TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ታይበር ዦው ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኃላፊዎች ጋራ መከሩ
=========================
የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታይበር ዦው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ቻርለስ ዲንግ ትናንት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በመገኘት ውይይት አድርገዋል፡፡ አቶ ታይበር በውይይታቸው ከቀናት በፊት አቶ ቻርለስ ዲንግ በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው በተነጋገሩበት ወቅት የተደረሱ መግባባቶች ላይ በማፅናት ከኢንስቲትዩቱ ጋራ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አንፀባርቀዋል፡፡
ከውይይቱ በተጨማሪ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ያግዝ ዘንድ ድርጅቱ ቃል በገባው መሰረት 2000 የፊት መሸፈኛ ጭንብል፣ 100 ሳኒታይዘር እና 4 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ለኢንስቲትዩቱ አበርክቷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ስለ ስጦታው ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡
ቴክ- ሳይንስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ ነገ ቅዳሜ በ10 ይጠብቁን
==========================
እንደ ወትሮው ሁሉ በነገው ፕሮግራማችንም አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ዝግጅቶችን ይዘንልዎ እንቀርባለን
• ብልሀት ሊያቀብል የሚችል አጭር ቪዲዮ ይኖረናል
• በአብይ ፕሮግራም-ሸካ ባዮስፌር ክፍል 2 ይቀርባል
• በቴክኖሎጂ ታሪክ-የህትመት ቴክኖሎጂ ይዳሰሳል
• በተመራማሪ ህይወት ታሪክ-ጅማ የግብርና እና የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ተገኝተን ፕሮፌሰር ካሳሁን በንቴ ቢሰጠኝን እናስተዋውቆታለን
አይርሱ ከልጆችዎ ጋር ሆነው ነገ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይጠብቁን (Nilesat/12520/V/27500)፡፡
https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg/featured
E-Learning during lock down በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የዌብናር ውይይት ትናንት ተደረገ
==================================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው ኢ-ለርኒንግ ላይ ያተኮረ የዌብናር ውይይት ዛሬ ተደርጓል፡፡ ተማሪዎች ከቤታቸው ሆነው ትምህርትን በሚያገኙበት አማራጭ ላይ ለመወያየት ታስቦ ውይይቱ መጠራቱን የተናገሩት በኢንስቲትዩቱ ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ባለሙያ አቶ ዘሪሁን ከበደ ኢ-ለርኒንግ ከወጪ ቁጠባና አመቺነት አንፃር የሚሰጣቸውን ጥቅሞች ብሎብ አያይዞ በሚመጣቸው ችግሮች ዙርያ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርርሜሽን ሳይንስ ትምህርት ቤት ሀላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ በሻህ በኢ-ለርኒንግ ዙርያ ለተሳታፊዎቹ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋልለ፡፡ የመሰረተ ልማት (የበይነ-መረብ)፣ ዝግጁነት እና የተማሪዎች እውነተኛነት መኖር ኢ-ለርኒንግን ለመከታተል መሰረት መሆናቸውን የገለፁት ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ ተማሪዎች ከእነርሱ ብዙ እንደሚጠበቅ አውቀው ራሳቸውን ለማስተማርና ኃላፊነትን ወስደው ለመስራት መዘጋት እንዳለባቸውና አስተማሪዎችም በዚህ ረገድ የትምህርት ግብዓቶቻቸውን ለኢ-ለርኒንግ በሚመች መልኩ ማቅረብ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡ አክለውም ኮቪድ-19 ያመጣውን ለውጥ እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ መሰረተ ልማታችንን አሳድገን በተለይ በትምርት ዘርፉ ላይ ቴክኖሎጂውን ልናውለው እንደሚገባ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቴክኖሎጂውን በሀገራችን ማዳረስ በሚቻልበት መንገድና የፈተና አሰጣጥን የተመለከቱት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ ለጥያቄዎቹ በሰጡት መልስ ቴክኖሎጂው በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት እጅግ ወሳኝ መሆኑንና ማህበረሰባችንም ለዲጂታላይዜሽን ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በፈተና አሰጣጥ ረገድም ከልምዳቸው በመነሳት ፈተናን ቀጥታ ከመስጠት ይልቅ ተማሪዎች በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡
ህፃናት በኮቪድ 19 የመጠቃት ዕድላቸው በግማሽ ያነሰ ሊሆን ይችላል
=======================
ከዓለም ዙርያ የተወሰዱ የምርመራና ክትትል መረጃዎችን ያጠኑ ሳይንቲስቶች ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ያላቸው ተጋላጭነት ከአዋቂዎች ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ያነሰ መሆኑን አሳይተዋል፡፡ የትምህርት ቤቶች መከፈት አለመከፈት ትልቅ አጀንዳ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት ይፋ የሆነው ጥናቱ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች ከ20 ዓመት በላይ ከሆኑት ጋር ሲነፃፀር ለቫይረሱ ያላቸው ተጋላጭነት በ56 በመቶ ማነሱን ጠቁሟል፡፡
አጥኚዎቹ ለጥናቱ ግብዓት ይሆናቸው ዘንድ በወረርሺኙ ዙርያ የተሰሩ ከስድስት ሺህ በላይ ፅሁፎችን የተመለከቱ ሲሆን (ምንም እንኳን አብዛኞቹ በባለሙያዎች ያልተገመገሙና ለህትመትም ያልበቁ ቢሆኑም) በህፃናት ተጋላጭነት ዙርያ ጠቃሚ መረጃን ይዘዋል ያሏቸውን 18ቱን ለይተው አውጥተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ዘጠኙ የቫይረሱን ከሰው ወደ ሰው ስርጭት የሚከታተሉ፤ ሌሎች ስምንቱ ደግሞ በቫይረሱና በበሽታ መከላከል ላይ የተሰሩ ሙከራዎችን መረጃ ይዘዋል፡፡ የተቀረው አንዱ በአባወራ ቤተሰብ ደረጃ ያለውን ስርጭት የሚያጠና ነው፡፡
በኮቪድ-19 በተጠቁ 31 አባወራ ቤተሰብ ስብስቦች ላይ የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው ሶስቱ ቤቶች ብቻ ህፃናት ወደቤታቸው ይዘውት በመምጣታቸው ሳብያ በቫይረሱ መያዛቸውን አሳይቷል፡፡ በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተሰራው ሌላ ጥናት በበኩሉ በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ ባይሆንም ህፃናት ወረርሺኙኝ ይበልጥ መቋቋም እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡
ይህ ጥናት ህፃናት የቫይረሱ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ አይደሉም ለሚለው ሀሳብ አቀንቃኞች ድጋፍን የሰጠ ሆኗል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን እንደ ሮሳሊንድ ባሉ ባለሙያዎች ከሆነ የትምህርት ቤቶች መከፈት በትምህር ቤቶች እና ማህበረሰቡ ውስጥ ስልሚኖረው የቫይረሱ ስርጭት አዲስ መረጃ ሰጪ ነው፡፡ ሆኖም የትምህርት ቤቶችን በፍጥነት መከፈት የማይደግፉ ምሁራን የመክፈቻ ቀን መቅረቡ አደገኛ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ምንም እንኳን የቫይረሱ ስርጭት ከሀገር ሀገር የተለያየ ቢሆንም በእንግሊዝ ትምህርት ቤቶች ግንቦት 24 እንደሚከፈቱ ማስታወቁን ተከትሎ ገለልተኛ የሆነ የምርመራ ኮሚቴ ቀኑን ቢያንስ በሁለት ሳምንታት ማራዘም ስጋቱን በግማሽ እንደሚቀንስ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian
የስልክ ቴክኖሎጂ ታሪክ በኢትዮጵያ
=========================
የዓለም ህዝቦችን የትስስር ታሪክ ለበጎ ከለወጡ ቴክኖሎጂዎቸ ውስጥ አንዱ ስለሆነው ስልክ የፈጠራ ታሪክ እንዲሁም በኢትዮጵያ በገባበት ወቅት ከነበሩት የቴክኖሎጂ አቀባበሎች ባለንበት ዘመን እስከደረሰበት የስርፀት መጠን ድረስ ያለውን ረጅም ሂደት አጠር አድርጋ የምትዘግበውን ይህችን ውብ ዝግጅት ይመልከቱ፡፡
መሰል ዝግጅቶቻችንን ለመመልከት ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በMOE TV የሚተላለፈውን ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችንን ይከታተሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=mBIpviZOHdk
የምርምር እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለሀገር ጥቅም ለማዋል በዘርፉ ያሉ ተቋማት ከምንጊዜውም በላይ በህብረት መስራት ይገባቸዋል
=================================
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፐሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩትን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡ ሚኒስተር ዴኤታው በጉብኝታቸው ወቅት ተቋሙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ሆኖ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን ወዳለው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት እስከተሸጋገረበት ጊዜ ድረስ ሲሰሩ በነበሩ ሰፋፊ ስራዎች እና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ በኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ገለፃ ቀርቦላቸዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የመግቢያ ንግግገር ያደረጉት የኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ተቋሙ በሃገርአቀፍ ደረጃ ፋይዳቸው የጎላ ስራዎችን ለመሰራት ትልልቅ መሰረቶችን እየጣለ ከመሆኑ አኳያ በጋራ ሊሰረባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ለመለየት እና ከአጋር ተቋማት ጋር በጥምረት ለመስራት እንዲቻል መሰል የውይይት መድረኮች መዘጋጀታቸው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም አንዳሉት የምርምር እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለሃገር በሚጠቅም መልኩ ለማዋል እና ከብዙ ትሩፋቱ ለመቋደስ እንዲቻል ተበጣጥሰው የሚገኙትን ስራዎች በአንድ ላይ በማቀናጀት ለተሻለ ጥቅም ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ሰፊ ሃሳብ የሰነዘሩት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፐሮፌሰር አፈወርቅ በምርምር እና በኢኖቬሽን ዘርፍ ሃገር አሻጋሪ ስራዎችን በጋራ ለመስራት በኢኒስቲትዩቱ የተሰሩት ስራዎች ተጨማሪ አቅም እንደሚሆኑ በማንሳት በጋራ የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች ለመለየት እና ማን ጋር ምን አለ የሚለውን ለመመለስ ውይይቱ አስፈላጊ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በገለጻቸው የምርምር እና የኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በህብረት ለመስራት ከተቋማቱ በተወጣጡ አመራሮች አማካኝነት የስራ ግብረሃይል አንዲቋቋም እና ጉዳዮችን ለይቶም ወደስራ የሚገባበት ሂደት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በወይይቱ ላይ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች ከኢኒስቲትዩቱ ጋር በህብረት በመሆን በተለይም በግዙፍ መረጃ ትንተና፣ በምርምርና ስርፀት እንዲሁም በዲጂታል ስርዓት ዝርጋታ ላይ የተሻለ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከአደማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ ከፍተኛ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በሸጎሌ በሚገኛው የኢኒስቲትዩቱ የምርምር ላብራቶሪ ማዕከልም እየተሰሩ ባሉ ሰፊ የመሰረተልማት ዝርጋታዎች ላይ ተጨማሪ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ሃለፊዎቹ በማዕከሉ በሚገኘው የአረንጓዴ ስፍራ ላይ ችግኞችን በጋራ በመትከልም ተሳትፈዋል፡፡
እንኳን ደስ ያላችሁ!
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት ከማይክሮሶፍት(4Afrika- Microsoft) ጋር በመተባበር ለአዲስ ተመራቂዎችና ለስራ ፈላጊዋችፈ በነፃ ከሶስት እስከ ስድስት ወር የሚቆይ የ Skills Lab ስልጠና አዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም AI, IoT, Data Science, Cloud DevelSoftwt and Softwarስልጠናዎችንeering ስልጠናዎችን ያካተተ ሲሆን ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን የማይክሮሶፍት ሰርተፍኬት ያገኛሉ! ይህ እድል እንዳያመልጦ አሁኑኑ ይመዝገቡ
ለመመዝገብ ከታች የተመለከተውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://gebeya.training/ethiopia/microsoft/apply
የኮሮና ቫይረስ እና የሌሊት ወፍ ግንኙነት ሚስጥር
======================
ኮቪድ-19 ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከየት ተነሳ የሚለው ነው፡፡ ብዙ ቫይረሶች ዙናቲክ ስፒሎቨር ተብሎ በሚታወቅ ሁኔታ ከእንስሳት ወደ ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡ ምንም እንኳን አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ማን እንዳመጣው እስካሁን በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የሌሊት ወፎች የጉዳዩ ዓይን ማረፊያ ሆነዋል፡፡ በአንንድ ቦታዎችም ጥፋት እየደረሰባቸው ነው፡፡
በሽታን ወደ ሰው ለማቀበል የሌሊት ወፎች ብቸኛ አይደሉም፤ ለምሳሌ አሳማዎች ኢንፍሉዌንዛን፣ ሌሎጭ የወፍ ዝርያዎችም የምዕራብ ናይል ቫይረስን፣ ሌሎች እንሰሳትም በየፊናቸው እንዲሁ፡፡ ታድያ የሌሊት ወፎች የትኩረት ምንጭ ሆኑ?
የሌሊት ወፎች ላይ የሚቀርበው አንደኛው ክስ ሳይንሳዊ ሳይሆን የትርክት መነሾ ያለው ነው፡፡ በብዙ ፊልሞች እንዳየነው የሌሊት ወፎች በቫምፓየር እና አስፈሪ ታሪኮች ላይ ተካተው ይቀርባሉ፡፡ ሌላው የክስ መነሻ ግን ሳይንሳዊ ነው፡፡ የሌሊት ወፎች ከአንታርክቲካ ውጪ ባለው ዓለም ከ1400 በላይ ዝርያ ያላቸው አጥቢ እንስሳት ናቸው፡፡ በከተማም ሆነ ተፈጥሮአዊ ቦታዎች ላይ ኑሯቸውን የመሰረቱት እነዚህ ዝርያዎች ሁሉም ቫይረሶችን የመሸከም አቅም አላቸው፡፡ አጥቢ እንስሳት መሆናቸው ደግሞ ከሌሎች ወፎች አልያም ከእባብና አዞ ቤተሰብ ከሆኑት እንስሳት (reptiles) በበለጠ ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችን በሽታን የመሸከም ዕድላቸውን ያሰፋዋል፡፡
አንዳንድ የሌሊት ወፍ ዝርያዎች በአንድ ስፍራ ታጭቀው መኖርን መምረጣቸው ደግሞ በሽታ አስተለላላፊ ተህዋሲያን በእነርሱ መካከል አልያም ከእነርሱ ተቀራርበው በበሚኖሩ ሌሎች እንስሳት ላይ በፍጥነት እንዲዛመቱ ያደርጋል፡፡ በተጨማም የሌሊት ወፎች መብረር የሚችሉ ብቸኛዎቹ አጥቢ እንስሳት መሆናቸው አይነ ምድራቸውን እንደልብ እንዲያሰራጩ ያስችላቸዋል፡፡
እዚህ ላይ ግን አስገራሚው ነገር የሚሸከሟቸውን ቫይረሶች በመቋቋም ረገድ ያላቸው ልዩ ችሎታ ነው፡፡
የሌሊት ወፎች በሚበሩበት ሰዓት ከፍተኛ ኃይልን ስለሚያወጡ የሰውነት ሙቀታቸው ከ38 እስከ 41 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡ በእነርሱ ላይ ያደሩ በሽታን አስተላላፊ ተህዋሲያንም ይህን ከፍተኛ የሙቀት መጠን የተላመዱ ስለሚሆኑ ለሰው ልጆች ይበልጥ አደገኛ ያደርጋቸዋል፤ ምክንያቱም የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓታችን በሽታ ተሸካሚ ተህዋሲያንን ለማስወገድ የሚጠቀምበትን ከፍተኛ ሙቀት የመልቀቅ ዘዴ ወይም ትኩሳትን ዋጋ አልባ ሊያደርግ ስለሚችል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታን ከማተላለፋቸው ጎን ለጎን ጥሩ ጎንም አላቸው፡፡ ለምሳሌ ብዙዎቹ የሌሊት ወፍ ዝርያዎች ነፍሳትን ተመጋቢ በመሆናቸው እህልና ሌሎች የእፅዋት ዝርያዎችን የሚያጠቁ ተባዮችን በማፅዳት ቀላል የማይባል ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ ሌላው በጥሩ የሚነሳው በሳይንሳዊ ምርምር ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ነው፡፡ ለምሳሌ ጠቃሚ የዘረ-መል ስንስል ለውጦች (mutation) እንዴት በሰዎች ውሰጥ የተለመዱ እንደሚሆኑ ለማወቅ በሚደረግ ጥናት ውስጥ የሌሊት ወፎች በግብዓትነት እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማም በማርጀት፣ ካንሰር፣ በሽታ መከላከል እና ባዮሜትሪክ ምህንድስና ምርምሮች ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ኮቪድ-19 እንዲሁም ሌሎች ቫይረሶችን በመዋጋት ውስጥ የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡ ከላይ እንዳስቀመጥነው የሰው ልጆችን ለሞት የሚዳርጉ ብዙ ቫይረሶች የሌሊት ወፎችን ሊገድሉ ይቅርና ህመም እንኳን አይፈጥሩባቸውም፡፡ በዚህ ላይ የሚደረግ ምርምር አሁን ለገባንበትም ሆነ ወደፊት ለሚከሰቱ ወረርሺኞች የመፍትሄ ቁልፍ ሊሆን ይችላል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የበሽታውን ምንጭ የሚያፈላልጉ ጥናቶች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ አስካሁን ባለው መረጃ መሰረትም የቫይረሱ መነሻ ከሌሊት ወፎች ዘንድ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ በሰዎች ውስጥ የተገኘው የበሽታው የዘረ-መል ውስጥ ቅንጣት (genome) በሌሊት ወፎች ውስጥ ካለው ጋር ሲነፃፀር 96 በመቶ ተመሳሳይ ነው፡፡ ነገር ግን ቫይረሱ ከነዚህ በራሪዎች ተነሳ ቢባል እንኳን ተጠያቂው የሰው ልጅ ነው፡፡ ተፈጥሮ በውስጧ አምቃ የያዘቻቸው ብዙ አደገኛ ቫይረሶች አሉ፡፡ ታድያ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ባጠፋ ቁጥር ከነዚህ አደገኛ ቫይረሶች ጋራ ያለው ትውውቅ መጨመሩ አይቀሬ ነው፡፡
ምንጭ፡ Live science
የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን እንዳያጡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል
================================
የኮቪድ 19 ወደከባድ የጤና ችግር እንዲያመራ እንደ ሳምባ ነቀርሳ፣ የደም ግፊት እና የልብ በሽታ ያሉ ተያያዥ የጤና እክሎች ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው በተደጋጋገሚ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ በተለይም ከሳምባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንደአስምና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቫይረሱ ይበልጥ አቅም እንዲያገኝ በማድረግ የጤናችንን ሁኔታ አደጋ ውስጥ እንዲገባ ምከንያት ይሆናሉ፡፡ ከእነዚህ የጤና እክሎች በተጨማሪ የስኳር በሽታ ሌላው ለኮሮናቫይረስ መባባበስ ትልቅ ምክንያት የሆነ ተጓዳኝ የጤና ችግር ሲሆን፤ ተመራማሪዎችም እንደሌሎቹ የጤና እክሎች ሁሉ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡
ከሰሞኑ በወጣ እንድ ጥናት እንደተገለፀው የስኳር በሽታ ካለባቸው አስር የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መካከል እንዱ በሳምንት ውስጥ ህይወቱን የሚያጣበት እድል ሊኖር የሚችል በመሆኑ መሰል የጤና እክል ላለባቸው ሰዎች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡ በፈረንሳይ የሚገኙት እነዚህ ተመራማሪዎች የስኳር በሽታ ኖሮባቸው በኮሮናቫይረስ በተጠቁ 1,300 ሰዎች ላይ ባደረጉት ምርመራና ክትትል 29 በመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች የትንፋሽ ማገዣ መሳሪያ ካልተገጠመላቸው ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ለጥናቱ ከመረጧቸው ታካሚዎች መካካል 89 በመቶ የሚሆኑት አይነት 2 በተባለው የስኳር በሽታ የተያዙ ሲሆን፤ እድሜያቸውም ከ50 እስከ 70 የሚገመት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በጥናቱ ላይ እንደታየው የኮሮናቫይረስ በእጅጉ ፀንቶባቸው በኣይ ሲ ዩ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ የሚደረጉት የስኳር በሽታ ታካሚዎች በቬንትሌተርና መሰል የህክምና ቁሳቁሶች የማይታገዙ ከሆነ ሆስፒታል በገቡ በአንድና በሁለት ሳምንታት ውስጥ ህይወታቸውን የሚያጡበት እድል እንዳለ ተመራማሪዎቹ ያስረዳሉ፡፡ በተለይም እድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት የሚታይባቸው እና በአብዛኛውም የወንድ ጾታ ያላቸው የበሽታው ተጠቂዎች ከቀዳሚዎቹ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች በኋላ በሚኖሩት የትንፋሽ መቆራረጥ ሂደቶች ውስጥ ህይወታቸውን ከመቅፅበት እንደሚያጡ ተማራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
ከዚህ በፊት በኢንፍሉዬንዛ እና የኮሮናቫይረስ ቤተሰብ በሆኑ ሌሎች ቫይረሶች እንደታየው የስኳር በሽታ ኬዞች ይበልጥ ወደተባባሰ የጤና ችግር ሊያመሩ መቻላቸውን የሚያስረዱት ተመራማሪዎች እንደአውሮፓውያኑ በ2009 ተከስቶ በነበረው H1N1 በሚባለው አለምአቀፍ ወረርሽኝ ላይ ህይወታቸውን ካጡ ብዙ ሰዎች መካከል የስኳር በሽታ የነበረባቸው ታካሚዎች ከፍጠኛ ቁጥር እንደሚያዙ ያስታውሳሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ ይህን አደጋ በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ ታካሚዎች በሃኪም የታዘዘላቸውን የኢንሱሊን መድሃኒት በሚገባ እንዲወስዱ እና የጤና ባለሙያዎች የሚመክሯቸውን የአኗኗር ሂደትም በሚገባ እንዲተገብሩ ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡ ምንጭ፡ ሲ ኤን ኤን
ለኮሮናቫይረስ ሲባል ከመጠን ያለፈ አንቲባዮቲክ መጠቀም ለተጨማሪ ሞት ሊዳርግ እንደሚችል WHO አስጠነቀቀ
==============================
===========
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው የአንቲባዮቲክ (antibiotic) መድሃኒት ጎጂነት ያላቸው ባክቴሪያዎችን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ከባድ እንደሚያደርገው እና በሂደትም ሌላ ቀውስና አደጋ ወደዓለማችን ይዞ እንደሚመጣ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስጠንቅቀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በትላንትናው ዕለት በነበራቸው የቪዲዮ ኮንፈረንስ መግለጫ እንዳስታወቁት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ገደብ በሌለው የአንቲባዮቲክ አጠቃቀም የተነሳ ብቻ መድሃኒቶችን በቀላሉ መገዳደር እንዲችል እና ለሌላ ተጨማሪ ቀውስና ሞት ዋና ምክንያት መሆኑ አንደማይቀር አስረድተዋል፡፡
በኮቪድ 19 የተጠቁ አንዳንድ ሰዎች ቫይረሱ ይዞባቸው የሚመጣውን ተያያዥ የባክቴሪያል ኢንፌክሽን ለመከላከል አንዲችሉ WHO በሚያስቀምጠው የአንቲባዮቲክ አጠቃቀም መመሪያ መሰረት መሰል መድሃኒቶችን እንዲወስዱ የሚፈቀድ ቢሆንም፤ ብዙዎች ግን ያለምክንያት እና ከተቀመጠው መመሪያ ውጭ የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶቹን በብዛት እየተጠቀሙ እንደሚገኝ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ እነዚህ የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ሰውነታችን ውስጥ ለሚከሰቱ የተለያዩ የባክቴሪያል ኢንፌክሽኖች ማጥፊያና መዋጊያ ተብለው የሚሰሩ ቢሆኑም አሁን ባለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በገፍ ጥቅም እየዋሉ መምጣታቸው ተገልጿል፡፡ ይህ ደግሞ ባክቴሪያዎቹ መድሃኒቶቹን በቀላሉ እንዲገዳደሩ (Antibiotic resistance እንዲፈጠር) እና በሂደትም የመድሃኒቶቹን የተዋጊነት አቅም በማውረድ ባክቴሪያዎች በሰዎች ላይ የሚኖራቸውን የረዥም ጊዜ ተፅዕኖ ከፍተኛ እንደሚያደርገው ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በአንዳንድ ሃገሮች ላይ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሀገራት ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ መጠን ያለው የአንቲባዮቲክ መድሃኒት ጥቅም ላይ እያዋሉ መምጣታቸው እና በሌሎች ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ደግሞ በእነዚሁ የመድሃኒት አጥረቶች ምክንያት ተጨማሪ ሞት እና አደጋ እየተመዘገበ መምጣቱን አስታውቋል፡፡ እንዲህ አይነት ችግሮች በመላው አለም በስፋት እየታዩ በሚገኝበት ሁኔታ በወረርሽኙ ሰበብ አድርጎ የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን በዚህ ልክ ጥቅም ላይ ማዋል በአለማችን ላይ ሌላ አደጋ መጥራት ነው የሚሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እየሄድንበት ያለው ሁኔታ በጣም አስፈላጊ የሚባሉትን አንቲማይክሮቢያል መድሃኒቶች ከጥቅም ውጭ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian