የኮሮናቫይረስ በጤና አገልግሎቱ ላይ በሚያሳርፈው ከፍተኛ ተፅዕኖ ምከንያት 6,000 ህፃናት በየቀኑ ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ Unicef አስታወቀ
=======================
የኮሮናቫይረስ በሚያስከትላቸው ተያያዥ ችግርች እና የጤና አገልግሎት መዳከም ጋር ተያይዞ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ስድስት ሺ የሚጠጉ ህፃናት በየቀኑ ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት አሳስቧል፡፡ ዩኒሴፍ በዘገባው እንደሚለው የዕለት ተዕለት የጤና አገልግሎቶች በወረርሽኙ ምክንያት ከመጎደታቸው አኳያ የቤተሰብ እቅድ፣ ከወሊድ በፊትና በኋላ የሚኖር የጤና ክትትል እንዲሁም የህፃናት የክትባት ሁኔታዎች በወረርሽኙ ምክንያት ይበልጥ ከባድ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡
ወረርሽኙ ባለፉት አስርት ዓመታት የህፃናትን ሞት ለመቀነስ የተደረጉትን አበረታች እንቅስቃሴዎች ወደኋላ የመመለስ ስጋት እንደሚኖረው የሚያነሳው ድርጅቱ ይህን አደጋ በስፋት በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጤና አገልግሎቱን መደገፍ ወሳኝ እንደሚሆን ያስረዳል፡፡ አሁን የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽ አለማችን ለመጨረሺያ ጊዜ ካስተናገደችው የሁለተኛ አለም ጦርነት መዓት በኋላ ሌላኛው ፈተና መሆኑን የሚናገሩት በእንግሊዛ የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ሳቻ ዳሽሞክ በቫይረሱ ተዘዋዋሪ ተፅዕኖ የተነሳ ብዙ ህፃናት መከላከል በሚቻሉ ምክንያቶች ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ህፃናት ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ መሳሳቱ፣ ድንበሮች መታገዳቸው፣ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው እና የምግብ አቅርቦት ሁኔታው አደጋ ላይ መውደቁ የችግሩ ስፋት ጥልቅ እንዲሆን ዋና ምክንያት ናቸው ይላሉ፡፡
በድርጅቱ ትንተና መሰረት ሊያጋጥም ይቸላል የሚባለው አደጋ በመጠኑ (optimistic scenario) ሲታይ የጤና አገልግሎቱን በ15 በመቶ በመቀነስ የህፃናትን ሞት በ9.8% ከፍ የሚደርገው ሲሆን፤ የእናቶችን የሞት መጠን ደግሞ 8.3% በማድረስ በየቀኑ 1,400 የሚሆኑ ህፃናት ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል አደጋው በከባድ ሁኔታ ሲታይ (worst-case scenario) በወረርሽኙ ምክንያት የጤና አገልግሎቱ በ45 በመቶ በመቀነስ የህፃናቱን የሞት መጠን ወደ 44.7% ሊያደርሰው እንደሚችል እና የእናቶችም የሞት መጠን ወደ 38.6% ከፍ ሊል እንደሚችል በዘገባው ገልጿል፡፡
ይህ አደጋ አንዣቦባቸዋል የሚባሉት ሃገራት የጤና ስርዓታቸው እጅግ ደካማ ነው ሊባል ባይችልም ከሌሎች ተያያዥ ውስጣዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ለአደጋው ተጋላጭ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ ከእነዚህ ሃገራት መካከል ባንግላዲሽ፣ ብራዜል፣ ፓኪስታን እና ኡጋንዳ በወናነት የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ለአዳገው ተገላጭ ከሆኑት ሀገራት ማካከል አንደኛዋ ነች፡፡
The Guardian

ኮሮናቫይረስ ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ ሊኖር ይችላል
=================================
የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት በትላንትናው እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በኮቪድ 19 ወረርሽኛ ዙሪያ ወደፊት በሚጠበቁ ሁነቶች እና ተያያዥ ምልከታዎች ላይ ሰፊ ገለፃ ሰጥቷል፡፡ በዕለቱ በነበረው የጋራ መግለጫ የተቋሙ ኢመርጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ማይክ ርያን ከወረርሽኙ የወደፊት እጣፋንታ ጋር በተያያዘ እንደተናገሩት ምንም እንኳን ለበሽታው የሚሆን ክትባቶች በቅርብ ጊዜ ሊደርሱ ቢችሉም፤ ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚያስፈልገው አቅም ግን እጅግ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
ወረርሽኙ በአለም አቀፍ ደረጃ 4.3 ሚለዮን ሰዎችን በማጥቃት ለ300,000 ሰዎች ደግሞ የሞት ምክንያት በሆነበት በአሁን ወቅት ብዙዎች ለጭንቀት እና ለአዕምሮ ህመም የመጋለጥ እድል እንደሚኖራቸው በመገንዘብ ሁሉም መንግስታት ለአዕምሮ ጤና የሰጡትን ትኩረት ማሳደግ እንደሚገባቸውም ድርጅቱ በመግለጫው አሳስቧል፡፡ የኮሮናቫይረስ ከዚህ ቀደም በማህበረሰባችን እንደተከሰቱት ሌሎች ቫይረሶች ሁሉ ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል የሚሉት ዶ/ር ማይክ ርያን፤ ኤች አይ ቪ ከሰዎች ጋር የሚኖርበትን ሁኔታና ሰዎችም ለቫይረሱ የሚሰጡትን ምላሽ እንደምሳሌ እንስተው ያስረዳሉ፡፡
አሁን ላይ በስፋት እየተነገረ እንደሚገኘው ቢያንስ 100 የሚጠጉ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተለያዩ ሙከራዎችን በማለፍ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ይሁንና እንደ ዶ/ር ማይክ ርያን ገለፃ አሁን ላይ የትኛውም አካል ቫይረሱ የሚጠፋበትን ትክከለኛ ጊዜ በእርግጠኝነት ማወቅ እንደማይችል እና ምናልባት የኩፍኝ በሽታ ክትባት ተገኘቶለት እንኳን ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ እንደቆየ ሁሉ የኮሮናቫይረስም እንዲሁ ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ ሊዘልቅ እንሚችል መገንዘብ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ ዶ/ር ርያን ይህን ሃሳብ በመግለጫው ላይ ቢያነሱም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እየተደረጉ ያሉ እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች አሁን ካለው ተጠናክረው ቢቀጥሉ ወረርሽኙን ለማቆም አሁንም እድል እንዳለ ይናገራሉ፡፡
ብዙ ሃገራት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወሰዱትን ትልልቅ እርምጃዎች በመጠኑም ቢሆን እያላሉ እና የቆመውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደነበረበት ለመመለስ እየጣሩ የሚገኝ ቢሆንም፤ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ግን ይህ ሁኔታ ለሌላ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ ሃገራት እየወሰዷቸው የነበሩ እርምጃዎች እያቀለሉ መምጣታቸው የሚመከር አይደለም የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ሆነን ቫይረሱን የምንቆጣጠርበትን መንገድ መፈለግ እጅግ የሚበጅ ነው ይላሉ፡፡
ቢቢሲ

CDC ኮሮናቫይረስ በህፃናት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ከባድ የጤና ቀውስ እያስጠነቀቀ ነው
=================================
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) በትላንትናው ዕለት ለብዙ ሺ የሃገሪቱ ዶክተሮች በሰጠው ማስጠንቀቂያ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ህፃናት ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የተለያየ የበሽታ ምልክቶች ወይም (syndromes) በሚገባ እንዲያጤኑ እና በትኩረት እንዲከታተሉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል የሚባለው ይህ ሲንድረም multisystem inflammatory syndrome (MIS-C) ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በአውሮፓ በተለያዩ ሀገራት እና በአሜሪካ በ18 ግዛቶች ሊገኝ እንደቻለም ተገልጿል፡፡
በእንግሊዝ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ይህን መሰሉን ሲንድረም ለመጀመሪያ ጊዜ ያጤኑት በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ ቢሆንም ከሶስትና ከአራት ሳምንታት በኋላ ቁጥሩ አይሎ በሌሎች ሃጋራት እየተስተዋለ መምጣቱም ተነግሯል፡፡ በቦስተን የጤና ትምህርት ቤት እና የህፃናት ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ጄፍሪ በርንስ እንደሚያስረዱት ከአምስትና ከስድስት ሳምንታት ቢፊት ጉዳዩን ስንምለከተው በባክቴሪያ የተመረዘ የሰውነት ጥቃት (toxic shock) መስሎን የነበረ ቢሆንም፤ ቆይቶ ግን ቁጥሩ እየጨመረና ሌላ መለክ እየያዘ መምጣቱን ተረድተናል ብለዋል፡፡ ይህ ሲንድረም Kawasaki ተብሎ ከሚታወቀው ተያያዥ የህፃናት በሽታ ጋር በብዛት ቢመሳሰልም በህፃናት ላይ ከሚኖረው ከባድ የጤና ቀውስ አንጻር በጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባው CDC ያስገነዝባል፡፡
ተቋሙ በኒውዮርክ አገኘኋቸው የሚላቸውን 110 ተመሳሳይ የሲንድረም ኬዞች በመጥቀስ በጉዳዩ ላይ የሚያደርገውን ተጨማሪ ምርመራ እስከሚያጠናክር የጤና ባለሙያዎች ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ በህፃናት ላይ የሚመለከቷቸውን ተቀራራረቢ ምልክቶች በሚገባ እንዲያጤኑ እና መረጃዎችንም ለጤና ተቋማት እንዲልኩ አሳስቧል፡፡ ይህ ሲንድረም በሰውነታችን ውስጥ በሚከሰቱ ጎጂ ተህዋሲያን (pathogens) የተነሳ በአካላችን የሚሰጡ ባዮሎጂካል ምላሾችን የሚሳይ ሲሆን፤ ትኩሳት ተቅማጥ እና ሌሎች ተያያዥ ምልክቶች በስፋት የሚታዩበት ነው፡፡ ሲንድረሙ በተለይም የተለያዩ የሰውነት ክፈሎች ስራቸውን በትክክል እንዳይከውኑ ሊያደርጋቸው ሲለሚችል የሰውነት መቆጣት እና እብጠት አልፎ አልፎ ሊታይ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ይህ አይነቱ ሲንድረም በህፃናት ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም በልጆች ላይ የሚኖረው ከባድ የጤና ቀውስ ከፍተኛ በመሆኑ ተያያዣ ምልክቶች የሚታዩባቸውን ህፃናት ተኝተው እንዲታከሙ በማድረግ፣ እንደ Kawasaki ያሉ በሽታዎች የታዩባቸውን ህፃናት በሚገባ በመከታተል እና ከዚህ በፊት በዚህ ሲንድረም ተይዘው የሞቱ ካሉ በመመርመር አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተቋሙ ያስገንዝባል፡፡
ምንጭ፡ CNN እና Healthy Children

የሁዋዌይ የኢትዮጵያ ሀላፊ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተገኝተው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል
===================
በኢትዮጵያ የሁዋዌይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቻርለስ ዲንግ እና የአካውንት ማናጀሯ ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንቲትዩት ተገኝተው በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ መግቢያ ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገፅታ የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክተር በሆኑት አቶ በረከት ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ተቋማት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ተግባራትም በገለፃው ተካቶ ቀርቧል፡፡
ሁዋዌይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ያለውን ተሳትፎና በተለይም የዳታ ሴንተሮች ግንባታና ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጡና በመሰጠት ላይ ያሉ ስልጠናዎችን አቶ ቻርለስ ዲንግ እና ወ/ሮ ሰላም አብረሀም በውይይቱ ወቅት ያብራሩ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ጋራም ወደፊት በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍቃደኝነት ገልፀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሙቀት መለኪያ መሳርያ፣ የፊት መሸፈኛ ጭንብል እና ሳኒታይዘሮችን ለመለገስ ቃል ገብተዋል፡፡
የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለተለያዩ ችግሮች ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄ የሚሰጡ ስራዎችን ለብዙ ሀገር አቀፍ ተቋማት ሰርቶ ማስረከቡን ለእንግዶቹ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም ሁዋዌይ ግንባር ቀደም የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከመሆኑም ባሻገር ለታዳጊ ሀገራት አጋር ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከኩባንያው ጋራ ኮቪድ-19ኝን ጨምሮ በኢኖቬሽን ማዕከላት እንዲሁም በዲጂታላይዜሽን ረገድ ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ታልሞ በተቀረፀው የቴክ ፎር ኦል ፕሮጀክት ዙርያና ሌሎችም የትብብር መስኮች ኢንስቲትዩቱ በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት “E-learning during the lock down” በሚል ርዕስ ዌብናር አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሰረት በቪድዮ በሚደረገው በዚህ ውይይት ለመሳተፍ ከፈለጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት ይመዝገቡ፡፡ ውይይቱ አርብ ግንቦት 14 2012፣ ከቀኑ 8ሰዓት ይካሄዳል፡፡
Technology and innovation institute is hosting a webinar on “E-learning during the lock down”. So if you wish to participate in this video conference, register using the link below. The conference will be held in Friday may 22, at 2pm.
https://docs.google.com/forms/d/1lFbYsXDR3SrYjzI8EJb7OOR9zp1SJc1XUOIRfq_Q9Kw/viewform?edit_requested=true

በኮቪድ 19 ዙሪያ ችግር ፈቺ ፈጠራዎቸን ያቀረቡ ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው
===================================
በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በጋራ በመሆን covid-19 solution challenge በሚል የተዘጋጀው የፈጠራ ባለሙያዎች የውድድር ፕሮግራም በዛሬው ዕለት የእውቅና እና የሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ ለአንድ ወር በዘለቀው በዚህ የፈጠራ ባለሙያዎች ውድድር በጠቅላላው 446 ፕሮጀክቶች ቀርበው ከፍተኛ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ 30 ፕሮጀክቶች ወደቀጣዩ የግምገማ ሂደት ያለፉ መሆናቸውን ያስረዱት የግብረ ሃይሉ ዋና መሪ አቶ ሙሉቀን ቀሬ፤ እጅግ በጥንቃቄ በተለዩ መስፈርቶች አማካኝነትም በፍጥነት ወደስራ ሊገቡ የሚችሉት እና አዋጭነታቸው የተረጋገጡ 12 ፕሮጀክቶች መመረጣቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህ የፈጠራ ውድድር ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ያቀረቡ ባለሙያዎች እንደሃገር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ያስረዱት የUNDP ተወካይ አቶ ግዛቸው ሲሳይ መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማገዝም ተቋሙ የበኩሉን ድርሽ እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ስነስርዓት አዋጭነታቸው ተረጋግጦ የገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎች እንዲያገኙ ከተመረጡ 12 ፕሮጀክቶች ውስጥ አራት የሚሆኑት የቬንትሌተር መሳሪያዎች ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከእጅ ንክኪ የፀዱ የእጅ መታጠቢያዎች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የሶፍትዌር ስራዎች ናቸው፡፡
በዚህ ስነስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተጋበዙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ወረርሽኙን ለመከላከል የቀረቡት የፈጠራ ሃሳቦች በሃገርበቀል ደረጃ እምቅ የፈጠራ ሃብት እንዳለ የተረዳንበት ነው ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስቴሩ አክለውም የተመረጡትን እነዚህን ፕሮጀክቶች ወደመሬት በማውረድ ህበረተሰቡ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ የተሟላ ድጋፍ እንደሚደረግ እና ሌሎች በግሉ ዘርፍ ያሉ ተቋማትም ፈጠራዎቹ ወደ ኮመርሺያላዜሽን እንዲያመሩ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ታይበር ዦው ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኃላፊዎች ጋራ መከሩ
=========================
የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታይበር ዦው እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ቻርለስ ዲንግ ትናንት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በመገኘት ውይይት አድርገዋል፡፡ አቶ ታይበር በውይይታቸው ከቀናት በፊት አቶ ቻርለስ ዲንግ በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው በተነጋገሩበት ወቅት የተደረሱ መግባባቶች ላይ በማፅናት ከኢንስቲትዩቱ ጋራ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አንፀባርቀዋል፡፡
ከውይይቱ በተጨማሪ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ያግዝ ዘንድ ድርጅቱ ቃል በገባው መሰረት 2000 የፊት መሸፈኛ ጭንብል፣ 100 ሳኒታይዘር እና 4 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ለኢንስቲትዩቱ አበርክቷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ስለ ስጦታው ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡

ቴክ- ሳይንስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ ነገ ቅዳሜ በ10 ይጠብቁን
==========================
እንደ ወትሮው ሁሉ በነገው ፕሮግራማችንም አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ዝግጅቶችን ይዘንልዎ እንቀርባለን
• ብልሀት ሊያቀብል የሚችል አጭር ቪዲዮ ይኖረናል
• በአብይ ፕሮግራም-ሸካ ባዮስፌር ክፍል 2 ይቀርባል
• በቴክኖሎጂ ታሪክ-የህትመት ቴክኖሎጂ ይዳሰሳል
• በተመራማሪ ህይወት ታሪክ-ጅማ የግብርና እና የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ተገኝተን ፕሮፌሰር ካሳሁን በንቴ ቢሰጠኝን እናስተዋውቆታለን
አይርሱ ከልጆችዎ ጋር ሆነው ነገ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይጠብቁን (Nilesat/12520/V/27500)፡፡
https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg/featured