TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በፍቅር ውስጥ ኖት? እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?
ሳይንሳዊ ማረጋገጫዎች
የግንኙነቶች ጅማሬ ሁሌም ግራ ያጋባል፡፡ ስለ ሁለተኛው ሰው የሚሰማን ስሜት ዘላቂ ይሁን ጊዜያዊ፣ ፍቅር ይሁን ስበት እንዲሁም ተጨባጭ ይሁን ምናብ ለማወቅ እጅግ እንቸገራለን፡፡
ይሁንና ለእነዚህ ጥያቄዎች የምንሰጠው ምላሽ የወደፊት ህይወታችንን መልክ ቅርፅ የሚያስይዘው እውነት ነው፡፡
በቅርብ ጊዜ የወጣው ጥናት ስለዚህ የሚለው አለው፡፡ እየተሰማን ያለው ስሜት ፍቅር እንደሆነ ለማረጋገጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እውነቶች በማመሳከር ማወቅ ይቻላል ይላል ብሏል፡፡
1- በድንገት እራስዎን እንግዳ በሆነ ልማድ ውስጥ አጊኝተውት ይሆን?
በJournal of Personality and Social Psychology በ ፓሪስ ለህትመት የበቃው ጥናት እንዳሳየው ከሆነ ሰዎች በፍቅር ውስጥ ሲሆኑ ከልማዳቸው ወጣ ብለው በአዳዲስ ፍላጎቶች እና ተግባራት ውስጥ ሲዘፈቁ ይስተዋላሉ፡፡ በፍቅር ውስጥ የሆኑ ሰዎች የተሸለ የግል ብቃት እድገት እና ብዝሃነት እንደተስተዋለባቸው ጥናቱ አክሎ ገልጧል፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ምናልባትም የሚያፈቅሩትን ሰው ፍላጎት እና ተግባር የመጋራት በሃሪ ስለሚኖርባቸው ይሆናል፡፡
2- በተለየ ሁኔታ ውጥረት ይሰማዎታል?
በፍቅር ውስጥ መሆን ደስታ እንዳለው ሁሉ ጭንቀትም አለው፡፡ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በፍቅር ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ኮርቲሶል የተሰኘው እና ለጭንቀታችን ምክኒያት የሆነው ሆርሞን በሰውነታችን ውስጥ ይለቀቃል፡፡ ስለዚህ አፍቃሪ የሆነ ሰው የማያውቀው ውጥረት እና ሃሳብ ውስጥ የመዘፈቅ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክኒያት ምናልባትም ከዚህ በፊት ካተሰጠው የጎደረ የፍቅር ስሜት ጋር ተያያዥነት ይኖረዋል ያሉት Hormonal changes when falling in love የሚለውን ጥናት ያከናወኑት ሳይኮ ኒውሮሎጂሰቶቹ ማራዚቲ እና ካኔል ናቸው፡፡
3- ከዚህ ሰው ጋር የመሆን ጉጉቶ እንዴት ነው?
ከዘፈቀደ ጉድገኝት ወደ ፍቅር ሲሸጋገሩ አዕምሮ ውስጥ የሚካሄድ ታላቅ የኬሚካል ለውጥ አለ፡፡ ማስረጃዎች እንደሚሳዩት ከሆነ በፍቅር የመጀመሪያ ሰሞን ዶፓሚን ሪች ኤሪያስ የሚባለው የአእምሮ ክፍል መነቃቃትን ያሳያል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ያሰው(አፍቃሪው) ይበልጡን በሌላኛው(በተፈቃሪው ) ሰው ላይ የሚኖረው ተጣብቆ እየጨመረ ይመጣል ሲል ያስነበበው በJournal of Comparative Neurology, ላይ የወጣው ጥናት ነው፡፡
4- ….. ይቀጥላል….. ሼር
ምንጭ፡- PSYCHOLOGY TODAY
ከመጠን ያለፈ ውፍረት

የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከ 1975 ዓ.ም ጀምሮ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በ 3 እጥፍ እያደገ መጥቷል፡፡

በ 2016 ፣ 650ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከመጠን ባለፈ ውፍረት ተጠቂ የነበሩ ሲሆን ከዛ ውስጥ 41ሚሊዮን የሚሆኑት ከ 5 ዓመት በታች የነበሩ ሲሆን 340ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከ 5 እስከ 19 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ነበሩ፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት አንድ ግለሰብ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ተጠቂ ነው(obese) ነው የምንለው BMI ዩ 30 እና ከዛ በላይ ሲሆን ነው፡፡ (BMI= ኪሎ/ ቁመት *ቁመት)

የዚህ ሁኔታ አስጊነት ያሳሰባቸው የ Friedman School of Nutrition Science and Policy at Tufts University ተመራማሪዎች በቅርቡ ባወጡት ጥናት መሰረት ዓለምን በዚህ ሁኔታ ስጋት ውስጥ የከተታት እና ለበርካቶች ህልፈት ተጠያቂ የሆነውን ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለመዋጋት የ መንግስት ፖሊሲ እርዳታ የማያዳግም አማራጭ ነው ብለዋል፡፡

ተመራማሪቹ በጥናታቸው ውስጥ እንዳሰፈሩት ከሆነ ህፃናት ያሉበት አከባቢ የታሸጉ ጣፋጭ ለስላሳዎች እና ምግቦች የማይሸጡበት እና በምትኩ ፍራፍሬ እና አትክልቶች የሚቀርቡበት ሁኔታ ቢመቻች ይህንን ገዳይ በሽታ ልንቋቋመው ይቻለናል ብለዋል፡፡

ጥናቱ እንዳመላከተው ከሆነ በትምህርትቤቶች ውስጥ ነፃ የሆነ የፍራፍሬ እና የአትክልት እደላ ቢካሄድ ከ 1 እስከ 2 ዓመት ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፡-

• የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እነዚህን ምግቦች የመመገብ ልምድ 17 በመቶ የሚያዳብሩ ሲሆን
• መሀል ላይ ያሉት ማለትም ከ( 7-9ኛ ክፍል) የሚገኙት 22 በመቶ ያዳብራሉ
• የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ 25 በመቶ እነኚህን ጤናማ ምግቦች የመመገብ በጎ በሃሪ ይላመዳሉ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የጣፋጭ ለስላሳ መጠጦች ክልከላ ፖሊሲ ተግባራዊ ቢሆን ደግሞ በ ተማሪዎቹ የ BMI ውጤት እና ስኳር የመውሰድ ልምዳቸው እንደሚከተለው ለውጥ ያመጣል ብለዋል፡-

• የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ስኳር የመውሰድ መጠን በ 27 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን የ BMI ልኬታቸው ደግሞ በ 7 በመቶ ይቀንሳል
• ከ( 7-9ኛ ክፍል) የሚገኙት ተማሪዎች ስኳር የመውሰድ መጠን 19 በመቶ ሲሆን የ BMI ልኬታቸው ደግሞ በ 5በመቶ ይቀንሳል
• የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስኳር የመውሰድ መጠን 15 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን የ BMI ልኬታቸው ደግሞ በ 5 በመቶ ይቐንሳል ብለዋል፡፡

ህፃናት የወደፊት ዓለም ተስፋዎች ከመሆናቸውም በላይ የወደፊት መልካችንን ቅርፅ የመለወጥ እምቅ ሃይል አላቸው ያሉት ተመራማሪዎች መንግስታት ፖሊሲዎችን ዳግም መዳሰስ ከቻሉ የብዙ ችግሮችን መፍትሄ ለማጣት የትም መሄድ አይጠበቅብንም ብለዋል፡፡ሼር

ምንጭ፡- ScienceDaily
ማጨስ ጡት የማጥባት ልምድን ይጎዳል
በተመራማሪዎች የተገኘ ጥናት እንደሚያሳየዉ በቤታቸዉ ለሲጋራ ማጨስ የተጋለጡ አዳዲስ እናቶች ከሌሎች ለሲጋራ ማጨስ ካልተጋለጡ ሴቶች ጋር ስነጻጸሩ ጡት ማጥባትን ቶሎ ያቆማሉ፡፡
ይህ በሆንግ ኮንግ የተጠና ጥናት ዉስጥ ከአራት ትላልቅ ሆስፕታሎች የተሰባሰቡ ከ1200 በላይ የሆኑ ሴቶች የተሳተፉ መሆኑንና ጥናቱ ለእናቶችና ለልጆች ጤና ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን የኦካናጋን ትምህርት ቤት የነርስ ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ማሬ ታራንት አብራርቷል፡፡
ታራንት እንዳሉት የሚያጭስ ቤተሰብ አባል በመሆን ብቻ ማለትም ከቤተሰብ አባላት መካከል አባት፣ እናት ወይም ሌላ የቤተሰብ አባል የሚያጭስ ከሆኔ ልጆች ጡት የሚያጠቡበት ግዜ እንደሚቀንስ የጥናቱ ዉጤት እንደሚያሳይ ተናግሯል፡፡ በእርግጥ የሚያጨሱ ሰዎች ቤት ዉስጥ በበዙ ቁጥር የጡት ማጥባት ግዜ ይቀንሳል፡፡
ታራንት እንዳሉት በሆንግ ኮንግ የቤተሰብ አባላት የሚያጭስ ከሆነ የጡት ማጥባትን ግዜ እንደሚጎዳ ያሳየ የመጀመርያ ጥናት ነዉ ብሏል፡፡ በሆንግ ኮንግ አራት ከመቶ (4%) የሚሆኑ ሴቶችና አስራ ስምንት ከመቶ (18%) ወንዶች ያጨሳሉ፡፡
ኒኮቲን (Nicotine) ወደ ልጅ የሚተላለፈዉ በጡት ወተት ሲሆን እንደ የታራንት አስተያይት ይህ የጡት ወተት መጠን ልቀንስ ይችላል፡፡
ጥናቱ እንደሚያሳዉ የሚያጭሱ የእናት አጋሮች ጡት ማጥባት የማቆም ዉሳኔ የሚጎዳ ነወ፡፡ የጥናቱ ዋና አላማ ሴቶችና የቤተሰቦቻቸዉ አባላት ለአዳድስ እናቶች ከእርግዝና በፊት ጀምሮ ጡት ማጥባት እስከሚያቆሙ ድረስ ማጨስ ብፈልጉ እንኳን ማቋረጥ እንዳለባቸዉ ለመምከር ነዉ፡፡
ህፃናት ባሉበት አካባቢ ወይም ቦታ ሲጋራ ማጨስ የመተንፈሻ አካላታቸዉን የሚጎዳ እና ሌሎች የመተንፈሻ ችግሮች የሚያመጣባቸዉ መሆኑን እናዉቃለን በማለት ታራንት ጨምሮ ተናግሯል፡፡ ሼር
ምንጭ፡ Science daily
ህጻናት ስለደስታ የሚያስተምሩን 10 ነገሮች
1- ውስጣቸውን የተሸለ ያዳምጣሉ፡- ሀፃናት ስለ ውሳኔያቸው ትክከለኝነት ሲጨነቁ የሚያባክኑት ጊዜ የላቸውም ፡፡
2- አሁንን ይኖራሉ፡- እነርሱ ስለትናነት እያስታወሱ በትዝታ ውስጥ የሚማስኑ ፍጡች ካመሆናቸው በላይ ስለወደፊትም በምንም መልኩ አያስቡም፡፡
3- ያምናሉ፡- ህፃናት ማንኛው የተነገራቸውን ነገር የሚያምኑ ሲሆኑ በነሱ አዕምሮ ውስጥ ላይሆን ይችላል የሚል የጥረውጣሬ መንፈስ አይከሰትም፡፡ ምንም እንኳ ትናነት የተነገራቸው ነገር ዛሬ ላይ ባይከሰትም እንኳ እነርሱ ከማመን ሰንፈው አያውቁም፡፡
4- ሰራተኞች ናቸው፡- ህፃናት ሁሌም በስራ ላይ ናቸው ይቆርጣሉ፣ ይቀባሉ፣ ይስላሉ፣ ያቦካሉ ፣ያጣብቃሉ ፡፡ ህጻናት ከልባቸው ታትረው ይለፋሉ፡፡
5- ይጨፍራሉ፡- "ማንም ሰው እያያቹ እንዳልሆነ አስባችሁ ጨፍሩ " የሚለውን ንግግር ያውቁታል? አዎ ህፃናት እንደዚያ ናቸው፡፡ ማንም አጠገባቸው ቢኖር እነርሱ በራሳቸው መንገድ የራሳቸውን የነፃነት ጭፈራ በሙሉ ደስታ ይጨፍራሉ፡፡
6- ይዘፍናሉ፡- ህፃናት በየትኛውም ሰዓት ይዘፍናሉ፡፡ እየታጠቡ ፣ እየተራመዱ ፣ እየተኙም በእንቅልፍ ልብ ሳይቀር ህፃናት ከመዝፈን ወደ ኋላ አይሉም፡፡
7- ማለት የሚፈልጉትን ሁሉ ይላሉ፡- ህፃናት አዕምሯቸው ውስጥ ተከስቶ የማይተነፍሱት ነገር የለም ምናልባት ረስተውት ካልሆነ፡፡ በልባቸው ውስጥ አስቀምጠው የሚታመሙበት ጉዳይ የለም፡፡ ምናልባት አዋቂዎች እንዲህ የሚያደርጉት ለፋሲካ ዋዜማ ከጠጡ ብቻ ነው፡፡
8- ጉጉ ናቸው፡- ህፃናት በጣም ይጓጓሉ፡፡ ሆኖም ሰዓትን የመለየት ችግር ስላለባቸው ወደፊት ምን ያህል እንደሚርቅ አዕምሯቸው መቀመር አይችልም፤ ስለዚህ ልደታቸው እንደቀረበ ከሳምንት እና ከወር በፊት መናገር ለወላጆች እራስ ላይ ጦርነት እንደ ማወጅ ነው፡፡
9- አዲስ ይሁን አይሁን ግድ አይሰጣቸውም፡- ህፃናት ይመቻቸው እንጂ ፊልሙን በየቀኑ አይተውት ይሁን አይሁን አያስጨንቃቸውም፡፡ ይውደዱት እንጂ ያንን ቀሚስ በየቀኑ መልበስ ይፈልጋሉ ፡፡ ያ የወደዱትን ተረትም ቢሆን በየቀኑ መስማት ያስደስታቻል፡፡ ትልልቅ ሰዎች ግን እንደዚያ አይደሉም ፤ሁሌም አዲስ እና የመጀመሪያ ነገሮችን ብቻ የሚፈልጉ ሲሆኑ ይህ በሃሪያቸው ህይወትን ቶሎ እንዲሰለቿት ያደርጋቸዋል፡፡
10- ይቀበላሉ፡- እነርሱ በሰዎች መሃለል ስላለው ልዩነት የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ የተማረ እና ያልተማረ ደሃ እና ሃብታም ልዩነት የለውም ህጻናት ከሁሉም ጋር እኩል ሊጫወቱም ሆነ ሁሉማ ላይ እኩል ሊጮሁ ይችላሉ፡፡ ለዛም ነው የህጻ ናት ስድብ "ልጅነት " የሚል በጎ ስያሜ የኖረው፡፡
(መረጃዉን ለወዳጆቾ ፎርዋርድ ማድረጎን አይርሱ)
ምንጭ፡-huffpost
ንዴቶን መቆጣጠር ይፈልጋሉ?
ንዴት ማለት የስሜት መረበሽ ተቀጣጣይ ውጤት ነው፡፡ በንዴት ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቀው ሳይኮሎጂስቱ ዶ/ር ቻርለስ ሰፒልበርገር እንዳለው ከሆነ እንደሌሎቹ ስሜቶች ሁሉ ንዴትም በተናዳጁ ላይ የስነልቦና እና የአካል ለውጥን ያስከትላል፡፡
አንድ ሰው ሲናደድ የልብ ምቱ፣ የደም ግፊቱ እና የኃይሉን መጠን የሚቆጣጠሩት የሆርሞኖቹ መጠን ከፍ ይላል፡፡
ንዴት ውስጣዊም ሆኑ ውጫዊ በሆኑ ምክኒያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም አንድ ሰው በሁለተኛ ሰው ፣ በትራፊክ መዘጋጋት አሊያም በቁስ ሊበሳጭ የሚችል ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ውስጣዊ በሆኑ ስሜቶቹ፣ ባለፉት ታሪኮቹ እና በትውስታዎቹ ሊበሳጭ ይችላል፡፡
ንዴት ተፈጥሯዊ እና ሰዋዊ የሆነ ስሜት በመሆኑ መከሰቱ ክፋት የለውም ፤ ይሁንና ነገሩን ከፋ የሚያደርገው የሚገለጥበት መልክ
ነው፡፡
ሰዎች ንዴታቸው በተለያየ መንገድ ይጋፈጣሉ እነዚህም በማፈን፣ በመተንፈስ አልያም ደግሞ እራስን በማረጋጋት ሊሆን ይችላል፡፡
ንዴትን መተንፈስ እና መግለጥ መጥፎ አይደለም እደውም ከብዙ ነገር አንጻር ተመራጭ ሊሆን ይችላል ጉዳዩ ግን የምንገልጥበት ስነምግባር ምን መምሰል አለበት የሚለው ነው፡፡
ሳይኮሎጂስቱ ንዴትን ማፈን ብዙ ግዜ ጥሩ ተግባቦት እና መልካም ስነምግባር ያላቸው ሰዎች በሃሪ ነው ያሉ ሲሆን፤ ይሁንና ሁለተኛውን ሰው ላለመጉዳት እና ላለማስቀየም ተብሎ የሚታፈን ንዴት እንደተዋጠ ቦንብ በመሆን መልሶ እራስን በመጉዳት እነደ ስኳር. ደም ግፊት እና ድብርት የመሳሰሉ በሽታዎች ያጋልጣል ብለዋል፡፡
ስለዚህ በትክክለኛ መንገድ የሚገለጥ ንዴት ሁሌም ለሁለቱም ወገኖች መልካም ነው ይላሉ
ንዴትን መቆጣጠር (anger management)
ንዴትን መቆጣጠር አለመቻል የሚገለጠው በምን ያህል ጊዜ እንደሚናደዱ በመለካት እና የተፈጠረውን ንዴት መቆጣጠር ባለመቻልዎ ነው፡፡
ተናዳጅ ሰው የንዴቱን መጠን እና ሁኔታ መቆጣጠር ከቻለ እራሱንም ሰዎችን ከመጉዳት ይታደጋል፡፡ንዴትን ለመቆጣጠር የተለያዩ መንገዶች ያሉ ሲሆን ከዛም ውስጥ ፡-
1- በተደጋጋሚ የሚያናዶትን ነገር ምንነት በማወቅ
ንዴት ውስጥ ባልሆኑበት ወቅት የሚናደዱበትን ሁኔታ እና ጉዳይ በደንብ ማጤን ከቻሉ እና ለመገንዘብ ከሞከሩ እነዛን ሁኔታዎች በመራቅ እና በተቻለ አቅም ርቀትን በመጠበቅ የሚናደዱበትን የጊዜ ፍጥነት ማራዘም የሚችሉ ሲሆን ቶሎ ተናዳጅ እንዳይሆኑ መሆንም ይችላሉ፡፡
2- የንዴትን የመጀመሪያ ደረጃ መለየት
ሁሌም ቢሆን ከማንፈልገው ነገር ሸሽተን መኖር አንችልም፡፡ ስለዚህ ስሜታችንን የሚያስቆጡ ነገሮች ሳናስባቸው ይከሰታሉ፤ በዚህ ጊዜ ንዴት ሲጀምረን ልብ ማለት ከቻልን መቆጣጠሩ ቀላል ይሆንልናል፡፡
ንዴት ተቀጣጠይ ስሜት በመሆኑ ከትንሽ ወደ ትልቅ እያደገ ነው የሚመጣው፡፡ በመሆኑም ልብ በማለት እና እራስን በማረጋጋት እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች እራስን በመጥመድ ከአስከፊ ንዴት እራስን ማዳን ይቻላል፡፡
3- እራስን የማረጋጋት ቴክኒኮችን መጠቀም
ሁሉም ሰው ለራሱ የሚሆነውን መንገድ በመምረጥ እራሱን ማረጋጋት ይችላል፡፡ ምናልባትም አንድን ነገር ደጋግሞ በውስጥ በማለት፣ በረጅሙ በመተንፈስም ሆነ የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከሚከሰትብን የንዴት ማዕበል እራሳችንን ልንታደግ እንችላለን፡፡
የሰው ልጅ ከስሜቱ በላይ ነው፡፡ በመሆኑም ሊቆጣጠረው እና ሊያሸንፈው የማይችልው የስሜት ዓይነት የለም፡፡ሼር
ምንጭ ፡- American Psychological Association
እርጅናን ለመከላከል የሚረዱ ምግቦች

እርጅና የሚቀር አይደለም፤ ማንም ሰው እድሜው ከፈቀደለት እና በህይወት ከቆየ ይህንን እድል ማየቱ የማይቀር ነው፡፡ ይሁንና እርጅናን መከላከል ሲባል በእርጅና ሳቢያ የሚመጣ የቆዳ መሸብሸብ ፣ የድካም ስሜት እና የመጫጫን ስሜቶች ሳይኖሩ መቆየት መቻል ማለት ነው፡፡

1- በለስ
በለስ የሚጣል ክፍል የሌለው ድንቅ ተክል ነው፡፡ ከቆዳው አንስቶ እስከ ፍሬው ድረስ ለአዕምሮ ጤና እና ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ጥቅም የሚሰጥ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ እርጅናን በተመለከተም በበለስ ውስጥ የሚገኘው ፋይሰን ተሰኘው ኢንዛይም በእድሜ ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ ብግነቶችን በመከላከል ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡

2- እርድ
እርድ ከቁንጅና እስከ ህክምና ድረስ መጠነ ሰፊ ጥቅም ያለው ተክል ነው፡፡ በ እርድ ውስጥ የሚገኘው ቱምርን እርጅናን የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ በምንመገበው ምግብ ውስጥ እርድን መቀላቀል ባህል ማሳደግ ይኖርብናል፡፡

3- አቮካዶ
1 አቮካዶ በቀን መብላት የቆዳ ሃኪም ጋር ድርሽ እንዳይሉ ያደርጋል የሚለው አባባል በጣም ታዋቂ እና እውን ነው፡፡ ለቆዳ ፍካት እና ውበት ከመጥቀሙ ባሻገር እርጅናን መከላከል አቅሙም የሚናቅ አይደለም፡፡
ሼር
ምንጭ፡- ANCIENT MEDICINE TODAY
ሃሳብን መቀየር ለምን ይከብዳል?
የሚቀየር እና የማይቀየር ሃሳብ ስንል እምነት ማለታችን ነው፡፡ የሰው ልጅ የሆነ ኢንፎርሜሽንን በአዕሮው ውስጥ ሲያከማች እና ያከማቸውን ነገር በሆነ መንገድ ቅርፅ አስይዞ በቀን የቀን ተቀን ህወቱን በእርሱ ተፅዕኖ ስር እንዲውል ሲፈቅድ አመነ እንላለን፡፡
አመለካከት፣ ሃሳብ እና እምነት የተሰኙት ፅንሰ ሓሳቦች ለዘመናት ብዙ ፈላስፎችን ያነጋገሩ ሲሆኑ የሳይንቲስቶችና የስነ-አዕምሮ ባለሞያዎችም ትኩረት ከሳቡ ሰነባብተዋል፡፡
ሳይካትሪስቱ ራልፍ ሌዊስ እንዳስረዳው ከሆነ ሃሳቦች ልክ ሆኑም አልሆኑም አንዴ አእምሮ ውስጥ ኑረውና ወደ እምነትነት ከተቀየሩ በቀላሉ እነሱን መቀይር አይቻልም፡፡
እምነት ማለት አዕምሯችን የተወሳሰበውን ዓለም ለመረዳት የሚያሰምረው የራሱ መንገድ ነው፡፡ ነገሮች ከነገሮች ጋር በምን መንገድ መተሳሰር እንደሚኖርባቸው የሚያትትበት እና ነገሮች በምን መንገድ መተግበር እንደሚኖርባቸው ቀድሞ የራሱን ግምት የሚያስቀምጥበት ሂደትም ጭምር ነው፡፡
እምነቶች የመማር አቅማችንን የመወሰን ስልጣን ያላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ የመኖር ምክኒያታችን እስከመሆንም ጭምር ይደርሳሉ፡፡
አዕምሮ ኃይል አሟጣጭ አካል ነው፡፡ የሰውነታችንንን አብዛኛውን ኃይል ከመውሰዱም በተጨማሪ የወሰደውን ኃይል በቁጠባ እና በአግባቡ መጠቀም ይኖርበታል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ ዘዴዎችን የሚጠቀም ሲሆን ከዛም ውስጥ አንደኛው መንገድ የሆነ ጊዜ ላይ በሆነ መንገድ ተሰርተው የተቀመጡ ኢንፎርሜሽኖችን አንዴ ‹ሴቭ› አድርጎ በማስቀመጥ በሚፈልገው ሰዓት እሱን እንደ ፋይል ‹ክሊክ› በማድረግ እየመነዘሩ መጠቀም ነው፡፡
ይህ ለአዕምሮ ስራ አቅላይ ከመሆኑም በተጨማሪ ኃይል ቆጣቢ አሰራርም ነው፡፡ ምክኒያቱም አንድን ነገር ማሰብ ማደራጀት መተንተን እና መደምደሚያ ላይ መድረስ ከባድ ስራ ነው፤ በመሆኑም ያንን ሁላ መንገድ ሳይጓዝ አዕምሮ በቀላሉ ነገሮችን እያጠጋጋ እና እያመሳሰለ የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ በመድረስ አቅሙን መቆጠብን እንደ አማራጭ ያየዋል፡፡
ስለዚህ ይህ የአዕምሮ ስንፍና እኛን በአንድ ሃሳብ ላይ ፀንተን እንድንቆይ ከማድረጉም በላይ ለየትኛውም አዲስ እውቀትም ሆነ አዲስ አመለካከት ክፍት እንዳንሆን ያደርገናል፡፡
መረጃን መተንተን፣ ማመሳከር ፣ ማዋቀር እና መደምደም ትልቅ ስራ ነው ስለሆነም ከአንዳንድ ግልሰቦች ውጭ ይሄንን ሂደት ለመስበረር የሚደፍር የለም፡፡
አዕምሮን በማላመድ እና ይሄንን የአስተሳሰብ ‹ትሬንድ› በመስበር የተሻለ አዕምሮን መፍጠር እንችላለን፡፡ ሼር
ምንጭ ፡- Psychology Today
የወንዶች ስነ-ተዋልዶ ጤናን ቀያሪ ሁናቴዎች
የወንድ ዘር ፍሬ ከሴት እንቁላል ዘንድ ደርሶ ዘር ማፍራት እንዲችል ጤናማና ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ በተለይም የዘር ፍሬው በቂ የብዛት መጠን እና ቅርፅ፣ ትክክለኛ የጉዞ አቅጣጫ እንዲሁም ወደ እንቁላሉ ሊያደርሰው የሚችል በቂ ፈሳሽ እንዲኖረው ይገባል፡፡ ልጅ መውለድ ያለመቻልን ሊያመጡ ይችላሉ ከሚባሉት ምክንያቶች ውስጥ 80 በመቶዎቹ በህክምና ባለሙያዎች ሲታወቁ ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ በወንዶች አማካኝነት የሚከሰት ነው፡፡ የወንዶችን ስነ-ተዋልዶ ቁመና በመወሰን ረገድ ትልቅ ድርሻ ያላቸው እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡-
፩. ክብደትን መቀነስ፡- በተለያዩ ጥናቶች መሰረት የወንዱ ክብደት ከፍተኛ የሆነባቸው ጥንዶች ለመውለድ በመቸገር ረገድ ከፍ ያለ እድል አላቸው፡፡ ይህ ከፍተኛ ክብደት የወንዱን የዘር ፍሬ ብዛትና ጥራት ከመቀነስና የዘረ-መሉ ላይ ጉዳት ከማድረሱም በተጨማሪ የመንሳፈፍ ብቃቱንም ይጎዱታል፡፡
፪. ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን መከላከል፡- እንደ ስኳርና ደም ግፊት ያሉ ዘላቂ በሽታዎችን መከላከል የማስረገዝ ብቃትን የተሸለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ሆኖም እነዚህን በሽታዎች ጨምሮ ድብርትን፣ መረበሽን፣ ራሰ በረሃነትን የሚያክሙ እና ህመምን አስታጋሽ መድሃኒትና ህክምናዎችን መውሰድ የመውለድ ብቃት ላይ ችግርን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
፫. ጤናማ ምግቦችን መመገብ፡- ሳይንስ ጤናማ ምግቦችን መመገብ ከስነ-ተዋልዶ ጤና ጋር ያለው ግንኙነት በግልፅ ባያስቀምጥም የወን የዘር ፍሬን በጥራት ለማምረት የሚችሉ እንደ ሃባብ፣ ብርቱካን፣ ምስር ቲማቲም እና እንጆሪን ያሉ የፍራፍሬ፣ ጥራጥሬና አትክልት ምግቦችን መመገብ ግን ይመከራል፡፡
፬. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በየዕለቱ መከወን ዘላቂ አካላዊና ውስጣዊ ጤናን ይሠጣል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህን ጥቅሞች መስጠት ቢችሉም ማራቶንን የመሰሉ ከባባድ እንቅስቃሴዎች ግን በስነ ተዋልዶ ላይ ተፅዕንዖ ሊኖራቸው እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
፭. ቫይታሚን ሰጪ መድሃኒቶች (Multivitamin)፡- ቫይታሚንንና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን ለሰውነት እንዲሰጡ ታስበው የሚዋጡት እነዚህ መድሃኒቶች በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የቫይታሚን ሲ እና ኢ እንክብሎችም የዘር ፍሬን ጥራትና እንቅስቃሴን በማሻሻል እንደሚረዱ ተቀምጧል፡፡
፮. ዕድሜ፡- ምንም እንኳን ከሴቶች አንፃር ዘግይቶ ቢገጥማቸውም የወንዶች ዕድሜ መጨመር በስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ተፅዕኖን ያመጣል፡፡ ይህም በተለይ የዘር ፍሬ ጤናማነትና የዘረ-መል መጎዳት እንዲሁም በመጠንና ጥራቱ ላይ ማነስ መኖሩን ነው፡፡
፯. ተጓዳኝ ሱሶች፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩን ሲጋራን ማጨስ የወንድ ዘር ፍሬ እንቅስቃሴ እና ብዛትን ከመቀነስም ባሻገር የቅርፅ ለውጥን ያስከትላል፡፡ ከፍተኛ የአልኮል አጠቃቀምም የዘር ፍሬውን ጤና ይጎዳል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ ማሪዋናና በሰውነት ግንባታ ተወዳዳሪዎች ጥቅም ላይ የሚውለው ስቴሪኦድን መሰል ቁሶችም ተመሳሳይ አሉታዊ ጉዳቶች አሏቸው፡፡
፰. ሙቀት፡- በሙቅ ገንዳ፣ ሳውናና ስቲሞች ውስጥ ለበዛ ሰሠዓታት መቆየትና ደጋግሞ መጠቀም የመራቢያ አካላትን ሙቀት በመጨመር ለዘር ፍሬ መመንመንና ጥራት መውረድ ሊዳርግ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ይህን መሰል ጉዳቶች ዘላቂ አይደሉም፤ ከነዚህ ተግባራት ስንርቅ መደ ጤናማ አኳኋን እንመለሳለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን በሰውነት አካል ላይ አኑሮ መጠቀም ተመሳሳይ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
፱. የህክምና እርዳታ፡- የሴቷ እድሜ ከሰላሳ አምስት ዓመት በታች የሆነባቸው ጥንዶች የህክምና እርዳታን ከመሻታቸው አስቀድሞ በመካከላቸው ያለ ወሊድ መከላከያ ለአንድ ዓመት ያህል ተከታታይ ሩካቤ ስጋን እየፈፀሙ ልጅ ለመፀነስ መሞከር እንዳለባቸው ይመከራል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሙከራ የሴቷ ዕድሜ ከሰላሳ አምስት በላይ ከሆነ ስድስት ወር እንዳለፈ ወደ ህክምና ማቅናት ይኖርባቸዋል፡፡
ምንጭ፡- Live Science
እንኳን ደስ አለን❗️❗️❗️
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት የስልጣን፣ ተግባርና አደረጃጀት ደንብ በሚኒስትሮች ምክርቤት ጸደቀ።

የሚኒስትሮች ምክርቤት በትላንትናው እለት ህዳር 5/2011 ባካሄደው ስብሰባ መንግስት በቅርቡ ያደረገውን ለውጥ ተከትሎ የፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሰረት የተደራጀውን የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ስልጣን፣ ተግባር እና አደረጃጀት ለመወሰን ተዘጋጅቶ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃን በማዕከላዊነት ለመምራት በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 257/2004 የተቋቋመው የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ከተቋቋመበት ከ2004 ጀምሮ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት እስከሆነበት ጥቅምት 2011 ድረስ ለቴክኖሎጂ፣ ለምርምርና ለማምረቻ ተቋማት ግብአት የሚሆኑ እሴት የታከለባቸውን መረጃዎች በማሰራጨት ሀገራዊ ተልዕኮውን ሲወጣ ቆይቷል።

በአዲሱ አደረጃጀርት መሰረትም ኢኒስቲትዩቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የምርምር መሰረተ ልማቶችን መገንባትን፣ ለኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብና እሴት አክሎ ማሰራጨት፣ በአምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመንግስት ተለይተው ቅድሚያ በሚሰጣቸው ሴክተሮች ላይ ምርምርና ልማት ስራዎችን መስራትና መሰል የጥናትና ምርምር ስራዎችን መደገፍና ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ ሰፋፊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ተልዕኮዎችን አንግቦ ይሰራል።
Channel name was changed to «TechIn2»