TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
Channel name was changed to «STIC Ethiopia»
አዲስ የሞባይል ቀፎ ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ሲገዙ በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ለማወቅ :-
• ሲም ካርድ አስገብተው ለሙከራ መጠቀም
• *868# ደውለው 3ኛ ቁጥር ላይ የሚገኘውን የመለያ ቁጥር ሁኔታ ማወቂያ (Check Status) የሚለውን መምረጥ ፤ በመቀጠል by IMEI የሚለውን መርጠው፤ ሊገዙ ያሰቡትን የቀፎ መለያ ቁጥር /IMEI/ አስገብተው ቀፎው በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
- የሚገዙትን ቀፎ የIMEI ቁጥር ለማወቅ፡
• *#06# ይደውሉ
• ከቀፎው ማሸጊያ ካርቶን ላይ ይመልከቱ፡፡
ግዢ ከፈፀሙ በኋላ ቀፎዎ በኔትዎርኩ ላይ የማይሠራ ከሆነስ?
• ከግዢ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በህግ አግባብ ለመፍታት እንዲችሉ ግዢ ሲፈፅሙ የቀፎውን መለያ ቁጥር የያዘ ህጋዊ ደረሰኝ መቀበልዎን አይርሱ፡፡
ስርቆት ወይም መጥፋት ቢያጋጥምዎ?
• በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች በተለይ የሞባይል ስልክ በስርቆትም ሆነ በሌላ ምክንያት ከደንበኞች እጅ ሲጠፋ 994 ላይ ደውለው በማዘጋት ቀፎው በሌላ አካል የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ጠቃሚ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን እንዲሁም የጤና ምክሮችን በየቀኑ እናደርሳችኋለን። ወዳጅ ጓደጎቻችሁንም ወደዚህ ቻናል ይጋብዙ።