TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
TechIn2 pinned «የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎች የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው አንዱ ፈተና ነዉ። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ምንም እንኳ ኩባንያው ምርቶቹን እያሻሻለ ቢሆንም በአሜሪካ ብዙ ክሶች ተመስርተውበታል። ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት…»
የእንግሊዘኛ ሰዋሰው(grammer) ለመረዳት እና ለመማር ሚጠቅሙ
4 ነፃ ድህረገፆች

1- EnglishGrammar.org
ይህ ድህረገፅ ለመማሪያነት የሚረዱ ቪድዎችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የእንግሊዘኛ እውቀት ላላቸው ሁሉ የሚሆኑ አጀንዳዎችን ይዳስሳል፡፡ በተጨማሪም እንግሊዘኛን በተመለከተ ያሏችሁን ጥያቄዎች ሁሉ በ ኮሜንት ባር ላይ መፃፍ የሚቻል ሲሆን በውስጥ መሰመርም መልዕክት መላክ ይቻላል፡፡

2- English Grammar Secretes
ይህ ከላይ የጠቀስነው ድህረገፅ የሌለወን ሁሉ ጨምሮ የያዘ ሲሆን ከእያንዳንዱ ትምህርት በኃላም የተማርነውን ምንለማመድበት መልመጃዎች አሉት፡፡

3- UsingEnglish.com
የተማሩትን መልሶ መለማመድ ከሚለው ሀሳብ ሳንወጣ ይህ ድህረገፅ ፕሪንት ተደርገው የሚወሰዱ በግል እራስን ማለማመጃ ጥቄዎችን ያዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር የሚማማሩበት መድረክ ያለው ሲሆን የቋንቋው ኤክስፐርቶችንም አግኝተው ጥያቄዎችን መጠየቅ የሚችሉበት አሰራር አመቻችቷል፡፡

4- Learn English by British Council
ብሪቲሽ ካውንስል በዓለም አቀፍ ደረጃ የእንግሊዘኛ እውቀትን ለማሳደግ ከሚሰሩ ተቋማት ውስጥ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ ተቋም ሰዋሰውን በ ደህረገፅ ከማስተማርም በተጨማሪ የተለያዩ ፎረሞችን እና ትምህርታዊ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት እና የእንግሊዘና ማህበረሰብ በመፍጠር እንግሊዘኛን በ ተግባር እንዲማሩ ይረዳል፡

ሼር በማድረግ ያወቁትን ያካፍሉ

ምንጭ ፡- my English Teacher.eu
በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን ?

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በሂሳብ ትምህርት ደካማ መሆናቸውን ከተፈጥሮ ጋር በማያያዝ እንደማይሻሻሉ ያስባሉ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሂሳብ የተሻሉ ለመሆን ከተሰጥኦ በላይ ጠንክሮ መስራት የመጀመሪያው መንገድ ነው፡፡ በቀላሉ በሂሳብ ትምህርት ጥሩ ለመሆን ለትምህርቱ ያለንን ያልተገባ አመለካከት በመቀየር እና ደጋግሞ በመሞከር ለውጡን ማየት እንችላለን፡፡ ስለዚህም በሂሳብ ትምህርት ጥሩ አይደለሁም ለወደፊቱም ቢሆን አይሆንልኝም ብሎ ከመደምደም ይልቅ እነዚህን ምክሮች ቢተገበሩ መልካም ነው እንላለን፡፡

1-በመጀመሪያ ስለ ሒሳብ ትምህርት አዎንታዊ አመለካከት ይኑረን

ብዙ ሰዎች ሒሳብን የሚጠሉበት ዋና ምክንያት አንሰራውም ብለው እራሳቸውን ስለሚያሳምኑ ነው፡፡ ይህም በቀላሉ ተስፋ እንዲቆረጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ነገረ ግን ስለ ትምህርቱ ያለንን መጥፎ አመለካከት ወደ ጎን በመተው አዎንታዊ አመለካከት ብናዳብር በንቃት እንደንሰራ እና ደጋግሞ ለመሞክር ሚያስችለንን ብርታት እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ ከዚህ አኳያ የሒሳብ ትምህርትን ስንማር በትኩረትና ባለመሰልቸት ቢሆን ለተሻለ ውጤት እንድንበቃ ያደርገናል፡፡ በሌላ በኩል አንዳንዶች የሚያነሱት ዲስካልኩሊያ (dyscalculia) የተሰኘው የጭንቅላት በሽታ ሰዎች ሂሳብ ትምህርት ላይ ደካማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል የሚል ነው፡፡ ሆኖም በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናች እንደሚያሳዩት በሽታው እነዲሁ ሰዎች በራሳቸው የሚፈጥሩት አልችልም ወይም አይሆንልኝም የሚል እሳቤ እንጂ መደበኛ በሽታ እንዳልሆነ ተረጋገጧል፡፡

2-ትኩረትን መሰብሰብ በሚያስችል ቦታ ማጥናት

አብዛኛውን ጊዜ ሒሳብን ስናጠና ወይም ስንሰራ ፀጥታ ያለበትና ትኩረታችን በማይበታተንበት ቦታ ቢሆን ይመረጣል፡፡ እንዲሁም በምናጠናበት ጊዜ ኢንተርኔት መጠቀም፣ ሙዚቃ መስማት እና ማስጮህ ከትኩረታችን በቀላሉ ሊያስወጣን ይችላል፡፡ እየሰማን ለመስራት ከፈለግን እንኳን የኢንስቱሩመንታል ሙዚቃዎችን ብቻ ብናደምጥ ይመከራል፡፡

3- በየቀኑ ለሒሳብ ጥቂት ጊዜ መስጠት

በሒሳብ የተሻሉ ሆኖ ለመገኘት ደጋግሞ ከመሞከር ውጭ ሌላ ሚስጥር የለም፡፡ እየሰራን ስላለነው የሂሳብ ቀመር ወይም ኢኴሽን በደንብ ፍንጭ እስክናገኝ እና እስኪገባን ድረስ ደጋግሞ መሞከር እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ እንዲሁም በቀን ውስጥ ጥቂት ጊዜ በመስጠት ምሳሌዎችን ደጋግሞ መስራት ተገቢ ነው፡፡ ይህም ሲባል ያለረፍት ለሰዓታት ማንበብ ጭንቀት ሊፈጥር ስለሚችል በቀን ውስጥ ከአነድ ሰዓት
ያልበለጠ ጊዜ መስጠት የሚመክር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በምናጠናበት ጊዜ ያሰራሩን ሂደትና አመክንዮ ለመረዳት መሞከር የተሻለ ነው፡፡ ሂሳብ በባህሪው ተከታታይ (sequential) በመሆኑ አንዴ
ፅንሰ ሃሳቡን ወይም ቀመሩን ይዘን ለመስራት ይከብዳል፤ ከዚህ ይልቅ ከቀመሩ ወይም ከኢኴሽኑ ጀርባ ያለውን አጠቃላይ ፅንሰ ሃሳብ ለመረዳት መሞከር ተመራጭ ነው፡፡

4- ለመረዳት በቸገረን ጊዜ እርዳታ መጠየቅ

ሂሳብን በምንማርበት ወይም በምናጠናበት ጊዜ ያልገባን ነገር ካለ ከመጠየቅ ወደ ኋላ ማለት የሚመከር አይደለም፡፡ ሊያስረዳኝ ይችላል ወይም ትንሽ ፍንጭ አገኝበታለሁ ብለን ያሰብነው ሰው ለመጠየቅ መፍራት የለብንም፡፡ በተለይም በትምህርት ሰዓት ከሆነ ስላልገባን ነገር ያለፍርሃት በቀጥታ መጠየቅ እጅግ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ድህረገፆች ላይ የሚሰራጩ የቀጥታ ትምህርቶችን መከታተል የሂሳብ ክህሎታችንን ለማሳደግ ይረዳናል፡፡ በሌላ በኩል ስለተረዳናት ወይም ስላወቅናት ትንሽ ነገር ካጠገባችን ላለ ሰው ብናካፍል ስለ ጉዳዩ ያለን ግንዛቤ የበለጠ እንዲጎለብትና እንዲያድግ ይረዳናል፡፡

Source; getcollegecredit
እርሶ ያወቁትን ለወዳጆ ያጋሩ፡፡
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት በአይምሯችን ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያውቀሉ?
እንቅልፍ ከምንገምተው ባላይ ለአዕምሯችን ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የእንቅልፍ መቋረጥ ችግሮች ማለትም የድካም ስሜት እና ትኩረት ማድረግ ችግር ያጋጥመናል፡፡
የአዕምሮ ኤሌክትሪካል ክዋኔ ጥናት እንደሚያመለከተው የሰው ልጅ በሚተኛበት ጊዜ አዕምሮው ሁለት ዑደቶችን ይከውናል፡፡ እነዚህም ፈጣን የዓይን እንቅስቃሴ እንቅልፍ (rapid eye movement (REM)) እና ዝግተኛ እንቅልፍ (slow-wave sleep) ናቸው፡፡
ዝግተኛ እንቅልፍ የሚፈጠረው ልክ በምሽቱ መጀመሪያ እንደተኛን አካባቢ ነው፤ ነገር ግን ምሽቱ እየገፋ ሲሄድ ወደ ፈጣን የዓይን እንቅስቃሴ እንቅልፍ እየገባን እንሄዳለን፡፡
በምንተኛ ጊዜ አዕምሯችን ምን ያደርጋል?
እንቅልፍ በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህም ውስጥ ዋነኞቹ
1. ማስታወስ፡-
እንቅልፍ በቀን ውስጥ ያደረግናቸውን ድርጊቶች እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡ በተለይ ፈጣን የዓይን እንቅስቃሴ እንቅልፍ ስሜታዊ ትውስታዎች (ለምሳሌ ፍርሀትን) ወይም የድርጊት ቅደም ተከተል ያላቸውን ትውስታዎች (እንደ ሳይክል መንዳት ያሉትን) ለማሰታወስ ይረዳል ፡፡ ዝግተኛ እንቅልፍ ደግሞ ገላጭ ትውስታዎችን ወደ አዕምሯችን ያመጣል፡፡ ማለትም ከምናውቀው እና ከእውናዊ ልምዳቸን የተቀመጡ ትውስታዎችን የምንገነዘብበት ነው፡፡ (ለምሳሌ ቁርስ ምን እንደበላን)፡፡
2. አዕምሯችን ንቁ ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ፡-
እንቅልፍ አዕምሯችን ንቁ ሆኖ እንዲቆይ የማድረግ ሀይል አለው፡፡ ጥሩ እንልፍ የሚተኙ ሰዎች ጥሩ እንቀልፍ ከማይተኙ ሰዎች በተሻለ አዕምሯአቸው ነቅቶ ነገሮች ይከታተላል፡፡
3. ለአዕምሯችን የቤት ጠባቂ ሆኖ ማገልገል፡-
በአይጦች ላይ የተጠና ጥናት እንዳመለከተው እንቅልፍ አዕምሮን በንቃት ሰዓት ከሚከማቹ እና ከሚበክሉት ነገሮች ለማፅዳት ይረዳል፡፡ እነዚህ በካዮች አንዳንዶቹ ከኒውሮዲጄነሬቲቭ (neurodegenerat
ive) በሽታዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡ በእንቅልፍ ጊዜ በአንጎል ሴሎች መካከል ክፍተቱ ስለሚሰፋ በካይ ፕሮቲኖች ታጥበው እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ እንቅልፍ እነዚህን በካዮች በማጽዳት እንደ መርሳት በሽታ (Alzheimer) ያሉትን የኒውሮዳጄነሬቲቭ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ይከላከላል፡፡
በቂ እንቅል ባናገኝ ምን ይከሰታል ?
1-ለነገሮች ትኩረት ማድረግ አለመቻል፡-
በቂ እንቅልፍ በማንተኛበት ጊዜ በትላልቅ መረጃዎች ወይም ለረጅም ሰዓት ትኩረት ማድረግ ያቅተናል፡፡
2-ለነገሮች ያለን ምላሽ የቀዘቀዘ መሆን
3- የፈጠራ አቅም መቀነስ እና ድብቅ ነገሮችን ለመፈተሽ ያለን ጉጉት እና አቅም ይቀንሳል፡፡
ጥሩ እንቅልፍ ባላገኘን ቁጥር አዕመሯችን ራሱን እንዲዘጋ በማድረግ ለተወሰነ ሴኮንድ ከንቃተ ህሊናችን ውጪ አንድንሆን እና ለተለያዩ አደጋዎች አንድንጋለጥ ያደርገናል፡፡ ድንገት መኪና እያሽከረከርን ላልታሰበ አደጋ ልንጋለጥ እንችላለን፡፡
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት በረዥም ጊዜ ምን ሊፈጥር ይችላል?
• ስኪዞፈርሬንያ (schizophrenia)
• ኦቲዝም (autism)
• የመርሳት በሽታ (Alzheimer’s) ለተባሉ የአዕምሮ በሽታ ሊያጋልጠን ይችላል፡፡
በአጠቃለይ በርካታ ጥናቶች እንዳረጋገጡት የጤናማ እንቅልፍ ሂደት ማለትም ያልበዛም ሆነ ያላነሰ ከሆነ ጤናማ እና ጥሩ ግልጋሎት ላለው አዕምሮ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
ስለ እንቅልፋችሁ ተጨንቆ ያስነበባችሁ፡- የአለም የኢኮኖሚ ፎረም (World Economic Forum)
ዉበትዎን በቤትዎ

1- ካሮት
ከ ካሮት ጥቅሞች መካከል የኮሌስትሮል መጠንን መቀነስ፣ የልብ ድካም አደጋን መቆጣጠር የተወሰኑ የ ካንሰር ዓይነቶችን መከላከል፣ የዓንን የእይታ መጠን ማጎልበት፣ እንዲሁም ያለ ዕድሜ የሚከሰቱ የእርጅና ምልክቶች እንዳይኖሩ ማድረግ የሚሉት ይካተቱበታል፡፡ ካሮት በውስጡ ጠቃሚ ቫታሚኖችን እና ፖታሺየም የተሰኘ የደም ግፊትን መቆጣጠር የሚችል ማዕድንን ይዟል፡፡ በተጨማሪም የ ካሮት ሰማንያ ስምንት በመቶ የሚሆነው ክፍል ውሃ በመሆኑ ለጤናማ ሰውነት ዓይነተኛ አማራጭ ነው፡፡
የካሮት የውበት ጥቅሞች
በካሮት ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚኖች ለቆዳ ውበት እና ጤንነት በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፡፡ ከዛም ውስጥ ጥቂቱን፡-
1- ብሩህ ቆዳ ይሰጣል
ካሮት በውስጡ ቫይታሚን ሲ ያለ በመሆኑ መርዛማ የሆኑ ውህዶችን ከሰውነታችን የማስወገድ ኃይል አለው፡፡ ስለዚህ ካሮት አብዝተን በምንመገብ ወቅት የሞቱ እንዲሁም ጤናማ ያልሆኑ ቆዳዎች ከላይችን ላይ እየተወገዱ እንዲመጡ እና ብሩህ እና አንፀባራቂ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል፡፡
ካሮትን በመፍጨት እና ከማር ጋር በመለወስ በቤት ውስጥ ለፊት እንደማስክ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለቆዳ ብሩህነት ወደር የሌለው አማራጭ ነው ሲሉ የስነ ውበት ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
2- የእርጅና ምልክቶችን ያጠፋል
የቆዳ መሸብሸብ፣ ዓይን እና ከንፈር አካባቢ መኮማተር እና የመሳሰሉት የእርጅና ምልክቶች በዕድሜ የሚመጡ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ግን ፍሪ ራዲካል የተሰኙ ጎጂ ውህዶች በሰውነታችን ውስጥ በመበራከታቸው ምክኒያት ያለ እድሜም ይታያሉ፡፡ ካሮት በውስጡ እንደ ቫይታሚን ኤ እና ሲ ያሉ ፀረ መርዛማ ውህዶች ያሉት በመሆኑ የቆዳ መሸብሸብን እና መጨማደንን በመከላከል ውጥር ያለ እና አዲስ የሆነ ቆዳ እንዲኖር ያስችላል፡፡
3- እንደ ዣንጥላ ያገለግላል
ካሮት በውስጡ ቤታ ካሮቲን የተሰኘ ንጥረ ነገር ያለ በመሆኑ ህብረህዋስን በአዲስ በመተካት አላስፈላጊ በሆኑ የፀሀይ ጨረሮች የተጎዳውን ቆዳ የመተካት በሀሪ አለው፡፡ ከዛም በተጨማሪ የቆዳን እራሱን የመከላከል አቅም( immunity) በማሳደግ በፀሀይ ጨረር የተጎዳ እና የተጠበሰ ቆዳን ያክማል፡፡ በቋሚነት የካሮት ጁስን በቤት ውስጥ እያዘጋጁ መጠቀም የሚመከር ነው፡፡

2- ኪያር
በተለምዶ አትክልት እየተባለ የሚጠራው ይህ ኪያር የተሰኘ ተክል ፍራፍሬ እንደሆነ ሰምተው ያውቃሉ? ኪያር በውስጡ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ በተጨማሪም በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የውሃ መጠን እና ዝቅተኛ የሆነ የካሎሪ መጠን ስላለው ሰውነትን ረስራሳ (hydrated) እንዲሁም ሸንቃጣ እንሚያደርግ ይታመናል፡፡
የኪያር የውበት ጥቅሞች ውስጥ ጥቂቱን፡-
1- ለሰውነት ርስራሴ(hydration)
ኪያር 95 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ውሀ ነው፡፡ ስለሆነም ሰውነታችን ውስት ሉ መርዛማ ውህዶች በመጠራረግ እና የደም ዝውውርን ጤናማ በማደረግ ለሰውነታችን በቀ የሆነን ፈሳሽ ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ ጤናማ ለሆነ ውብ የሆነ ቆዳን ይሰጣል፡፡
2- ለ ፈካ ቆዳ
አሁን አሁን ቆዳን ለማፍካት የተለያዩ የኬሚካል ይዘታቸው ከፍ ያሉ ሜካፖችን መጠቀም የተለመደ ሆኗል፡፡ ይሁንና እነዚህ ኬሚካሎች ከጊዜ በኋላ የሚፈጠጠሩት የቆዳ ችግር በቀላሉ የሚታከም አይሆንም፡፡ ኪያር ውስጡ ያለው ንጥረ ነገር ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ቆዳን ማፍካት የሚስችለው በመሆኑ በቤት ውስጥ በቀላሉ በማዘጋጀት መጠቀም ይቻላል፡፡
3- ለፀጉር እድገት እና ጤና
ኪያር በውስጡ በቂ የሆነ የ ሲልከን እና የ ሰልፈር መጠን ስላለ ጤናማ የሆነ የፀጉር እድገት እንዲኖር ይረዳል፡፡ ኪያርን በመፍጨት እና ውሃውን የራስ ቅል ውስጥ በመቀባት ከ 15-20 ደቂቃ ድረሰ አቆቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ ይመከራል፡፡

ለቀን ተቀን ህይወታችን እንት እንዴት እንጠቀማቸው?
2 የተፈቀፈቀ ካሮት፣ 1 ተለቅ ያለ ኪያር (ኪያሩን ሳንልጥ ቢሆን ይመከራል)፣ ቆራርጦ ጁስ መፍጫ ውስጥ ማድረግ ከዛ 1 ወይም 2 ብርቱካን ውስጡ መጭመቅ እስከ 4 ማንኪያ ድረስ እርጎ (እንዳስፈላጊነቱ ማካተት ካልሆነም መተው ይቻላል)ውስጡ መክተት፣ በስተመጨረሻም ሩብ ብርጭቆ ውሃ በማድርግ በደንብ መፍጨት እና መጠጣት፡፡
ማታ ሊተኙ ሲሉ አሊያም ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ይህንን ጭማቂ ሁሌም በመጠጣት የውበትም የጤናም ተጠቃሚ ይሆናሉ ያለችን editorialnatualbeauty ናት፡፡
ምንጭ healthline, organicfact እና editorialnatualbeauty
ያወቅነውን ማሳወቅ ቅንነት ነው፡፡
ረጋ ዘይት እስከሁን?

በሚረጋ ዘይት ውስጥ ያለው የተከማቸ ስብ አላስፈላጊ ለሆነ ክብደት መጨመር እና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳቶች ከመዳረጉም በላይ ኒውክለስ አኩንቢን የተባለው የአዕምሯችን ክፍል ውስጥ ብግነት( inflammation) እንዲፈጠር ምክኒያት እንደሚሆን የሰሞኑ የ ሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመለከተ፡፡

ኒውክለስ አኩንቢን በአዕምሯችን ውስጥ የሚገኝ ክፍል ሲሆን ተግባሩ ስሜታችን፣ እና ሁኔታችንን መቆጣጠር ነው፡፡ እናም የዚህ የአዕምሮ ክፍል መጎዳት አሊያም መቆጣት አዕምሯችን ስሜታችን ላይ ያለውን ቁጥጥር እንዲያጣ እና ግለሰቡ ለጭንቀት እና ለውጥረት እንዲዳረግ ከማረጉም በላይ የሰውነትን የኬሚካል ዑደት ይረብሸዋል፡፡

በሞንትሪያል ዩኒቨርስቲ ውስጥ በ አይጥ ላይ በተደረገው ጥናትም የረጋ ዘይት (palm oil ) ይህንን ቀውስ ሊያስከትከል እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡ በተመሳሳይ እዛው አይጦቹ ላይ የተሞከረው ሌላኛው (monounsaturated fat)የተሰኘው የዘይት ዓይነት ማለትም ከ ኦሊቭ ፍሬ የምናገኘው ዘይት በ አይጦቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሲያደርስ አልታይም፡፡

አጥኚዎቹ እንደገለጡት ከሆነ ይህንን ዘይት ከተጠቀሙ በኋላ በሰውነት ላይ የታየው የኬሚካል ዑደት መረበሽ ልክ የስኳር በሽተኛ ሰውነት ውስጥ እንደሚከሰተው ዓይነት ነው፡፡ ማለትም የቅድመ ስኳር በሽታ ምልቶች ሁሉ ይታያሉ እንደማለት ነው፡፡

ብዙ ጥናቶች እንደዚህ ያለ ዘይት የማይመገቡ ህዝቦች የሚኖሩበት አከባቢ የ ድብርት እና ጭንቀት በሽታዎች ያን ያህል እንደማይታዩ ያሳዩ ሲሆን በዚህ ጥናት ደግሞ በውፍረት በሽታ(obesity) እና በ ዱባቴ (depression) መሀከል ያለው ትስስር ሊታወቅ ችሏል፡፡

በሰውነት ውስጥ የሚኖር የአላስገላጊ ስብ ክምችት እና የውፍረት መጨመር መንስዔ ከዚህ ከታጨቀ ዘይት አመጋገብ (saturated fat) ጋር የሚገናኝ በመሆኑ እና ይህ የዘይት ዓይነት ደግሞ በአዕምሮ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ለጭንቀት እና ለ ውጥረት እንዲሁም ለመደበት ስለሚዳግ በውፍረት እና በ መደበት መካከል ተያያዠ ችግር ሊፈጠር ችሏል፡፡

ጥናቱ ብዙ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የያዘ ቢሆንም ስቲክ ኢትዮጲያ ግን ለዛሬ ብታውቁት እና ብታሰምሩበት ያለውን የረጋ ዘይት ጉዳት እንካችሁ ብሏል፡፡
በስተመጨረሻም የሰው ልጅ የሚበላውን ነውና ወደ ሰውነታችን ስለሚገቡ ነገሮች ሁሉ ጠንቃቃ እይታ ይኑረን እያለ መልም ቀን ይመኝላችኋል፡፡
ምንጭ፡- sciencedaily

መረጃው ጠቃሚ ነውና እናካፍል፡፡
ዛሬ በታሪክ ውስጥ
ልክ በዛሬው እለት 1929 ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያንን በ ሙስታርድ ጋዝ ጨረሶ ነበር፡፡
ለመሆኑ ሙስታርድ ጋዝ ምንድነው?
ሙስታርድ ጋዝ ወይም ሰልፈር ሙስታርድ (Cl-CH2CH2)2S በጋዝ ደረጃ ከለር የሌለው ነገር ግን በሌላ ደረጃ ደማቅ ቢጫ ወይም ጎመኔ ከለር ያለው ኬሚካል ነው፡፡
ሙስታርድ ጋዝ በቆዳ፣ በአይን እና በእስትንፋስ ላይ ችግር የሚፈጥር ጋዝ ነው፡፡ ሙስታርድ ጋዝ በትንፋሽ፣ እንዲሁም በዓይን እና በሰውነት ንክኪ ወደ ሰውነታችን በቀላሉ ሊገባ ይችላል፡፡
ሙስታርድ ጋዝ ወደ ሰውነትችን ከገባ እነዚህን ጉዳቶች ይፈጥራል
• ዓይናችን፡- ቀይ መሆን፣ ማቃጠል፣ መጉረብረብ፣ መመረዝ እና አስከ መጥፋት ድረስ ሊፈጠርበት ይችላል
• ቆዳችን፡- እከክ የሚመስል ቀይ መሆን እናም ከዛ በኋላ ወደ ቢጫ ውሀ መቋጠር ይቀየራል
• የመተንፈሻ አካለችን ላይ ፡- ማስነጠስ፣ ማሳል፣ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ፣ የጉሮሮ መጎርነን፣ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የአስም በሽታ መፈጠር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡
• የምግብ መፈጨት ሥርዓታችን ላይ ፡- የሆድ ህመም፣ ማስመለስ፣ ማስቀመጥ፣ ትኩሳት እና ማቅለሽለሽ ያጋጥመዋል
ከዚህ በተጨማሪ ሙስታርድ ጋዝ የሰው ልጆችን ዲ.ኤን.ኤ( DNA) በመጉዳት ለተለያዩ ካንሰሮች የመጋለጥ ዕድላቸውን ይጨምራል፡፡
ለሙስታርድ ጋዝ የተጋለጡ እርጉዝ ሴቶች ጉዳት የተፈጠረበት ልጅ ወይም በካንሰር የተጠቃ ልጅ የመውለድ እድላቸው የጎላ ነው፡፡
ሙስታርድ ጋዝ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሲሆን እ.ኤ.አ በ1993 የተባበሩት መንግስታት የኬሚካል የጦር መሳሪያ ኮንቬንሽን የሙስታረድ ጋዝንና የሌሎች የኬሚካል መሳሪያዎችን በጦረነት ላይ መጠቀም አግዷል፡፡
ከብር ለሀገራቸው ብለው በየካቲት 12 /1929 በሙስታርድ ጋዝ ላለቁት ወገኖቻችን፡፡
ለወገኖቻቸን ክብር ይህን ማስታወሻ ሼር እናድርግ፡፡
የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የጡት ሕዋሳት ዕድገት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ በጽሽታ የሚጠቁት ሴቶች ቢሆኑም በወንዶች ላይም የመከሰት ዕድል አለው፡፡

የጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የመከሰት ሰፊ ዕድል አለው፡፡ የካንሰር ሕዋሳት ቀድሞ የሚሰራጨው ብብታችን ስር ወደ ሚገኘው አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የጡት ካንሰር ቅድሚያ ካልተደረሰበትና ሕክምና ካላገኘ ወደ ጉበት እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል በሽታ ነው፡፡

የጡት ካንሰር መንስዔዎች

የጡት ካንሰር መነሻ መንስዔዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለሕመሙ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች በከፊል እንደሚከተለው ቀርበዋል

• ዕድሜ፡- በጡት ካንሰር የመጠቃት ዕድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት የሕይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
• በዘር፡- ይህ የካንሰር ዓይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንሰር ሕመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
• ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ሕመም የነበረባቸው
• በቶሎ ልጅ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
• ጡት ያለማጥባት
• ደረታቸው ለብዙ ጊዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
• ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
• ሲጋራ ማጨስ

የጡት ካንሰር ሕመም ምልክቶች

1. በጡት ላይና በአካባቢው የሚወጣ እባጭ፡- አብዛኛውን ጊዜ የጡት ካንሰር ሕመም ምልክት የሚሆነው ሕመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር ዓይነት ሊሆን ይችላል፡፡ ነግር ግን ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

2. የጡት መጠንና ቅርጽ መለያየት፡- አንዱን ጡት ከሌላኛው ጡት ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ሕክምና በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት

4. የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ፡- ይህ ዓይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሯዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም፡፡

5. የሕመም ስሜት፡- አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የሕመም ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ሕመም በአብዛኛው የካንሰር ሕመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡

የማይሞት መረጃ ስለሆነ ተጠቅመን ሌሎችን ለመጥቀም እንትጋ፡፡ ሼር
ምን ጊዜዎትን በመቀመጥ ያሳልፋሉ?
አብዝቶ መቀመጥ ለአእምሯችንለምንድነው አደገኛ የሚሆነው?

በብዙ የህይወት መንገዶች አእምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን እናዘወትራለን፡፡ በቅርቡ በወጣ ጥናት ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የአእምሮ ነዳጅ (brain’s fuel) አቅርቦት ላይ ተጽኖ ከማሳደር ባሻገር በአእምሮም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡
አእምሯችን ጉሉኮስ የተራበ አካል ነው፡፡ ምንም አንኳ የሰውነታችንን ክብደት 2% ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም 20% የኛን ሀይል/ኢነርጂ የሚጠቀመው እርሱ ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ በአብዛኛው የመጀመሪ ደረጃ የአዕምሮ ነዳጅ በሆነው ጉሉኮስ መልክ የሚገኝ ነው፡፡ የዚህ ሀይል ስርጭት ከተቋረጠ የአዕምሯችንን ሴሎች ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ የጉሉኮስ በበቂ ደረጃ መኖር ከአይምሮ ጤንነት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡
አይሞሯችን ለከፍተኛ ጉሉኮስ መጠንም ይሁን ለአነሰተኛ ጉሉኮስ መጋለጥ ( dementia) ዲሜንሺያ ለተሰኘው ህመም የመጋለጥ አደጋን ይጨምርበታል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በተገቢው መንገድ ጉሉኮስን መቆጣጠር ለአእምሮ ጤና እጅግ አስፈላጊ አስፈላጊመሆኑን ነው፡፡
አብዝቶ መቀመጥ ከሚያመጠው የጤና እክል ውስጥ፡-
• በለጋ ዕድሜ ለሞት የመጋለጥ (early death) አደጋን ከፍ ያደርገወል
በግምት 60-75 መጠነኛ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ በቀን ስምንት ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣን በለጋ አድሜ ለሞት የመጋለጥ አደጋን ለማጥፋት ይረዳል፡፡
• አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መጠንን በማዛባት ለአእምሮ ጤና ችግር ያጋልጥል
አብዘኛው ጥናቶች መቀመጥ በመቀነስ በተወሰነ መጠን መራመድ ከምግብ በኋላ ጉሉኮስ መጠንን ይቆጣጠራል፡፡
• አብዝቶ መቀመጥ በአእምሯችን የደም ስርጭትን ሊቀንስ ይችላል
ከመቀመጥ ይልቅ መራመድ በአእምሯችን የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ይረዳል፡፡ የአእምሮ የደም ዝውውር ለአእምሮ የሚቀርበውን የጉልኮስ መጠን በመቆጣጠር አእምሮ ጤና ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል፡፡ በአእምሮ የደም ዝውውር መቀነስ የአእምሮ ስራ በፍጥነት እንዲቀንስ የማድረግ እና ከመርሳት በሽታ (Alzheimer’s disease) ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡
ስለዚህ ምን እናድርግ ካለችሁን
አብዝቶ መቀመጥ ስለሚያመጣው የአእምሮ ጤና ጉደት ሁሉንም የሚያስማማ አንድ የሆነ ጥናት ባይኖርም አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መቆጣጠር መጠን በመቀነስ የአእምሮ ጤናችን ላይ እክል ስለሚፈጥር
• ከምግብ በኋላ የመቀመጥ መጠናችንን ብንቀንስ መልካም ነ
• ከምሳ በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ
• ከራት በኋላ በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረግ(ለምሳሌ፡- የተበላበትን እቃ በማጠብ ሊሆን ይችላል)
• ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይም ከስራ በኋላ በእግር መጓዝ
የምንቀመጥበትን ሰዓት በመቀነስ የአዕምሯችንም ሆነ የአካላችንን ጤና እናስጠብቅ፡፡ ሼር ማድረግ አይዘንጉ፡፡
ምንጭ፡- የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ከ the Conversation ጋር በጋራ
ትኩስ ሻይ መጠጣት ለምግብ ቧንቧ ካንሰር ያጋልጣል

በ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ፊዚሻን የወጣው ጥናት እንሚያሳየው ትኩስ ሻሂ የሚጠቀሙ በጨማሪም ሲጋራ የሚያጨሱና አልኮል የመጠጡ ሰዎች በ ጎሮሮ ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ረዥም ጊዜ የፈጀው ይህ ጥናት አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ተሳፊዎች ነበሩት፡፡

የጎሮሮ ካንሰር በአብዘኃኛው የታዳጊ አገራት ሰዎችን በተለይም ወንዶችን የሚያጠቃ በሽታ እንደሆነ የከዚህ በፊት ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ቻይና ከፍተኛ የ ጎሮሮ ካንሰር የሚያጠቃቸው ሰዎች የሚበዙባት አገር ስትሆን ከጊዜ ወደጊዜም ይህ በሽታ በአገሪቷ ውስጥ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በጥናቱም 450 ሺህ የሚጠጉ እድሜቸው ከ 30 – 70 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ጥናቱን ለማጠናቀቅ 9 ዓመት ገደማ ፈጅቷል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ 3ቱ በሃሪ ያላቸው ማለትም አልኮል የሚጠቀሙ ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ እና ትኩስ ሻሂ የሚጠጡ ሰዎች 3ቱ በሃሪ ከሌለባቸው ሰዎች ይልቅ በ አምስት እጥፍ በጎሮሮ ካንሰር የመያዝ እድል ኖሯቸዋል፡፡ አጥኚዎቹ እንዳሉት ከሆነ የሲጋራ እና የመጠጥ ኬሚካሎች ከትኩስ ሻሂ እንፋሎት ጋር የሚኖራቸው ውህድ ለጎሮሮ ጤናማ ሁኔታን አይፈጥርም፡፡

በመጨረሻም ሳይንቲስቶቹ አልኮል የሚጠቀሙ እና ሲጋራ የሚያጨሱ ግለሰቦች ትኩስ ሻሂ ከመጠጣት ቢታቀቡ በጎሮሮ ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስ ጠቁመዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ትኩስ ሻይ መጠቀም ለብቻው ለጎሮሮ ካንሰር አያጋልጥም፡፡ አልኮሆል እና ሲጋራ እስካልተጨመረበት ድረስ፡፡ ሼር

ምንጭ ፡-sciencedaily and others
በቀን ምን ያህል ጨው መውሰድ ይኖርብናል?

ይህ ጥያቄ በየጊዜው የሚነሳ እና ሳይንቲስቶችን የሚያጨቃጭቅ አጀንዳ ነው፡፡ ጨው 40 በመቶ ሶዲየም እና 60 በመቶ ክሎሪን ሲሆን 100 በመቶ ደግሞ ጣፋጭ ነው!!

ሰው ለመኖር ምን ያህል ጨው መውሰድ አለበት ሲባል ምን ያህል ሶዲያም መውሰድ አለበት እንደማለት ነው፡፡ በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የ global public health ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ፖል ዌልተን ከ ሊቭ ሳይንስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጡት ከሆነ ሶዲየም በ ሴሎች በስተውጪ የሚገኝ እጅግ ጠቃሚ ኤሌክትሮላይት ነው፡፡

ኤሌክትሮላይቶች ማለት በጣም ጥቃቅን የሆኑ ንጥረ-ነገሮች ሲሆኑ በውሃ ውስጥ በመዋሃድ ፖዘቲቭ ወይንም ኔጌቲቭ የሆኑ ኤሌክትሪኮች ያመነጫሉ፡፡ የእነዚህ ንጥረ ነገሮች በተመጣጣኝ ሁኔታ መኖር ጤናችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ የደም ግፊት፣ የነርቮች ጤናም ሆነ የጡንቻዎች በተገቢው ሁኔታ መስራት ከእነዚህ ኤሌክትሮላይቶች ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡

ይሁንና አሜሪካን ውስጥ በተጠናው ጥናት መሰረት አሜሪካዊያን ከተገቢው በላይ ሶዲየም እንደሚጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ አንድ አሜሪካዊ ሊወስደው የሚገባው የሶዲየም መጠን በቀን በአማካኝ 2300 ሚሊገራም ሆኖ ሳለ ጥናቶች የሚያሳዩት እስከ 3400 ሚሊገራም ድረስ እንደሚጠቀሙ ነው፡፡

እንደዚህ ያለ የበዛ የጨው አጠቃቀም ለ ደም ግፊት እና ለድንገተኛ የልብ ድካም እንደሚያጋልጥ የተለያዩ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡

ስለዚህ ለመኖር በቀን ምን ያህል ጨው ብንመገብ ይበቃል?
ዶ/ር ፖል እንደተናገሩት ከሆነ አንድ አሜሪካዊ በ ቀን ውስጥ 1500 ሚሊ ግራም ጨው ቢመገብ ይበቃዋል ብለዋል፡፡ ይህ መጠን ማለት የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች የመጨረሻው በቀን ውስጥ ሊመገቡት የሚችሉት የጨው መጠን ማለት ነው፡፡ ወይንም Center for Disease Control and Prevention (CDC) ከ 3 አመት በታች ያለ ህፃን ልጅ ሊመገበው የሚገባው የጨው መጠን ብሎ ካስቀመጠው የጨው መጠን ጋር እኩል እንደማለት ነው፡፡

እንደ American Heart Association (AHA) ያሉ ተቋሞች ደግሞ እንደውም ከዚህ በጣም ያነሰ ቢሆን ጥሩ ነው ይላሉ ፡፡ ማለትም 500 ሚሊገራም እና ከዛ በታች፡፡ ማለትም ሩብ የሻሂ ማንኪያ ጨው እንደማለት ነው፡፡

እንዲህ ያለው የጨው አጠቃቀም አንደ አሜሪካን ላሉ በፋብሪካ ውስጥ ፕሮሰስ ተደርጎ የወጣን ምግብ ለሚመገቡ አገራት እጅግ በጣም ሩቅ ሊሆን የማይችል ዓይነት ምክር ነው፡፡ ምክኒያቱም አንድ አሜሪካዊ በቀን ይመገበዋል ከተባለው የሶዲየም መጠን ማለትም (3400 ሚሊግራም) 71 በመቶ የሚሆነው የሚመጣው ከእነዚህ በፋብሪካ ፕሮሰስድ ሁነው ከሚመጡት ምግቦች ነው፡፡

ስለዚህ ከእንደዚህ ያለ ነገር እራስን ለመታደግ ተፈጥሯዊ የሆኑትን ምግቦች በቤት ውስጥ እያዘጋጁ መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡

በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ ሰዎች ሊኖራቸው ከሚገባ ያነሰ የሶዲየም መጠን ይኖራቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ሶዲየሞች ከሰውነታቸው በፍጥነት ስለሚወገድ እና የወጣው ደግሞ ስለማይተካ ነው፡፡

ይህ የሶዲየሞች ሙሉ ለሙሉ በውሃ ውስጥ ቀልጦ መጥፋት እና ከሰውነት መወገድ የመድከም፣ የተደጋጋሚ እራስ ምታት እና አንዳንዴም ለህይወት አስጊ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ይህ ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በተለይም ሯጮች ላይ ይከሰታል፡፡ ለዛም መፍትሄው sport drinks የተሰኙ ተጨማሪ ኤሌክትሮላይቶችን የያዙ ፈሳሾቸን መጠጣት ነው፡፤
የምንመገበው ስለኛ ብዙ ያወራል፡፡

ወደ ውስጣችን ስለሚገባው ሁሉ ግድ ይኑረን፡፡ ሼር

ምንጭ፡- Live Science