በሽታን ስለመከላከል ከጉንዳኖች ምን እንማራለን?
==================
ወደቤታቸው ከመግባታቸው በፊት እራሳቸውን ያፀዳሉ፣ ለየት ያለ ኬሚካልን በመጠቀም ንፅህናቸውን ይጠብቃሉ፣ በእግረኞች በተጨናነቁ ስፍራዎች ላይ ጉዞ እንዳይደረግ ገደብ ያደርጋሉ፡፡ ውድ አንባብያን እምናወራው ስለ ስልጡኑ የሰው ልጅ አይደለም፤ ስለ ጉንዳኖች እንጂ፡፡ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሺኝ መከሰትን ተከትሎ የተዋወቅነው ፅንሰ ሀሳብ ቢሆንም ጉንዳኖች ግን በሽታን ለማራቅ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡
ምንም እንኳን ጉንዳኖች በጣም ተጠጋግተው የሚኖሩ እንስሳት ቢሆኑም በሽታን ከመኖርያ አካባቢያቸው በማራቅ ረገድ ግን እጅግ ስኬታማ ናቸው፡፡ እንደውም በነዚህ የጉንዳን ሰፈሮች በሽታ የመገኘቱ ነገር እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ እናገኘዋለንለ፡፡ ለዚህም ነው ጉንዳኖች በምድራችን ካሉ እጅግ ስኬታማ ዝርያዎች መካከል ከቀዳሚዎቹ ለመገኘት የበቁት፡፡ እንደ አንዳንድ ጥናቶች ከሆነ በምድር ከሚገኙ እንስሳት ይዘት መካከል አንድ አራተኛው ጉንዳኖች ናቸው፡፡
እነዚህ እራሳቸውን ለመጠበቅ ለረጅም ጊዜ ሲወስዷቸው የቆይዋቸውእርምጃዎች ጉንዳኖችን በተለየ መልኩ የብልህ እንስሳ ገፅታን አላብሷቸዋል፡፡
አካላዊ ርቀትን መጠበቅ
ከሁለት ዓመታት በፊት የወጣ አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ጉንዳኖች ለበሽታ አስተላላፊዎች በሚጋለጡበት ጊዜ በምላሹ አኳሀናቸው ላይ ለውጦችን ያደርጋሉ፡፡ ጉንዳኖቹ ቀድሞውንም በሁለት ቡድኖች የተከፈሉ ናቸው፤ በጎጆው ውስጥ ያሉትን እንቁላል እና ጨቅላ ጉንዳኖች የሚንከባከቡ እና ከውጭ ሆነው ምግብ የሚሰበስቡ፡፡ አጥኚዎቹ በ11 የተለያዩ ስፍራዎች የሚኖሩ የጉንዳን ማህበረሰቦችን ለበሽታ ዘሮች (Spores) ካጋለጧቸው በኋላ ጉንዳኖቹ ከሌላ ቡድን ጉንዳንም ሆነ እርስ በእርሳቸው ያደርጉት የነበረውን ግንኙነት መቀነሳቸውን ለመመልከት ችለዋል፡፡ ቡድኖቹም ይበልጥ እየተለያዩ መምጣታቸውን ተከትሎም የዘሮቹ ስርጭት እንዲቀንስ ሆኗል፡፡ በሌላ መልኩ ሌሎች 11 ማህበረተሰቦችን ላይ አጥኚዎቹ ባካሄዱት ሙከራ ጥናቱ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የሚላቸውን ጉንዳኖች ማህበረሰቡ ሲጠብቅ ታይቷል፡፡ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የሚባሉት ንግስቷ እና ታዳጊዎቹ ጉንዳኖች ናቸው ሁሌም በተሻለ ሲተርፉ እና በበሽታ ዝርያዎቹም የመጠቃት ዕድላቸው ያነሰ ሆኖ ብቅ የሚሉት፡፡ እንዲሁ ለበሽታ ዝርያዎቹ አነስተኛ ተጋላጭነትን ያሳዩት ጉንዳኖችም ክትባት ከተከተቡ ሰዎች ጋራ በሚመሳሰል መልኩ ከፍተኛ በሽታን የመከላከል ምላሽ አሳይተዋል፡፡
ንፅህናን መጠበቅ
ከጉንዳኖች አኗኗር ትምህርትን የምናገኘው ከሚተገብሩት አካላዊ ርቀት ብቻም አይደለም፡፡ በአንድ ወቅት በጆርናል ኦፍ ኢቮልዩሽነሪ ባዮሎጂ ላይ የወጣ ጥናት እንደሚያመላክተው ከሆነ ጉንዳኖች የእርስ በራሳቸውን ንፅህና መጠበቂያ ልዩ መንገድ ይጠቀማሉ፡፡ ይህን ጥናት እንደመነሻ አድርጎ የተጠና ሌላ ጥናት በበኩሉ ጉንዳኖቹ የጎጆ ውስጥ ጓደኞቻቸውን የበሽታ ተጠቂነት ደረጃ ከግምት በማስገባት የፅዳት ሁኔታቸውን እንደሚያስተካክሉ አመላክቷል፡፡
የጎጆ ውስጥ ጓደኛሞች ወደ ጎጆው ከመግባታቸው በፊት እራሳቸውን ከማፅዳትም ባሻገር አንዱ የሌላውን ያፀዳል፡፡ በዚህ ሂደት አንዱ ጉንዳን በሌላኛው ጉንዳን አካል ላይ ያየውን በሽታ አምጪ ቁስ ከአካሉ ላይ በማንሳት ያስወግድለታል፡፡ ከአንድ በላይ በሽታ አምጪዎች (Pathogen) በላዩ ላይ ያለበትን ጓደኛቸውን በሚያፀዱበት ጊዜ ደግሞ ጉንዳኖቹ የራሳቸውን ፀረ ተህዋስያን መርዝ የሚጠቀሙ ሲሆን አካላዊ ግንኙነታቸውንም ይቀንሳሉ፡፡ በዚህ መንገድ አነስተኛ የበሽታ ዝርያ መጠን የሚኖርባቸው ጉንዳኖች በሌላ በኩል የፈንገስ ዝርያዎችን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ያለ በመሆኑ በሽታን ይከላከላሉ፡፡
በተጨማሪም ጉንዳኖች ጎጆዋቸውን ከመስራታቸውም አስቀድሞ በቦታው ያሉ በሽታ አስተላላፊዎችን ኬሚካል ተጠቅመው ያስወግዳሉ፡፡ ብዙ የጉንዳን ዝርያዎች ፎርሚክ አሲድ የተባለ መርዛማ ንጥረ ነገርን በመርዝ ማመንጫ እጢዎቻቸው ያመርታሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ይህን ንጥረ ነገር የሚጠቀሙት እራሳቸውን ከአዳኞች ለመጠበቅ እና ጎጆዋቸውን ለማፅዳት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን በአስገራሚ ሁኔታ ጉንዳኖችም ልክ እንደ ሰው ልጆች ወደ አዲስ መኖርያ ሲዘዋወሩ በአዲሱ ቤታቸው መኖር ከመጀመራቸው አስቀድሞ ፅዳት ያከናውናሉ፡፡
አውስትራሊያ ውስጥ በተጠና ሌላ ጥናት ጉንዳኖች የመኖርያ አካባቢያቸውን በፎርሚክ አሲድ አማካኝነት ሲያፀዱ በጎጆው ውስጥ በቅርፊት (Cocoons) ተደርገው የተቀመጡ በመፈልፈል ላይ ያሉ እንቁላሎችን (Pupae) የያዘው የመፈልፈያ ቅርፊት ግን ይህን መርዛማ ነገር መቋቋም እንደሚችል አሳይቷል፡፡ ቅርፊቶቹ ልክ የሰው ልጆች ኬሚካሎችን ሲረጩ ሰውነታቸውን በመጠበቂያ ቁሶች እንደሚያከናንቡ ሁሉ እነርሱም ይህን አገልግሎት ይወጣሉ፡፡
የተፈጥሮ ህክምና
የእራሳቸውን እና ሌሎች ጓደኞቻቸውን ተህዋስያን ከማራገፋቸውም በተጨማሪ ጉንዳኖች ሌሎች የበሽታ መከላከያ መንገዶችንም ይከተላሉ፡፡ የእንጨት ጉንዳን ተብለው የሚጠሩት የጉንዳን ዝርያዎች በበኩላቸው ሌሎች ጉንዳኖች የሚገለገሉበት ፎርሚክ አሲድን ተጠቅመው አደን ያድናሉ ጎጆዋቸውንም ያፀዳሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን እነዚህ የጉንዳን ዝርያዎች ከጎጆዋቸው ውጭ ካለው ዛፍ የሚመነጩና የፀረ ተህዋሲነት ባህርይ ያለውን ሙጫ በመሰብሰብ ከእንቁላል መፈልፈያው በቅርብ ርቀት ያስቀምጡታል፡፡ ሆኖም ንጥረ ነገሩን ለብቻው ከመጠቀም ይልቅ ከአሲዱ ጋራ በጎጆዋቸው ውስጥ በመቀላቀል ይበልጥ ኃይለኛ የሆነ የበሽታ መከላከያን እንደሚያመርቱ የጥናት ቡድኑ ውጤት ያስቀምጣል፡፡ የጥናት ቡድኑ እንደ ስንጥር፣ ድንጋይ እንዲሁም ሙጫ ያሉ ቁሳቁሶችን ሰራተኛ ጉንዳኖች በሚገኙበት አካባቢ ሲያስቀምጥ ሌሎች ቁሳቁሶችን ደግሞ ከስፍራው አርቆ አስቀምጧል፡፡ በውጤቱም ከጉንዳኖቹ አጠገበብ በተቀመጡት ደረቅ ሙጫዎች ላይ ከፍ ያለ የፎርሚክ አሲድ ይዘት አግኝተዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም ከሰራተኛ ጉንዳኖቹ ጋራ ግንኙነት የነበራቸው ሙጫዎች ርቀው ከተቀመጡት አንፃር ከፍ ያለ የፀረ ተህዋስያን ንጥረ ነገር ይዘት ተገኝቶባቸዋል፡፡ ለአሲዱ ተጋልጠው የነበሩ ሌሎች የጎጆው ቁሳቁሶች ግን ይህን መሰል በሽታን የመከላከል ባህርይ አልተገኘባቸውም፡፡
ከዋና ዋና የበሽታ ስርጭት መከላከያ መሳርያዎቻችን መካከል የተወሰኑት መገኛ በተፈጥሮ ውስጥ ነው፡፡ ታድያ እኛም ጉዳኖችን በመመልከት የአካላዊ ርቀትንም ሆነ ፅዳት የመጠበቅን ውጤታማነት መገምገምና ተፈጥሮአዊ ቁሶችን መጠቀምም እንችላለን፡፡ በሂደት ውስጥ ያለ አዲስ ጥናት ከብዙ ግለሰቦች ጋራ ግንኙነት ያላቸውንን እና በሽታን ለብዙዎች የሚያሰራጩ ሰዎችን “Super-Spreaders” ለማጥናት ጉንዳኖችን በሞደዴልነት እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ ይህ አይነት ሞዴል ወደፊት በሽታን በማህበረሰብ ውስጥ በስፋት የሚያሰራጩ ግለሰቦችን ለመለየት እና ክትባት ለመስጠትም ሆነ ከበሽታው የተጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ይረዳን ይጉንዳኖች
ይህ ማለት ግን ጉንዳኖች በሚሄዱባቸው በሁሉም መንገዶች መሄድ አለብን ማለት አይደለም፡፡ ጉንዳኖች በበሽታ መከላከል ውስጥ ለእኛ የማይመከሩ ስልቶችን ይከተላሉ (ለምሳሌ ታዳጊ ጉንዳኖች በበሽታው ተጠቅተው ሲገኙ በመርዝ በመመረዝ ማባረር ይገኝበታል)፡፡ ከዚህ ይልቅ በጥሩነት ከተፈረጀው ጎናቸው ለይቶ በማውጣት መጠቀም ይገባል፡፡
ምንጭ፡ Discover መፅሄት

ማሽኖች ማሰብ ይችላሉን?
==============
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቃት በኋላ አለን ቱሪንግ የተባለ የሂሳብ ሊቅ ቀላል የሚመስል የፈጠራውን አለም ታሪክ የቀየረ ጥያቄን አቀረበ፡፡ ጥያቄውም "Can machines think?" ወይም ማሽኖች ማሰብ ይችላሉ? የሚል ነበር፡፡ የዚህን የሂሳብ ሊቅ ትያቄ በአውንታ የሚመልስ የኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ለመሆኑ አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ ምንድን ነው?
የሁለቱን ቃላት ድምር ሀሳብ በግርድፉ የማሽኖች እንደሰው ማሰብ፣ ማሰላሰልና ድርጊትን በተጠየቃዊ (rationally) መንገድ መፈጸም ተብሎ ሊወሰድ እንደሚችል ሰቱዋርት ሩስል እና ፒተር ኖርቪንግ የተባሉ ምሁራን ለዚሁ ዘርፍ የመጀመሪያ በሚባል መጽሐፋቸው ገልጸዋል፡፡
በቅርብ ጊዜ ደግሞ የጃፓኑ DataRobot CEO የሆነው ጀርሚ አኪን አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ በመሰረታዊነት የሰውን ጥልቅ የማሰብ ችሎታ የሚፈልግ የኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ይህ ዘርፍ በሁለት ሰፋፊ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም ውስን አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ (Narrow AI) እና አጠቃላይ አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ Artificial General Intelligence (AGI) በመባል ይታወቃሉ፡፡
ውስኑ አርቲፍሻል ኢንተለጀንስ (Narrow AI) በመሰረታዊነት ውስን ተግባራትን የሚፈጽም ሲሆን በ2016 በወጣ አንድ ዘገባ እንደ Google search፣ Image recognition software፣ Siri፣ Alexa and other personal assistants, Self-driving cars እና IBM's Watson ያሉ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ሌላኛው እና ጠንካራው ክፍል Artificial General Intelligence (AGI) የሚባለው ሲሆን ሰዎች ከሚሰሩት ተግባር በተቀራረበ የሚሰራ እና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት አገልግሎት ላይ የሚውል ነው፡፡ ይህ ዘርፍ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ደረጃ ላይ የደረሱ የአለማችን ክፍሎች እያዳበሩት ያለ ጉዳይ ቢሆንም በአስፈላጊነቱ ዙሪያ በተመራማሪዎች ዘንድ መግባባት ላይ አልተደረሰም፡፡
ሀገራችን ኢትዮጲያም የዚህን ሀሳብ ተግባራዊነት ”ዓለም የደረሰበትን የኢንዱስትሪ አብዮት ተመልካች እና ተቀባይ ብቻ የሚሆን ወጣት እንዲኖረን አንሻም” በሚል መሰረታዊ ሀሳብ የመጀመሪያው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በመክፈት አሀዱ ብላለች፡፡
Builtin.comን በምንጭነት ተጠቅመናል፡፡

1% የሚሆኑት የዓለማችን ሃብታሞች እጅግ እየጨመረ ለመጣው የካርቦን ልቀት ዋና ምክንያት ናቸው ተባለ
======================
የአለማችን ትልቅ ስጋት ሀኖ የቆየው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት ከአውፓውያኑ 1990 ጀምሮ አስከ 2015 ድረስ በ60% ያደገ ሲሆን፤ በዚህ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ደግሞ 1% የሚሸፍኑት የአለም ሃብታሞች የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ግማሽ በመቶ ህዝቦች ሊለቁት ከሚችሉት የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት በሶስት እጥፍ የላቀ መሆኑ ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
የስቶኮልም ኢንቫይሮመንት ኢኒስቲትዩት እና Oxfam በጋራ የሰሩት የሰሞኑ ጥናት በእነዚህ የአለማችን ሃብታም ሰዎች ጥቅም ላይ የሚውለው ገደብ የለሽ የፍጆታ መጠን እና ከፍተኛ የካርቦን ልቀት የሚያስከትለው የትራንስፖርት ኢንዱስትሪው የቢሊዮኖችን ነፍስ አደጋ ላይ እንደሚጥል የኦክስፋም ተመራማሪ ቲም ጎሬ ይናገራሉ፡፡
በጥናቱ እንደተመለከተው ከ1990 ጀምሮ በነበሩት ተከታታይ 25 አመታት 10% ወይም 630 ሚሊዮን የሚጠጉት የአለም ሃብታም ሰዎች 52% ለሚሆነው የካርቦን ልቀት ጭማሪ ዋና ምክንያት የነበሩ ሲሆን የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ግማሽ በመቶ ህዝቦች ሊለቁት ከሚችሉት የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት በሶስት እጥፍ የላቀ ነው፡፡ የአከባቢ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚያስቀምጡት ይህ የካርቦን ልቀት ምጣኔ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በቀጣያቹ አስርት አመታት የአለም ሙቀት በ 1.5 ዲግሪ ሴልሺ ጭማሪ በማሳየት የአለማችንን የተፈጥሮ ሁኔታ አደጋ ውስጥ እንደሚከተው ያስጠነቅቃሉ፡፡
በዚህ የኦክስፋም ሪፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ 10% የሚሸፍኑት ሃብታም ሰዎች በአመት ከ35,000 ዶላር በላይ የሚያገኙ ሲሆን፣ አንድ በመቶ የሚሸፍኑት ሃብታም ሰዎች ደግሞ በአመት ከ100,000 ዶላር በላይ የሚያገኙ ናቸው፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ስልክን ለልጆች መቼ ?
=========
በሰለጠኑት የአለማችን ሀገራት የእጅ ስልክ ለልጆች መስጠት እንደ ብክነት የሚቆጠርበት ጊዜ ሩቅ እንዳልነበር ዘገባወች ያመለክታሉ፡፡ በ2004 አካባቢ 18 በመቶ የሚሆኑ የ12 ዓመት ልጆች ቴክኖሎጂውን መጠቀም እንደጀመሩ በዚህ ረገድ ጥናት ደረጉ እንደ the Pew Internet እና American Life Project የተሰኙ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡ ጥቂት አለፍ ብሎ በ2011፣ 58 በመቶ የሚሆኑ የ12 ኣመት ልጆች የእጅ ስልኮችን መጠቀም እንደጀመሩና 75 በመቶ የሚጠጉ ከ12-17 የሆናቸው ልጆች የራሳቸው የእጅ ስልክ እንደያዙ ሌሎች ጥናቶች አመላክተዋል ይለናል የዘገባ ምንጫችን howstuffworks.com.
ውድ የዚህ ገጽ ተከታታዮች ልጆች አሎት? ወይስ ልጅ ቢኖሮት በስንት አመቱ/ቷ የእጅ ስልክ ለመስጠት ያስባሉ? እንደምንጫችን ከሆነ ለልጆች ስልክ ለመጠት ትክክለኛ የሚባል ጊዜ ላይኖር ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ጉዳዩ የእድሜ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህ ባሻገር ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ጉዳዮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ልጆች ሁሉ የተለያየ ባህሪ አላቸው፡፡ አንዳንዶች ታዛዦች ናቸው አንዳንዶች ደግሞ እመቢተኞች፡፡ አንዳንዶች የቤተሰብ የቤት ውስጥ ህግን ያከብራሉ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው፡፡
በነገራችን ላይ ወላጆች ለልጆች ስልክ የሚገዙት በምን ምክንያት ነው? ልጆችስ ስልክ የሚፈልጉት ለምን ይሆን? በሁለቱ ፍላጎቶች መካከል መመሳሰል ካለ ጉዳዩ ያን ያክል አሳሳቢ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገርግን የወላጆች ፍላጎትና የልጆች ስሜት ካልተቀራረበ ችግሮች መፈጠራቸው አይቀርም፡፡
ስለዚህ ወላጆች ልጆቻችን ስልክ እንዲይዙ ከመፍቀዳችን በፊት የተወሰኑ ጥያቄወችን ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ለምሳሌ ልጄ በብዛት ብቸኝነት ይሰማታል/ዋል? ልጄ ሀላፊነት ይሰማታል/ዋል? ልጆቼ የምነግራቸውን ይሰማሉ? እነዚህንና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ራሶትን ጠይቀው የአወንታ መልስ ካገኙ የልጆቸዎ ስልክ መያዝ ክፋት ላኖረው ይችላል፡፡ ካልሆነ ግን ወላጆች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ልጆች የግል ስልክ መያዝ ከጀመሩ በኋላ ግለኝነት (privacy) ያበዛሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ልጆች ከቤተሰ እየተገለሉ ይሄዳሉ፡፡ የልጆቻችን ከቁጥጥር ውጭ መሆን ከዚህ ጀምራል፡፡ privacy ለልጆች ያስፈልጋል ? ሐሳባችሁን አጋሩን፡፡
ምንጭ ፡ howstuffworks.com.

(43,252,003,274,489,856,000) ለመሆኑ ይህ ቁጥር ስንት ነው
==========
በአለማችን የተለያዩ የማሰብ ችሎታን የሚያዳብሩ ጨዋታወች ተፈጥረዋል እንደ ቼዝ፣ ፑል፣ ሌሎች የስልክ ጌሞችን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአለማችን ከተፈጠሩ ከፍተኛ የማሰብ ብቃትንና ትዕግስትን ከሚጠይቁ ጨዋታወች መካከል አንዱ የሆነውን Rubik’s Cube የተባለውን ባለ ስድስት ጎን ተመሳሳይ ቀለም ያላቸውን ክፍሎች በአንድ በኩል መደርድር ጨዋታ ነው፡፡
ይህ ጨዋታ ስያሜውን ያገኘው በ1974 ጨዋታውን በፈጠረው ኢሮን ረቢክ ( Erno Rubik) አማካኝነት ነው፡፡ ታዲያ የዚህ ፈጠራ ባለቤት የሆነው ኢሮን ረቢክ መጀመሪያ እነዚህን የተዘበራረቁ ቀለማት በተመሳሳይ ስፍራ ለማድረግ ከአንድ ወር በላይ ጥረት አድረጓል፡፡ መጫወቻውን ሲሰራ በፍጹም ጨዋታውን የሚያሸንፈው አለ ብሎአላሰበም ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ የሂሳብ ሊቆች ስኩየሩን ለማስተካከል 43,252,003,274,489,856,000 መንገዶች ያሉ ቢሆንም ከእነዚህ መካከል ግን ትክክል የሚሆነው አንዱ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በ2018 አንድ Yusheng Du የተባለ ቻይናዊ የአለም ሪከርድ በሆነ 3.47 ሴኮንዶች ማስተካከል ችሏል፡፡ ታዲያ እርሶ አንድን ነገር ለማሳካት 43,252,003,274,489,856,000 ያክል ጊዜ መሞከር ሊኖርባችሁ እንደሚችል እያወቃችሁ ሙከራውን ትቀጥላላችሁ? ወይስ? የዚህ ፈጠራ ባለቤት ዛሬም ከ46 አመት በኋላ ጨዋታው እየገባኝ ነው ሲል መናገሩን የዘገበው የዜና ምንጫችን The New York Times ነው፡፡

ኮምፒውተር ሲጠቀሙ ጊዜዎትን መቆጠብ እንዲችሉ እነዚህን ይጠቀሙ
****************
Basic Windows keyboard shortcuts
Ctrl+Z: Undo
Ctrl+W: Close
Ctrl+A: Select all
Alt+Tab: Switch apps
Alt+F4: Close apps
Windows navigation shortcuts
Win+D: Show or hide the desktop
Win+left arrow or Win+right arrow: Snap windows
Win+Tab: Open the Task view
Tab and Shift+Tab: Move backward and forward through options
Ctrl+Esc: Open the Start menu
Advanced Windows shortcut tricks
F2: Rename
F5: Refresh
Win+L: Lock your computer
Win+I: Open Settings
Win+S: Search Windows
Win+PrtScn: Save a screenshot
Ctrl+Shift+Esc: Open the Task Manager
Win+C: Start talking to Cortana
Win+Ctrl+D: Add a new virtual desktop
Win+X: Open the hidden menu
ምንጭ፡ populare science

የኤሌክትሪክ መንገድ በቴላቪቭ
*************************
የቴላቪቭ ከተማ በአለም የመጀመሪያ የሚያደርጋትን ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል የኤልክትሪክ መንገድ በተሳካ ሁኔታ መገንባቷን CNN በቢዝነስ ዘገባው አመልክቷል፡፡ መንገዱ የኤሌክትሪክ መኪናወችን ባትሪ መሙላት እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ ዘገባው እንዳመለከተው Tel Aviv-Yafo እና ElectReon በተባሉ ድርጅቶች የሚመራ ሲሆን የቴላቪቭ ከተማ አስተዳደርና የግሉ ዘርፍ ፋይናንስ አድርገውታል፡፡
ከዚህ በፊት የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ለማድረግ ወደ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ማምራት ይጠበቅባቸው የነበረ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ግን ይህን ሁሉ አስቀርቷል፡፡
ይህ በፓይለት ወይም በሙከራ ደረጃ ያለው ስራ ከተሳካ አለማችን በከባቢ አየር ብክለት ምክንያት እየገጠማት ያለውን ቀውስ ለመቀነስ ያስችላታል፡፡ በተለይም ወደፊት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሐይል ማመንጫ ግንባታዎችን አጠናክራ ከገነባችና እነዚህን መኪኖች የማምረትና የመገጣጠም ስራው እንደ ኒያላ ሞተርስ ባሉ ድርጅቶች ከተከናወነ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መቅረፍ ትችላለች፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአለማችን ትልቁ የመኪና አምራች ድርጅት ቴስላ በቅርቡ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪን አሁን ካለበት ዋጋ በጣም ይቀንሳል ያለውን የባትሪ ማሻሻያ ሰርቷል፡፡ ይህም የዚህን የኤሌክትሪክ መኪና ተመራጭነት ከፍተኛ እንዲሆን በማድረግ የካምፓኒውን መኪናዎች ተፈላጊነት በ20% ከፍ ያደርገዋል፡፡ እንደ tuchcrunch ዘገባ ከሆነ ካምፓኒው የባትሪ መሙያውን ዋጋ ወደ $1.20 ዝቅ ያደርገዋል፡፡
የእነዚህ ከላይ የተገለጹት ግኝቶች ጥምረት ሊኖረው የሚችለውን ጥቅም ማሰብ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ ፈጣን የአውቶብስ መንገድ የመስራት እቅድ እንዳላት ይታወቃል፡፡ ታዲያ እንደነዚህ አይነት ግኝቶችን አብሮ ማሰብ ጠቃሚ አይደለም ትላላችሁ፡፡ ሀሳባችሁን አካፍሉን፡፡
ዘገባው የCNN international እና Techcrunch ነው፡፡

170 የሚጠጉት የኮቪድ 19 ክትባቶች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
--------------------------------------------------------------
አሁን ላይ የአለም ጤና ድርጅት ክትትል የሚያደርግባቸው ከ170 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ውጤታማነታቸውና ደህንነታቸው በተረጋገጠ መልኩ ለማከናወን አራት መሰረታዊ የክሊኒካል የሙከራ ደረጃዎችን የሚያልፉ ሲሆን አራቱም ሂደቶች የየራሳቸው መስፈርቶች እና መገለጫዎች ያሏቸው ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት አራቱን መሰረታዊ የሙከራ ደረጃዎች ክትባቶቹ ከሚገኙባቸው ሂደቶች አንፃር ብናስቀምጣቸው የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡
ሙሉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ http://www.techin.gov.et/post/282/

www.techin.gov.et
Technology Innovation Inistitute
The Federal Democratic Republic of Ethiopia’s Office of the Prime Minister is currently restructuring under the premiership of Prime Minister Abiy Ahmed. Under the new structure the Office comprises eleven structures.
የማስታወስ ችሎታን የሚያዳብሩ መንገዶች
***********************************
ምንም እንኳን ሰዎች ከዕድሜ ብዛት የተነሳ አንዳንድ ነገሮችን ብንረሳም የማስታወስ አቅማችንን ማሳደግ የምንችልባቸው መንገዶች እንዳሉ መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ የጤና ህግ ለሰውነታችን ተስማሚ የሆነ ነገር ሁሉ ለአእምሯችንና ለማስታወስ ብቃታችን ተስማሚ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ አምስት የማስታወስ ብቃትን ማሳደግ የሚያስችሉ መንገዶችን ልናስታውሳችሁ ወደድን፡፡
1ኛ. ተስማሚ ምግቦችን መመገብ
በቫይታሚን ቢ፣ በኦሜጋ 3 እንዲሁም በፋቲ አሲድ የበለጸጉ ምግቦች አእምሯችን ጤናማ እንዲሆን በመርዳት ረጅም ትውስታ እንዲኖረን ያደርጋሉ፡፡ ለአእምሯችን ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች እንደ ፍራፍሬ፣ አሳ፣ ቅጠላ ቅጠል የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
2ኛ. የልብን ጤንነት መጠበቅ
ብዙዎቹ የአእምሮ ሀኪሞች ለልብ ጥሩ የሆነ ለአእምሮም ጥሩ ነው በሚል አባባላቸው ይታወቃሉ፡፡ በአብዛኛው የልብ ችግር የሚያጋጥማቸው ሰዎች የማስታወስ ችግርም ተጠቂዎች ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ የደም ግፊትን መቆጣጠር፣ በሰውነታችን ያለውን የስብ መጠን መቆጣጠር፣ የስኳር መጠናችንን መቆጣጠር፣ አልኮል መቀነስና ሲጋራን መተው ልባችንን የምንንከባከብባቸው መንገዶች ናቸው፡፡
3ኛ. የጸሐይ ብርሐን በበቂ ሁኔታ ማግኘት
ሰዎች የሚያገኙትን የጸሐይ ብርሐን መጠን ባሻሻሉ ቁጥር የማስታወስና የማሰብ ችሎታቸውን ማዳበር ይችላሉ፡፡ በተለይ የብርሐን መጠን በሚያንስበት በክረምት ወቅት የመጨነቅ ባህሪ ለሚያሳዩ ሰዎች ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡
4ኛ. ጥሩ እንቅልፍ መተኛትና በጥዋት መንቃት
ጥናቶች እንደሚያሳዩት አርፍደው የሚነሱ ሰዎች በጥዋት ከሚነሱ ሰዎች ያነሰ የማስታወስ ችሎታ አላቸው፡፡ በንጽጽር ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት በጥዋት ከመነሳት የተሻለ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተቻለ መጠን በሳምንቱ ቀናት ውስጥ የምንተኛባቸውና የምንነቃባቸው ሰዓቶች ተመሳሳይ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
5ኛ. የማስታዎስ ችሎታ ልምምዶችን ማድረግ
የማስታዎስ ችሎታችሁ ከሚጠበቀው በታች ከሆነ በባለሙዎች የሚዘወተሩ እንደ በምስል መከሰት (Visualization) እና ማመሳሰል ወይም ማዛመድ (association) የመሰሉ ተግባራትን መከወን ስሞችንና ዝርዝር ነገሮችን ለማስታወስ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ howstuffworks

የሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተአማኒነት እስከ ምን?
==========================
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትልቁ ሀሳብ ማሽኖችን እራስ ገዝ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት እራሳቸውን በራሳቸው የሚያሽከረክሩ መኪኖች፣ ውሳኔ የሚወስኑ ሮቦቶችን እና ሌሎችንም እንደዛ የሆኑ ማሽኖች እየተመረቱ እና እየተሰሩ ነው፡፡ይሁንና እነዚህን ማሽኖች ምን ያህል ማመን ይቻላል የሚለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
የሰው ልጆች አዕምሮ እንዳላቸው ሁሉ ኒውራል ኔትዎርክ የሰውሰራሽ አስተውሎቶች አዕምሮ ነው፡፡ ይህ መረብ አዕምሮ ለሰው ልጆች የሚሰራውን ሁሉ ለማሽኖች እንዲሰራ የታሰበ ሲሆን በዋናነት ትንበያን ማመንጨት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ይሁንና ይህ ምንጭ ተአማኒነቱ ምን ያህል ነው የሚለው ነገር አሳሳቢ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ብናይ የእራስ ገዝ መኪናዎች ፈተና በመንገድ ላይ የሚገጥሟቸውን ነገራት ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ አለማወቅ ላይ ነው፤ ማለትም መንገድ እያቋረጠ ያለው ነገር እንስሳ ነው ወይስ ህጻን ልጅ ፣ ይህ አካል ፈጣን እርምጃ ነው ያለው ወይስ ቀርፋፋ ፣ ሌላ መኪና በተሳሳተ አቅጣጫ ቢመጣበትስ ወደየትኛው ለመንዳት ይወስናል እና የትኛው ያነሰ ጉዳት ያመጣል የሚሉትን በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ የሚወሰኑ ውስበስብ ውሳኔዎችን ለመወሰን ለማሽኖች ቀላል አይሆንም፡፡
ለመኪናው መረጃ አቀባይ ምንጮች ብዙ ናቸው፡፡ የፊት ለፊት ካሜራ፣ የኮምፒውተር እይታ እና ሌሎችም ይህ መኪናው የትኛውን ሴንሰር ማመን እና መቀበል እንዳለበት ግራ እንያጋባው ያደርጋል፡፡ በተለይም የመረጃ መጣረሶች በሚከሰቱበት ሰዓት መኪናው የሚወስነውን ነገር ጠንቆ ማወቅ ይቸገራል፡፡
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስከዛሬ ድረስ የሰው ሰራሽ አስተውሎቶችን ተአማኒነት የሚለካ ምንም ዓይነት አሰራር እና መሳሪያ የለም የሚሉት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ተመራማረዎች ምንም እንኳን ስህተት የማሽኖች ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችም መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን የሰው ልጆችም የመወሰን ችግር፣ የመዘግየት በሃሪ እና ሌሎችንም የትንበያ እክሎች እንደሚያተናግዱ እናውቃለን ብለዋል፡፡
ይሁንና አሁንም ቢሆን ኒውራል መረብ ላይ እጅግ መልፋት እና የትክክለኝነቱን መጠን ማሰፋት ላይ በትጋት ሊሰራ ይገባል ያሉ ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በኦገስት31 /2020 ማሽኖች በማያውቁበት እና ግራ በሚጋቡበት ጊዜ አናውቅም ማለት የሚችሉበትን አዲስ አሰራር የፈጠሩ ሲሆን ይህ ሁኔታ በተሳሳቱ ውሳዎች የሚከሰቱ ውድመቶችን ለመከላከል ዓይነተኛ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily