመባል በሚታወቀው የኳንተም ብዛት ተተክቷል፡፡
ይህ ልኬት ታድያ በህዋም ሆነ በጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ አይለወጤ ልኬት እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ ለንፅፅ ትንሽ ጭረት እንኳን ቢያጋጥመው የመጠን ለውጥ በማምጣት ልኬቶችን ሊያዛባ ከሚችለው የብረት ሲሊንደር አኳያ ይህ መለኪያ በላቀ አስተማማኝ ነው፡፡ ይህን የልኬት ለውጥ ባፀደቀው 26ኛው የክብደትና ልኬቶች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተጨማሪነት የሙቀት፣ ኤሌክሪክ ከረንትና የቁሶችን መጠን መለኪያ የሆኑት ኬልቪን፣ አምፒር እና ሞል ድግም ልኬታቸው ተወስኗል፡፡
ሳይንቲስቶቹ በቀጣይነት አይናቸውን የጊዜ መለኪያ ወደሆነነው ሴኮንድ አማትረዋል፡፡ በምንገለገልበት ልኬት መሰረት ሴኮንድ ከሲዚየም አተሞች በተሰሩት አቶሚክ ሰዓቶች ዓማካኝነት ይለካል፡፡ እነዚህ አተሞች የብርሃን ፍሪክዌንሲን የሚመጡ ሲሆኑ የብርሃኖቹ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ዌቮች የጎንዮሽ ደርሶ መልስ እንቅስቃሴ ልክ በቀድሞዎቹ የግድግዳ ሰዓቶች ላይ እንደሚገኘው ባለ ክብ አናት ብረት በመሆን ጊዜን ያስቆጥራሉ፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ሴኮንድ 9,192,631,770 የብርሃን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጡት የአዲሱ ትውልድ አቶሚክ ሰዓቶች ከሲዚየሞቹ አንፃር አንድ መቶ እጥፍ በተሸለ ጊዜን የመለካት ብቃት አላቸው፡፡ ይህ የልኬት ቅያሬ በ2020ዎቹ መባቻ እውን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ሆኖም ይህ ማለት ቀኑ ያጥራል ወይም ክብደት ይጨምረል ማለት አይደለም፡፡ በክብደትም ሆነ ጊዜ ላይ የሚደረጉት የልኬት ለውጦች ከተለመደው የኪሎግራም አሊያም ሴኮንድ መጠን ልዩነት እንዳያመጡ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚከውኑ ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ Science News

አንድ ቢሊዮን ዓመታትን ያስቆጠረ ቅሪተ-አካል ተገኘ
======================
ትናንት ኔቸር ጆርናል ላይ በወጣ ጥናት ከአንድ ቢሊዮን አመታት በፊት ይኖር እንደነበረ የተነገረለትን ፈንገስ ማግኘታቸውን ሳይንቲስቶች ይፋ አድርገዋል፡፡ ጥናቱ የህይወትን ዝግመተ ለውጥ እንመለከትበት የመነበረውን እይታ ሊለውጥ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡
ለብዙ አስርት ዓመታት በሰው ልጅ ዘንድ ቀደምት ተብለው ይታወቁ የነበሩት የመሽሩም፣ መኦልድ እና ዪስት ፈንገሶች ግማሽ ቢሊዮን ዓመታትን በምድር እንደኖሩ ጥናቶች ይነግሩናል፡፡ ሆኖም ይህ በካናዳ የተገኘው የፈንገስ ዝርያ በዘመን አፈራሽ የዕድሜ መመርመሪያ መሳሪያ ተመርምሮ በተረጋገጠው መሰረት ፈንገሶች በምድር ላይ ኖረዋል ተብሎ ይታመንበት የነበረውን ዕድሜ በእጥፍ ወደኋላ ገፍቶታል፡፡
በቤልጂየሙ ሊጅ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪው ኮረንቲን ሎሮን የቅሪቶቹን ኬሚካላዊ ቅንብር የሚለይ ምርመራ ያካሄዱ ሲሆን በውጤቱም የፈንገስን ህዋስ ግድግዳ የሚገነባውን ቺቲን የተሰኘ ፋይበር ነክ አካል በውስጡ ማግኘት ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ቅሪቶቹ የተገኙበትን አለት ውስጥ የራዲዮአክቲቭ ግብዓቶች የያዙትን ድርሻ በመለካት መርምረዋል፡፡ በመጨረሻ ውጤቱም ቅሪቱ ከ900 ሚሊዮን እስከ አንድ ቢሊዮን ዓመታት ያስቆጠረ እንደሆነ ደምድመዋል፡፡ እንደ ኮረንቲን ከሆነ ከቢሊዮን ዓመታት በፊት ፈንገሶች ይኖሩ ከነበረ ፈንገሶች ከእንስሳትና እፅዋት ጋራ ኢዩካሪዮትስ የተባለ የስነ-ህይወት ምድብን ስለሚጋሩ እንስሳትም በምድር ላይ ተመሳሳይ ጊዜን አስቆጥረዋል ማለት ነው፡፡ ይህም የሩቅ ዘመን ናቸው ብለን የደመደምናቸው ፍጥረታት በአንፃሩ ካሰብነው በላይ የቅርብ እንደሚያደርጋቸው ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡
ፈንገሶች በፕላኔታችን ላይ በበስፋት የሚገኙ ፍጥረታት ሲሆኑ ከእፅዋት እና ባክቴሪያዎች በመቀጠልም ሶስተኛ ደረጃን ይዘው የሚገኙ የምድራችን ባዮማስ ባለድርሻዎች ናቸው፡፡ አንድ ላይ ብንመዝናቸው እንኳን መላው የሰው ልጅ እና እንስሳት ተዳምረው ካላቸው ክብደት ስድስት እጥፍ የላቀ ነው፡፡
ምንጭ፡ phys.org

የረመዳን ወርን በእኛው ቤት
**********************
ቅዱሱን የረመዳን ወር በማስመልከት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ ልዩ የበዓል ዝግጅት አዘጋጀ፡፡ በዚህ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በቀረቡበት ዝግጅት ላይ የኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞችን ጨምሮ ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶችም ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ የዝግጅቱን መክፈቻ ንግግር ያደረት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የተቀረው የፆሙም ወቅት መልካም ይሆን ዘንድ ምኞታቸውን አጋርተዋል፡፡
በተጋባዥ እንግድነት ተካፋይ የነበሩት የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ታደለም የበጎ አድራጎት ማህበሩ እያከናወናቸው ስላሉት ተግባራት ለታዳሚያኑ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ ጨምረውም ኢኒስቲትዩቱ እና የበጎ አድራጎት ማህበሩ በጋራ ስላከናወኗቸው ስራዎች ተናግረዋል፡፡
ዝግጅቱን ያዘጋጀው የላምባዲና ሶሻል ኮሜቴ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራተኞችን እርስ በእርስ መስተጋብር ይበልጥ ለማሳደግ ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ መሰል አሳታፊ ሁነቶችን ከማዘጋጀት ባለፈም በልዩ ልዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ሰራተኞችን የሚያሳትፍ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ የአንድ ልጅን ወጪ በመሸፈን ማሳደግ ይገኝበታል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይም ሰራተኞቹ ወጪ በመሸፈን የሚያሳድጉትን ህፃናት ቁጥር ወደ ሁለት ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡

በሳይንሳዊ የሐብት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተጀመረ
ሐገራዊ የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ሊሰሩ የሚገባቸውን መዋቅራዊ ተግባራት እንዲሁም እንዲጎሉ የሚጠበቁ ጥንካሬዎች ለማመላከት ያለመ ወርክሾፕ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ፡፡ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዓለም አዕምሮ ንብረት ድርጅት (WIPO) ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ወርክሾፕ ላይ ኢኒስቲትዩቱን ጨምሮ ከሶስት ተቋማት ተውጣጡ ተሳታፊዎች ሲታደሙበት እስከ ግንቦት 21 ድረስም የሚቀጥል ነው፡፡
በዛሬው ውይይት ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እና ስልጠና ተካሂዶባቸው አልፈዋል፡፡ ከነዚህም ቀዳሚው በሐገራችን ያለው የጥናት እና ምርምር ተቋማት እጥረት እንዲሁም የሣይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን በመጠቀም ረገድ ያለው ክፍተት ነው፡፡ በውይይቱም ይህን ክፍተት መድፈን ይቻል ዘንድ ሁሉን አቀፍ የሆነና በዋናነትም አመራሩን ያሳተፈ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባና በዋናነት የትምህርት ስርዓቱን በማሻሻል ላይ ያተኮሩ ተግባራት እንዲከወኑ ምክረ ሀሳብ ቀርቦባቸዋል፡፡
ሌላው በመድረኩ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረው በሐገራችን ያለው የተፈጥሮ ሐብት አጠቃቀም ነው፡፡ በሐገራችን ያለው የተፈጥሮ ሐብት በቀላሉ ሊታይ የማይገባ ቢሆንም ዋና ትኩረቱ ግን ወደ ሰው ሐብት ልማት እና እነዚህን የተፈጥሮ ሐብቶች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ወደመጠቀም ሊዞር እንደሚገባ ተነስቶበታል፡፡ በዚህ ረገድ እንደ ቡናና ሽፈራው ያሉ የሐገራችን ሐብቶች ላይ አብይ ትኩረት እነዲሰጥና በእነርሱም ዙሪያ ሰፊ የምርምር እና ስርፀት ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሳህለማርያም ጋራ በነበረን ቆይታ መሰል ሳይንሳዊ የሐብት አጠቃቀምን እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ ዝግጅቶች በቀጣይነት እንደሚዘጋጁ ለማወቅ ችለናል፡፡

ሳይንስን በስልካችን
በእጆቻችን ላይ የሚገኙ ስማርት ስልኮቻችን ብዙ ነገሮችን እንድንከውን በሚያስችሉን ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ ታድያ ስልካችንን ለፎቶ መነሳት እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ፍጆታ ከማዋል ባለፈ ተከታዮቹን መተግበሪያዎች ተጠቅመን ሳይንስን በተለየ መነፅር መመልከት እንችላለን፡፡
1. eBird
በስነ-አዕዋፍ (Ornithology) ጥናት ላይ በተሰማራ ቤተ-ሙከራ የሚተዳደረው ይህ መተግበሪያ የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንድናውቅና እንድንመረምር ከማስቻል ባለፈ ከዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር ጭምር መረጃውን እንድንለዋወጥ ያደርገናል፡፡ በመተግበሪያው አድራሻችንን በማስገባት በዙሪያችን ያሉ ዝርያዎችን ማየት ስንችል የወፍ መገኛ ስፍራዎች ላይ በአጋጣሚ ከተገኘንም ያሳውቀናል፡፡ ታድያ ከበይነ መረብ ውጪም ስለሚሰራ ገጠራማ ቦታዎች ላይ አንቸገርም፡፡
2. Star Walk
Star Walk በአመሻሹ ሰማይ ካሜራችንን ወደ ከዋክብት እንድናማትር በማድረግ ብቻ በእይታችን ስለገቡትን ከዋክብት እና ፕላኔቶች ገለፃ ያደርግልናል፡፡ ከማርስ የፀሐይ መውጫና መጥለቂያ ሰዓት አንስቶ እጅግ የበዙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ያቀብለናል፡፡
3. NASA Globe Observer
ይህ መተግበሪያ ከቀድሞዎቹ በተለየ ወደ ረጂነት ይለውጠናል፡፡ በዳመና ሽፋን፣ መሬት ሽፋን እና ወባ ትንኝ ዙሪያ መረጃን የሚሰበስብ ሲሆን እኛም ቢሆን የምንመለከተውን ዳመና ፎቶ በማንሳት ለናሳ እንድናደርስና የአየር ፀባይን በመረዳት ረገድ ሚና እንድንጫወት ያደርገናል፡፡
4. MyShake
ለምርምር ታስቦ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰራ ሲሆን በዙሪያችን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴዎችን ያሳውቀናል፤ እኛ ላይ ቢከሰቱ ምን ማድረግ እንዳለብንም ይነግረናል፡፡ ሌላኛው የዚህ መተግበሪያ ስራ ስልካችን ላይ ተፅዕንዖ ሳያደርስ ያለንበትን ስፍራ የመሬት መንቀጥቀጥ ሁናቴ በመገምገም ምሁራኑ ግምቶችን እንዲያስተካክሉና ህይወትን እነዲያድኑ መረጃ ያቀብላል፡፡
5. The Elements (በክፍያ)
iOS በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን Periodic Table ላይ የሚገኙትን ንጥረ-ነገሮች አካላዊ ቅርፅ ከመረጃ ደብሎ ያደርሰናል፡፡ ለምሳሌ እያንዳንዱን ንጥረ-ነገር ዙሪያውን ባሻን አቅጣጫ እንድንቃኝና ብሎም ስለ ይዘቱ፣ የግኝት ታሪኩ፣ ጥቅሙ፣ የገበያ ዋጋው ወዘተ… ጥልቅ ትንታኔ ይሰጠናል፡፡
6. Wolfram Alpha (በክፍያ)
በድረ-ገፁ አማካኝነት የምናገኘው ይህ መተግበሪያ የፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ቀመሮችን፣ የቁሶችን ይዘት፣ የምድራችን ንብርብሮችን መረጃ፣ የከዋክብት ካርታን እና ሌሎች መረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ የሂሳብ ኢኩዌዥኖችን የማስላትና የአየር ሁኔታንም የማሳወቅ ስራ ይሰራል፡፡
7. Science Journal
ይህ የጎግል ምርት በዙሪያችን ያሉ ሁቴዎችን እንድንመዘግብ ያደርገናል፡፡ ለምሳሌ፡- የስልካችንን ሴንሰሮች በመጠቀም ብርሃን፣ ድምፅ፣ ግፊት፣ እንቅስቃሴን ያነባል፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት ከሌሎች ማሳሪያዎች ጋር በመቀናጀትም ይሰራል፡፡ ውጤቶችን በፎቶና ፅሁፍ ሲያስቀርልን እነዚህን መረጃዎች ወደ ሌሎች መሳሪያዎች በማስተላለፍ መጠቀም እንድንችልም ያደርገናል፡፡
ምንጭ፡- popular science

ሜዲካል ቱሪዝም
***************
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከሐገራቸው በመውጣት የሕክምና አገልግሎትን እንዲገኙ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ሜዲካል ቱሪዝም በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ኢንዱስትሪ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየገዘፈና በጤናው ዘርፍ የተሸለ ደረጃ ላይ የደረሱት ሐገራትንም ከቀን ወደቀን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ቁጥራቸው የበዛ ሐገራት እና ፖሊሲ አውጪዎቻቸውም በዘርፉ ላይ አይናቸውን ከጣሉ ሰነባብተዋል፡፡
ሜዲካል ቱሪዝም ከረጅም ጊዜያት አንስቶ ሲተገበር የቆየ የህክምናው ኢንዱስትሪ አካል ነው፡፡ በተወሰኑ ሐገራት ያሉት ፈዋሽ ፍል ውሃዎች ቀዳሚዎቹ የሜዲካል ቱሪዝም አስጀማሪዎች ነበሩ፡፡ ታድያ ከጥቂት አስርት ዓመታት ወዲህ በተወሰኑ የህክምና አገልግሎቶች ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ የዘርፍ ዕድገትን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ለዚህ የቁጥጥር ስርዓቶች፣ የቴክኖሎጂ ዕድገት፣ የባለ ዝቅተኛ ታሪፍ አየር መንገዶች መስፋፋት፣ በባህል ዙሪያ እየተቀየረ ያለው አመለካከት እና ሌሎችም በገፊ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የደቡብ ምስርቅ እሲያ፣ አውሮፓ እና ላቲን አሜሪካ ሐገራት ቀዳሚዎቹ የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ በመሆን ገበያውን ይመራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ እንደ ህንድ፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ብራዚል፣ ኩባ፣ ሜክሲኮ እና ኮስታ ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ ክልሎች ወጣ ብለው በተቀመጡት ደቡብ አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶችም የሜዲካል ቱሪዝም እንቅስቃሴ ጎልቶ በመታየት ላይ ነው፡፡ ለነዚህ ሐገራት ጎልቶ መውጣት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አንፃራዊ የዋጋ ልዩነት፣ የሐገራቱ ትስስር፣ የህክምናው ዓይነት፣ መልከዓ ምድራዊ ቅርበት እንዲሁም የጤና መሰረተ ልማት፡፡ ከነዚህ መካከል በህክምው ዓይነት ላይ የተመሰረቱትን ያየን እንደሆን በላቲን አሜሪካን ያሉ ሐገራት በጥርስ፣ ውፍረት ቅነሳ፣ ውበት እና ፕላስቲክ ቀዶ ህክምናዎች የጠነከረ ስምን ለመገንባት ችለዋል፡፡ ህንድን ጨምሮ እነደ ማሌዢያ፣ ሲንጋፖር እና ታይላንድ ያሉ የደቡብ ምስራቅ እሲያ ሐገራት ደግሞ በልብ እንዲሁም አጥንትና ጡንቻ ህክምናዎች ዝናን አግኝተዋል፡፡ ሌላው በዋጋ ረገድ ሐገራት ያላቸው ተመራጭነት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የደቡብ ምስራቅ እሲያ ሐገራት ባላቸው አንፃራዊ የዋጋ ቅናሽ ከበለፀጉት ሐገራት ጭምር ታካሚዎችን ለመሳብ ችለዋል፡፡
ሆኖም እንደሌሎቹ ዘርፎች ሁሉ የሜዲካል ቱሪዝምም ከተግዳሮቶች አላመለጠም፡፡ በተለይ በህክምና እንዲሁም ስነ-ምግባር እና ሕግ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያሉ ስጋቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ ለዚህ ሐገራት ያላቸው የተለያየ የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ፣ አሰራር እና ሕግጋት እንዲሁም እነዚህን ተከትሎ የሚመጣው የህምና ተቋማት እና ባለሙያዎች ደረጃ መለያየት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡
ወደ ሐገራችን ስንመጣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎችን ወደ ውጪ ሐገራት በመስደድ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህም ለሐገራችን ሌላ ምጣኔ-ሐብታዊና ማሕበራዊ ጫና ይዞልን መጥቷል፡፡ ይህን ሁናቴ የሚለውጡና ሐገራችንን ወደ ሌላ የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻነት ከፍ የሚያደርጉ እርምጃዎችን መውሰድ ከመንግስትም ሆነ የግል ባለሐብቶች ይጠበቃል፡፡ ታድያ ምንም እንኳን በዘርፉ መሪ ወደሆኑት ሀገራት ለመጠጋት ረጅም ጊዜን የሚፈጅ ቢሆንም ባለንበት አካባቢ እንኳን የስበት ማዕከል የሚያደርጉንን ስራዎች መስራት ይገባናል፡፡
ምንጭ፡- News Medical

3ኛው ዓለም ዓቀፍ የICT ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ
*************
ኢኖቬት ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት የሚከናወነው 3ኛው ዓለም አቀፍ የICT ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል፡፡
የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሐገራችን ለገባችበት የለውጥ ምህዋር ስኬት ሳይንስና ኢኖቬሽን ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም የተለያዩ ዘርፎቻችን በቴክኖሎጂ በማገዝ ማበልፀግና ሐገራችንንም አሁን ካለችበት የቴክኖሎጂ ኋላ ቀርናት ማላቀቅ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው ዘርፉ ላይ በሚሰሩት ሐገሀራዊ እንዲሁም ተቋማዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያተኮረ ንግር ለታዳሚያኑ አድርገዋል፡፡ በሐገራችን የ25 ሺህ ኪ.ሜ ፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ መሆኑንና ከወረዳ አንስቶ ባሉት ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሴኮንድ እስከ 1 ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው የፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎትም ዝርጋታ በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡
በኤክስፖው ላይ በሐገር ውስጥ እና ዊጪ ሐገራት መሰረታቸውን ያደረጉ በርካታ የግል እንዲሁም የመንግስት ተቋማት ተሳታፊ የሚሆኑበት ሲሆን ቁጥሩ ከፍ ያለ ህብረተሰብም እንደሚጎበኘው ይጠበቃል፡፡

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የዕፅዋት ተከላን አከናወኑ
******************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስትቲውት ሰተራተኞች በዛሬው እለት የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ በመገኘት ዕፅዋትን ተክለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የክፍያ መንዶች ኢንተርፕራይዝ ጋራ በጋራ የተከወነው ይህ የዕፅዋት ተከላ በዓመቱ አራት ቢሊዮን ዕፅዋትን ለመትከል የተያዘው ሐገራዊ ዕቅድ አካል ነው፡፡
ይህን ተግባር በማስመልከት ቃለ መጠይቅ ያደረግንላቸው የኢንስትቲውታችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ መሰል ክንውኖች ለተቋሙ አዲስ ሁነት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም በተያዩ ጊዜያት ዕፅዋትን የመትከል ስነ ስራ እንደተሰራ ገልፀውልናል፡፡ አያይዘውም የተጀመረውን ሐገር ዓቀፍ እንቅስቃሴ በበጎ በመመልከት ሌሎች አካላትም እንዲሁ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በዓመት ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በአየር መበከል ምክንያት ለህልፈተ ህይወት ሲዳረግ 2.4 ሚሊዮን የሚሆኑትም ደግሞ የዓየር ንብረት መበከልን ተከትሎ በሚመጣ የልብ ህመም ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡