ለመሆኑ ብዙ ተስፋ የተጣለባት ብላክ ቦክስ ምንድን ናት?
*********************************************************
ከሰሞኑ የብዙዎችን ልብ ከሰበረው አውሮፕላን አደጋ በኋላ በኢትዮጵያም ይሁን በመላው ዓለም የሚገኙ የተጎጂ ቤተሶቦች እና መላው ህዝብ አደጋው የተፈጠረበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማውቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ደግሞ አደጋው ከተከሰተ ጥቂት ቀናት በኋላ በብዙ ፍለጋ የተገኘቸው ብላክ ቦክስ ወደ ፈረንሳይ ተልካ በአደጋው ወቅት የነበረውን አጠቃላይ ሁነት ለማሳየት የሚያስችሉ መረጃዎችን ልትሰጥ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ናት የሚል መረጃ ከወጣ ጀምሮ የሁሉም ዓይን በመረጃ ሳጥኗ ላይ ያነጣጠረ ሆኗል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም የሚያስችል አቅም አላት የምትባለው ይህች ብላክ ቦክስ አጠቃላይ መረጃዋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ስለቴክኖሎጂዋ አፈጣጠር
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1934 የዶክተር ዴቪድ ዋረን አባት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ዴቪድ ገና የዘጠኝ አመት ልጅ ነበር፡፡ አባቱን ይዞ እንደወጣ ያልተመለሰው አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት እንኳን ሳይታወቅ የዴቪድን ልብ እንደሰበረ ቀረ፡፡ ይህ ሁነት ሁሌም ቁጭት የሚፈጠጥርበት ዴቪድ በ1950 በበረራ ወቅት መረጃዎችን የምትመዘግብና የድምፅ ምልልሶችን የምትቀዳ መሳሪያ ለመፍጠር መነሻ ሆነው፡፡ የአዎስትራሊያ ዜጋ የሆነው ዴቪድ የዚችን መሳሪያ ፕሮቶታይፕ በ1956 ሲሰራ በመጀመሪያ "ARL Flight Memory Unit" የሚል መጠሪያ የሰጣት ቢሆንም ከአምስት አመት በኋላ በአሜሪካ እና እንግሊዝ አማካኝነት ወደ ሙሉ ምርት እንድትገባና እና አሁን የያዘችውን ስያሜም እንድታገኝ ሆኗል፡፡
የብላክ ቦክስ ገፅታ
የመረጃ ሳጥን ወይም ብላክ ቦክስ ሁለት አይነት ገፅታ ሲኖራት እነሱም flight data recorder (FDR) እና cockpit voice recorder (CVR) ይሰኛሉ፡፡ FDR የሚባለው በቋሚነት በየቦታው በተገጠሙለት ሴንሰሮች አማካኘነት ከኤሌክትሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እያንዳንዳቸውን ነገሮች ለምሳሌ የሞተር ኃይል እና ፍጥነትን ሲመዘግብ፤ CVR የተባለው ደግሞ በበረራው ወቅት የተሰሙ የፓይለቶችን እና የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ አካላትን አጠቃላይ ግንኙነቶችን የሚመዘግብ ነው፡፡ ብላክ ቦከስ ብዙዎች እንደሚያስቡት ጥቁር ቀለም ያላት ሳጥን ሳትሆን በአለም አቀፉ የኤሮስፔስ የቀለም አጠቃቀም መሰረት ከተፈጥሮአዊ ገፅታዎች ለመለየት የብርቱካናማ ቀለም እንዲኖራት ተደርጓል፡፡
የብላክ ቦክስ መሳሪያ ይዘት
የብላክ ቦክስ መሳሪያ አብዛኛውን ጊዜ በቲታንየም ወይም በማይዝግ ብረት የሚሸፈን ሲሆን 227 ኪ.ግ ክብደትም ይመዝናል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም ይችላል የሚባለው የብላክ ቦክስ መሳሪያ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ የ100 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መቋቋም ከመቻሉም በላይ ከፍተኛ እርጥበት እና በግፊት የተሞላ ጨዋማ ውሃ ውስጥ ሆኖ እንኳን የያዘውን መረጃ ሳያጣ ለ2 ዓመት መቆየት ይችላል።
መረጃ የማከማቸት አቅም
ብላክ ቦክስ በቀላሉ የማይጎዳ ከመሆኑም ባለፈ 3400 Gs የመረጃ ቋትም አለው። ይህም ማለት ከአዲስ አበባ ሳኦ ፖሎ ብራዚል የሚበር አውሮፕላን፤ ደርሶ አስኪመለስ ያለውን አጠቃላይ መረጃ ማለትም የአብራሪውን እንቅስቃሴ፣ የአውሮፕላኑን ፍጥነት፣ ከፍታውን፣ የነዳጅ ሁኔታ እና ሌሎች አንቅስቃሴዎቹን ይመዘግብለታል ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ CVR የተባለው የብላክ ቦክስ ገፅታ ለ25 ሰዓታት የሚቆይ የበረራ መረጃን ለማከማቸት ዲጂታል መቅጃዎችን የሚጠቀም ቢሆንም በራሱ ለመቅዳት ሲፈልግ ግን የሁለት ሰዓት የበረራ መረጃን ብቻ ይይዛል፡፡
ምንጭ፡ ABC News እና wired.com

ውሃ የሰው ልጆች ፀጋ!!!
*********************
ዛሬ ለሰው ልጅ ከማናቸውም ነገሮች በላይ አስፈላጊ የሆነው “ውሃ” ታስቦ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ፀጋ ምናልባት ከኦክስጂን ቀጥሎ ለሰው ልጅ ህልውና እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው ቢባል የሚያከራክር አይደለም፡፡ ሰውነታችን ያለ አንዳች ሳንካ በተስተካከለ ሁኔታ ይሰራ ዘንድ ውሃ በጣም ያስፈልገዋል፡፡ በቀላል አነጋገር በበቂ ሁኔታ ንፁህ ውሃ በጠጣን ቁጥር ይበልጥ ጤናችንን አስተማማኝ እናደርጋለን፡፡ በቂ ውሃ መጠጣትን ችላ ማለት ወይም መዘንጋት ለህይወታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ኦክስጂንን የመርሳት ያህል ሊቆጠር ይችላል፡፡ ውሃ ጤንነታችንን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ረጅም ዕድሜና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ይህንን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ስለውሃ አንዳንድ ዕውነታዎችን አብረን እንቃኝ ፡፡
ውሃን የሚተካው ውሃ ብቻ ነው
ማናቸውም የውሃ ይዘት ያላቸው እንደ ጭማቂ፣ ሶዳ፣ ሻይ ቡና ወዘተ-- አይነት ፈሳሾች ከውሃ የምናገኘውን ከፍተኛ ጥቅም ተክተው እንደ ውሃ በመሆን ፈፅሞ አያገለግሉም፡፡ ይልቁንም አንዳንዶቹ ውሃ በውሃነቱ የሚሰጠን ጥቅም ከማሳጣት አልፈው በጤናችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡ ለምሳሌ በውስጣቸው የካፊን ንጥረ ነገር የያዙ ፈሳሾች ከሰውነት ውስጥ በመቀነስና በማድረቅ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሁኑ ቫይታሚኖችንና ሚኒራሎች በማስወገድ ጉዳት ያስከትላሉ ፡፡ በውስጣቸው ስኳር የያዙ መጠጦችንም እንዲሁ ጣፍያችንን በማነቃቃትና የኢንሱሊን መጠን እንዲጨምር በማድረግ ሰውነታችን በተለመደው መንገድ ስብ የማቃጠል ስራውን እንዲያካሂድ በማወክ ለችግር ያጋልጣሉ፡፡
ውኃና ክብደት፡- ውሃ ክብደትን በመቀነስ ረገድ አስገራሚ ውጤትን ያስገኛል፡፡ ልብ ይበሉ ውሃ በውስጡ ምንም አይነት ካሎሪ፣ ስብ ወይም ለኮሌስትሮል የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር የለውም ፡፡ የሶዲየም ይዘቱም እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ የክብደት መጨመር ችግር ላለባቸው በቂና ንፁህ ውሃ መጠጣት ከፍተኛ የምግብ ፍላጎታቸውን በመቀነስ ተጨማሪ የስብ ክምችት ወደ ሰውነታችን እንዳይገባ በማድረግ የስብ ክምችትን በማቃጠል ክብደታቸውን እንዲቀንሱ ያግዛቸዋል፡፡ የቅርብ ግዜ ጥናቶች እንዳሳዩትም በቂ ውሃ የማይወስዱ ሰዎች ለከፍተኛ የስብ ክምችት የተጋለጡ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
ውሃና ኩላሊት፡- ኩላሊታችን ከሰውነታችን መወገድ የሚገባቸውን ነገሮች በማጣራት የማስወገድ ተግባርን ያከናውናል፡፡ ሰውነታችን በቂ ውሃ ካለገኘ በቀላሉ በውሃ የሚሟሙ እንደ ዩሪክ አሲድ፣ ዩሪያ ላክቲክ አሲድና ሌሎች መሰል ከሰውነታችን መወገድ የሚገባቸውን ንጥረ ነገሮች ማስወገድ ስለሚሳነው ኩላሊታችን በመጉዳት ለአደጋ ያጋልጠናል፡፡
ውሃና አንጎላችን፡- የአንጎላችን ቲሹ /Brain tissue/ 85 በመቶ ውሃ ነው፡፡ አንጎላችን ከጠቅላላ የሰውነት ክብደት 1/50ኛ ያክል የሚመዝን ሲሆን ከጠቅላላ የሰውታችን የደም ዝውውር ደግሞ 20 ከመቶውን ይወስዳል፡፡ በመሆኑም በቂ ውሃ አለመውሰድ ወደ አንጎላችን መድረስ የሚገባውን የደም ዝውውር መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር የመጫጫን ስሜትና ቋሚ የድካም ስሜትን እንደሚፈጥር ጥናቶች ይጠቁማሉ ፡፡
ውሃና እርግዝና፡- የማለዳ ህመም /Morning sickness/ በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት የታወቀና የተለመደ ነው፡፡ ለዚህ ህመም ምክንያት ናቸው ከሚባሉት አንዱ የሰውነታችን ውሃ ይዘት አነስተኛ መሆን ወይም በቂ አለመሆን ነው፡፡ ይህም በእርግዝና ወቅት እናት ከራሷ በተጨማሪ ሽሉን የምትመግብ በመሆኗ ሰውነት ከወትሮው በተለየ ተጨማሪ ውሃን ሲፈልግ ማግኘት ባለመቻሉ የሚፈጠር የህመም ስሜት ነው፡፡ በእርግዝና ወራት በቂና ንፁህ ውሃ አለመውሰድ ከእናትዮዋ አልፎ ለሽሉም አይበጅምነና እናቶች ልብ በሉ፡፡
ለጤንነታችን ካሰብን ውሃ እስኪጠማን አንጠብቅ
ውሃ ጥም /Thirst Refle/ ውሃ ከሰውነታችን እየተሟጠጠ መሆኑን የሚያመለክት ከባድ መልዕክት ነው፡፡ ውሃ እስኪጠማን በፍጹም መጠበቅ አይኖርብንም ፡፡ የውሃ ጥም ተሰማን ማለት ሰውነታችን በወቅቱ ማግኘት የሚገባውን የውሃ መጠን ባለማግኘቱ የሚፈጠረው ጉዳት ደርሷል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አስኪጠማን ሳንጠብቅ የመጠጣት ልማድን ልናዳብር ይገባናል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ሰው በአማካይ በቀን ምን ያህል ውሃ መጠጣት አለበት? የሚል ተገቢ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በመሆኑም መውሰድ የሚገባን የውሃ መጠን እንደ የስራ ባህሪያችን፣ እንደምንኖርበት የአየር ፀባይ፣ እንደ ሰውነት ክብደታችንና እንደ አመጋገብ ልማዳችን እንዲሁም እንደ አካላዊ እንቅስቃሴያችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ 45 ኪ.ግ የሚመዝን ሰው በቀን 1.486 ሊትር ውሃ እንዲጠጣሁኔታ ይመከራል ፡፡ ስለሆነም ውሃ ለሰው ለጅ ከማናቸውም መደኃኒት በላቀ ፈውስን የሚይገኝ ሰለሆነ ንፁህና በቂ ውሃ በመጠጣት ጤንነታችንን እንጠብቅ መልዕክታችን ነው፡፡
ምንጭ፡ BG WIEB

የስራ ማስታወቂያ
ተቋማችን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በምስሉ ላይ በተገለፁት የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጥር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኢንስቲትዩታችን ድህረ-ገፅ ላይ (http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/techin11) ሄዳችው መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የዓለም ምርጥነት ክብርን ስለተቀናጀው ሲንጋፖራዊ ህንፃ
===================================
ዓለማችን አሁን ከደረሰችበት የብክለትም ሆነ የግንዛቤ ደረጃ ጋር በተገናኘ አረንጓዴ ልማት ወደ ቀዳሚ አጀንዳነት ተሸጋግል፡፡ ከዚህ ባህረ ሃሳብ ውስጥ ደግሞ የአረንጓዴ ህንፃዎች ግንባታ አንዱ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተከናወነው የዓለም ኪነ ህንፃ ፌስቲቫል (WAF) ላይ የዓመቱ ምርጥ ህንፃ በመሰኘት የሲንጋፖሩ ካምፑንግ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ይህ ህንፃ ሽልማቱን እንዲያገኝ ያስቻለው ታድያ ይህን የአረንጓዴነት ባህርይ ከሌሎች ማህበራዊ እሳቤዎች አስተሳስሮ በመሰራቱም ነው፡፡
በሰሜናዊው የከተማይቱ ክፍል የታነፀው ይህ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ሰጪ ህንፃ ከአንድ ሄክታር ባነሰ መሬት ላይ የቆመ ነው፡፡ በውስጡም ክፍት የህዝብ ቦታ፣ የህዝብ ፓርክ እና የህክምና ዓገልግሎት መስጫን ከመኖሪያ ቤቶች አዋህዶ ይዟል፡፡ የህንፃው ዲዛይን በኪነ-ህንፃው አርቃቂዎች ዘንድ “club sandwich” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በተለያዩ ወለሎች ላይ ይሰጣል፡፡ ህንፃው በዓጠቃላይ የታች፣ መካከለኛ እና የላይኛው በተባሉ ሶስት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን ባለ አስራ አንድ ወለል እና 104 አፓርታማዎችንም አቅፎ ያዘ ነው፡፡ የታችኛው ክፍል ለህዝብ ክፍት የተደረጉ መናፈሻ፣ ቴራሶችን እንዲሁም የመመገቢያ ስፍራዎችን ይዟል፡፡
የካምፑንግ ህንፃ በሃገሪቱን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰውን የእርጅና ጉዳይ ከግምት ውስጥ ማስገባቱ በታላላቅ የኪነ-ህንፃ ባለሙያዎች ዘንድ አድናቆትን ገዝቶለታል፡፡ ዕድሜው እየገፋ የመጣውን የሃገሪቱን ነዋሪ አካታች በሆነ መልኩ መገንባት እንደሚቻል ለማሳየት የታነፀ ሰርቶ ማሳያ መሆኑ ደግሞ ገና የአግራሞች መጀመሪያ እንጂ መቋጫ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ መሰል ዘጠኝ የቤት ግንባታዎችን ለመስራትም የሃገሪቱ መንግስት እየተንቀሳቀሰ ነውና፡፡
ሐገርም ከተማም የሆነችው ሲንጋፖር በእርግጥ በግንባታ ጥበብ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ህንፃዎችን ገንብታ ለአድናቆት እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ስታበቃ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም፡፡ ከዚህ አስቀድሞ ለሁለት ጊዜ ያህል ህንፃዎቿ በተመሳሳይ ሁኔታ ለሽልማት በቅተውላታል፡፡ ሆኖም እዛው ሃገሪቱ ላይ መሰረቱን ባደረገ ተቋም ዲዛይን ተደርጎ ለዚህ ክብር ሲበቃ ግን የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ CNN style

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አመላካች ጥናቶችን ሊያከናውን ነው ====================================
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሐገራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁኔታ-አመላካች የሆኑ የኢኖቬሽን ዳሰሳ እንዲሁም የማህበረሰቡን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ግንዛቤ ዳሰሳ ጥናት ከመጋቢት 23 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ወራት በመላው ሐገሪቱ በሚገኙ 408 ቀበሌዎች ይከናወናል፡፡
የኢኖቬሽን ዳሰሳ ጥናት፤ በሃገሪቱ በሚገኙ የንግድ ተቋማት የኢኖቬሽን ተግባራትን የሚዳስስ ሲሆን ጥናቱ ሲጠናቀቅ ለመንግስት አካላት፣ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት ግብዓት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
የማህበረሰቡን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው ጥናት ማህበረሰቡ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዙሪያ ያለውን ዕውቀት፣ ዝንባሌ፣ ፍላጎት እንዲሁም አመለካከት በመዳሰስ በሐገራችን ያለውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ደረጃ ያመላክታል፡፡
ጥናቶቹ ለሐገሪቱ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዕድገት፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሰጪነት ላይ የላቀ አስተዋፅም ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ህብረተሰቡ ይህን በመገንዘብ ወደ እነርሱ ለሚመጡ የጥናት ቡድኖች ተገቢውን ድጋፍ እና መረጃ በመስጠት ሐገራዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ በአክብሮት ጠይቋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ዕርዳታ፤ ለትራፊክ አደጋ
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
ሐገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም ሚሊዮኖች በየዓመቱ ህይታቸውን በትራፊክ አደጋ ያጣሉ፡፡ ለዚህ የአደጋው መከሰት ዋነኛው ምክንያት ቢሆነም ከአደጋው በኋላ ያለ የተጎጂዎች ዕርዳታ አሰጣጥም የራሱን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ለዛሬ የትራፊክ ዓደጋ ለሚያጋጥማቸው ሁሉ እንዴት የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጠት እንዳለብን እንይ፡፡
• የመጀመሪያ ዕርዳታ በመስጠረት ውስጥ ቀዳሚው እርምጃ ሊሆን የሚገባው እራስን ከተጨማሪ አደጋ መጠበቅ ነው፡፡ ወደ አደጋው ስፍራ ሲያመሩ በዙሪያዎ የሚንቀሳቀሱ መኪኖች አለመኖራቸውን ያረጋግጡ፡፡
• ከደረሱም በኋላ የነዳጅ መፍሰስና ሌሎች እሳት አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች ካሉ የመኪናውን ሞተር ያጥፉ፡፡
• በአጠገብዎ ሌሎች ሰዎች ካሉ ወደ አንቡላንስ እንዲደውሉልዎ ያድርጉ፡፡ ሆኖም ብቻዎን ከሆኑ ተጎጂው ለህልፈት ሊያበቁ ከሚችሉ ሁናቴዎች ካላቀቁ በኋላ ወደ አንቡላንስ ይደውሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በአደጋው የተሳተፉ መኪኖችን እና በውስጣቸው ያለውን ተጎጂ ሁኔታ በአፅንዖት ይገምግሙ፡፡
• ቀዳሚ ትኩረትዎን ድምፅ እያሰሙ ያልሆኑ ወይም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ተጎጂዎች ላይ በማድረግ መተንፈስ አለመተንፈሳቸውን ምላሽ መስጠት አለመስጠታቸውን ያረጋግጡ፡፡
• እየተነፈሱ ሳለ እንቅስቃሴ ካላከናወኑ በእርጋታ በትክክል በሚተነፍሱበት አቀማመጥ ላይ ያድርገዋቸው፡፡ ታድያ ይህን ሲያደርጉ ተጎጂውን ለማዋራት መሞከርዎን እንዳያቋርጡ፡፡
• ሆኖም ተጎጂው አደጋ ውስጥ (የእሳት፣ ጎርፍ፣ ፍንዳታ…) ካልሆኑ በስተቀረ የህክምና ባለሙያ እስከሚደርስ ካሉበት ባያወጧቸው ይመረጣል፡፡ የግድ ከሆነ ግን እንደ ስልክ ያሉ መንገዶችን በመጠቀም ከህክምና ባለሙያዎች እርዳታ በማግኘት ጭምር ያውጧዋቸው፡፡
• የጀርባ አጥንት ላይ ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል የተጎጂዎቹን አንገት አያንቀሳቅሱ፤ እየደማ ያለ የሰውነት አካል ካለም ጓንትን ተጠቅመው በጨርቅ የደም ፍሰቱን ማስቆም፡፡
• በቦታው ላይ ማንም ሰው እንዳያጨስና ለተጎጂዎቹም ምንም አይነት መጠጥም ሆነ ምግብ እንዳይሰጥ ያድርጉ፡፡
• ተጎጂው የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ከሆነና እራሱን ከሳተ ሂልሜታቸውን በጥንቃቄ ያውልቁት፡፡ ሆኖም እራሳቸውን ካልሳቱ የፊት መስታውቱን በመክፈት ብቻ እርዳታ ይስጧቸው፡፡
• ተጎጂው በመኪና ተገጭቶ የወደቀ እግረኛ ከሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበርና የጀርባ አጥንቱን በማይጎዳ አኳሃን ቀጥ ብለው እንዲተኙ በማድረግ ምቹ የአተነፋፈስ ሁኔታን መፍጠር ይገባል፡፡ ተጎጂው በመኪና ተገጭተው አሊያም ከመኪና ውስጥ በግጭቱ ተወርውረው የወጡ ከሆኑና እራሳቸውን ካልሳቱ እንደነቁ እንዲቆዩ ያበረታቷቸው፤ ሙቀት ወዳለበት ስፍራም ይውሰዷቸው፡፡
• ይህን ሁሉ ከሲያደርጉ ቀድሞ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በዙሪያዎያለን የትራፊክ እንቅቃሴ በማስቆም አሊያም የሚያስተናብር ግለሰብ በመሰየም እራስዎን እና ተጎጂን ከተጨማሪ አደጋ ይታደጉ፡፡
ሼር በማድረግ ሃላፊነትዎን ይወጡ
ምንጭ፡ First Aid For Life

በዓይነቱ ልዩ የሆነው አውሮፕላን
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
ጀማሪ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ፋራዳየር ኤሮስፔስ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ባለ አስራ ስምንት መቀመጫ የባዮኤሌክትሪክ ሃይብሪድ (ቅልቅል) አውሮፕላን ዲዛይኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ አውሮፕላኑንም ባዮ ኤሌክትሪክ ሃይብሪድ ኤርክራፍት (BEHA) ሲል ሰይሞታል፡፡ ሞዴሉም ኤም 1 ኤች ሲባል ሶስት ባለ ሳጥን ቅርፅ ክንፍ ይኖረዋል፡፡
ኤም 1 ኤች በሚነሳበት እና በሚያርፍበት ወቅት የኤሌክትሪክ ሞተሩን ይጠቀማል፡፡ ይህም የተለምዶዎቹ የጀት አውሮፕላኖች ከሚያወጡት 140 ዴሲ ቤል በእጅጉ ያነሰ የ60 ዴሲ ቤል ድምፅ እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ አውሮፕላኑ እንዲነሳና እንዲያርፍ የሚያስችለውን ሞተር ቻርጅ ለመሙላት እንዲሁም እንዲበር ያደርገው ዘንድ 1,600 የፈረስ ጉልበት ያለው የቱርቦፕሮፕ ሞተር ይገጠምለታል፡፡ እንደ ተቋሙ ገለፃ ከሆነ ከተለምዶው አውሮፕላን ያነሰ የመንደርደሪያ ቦታንም ይፈልጋል (ሶስት መቶ ሜትር ብቻ)፡፡ ይህ እንዲሆን ያስቻሉት በተቃረነ አቅጣጫ የሚዞሩ ሽክርክሮሾቹ በሚያመነጩት የቬክትረም ትረስት፣ የክንፎቹ ዲዛይን እና በተሰራበረት የካርበን ንጥረ-ነገሮች ሳቢያ አውሮፕላኑ የተላበሰው ቀላል ክብደት አማካኝነት ነው፡፡ በተጨሪም አውሮፕላኑ በሰዓት እስከ 370 ኪ.ሜ ድረስ የመክነፍ ብቃት እንደሚኖረው ታውቋል፡፡
በዚህ ስራ ላይ የስዋንሲዩኒቨርሲቲን በአጋርነት ያቀፈው ይህ ተቋም አውሮፕላኖቹን በ2025 ወደ አገልግሎት እንደሚያስገባ ገልጿል (አውሮፕላኖቹን አነስተኛ የአየር መንገዶች እንደሚሸምቱ በመጠበቅ መሆኑ ነው)፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ አውሮፕላኑ የሚበረው የባዮፊውልን በመጠቀም መሆኑና የኤሌክትሪክ ሞተሩን ለማኮብኮብ መገልገሉ ለከባቢ አየር ተስማሚ ብሎም ወጪ ቆጣቢ አማራጭ እንደሚያደርገው ተነግሮለታል፡፡ በሚያጓጉዘው ጭነት ረገድም አውሮፕላኑ ከተሳፋሪዎች ጫኝ አውሮፕላንነት ወደ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላንነት ለመለወጥ አስራ አምስት ደቂቃዎችን ብቻ መውሰዱ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ Techxplore

አማዞን የፈጣን በይነ-መረብ አቅራቢ ሳተላይቶችን ሊያመጥቅ ነው
===============================================
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሳተላይት ላይ የተመሰረተ የበይነ-መረብ (Internet) ዓገልግሎትን ለማቅረብ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት በመሽቀዳደም ላይ ናቸው፡፡ በትናንትናው ዕለትም አማዞን የ3,236 ሳተላይቶች እርስበእርስ ግንኙነትን በመዘርጋት ፈጣን የበይነ-መረብ አገልግሎትን ለመላው ዓለም ለማዳረስ እንደሚሰራ በመግለፅ ሩጫውን ተቀላቅሏል፡፡ ፕሮጀክት ኩኢፐር የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ስራ ሳተላይቶቹን በዝቅተኛው የምድራችን ምህዋር በማስፈር አነስተኛ የመዘግየት መጠን ያለውን ፈጣን የበይነ-መረብ ዓገልግሎት በይነ-መረብ በበቂ ሁኔታ አሊያም ሙሉ ለሙሉ ባልተዳረሰባቸው የዓለማችን ስፍራዎች ላይ ለማዳረስ እንደሚሰራ አማዞን ገልጿል፡፡
ታላላቆቹ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ትኩረት እየሳበ በመጣው በዚህ ዘርፍ ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የበይነ-መረብ አገልግሎት ላልደረሳቸው 3.8 ቢሊዮን የዓለማችን ነዋሪዎች ከአገልግሎቱ እንደሚያስተዋውቁ ሲጠበቅ ለኩባንያዎቹም ጠቀም ያለ ትርፍን እንደሚያስገኙ ይነገርላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ከወራት በፊትም ዋን ዌብ የተሰኘ ኩባንያ መሰል ፈጣን የበይነ-መረብ አገልግሎትን አቅራቢ የሳተላይቶች ትስስርን ለመመስረት ይረዳው ዘንድ የመጀመሪያ ሳተላይቱን ማምጠቁ ይታወሳል፡፡ ሌላኛው ስመ ጥር የህዋ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ተቋም ስፔስ ኤክስም ለተቋማቱ ሳተላይቶችን የማምጠቅ ስራን ከመስራቱም በተጓዳኝ የራሱን መሰል የሳተላይት ትስስር ለመገንባት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም ሁለት ሰርቶ ማሳያ ሳተላይቶችን ማምጠቅ ችሏል፡፡ ፌስቡከልም ቢሆን ከዚህ አልቦዘነም፤ ከስፔስ ኤክሱ የስታርሊንክ ሳተላይት አስር እጥፍ መረጃን የማስተላለፍ ፍጥነት ያለውን አተና የተሰኘ ሳተላይቱን ለዚህ ተግባር በማሰብ እያበለፀገ ይገኛል፡፡
ይህች የአማዞኗ ኩኢፐር ሳተላይት የንድፍ፣ ማበልፀግ እና ወደ ህዋ የማጓጓዝ ስራዋ በሌላኛው የጄፍ ቤዞስ ኩባንያ ብሉ ኦሪጅን አማካኝነት የሚከወን ይሆናል፡፡ ብሉ ኦሪጅን ከዚህ በተጓዳኝ ቴሳት ከተባለ ተመሳሳይ የበይነ መረብ አገልግሎትን ለማቅረብ ከሚሰራ ተቋም ጋር ሳተላይቶችን የማምጠቅ ውል አስሯል፡፡
ምንጭ፡ Tech Crunch