TechIn2
1.23K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የሳተላይቶች አይነትና ምንነት
ሳተላይቶች በሚሰጡት ሚና እና ሌሎች መመዘኛዎች ተከፋፍለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ አነዚህ ሳተላይቶች በቴክኖሎጂ ባህሪያቸው እና በቁሳዊ ይዘታቸው ከፋፍለን ካስቀመጥናቸው በተለያዩ ግዜያት ስርአተ-ፀሀያችን ውስጥ ወዳሉ የህዋ አካላት የተላኩ ሳተላይቶች በዋነኝነት በሶስት ጎራ ሊመደቡ ይችላሉ። አነዚህ ሳተላይቶች ወይም የጠፈር መንኮራኩራኩሮች ኦርቢተር፣ ላንደር እና ሮቨር ሲሆኑ ምንነታቸውም እንደሚከተለው ነው፡፡
ኦርቢተር (orbiter) የምንላቸው ሳተላይቶች ያንን የህዋ አካል (ፕላኔት፣ ኮሜት፣ አስትሮይድ ወዘተ) በመጠጋትና ምህዋሩ ውስጥ በመግባት እና በመዘዋወር መረጃ የሚሰበስቡ ናቸው። እንደ ምሳሌ ምድራችንን ከ 400 ኪ.ሜ ከፍታ ሆኖ የሚዞራትን የአለም አቀፉን የጠፈር ማእከል (International space station) ማንሳት እንችላለን።
ላንደር (Lander) የምንላቸው ሳተላይቶች የኦርቢተሮች ንኡስ-አካል ሲሆኑ ከኦርቢተሮች ተገንጥለው ወደ ህዋ አካሉ ወለል በመውረድ እና ራሳቸውን በመትከል ውስን ቦታ ላይ ሆነው የታቀደላቸውን አላማ ያከናውናሉ። ለአብነት ያህል የሳተርን ግዙፏ ጨረቃ የሆነችው ታይታን (Titan) ፎቶ ያነሳችውን ሀይጅንስ የተባለችውን ላንደር ማንሳት ይቻላል።
ሮቨር (Rover) የምንላቸው የኦርቢተሮች ንኡስ-አካል ሆነው ወደ ህዋ አካሉ ወለል ከወረዱ በሁዋላ በመንቀሳቀስ መረጃን የሚሰበስቡ የሳተላይት አይነቶች ናቸው። ፕላኔት ማርስ ላይ ካሉት 3 ሮቨሮች ውስጥ 'ኪውሪዮሲቲ' የተባለችው ሮቨር በምሳሌነት ልትጠቃስ ትችላለች።
ምንጭ፡ Airtable universe እና E.A
አየርን ከብክለት መጠበቅ መጠነ ሞትን ለመቀነስ
***************************
የአለም ጤና ድርጅት የአየር ብክለትን በመቀነስ በአውሮፓ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞት መታደግ እንደሚቻል አሳወቀ፡፡ እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በአለማችን በየአመቱ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአየር ብክለት ምክንያት እየሞቱ ሲሆን ለሰዎች ጤና መታወክ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ዋነኛውም ይህ የአየር ብክለት ነው፡፡
ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ያለባቸውና ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀሙ ከተሞች ከአየር ብክለት ጋር ለተያያዙ ችግሮች የመጋለጥ እድላቸው ላቅ ያለ ነው፡፡ የአለም ጤና ድርጅት PM2.5 በመባል የሚታወቁት ብናኞች በከባቢ አየር ውስጥ ያላቸው መጠን በኪዩቢክ ሜትር ከ10 ሚሊ ግራም እንዳይበልጥ የሚመክር ሲሆን ለ NO2 ደግሞ ከ40 mg/m3 እንዳይበልጥ ይመክራል፡፡ በቅርብ የወጣ አንድ ጥናት እነዚህ ሁለት በካይ ነገሮች 1000 በሚሆኑ የአውሮፓ ከተሞች ለሰዎች ህይወት መጥፋት ያላቸውን ተጽእኖ አሳይቷል፡፡ በዚህም የPM2.5 እና NO2 መጠንን መቀነስ በየአመቱ 51,213 ሰዎችን ከሞት መታደግ እንደሚያስችል አመልክቷል፡፡
አንድ የባርሴሎናው አለማቀፍ ጤና ምርምር ተቋም ተመራማሪ ምርምሩ ከተሞች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እየሰሩት ያለው ስራ አነስተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ በአየር ብክለት ምክንያት ያለው የሞት ሁኔታ የተለያዩ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን ለምሳሌ NO2 ከአጠቃላዩ የሞት መጠን 7 በመቶውን የሚይዝ ነው፡፡ ጥናቱ በከተማ የሚኖሩ ሰዎች 84 በመቶ ያክል የአለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ልኬት በላይ ለሆነ የPM2.5 ብክለት ተጋላጮች ናቸው፡፡
ምንጭ PHYS.ORG
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትት “artificial intelligence, robotics and its impact on society” በሚል ለሁለት ቀናት የሚቆይ ተጠባቂ ውይይት ሊያደርግ ነው፡፡ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል አካል የሆነው ውይይቱ በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ዕድገት፣ አጠቃቀም እና የወደፊት እጣ ጉዳዩ አድርጎ ይካሄዳል፡፡ ከውይይቶች በተጨማሪም ክርክርም የሚከናወንበት ይሆናል፡፡
ዝግጅቱ የሚደረግበት ዕለት፤ ከነገ ጥር 13 ጀምሮ እስከ ጥር 14 ድረስ
የሚጀምርበት ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2፡30
ቦታ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ
Technology and innovation institute is holding a highly anticipated two days discussion regarding “artificial intelligence, robotics and its impact on society”. The discussion which is part of the institute’s Tech-Fest program will cover development, utilization, future prospect of AI and robotics Ethiopia. A debate session is also included.
Date January 21 and 22
Starting time 2:30 am LT
Place MINT hall
አየር መንገዶችና የአፍና የአፍንጫ ጭንብል የለበሱ ደንበኞች
**************************
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በአለማችን የተለያዩ ችግሮች ተስተውለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ወረርሽኙ ይዞት ከመጣው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በሽታውን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ እጥረቶች ናቸው፡፡
በቴክኖሎጂ እጥረት ረገድ ለወረርሽኙ ፍቱን ክትባት ለማግኘት የወሰደው ጊዜ እንዳለ ሆኖ ከዚህ በፊት በነበረን ጽሁፍ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ያደረጉ ሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንዳልዳበረና እንደ መፍትሔም ሰዎች የራሳቸውን የፊት ቅርጽ ተከትለው የተሰሩ ጭንብሎችን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ታስቦ እንደነበር ነግረናችኋል፡፡
የሰዎችን ማንነት መለየት በሚያስፈልግባቸው እንደ አየር መንገድ ባሉ ተቋማት ያሉ ካሜራዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የለበሱ ሰዎችን ማንነት እስከ 96 በመቶ ትክክለኝነት መለየት የሚያስችላቸው መሻሻል እንደተደረገላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህም መንገደኞች ካሜራዎች አካባቢ ጭንብላቸውን እንዲያወልቁ በማድረግ የወረርሽኙን መስፋፋት እያባባሰ የነበረውን ሁኔታ በእጅጉ እንደሚለውጠው ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
በሙከራ ወቅትም ቴክኖሎጂው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የለበሱ ሰዎችን ማንነት በ96 በመቶ መለየት እንደሚያስችል ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ውጤትም የሰራተኞቻቸውን መለያ ፎቶ ማረጋገጥ የሚፈልጉ ተቋማት ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የወረርሽኙን ስርጭት መቀነስ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡
የ S&T ባዮሜትርክ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አሩን ቬሙሪ ምንም እንኳን መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም አየር መንገዶች በተጓዦች ስለሚጨናነቁ የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞችንና የደንበኞችን ደህነት መጠበቅ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ TECHNOLOGY.ORG
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ዛሬ ተጀመረ
===
Artificial Intelligence, Robotics And Its Impact On Society በሚል ርዕስ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው የባለድርሻዎች ውይይት መድረክ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ በውይይቱ ከተለያዩ የሀገራችን የግልና መንግስታዊ የቴክኖሎጂ ተቋማት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ሲሆን እስከ ነገ ድረስም ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ብሎም ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ የሚኖረውን ሚና መሰረት በማድረግ ምክክሮች የሚደረጉበት ይሆናል፡፡
በዝግጅቱ ጅማሮ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለ ማርያም አዲስ እየመጡ ባሉ ቴክኖሎጂዎች ላይ በመሰራቱ የተለያዩ የሰው ልጆች ችግሮችን በከፍተኛ ደረጃ ማቃለል መቻሉን በማውሳት ይህ ውይይም ግዛቤን ለመፍጠር፣ተግዳሮትና ዕድሎችን አውቆ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና ፈጠራን ለማበረታታት ታስቦ የተሰናዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ አዲስ እየመጡ ባሉ ቴክኖሎጂዎች ዙርያ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎ ላይ ዕውቀትና ክህሎትን ለማዳበር አስፈላጊውን ፕላትፎርም ለመፍጠር እየሰራ ነው ያሉት ኢ/ር ተሸመ ቴክኖሎጂዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጉን በመገንዘብ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ያደርጋል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን እና ሞደርናይዜሽን ማዕከል አስተባባሪና የስታርታፕ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በረከት አባይነህ በበኩላቸው የኢንስቲትዩቱን ተቋማዊ መዋቅር፣ በስሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የተጣሉበትን ግዴታና ኃላፊነቶች አስመልክተው ለውይይቱ ታዳሚያን ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪነትም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይጫወተዋል ተብሎ ሚጠበቀውን ሚና፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴና ይከስታቸዋል ተብለው የሚሰጉ አሉታዊ ጎኖችን አስቃኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በመወከል በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምንነት ብሎም ቴክኖሎጂው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለበትን ደረጃና እምቅ አቅሙን አስመልክቶ አቶ ሳሙዔል ራመቶ ገለፃቸውን አቅርበዋል፡፡ ቴክኖሎጂውን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ከ250 በላይ የጥናት ስራዎች እንደተሰሩ የሚገልፁት አቶ ሳሙኤል አሁን ላይ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም እየሰሩ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተቋማትንም አሳይተዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል ቴክኖሎጂው በሀገራችን ማንዩፋክቸሪንግ፣ ጤና፣ ፋይናንስ እና ግብርናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዘርፎች ላይ ትልቅ እምርታን የማምጣት አቅም እንዳለው ምሳሌዎችን በመጥቀስ የተናገሩ ሲሆን በኢትዮጵያም እንደ መሰረተ ልማት ዕጦት፣ ዝግጁነት፣ አመለካከት ያሉ ተግዳሮቶችን እንዲሁም የነበሩና እየተፈጠሩ ያሉ መልካም ዕድሎችን አመላክተዋል፡፡
የውይይት መድረኩ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የሚሰናዳው የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል አንድ አካልና ቀዳሚው ዝግጅት ሲሆን በቀጣይም ኤግዚቢሽን እና አፍሪካን ሮቦቲክስ ያሉትንም የዝግጅቱ አካል ሆነው የሚካሄዱ ይሆናል፡፡
አዲሱ የድንች ዝርያ ለምስራቅ አፍሪካ አርሶ አደሮች ትልቅ ተስፋን ይዞ መቷል
ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የድንችን ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚቀንሱ መሰረታዊ ችግሮች መካከል ዘግይቶ የሚከሰት የድንች በሽታ ወይም በእንግሊዘኛ አጠራሩ (Late blight disease) አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ አርሶ አደሮች በዚህ ችግር የተነሳ ከፍተኛ መጠን ያለው የድንች ምርት በየጊዜው ከማጣታቸው ባለፈ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
አርሶ አደሮች ለዚህ ችግር እንደዋና መፍትሄ የሚጠቀሙት በሽታውን ሊቆጣጠር የሚችል የፀረ ፈንገስ ኬሚካል ጥቅም ላይ ማዋል ቢሆንም የኬሚካሉ ወጪ ከፍተኛ መሆን እና ደቂቅ አካላቱ ኬሚካሉን በጊዜ ሂደት እየተላመዱ መሄዳቸው ችግሩን በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የፀረ ፈንገስ ኬሚካሎች በሰዎች ጤና እና አካባቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ በመቻላቸውም ሌሎች የመፍትሄ አማራጮች የግድ ያስፈልጉ ነበር፡፡
ይህ የድንች ምርት በምስራቅ አፍሪካ ላሉ አብዛኞቹ ሀገራት እጅግ ወሳኛ ከሚባሉት የምርት አይነቶች በቀዳሚት የሚመደብ ከመሆኑም ባለፈ ዝቅተኛ የስብ ይዘት በማቅረብ በአካባቢው ለሚታየው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ወይም (malnutrition) መሰረታዊ መፍትሄ እንደሚሰጥም የሚታመን ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ከላይ የተጠቀሰው ችግር በቀጥታ አካባቢውን የሚጎዳ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ለአብነት በሃገራችን ኢትዮጵያ ይህን የድንች ምርት ከአንድ ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች እንደሚያመርቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ በጥቅሉ 70 በመቶ የሚሆነው የሚታረስ መሬትም ለድንች ምርት እጅግ ተስማሚ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በኡጋንዳ 300,000 የሚጠጉ አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች እንዲሁ የድንች ምርትን ለራሳቸው እና ለአከባቢ ገበያ በማቅረብ የሚተዳደሩ ሲሆን በሌሎች አከባቢዎችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይታያል፡፡
ይህ የምርት ምጣኔ እንደ ኡጋንዳ ባሉ የምራቅ አፍሪካ ሀገራት ከሃምሳ እስከ ስልሳ በመቶ በዚህ ሌት ብላይት (Late blight) በተባለ የድንች በሽታ የመጥፋት አደጋ የሚጋረጥበት ሲሆን በትንሹም 129 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በበሽታው የተነሳ ለጥፋት ይዳረጋል፡፡ ታዲያ ከሰሞኑ ይፋ የተደረገው የምርምር ውጤት ይህን በሽታ ሊቋቋም የሚችል አዲስ የድንች ዝርያን ያስተዋወቀ ምርምር ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በድንች ዙሪያ በሚሰራ ተቋም እና በኡጋንዳ በሚገኝ የግብርና ምርምር ማዕከል በትብብር የተሰራ ነው፡፡
ተመራማሪዎች በአካባቢው በብዛት በሚታወቀው ቪክቶሪያ (Victoria) ተብሎ በሚጠራው የድንች ዝርያ ላይ አዲስ የሞሎኪዩላር ቴክኒክ በመጠቀም በሽታውን መቋቋም የሚችል በራሂ (genes) ወደ ድንቹ ዝርያ ላይ ማስተላለፍ የቻሉ ሲሆን በዚህም በአካባቢው በስፋት ከሚታወቀው የድንች ዝርያ ጋር ብዙም ያልተለያያ ነገር ግን በሽታውን በሚገባ መቋቋም የሚችል አዲስ ዝርያ ማግኘት ችለዋል፡፡ 3R Victoria የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የድንች ዝርያ በሽታውን ለመቋቋም ያስቻለው ዋነኛ ምክንያት በጂን መዋቅሩ ላይ የተጨመሩለት 3 መሰረታዊ የበራሂ አይነቶች ሲሆኑ እነዚህ የማደቀል ሂደቶችም በኡጋንዳ በሚገኘው የግብርና ምርምር ማዕከል በህጋዊ ማዕቀፍ የተከናወኑ ናቸው፡፡
አሁን ላይ በአነስተኛ የእርሻ መሬት ላይ የሚያርሱ አብዛኞቹ አርሶ አደሮች ይህን የድንች በሽታ የሚቆጣጠር የፀረ ፈንገስ ኬሚካል በየሶስት ቀኑ የማድረግ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን፤ ለኬሚካሉ የሚያወጡት ወጪም ከድንች ምርቱ ከሚያገኙት ገቢ ከ20 እስከ 25% ይሸፍናል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ በሰዎችና በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እጅግ የበዛ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር አዲሱ የድንች ዝርያ ይዞት የመጣው ሁለንተናዊ በረከት ለአርሶ አደሩ ህይወት እና በጠቅላላው ለምስራቅ አፍሪካ የድንች ምርት ማደግ ትልቅ አስተዋፅዖ ከማበርከቱም ባለፈ ለአካባቢው ሀገራት የምግብ ደህንነት መረጋገጥም የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የአካባቢው ሀገራት በብሄራዊ ተቋሞቻቸው እና በዩኒቨርስቲዎቻቸው አማካኝነት አዲሱን የምርምር ውጤት የሚያገኙበት እና አብረው የሚሰሩበት ሂደት መጀመሩ ውጤቱን ይበልጥ ያሳምረዋል፡፡
ምንጭ፡ The Conversation
አስገራሚው የአለም ክብረ-ወሰን
*********************
እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ከረጅም ርቀት የተቆጠረች የአለማችን ብቸኛ ጎል ባለቤት በመሆን በአለም የክብረወሰን መዝገብ ውስጥ ስሙን አስፍሯል፡፡ ኒውፖር ካንትሪና ቼልተንሃም ከተማ ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በዚህ ጨዋታ የኒውፖርት ካንትሪው ግብ ጠባቂ ቶም ኪንግ ያስቆጠራት ግብ በአለማችን ከረጅም ርቀት የተቆጠረች በመሆን በክብር መዝገብ ውስጥ ሰፍራለች፡፡ ርቀቱም 96.01 ሜትር ተለክቷል፡፡ ያኛው ግብ ጠባቂ ምን የከበደ ነገር ገጥሞት ይሆን ሳያስብል አይቀርም፡፡
ቶም ኪንግ ኳሷን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል መስመር ላይ አስቀምጦ እንደለጋት የገለጸው የመረጃ ምንጫችን መረብ ላይ ካረፈች በኋላ ነበር የቼልተንሃሙ ግብ ጠባቂ ኳሷን ማየት የቻለው፡፡
ከዚህ በፊት ለስቶክ ሲቲ ይጫወት የነበረው ቤጎቪክ ሳውዛምተን ላይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2003 ያስቆጠራት ግብ በ91.9 ሜትር የአለምን ክብረ ወሰን ይዛ ነበር፡፡
ምንጭ Ginuss World Record
አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት የተገኘባቸው ሀገራት ቁጥር ከ50 በለጠ
====================
መነሻው ከሀገረ እንግሊዝ ያደረገውና ባለው ከፍተኛ የመስፋፋት ፍጥነት ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ያጫረው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ አይነት ቢ.1.1.7 እስከ ትናንት ዕለት ድረስ በ55 ሀገራት መገኘቱ ተነግሯል፡፡
የቫይረስ አይነቱ ከቀድሞዎቹ በበለጠ ገዳይ ይሁን አልያም ከአውሮፓና ሰሜን አሜሪካን ውጭ ባለው ዓለም ላይ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራጨ ስለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም በተላላፊነቱ ረገድ ግን በ50 በመቶ የላቀ አቅም እንዳለው አሁን እየወጡ ያሉ ጥናቶች እያሳዩ ነው፡፡ ይህ ታድያ የበለጠ ገዳይ ቢሆን እንኳን ከሚያመጣው በላይ ከፍ ያለ ችግርን እንደሚፈጥር ይነገራል፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ ውሰጥ ባለው መረጃ ተመስርተን ስናይ በአንድ ከተማ ውስጥ 10 ሺህ ሰዎች ቢያዙና እያንዳንዳቸው በአማካኝ ቫይረሱን ለ1.1 ሰዎች ቢያሰራጩ በአንድ ወር ውስጥ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ቁጥር 16 ሺህ ይሆናል፡፡ የሞት መጠኑንም እንዲሁ እንግሊዝ ውስጥ ባለው ላይ ተመስርተን 0.8 በመቶ ነው ብንል የመጀመሪያው የወረርሺኙ ማዕበል ላይ 128 ሰዎች ለህልፈት የሚዳረጉ ይሆናል፡፡ አዲሱ የቫይረሱ አይነት ከመሰራጨት ይልቅ በ50 በመቶ የበለጠ የመግደል አቅም ቢኖረው ኖሮ ከ16 ሺው 192 ሰዎች ይሞታሉ፡፡ ሆኖም በ50 በመቶው የጨመረው የመተላለፍ መጠኑ ከሆነና ገዳይነቱ ላይ ግን ምንም ዓይነት ለውጥ ካልታየ በአንድ ወር ውስጥ በቫይረሱ የሚያዘው ቁጥር 122 ሲሆን ከላይ በተቀመጠው የእንግሊዝ የሞት ምጣኔ መሰረት ስናሰላውም የሟቾቹ ቁጥር 976 ይደርሳል፡፡
አሁን ላይ ቢ.1.1.7 በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትና የአሜሪካን ግዛቶች ውስጥ ለውስጥ እየተላለፈ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ በተቀረው አለም ግን የቫይረስ አይነቱ የተገኘባቸው ሰዎች በዋናነት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ሀገራቱ አዲሱን የቫይረስ አይነት ከተጓዦች ላይ ብቻ የማግኘታቸው ሚምስጢር በውስጣቸው እየተሰራጨ ያለውን ቫይረስ የበራሒ ስንስሉን (genetic sequence) የመለየት ስራ ባለመስራታቸው ሊሆን ይችላል፤ ብዙ ሀገራት ይህን ተግባር ቢ.1.1.7 እስኪከሰት ድረስ ችላ ብለውት ቆይተዋል፡፡
በአንፃሩ የደቡብ አፍሪካው ቢ.1.351 ኮሮና ቫይረስ አይነት ያሳየው ስርጭት የተገደበ ነው፡፡ በአስራዎች የሚቆጠሩ ሀገራት የቫይረስ አይነቱን ማግኘታቸውን ቢያሳውቁም እስካሁን ግን ውስጥ ለውስጥ እየተላለፈ ያለው በቦትስዋና፣ ዛምቢያ እና እንግሊዝ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ምንጭ፡ New Scientist
ለምግብነት የሚውል ስጋን በቤተሙከራ ማበልጸግ
***********************
አዲስ የተገኘው ቀመር የቤተ ሙከራ ስጋ ተፈጥሯዊ ጣዕምና መልክ እንዲኖረው እያስቻለ መሆኑ ተነገረ፡፡ ተመራማሪዎቹ ተፈጥሯዊውን የእንስሳት ስጋ መተካት የሚችልና ጣዕሙ ከሌሎች አማራጮች ለተፈጥሯዊው የእንስሳት ስጋ የቀረበ እንደሆነ ስለ ግኝታቸው አስረድተዋል፡፡
በምርምሩ ሂደት በቤተ ሙከራ የበለጸጉ የጡንቻ ህዋሳትና የስብ ህዋሳት በአንድ ላይ ሆነው የተለያዩ ደረጃዎችን አልፈዋል፡፡ ይህ ስልትም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የአካል ንቅለ ተከላ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ህዋሳትን ለማበልጸግ ጥቅም ላይ ከዋለው መንገድ የተቀመረ ነው፡፡
አሁን ላይ በተለያየ መጠን ሰው ሰራሽ ስጋውን እያመረቱ እንደሆነ የተናገሩት ተመራማሪዎቹ ሰዎች ከጤናቸውና ከፍላጎታቸው ጋር የተስማማ የስብ መጠን ያለውን ስጋ መሸመት የሚችሉበት እድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡
ወደ ዚህ ስራ እንዴት እንደገቡ ሲናገሩ ተመራማሪዎቹ ምንም እንኳን በአለማችን ላይ ያለው የስጋ ፍላጎት እየጨመረ ቢሄድም አቅርቦቱ የመቀነስ ችግር ውስጥ በመግባቱ ነው ብለዋል፡፡ ከእንስሳት እርባታ ጋር የተያያዘውን የስጋ አቅርቦት ብቻ ተማምኖ መቀመጥ አይገባም ስለዚህ እንደዚህ ያሉ አማራጫቾች መኖር አለባቸው ሲሉ አክለዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily