የሁዋዌይ የኢትዮጵያ ሀላፊ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተገኝተው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል
===================
በኢትዮጵያ የሁዋዌይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቻርለስ ዲንግ እና የአካውንት ማናጀሯ ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንቲትዩት ተገኝተው በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ መግቢያ ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገፅታ የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክተር በሆኑት አቶ በረከት ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ተቋማት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ተግባራትም በገለፃው ተካቶ ቀርቧል፡፡
ሁዋዌይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ያለውን ተሳትፎና በተለይም የዳታ ሴንተሮች ግንባታና ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጡና በመሰጠት ላይ ያሉ ስልጠናዎችን አቶ ቻርለስ ዲንግ እና ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በውይይቱ ወቅት ያብራሩ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ጋራም ወደፊት በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍቃደኝነት ገልፀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሙቀት መለኪያ መሳርያ፣ የፊት መሸፈኛ ጭንብል እና ሳኒታይዘሮችን ለመለገስ ቃል ገብተዋል፡፡
የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለተለያዩ ችግሮች ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄ የሚሰጡ ስራዎችን ለብዙ ሀገር አቀፍ ተቋማት ሰርቶ ማስረከቡን ለእንግዶቹ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም ሁዋዌይ ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከመሆኑም ባሻገር ለታዳጊ ሀገራት አጋር ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከኩባንያው ጋራ ኮቪድ-19ኝን ጨምሮ በኢኖቬሽን ማዕከላት እንዲሁም በዲጂታላይዜሽን ረገድ ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ታልሞ በተቀረፀው የቴክ ፎር ኦል ፕሮጀክት ዙርያና ሌሎችም የትብብር መስኮች ኢንስቲትዩቱ በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት “E-learning during the lock down” በሚል ርዕስ ዌብናር አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሰረት በቪድዮ በሚደረገው በዚህ ውይይት ለመሳተፍ ከፈለጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት ይመዝገቡ፡፡ ውይይቱ አርብ ግንቦት 14 2012፣ ከቀኑ 8ሰዓት ይካሄዳል፡፡
Technology and innovation institute is hosting a webinar on “E-learning during the lock down”. So if you wish to participate in this video conference, register using the link below. The conference will be held in Friday may 22, at 2pm.
https://docs.google.com/forms/d/1lFbYsXDR3SrYjzI8EJb7OOR9zp1SJc1XUOIRfq_Q9Kw/viewform?edit_requested=true

በኮቪድ 19 ዙሪያ ችግር ፈቺ ፈጠራዎቸን ያቀረቡ ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው
===================================
በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በጋራ በመሆን covid-19 solution challenge በሚል የተዘጋጀው የፈጠራ ባለሙያዎች የውድድር ፕሮግራም በዛሬው ዕለት የእውቅና እና የሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ ለአንድ ወር በዘለቀው በዚህ የፈጠራ ባለሙያዎች ውድድር በጠቅላላው 446 ፕሮጀክቶች ቀርበው ከፍተኛ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ 30 ፕሮጀክቶች ወደቀጣዩ የግምገማ ሂደት ያለፉ መሆናቸውን ያስረዱት የግብረ ሃይሉ ዋና መሪ አቶ ሙሉቀን ቀሬ፤ እጅግ በጥንቃቄ በተለዩ መስፈርቶች አማካኝነትም በፍጥነት ወደስራ ሊገቡ የሚችሉት እና አዋጭነታቸው የተረጋገጡ 12 ፕሮጀክቶች መመረጣቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህ የፈጠራ ውድድር ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ያቀረቡ ባለሙያዎች እንደሃገር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ያስረዱት የUNDP ተወካይ አቶ ግዛቸው ሲሳይ መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማገዝም ተቋሙ የበኩሉን ድርሽ እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ስነስርዓት አዋጭነታቸው ተረጋግጦ የገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎች እንዲያገኙ ከተመረጡ 12 ፕሮጀክቶች ውስጥ አራት የሚሆኑት የቬንትሌተር መሳሪያዎች ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከእጅ ንክኪ የፀዱ የእጅ መታጠቢያዎች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የሶፍትዌር ስራዎች ናቸው፡፡
በዚህ ስነስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተጋበዙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ወረርሽኙን ለመከላከል የቀረቡት የፈጠራ ሃሳቦች በሃገርበቀል ደረጃ እምቅ የፈጠራ ሃብት እንዳለ የተረዳንበት ነው ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስቴሩ አክለውም የተመረጡትን እነዚህን ፕሮጀክቶች ወደመሬት በማውረድ ህበረተሰቡ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ የተሟላ ድጋፍ እንደሚደረግ እና ሌሎች በግሉ ዘርፍ ያሉ ተቋማትም ፈጠራዎቹ ወደ ኮመርሺያላዜሽን እንዲያመሩ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ታይበር ዦው ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኃላፊዎች ጋራ መከሩ
=========================
የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታይበር ዦው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ቻርለስ ዲንግ ትናንት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በመገኘት ውይይት አድርገዋል፡፡ አቶ ታይበር በውይይታቸው ከቀናት በፊት አቶ ቻርለስ ዲንግ በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው በተነጋገሩበት ወቅት የተደረሱ መግባባቶች ላይ በማፅናት ከኢንስቲትዩቱ ጋራ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አንፀባርቀዋል፡፡
ከውይይቱ በተጨማሪ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ያግዝ ዘንድ ድርጅቱ ቃል በገባው መሰረት 2000 የፊት መሸፈኛ ጭንብል፣ 100 ሳኒታይዘር እና 4 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ለኢንስቲትዩቱ አበርክቷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ስለ ስጦታው ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡

ቴክ- ሳይንስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ ነገ ቅዳሜ በ10 ይጠብቁን
==========================
እንደ ወትሮው ሁሉ በነገው ፕሮግራማችንም አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ዝግጅቶችን ይዘንልዎ እንቀርባለን
• ብልሀት ሊያቀብል የሚችል አጭር ቪዲዮ ይኖረናል
• በአብይ ፕሮግራም-ሸካ ባዮስፌር ክፍል 2 ይቀርባል
• በቴክኖሎጂ ታሪክ-የህትመት ቴክኖሎጂ ይዳሰሳል
• በተመራማሪ ህይወት ታሪክ-ጅማ የግብርና እና የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ተገኝተን ፕሮፌሰር ካሳሁን በንቴ ቢሰጠኝን እናስተዋውቆታለን
አይርሱ ከልጆችዎ ጋር ሆነው ነገ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይጠብቁን (Nilesat/12520/V/27500)፡፡
https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg/featured

E-Learning during lock down በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የዌብናር ውይይት ትናንት ተደረገ
==================================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው ኢ-ለርኒንግ ላይ ያተኮረ የዌብናር ውይይት ዛሬ ተደርጓል፡፡ ተማሪዎች ከቤታቸው ሆነው ትምህርትን በሚያገኙበት አማራጭ ላይ ለመወያየት ታስቦ ውይይቱ መጠራቱን የተናገሩት በኢንስቲትዩቱ ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ባለሙያ አቶ ዘሪሁን ከበደ ኢ-ለርኒንግ ከወጪ ቁጠባና አመቺነት አንፃር የሚሰጣቸውን ጥቅሞች ብሎብ አያይዞ በሚመጣቸው ችግሮች ዙርያ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርርሜሽን ሳይንስ ትምህርት ቤት ሀላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ በሻህ በኢ-ለርኒንግ ዙርያ ለተሳታፊዎቹ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋልለ፡፡ የመሰረተ ልማት (የበይነ-መረብ)፣ ዝግጁነት እና የተማሪዎች እውነተኛነት መኖር ኢ-ለርኒንግን ለመከታተል መሰረት መሆናቸውን የገለፁት ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ ተማሪዎች ከእነርሱ ብዙ እንደሚጠበቅ አውቀው ራሳቸውን ለማስተማርና ኃላፊነትን ወስደው ለመስራት መዘጋት እንዳለባቸውና አስተማሪዎችም በዚህ ረገድ የትምህርት ግብዓቶቻቸውን ለኢ-ለርኒንግ በሚመች መልኩ ማቅረብ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡ አክለውም ኮቪድ-19 ያመጣውን ለውጥ እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ መሰረተ ልማታችንን አሳድገን በተለይ በትምርት ዘርፉ ላይ ቴክኖሎጂውን ልናውለው እንደሚገባ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቴክኖሎጂውን በሀገራችን ማዳረስ በሚቻልበት መንገድና የፈተና አሰጣጥን የተመለከቱት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ጥበበ ለጥያቄዎቹ በሰጡት መልስ ቴክኖሎጂው በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት እጅግ ወሳኝ መሆኑንና ማህበረሰባችንም ለዲጂታላይዜሽን ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በፈተና አሰጣጥ ረገድም ከልምዳቸው በመነሳት ፈተናን ቀጥታ ከመስጠት ይልቅ ተማሪዎች በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡

ህፃናት በኮቪድ 19 የመጠቃት ዕድላቸው በግማሽ ያነሰ ሊሆን ይችላል
=======================
ከዓለም ዙርያ የተወሰዱ የምርመራና ክትትል መረጃዎችን ያጠኑ ሳይንቲስቶች ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ያላቸው ተጋላጭነት ከአዋቂዎች ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ያነሰ መሆኑን አሳይተዋል፡፡ የትምህርት ቤቶች መከፈት አለመከፈት ትልቅ አጀንዳ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት ይፋ የሆነው ጥናቱ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች ከ20 ዓመት በላይ ከሆኑት ጋር ሲነፃፀር ለቫይረሱ ያላቸው ተጋላጭነት በ56 በመቶ ማነሱን ጠቁሟል፡፡
አጥኚዎቹ ለጥናቱ ግብዓት ይሆናቸው ዘንድ በወረርሺኙ ዙርያ የተሰሩ ከስድስት ሺህ በላይ ፅሁፎችን የተመለከቱ ሲሆን (ምንም እንኳን አብዛኞቹ በባለሙያዎች ያልተገመገሙና ለህትመትም ያልበቁ ቢሆኑም) በህፃናት ተጋላጭነት ዙርያ ጠቃሚ መረጃን ይዘዋል ያሏቸውን 18ቱን ለይተው አውጥተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ዘጠኙ የቫይረሱን ከሰው ወደ ሰው ስርጭት የሚከታተሉ፤ ሌሎች ስምንቱ ደግሞ በቫይረሱና በበሽታ መከላከል ላይ የተሰሩ ሙከራዎችን መረጃ ይዘዋል፡፡ የተቀረው አንዱ በአባወራ ቤተሰብ ደረጃ ያለውን ስርጭት የሚያጠና ነው፡፡
በኮቪድ-19 በተጠቁ 31 አባወራ ቤተሰብ ስብስቦች ላይ የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው ሶስቱ ቤቶች ብቻ ህፃናት ወደቤታቸው ይዘውት በመምጣታቸው ሳብያ በቫይረሱ መያዛቸውን አሳይቷል፡፡ በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተሰራው ሌላ ጥናት በበኩሉ በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ ባይሆንም ህፃናት ወረርሺኙኝ ይበልጥ መቋቋም እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡
ይህ ጥናት ህፃናት የቫይረሱ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ አይደሉም ለሚለው ሀሳብ አቀንቃኞች ድጋፍን የሰጠ ሆኗል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን እንደ ሮሳሊንድ ባሉ ባለሙያዎች ከሆነ የትምህርት ቤቶች መከፈት በትምህር ቤቶች እና ማህበረሰቡ ውስጥ ስልሚኖረው የቫይረሱ ስርጭት አዲስ መረጃ ሰጪ ነው፡፡ ሆኖም የትምህርት ቤቶችን በፍጥነት መከፈት የማይደግፉ ምሁራን የመክፈቻ ቀን መቅረቡ አደገኛ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ምንም እንኳን የቫይረሱ ስርጭት ከሀገር ሀገር የተለያየ ቢሆንም በእንግሊዝ ትምህርት ቤቶች ግንቦት 24 እንደሚከፈቱ ማስታወቁን ተከትሎ ገለልተኛ የሆነ የምርመራ ኮሚቴ ቀኑን ቢያንስ በሁለት ሳምንታት ማራዘም ስጋቱን በግማሽ እንደሚቀንስ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

የስልክ ቴክኖሎጂ ታሪክ በኢትዮጵያ
=========================
የዓለም ህዝቦችን የትስስር ታሪክ ለበጎ ከለወጡ ቴክኖሎጂዎቸ ውስጥ አንዱ ስለሆነው ስልክ የፈጠራ ታሪክ እንዲሁም በኢትዮጵያ በገባበት ወቅት ከነበሩት የቴክኖሎጂ አቀባበሎች ባለንበት ዘመን እስከደረሰበት የስርፀት መጠን ድረስ ያለውን ረጅም ሂደት አጠር አድርጋ የምትዘግበውን ይህችን ውብ ዝግጅት ይመልከቱ፡፡
መሰል ዝግጅቶቻችንን ለመመልከት ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በMOE TV የሚተላለፈውን ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችንን ይከታተሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=mBIpviZOHdk

YouTube
የስልክ ቴክኖሎጂ ታሪክ በኢትዮጵያ History of Telephone Technology in Ethiopia
የስልክ ቴክኖሎጂ በአለም መቼ ተጀመረ?ወደ አፍሪካ እንዴት ገባ ?ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያስ መች እና እንዴት ገባ?ከገባ በኋላስ ያለዉ አቀባበል ምን ይመስል ነበር የሚለዉ በዚህ ፕሮግራም ስር ተካቷል፡፡