አዲስ የሞባይል ቀፎ ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ሲገዙ በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ለማወቅ :-
• ሲም ካርድ አስገብተው ለሙከራ መጠቀም
• *868# ደውለው 3ኛ ቁጥር ላይ የሚገኘውን የመለያ ቁጥር ሁኔታ ማወቂያ (Check Status) የሚለውን መምረጥ ፤ በመቀጠል by IMEI የሚለውን መርጠው፤ ሊገዙ ያሰቡትን የቀፎ መለያ ቁጥር /IMEI/ አስገብተው ቀፎው በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
- የሚገዙትን ቀፎ የIMEI ቁጥር ለማወቅ፡
• *#06# ይደውሉ
• ከቀፎው ማሸጊያ ካርቶን ላይ ይመልከቱ፡፡
ግዢ ከፈፀሙ በኋላ ቀፎዎ በኔትዎርኩ ላይ የማይሠራ ከሆነስ?
• ከግዢ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በህግ አግባብ ለመፍታት እንዲችሉ ግዢ ሲፈፅሙ የቀፎውን መለያ ቁጥር የያዘ ህጋዊ ደረሰኝ መቀበልዎን አይርሱ፡፡
ስርቆት ወይም መጥፋት ቢያጋጥምዎ?
• በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች በተለይ የሞባይል ስልክ በስርቆትም ሆነ በሌላ ምክንያት ከደንበኞች እጅ ሲጠፋ 994 ላይ ደውለው በማዘጋት ቀፎው በሌላ አካል የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ጠቃሚ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን እንዲሁም የጤና ምክሮችን በየቀኑ እናደርሳችኋለን። ወዳጅ ጓደጎቻችሁንም ወደዚህ ቻናል ይጋብዙ።
የሳንባ ካንሰር ዘጠኝ ዋና ዋና ምልክቶች
1. ደረቅ ሳል
ለሶስት ሳምንት እና ከዚያ በላይ የዘለቀ እና ደረቅ ሳል የሳንባ ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል። በሳል ወቅት ከደረት ጀምሮ እስከ ወገብ የሚዘልቅ የህመም ስሜት ሲሰማም ለዚሁ በሽታ መጋለጥን ሊያመላክት እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
2. ደም የቀላቀለ ሳል
በተለይም አጫሾች ደም የቀላቀለ ሳል ካላቸው ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን ሊያሳይ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎችን ማነጋገር ተገቢ ነው። ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከባድ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር እና ትኩሳትም የህመሙ ምልክቶች ናቸው።
3. የድምጽ መቀየር
የአየር መተላለፊያ ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የድምጽ መቆራረጥና መቀየር ያስከትላል። ለአስም እና ለተለያዩ አለርጂዎች መጋለጥ ብዙ ጊዜ ለድምጽ መቀያየር በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፤ ይሁን እንጂ የሳንባ ካንሰር ምልክትም ሊሆኑ እንደሚችሉ ይነገራል። የድምጽ ለውጡ ለተከታታይ ቀናት ከቀጠለ እና ጉንፋንም ይሁን አስም ከሌለበዎት ሀኪም ማማከር ይገባል።
4. የትንፋሽ መቆራረጥ
ከ10 የሳንባ ካንሰር ተጠቂዎች ዘጠኙ የትንፋሽ መቆራረጥ ችግር ይስተዋልባቸዋል። የደም ቧንቧዎች መዘጋት፣ የደም ማነስ፣ የመተንፈሻ አካላት ማመርቀዝ እና ከፍተኛ ቦታዎች ላይ መኖር የአተነፋፈስ ስርዓትን ሊያዛባ ይችላል። ነገር ግን ከመደበኛ ኑሯችን በተለየ አየር የመሳብ ችግር ካጋጠመን እና ከዚህ ቀደም በቀላሉ የምንከውናቸው ስራዎች እጅግ እየከበዱን ከመጡና መተንፈስ ካቃተን ለሳንባ ካንሰር መጋለጣችን ያሳያል።
5. የደረት እና አጥንት ህመም
በሳል ወቅት የሚበረታ የደረት ህመም፣ ሳቅ እና ጥልቅ አተነፋፈስ በአብዛኛው የሳንባ ካንሰር የመጀመሪያ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ ምልክቶች የሚስተዋሉት ካንሰር በሳንባ ውስጣዊ ግድግዳ ላይ ሲስፋፋ ነው። ካንሰሩ ሲጠናከርም ወደ ተለያዩ አጥንቶች የሚዘልቅ ሲሆን፥ በእጅ፣ አፍንጫ፣ ወገብ፣ ጀርባ እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የህመም ስሜትን ይፈጥራል። ስለሆነም ለአራት ሳምንት እና ከዚያ በላይ የቆየ የደረት እና አጥንት ህመም የሳንባ ካንሰር ምልክት ሊሆን ስለሚችል ባለሙያ ማማከር ይበጃል።
6. የጉሮሮ ቁስል እና የሳንባ ምች
ፀረ ባክቴሪያ መድሃትን እየወሰድን እንደ ብሮንካይት ያሉ የደረት አካባቢ ኢንፌክሽኖን በተደጋጋሚ የሚከሰቱብን ከሆነ ሌላው የሳንባ ካንሰር ምልክት ሊሆን ስለሚችል አስቸኳይ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው ።
7. ምግብ የመዋጥ ችግር
ለተከታታይ ሳምንታት የዘለቀ ምግብ የመዋጥ ችግር የጉሮሮ አልያም የሆድ ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል። ምግብ በምንወሰድ ስዓት ለመተንፈስ የመቸገር እና የሚያስለን ከሆነም ለሳንባ ካንሰር መጋለጥን ያሳያሉ። በ2004 ዓ.ም በግብጽ የተደረገ ጥናት ምግብ የመዋጥ ችግር ዋነኛ የሳንባ ካንሰር ምልክት መሆኑን ጠቁሟል።
8. ከፍተኛ የክብደት መቀነስ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ10 የሳንባ ካንሰር ተጠቂዎች ስድስቱ ክብደታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። የካንሰር ህዋሳት በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመውን ሀይል መጠቀም ሲጀምሩ ነው ክብደታችን የሚቀንሰው። ከክብደት መቀነሱ ተዳምሮ የድካም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት ማነስ እና አቅም ማጣት የህመሙ ምልክቶች ናቸው።
9. የጣት እና ጥፍሮች ቅርጽ መበላሸት
ከልብ አልያም ከሳንባ ጋር በተያያዘ ችግር በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጅን መጠን አነስተኛ መሆን ለጣት እና የጣት ጥፍሮች ቅርጽ መበላሸት ይዳርጋል።
ምንጭ፡ fbc