TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
TechIn2 pinned a file
# ከኮሮና # ቫይረስ ጋር በተያያዘ # ስራዎን # ለመስራት
# ተቸግረዋል? እነዚህን የቴክኖሎጁ አማራጮች ይሞክሩ
***************************************
ወቅታዊው የዓለማችን አደጋ COVID-19 የስርጭት መጠኑ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችን ከእንቅስቃሴ ውጭ እያደረገ መምጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ብዙዎች በሽውታውን ለመከላከል እና የስርጭት መጠኑን ለመግታት ከመንግስት በወረዱ መመሪያዎች አማካኘነት ስራዎችን ከቤት በመሆን በመከወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ሌሎችም እያንዳንዷን ግንኙነታቸውን በርቀት እየተገበሩ ይገኛል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እነዚህን እንቅስቃሴዎች በቀላሉ ለመፈፀም እና ደህንነታችንንም በሚገባ ለመጠበቅ የቴክኖሎጂ እገዛ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡
እነዚህ ከስር የምትመለከቷቸው መተግበሪያዎች እና ድረ ገፆች በአብዛኛው የአለም ክፍል መሰል እንቅስቃሴዎችን ከቤት ሆኖ ለመከወን እና ስራዎችን ለማቅለል የሚያገለግሉ ሲሆን፤ በእኛ ሃገር ሁኔታም በሚቻለው አቅም ቢተገበሩ የሚጠቅሙ ናቸው፡፡
መረጃዎችን በአካል መገናኘት ሳያስፈልግ መላላክ የሚቻልባቸው ዌብ ቤዝድ መተግበሪያዎች
1. Dropbox
2. Pipebytes
3. MailBigFile
4. filedropper
5. Google drive
ስብሰባዎችን እና ውይይቶችን በርቀት ለማከናወን የሚያግዙ ዌብ ቤዝድ መተግበሪያዎች
1. Crowdcast
2. GoToMeeting
3. Cisco Webex Teams
4. Intermedia AnyMeeting
5. https://zoom.us/download ፡ ይህ በተለይም መረጃዎችን ፊት ለፊት በገጽታ ለማዉራት የሚያስችል ታወቂ ሶፍትዌር ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎችንም ተግባራት ለማከናወን ይረዳል፤ መረጃን (File) ለመላላክ፣ ጽሁፍ ለመጻጻፍ እና ከ ሁለት በላይ የሆኑ ሰዎችን በተመሳሳይ ሰዓት በተለያየ ጊዜ አስቻይ በሆነ መንገድ ለማገናኘት፣ የተለያዩ ቦታ ሆኖ ህክምና ለመስጠት፣ ሪፖርት ለማድረግ፣ ኮንፈረንስ ለማካሄድ እና ሌሎችም
የርቀት ትምህርቶቸን በኢተርኔት ለማግኘት እና ለመማማር የሚያግዙ ድረገፆች
1. Adobe Connect
2. Blackboard Collaborate
3. WizIQ
4. LearnCube
5. BigBlueButton ፡ ይህ በተለይም ብዙዎች የሚመርጡት የመስመር ላይ መማሪያ ስርዓት ሲሆን፤ ሩቅ ላሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን በቪዲዮ እና ኦውዲዮ ማጋራት የሚያስችል ነው፡፡
ከዛ ባለፈ በሃገራችን የካሽ ብር መያዝ ሳያስፈልግ ሂሳብ መክፈል የሚችሉባቸውን እነዚህን መንገዶች በሚቻለው ቦታ በመጠቀም ከበሽታው ራሳችንን መከላከል እንችላለን
1. M-birr
2. Amole
3. Helocash
4. Awash mobile
የስፓኒሽ ፍሉን መአት ያለፉት የ 101 ዓመት አዛውንት ለኮሮናም እጅ አልሰጡም
********************************
በሃገረ ጣልያን የኮሮናቫይረስ አደጋ እጅግ በተባባሰበት በአሁን ወቅት በተደጋጋሚ ሁኔታ እጅግ ልብ የሚሰብሩ ታሪኮችን ሲሰሙ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም ሃገሪቱ ከጃፓን ቀጥሎ የብዙ አዛውንቶች መኖሪያ በመሆኗ ብዙ ሞት ለማስተናገዷም ዋና ምክንያት እንደነበረ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ሲሻገርም አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ በጊዜው ማድረግ ባለመቻሏ የአደጋው መጠን የከፋ እንዲሆን ትልቅ በር ከፍቷል፡፡ ታዲያ እነዚህ እና ሌሎች ሁነቶች ተደማምረው ወጤቱን የከፋ አደረገው፡፡
ይሁንና በእነዚህ አሳዛኝ ሁኔታዎች ወስጥ ያለፈቸው ይህች ሃገር ተስፋን የሚያለመልም መልካም ዜና ፈፅሞ አልጠፋባትም ነበር፡፡ የ 101 ዓመት አዛውንት የሆኑት Mr. P ደግሞ ለዚህ ተስፋ መለምለም ዋነኛው ምክንያት ናቸው፡፡ እኝህ የ 101 ዓመት አዛውንት በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው ብዙዎች ሞታቸውን ሲጠባበቁላቸው የቆዩ ቢሆንም በተደረገላቸው የሃኪም እገዛ እና በሰነቁት ትልቅ ተስፋ ከቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ አገግመው የታሪክ ነጋሪ መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡ እኝህ አባት የስፓኒሽ ፍሉ ተብሎ በሚታወቀውና የብዙዎችን ነፍስ በቀጠፈው በዚያ ስከፊ ጊዜ እንደተወለዱ ያስታወቁት የኢንፈርሚ ሆስፒታል ዶክተሮች የዘመናችን አደጋ የሆነውን ኮሮናቫይረስን ዳግም ያሸነፉ ትልቅ አባት ሲሉ አሞግሰዋቸዋል፡፡
Mr. P በዚህ እድሜያቸው ከቫይረሱ አገግመው ወደቤታቸው የሄዱ ብቸኛው የጣልያን ዜጋ ሲሆኑ፤ ከዚህ ቀደምም በቻይና የሚኖሩ የ 103 የእድሜ ባለፀጋ ከሀኪሞች በተደረገላቸው ከፍተኛ እገዛ ከኮሮናቫይረስ ሙሉ ለሙሉ አገግመው ለብዙዎች ተስፋ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ምንጭ፡ IFLScience Store
በቤልጂየም የ12 ዓመቷ ህፃን በኮሮናቫይረስ ህይወቷ አልፏል
ይህ ለወጣቶች ምን መልእክት ይሰጣል
************************************
በቤልጂየም በኮሮናቫይረስ የተያዘች አንዲት የ12 ዓመት ህፃን ህይወቷ ማለፉን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ የሃገሪቱ የመንግስት ቃል አቀባይ ኢማኑዬል አንድሬ በዛሬ መግለጫቸው እንዳስረዱት ህፃኗ የትኩሳት ምልክት ከታየባት ከሶስት ቀን በኋላ በቫይረሱ መየዟን ለመረጋገጥ የተቻለ ቢሆንም በዚህ ፍጥነት ህይወቷ እንዴት ሊያልፍ እንደቻለ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣቶችና ህፃናት በኮሮናቫይረስ መሞታቸው እየተስተዋለ መምጣቱን ያስረዱት ቃል አቀባዩ አንድሬ ምንም አይነት መዘናጋት ሳየስፈልግ ተገቢው ጥንቃቄ በወጣቶች እንዲወሰድ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በአውሮፓ ከዚህ በፊት በእንግሊዝ የ18 ዓመት ወጣት፣ በፈረንሳይ የ16 ዓመት ሴት ልጅ፣ በፖርቹጋል የ14 ዓመት ልጅ እንዲሁም አሁን ደግሞ 12 ህፃን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መሞታቸውን ተከትሎ ወጣቶች እና ህፃናት ከአላስፈላጊ መዘናጋት ወጥተው ራሳቸውን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲጠብቁ የጤና ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛል፡፡
በበርካታ አገራት በእድሜ የገፉ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚሰጡ የጤና ማሳሰቢያዎችም ከዚህ ጋር ብቻ የተያያዙ በመሆናቸው ወጣቶች እኛን አየጠቃንም ወደሚል እሳቤ እንዲሄዱና ከፍተኛ መዘናጋት ውስጥ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅርቡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለወጣቶች እንዳስጠነቀቁት የኮሮናቫረስ እድሜያቸው እንደገፋ ሰዎች ወጣቶችን በፍጥነት ባይገድልም ለሳምንታት ሆስፒታል ሊያስተኛቸው እና ከዚያም ሲያልፍ ለሞት ሊያደርሳቸው አንደሚቸል መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ወጣቶች ምንም የህመም ስሜት ባይሰማቸው እንኳ ወዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው እና የሚወስኗቸው እያንዳንዷ ውሳኔዎች ለሌሎች የሞትና የሕይወት ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ከመቼውም ጊዜ በማስተዋል እንዲጓዙ ጥሪ አስተላልፈው ነበር።
በህጻናት በኩልም እስካሁን በይፋ እንደተረጋገጠው አብዛኞቹ በዚህ ቫይረስ የተጠቁ ህፃናት በበሽታው የመሞት መጠናቸው እጅግ ዝቅተኛ ቢሆንም በሽታውን ወደሌሎች የማስተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ግን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ምክንያቱም በዚህ የዕድሜ ክልል ያሉ ህጻናት የሚታይባቸው የበሽታው ምልክት በጣም አናሳ በመሆኑ እና በሃላፊነት ስሜት ራሳቸውን እና አካባቢያቸውን መጠበቅ ስለማይችሉ ምናልባት የበሽታው ዋነኛ አስተላለፊዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ያም ሆነ ይህ ግን ነገሮች ይበልጥ አስከሚታወቁ ድረስ ወጣቶች እና ህፃናት በፍፁም ሃላፊነት ራሳቸውን እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ከቫይረሱ መጠበቅ እንደሚገባቸው የሁሉም መልዕክት ነው፡፡
ምንጭ፡ express.co.uk/
25 በመቶው የኮሮናቫይረስ ተጠቂ ምልክቶችን ላያሳይ ይችላል፡ ጥናት
**********************
ቀላል ቁጥር የሌለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ምልክቶችን በትክክል ሊያሳይ ባለማቻሉ የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ሊያበዛው እንደሚችል አንድ የአሜሪካ የጤና ባለስልጣን አስታወቁ፡፡ በአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሮበርት ሬድፊልድ 25 በመቶ የሚሆነው በቫይረሱ የተያዘ ሰው ምልክቶችን ማሳየት በሚገባበት በመጀመሪያዎቹ አጭር ቀናት ውስጥ የትኞቹም ምልክቶች የማይታዩበት ወይም በህክምና አጠራሩ (asymptomatic) በመሆኑ ለቫይረሱ መዛመት ትልቅ መደላድል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም በትናትናው ዕለት በ CDC ጆርናል የታተመውን እንድ ጥናት ዋቢ በማድረግ የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ይህ ጥናት ከጥቂት ወራት በፊት በሲንጋፖር መረጃቸው ተሰብስቦ ክትትል ሲደረግባቸው በነበሩ 243 ኬዞች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ ከእነዚህ ኬዞች ውስጥ ደግሞ 150 የሚሆኑት ከላይ ከተጠቀሰው ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው በሚል የተለዩ ነበር፡፡ ታዲያ ተለይተው በተቀመጡት 150 ኬዞች ላይ በተደረገ ሰፊ ምርምር 6.4 በመቶ ወይም 19 የሚሆኑት ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይባቸው ቫይረሱን ወደሌሎች ሲያሰራጩ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
ይህ ጉዳይ በመጋቢት 19 በወጣ አንድ ጥናት ላይ እንዲሁ በስፋት የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ቀደም ብለው በቻይና ከሁቤይ ግዛት ውጭ በሆኑ ቦታዎች በተሰበሰቡ 468 ኬዞች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡ ታዲያ በዚህም ጥናት እንደታየው ክትትል ሲደረግባቸው ከነበሩት 468 ኬዞች ውሰጥ 58 የሚሆኑት ቫይረሱን ያስተላለፉባቸው ተጠቂዎች ምንም ምልክት ሳይታይባቸው፤ እነዚህ 58 ሰዎች ግን የበሽታው ዋና ዋና ምልክት ታይቶባቸው እንደነበረ በጥናቱ ተገልጿል፡፡ ይህም 12.6% የሚሆነው ኬዝ በአንድም ይሁን በሌላ በ asymptomatic transmission ሁኔታ ውስጥ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ታዲያ እነዚህን መረጃዎች ሲያጠናቅር የነበረው ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰሩት ተጨማሪ ምርምሮች ይበልጥ እስከሚጠናከሩ ሰዎች የሚጠቀሟቸው የፊት መሸፈኛ ጭብሎች እጀግ አስፈላጊ እንደሚሆኑ ተነግረዋል፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት ሰዎች በዚህ መልኩ በቫይረሱ ተጠቅተው ምልክቶች የማይታዩባቸው ከሆነ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ አንደኛው መንገድ የሚሆነው ይህን ማስክ ማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደተነገረው የፊት ማስክ ማድረግ ያለባቸው ሰዎች የጤና ባለሙያዎች ወይም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች (ወደሌሎች እንዳያስተላልፉ በሚል ስለሆነ) አሁን ላይ በዚህ ጉዳይ የተነሳ ብዙ የፊት መሸፈኛ ጭብሎች ሊያስፈልጉ እንደሚችለ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡
ታዲያ ከዚህ ተያይዞ ሁላችንም ልብ ልንለው የሚገባው ነገር ቫይረሱ የሚተላለፍብን ብቻ ሳንሆን አኛ እራሳችን ቫይረሱን ወደሌሎች የምናስተላልፍ መሆናችንን ተረድተን ለይምሰል ያልሆነ ጥንቃቄን ማድረግ እንደሚገባን ነው፡፡ በተለይም ወጣቶች እና ታደጊዎች በቫይረሱ ከተጠቁ በኋላ የትኛውም የህመም ስሜት ሳይሰማቸው እና ምልክቶች ሳይታይባቸው ቀናትን ሊያሰቆጥሩ ይችላሉና የሚያደርጉት ጥንቃቄ ይህን ከግምት ያስገባ መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ለበለጠ፡ https://www.livescience.com/
coronavirus-asymptomatic-spread.html
ኮሮናን ለመከላከል ሲባል የሰዎችን እንቅስቃሴ መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ ጎግል አስታውቋል
========================
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከሚከላከሉ መንገዶች ውስጥ ዋነኛው ከሰዎች ጋራ ያለ ርቀርን መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ግን በሁሉም ዘንድ እኩል ሲተገበር አናየውም፡፡ ታድያ መንግስታት ዜጎቻቸው በምን ያህል የአካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ አሰለመጠበቃቸውን እንዲያውቁ በማሰብ የተጠቃሚዎቹን እንቅስቃሴ ይፋ እንደሚያደርግ ጎግል አስታውቋል፡፡ መረጃው በ131 ሀገራት ያሉ ተጠቃሚዎቹን የእንቅስቃሴ መረጃ በልዩ ድረ-ገፅ ላይ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ሰዎች መቼና የት ተገኝተው እንደነበረ ያሳያል፡፡ መረጃዎቹ ሰዎች እንደ ገበያ ማዕከል፣ ሱቅ፣ ቤቶች እና ፓርኮች ባሉ ስፍራዎች የሚያደርጉት ምልልስ በምን ያህል መጠን እንደጨመረና እንደቀነሰ በመቶኛ አስልቶ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ከሰሞኑን በፈረንሳይ ሰዎች ወደ ምግብ ቤት፣ ካፌ፣ ገበያ ማዕከላት፣ ቤተ-መዘክሮች እና መዝናኛፓርኮች ያደረጉት ጉዞ በ88 በመቶ መቀነሱን መረጃው አመላክቷል፡፡ ወደ አቅራቢያ ገበያዎች የሚደረጉት ጉዞዎች ቀድሞ በ40 በመቶ ያደጉ ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን በሰባ በመቶ ወርደዋል፡፡ በቢሮ አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም እንዲሁ በ56 በመቶ ቀንሷል፡፡
መረጃዎቹ በዓለም ዙርያ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች ባሉት የጎግል ማፕ አገልግሎት አማካኝነት የሚሰበሰብ ነው፡፡ ይህም በዓለም ላይ ካለ ማንኛውም ስርዓት በላይ የሰዎችን መረጃ አጥርቶ የሚያቀርብ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ መረጃዎቹ ግን የግንኙነት ዝርዝር፣ መገኛ እና እንቅስቃሴን የመሰሉ የግለሰቦችን ማንነት ይፋ የሚያደርጉ መረጃዎችን እንደማይሰጡ የተገለፀ ሲሆን የግለሰቦቹን ማንነት እንዳይታታወቅ የሚረዱ ስልቶችንም በግብዓትነት መያዙ ተነግሮለታል፡፡
የቻይና፣ ሲንጋፖር እና እስራኤልን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም መንግስታት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ያግዝ ዘንድ በዜጎቻቸው ላይ የኤሌክትሮኒክስ ክትትል እንዲደረግ አዘዋል፡፡ በአውሮፓና አሜሪካን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ተቋማትም የተጠቃሚዎቻቸውን ማንነት በሚሰውር መልኩ የስማርት ስልኮችን መረጃ ቫይረሱን ለመከላከል እያዋሉት ይገኛሉ፡፡ ግለሰበዊ ነፃነትን የሚጋፋ መረጃ ስብሰባን አጥብቃ የምትቃወመው ጀርመን እንኳን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚያስችል የስማርት ስልክ መተግበሪያ ወደስራ ለማስገባት እያሰበች ትገኛለች፡፡
ሆኖም ይህ አይነት አሰራር ከትችት አላመለጠም፡፡ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ይህ ዘዴ ኮሮናን ምክንያት በማድረግ አምባገነን መንግስታት የገለልተኞችን ድምፅ ለማፈን እና መንግስታዊ ስለላን ለማጠናከር እየተጠቀሙበት መሆኑን ቅሬታ እያሰሙ ናቸው፡፡ ዲሞክራሲያዊ በሚባሉ ሀገራት ዘንድም ይህ ዘዴ የሰዎችን ግለሰበዊ ነፃነት በዘላቂነት እንደሚጎዳ ተፈርቷል፡፡
ምንጭ፡ Bloomberg እና Tech Xplore
ቅዳሜ በ10 ሰዓት ይጠብቁን!!!
===================
የቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን በምዕራፍ 2 ክፍል 5 ዝግጅቱ ነገ ቅዳሜ ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ ወደ እናንተ ይደርሳል፡፡ በዚህ ሳምንቱም ፕሮግራማችን እንደወትሮው ሁሉ ከልዩ ልዩ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢኖቬሽንን የተመለከቱ ዜናዎች፣ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ትንታኔዎችቻችን ጋራ እንጠብቆታለን፡፡ ቻናሎን በ # MOE # TV ላይ በማድረግ በውብ ዝግጅቶቻችን እየተዝናኑ የሳይንስ እውቀቶን ያሳድጉ፤
በነገው መሰናዷችን
• በአብይ ፕሮግራም ውሽውሽ የሻይ ቅጠል እርሻ
• በተቋማት ታሪክ የባዮቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት
• በብላቴናት ፕሮግራም ስካቫተር ስለሰራው የኮንሶ ታዲጊ
• በቴክኖሎጂ ታሪክ ስለፕሌን እና ሌሎችም አጓጊ ዝግጅቶች አንጠብቃችኋለን
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
===================
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዚህ ቀጥሎ ባሉት የስራ መደቦች በቋሚነት አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የተቋሙን ድህረ ገፅ በመጠቀም በ Online techin.gov.et/announcement/ ላይ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡
ሌላኛው ቀውስ
==========
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመግታት ጋራ ተያይዞ ብዙ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ እየተገደዱ ይገኛሉ፡፡ ትምህርት እና ስራን ጨምሮ በብዙ ሀገራት የተለያዩ ተቋማት በጊዜያዊነት ስራቸውን አቁመው ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን ቤት የመቆየቱ ነገር እጅጉን የሚመከከር እና ቫይረሱንም ለመዋጋት ዋነኛው መፍትሄ ቢሆንም በተለያዩ ሰዎች ላይ የስነ-ልቦና ተፅዕንዖ ሊያሳድርም ይችላል፡፡ ለአንዳንድ ሰዎች ይህ ከሰዎች ጋራ መራራቅ ምግብ ካለመብላት እስከሚስተካከል ድረስ ተፅዕንዖው ጎልቶ ሊወጣ እንደሚችልም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ዓለማችን ከገባችበት የኮሮና ቀውስ ጋራ ተያይዞ በዚህ ወቅት ይህን ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥናቶችን መስራት አዳጋች ነው፡፡ ሆኖም በቅርብ የተሰራ አንድ ጥናት የአውሮፓውያኑ 2000 ከገባ በኋላ ተቀስቅሰው የነበሩትን የሳርስ፣ H1N1 ፍሉ፣ ኢቦላ እና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎችን ተከትለው በተደረጉ የለይቶ ማቆያ እርምጃዎች ወቅት የተሰሩ 24 ጥናቶችን አገላብጦ ማሳያውን ይዞ መጥቷል፡፡ በውጤቱም እራሳቸውን የለዩ አልያም ለይቶ ማቆያ ውስጥ የገቡ ብዙ ታማሚዎች የአጭር ጊዜም ሆነ ዘላቂ የአዕምሮ ጤና ጉዳት እንደገጠማቸው ሲረጋገጥ ጭንቀት፣ የስሜት መዳከም፣ የእንቅልፍ እጦት ከነዚህ የጤና ችግሮች መካከል ተገኝተውበታል፡፡ ለምሳሌ በኢንፍሉዌንዛ ወረርሺኝ ምክንያት ተለይተው እንዲቆዩ ተደርገው ከነበሩ 2760 ሰዎች መካከል 34 በመቶው ወይም 938ቱ ከፍተኛ የስነ-ልቦና መጨነቅ አጋጥሟቸዋል፡፡ ይህም በተለምዶ ከሚያጋጥመው የ12 በመቶ በአንፃራዊነት ከፍ ያለ ነው፡፡ ሌላው በአውሮፓውያኑ 2003 የሳርስ ወረርሺኝ በተከሰተበት ወቅት 549 የሆስፒታል ሰራተኞችን አካሎ የተጠና ጥናት ደግሞ፤ ተለይተው እንዲቆዩ የተደረጉ አልያም ከፍተኛ ሰጋት ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሲሰሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ከወረርሺኙ መከሰት ሶስት ዓመታት በኋላ ሲታይ ስጋት ባልነበረበት ሁኔታ ውስጥ ሲሰሩ ከቆዩት አንፃር የአልኮል ሱሰኝነታቸው ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በለይቶ ማቆያ ጊዜያት ውስጥ እንዳንድ ሁናቴዎች የሰዎችን በአዕምሮ ጤና መታወክ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ይገለፃል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የለይቶ ማቆያው ጊዜ ከ10 ቀናት ያለፈ ሲሆን፣ ስለ ለይቶ ማቆያው እፈላጊነት በቂ መረጃ ሳይሰጥ ሲቀር እንዲሁም የአስፈላጊ ቁሳቁሶች እና የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ተደራሽነት አናሳ መሆን ነው፡፡
ከለይቶ ማቆያም ባሻገር ከሰዎች ጋራ ያለው አካላዊ ርቀት እና በየጊዜው አለመገናኘትም የራሳቸው ተፅዕንዖ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በ2015 3.4 ሚሊዮን ተሳታፊዎችን አካቶ የተሰራ አንድ ጥናት ብቸኝነት የሚሰማቸው ሰዎች በ26 በመቶ ቀድሞ የመሞት ዕድል እንዳላቸው ሲያረጋግጥ ከማህበራዊ ግንኙነቶች የራቁት በ29 በመቶ በብቸኝነት የሚኖሩት ደግሞ 32 በመቶ ቀድሞ የመሞት ዕድል እንዳላቸው አሳይቷል፡፡ ታድያ በእንደዚህ አይነት የመራራቅ ወቅቶች ወትሮውንም ከዕድሜያቸው መግፋት ጋር ተያይዞ የማህበራዊ ግንኙነታቸው የቀነሱ ሰዎች እና በህክምና ሳብያ በየሆስፒታሉ አልጋ የያዙ ታማሚዎች ይበልጥ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡
ሆኖም ከላይ የተቀመጡ የጥናት ውጤቶች እንዳሉ ሆነው በነዚህ ወቅቶች የሚደረጉ ግንኙነቶች መቀነስ ሁሉንም በእኩል ይጎዳል ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዶች ከቤት ላለመውጣታቸው ምስጋና ይግባና ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ያላቸው ትስስር እንዲጠብቅና የማህበራዊ ትስስር ደረጃቸውም እንዲያድግ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በስልክና በበይነ-መረብ የሚፈጥሯቸው ትስስሮች ተጎጂነታቸውን በእጅጉ ሲቀነሰው ይታያል፡፡ መሰል ቴክኖሎጂ አመጣሽ ግንኙነት ከፍ ሲልም በርቀት የአዕምሮ ጤና ህክምናዎችን እንዲከወኑ ሊያደርጉም ይችላሉ፤ የማታ ማታ የግንባር ህክምና እንደሚያስፈልግ ቢቀመጥም፡፡
ምንጭ፡- Science News