ሰበር ዜና
ቻይና የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዎቹን ሁለት የህመም ደረጃዎች ለማከም የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ከቻይና የባህል ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ጋር ቫይረሱን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡
ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትም በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ እና በሙያም እደግፋለሁ ብላለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ ሀገር ከተጀመሩ ስራዎች ጎንለጎን የቻይና ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል
==================
ትናንት የተፈራረሙት ስምምነት ማስተር ካርድ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዙርያ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችላቸው ነው፡፡ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት በተካሄደው ስነ-ስርዓቱ ላይ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ እና በኢትዮጵያ የማስተር ካርድ ተወካይ አቶ አለማየው ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ረገድ ማስተር ካርድ ከፍተኛ የሰው ኃይልና ቴክኒክ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህ ስምምነት ድጋፉ በትግበራ ረገድም እንዲቀጥል የሚያደርገው ይሆናል፡፡
ዲጂታሊዜሽን ስራው የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥ በመቀየር ለዜጎች የሚሰጣቸውን አገልግሎች ለማሻሻል እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከሚኖረው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ባሻገር በሚፈለገው መልኩ ከለማም ከፍተኛ የሆነ ሐብትና የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ክቡር ሚንስትር ደኤታው ገልፀዋል፡፡
አቶ አለማየሁ በበኩላቸው ተቋማቸው በአፍሪካ ለቀረፀው ፕሮጀክት ኢትዮጵያም ቁልፍ ተካፋይ መሆኗን ጠቅሰው በናሽናል ዲጂታሊዜሽን ፕላኑ ላይ ከተቀመጡት የትኩረት መስኮች ውስጥ የትኛውን ወደ ስራ ዕድል ምንጭነት መቀየር በሚቻልበት ሁኔታና ሊሎችም ስራዎች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋራ የጋራ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂው በአሁኑ ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ የማፀደቅና በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ተግባር ላይ ሲውልም የስራ ዕድሎችን በመፍጠር ለሀራችን ምጣኔ ሐብት ጉልህ ድርሻን እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

የኢትየጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ(COVID-19 Test) ለማድረግ የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቀቀ፡፡
====================
ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና ፕሮፈሰር ጣሰው ወልደሀና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከሌሎች የተቋሙ ክፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የቤተሙከራውን ሂደት የጎበኙ ሲሆን በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በመላው ሀገሪቱ ደረጃ የምርመራ ስራውን በስፋት ለማካሄድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ያደራጀው የኮሮና ቫይረስ መመርመርያ (COVID-19 Test) ላቦራቶሪ ክፍተኛ ሚና ይኖረዋል ፡፡
ይህንኑ ከግብ ለማድረስ ተቋሙ 2 ሪል ታይም ፒሲአር (Real Time-PCR) ማሽኖች በመጠቀም ለጊዜው በቀን ውስጥ እስከ 100 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ በሚችል መልኩ ተደራጅቷል፡፡
ይህ ኢንስቲትዩቱ የጀመረው ተግባር ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የተጀመረው ኮሮናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዋነኛ መንገድ በምርመራ የሚገኝ ውጤት በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ በስፋት በመመርመር ሂደት ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክትና የሚደረገውን የምርመራ ሥራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠናክረው ይሆናል።
የኮሮና ቫይረስ ምርመራውን ለማድረግ ስራውን ለሚሰሩት ለኢንስቲትዩቱ የቤተሙከራ ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ስልጠናዎች በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም የኢትዮጵያ ባዮቴክሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ወደ ተቋሙ የሚገቡ ሰራተኞችም ሆነ ማንኛውም እንግዳ ወደ ተቋሙ ሲገቡ የሰውነት ሙቀታቸው እያረጋገጠ እንዲገቡ የማድረግ ስራም እያከናወነ መሆኑንም ታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተቋሙ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በWHO የጥራት ደረጃ አዘጋጅተው ለተቋሙ ሰራተኞች እያከፋፈለ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ለአነስተኛና መካከለኛ እንተርፕራይዞች ስልጠና እና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም እጃችንን በውሀና በሳሙና በመታጠብ፤ ሰዎች ከሚበዙበት ቦታ በመራቅ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንከላከላለን እያለ ኢንስቲትዩቱ መዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የኮሮናቫይረስ ህክምና መመሪያ ታትሞ ለንባብ ቀርቧል
==========================
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመቆጣጠር ሂደት ውስጥ ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች የህክምና አገልግሎቶች በሁሉም ደረጃ የሚያገለግል ስታንዳርዳይዝ የህክምና መመሪያ በትናትናው ዕለት ታትሞ ቀርቧል፡፡
ይህ ብሄራዊ መመሪያ ሃገሪቱ በዘርፉ ያላትን የተገደበ የቴክኖሎጂ አቅም እና የሰው ግብረሃይል ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀብቱን በውጤታማነት እና ብቃት ለመጠቀም እንዲያስችል በሁሉም መልኩ የሚረዳ ነው፡፡ በስራው ላይ ከመላው ሃገሪቱ የተወጣጡ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን በዋናነትም የጤና ሚኒስቴር ባደራጀው ብሄራዊ የኮቪድ 19 አማካሪ ኮሚቴ አማካኘንት ስራው ሲተገበር እንደነበር ተገልጿል፡፡
መመሪያው በወረርሽኙ ዙሪያ አሁን ያለውን እና በቀጣይ ወራት የሚኖረው አጠቃላይ መረጃ በመዳሰስ ለውሳኔ እነደሚረዳ የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ አጭር ጊዜ ውሰጥ ይህን ስራ ለማጠናቀቅ ጊዜያቸውን እና እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ባለሙያዎች አመስግኗል፡፡
መመሪያውን ከስር ባለው ሊንክ ማግኘት ይቻላል
http://www.moh.gov.et/ejcc/sites/default/files/2020-04/COVID%2019%20Handbook%20for%20health%20professionals%20FMOH%202020.pdf

ቻይና በኮሮናቫይረስ አነሳስ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ምርምሮችን እያገደች ነው
*******************************
የኮሮናቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባት ቻይና በቫይረሱ አነሳስ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የምርምር ውጤቶች እንዳይታተሙ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች ነው፡፡ እንደመረጃው ከሆነ ከማዕከላዊ መንግስት በተሰጠ ማሳሰቢያ መሰረት ሁለት ዩኒቨርስቲዎች ከዚህ በፊት በድረገፃቸው ለጥፈውት የነበረውን የምርምር ፅሁፍ ማንሳታቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡
በአዲሱ ፖሊሲ መሰረት በኮቪድ 19 ላይ የሚደረጉ ማንኛቸውም ምርምሮች ወደህትመት ከመሄዳቸው በፊት ሌላ ተጨማሪ ግምገማ እንዲደረግባቸው የሚያዝ ሲሆን፤ በቫይረሱ አነሳስ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የምርምር ውጤቶች ደግሞ በጥብቅ ምርመራ ወይም (scrutiny) እንዲያልፉና የማዕከላዊ መንግስት ባለስልጣናት እንዲያፀድቋቸው የሚያስገድድ ነው፡፡ ሃገሪቱ ለዚህ እርምጃ እንደምክንያት ያቀረበችው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አነሳስ ወይም አጀማመር ላይ እየበረከቱ የመጡትን ትርክቶችን ለመቆጣጠር እንደሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
በቻይና ከጥር ወር አንስቶ አያሌ የጥናት ውጤቶች እና የምርምር ፅሁፎች በታወቁ አለምአቀፍ ጆርናሎች ሲታተሙ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው በቫይረሱ አነሳስ ዙሪያ ያተኮሩ ምርምሮች ያለምንም የመንግስት ጣልቃገብነት ወደ ህዝብ ሲደርሱ እንደነበረና ምንም አይነት እገዳዎች ሲጣሉ እንዳልነበር አወስቷል፡፡
የቻይና ተመራማሪዎች የተወሰደው እርምጃ በቫይረሱ ዙሪያ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ምርምሮች በፍጠነት እንዳይደረጉና እድገታቸው እንዲቀንስ አስተዋፅ ያደርጋል ቢሉም፤ የሃገሪቱ መንግስት ግን በቫይረሱ አነሳስ ላይ የሚፈጠሩ አመለካከቶችን እና ትርክቶችን ለመቆጣጠር እርምጃው አስፈላጊ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡
CNN

ቢያንስ 70 የሚሆኑ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በመሰራት ላይ ናቸው፤ ሶስቱ ደግሞ በክሊኒካል የሙከራ ሂደት እያለፉ ይገኛል
======================
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው አሁን ላይ ቢያንስ ቁጥራቸው 70 የሚሆኑ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ወይም (vaccines) በመሰራት ላይ ሲሆኑ፤ ሶስቱ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ እጩ በመሆን የክሊኒካል ሙከራ በማለፍ ላይ እንደሚገኙ በዘገባው አመላክቷል፡፡ እነዚህ ከፍተኛ የምርምር ሂደት የሚያስፈልጋቸው ክትባቶች ውጤታማነታቸው እና ደህንነታቸው ተረጋግጦ ወደህዝቡ ለመድረስ ከሚወስዱት የረዥም ጊዜ የሙከራ ሂደት አንፃር እና ከሚጠይቁት ከፍተኛ በጀት አኳያ ብዙ ጊዜ ቢያስፈልጋቸውም ቫይረሱ በደቀነው ከፍተኛ አደጋ የተነሳ ብቻ ስራዎች በፍጥነት እንዲካሄዱ እኝሁ የጤና ባለስልጣናት ያሳስባሉ፡፡
የአለም ጤና ድርጀት በስሩ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን ከትልልቅ የፋርማሲ ኢንዱስትሪዎች እና ከተለያዩ የባዮቴክ ኩባንዎች ጋር የሚያከናውኗቸው እነዚህ የተናጥል እና የጋራ ፕሮጀክቶች በመደበኛው ሂደት በትንሹ ከአምስት እስከ አስር ዓመት የሚፈልጉ ቢሆንም እነዚህ የመድሃኒት አምራቾች ግን አንዳንድ ሂደቶችን በማለፍ በአንድ አመትና ከዛ በጣረ ጊዜያት ውስጥ ስራዎች እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በሪፖርቱ እንደሚያመለክተውም በዚህ ሁኔታ በማለፍ በክሊኒካል የሙከራ ሂደት እያለፉ የሚገኙ እና በመጀመሪያ እጩነት የተካተቱ ሶስት ክትባቶች ያሉ ሲሆኑ፤ አነሱም በቻይናው የባዮቴክ ኩባንያ CanSino እና በአሜሪካ መቀመጫቸውን ባደረጉት ሁለት የባዮቴክ ኩባንያ Inovio Pharmaceuticals እና Moderna የሚሰሩ ክትባቶች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ እነዚህ ኩባንዎች ባገኙት ፈቃድ መሰረት ሌሎች ሂደቶችን በማለፍ ሙከራዎቻቸውን በሰዎች ላይ ማድረግ የጀመሩ ሲሆን፤ ከቤጂንግ የባዮቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ጋር በትብብር የሚሰራው CanSino ደግሞ ከሁለቱ ኩባንያዎች በተሻለ ፌዝ ሁለት ወደሚባለው የክሊኒካል ሙከራ እንደተሻገረም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
እነዚህ እንቅስቃሴዎች በዚህ መልኩ ይደረጉ እንጂ ክትባቶቹን በዚህ ፍጥነት እንዲደርሱ ማድረጉ አደጋ ሊኖረው እንደሚችል የሚከራከሩም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ብሄራዊ የአልርጂና ተላላፊ በሽታዎች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፉቺ መስል ስራዎችን በብርቱ የሚቃወሙ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ሁለትና ከዛ በላይ አመት የሚስፈልጋቸውን መሰል ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመስራት መሞከር በመጨረሻው ውጤት ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን ይጋልፃሉ፡፡ ይሁንና ቫይረሱ ከደቀነው ሁለንተናዊ አደጋ አንፃር ክትባቶቹ በሚቻለው አቋረጭ መንገድ ወደምርት መግባታቸው እጅግ አስፈላጊ እንደሚሆን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው፡፡
ምንጭ፡ Bloomberg

የውድድር ጥሪ ለፈጠራ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በሙሉ
==============================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በCOVID-19 ቫይረስ መከላከል ላይ የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳብና ፈጠራ ያላቸውን ተመራማሪዎችን እንዲሁም የፈጠራ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በመደገፍ ሀገራችን ላይ የተጋረጠዉን ከፍተኛ አደጋ ለመዋጋት የፈጠራ ዉጤቶች በስፋትና በፍጥነት ተመርተው ጥቅም ላይ የሚዉሉበትን ሂደት ማመቻቸት ይፈልጋል።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በፍጥነት እየተንሰራፋ እና ከፍተኛ ስጋት የሆነ የመጣዉን የ COVID-19 ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ስርጭቱን ለመግታት ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን መፍትሄ ለማበጀት የሚያስችሉ ሃገር በቀል የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችን አወዳድሮ በቀጥታ ወደ ተግባር ለማስገባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ሃሳብና ፈጠራ ያላችሁ በተቋማችን ድህረ ገፅ www.techin.gov.et/announcement ላይ እስከ ሚያዚያ 16፣ 2012 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ይህ የዉድድር ፕሮግራም COVID-19 Solution Challenge የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ከUNITED NATIONS DEVELOPMENT PROGRAMME (UNDP) ጋር በመተባበር እየተኪያሄደ የሚገኝ ነው።
ለበለጠ መረጃ በ 0111265762 ይደውሉ
ማሳሰቢያ፡ -በአካል መገኘት አስፈላጊ አይደለም
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር