ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ በአእምሮ እንቅስቃሴ ላይ ለውጥ ያመጣል በተጨማሪም የትውስታ ብቃትን ያሳድጋል፡፡
ሰዎች ወደ ውስጥ በሚተነፍሱበት ጊዜ አየር ወደ ውጪ ከሚያስወጡበት ጊዜ በተሻለ የፍርሀት ስሜትን በፍጥነት ማስወገድ ችለዋል፡፡
ወደ ውስጥ በምንተነፍስበት ጊዜ
• የማስታወስ ችሎታ በአወንታዊ ጎኑ ለውጥ ያመጣል፡፡ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ሰዎች ነገሮችን የሚያስታውሱት አየር ወደ ውስጥ በሚያስገቡበት ጊዜ ነው
• አየር ወደ ውስጥ ማስገባት በኦሊፋክተሪ ኮርቴክስ (olfactory cortex)፣ በአሚገዳላ (amygdala) እና በሂፖቻምፐስ (hippocampus) በአጠቃለይ በሊምቢክ ስርዓት (limbic system) ውስጥ ያሉ የነርቭ ሴሎችን (neurons) ያነቃቃል፡፡
ሊምቢክ ስርዓት (limbic system) ፡- ደመ ነፍስ (instinct) እና ስሜትን (mood) የሚቆጣጠር ስርዓት ነው
• የነርቭ ሴሎችን በማነቃቃቱ ደግሞ
የስሜት ሂደት (emotional processing) እና
የአእምሮ የትውስታ ክፍሎች ላይ ለውጥ ያመጣል
እነዚህ የምርምር ውጤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ምርምር ውጤቶች ቢሆኑም አንድ ነገር ግን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡እሱም አየር ወደ ውስጥ ማስገባት በአእምሮ ላይ አወንታዊ ተጽኖ ያሳድራል፡፡
ምንጭ፡- Time, Telegraphs

ስቲቨን ሃውኪንግ
ዛሬ ዕለተ እሮብ በ መጋቢት 10 2010 ዓመተ ምህረት ሳይንስ ታላቅ ባለውታዋን ሸኘች፡፡
የዘዋርድ ፕሮፌሰር ሰቲቨን ሃውኪንግ በ 76 ዓመቱ ከዚህች ዓለም በሞት ተለየ ተለይቷል፡፡
ስቲቨን ሃውኪንግ ገና በለጋ እድሜው ALS በተሰኘው በሽታ የተጠቃ እና ሙሉ ህይወቱን ያለ እንቅስቃሴ እንዲሳልፍ የተገደደ ቢሆንም ከበሽታው በላይ በመሆን ለዓለም አለሁልሽ ብሏታል፡፡
ስቲቭን በጃንዋሪ 8፤ 1942 ዓመተ ምህረት (ልክ ጋሊሊዮ በሞተ በ300 ዓመቱ )በእንግሊዝ በኦክስፎርድ ከተማ ተወለደ፡፡ ይህ ታላቅ ሰው ለሳይንስ የታጨው ከመወለዱ በፊት ይመስላል፡፡ አባቱ ፈራነንከ ሃውኪንግ ባዮሎጂስት የነበረ ሲሆን እናቱ ኢዛቤል ደግሞ የህክምና ምርምር ተቋም ሰራተኛ ነበረች፡፡
በ 1959 በ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ስኮላር በማግኘት በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ለማግኘት ችሏል፡፡
በሳይንስ ውስጥ ልዩ ጠዓምን እያገኘ የመጣው ይህ ታላቅ ሳይንቲስት በ 1962 ዓመተ ምህረት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲበ Department of Applied Mathematics and Theoretical Physics (DAMTP) የኮስሞሎጂ ምርምር ስራዎችን ማከናወን ጀመረ፡፡
ይሁንና በ 1963 ልክ የ 21 ዓመቱን ልደት እንዳከበረ ከባድ ነገር አጋጠው፤ እድሜውን በሙሉ በወንበር ላይ እንዲታሰር ሆነ፡፡ ይህ በሽታ እንቅስቃሴውን ብቻ አልነበረም የቀማው ድምፁንም ጨምሮ ቢሆን እንጂ፡፡ ሰቴቭን የኮምፑተር ጥገኛ ሆነ፡፡
የስቲቭን ጉዞ ግን በዚህ አላበቃም ጅማሬው ቢሆን እንጂ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በ1965 ዓ.ም Properties of Expanding Universes በሚለው የምርምር ውጤቱ ምክኒት የPhD ማዕረጉን ሊያገን ቻለ፡፡
ስቲቭን 30 የሚሆኑ የክብር ዲግሪዎችን ያገኘ ሰው ሲሆን በርካታ ሽልማቶችንም ተጎናፅፏል፡፡ ስቲቭን በ አልበርት የተጀመሩ ስራዎችን ያስቀጠለ እና በተለይም በ relativity እና በ quantum theory ውስጥ ጥልቅ አሻራን ያስቀመጠ ሰው ነው፡፡
ፕሮፌሰር ሰቴቭን የ3 ልጆች አባት እና የ 3 ልጆች አያት ነው፡፡
ስቴቭን በ 2010 ዓ.ም ለABC's "World New Tonight," በሰጠው ቃለ ምልልስ ወቅትም ለልጆችህ ሰጥተኸው የምታውቀው ምርጥ ምክር ምንድ ነው በተባለ ሰዓትም እንዲህ ብሎ መልሷል፡፡
"ለልጆቼ የሰጠኋቸው 3 ምርጥ ምክሮች አሉ እነርሱም ፡-
1ኛ፡- ሁሌም ቢሆን ወደ እግራችሁ ታች እየተመለከታችሁ ወደ ላይ ወደ ኮከቧማንጋጠጥን አትርሱ፡፡
2ኛ፡— ሁሌም በስራ ላይ ሁኑ፡፡ ስራ ለህይወታችሁ ምክኒያት እና ለመኖራችሁ ዓላማን ያጎናፅፋችኋል፡፡
3ኛ፡- እድለኛ ሁናችሁ ፍቅርን በህይወታችሁ ውስጥ ልታገኙ ከቻላሁ በጣም የማይገኝ ዕድል ነውና በቀላሉ አትልቀቁት፡፡
ዓለም እንዲህ ያሉ ሰዎችን በቀላሉ የምትለግስ ባትሆንም ሁሌም ግን ህልፈታቸውን የሚተካ ሳታዘጋጅ አልፋ አታውቅም፡፡
ይህንን ታላቅ ሳይንቲስት በማጣችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን A Brief History of Time እና The Universe in a Nutshell የሚሉትን የእርሱን 2 ምርጥ መፅሀፎች ተጋበዙልን እንላለን፡፡ ሼር
ምንጭ ፡- BBC News

ሳይንስና ስኬታማው የህይወት ጎዳና
ሳይንስ በዘመናችን በሰፊው ተቀባይነት ካገኙ ክስተቶች ውስጥ ትልቁን ስፍራ ተቆናጦ ይገኛል፡፡ በተለይም አሁን አሁን በየትኛውም ቦታ ለሁሉም ሰው እኩል ሊጠቅም ይችላል የሚለው እሳቤ እያደገ ሲመጣ ሰዎች ለኃይማኖት ካላቸው ቀናኢነት የበለጠ ለሳይንስ እየኖራቸው ነው፡፡
ለመሆኑ ሳይንስ ከየትኛውም የዓለማችን ክስተት የበለጠ እንዴት ተቀባይነትን ሊያገኝ ቻለ; ሰዎችስ ለምን ያን ያህል አመኑት?
ለዚህ መልስ የሚሆኑ እና አንድ ሁለት ተብለው የሚዘረዘሩ እውነቶች በርካታ እንደሚሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ይሁንና እኛ ዛሬ ከነሱ ውስጥ አንዱን እና ዋነኛ ሊሆን ይችላል ያልነውን ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡
እራስን ማረም
ሳይንስ ክፍት ፍልስፍና ነው፡፡ ለወቃሽ እና ለ ተቺ የተመቻቸ በመሆኑ ማንም እንዲያርመው ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ሳይንስ እራሱን አራሚ ነው፡፡
ሳይንስ እንደባልዲው እንጂ እነደ ውሃው አያገለግልም፡፡ ለሳይንቲስቶች ሳይንሳዊ ምርምራቸውን የሚያካሂዱበትን ፍሬም እንጂ ምርምሩን እራሱን አይሰጣቸውም፡፡ ሳይንስ እንደ ቤት ነው (ክፍት መጠለያ) ከስሩ የተያየ ዓላማ እና የተለያየ መነሻ ያላቸውን ሁሉ አቅፎ ማኖር የሚችል፡፡
ሳይንስ በእውነት አንደሚያምን በግላጭ ሊያሳይ በመሞከሩ የሰው ልጆችን ትኩረት ወደ እራሱ ሊመልስ ችሏል፡፡ በሳይንስ ቤት ውስጥ ትልቁ ቁልፍ መረጃ እና ማስረጃ ነው፡፡ ምንም ያህል ወጪ፣ ጉልበትም ሆነ አድናቆትን ፈሰስ ያደረገ ግኝት ቢሆንም እንኳ እርሱን የሚያፋልስ አዲስ ማስረጃ እስከተገኘ እና እውነተኝነቱን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚሞግት እስከኖረ ድረስ ለመሻር ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሳይንስ ትናንቱን አይረሳም፡፡ የአሰራሩ ሁኔታም ትናንቱን እንዲክድ እንዳይፈቅድለት አድርጓል፡፡ ሳይንስ ይሞክራል ይሳሳታል ስህተቱን ግን በአደባባይ ያቀርባል፡፡ ሁሌም ለውጥን እና አዲስ ሀሳብን ባለመፍራቱ እየፈረሰ እንዲገነባ ምክኒያት ሆኖታል፡፡
ሳይንስ በዚህ ረገድ ሁለት ትልልቅ መንገዶችን አመላክቷል፡፡ ገንቢ ወቃሽ እና አዳጊ ተወቃሽ፡፡ ሳይንሳዊ ወቀሳ መልስ አቀፍ ነው፡፡ አልሆነም ያለ ካለ ቢሆን የሚለውን እንዲያመጣ ይገደዳል፡፡ ይህ ጎዳና አዳጊ ተወቀቀሾችን ይፈጥራል፡፡
እራስን ማረም ትልቅ ፍልስፍና ነው፡፡ የሰው ልጆች ከሳይንስ ሊዋሱት የሚገባም ጭምር፡፡ ለመታረም ዝግጁ የሆነ ማንነት ከቀውስ ይተርፋል፡፡ ገንቢ ትችት ያሳድጋል፡፡
መልካም ቀን! ሼር
ስቲክ ኢትዮጵያ

አዎንታዊ ስነልቦና (Positive Psychology)
የኃይማኖት እና የሳይንስ ዋናው ልዩነት ጎልቶ የሚታየው ስለ ሰው ልጅ የግል ሂወት ሃሳብ፣ ደስታ እና ስሜት የመሳሰሉት ጉዳዮች መነሳት ሲጀምሩ ነው፡፡
ሳይንስ በሚታዩ ውጤቶች እና ምክኒያቶች ላይ የተመረኮዘ አስተምህሮት ሲሆን ኃይማኖት ከሳይንስ አስተምህሮ በተጨመሪ ስለማይታዩ እና ስለማይዳሰሱ ነገር ግን በሰው ህይወት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ስላላቸው ነገሮች የሚያስተምር ነው፡፡
አዎንታዊ ስነልቦና የተሰኘው ይህ ሃሳብ ግን ታሪክን ሊቀይር ይመስላል ፤ ሳይንስ ኃማኖታዊ ይዘት ያላቸውን አስተምህሮቶች ሳንሳዊም ጭምር እንደሆኑ እንዲያምን እያደረገ ነው፡፡
ለመሆኑ አዎንታዊ ሳይኮሎጂ ምንድን ነው?
አዎንታዊ ስነልቦና ህይወትን ለመኖር ብቁ ስለሚያደርጋት ነገርና እና የሰዎችን የመኖር አዎንታዊ ፍላጎት ምንጭ ምንነት የሚመረምር የሳይንስ ዓይነት ነው፡፡
አዎንታዊ ስነልቦና ከሌሎች የሳኮሎጂ መንገዶች በተለየ ተግዳሮቶች ላይ ሳይሆን መልካም ጎኖች ላይ የሚያተኩር የሳይንስ ዓይነት ነው፡፡
ማለትም የተፈጠሩ ችግሮች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ያሉን ጠንካራ ጎኖች እና ወደ ፊት የሚኖሩን ብሩህ ተስፋዎች ላይ ያነጣጥራል፡፡
ይህ ሳይንስ ሌሎቹን የስነልቦና (Psychology) ሳይንሶች በማፍረስ ሳይሆን እነርሱ ላይ በመደመር ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎም ያምናል፡፡
የዚህ ሳይንስ ዋናው ሀሳብ ደህንነት ነው፡፡ ሰዎች እንዴት ደህና ይሆናሉ?
ማርቲን ሴሊግማን የአዎንታዊ ስነልቦና ሃሳብ ጠንሳሽ ከሆኑት ተመራማሪዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ስለደህንነት (well beingness) ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር ደህንነት አምስት መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው እነርሱም፡-
1- አዎንታዊ ስሜት
ሰዎች ስለነገሮች የሚኖራቸው ስሜት አዎንታዊ አሊያም አሉታዊ መሆን በአዕምሯቸው ላይም ሆነ በሰውነታቸው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ልዩነትን ሊመጣ ይቻለዋል፡፡
2- መጠመድ(engagement)
ሰዎች በስራቸው አሊያም በሂወት ዓላማቸው በተጠመዱ ቁጥር ደህንነታቸው አስተማማኝ እየሆነ ይመጣል፡፡ የሰው ልጆች አዕምሮ ስራ መፍታትን ከሆነ ገደብ በላይ መቀበል አይቻለውም ያም ደህንነታቸውን አስጊ ወደሆነ ደረጃ እንዲያሽቆለቁለው ያረጋል፡፡
3- ግንኙነት
የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ውስጣዊ ክፍተትን የመሙላት በሀሪ ስላላቸው ሰዎች እንደ ብቸኝነት እና ባተዋርነት ያሉ አፍራሽ ስሜቶች እንዳይሰማቸው በማድረግ ለደህንነታቸው እንደ ዋስትና ያገለግላል፡፡
4- ትርጉም
ሰዎች በህይወት ለመቆየታቸው እና ለእያንዳንዷ እንቅስቃሴቸው ትርጉም ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ ሰዎች ትርጉም አልባ ህይወት እንዳይኖሩ የሚደርጓቸውን የህይወት ትርጓሜዎች ባበጁ ቁጥር ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል፡፡
5- ማጠናቀቅ
ሰዎች ከልፋታቸው ማግስት ውጤት ከድካማቸው በኋላም ፍሬን ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም የተጠመዱበትን ነገር መጨረሻ ማየት ደህንነታቸውን ያረጋግጥላቸዋል::
….. እነዚህ ግን እውን የመጀመሪያዎቹ መንደርደሪያዎች ናቸው? እነዚህን 5 ነገሮች ለማሳካት እንድችል የሚጠቅሙን ሌሎች ቅደመ መሰረቶች ይኖሩ ይሆን? መጀመሪያ ላይ አንስተነው የነበረው የኃይማኖት አስተምህሮ እና የዚህ ሳይንስ አስተምህሮ ግንኙነትስ ምንድን ነው? ፅሁፉ አላለቀም ይቀጥላል….. ሼር
ምንጭ፡- ከpsychologytoday በተወሰነ መልኩ የተወሰደ

ስጦታ ለወላጆች
ሁሉም ሰው ታዛዥ እና መልካም ልጅ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ይሁንና ይህ ህልም በቀላሉ የሚሳካ አይሆንም፡፡ ወላጆች በገዛ ልጆቻቸው መሀል የሚፈጠረውን ልዩነት እንኳ መቀበል ይከብዳቸዋል፡፡ ማለትም በመጀመሪያዋ/ው ልጅ ያገኙትን በተከታይዋ/ዩ ልጅ ላይ ማጣትን መቀበል አይደፍሩም፡፡
ወላጆች ልጆቻቸው ከሆኑት ይልቅ እንዲሆኑ የሚፈልጉት ነገር ላይ ትኩረት በማድረጋቸው ምክኒያት የተሳካ የቤተሰብ ግንባታ እንዳይኖራቸው አድርገዋል የምትለው ፕሮፌሰር ዶና ማቲዎስ ልጆች ሁሌም የሆኑትን የሚሆኑት በአከባቢው ተፅዕኖብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ አስገዳጅነትም ጭምር ነው ብላለች፡፡
ልጆች ከውልደታቸው በኋላ የሚያዳብሩት ግለ-በሀሪ(ፀባይ) እንዳላቸው ሁሉ በተፈጥሮ የሚቸሩት ማንነት እና ፀባይም አላቸው፡፡
እነዚህ ፀባዮች(Temperament) 10 ዋና ዋና ነገሮችን ያቅፋሉ የምትለው ፔሮፌሰር ዶና እንዚህን መረዳት እና ልጆቻችን ስለየትኛው በሀሪ የትኛው ዓይነት ተፈጥሯዊ ግንባታ እንዳላቸው ማወቅ እነሱን ለማነፅ እና እነሱ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ይጠቀማል ብላለች፡፡
1- የእንቅስቃሴ መጠን፡- ጉልበት ፣ መንቀዥቀዥ እና እርጋታ
2- ስርዓተ-ኑሮ ፡- የአካል እንቅስቃሴ፣ የእንቅልፍ ሁኔታ፣ የምግብ አቀባበል እና የሽንት ቤት አጠቃቀም
3- አቀራረብ፡- ለአዲስ ሰው ያላቸው ምላሽ
4- መላመድ፡- ለአዲስ አከባቢ፣ ለሁኔታ ለውጥ እና ለመሳሰሉት ያላቸው የመላመድ መጠን
5- ስሜታዊነት፡- ለሌሎች እና ለራሳቸው ያላቸው የስሜት ቅኝት
6- ግለት፡- ለአዎንታዊ ም ሆነ ለአሉታዊ ሁኔታዎች ያላቸው የምላሽ ግለት
7- ሁኔታ ፡- ቁዘማ፣ ተስፈኝነት እና ከህፃኑ/ኗ በሚወጣው ቃል ውስጥ የሚነበብ የስሜት ግልባጭ
8- ትኩረት፡- ለያዙት ስራ የሚሰጡት ትኩረት እና በስራው ላይ የመዘውተር ባህሪ
9- መሰረቅ፡- ከያዙት ስራ በቀላሉ የሚሰረቁ መሆናቸው እና ዳግም ወደዛ የሚመለሱበት ሁኔታ መኖር አለመኖር
10- የህዋሳቸው ምላሽ፡- ለምላሽ የሚያስፈልገው የማነቃቃት መጠን
የልጆች ተፈጥሯዊ ፀባይ( Temperament) ዓለምን የሚዩበትን መነፅር ይሰራዋል፡፡
ለድግስ እና ለግርግር ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ጊዜ የሚወስድበት ልጅ እና ከእናቱ እጅ ምንጥቅ ብሎ ሄዶ እስኪቀላቀል የሚጨንቀው ልጅ አንድ አይደሉም፡፡
ወላጆች የልጆቻቸውን ፀባይ መምረጥም ሆነ መስራት አይችሉም ነገር ግን የፀባዩን መጠን እና ሁኔታ ግን ቅርጥ ማስያዝ ይቻላል፡፡
ወላጆች እንዴት ይህንን ፀባይ ቅርፅ ማስያዝ እና መግራት ይቻላቸዋል?
በ ፕሮፌሰሯ የተቀመጡትን 12 መንገዶች በ ከሰዓቱ ቆይታችን ምናይ ይሆናል፡፡ እስከ እዛ ድረስ መላከም ቆይታ….
ሼር
ምንጭ፡- psycologytoday

ስጦታ ለልጆች…..የቀጠለ (2)
ልጅ አስተዳደግ እጅግ ከባድ ነገር ነው ፡፡ ከበድ ያለ ልጅ ማሳደግ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ያከብደዋል፡፡ journal Psychological Bulletin ላይ የወጣው ጥናት እንደጠቆመው ከሆነ እንደመንቀዥቀዥ እና እንደ የስሜት አሉታዊነት ያሉ ነገሮች ተፈጥሯዊ የሚሆኑበት ሁኔታ የጎላ ነው፡፡
ይሁንና የወላጆች የተስተካከለ የልጀ አስተዳደግ መኖር ከልጆቹ ተፈጥሯዊ በሃሪ በበለጠ የልጆቹ እጣ ፈንታ ላይ የመወሰን አቅሙ የጎላ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ በሃሪያቸው አስቸጋሪ የሆኑ ልጆች ፤ የተስተካከለ የአስተዳደግ ስልት ይበልጡኑ የሚያስፈልጋቸው እንደሆነ ጥናቱ አክሎ ጠቅሷል፡፡
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ መንገድ የሚከተሉ ወላጆች አሉታዊ የአስተዳደግ አካሄድ ከሚከተሉ ወላጆች በበለጠ ስኬታማ እና ፍሬያማ ልጆች ማሳደግ ችለዋል፡፡
አሉታዊ አስተዳደግ ስልት
• ውይይት አልባ፡- በዚህኛው የአስተዳደግ ስልት ውስጥ ነግግር የሚኖረው ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ነው፤ እሱም ከወላጅ ወደ ልጅ፡፡
• የተዘጋ ስርዓት ነው፡- በዚህ የአስተዳደግ ስልት ውስጥ ልጆች አማራጭ እንዲኖራቸው አይደረግም፡፡ ማለትም በልጆች እና በወላጆች መሃል ምንም ዓይነት ድርድር የለም፡፡
• ፈፃሚዎች ናቸው፡- በዚህ ቤት ውስጥ ልጆች ፈፃሚዎች ናቸው፡፡ ወላጆች የልጆቹን ያልተገራ በሀሪ የሚገሩት ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፍ ይመስላቸዋል፡፡
• ህግ ይበዛዋል፡- በዚህ ቤት ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ህግ ይበዛል፡፡ ያ ደግሞ ልጆቹን ይበልጥ እያራቀ እና ወላጆች እራሳቸውን ከልጆቻቸው እነዲነጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡
እንዲህ ያለው የአስተዳደግ ዓይነት የልጆቹን የተፈጥሮ አስቸጋሪ በሃሪ ለማስተካከል የማይረዳ ከመሆኑም እና ህፃናቱ ያለባቸውን የበሃሪ ችግር በራሳቸው እንደያዩት ካለማረጉ በተጨማሪ ለ ሁለት ዋና ዋና ችገሮች ያጋልጣቸዋል፡፡ እሱም
1ኛው፡- ለውስጣዊ ችግር ሲሆን በራስ መተማመናቸውንና ራስን የማወቅ ደረጃቸውን ይጎዳዋል፡
2ኛው፡- ለውጫዊ ችግር የሚያጋልጣቸው ሲሆን ከአከባቢያቸው እና ከሰዎች ጋር ጥሩ ተግባቦት እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ ሚከተሉ ወላጆች የተሳካ ደስተኛ እና ህይወት ያላቸውን ልጆች የማፍራት እድላቸው የሰፋ መሆኑን ጥናቱ ገልጧል፡፡ እኚህ ወላጆች ጠንካራ ህጎች ያሏቸው ቢሆኑም ፍቅር አይለያቸውም ይህም፡-
• ስለልጆቻቸው ህይወት ግድ እንሚሰጣቸው በተግባር ያሳያሉ
• ለልጆቹ ስኬት እና መልካም ስራ ሁሉ ሙገሳ እና አድናቆትን ይለግሳሉ
• ከልጆቻቸው የሚጠብቁት ነገር ግልፅ እና ተጨባጭ ጉዳይ ነው
• ልጆቻቸውን ያዳምጣሉ
• ቋሚ ስሜቶች አሏቸው
• የልጆቻቸውን አስተያየት ከግምት ያስገባሉ
• ፍቅራቸውን በቃላት ይገልጻሉ፡፡
• ልጆች የራሳቸውን እንዲመርጡ እድል ያመቻቻሉ
• የምርጫዎቻቸውን ውጤት ቀድመው ያስረዳሉ
እውቀት ከሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ውስጥ የልጅ አስተዳደግ የቁንጮውን ቦታ ይይዛል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትንሽ ስህተት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
አሉታዊ የሆነ በሀሪ የሚበዛባቸውን ልጆች ማስተካከል የሚቻለው በአሉታዊ መንገድ አይደለም፡፡ ይህ በልጡን ጥፋተኝነት እንዳሰማቸው ያደርጋል፡፡

አዎንታዊ ስነልቦና…..ክፍል ሁለት
ቀደም ብለን ባቀረብነው ፅሁፍ ውስጥ ለማሳይት እንደሞከርነው የዘመናዊ የስነልቦና ሳይንስ ትኩረት የተበላሸን መጠገን ላይ እና ችግርን ማወቅ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡
ለሳንቲስቶች እንደ ደስታ፣ ተስፋ እና ማገገም ያሉ እድሜ ጠገብ ፍልስፍናዎች ላይ አዲስ አሊያም ደግሞ ተጨማሪ እይታ እና አቅጣጫን ለመጠቆም መቻል ቀላል የቤት ስራ አይደለም፡፡ ምክኒያቱም እንደ እነዚህ ያሉ አጀንዳዎች ባለ ብዙ አቀጣጫ እውነታዎች ናቸውና፡፡
የአዎንታዊ ስነልቦና ታሪካዊ አውድ
ይህ ሳይንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በማርቲን ሴሊግማን በ1998 የተዋወቀ አንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁንና በርካታ ጥናቶች ሊያረጋግጡ እንደቻሉት ከሆነ ሳይንሱ ቀደም ብሎ የታወቀና ብዙ የተባለለት እንደሆነ ነው፡፡
አዎንታዊ ስነልቦና በዊሊያም ጄምስ እና ከዛም ቀጥሎ በ1950 አከባቢ በአብራሃም ማስሎው በሰፊው ተቃኝቷል፡፡ ይሁንና በ1998 አከባቢ የተጀመረው የዳግማዊ አዎንታዊ ስነልቦና አብዮት ለእነዚህ ቀደምት ሳይንቲስቶች እውቅና አልሰጠም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ ሳንቲፊክ የሆኑ ማስረጃዎች ይጎሏቸዋል የሚል ነበር፡፡
ይሁንና ሁሉም ተመሳሳይ ሃሳብ እና ዘውግ ላይ የሚያጠነጥኑ በመሆናቸው ጉዳዩ ያን ያህል አሳሳቢ ሳይሆን ቀጥሏል፡፡
የዚህ ሳይንስ መነሸ ሃሳብ የስነልቦና ሳይንስ አጠቃላይ አንድምታ አሉታዊ ስሜትን ይፈጥራል የሚል ነበር፡፡
ያም የሚሆንበት ምክኒያት ሳይንሱ ማለትም የስነልቦና ሳይንስ ሰዎች ስለጎደላቸው ነገር ብቻ የሚያወራ በመሆኑ ነው የሚሉት እነዚህ የአዎንታዊ ስነልቦና ሳይንስ አቀንቃኞች የስነልቦና ሳይንስ ቅኝት ወደ አዎንታዊነት ሊዞር ይገባዋል ብለዋል፡፡
የሰው ልጅ የጎደለውን ከማወቁ ይልቅ ያለውን ቢያውቅ የተሸለ የስነልቦና ደረጃ ላይ ይደርሳልም ብለዋል፡፡
በአዎንታዊ ስነልቦና ሳይንስ ውስጥ የተለያዩ የእርዳታ መንገዶች ተቀምጠዋል እነርሱም “positive psychology interventions.” (ppi) በመባል የሚጠሩ ሲሆኑ እነርሱም አስራ ሁለት ናቸው፡፡
እነዚህን የአዎንታዊ የስነልቦና የእርዳታ መንገዶች ሁሉም የስነልቦና ባለሞያዎች ቢጠቀሙበት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላልም ብለዋል፡፡
1- ምስጋና መለማመድ፡- በዚህ ልምመድ ውስጥ ሰዎች ቢያንስ ስላላቸው እና ደስ ስለሚሰኙበት የህይወታቸው አካል ቢያንስ 3 ነገር እንዲፅፉ ይደረጋል፡፡ ይህ መንገድ የማመስገን ባህላቸውን እና የደስታ መጠናቸውን ከፍ የሚያደርገው እንደሆነ ሊረጋገጥ ችሏል፡፡ ሰዎች ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ፀጋ በሚቆጥሩበት ጊዜ የሚፈጠርባቸው የስሜት ከፍታ ስነልቦናቸውን ረዘም ላለ ጊዜ ማደስ እንደቻለ ጥናቶቹ አሳይተዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ ሰዋዊ የሆኑ ሳይንሶች እያደጉ እና እየበለፀጉ በመጡ ቁጥር መንፈሳዊነትን እና ኃይማኖተኝነትን እያረጋገጡ እና እያጎለበቱ እንደሚሄዱ ግልፅ ነው፡፡ ምስጋና የስነልቦናን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ እና ማመስገን የዕለታዊ ስንቃችን እንደሆነ የሚናገሩ ብዙ የቅዱሳን መፃህፍት አናቅፆች ያሉ ሲሆን ለምሳሌ ያህል በመፅሀፍ ቅዱስ ቆሮ 9፤15 እና በቅዱስ ቁርአን 14፤34 የተጠቀሱት ለዚህ እንደማስረጃነት መቀመጥ ይችላሉ፡፡
በቀጣይ ክፍላችን የቀሩትን የ “positive psychology interventions.” አንድ በአንድ ለማይት ምንሞክር እንደሆነ ቃል እየገባን መልካም ቀን ተምኝተናል፡፡
ሼር
ምንጭ፡- psycologytoday, he History of Positive Psychology እና ሌሎችም

የ 'Black Panther' ፊልም ቴክኖሎጂዎች ከልብ ወለድነት ከፍ ያሉ ናቸው
ይህ ፊልም ዓለምን ያነጋገረ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገቢን ለፊልም ኢንደስትሪው ያስገባም ጭምር ነው፡፡ በ 'Black Panther' ፈልም ውስጥ ያለችው የዋካንዳ ግዛት እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂዎች የሚታዩባት እና ፍፁም ስልጡን ከተማ ነች፡፡ ፊልሙ ውስጥ የታዩት ቴክኖሎጂዎችም እጅቅ ምጡቅ እና የተጋነኑም ይመስሉ ነበር፡፡
ከነሱም ውስጥ በራሳቸው የሚበሩ አውሮፕላኖች፣ በ virtual reality (VR) ቴክኖሎጂ በቀላሉ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ መኪናዎች ፣ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥራት ያላቸው ስክሪኖች እና ማግኔታማ የባቡር ሃዲዶች በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡
ከዛም በተጨማሪ ንጉሱ የሚለብሳቸው የተለየ አቅም እና ጉልበት የሚሰጡ እንዲሁም የሰበቃ ቅስቃሴውን (kinetic energy)የሚቆጣጠሩ እና ሃይል የሚሰበስቡ አልባሳቶች በፊልሙ ላይ ተስተውለዋል፡፡
እነዚህ አስደናቂ ቴክኖሎጂዎች ምናባዊ ብቻ አይደሉም፡፡ በ ማርች 30 በፊልሙ ውስጥ ስላሉት የሳይንስ ውጤቶች እና ሃሳቦች የሚተነተኑበት የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን በውይይቱ ወቅትም ከተለያየ አቅጣጫ የመጡ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች የነበሩ ሲሆን ፊልሙ ውስጥ ስላሉት ቴክኖሎጂዎች እውነተኝነትም ተናግረዋል፡፡
ከዛም በተጨማሪ ቴክኖሎጂዎቹ የሚዋቀሩበት ንጥረ ነገሮች በአፍሪካ ብቻ በተረፍ የሚገኙ አንጡር ሃብቶች መሆናቸውም ሌላው አስደናቂ እውነት ነው ብለዋል ፡፡
የ Smithsonian National Museum ዳይሬክተር የሆኑት Gus Casely-Hayfor በውይይቱ ወቅት አሁን አሁን የአፍሪካ አገራት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከ ምዕራባዊያኑ በላይ እንደሆነ ገልፀው የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓመት በወጣው የአፍሪካ ታይም መፅሄት ላይም የስማርት ስልክ እና ኮምፑተርን በመጠቀም አፍሪካ አንደኛ ናት ያለ ሲሆን ከዛም ውስጥ ናይጄሪያ፣ጋና ፣ ኮንጎ እና ኮትዲቯር በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ ሲልም አስነብቧል፡፡
ይህ ፊልም ለጥቁር ህዝቦች የተለየ ስሜትን ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ለኢትዮጲያዊያን ደግሞ ልዩ ትርጉም ነበረው፡፡ ፊልሙ ውስጥ የታዩት ገፅታዎች ለኢትዮጲያ እና ለኢትዮጲያዊያን የሚቀርብ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በተሰጡ አስተያየቶች ማወቅ ተችሏል፡፡
ያልተነካ ኃይል፣ እውቀት እና መሬት ያላት አፍሪካ ዋካንዳን መሆን የምትችልበት ብዙ ምክኒያቶች አሏት እያልን 'Black Panther ፊልምን ተጋበዙልን ብለናል፡፡ ሼር
ምንጭ፡- Live Science

ብቸኝነት፡- ለህብረተሰብ ጤና ዋነኘው ተጠያቂ ሆነ
ዓለም አቀፋዊነት የዓለማችን እጣ ፈንታ ሁኗል፡፡ ዓለም እንደ አንድ ቤት የዓለም ህዝቦች ደግሞ እንደ አንድ ቤተሰብ ከሆኑ ቆይቷል፡፡ በአንድ ጥላ ስር ለሚኖር ቤተሰብ ደግሞ ተነጣጥሎ የሚመጣ ችግርም ሆነ በረከት አይኖርም የአንዱ ቃስታ ለአንዱ ይሰማል በአንዱ ሙዚቃም ሌላው ይዝናናል፡፡
ይህ ዓይነቱ ትስስር ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ፣ ተመሳሳይ የአመለካካት ውቅር እና ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እንዲኖር ያስገድዳል፡፡
ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ አሁን አሁን በከፍተኛ ሁኔታ የህብረተሰብ ጤና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ የበዛ የአልኮል አወሳሰድ ፣ የታዳጊዎች በአደገኛ ሁኔታ በሱስ መጠመድ እና ረዘም ላለ ሰዓት መቀመጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሱ ሲሆን በቅርቡ የብሪገሃም ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር በሆኑት በፕሮፌሰር ጁሊያን ሆልት ለንስታንድ የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን ብቸኝነት አሁን ላይ ከፍተኛውን የህብረተሰብ ጤና ስጋትን በበላይነት ይመራል ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ እናዳሉት "የሰው ለሰው ግንኙነቶች ለሰው ልጅ ለመኖር እና በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የጨቅላ ህጻናት ማቆያን በተመለከተ የተደረገው ጥናት እንዳሳየው ከሆነም አጠገባቸው ሰው ከነበራቸው ጨቅላ ህፃናት ይልቅ ለብቻቸው ተነጥለው ተቀምጠው የነበሩት ለሞት የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነበር፡፡ ከዛም በላይ ሰዎችን ከህብረተሰባቸው ተነጥለው እንዲቆዩ ማድረግ የሰው ልጆች ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረ የቅጣት ዓይነት እና ፍርድም ጭምር ነው፡፡ይሁንና አሜሪካዊያን በአሁኑ ሰዓት ይህን የቅጣት ፍርድ በራሳቸው ላይ እየፈረዱ ይገኛሉ፡፡"
ይህንኑ የብቸኝነት ጣጣን በተመለከተ AARP ያወጣው ጥናት እንሚያሳየው ከሆነ በአሜሪካ እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ወደ 42ሚሊዮን የሚጠጉ ጎልማሶች በአሰቃቂ የብቸኝነት ህይወትን እየገፉ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡
በቅርቡ የወጣው የህዝብ ቆጠራ ውጤት ደግሞ እጅግ አስፈሪ የሆነን ዜና ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ እሱም ግማሹ የአሜሪካን ህዝብ ያላገባ እንደሆነና ሩቡ ደግሞ በፍፁም ብቸኝነት እየኖረ እንደሚገኝ አሳይቷል፤ ይህም የማግባት እና የመውለድ ምጣኔ እጅጉን እንዲያሽቆለቁል ምክኒያት ሆኖታል ተብሏል፡፡
ሚሊዮኖችን ላይ የተሰራው የፕሮፌሰሩ ጥናት አሜሪካዊያንን ፣ አውሮፓዊያንን እና አሲያዊያንን ያሳተፈ የነበረ ሲሆን የጥናቱ ውጤት እንዳሳየው ከሆነ ብቸኝነት ያለእድሜ ሞትን ያስከትላል፡፡ በተጨማሪም ማህበረሳዊ ግንኙነቶች ያላቸው ሰዎች 50 በመቶ ያህል ያለእድሜ ከመሞት የማምለጥ እድል አላቸው ብሏል፡፡
በስተመጨረሻም ፕሮፌሰሩ እንደዚህ ካለው አሳሳቢ ቀውስ ለመውጣት ለተማሪዎች፣ ለህጻናት እና ለህብረተሰቡ የተለያዩ ስልጠናዎች እና ትምህርቶች መሰጠት አለበት ያሉ ሲሆን አክለውም ሀኪሞች ከበሽተኞቻቸው ጋር ቅርበት ሊኖራቸው እና ህብረተሰቡም አንዱ ከአንዱ የሚተሳሰርበት የገንዘብ ፍሰት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
ጉዳዩ አሳሳቢ ነው በተለይም ዘመናዊነትን በፈርቀዳጅነት እየመሩ የሚገኙት ምዕራባዊያን የገቡበት ጉርጓድ ውስጥ ተከትሎ የማይገባ አንድ ህብረተሰብ በጠፋበት በዚህ ዘመን ውስጥ ይህ በሽታ ወደ ሌላው አይዛመትም ለማለት ይከብዳል፡፡
ስለዚህ ብቸኝነት የሚባል ገደል ከፊታችን እየጠበቀን እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ ኢትዮጲያዊነት ገደሉ ላይ የሚዘረጋ አስተማማኝ ድልድይ ነው ባህላችንን እንታጠቅ እያልን ከዚህ ልናመልጥ ያስችልናል የምንለውን መንገድ በኮሜንት መስጫ ሳጥን ውስጥ በማስቀምጥ እንድንማማር በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ለኮሜንት መንደርደሪያ፡- ምናልባት ፕሮፌሰሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በኛ ሲተረጎም እድራችንን እና እቁባችንን እናጠናክር የሚል አንድምታ ይኖረው ይሆን?..... ሼር
ምንጭ፡-RedOrbit

ጭንቀት ተላላፊ በሽታ እንደሆነ ተረጋገጠ
ከ ወደ nature neuroscience መንደር አእምሮንና ጭንቀትን በተመለከተ ፕሮፌሰር ጄዲፕ ቤን እና ቡድናቸው ባደረጉት ጥናት መሰረት ጭንቀት እንደሚተላለፍ ተረጋገጠ።
ጥናቱ ሁለት ወንድና ሴት ጥንድ አይጦች ላይ የተደረገ ሲሆን፡ በሂደቱ ውስጥ እንደታየው ከሆነ ወንዱ አይጥ ውስጥ የተፈጠረው ጭንቀት ወደ ሴቷ አይጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ሊተላለፍ ችሏል።
“ጭንቀትና ውጥረት ተዛማጅ በሽታዎች እንደሆኑ ጥናታችን ሊያረጋግጥ ችሏል” ያሉት ፕሮፌሰሩ “ስለሁኔታው ዘላቂነት ግን እስካሁን ያወቅነው ነገር የለም” ብለዋል።
አጥኚዎቹ ጥንዶቹን አይጦች በመነጣጠልና አንደኛውን አይጥ ብቻዉን ለጭንቀት እንዲጋለጥና ወደ አጋሩ ሳይመለስ ለብቻው እንቂቆይ ቢያደርጉም እንኳ አእምሮ ለጭንቀት ሲጋለጥ የሚመነጨው የCRH ኒውሮን በተመሳሳይ መልኩ የሴት አጋሩ አእምሮ ውስጥ ሊመነጭ ችሏል።
“ይህ በአይጦቹ ላይ የታየው ሁኔታ በሰው ልጆችም ላይ ሊሰራ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው” ያሉት የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ቤን “አስበነውም ይሁን ሳናስበው ጭንቀታችንን ለሌላ ሰው እናስተላልፋለን” ያሉ ሲሆን አክለውም “በተለይ በሚፋቀሩና ቤተሰብ በሆኑ ሰዎች ላይ ሁኔታው ይበረታል“ ብለዋል።
ተመራራማሪዎቹ ስለጥናታቸው አጠቃላይ አንድምታ ሲናገሩ እንዳሉት ከሆነ ከዚህ ምርምር የምንረዳው ትልቁ ቁም ነገር ማህበራዊ ህይወትና ስሜት ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው መሆኑንና ስለ አንዱ ጉዳት መጎዳት ያለንን ማህበራዊ ትስስር ማሳያም ጭምር እንደሆነ ነው ብለዋል።
ምንጭ፡ ScienceDaily

ጾም ከመንፍሳዊ ጥቅም ባሻገር
ጾምን የሚጾሙት መንፍሳዊ ጥቅምን ለማግኘት ነው። ነገር ግን ጾም ከመንፍሳዊ ጥቅም ባሻገር የጤና ጥቅሞችም እንዳሉት ያውቁ ኖሯል? እንግዲያውስ ፆም ከሜስገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ የተወሰኑቱን እንንገራችሁ፡-
• የኢንሱሊን መጠንን በመቆጣጠር ከዓይነት ሁለት ስኳር በሽታ ይታደጋል
ፃም በተለያዩ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ሰውነት ውስጥ የሚኖርን የስኳር መጠንን የመቀነስ በሀሪ ታይቶበታል፡፡
በተደረገው ጥናት ላይም እንታየው ከሆነ ትናንት ፆሞ የነበረ ሰው በነጋታው ጠዋት በፆም ሆዱ የስኳር መጠኑ በሚመረመርበት ጊዜ በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ከ 3-6 በመቶ መቀነስን ያሳየ ሲሆን የኢንሱሊን መጠኑ ደግሞ ከ20-31 በመቶ መቀነስን አሳይቷል፡፡
ከዛም በተጨማሪ በጥናቱ ውስጥ እንደተረጋገጠው የስኳር በሽታ መጥፎ ውጤት በመሆኑ ከሚታወቀው ከኩላሊት ውድመት ይታደጋል ተብሏል፡፡
በስተመጨረሻም ተመራማሪዎቹ ዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ ሊኖርባቸው ላሉ በሽተኞች (ድንበር ላይ ያሉ በሽተኞች) ፆምን እንደመከላከያ ቢጠቀሙት ውጤቱ ፍሬያማ ይሆናል ሲሉ መክረዋል፡፡
• ከልብ በሽታ ለመታደግ
ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ ፆም እንደ ደም ግፊት ፣ መጥፎ ኮሌስትሮል፣ የደም የስኳር መጠን እና ሌሎችንም ለልብ በሽታ መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉትን (risk factors) ሁሉ ከሰውነት የማስወገድ በሀሪ ስላለው በልብ በሽታ የመጠቃት እድልን ያጣብባል ብለዋል፡፡
ሆኖም ጉዳዩ ሰፊ ጥናት የሚስፈልገው በመሆኑ ከዚህ በላይ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር የለም ብለዋል፡፡
• ክብድት መቀነስ
በጾም ወቅት ሰውንታችን ከምግብ ሀይል ስለማያግኝ ሀይልን ፍለጋ ጉበት እና ጡንቻዎች ላይ ወደ ተጠራቀሙ ጉሉኮሶች ይጠጋል። ይህም ምግብ ከተበላ ከ8 ሰዓት በኋላ ይጀምራል።
የተከማቸዉን ግሉኮስ ከተጠቀመ በኋላ ሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ማቃጠል ይጀምራል ይህ ደግሞ በተራው ክብድት መቀነስን ያስክትላል። በተለይም ደግሞ ሆድ አከባቢ ያሉ አላስፈላጊ ስቦችን የማስወገድ አቅሙ ከፍተኛ ነው ብለወል፡፡
• የኮሌስትሮል መጠን (cholesterol levels) መቀነስ
የሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ማቃጠል ጡንቻን ለማቆየት እና የኮሌስትሮል መጠን ለመቀነስ ይረዳል።
• ሰውንት ማጥራት
ሰውነታችን ስብን(fat) በሚያቃጠል ጊዜ በሰውነታችን መርዝ የማስወገድ (detoxification) ሂድትም ይፈጠራል ።
ምክንያቱም ሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ሲያቃጠል በሰውነት ስብ ውስጥ ተከማችተው የነበሩ ማንኛውም መርዛማ ነገሮች ይሟሟሉ እንዲሁም ከሰውነታችን ይወገዳሉ።
• አእምሮ ጤና
ከትንሽ ጊዜ ጾም በኋላ ከፍ ያለ መጠን ያላቸው ኢንዶርፊኖች (endorphins) (የጥሩ ስሜት ሆርሞኖች) በደማችን ውስጥ ይመረታል ይህም አእምሮ ጤና ላይ መልካም ለውጥ ያመጣል። ሼር
ረመዳን ከሪም
ምንጭ፦ Medical News Today and healthline