የስድስተኛ ትውልድ (6G) ገመድ አልባ አገልግሎት ማበልጸጊያ ማእከል ተከፈተ
************************************
የእንግሊዙ ሰሬይ ዩኒቨርሲቲ የከፈተው ማዕከል ፈጣን ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዝ የስድስተኛ ትውልድ የገመድ አልባ አገልግሎትን ለማበልጸግ የታለመ ነው፡፡ ለምሳሌ በየትኛውም የአለም ክፍል የሚያስፈልግ የህይወት አድን ስራን ሀኪሞች ሮቦቶችን እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ምንም እንኳን በእንግሊዝ የአምስተኛ ትውልድ (5G) የገመድ አልባ አገልግሎት ጥቅም ላይ ለመዋል ጥቂት አመታት የሚያስፈልጉት ቢሆንም በስድስተኛ ትውልድ ላይ የተለያዩ ጥናቶች እየተተገበሩ እንደሆነ የዘገበው sky news ነው፡፡ የ4G አገልግሎት የተለያዩ የምስልና ድምጽ ቅንብሮችን (ቪዲዮ) እና ሙዚቃ ለመከታተል ያስቻለ ሲሆን የ5G አገልግሎት ደግሞ ካለው የተሸለ ከፍያለ አግልግሎትን በግዙፋን ኢንዱስትሪዎች ሳይቀር ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዩኒቭርሲቲው እየተዘጋጀበት ያለው የስድስተኛ ትውልድ ገመድ አልባው አገልግሎት ፈጣን የሆነ የቀጥታ ግንኙነት ወይም ተግባቦት እንዲኖር ያስችላል፡፡ ለዘ ታይምስ መጽሔት ሀሳባቸውን ያጋሩት ፕሮፌሰር አለን ዉድዋርድ አዲሱ ትውልግ ከመድሀኒት ጋር የተያያዘው ስራ ዋናው ተጠባቂ ነገር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ሀኪሞች በአለም ከአንዱ ጥግ ሆነው በሌላኛው የአለም ጥግ ያለን አንድ ታካሚ በሮቦት በመታገዝ ማከም ያስችላል ብለው ገልጸውታል፡፡ አክለውም ምንም እንኳን ምርምሩ አሁን በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ቢሆንም ተስፋ የተታለባቸው ግኝቶች እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡
የ5G አገልግሎት ከፍተኛ የሆነ ኤሌክትሮ መግነጢስ በመጠቀም ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን ማስተላለፍ የሚያስችል ሲሆን ይህ ግን ሁልጊዜ ላይሰራ እንደሚችል ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡ የስድስተኛ ትውልድ ማበልጸጊያ ማዕከሉ ዳይሬክተር የሆኑት ፐሮፌሰር ራሂም ታፋዞሊ በዚህ ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የተለየ አካሄድ መከተል አለማቀፍ ችግሮችን ለመፍታት ያስችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው "ambient information" እና "ubiquitous coverage" የተባሉ የጥናት ጭብጦችን እንደሚከተል አሳውቋል፡፡
የመጀመሪያው ሀረግ አካላዊውን እና ምናባዊውን አለም የሚገልጽ ጥምር ሲሆን ከፍ ባለ የዲጂታል አገልግሎት ደረጃ የሰዎችን ስሜት ከሩቅ በሌሎች መሳሪያዎች ላይ ለማጋባት የታለመ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በቦታ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት ገደብ እንዳኖር ለማስቻል የታለመ እሳቤ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ስራውን ያለውን ገመድ አልባ አገልግሎት ለማሻሻልና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም በማለም እየሰራ እንደሆነና አገልግሎቱን በየትኛውም የአለማችን ክፍል ለማቅረብ እንዳሰበ ተናግሯል፡፡
ይህንን አገልግሎት አሁን ላይ ማሰብ ያስፈለገበትን ምክንያት ዩኒቨርሲቲው ሲገልጽ የአምስተኛ ትውልድ አገልግሎትን እየተቆጣጠሩ ያሉ ሀገራትና ድርጅቶች ከ10 እና 15 አመታት በፊት ማሰብ እንደጀመሩ ስለሚታወቅና በዚህ ዘርፍ እንግሊዝ ቀዳሚ እንድትሆን በማሰብ እንደሆነ መረጃ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ sky news

እውነት ግን ግመሎች በሻኛቸው ውሃ ያጠራቅማሉ?
=========================
ግመሎች በዚያ አስከፊ በረሃ ውስጥ ያለ ብዙ ችግር ለመኖር ውሃን በሻኛቸው ያጠራቅማሉ የሚለው ሀሳብ በብዙ ሰዎች ውስጥ የሰረፀ ነው፡፡ ዕውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ድንቅ እንስሳት ያገኙትን ውሃ በቁጠባ የመጠቀምያ ብዙ መንገዶች ቢኖሯቸውም ሻኛቸው ግን ከነዚህ አንዱ አይደለም፡፡
ታድያ ሻኛው ምን ይሰራላቸዋል?
ለዚህ መልሱ ስብ ለማከማቸት ነው፡፡ ግመሎች ምግብ በሚያገኙበት ሰዓት በቂ ካሎሪን በመመገብ ሻኛቸውን ያደላድላሉ፤ በዚህም ምግብ ችግር በሚሆንባቸው ጊዜያት ብዙም ሳይቸገሩ ለብዙ ጊዜ መቆየት ይችላሉ፡፡ ሻኛውን ጠብሰቅ አድርጎ የሞላ አንድ ግመል ከ4 እስከ 5 ወራት ድረስ ያለ ምግብ የመቆየት አቅም አለው፡፡ ታድያ በነዚህ ምግብ አልባ ወራት ውስጥ የግመሉ ሻኛ ልክ በትንሹ እንደተከፈተ ፊኛ ቀስ በቀስ መሟሸሽ ይጀምራል፤ ፊኛውን መልሰን ስንነፋው እንደሚወጠር ሁሉ ሻኛውም ምግብ ሲያገኝ እንደቀድሞው መሙላት መደላደል ይጀምራል፡፡
ሌላው ምናልባት ለነዚህ እንስሳት ቅርበት ለሌለን ሰዎች አዲስ የሚሆንብን እውነታ ሻኛው ሲወለዱ አብሯቸው የማይወለድ መሆኑ ነው፡፡ እንደውም ጡት በሚጠቡበት ዕድሜያቸውም ሆነ ከዚያ ወድያ ባሉት ጥቂት ወራት ሁሉ ጀርባቸው ባዶ ሜዳ ሆኖ ይቆያል፡፡ ሻኛው ማደግ የሚጀምረው በተወለዱ በአስረኛው ወር ጀምሮ ነው፡፡
ምድራችን ሁለት አይነት ግመሎችን ታኖራለች፡፡ የመጀመሪያዎቹ የአረብ ግመል (Camelus dromedarius) ሲሆኑ በሀገራችን ጭምር ተስፋፍተው ያሉ ባለአንድ ሻኛ ግመሎች ናቸው፡፡ ሁለተኛው የግመል አይነት ግን ባክትሪያን ግመል (Camelus bactrianus) ተብለው የሚታወቁት ሲሆኑ በምዕራባዊ ቻይና እና ማዕከላዊው የእሲያ ክፍል ያሉና ባላቸው ሁለት ሻኛ ተለይተው የሚታወቁ ግመሎች ናቸው፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፤ የሻኛው መብዛት ከባለ አንድ ሻኛ ግመሎች ለበለጠ ጊዜ ምግብ ሳይመገቡ ሊያቆያቸው አይችልም፡፡
ብዙዎች እንስሳት ስብ የሚያጠራቅሙት በሆዳቸው በኩል ነው፡፡ ይህ ግን ለግመሎች አይሰራም፤ ስቡን የሚያጠራቅሙት ጀርባቸው ላይ ነውና፡፡ ለዚህ ከሚሰጡት ማብራርያዎች ውስጥ አንደኛው ግመሎች በዚያ በረሃ እረፍት የሚያደርጉት በሆዳቸው በመተኛት ስለሆነ ይህ ስብን በሆዳቸው በኩል ለማከማቸት ከባድ ማድረጉ ነው፡፡ ሁለተኛው ማብራርያ ደግሞ ግመሎቹ በበረሃ ውስጥ ስለሚኖሩ ወደጎን አለመስፋታቸው እና ቁመተ ለግላጋነታቸው ስቡ ከጎን ይልቅ ወደላይ ከመቀመጡ ጋራ ተዳምሮ ለፀሐይ እና ከፍተኛ ሙቀት ያላቸውን ተጋላጭነት ይቀንሰዋል የሚለው ነው፡፡
እስካሁን እንደተብራራው ግመሎች ሻኛቸውን ለውሃ ሳይሆን ለምግብ ማከማቻነት ይጠቀሙታል፡፡ በዚህም ምክንያት አስከፊውን በረሃ ይቋቋሙ ዘንድ ሌላ የውሃ እጥረትን መቋቋምያ መንገድ ተበጅቶላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ጊዜ ብቻ ግመሎቹ ሰላሳ ጋሎን አልያም 114 ሊትር ውሃ የሚጠጡ ሲሆን ይህን ውሃ ለማስቀመጥ ሲሉ ሰገራቸውን የሚያስወግዱ፤ ኩላሊታቸውም መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከውሃ ውስጥ በማስወገድ በተቻለው መጠን ውሃ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ ሌላም ብዙ ውሃን በአስገሚ አኳሀን የመጠቀሚያ መንገድ አላቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ በአፍንጫቸው ከሚስቡት አየር ውስጥ እርጥበትን ይሰበስባሉ፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ጠጣር (crystal) ኤሌክትሮን ከ86 ዓመታት ሙከራ በኋላ
*******************************************
በ1934 የነበረው የፊዚክስ ሊቅ ዩግኔ ዊግነር ለየት ያለ የክሪስታል እሳቤን በሀሳብ ደረጃን አስቀምጦ ነበር፡፡ አንድ ኔጌቲቭ ቻርጅ የተሞላ ኤሌክትሮን እፍግታው በተወሰነ ደረጃ ከቀነሰ ንኡስ ቅንታቶቹ (subatomic particles) በመደራረብ ክሪስታል ኤሌክትሮን ይፈጥራሉ ይህ ሀሳብ ነው የዊግነር ክሪስታል በመባል የሚታዎቀው፡፡
የኤሌክትሮኖች እረፍት አልባ ባህሪ በአንድ ቦታ ተወስነውና ረግተው እንዲቀመጡ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ነገርግን የፊዚክስ ተመራማሪዎች ቡድን የማይቻል የሚመስለውን ታንግስተን በሚባለው ንጥረ ነገር ማሳካት ችሏል፡፡
እንደ ዳይመንድና ኳርትዝ ያሉ ክሪስታሎች በታወቀ ልኬት ተስተካክለው በተቀመጡ ባለሶስት ጎን እይታ ተደራራቢና የተያያዙ ቅንጣቶች የተሰሩ ናቸው፡፡ እንደ ዊግነር ሀሳብ ኤሌክትሮኖች በተመሳሳይ አኳኋን በመሰደር ጠታር ክሪስታል መፍጠር ይቻላል ነገርግን ይህ የሚሆነው ኤሌክተሮኖቹ የረጉ ወይም የማይንቀሳቀሱ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
የኤሌክትሮኖች እፍግታ በበቂ ሁኔታ ከቀነሰ የእንቅስቃሴ ሀይላቸውን በመቀነስ በአንድ አካባቢ ረግተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ኤሌክትሮኖች በጣም ጥቃቅን ነገሮች ናቸው ምንም እንኳን እኛ የምናደርገው ነገር ባይኖርም እነሱ ግን ያለእረፍት እንቅስቃሴ ላያ ይሆናሉ፡፡
ኤሌክትሮኖች ካላቸው የእንቅስቃሴ ባህሪ የተነሳ ጠጣርነታቸው ሁሌም ለመቅለጥ የተጋለጠ ነው፡፡
በ2018 የ MIT ተመራማሪዎች በዊግነር ክሪስታል እሳቤ ኢንሱሌተር ለመስራት ያልተሳካ ሙከራ በግራፌን አድርገው ነበር፡፡ የአሁኑ ምርምር ቡድን tungsten disulfide (WS2) እና tungsten diselenide (WSe2) የሚባሉ በልዩ ሁኔታ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የበለጸጉ ሁለት ንጥረ ነገሮች ላይ ሙከራውን አድርጓል፡፡
ምንጭ ScienceAlert

እንቅልፍ እና እንስሳት
*******************
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሰረት ሁሉም እንስሳት እረፍት ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ በእንቅልፍ ባህሪያቸው እና በቀን ውስጥ በሚተኙት ሰዓት መጠን የተለያየ ባህሪ ያላቸው የእንስሳት ዝርያዎች አሉ፡፡ አንዳንድ እንስሳቶች እጅግ ለረዘመ ሰዓት በእንቅልፍ የሚወድቁ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ከነአካቴው እንቅልፍ የማይተኙም አሉ፡፡
እንቅልፍ ከድካም ለማረፍ ካለው ጥቅም ባለፈ ያለው መሰረታዊ ምክንያት በሳይንስ እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡ ባለፈው አመት በተፈጥሮ ጥናት በተሰራ ምርምር ሰዎችና እንስሳት እንቅልፍ የሚተኙት የጭንቅላት DNAን እንደገና ለማደስ ይሆናል የሚል መላምት የተመታ ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒው በ2017 በተሰራ ተመሳሳይ ጥናት jellyfish እየተባለ የሚጠራው ጭንቅላትና ማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ የሌለው የባህር ውስጥ እንስሳ እንቅልፍ እንደሚተኛ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ጥናቶች የተሰሩት በአእዋፋትና በአጥቢ እንስሳቶች ላይ ቢሆንም አብዛኞቹ እንስሳት እረፍት ሲሹ ይታያሉ፡፡
የአለማችን ረጅሙ እንስሳ ቀጭኔ ከአጥቢ እንስሳቶች መካከል እንቅልፍ አልባ ወይም በጣም ለጥቂት ጊዜ የሚተኛ እንስሳ ነው፡፡ ይህ እንስሳ እስከ 3000 ፓውንድ የሚደርስ ግዝፈት ሲኖረው በአብዛኛው በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ያክል ብቻ ያሸልባል፡፡ እንስሳው የ30 ደቂቃ ጥልቅ እንቅልፍ ለመተኛት 4 ሰዓት ከግማሽ ያክል አይኑን ይከድናል፡፡
ሌላው እንደቀጭኔ ሀሉ በቁሙ የሚተኛው አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያለው እንስሳ ዝሆን ነው፡፡ በ2017 በወጣ አንድ ዘገባ ዝሆኖች በቀን ለሁለት ሰዓታት ያክል ብቻ ይተኛሉ፡፡ ሁለቱ እንስሳት በግዙፍነታቸው ምክንያት የሚተኙት እንደቆሙ ወይም ክብደታቸውን የሚችል ትልቅ ዛፍ ወይም ሌላ ነገር ላይ ተደግፈው ብቻ ነው፡፡
ከነዚህ እንሰሳት በተቃራኒው ወንድ አንበሳ በቀን ውስጥ ለ20 ሰዓታት ያክል ሲተኛ ሴቷ ደግሞ እስከ 15 ሰዓታት ድረስ ትተኛለች፡፡ በአብዛኛው ስጋ በል የሆኑ እንስሳት ከሳርና ቅጠላቅጠል በል እንሰሳት በተለየ ለረጅም ሰዓታት የመተኛት ልምድ አላቸው፡፡ በአውስትራሊያ ብቻ የሚገኘው ኮዋላ እየተባለ የሚጠራው የድብ ዝርያ ከ18 እስከ 22 ሰዓታት ያክል በመተኛት የአለማችን እንቅልፋሙ እንስሳ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እንስሳ በብዛት የሚመገበው የባህርዛፍ ቅጠል ነው፡፡
በጣም አስደናቂ የሚባለው ደግሞ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ሁለ በል የሆኑት ጥቁርና ቡናማ የሆኑት ድቦች በተከታታይ ለስምንት ወራት ያክል ይተኛሉ፡፡
ከደረቅ መሬት ወጥተን ወደ ውሀ አካላት ስንሄድ ያልተለመደ የአተኛኝ ልምድ ያላቸው አሳዎችን እናገኛለን፡፡ አንዳንድ አሳዎች በሚተኙበት ጊዜ አይናቸውን አይከድኑም፤ ምን እንኩዋን ይሄ የአይን ሽፋል የሌላችው በመሆኑ ምክንያት ቢሆንም፡፡ እንዲሁም በከፊል ንቃት በከፊል እንቅልፍ ውስጥ ሆነው የሚተኙ የአሳ ዝርያዎችም አሉ፡፡
ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ ከነጭራሹ የማተኛው የእንቁራሪት ዝርያ ነው፡፡ ይህም bullfrog እየተባለ የሚጠራው ዝርያ ነው፡፡ የመረጃ ምንጫችን የሆነው Discover Magazine መረጃውን ሲያጠናቅቅ በሰዎችና በእንስሳት እንቅልፍ ዙሪያ ገና ያልተጠኑ ብዙ ምስጢሮች እንዳሉ በመናገር ነው፡፡

በህይወት አድን ግስጋሴ ላይ የሚገኙት የኮቪድ-19 ክትባቶች፤ ተስፋ እና ስጋት
===============
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን አጥቅቶ 1.3 ሚሊዮን የተሻገሩትን ህይወት የነጠቀው ኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመግታት ያለሙ ክትባቶችን የመስራቱ ሩጫ የወረርሺኙ መነሳት ከተሰማባቸው ጥቂት ሳምንታት አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በፍጥነት እየተከናወነ ነው፡፡ ከነዚህ መካከልም የሰው ልጆች ላይ የተሞከሩ እና በተጓዳኝ ሙከራ ላይ ያሉት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት 54 ክትባቶች የክሊኒካል ሙከራ መከወን ላይ ደርሰዋል፤ 87ቱ ደግሞ በእንሳት ላይ ሙከራቸው እየተከናወነ ነው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካን ፋይዘር የተሰኘው ክትባት እያደረገ የነበረው የሰዎች ላይ ሙከራም 90 በመቶ ስኬታማ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ ከ43 ሺህ በላይ ሰዎችን ተሳታፊ አድርጎ የነበረው ጥናቱ ገና በባለሙያዎች ሳይገመገም ይፋ የተደረገ ቢሆነም ለብዙ ሰዎች ተስፋ የሰጠ ውጤት ነበር፡፡
አሁን ደግሞ በኢቦላ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በስድስት ሺህ የእንግሊዝ ነዋሪዎች ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል፡፡ መቀመጫውን ሀገረ ቤልጅየም ባደረገው ጃንሰን ዓለም አቀፍ የመድሃኒት አምራች አማካኝነት የተሰራው ክትባቱ ለንደን፣ ማንቼስተር፣ ሳውዛምፕተን እና ሌስተርን ጨምሮ በ17 የተለያዩ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ ሙከራውን የሚያከናውን ሲሆን በቀጣይም 24 ሺህ ተጨማሪ በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊዎችን በዓለም ዙርያ አካቶ ሙከራውን እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡ ሙከራው በእንግሊዝ ብቻ የሚደረግ ሦስተኛው ወሳኝ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ያደርገዋል፡፡ ይህ ክትባት አቅሙ እንዲደክም የተደረገ አዴኖቫይረስ የተሰኘ የጉንፋን ቫይረስን የሚጠቀም ሲሆን ህዋሶችን በዚህ በማጥቃት የበሽታ መከላከል ስርዓታችንን የሚቀሰቅስ ነው፡፡ ታድያ ተመሳሳይ ክትባቱ ከዚህ ቀደም ለኢቦላ ወረርሺኝ ታስቦ ተስርቶ የነበረና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም ቫይረሱን እንዲመክት ከዓመት በፊት ጥቅም ላይ የዋለ ነበር፡፡
ፋይዘር የተሰኘውን ክትባት የሰራው ባዮኤንቴክ ኩባንያ መስራቹ ፕ/ር ኡሁር ሳሂን በተቋማቸው በተሰራው ክትባት ዙርያ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሰፊ መረጃዎችን የሚሰጡ ትንተናዎች ይፋ ይሆናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀው ነገሮች በጥሩ ሁኔታ የሚሄዱ ከሆነም ክትቶቹ ባለንበት የፈረንጆች ዓመት መባቻ ላይ ለተጠቃሚዎች መድረስ እንደሚጀምርና እስከሚያዝያ ድረስም 300 ሚሊዮን የክትባት ፍሬዎች እንደሚመረቱ አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ መጪዎቹ የኮቪድ 19 ክትባቶች በጊዜ ከመድረስ ጋራ ብቻ አይደለም ግብግባቸው፤ የህብረተሰብን እምነት ከማግኘት ጋራ ጭምር እንጂ፡፡ በቅርብ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሜሪካን ከሚኖረው ህዝብ መካከል የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ፍቃደኛ ሆኖ የተገኘው 51 በመቶው ብቻ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 21 በመቶው ብቻ ለመውሰድ እርግጠኛ ሲሆኑ የተቀረው 30 በመቶ ግን እርግጠኛ ያልሆነ ፍቃደኝነትን ያሳየ ነው፡፡ ለነዚህ ክትባቶቹ ላይ ላሉት አሉታዊ አመለካከለቶች በዋና ምክንያትነት የተቀመጡት ክትባቶቹን እውን የማድረግ ሂደቶችን ከመጠራጠር እና ከጎንዮሽ ጉዳት ከመስጋት ጋራ የተቆራኙት ናቸው፡፡ ለምሳሌ 78 በመቶው የሀገሪቱ ነዋሪ ሂደቶቹ ክትባቶቹ መድረስ ከሚገባቸው ጊዜ በላይ ባልተገባ ፍጥነት እየሄዱ እንዳይሆን የሚል ጥርጣሬ ሲያድርባቸው ፈፅሞ ክትባቶቹን ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆኑት ውስጥ ደግሞ 76 በመቶው ዋናው ስጋታቸው ክትባቶቹ ሊያደርሱት ከሚችሉት የጎንዮሽ ጉዳት ጋራ የተያየዘ ነው፡፡
ይህ ግን በአሜሪካን ብቻ የሚታይ ችግር አይደለም፤ ለምሳሌ በሰኔ ወር 19 ሀገራትን አካሎ በተሰራ ጥናት 71.5 በመቶው ሰው ክትባቶቹን ለመውሰድ ያለውን ፈቃደኝነት አሳይቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ቻይና 90 በመቶው ህዝቧ ክትባት ለመውሰድ ፍቃዱን ሲያሳይ በአንፃሩ ይህ ቁጥር በሩስያውያን ዘንድ ወደ 55 በመቶ ይወርዳል፡፡ ይህ ግን ቀድሞ የነበረው ፈቃደኝነት ወይም እንቢተኝነት አሁንም በቦታው ነው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያሳለፍነው ግንቦት ላይ በአሜሪካን የተሰራው ጥናት 72 በመቶ ያህሉ የሀገሩ ህዝብ ለክትባቶቹ ፍቃደኛ መሆኑን ያሳዩ ነበር፡፡
እንደ ፕ/ር ሳሂን ከሆነ የፋይዘር ክትባት ያሳው ጎንዮሽ ጉዳት ክትባቱ በተወጋበት አካል አካባቢ ላይ በመጣ መጠነኛ ህመም ስሜት ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ይህ በራሱ ጥሩ ዜና ይመስላል፤ የፋይዘር እና ሌሎች አዳዲሶቹ ሙከራዎች ስኬት ህዝቡ በክትባቶቹ ላይ ያለውን አመለካከት እንደሚያጠሩና ፍቃደኝነትንም እንደሚጨምሩ እየተጠቀሰ ይገኛልና፡፡
ምንጭ፡ Science News፣ The Guardian፣ BBC እና ሌሎችም

ዘመናዊው የእጅ ጓንት
*******************
በኮርኔል ዩኒቭርሲቲ የሚገኝ አንድ የምርምር ቡድን ተለጣጭ የሆነ እና VR (virtual reality) እንድንነካና ስሜቱን እንድንረዳ የሚያስችል የእጅ ጓንትን ሰርቷል፡፡ ይህ ዘመናዊ የእጅ ጓንት በጣቶቻችን የምናደርጋቸውን ተግባራት መረዳት የሚችል ሲሆን ከቨርቹዋል አለም ጋር ያለንን ግንኙነት በትልቁ ይለውጠዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡
በጓንት ስራው ላይ የተሳተፈው የዩኒቨርሲቲው ኢንጅነሪንግ ፐሮፌሰር የሆነው ሮብ ሺፓርድ በቨርቹዋል ስርዓት ውስጥ የሁነቶች እንቅስቃሴ ከፍተኛ በመሆኑ ንክኪ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በ Science today መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የጓንቱ የመጀመሪያ ስሪት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚችል እንደሚችል ተገልጧል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአንድን ቁስ የጉዳት መጠን፣ ግፊትና እጥፋትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ይህ ሴንሰር ያለው ጓንት የተሰራው በሽቦው የብርሀን መስመር እያንዳንዱ እጣት ያለውን እንቅስቃሴ መግለጽ በሚችሉ ቀጫጭን ሽቦዎች (fiber optic) ነው፡፡ ጓንቱን ተጠቅመን አንድን ስራ በምንሰራበት ወቅት በጓንቱ ላይ የተገጠመው ኮምፒውተር ስለእጃችን እንቅስቃሴ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይሰጠናል፡፡
ጓንቱ መሰረታዊ የሚባሉ እና ውድ ያልሆኑ እንደ ብሉቱዝ፣ ባትሪ (lithium ion) እና የተለያዩ LEDዎች ተገጥመውለታል፡፡ ተመራማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ግኝቱ ለአካል ብቃትና ለስፖርት (physical therapy) የጤና ክትትሎች ሊውል የሚችልበትን መንገድ እያጠኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ግኝቱ ትልቅ ተስፋ ከሰጣቸው ነገሮች ዋነኛው የቨርቹዋል እንቅስቃሴ ተጠቃሚዎች አሳማኝ የሆነ ምልከታ እንዲኖራቸው ማድረጉ ነው፡፡
እንደሚታወቀው Virtual reality የሚባለው ቴክኖሎጂ ከገሀዱ እውነታ ጋር የመመሳሰል ችግር አለበት፡፡ ይህ ተለጣጭ የሆነው የቆዳችንን ስሜት የሚረዳ (skin sensor)የእጅ ጓንት ይህንን ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ www.engadget.com

ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው፤ ከቴክኢን ቤተሰብ
====================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኛች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው” በሚል የተዘጋጀውን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊትን የማክበር ዝግጅት በተቋሙ አከናውነዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ከተቋሙ አመራር እና አብዛሀው ሰራተኞች በተጨማሪ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብር በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡

አፍሪካ እና ቴክኖሎጂ
በቁስ በፅሁፍ የተገኙ እንዲሁም ቋንቋን ባህልን ጊዜን መሰርት አድርገው የተካሄዱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አፍሪካና አፍሪካውያን ከአውሮፓ ስልጣኔ በፊት የሳይንስ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የነበሩ መሆናቸውን ያመለክታሉ፡፡
በርካታ ተመራማሪዎች አፍሪካውያን ለአለም ያበረከቱት አስተዋጽዖ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተከናወኑት ፈጠራዎች የማይተናነሱ እና ይልቁንም ከጥቁር ህዝብ የፈለቁት የጊዜ እና የወቅት መፈራረቅ ግኝት፣ የቀን አቆጣጠር፣ የሂሳብ ቀመር ግኝት፣ የእደ ጥብብ ብቃት፣ የግብርና እና የስነ ህንፃ ጥብብ ኋላ ለተፈጠሩት የሰው ልጅ የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ መሰርት ጥሏል፡፡
ቴክኖሎጂ እና የሳይንስ እውቀት የሁሉም የሰው ልጆች ንብረት እንደሆነ ሁሉ ለዚህ እውቀት እውን መሆን ሁሉም ባህሎች በአንድም ይሁን በሌላም የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዳደረጉ መዘንጋት ባይቻልም ቀደምት አፍሪካውያን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ በሚገባ መዘከር እና የወደፊቱንም አልሞ መስራት እጅግ ብልህነት ነው፡፡
ተከታዩን ዘጋባ ይከታተሉ
https://youtu.be/Sm56gb1KIsc

YouTube
አፍሪካና ቴክኖሎጂ ምንና ምን ናቸዉ?አህጉራችን አፍሪካ ለበርካታ ቴክኖሎጂዎች ቀደምት እንደሆነች ያዉቃሉ?Africa and technology
#አፍሪካና#ቴክኖሎጂ# ምንና ምን ናቸዉ?አህጉራችን አፍሪካ ለበርካታ ቴክኖሎጂዎች ቀደምት እንደሆነች ያዉቃሉ?Africa and technology
ማሊግብፅኢትዮጵያቴክኖሎጂዎችን ለመጀመር ፈር ቀዳጅ የነበሩ ሀገራት ዉስጥ ተጠቃሽ ናቸዉ::

94.5% ውጤታማ የሆነ የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት
****************************
በሶስት ዙሮች 43,000 ታማሚዎች በተሳተፉበት የሙከራ ስራ 94.5 በመቶ ውጤታማ የሆነ ክትባት መገኘቱን Biopharmaceutical Moderna በመባል የሚታወቀው ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡ መረጃው ያለፈው እሁድ የመረጃ ደህንነት በሆነ ገለልተኛ አካል ተረጋግጦ የወጣ ነው፡፡
በተገኘው ክትባት በጣም ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በታህሳስ መገባደጃ አካባቢ ስርጭትና ክትባት እንደሚጀመር ተገልጧል፡፡ በአለማችን ሁሉም አካባቢዎች እስከ ሚያዚያ ድረስ ክትባቱ ተደራሽ እንደሚሆን በተጨማሪ የተገለጸ ሲሆን ይህ መረጃ በትክክል የሚተገበር ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ችግር እንደሚፈታ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በፊት Pfizer እና German በተባሉ የመድሀኒት አምራች ድርጅቶች ውጤታማነቱ 90 በመቶ የሆነ ክትባት መገኘቱ እንደተገለጸ የማይዘነጋ ነው፡፡ ይህ Moderna በተባለው ድርጅት የተገኘው ክትባት በፍሪጅ ውስጥ ለ30 ቀናት ያክል መቆየት የሚችል በመሆኑ ስርጭቱን በጣም ቀላል ያደርገዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
ምንጭ Futurism