ቴሌሜዲስን! የመጪው ጊዜ የአፍሪካ የጤና ተስፋ
**********************
በአነስተኛ ዋጋ ለሁሉም ተደራሽ የሆነና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት መገንባት የታዳጊ ሀገራት ትልቅ ፈተና ሆኖ ቆይቷል፡፡ በበርካታ የማህበራዊና ኢኮኖሚ መስኮች ግልጋሎት ላይ ውሎ አመርቂ ውጤት ያመጣው የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ደግሞ ለጤናው ዘርፍም ትልቅ መፍትሄ ማምጣት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ የኮምፒውተሮች፣ ሞባይል ስልክ፣ ኢንተርኔት እና መሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች በበርካታ የአፍሪካ እና የደቡብ አሜሪካ ገጠር አካባቢዎች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ጥቅም ላይ ሲውሉ ማየትም ብርቅ አይደለም፡፡ ከኡጋንዳ እስከ ሴኔጋል፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ሞሮኮ በርካታ ሙከራዎች እየተደረጉ ሲሆን የእናቶችን ጤና ለማሻሻል እና የምዕተ ዓመቱን የጤናውን ዘርፍ የልማት ግቦች ለማሳካት እንደ ኡጋንዳ ባሉ አገራት በሞባይል ስልክ አማካኝነት የሚተላለፉ መልዕክቶች ያመጡትን ከፍተኛ ለውጥ ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡
ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ዕድገት፣ አነስተኛ የጤና ባለሞያዎች ቁጥር፣ ወባ፣ የቲቢ በሽታ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ችግር በሆኑባት አፍሪካ አማራጭ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መልኮችን ማፈላለግ ለተደራረቡት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ጥሩ ማቅለያ ሊሆን ይችላል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሁጉራችን አፍሪካ ለመቶ ሺህ ሰዎች የሚቀርቡት ሃኪሞች ከአስር ያነሱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ስፔሻሊስት የሚባሉት ሃኪሞች በአብዛኛው ተጠራቅመው የሚገኙት በከተሞች አካባቢ ነው፡፡ 24 በመቶው የአለማችን የበሽታዎች ጫና ያለባት አፍሪካ በጤና ላይ ከሚወጣው የገንዘብ ወጪ 1 በመቶ ብቻ የሚወጣባት እና 3 ከመቶ የጤና ባለሞያዎች ያሉባት አህጉር ናት፡፡ ከእነዚህ ባለሞያዎችም መካከል በገጠር አገልግሎት የሚሰጡት የጤና ባለሞያዎችም የስፔሻሊስቶችን እገዛ ከሚያገኙበት አማራጭ በብዙ ርቀው ስለሚገኙ ውጤታማ የሆነ የበሽታ መከላከልና ማዳን አገልግሎትን ለመስጠት ይቸገራሉ፡፡
ታዲያ እነዚህን ተደራራቢ ችግሮች በሂደት ለመፍታት የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂን መሰረት አድርገው ከሚሰሩ የተለያዩ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቶች ወስጥ የሚመደበው ቴሌሜዲስን አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ቴሌሜዲስንን በአጭሩ ለመግለፅ ቢሞከር በርቀት ሆነው የህክምና አገልግሎትን ማግኘት ሊባል ይችላል፡፡ ለከፍተኛ የባለሞያ ምክር እና ህክምና አቅርቦት እጅጉን ሩቅ ለሆኑ በገጠር አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ባሉበት ሆነው የምርመራ እና የህከምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ አገልግሎት በተለይ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ ዝቅተኛ በሆነባቸው የሰሃራ በታች የአፍሪካ አገራት አዋጭ መፍትሄ እንደሚሆን በማመን በርካታ አገራት ፍላጎታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከ1970ዎቹ እና 80ዎቹ ጀምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉበት የቆየው ቴሌሜዲስን አሁን ላይ ደግሞ በአሁጉራችን አፍሪካ የሚታዩትን የጤና ችግሮች እስከወዲያኘው ለመፍታት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት እየተከናወነ ያለ አዲስ ዘርፍ ነው፡፡
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ እና bigthink.com

ከ45 ኪ.ሜ ርቀት ምስሎችን ማንሳት የሚችለው ካሜራ
***********************************************
በረዥም ርቀት ውስጥ ፎቶግራፎችን ማንሳት እጅግ ከባድ ስራ ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ የከባቢ አየር ብክለት ሲጨመር ሁኔታውን ይበልጥ ከባድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ በተለይም በከተሞች ከፍተኛ የአየር ብክለት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ በቅርብ ርቀት ነው እንጂ እንዲ ባለ ሰፊ ርቀት ምስሎችን መቅረፅ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ይሁንና ብዙ የማይቻሉ ነገሮች በጊዜ ሂደት እየተፈቱ በሉበት በአሁን ወቅት፤ ይህም ጉዳይ ጊዜው ደርሶ ብዞዎችን ሊያስገርም እና ሊጠቅም በመንገድ ላይ ይገኛል፡፡
ቻይና ከሚገኘው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የወጣው ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ዜንግ ፒንግ ሊ በተባለ ተመራማሪ እና ሌሎች ጓደኞቹ የተሰራ ሲሆን ለየት ያለ ቴክኒክ ስለመጠቀሙም ተነግሯል፡፡ ይህ ቴክኒክ light ranging and detection ወይም በአጭሩ Lidar ተብሎ የሚጠራ ቴክኒክ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ እንደ ጂዮሎጂ እና አርኬዎሎጂ ባሉ የትምህርት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸውን ካርታዎች ለማንሳት የሚውል ነው፡፡
ዜንግ ፒንግ ሊ እና ተባባሪዎቹ ይህን ሲስተም ሲጠቀሙ በዋናነት ያተኮሩት ምስሉ በሚወሰድበት አካል (subject) ላይ በlaser light አማካኝነት ብርሃን እንዲፈጠርና ከዚያም በተገኘው የብርሃን ነፀብራቅ አማካኝነት ምስል ለመፍጠር ነበር፡፡ በዚህም ሂደት እያንዳንዱን ፎቶን (photon) በቀላሉ ለመለየት ብዛት ያላቸውን ሴንሰሮች፤ (የተዘረዘሩ እይታዎችን እና መረጃዎችን በመቀመር ከሚያደርስ) algorithm ጋር በማጣመር ከፍተኛ የምስል ጥራት ያለውን ካሜራ ለመስራት ችለዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ካሜራው በከተሞች ላይ ይበልጥ እንዲሰራ በማሰብ የሞገድ ርዝመቱ 1550 ናኖ ሜትር የሆነ infrared laser የተጠቀሙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የድግግሞሽ መጠኑ 100 ኪሎ ኸርትዝ እንዲሆንና የሃይል መጠኑም 120 ሚሊ ዋት የሚደርስ laser እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ይህም የሚጣሩትን ሶላር ፎቶኖች (solar photons) በቀላሉ በማጣራት የአይን ደህንነትን የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ተማራማሪዎቹ ሲስተሙን ከካሜራው ጋር በማጣመር ሻንጋይ ውስጥ በሚገኝ የቾሚንግ ደሴት እና 45 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው የፑዶንግ ሲቪል አቪዬሽን ህንፃ ጋር በመሆን የምስል ማንሳት ሙከራውን ያደረጉ ሲሆን ውጤቱም እጅግ አስደናቂ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ይህ አዲስ የካሜራ ሲስተም በትግበራ ሂደቱ እጅግ በተወሳሰበ የፊዚክስ ቀመር የተገለፀ ቢሆንም በቅርብ አመታት ውስጥ እንደማንኛውም የካሜራ አይነት ወደ ብዙዎች እጅ ለመድረስ የሚያስችለውን አስገራሚ ውጤት ማግኘታቸውን የሚናገሩት ተመራማሪዎች ለጊዜው ግን ያለአሽከርካሪ የሚሄዱ መኪኖች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚውል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ Technology review

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽንን ደረጃ አመላካች የሆኑ ጥናቶቹን በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቅጥር ውስጥ በተካሄደው በዚህ ስነ-ስርዓት የተቋሙ አመራሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ሚኒስትር እና ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተውበታል፡፡ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሩን ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ላይ ሰፊ ስራን ያከናወኑ ሐገራት በዓለም ገበያ ላይ ቀዳሚዎቹ ተጠቃሚ እና ተፅዕንዖ ፈጣሪ ለመሆን ሲችሉ በአንፃሩ ይህን ያላከናወኑት ታዳጊ ሐገራት የተፈጥሮ ሐብታቸውን እንኳን በአግባቡ ተጠቅመው ተወዳዳሪ ለመሆን መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ጥናቶችም በኢትዮጵያ የሚታየውን ፖሊሲዎችን ከጥናት ይልቅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሚደረጉ ምክክሮች ብቻ የመቅረፅ ልማድን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተቀምጧል፡፡
ዛሬ የተመረቁት ሶስት የዳሰሳ ጥናቶች ኢትዮጵያ ያለችበትን የምርምር እና ስርጸት፣ የቴክኖሎጂ ባላንስ ኦፍ ፔይመንት እና የፌደራል መንግስት ተቋማት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ወጪ ደረጃን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የቴክኖሎጂ ባላንስ ኦፍ ፔይመንትን የሚያሳየው በአፍሪካ በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ በጥናቶቹ ዙሪያ በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች አማካኝነት ለታዳሚያኑ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ በተደረገው ውይይትም ጥናቶቹ በተሳታፊዮቹ ዘንድ አድናቆትን አግኝተዋል፡፡ በመቀጠልም በጥናቶቹ ላይ የቀረቡት አመላካች ክፍተቶች በሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነት ሊሞሉ እንደሚገባጊዜያቸውን ሲሆን መሰል ጥናቶችም ጊዜያቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ምክረ ሐሳብ ተለግሷል፡፡

ሌኔቮ የመጀመሪያውን ታጣፊ ላፕቶፕ ይፋ አደረገ
********************************
የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሌኔቮ የመጀመሪያ የተባለውን ታጣፊ ላፕቶፕ በፍሎሪዳ በተደረገ የቴክኖሎጂ ጉባዬ ላይ አስተዋውቋል፡፡ ኩባንያው ይፋ ያደረገው ይህ ላፕቶፕ ThinkPad X1 በተሰኘው የላፕቶፕ አይነት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን 13.3 ኢንች ስፋት እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡
የኩባንያው ባለቤቶች በጉባዬው ላይ ለነበሩ ጋዜጠኞች እንደተናገሩት ይህ ላፕቶፐ ቀደም ብለው ይፋ ከተደረጉት ታብሌቶች እና ስልኮች ውስጥ የሚመደብ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ የላፕቶፕ ይዘት ኖሮት ለመተጣጠፍ እንዲችል በልዩ ገፅታ ተሰርቶ የቀረበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባለቤቶቹ በአዲሱ ላፕቶፕ ላይ ለሚነሱ ሌሎች ጥያቄዎች ወደፊት ሰፊ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረው በጥቂቱ ግን ከደቡብ ኮርያው የLG ኩባንያ ጋር በጥምረት ስለመስራታቸውና የኢንቴል ፕሮሰሰርም ስራው ላይ ስለመሳተፉ ጠቁመዋል፡፡
ከዋጋ ጋር ተያይዞም ለቀረበላቸው ጥያቄ አሁን መወሰን እንማይቻል ያስታወቁት ባለቤቶቹ፤ ከጥቂት ወራት በኋላ ላፕቶፑ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሽያጭ እንደሚገባና በተለይም በ2020 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ተናግረዋል፡፡
መረጃውን The Washington post ዘግቦታል

ጎግል በአይነቱ ልዩ የሆነ የመተርጎሚያ ሲስተም ይፋ አደረገ
***************************************
እርሶ በሚያውቁት ቋንቋ በሚናገሩበት ጊዜ የራሶን ድምፅ በሌላ ቋንቋ ቢያደምጡት ምን ሊሰማዎት ይችላል፡፡ በእርግጠኝነት ከመገረም አልፈው ራሶን ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡ እርሶ በሚያወሩበት ጊዜ የራሶን ድምፅ ከአናጋገር ስልቶ ጋር በሌላ ቋንቋ ማድመጥ እውነትም መገረም ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ሊያስደርግ ይችላል፡፡ ይሁንና ጎግል በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረገው አዲስ ሲስተም ይህን መገረም ወደ እውነታ የቀየረ ነበረ፡፡
ኩባንያው ልዩ በሆነው በዚህ ፈጠራው ሌሎች ቋንቋዎችን በቀላሉ እንድናውቅ ከማገዙ ባለፈ በመተርጎም ሂደት ውስጥ የግድ አስፈላጊ የነበረውን የሶስተኛ ወገን አጋዥነት እንዲቀር አድርጓል፡፡ Translatotron በሚል የተሰየመው አዲሱ ሲስተም ጎግል ከዚህ በፊት ሲሰራቸው እንደነበሩት የመተርጎሚያ ዘዴዎች ፅሁፍን መሰረት ያደረገ ሳይሆን ንግግርን በንግግር በቀጥታ በመተርጎም፣ በዚያ ላይ ደግሞ የተናጋሪውን ድምፀት እና የአነጋገር ስልት የሚጠብቅ ነው፡፡ https://www.facebook.com/TechinEthiopia/photos/a.565568780217878/2193351690772904/?type=3&theater

Facebook
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
ጎግል በአይነቱ ልዩ የሆነ የመተርጎሚያ ሲስተም ይፋ አደረገ ************************************************** እርሶ በሚያውቁት ቋንቋ በሚናገሩበት ጊዜ የራሶን ድምፅ በሌላ ቋንቋ ቢያደምጡት ምን ሊሰማዎት ይችላል፡፡ በእርግጠኝነት ከመገረም አልፈው ራሶን ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡ እርሶ...
የኪሎግራም ልኬት ተለወጠ
===============
ለ130 ዓመታት ገደማ የኪሎግራምን ክብደት ይወስን የነበረው ልኬት (Standard) ከትናንትናው ዕለት አንስቶ ተቀይሯል፡፡ በፓሪስ አቅራቢያ በሚገኘ ስፍራ የተቀመጠውና እስከትናንትናው ዕለት ድረስ የኪሎግራም ልኬት ሆኖ ያገለገለው የብረት ሲሊንደር ከስራው በጡረታ ሊሰናበት ግድ ሆኗል፡፡ በምትኩም ፕላንክ ኮንስታንት በመባል በሚታወቀው የኳንተም ብዛት ተተክቷል፡፡
ይህ ልኬት ታድያ በህዋም ሆነ በጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ አይለወጤ ልኬት እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ ለንፅፅ ትንሽ ጭረት እንኳን ቢያጋጥመው የመጠን ለውጥ በማምጣት ልኬቶችን ሊያዛባ ከሚችለው የብረት ሲሊንደር አኳያ ይህ መለኪያ በላቀ አስተማማኝ ነው፡፡ ይህን የልኬት ለውጥ ባፀደቀው 26ኛው የክብደትና ልኬቶች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተጨማሪነት የሙቀት፣ ኤሌክሪክ ከረንትና የቁሶችን መጠን መለኪያ የሆኑት ኬልቪን፣ አምፒር እና ሞል ድግም ልኬታቸው ተወስኗል፡፡
ሳይንቲስቶቹ በቀጣይነት አይናቸውን የጊዜ መለኪያ ወደሆነነው ሴኮንድ አማትረዋል፡፡ በምንገለገልበት ልኬት መሰረት ሴኮንድ ከሲዚየም አተሞች በተሰሩት አቶሚክ ሰዓቶች ዓማካኝነት ይለካል፡፡ እነዚህ አተሞች የብርሃን ፍሪክዌንሲን የሚመጡ ሲሆኑ የብርሃኖቹ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ዌቮች የጎንዮሽ ደርሶ መልስ እንቅስቃሴ ልክ በቀድሞዎቹ የግድግዳ ሰዓቶች ላይ እንደሚገኘው ባለ ክብ አናት ብረት በመሆን ጊዜን ያስቆጥራሉ፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ሴኮንድ 9,192,631,770 የብርሃን እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጡት የአዲሱ ትውልድ አቶሚክ ሰዓቶች ከሲዚየሞቹ አንፃር አንድ መቶ እጥፍ በተሸለ ጊዜን የመለካት ብቃት አላቸው፡፡ ይህ የልኬት ቅያሬ በ2020ዎቹ መባቻ እውን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ሆኖም ይህ ማለት ቀኑ ያጥራል ወይም ክብደት ይጨምረል ማለት አይደለም፡፡ በክብደትም ሆነ ጊዜ ላይ የሚደረጉት የልኬት ለውጦች ከተለመደው የኪሎግራም አሊያም ሴኮንድ መጠን ልዩነት እንዳያመጡ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚከውኑ ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ Science News

አንድ ቢሊዮን ዓመታትን ያስቆጠረ ቅሪተ-አካል ተገኘ
======================
ትናንት ኔቸር ጆርናል ላይ በወጣ ጥናት ከአንድ ቢሊዮን አመታት በፊት ይኖር እንደነበረ የተነገረለትን ፈንገስ ማግኘታቸውን ሳይንቲስቶች ይፋ አድርገዋል፡፡ ጥናቱ የህይወትን ዝግመተ ለውጥ እንመለከትበት የመነበረውን እይታ ሊለውጥ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡
ለብዙ አስርት ዓመታት በሰው ልጅ ዘንድ ቀደምት ተብለው ይታወቁ የነበሩት የመሽሩም፣ መኦልድ እና ዪስት ፈንገሶች ግማሽ ቢሊዮን ዓመታትን በምድር እንደኖሩ ጥናቶች ይነግሩናል፡፡ ሆኖም ይህ በካናዳ የተገኘው የፈንገስ ዝርያ በዘመን አፈራሽ የዕድሜ መመርመሪያ መሳሪያ ተመርምሮ በተረጋገጠው መሰረት ፈንገሶች በምድር ላይ ኖረዋል ተብሎ ይታመንበት የነበረውን ዕድሜ በእጥፍ ወደኋላ ገፍቶታል፡፡
በቤልጂየሙ ሊጅ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪው ኮረንቲን ሎሮን የቅሪቶቹን ኬሚካላዊ ቅንብር የሚለይ ምርመራ ያካሄዱ ሲሆን በውጤቱም የፈንገስን ህዋስ ግድግዳ የሚገነባውን ቺቲን የተሰኘ ፋይበር ነክ አካል በውስጡ ማግኘት ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ቅሪቶቹ የተገኙበትን አለት ውስጥ የራዲዮአክቲቭ ግብዓቶች የያዙትን ድርሻ በመለካት መርምረዋል፡፡ በመጨረሻ ውጤቱም ቅሪቱ ከ900 ሚሊዮን እስከ አንድ ቢሊዮን ዓመታት ያስቆጠረ እንደሆነ ደምድመዋል፡፡ እንደ ኮረንቲን ከሆነ ከቢሊዮን ዓመታት በፊት ፈንገሶች ይኖሩ ከነበረ ፈንገሶች ከእንስሳትና እፅዋት ጋራ ኢዩካሪዮትስ የተባለ የስነ-ህይወት ምድብን ስለሚጋሩ እንስሳትም በምድር ላይ ተመሳሳይ ጊዜን አስቆጥረዋል ማለት ነው፡፡ ይህም የሩቅ ዘመን ናቸው ብለን የደመደምናቸው ፍጥረታት በአንፃሩ ካሰብነው በላይ የቅርብ እንደሚያደርጋቸው ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡
ፈንገሶች በፕላኔታችን ላይ በበስፋት የሚገኙ ፍጥረታት ሲሆኑ ከእፅዋት እና ባክቴሪያዎች በመቀጠልም ሶስተኛ ደረጃን ይዘው የሚገኙ የምድራችን ባዮማስ ባለድርሻዎች ናቸው፡፡ አንድ ላይ ብንመዝናቸው እንኳን መላው የሰው ልጅ እና እንስሳት ተዳምረው ካላቸው ክብደት ስድስት እጥፍ የላቀ ነው፡፡
ምንጭ፡ phys.org

የረመዳን ወርን በእኛው ቤት
**********************
ቅዱሱን የረመዳን ወር በማስመልከት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ ልዩ የበዓል ዝግጅት አዘጋጀ፡፡ በዚህ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በቀረቡበት ዝግጅት ላይ የኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞችን ጨምሮ ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶችም ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ የዝግጅቱን መክፈቻ ንግግር ያደረት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የተቀረው የፆሙም ወቅት መልካም ይሆን ዘንድ ምኞታቸውን አጋርተዋል፡፡
በተጋባዥ እንግድነት ተካፋይ የነበሩት የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ታደለም የበጎ አድራጎት ማህበሩ እያከናወናቸው ስላሉት ተግባራት ለታዳሚያኑ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ ጨምረውም ኢኒስቲትዩቱ እና የበጎ አድራጎት ማህበሩ በጋራ ስላከናወኗቸው ስራዎች ተናግረዋል፡፡
ዝግጅቱን ያዘጋጀው የላምባዲና ሶሻል ኮሜቴ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራተኞችን እርስ በእርስ መስተጋብር ይበልጥ ለማሳደግ ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ መሰል አሳታፊ ሁነቶችን ከማዘጋጀት ባለፈም በልዩ ልዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ሰራተኞችን የሚያሳትፍ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ የአንድ ልጅን ወጪ በመሸፈን ማሳደግ ይገኝበታል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይም ሰራተኞቹ ወጪ በመሸፈን የሚያሳድጉትን ህፃናት ቁጥር ወደ ሁለት ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡

በሳይንሳዊ የሐብት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተጀመረ
ሐገራዊ የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ሊሰሩ የሚገባቸውን መዋቅራዊ ተግባራት እንዲሁም እንዲጎሉ የሚጠበቁ ጥንካሬዎች ለማመላከት ያለመ ወርክሾፕ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ፡፡ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዓለም አዕምሮ ንብረት ድርጅት (WIPO) ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ወርክሾፕ ላይ ኢኒስቲትዩቱን ጨምሮ ከሶስት ተቋማት ተውጣጡ ተሳታፊዎች ሲታደሙበት እስከ ግንቦት 21 ድረስም የሚቀጥል ነው፡፡
በዛሬው ውይይት ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እና ስልጠና ተካሂዶባቸው አልፈዋል፡፡ ከነዚህም ቀዳሚው በሐገራችን ያለው የጥናት እና ምርምር ተቋማት እጥረት እንዲሁም የሣይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን በመጠቀም ረገድ ያለው ክፍተት ነው፡፡ በውይይቱም ይህን ክፍተት መድፈን ይቻል ዘንድ ሁሉን አቀፍ የሆነና በዋናነትም አመራሩን ያሳተፈ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባና በዋናነት የትምህርት ስርዓቱን በማሻሻል ላይ ያተኮሩ ተግባራት እንዲከወኑ ምክረ ሀሳብ ቀርቦባቸዋል፡፡
ሌላው በመድረኩ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረው በሐገራችን ያለው የተፈጥሮ ሐብት አጠቃቀም ነው፡፡ በሐገራችን ያለው የተፈጥሮ ሐብት በቀላሉ ሊታይ የማይገባ ቢሆንም ዋና ትኩረቱ ግን ወደ ሰው ሐብት ልማት እና እነዚህን የተፈጥሮ ሐብቶች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ወደመጠቀም ሊዞር እንደሚገባ ተነስቶበታል፡፡ በዚህ ረገድ እንደ ቡናና ሽፈራው ያሉ የሐገራችን ሐብቶች ላይ አብይ ትኩረት እነዲሰጥና በእነርሱም ዙሪያ ሰፊ የምርምር እና ስርፀት ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሳህለማርያም ጋራ በነበረን ቆይታ መሰል ሳይንሳዊ የሐብት አጠቃቀምን እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ ዝግጅቶች በቀጣይነት እንደሚዘጋጁ ለማወቅ ችለናል፡፡