ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
===================
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዚህ ቀጥሎ ባሉት የስራ መደቦች በቋሚነት አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የተቋሙን ድህረ ገፅ በመጠቀም በ Online techin.gov.et/announcement/ ላይ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡

ሌላኛው ቀውስ
==========
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከመግታት ጋራ ተያይዞ ብዙ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ እየተገደዱ ይገኛሉ፡፡ ትምህርት እና ስራን ጨምሮ በብዙ ሀገራት የተለያዩ ተቋማት በጊዜያዊነት ስራቸውን አቁመው ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን ቤት የመቆየቱ ነገር እጅጉን የሚመከከር እና ቫይረሱንም ለመዋጋት ዋነኛው መፍትሄ ቢሆንም በተለያዩ ሰዎች ላይ የስነ-ልቦና ተፅዕንዖ ሊያሳድርም ይችላል፡፡ ለአንዳንድ ሰዎች ይህ ከሰዎች ጋራ መራራቅ ምግብ ካለመብላት እስከሚስተካከል ድረስ ተፅዕንዖው ጎልቶ ሊወጣ እንደሚችልም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ዓለማችን ከገባችበት የኮሮና ቀውስ ጋራ ተያይዞ በዚህ ወቅት ይህን ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥናቶችን መስራት አዳጋች ነው፡፡ ሆኖም በቅርብ የተሰራ አንድ ጥናት የአውሮፓውያኑ 2000 ከገባ በኋላ ተቀስቅሰው የነበሩትን የሳርስ፣ H1N1 ፍሉ፣ ኢቦላ እና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎችን ተከትለው በተደረጉ የለይቶ ማቆያ እርምጃዎች ወቅት የተሰሩ 24 ጥናቶችን አገላብጦ ማሳያውን ይዞ መጥቷል፡፡ በውጤቱም እራሳቸውን የለዩ አልያም ለይቶ ማቆያ ውስጥ የገቡ ብዙ ታማሚዎች የአጭር ጊዜም ሆነ ዘላቂ የአዕምሮ ጤና ጉዳት እንደገጠማቸው ሲረጋገጥ ጭንቀት፣ የስሜት መዳከም፣ የእንቅልፍ እጦት ከነዚህ የጤና ችግሮች መካከል ተገኝተውበታል፡፡ ለምሳሌ በኢንፍሉዌንዛ ወረርሺኝ ምክንያት ተለይተው እንዲቆዩ ተደርገው ከነበሩ 2760 ሰዎች መካከል 34 በመቶው ወይም 938ቱ ከፍተኛ የስነ-ልቦና መጨነቅ አጋጥሟቸዋል፡፡ ይህም በተለምዶ ከሚያጋጥመው የ12 በመቶ በአንፃራዊነት ከፍ ያለ ነው፡፡ ሌላው በአውሮፓውያኑ 2003 የሳርስ ወረርሺኝ በተከሰተበት ወቅት 549 የሆስፒታል ሰራተኞችን አካሎ የተጠና ጥናት ደግሞ፤ ተለይተው እንዲቆዩ የተደረጉ አልያም ከፍተኛ ሰጋት ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሲሰሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ከወረርሺኙ መከሰት ሶስት ዓመታት በኋላ ሲታይ ስጋት ባልነበረበት ሁኔታ ውስጥ ሲሰሩ ከቆዩት አንፃር የአልኮል ሱሰኝነታቸው ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በለይቶ ማቆያ ጊዜያት ውስጥ እንዳንድ ሁናቴዎች የሰዎችን በአዕምሮ ጤና መታወክ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ይገለፃል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የለይቶ ማቆያው ጊዜ ከ10 ቀናት ያለፈ ሲሆን፣ ስለ ለይቶ ማቆያው እፈላጊነት በቂ መረጃ ሳይሰጥ ሲቀር እንዲሁም የአስፈላጊ ቁሳቁሶች እና የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ተደራሽነት አናሳ መሆን ነው፡፡
ከለይቶ ማቆያም ባሻገር ከሰዎች ጋራ ያለው አካላዊ ርቀት እና በየጊዜው አለመገናኘትም የራሳቸው ተፅዕንዖ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በ2015 3.4 ሚሊዮን ተሳታፊዎችን አካቶ የተሰራ አንድ ጥናት ብቸኝነት የሚሰማቸው ሰዎች በ26 በመቶ ቀድሞ የመሞት ዕድል እንዳላቸው ሲያረጋግጥ ከማህበራዊ ግንኙነቶች የራቁት በ29 በመቶ በብቸኝነት የሚኖሩት ደግሞ 32 በመቶ ቀድሞ የመሞት ዕድል እንዳላቸው አሳይቷል፡፡ ታድያ በእንደዚህ አይነት የመራራቅ ወቅቶች ወትሮውንም ከዕድሜያቸው መግፋት ጋር ተያይዞ የማህበራዊ ግንኙነታቸው የቀነሱ ሰዎች እና በህክምና ሳብያ በየሆስፒታሉ አልጋ የያዙ ታማሚዎች ይበልጥ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡
ሆኖም ከላይ የተቀመጡ የጥናት ውጤቶች እንዳሉ ሆነው በነዚህ ወቅቶች የሚደረጉ ግንኙነቶች መቀነስ ሁሉንም በእኩል ይጎዳል ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዶች ከቤት ላለመውጣታቸው ምስጋና ይግባና ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ያላቸው ትስስር እንዲጠብቅና የማህበራዊ ትስስር ደረጃቸውም እንዲያድግ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በስልክና በበይነ-መረብ የሚፈጥሯቸው ትስስሮች ተጎጂነታቸውን በእጅጉ ሲቀነሰው ይታያል፡፡ መሰል ቴክኖሎጂ አመጣሽ ግንኙነት ከፍ ሲልም በርቀት የአዕምሮ ጤና ህክምናዎችን እንዲከወኑ ሊያደርጉም ይችላሉ፤ የማታ ማታ የግንባር ህክምና እንደሚያስፈልግ ቢቀመጥም፡፡
ምንጭ፡- Science News

ጨረቃ በውበቷ የምትሞሸርባቸው ዕለታት
=======================
ፈረንጆቹ ግዙፍ ጨረቃ ወይም Supermoon ይሉታል፤ ጨረቃ ሙሉ ሆና የምትታይበት ጊዜ ወደ ምድር ከምትቀርበበት ጋራ ሲገጥም የሚከሰት ውብ ክስተት ነው፡፡ ይህም ጨረቃን ከተለምዶው ጊዜ በተለየ ደደምቃና ወደኛም ቀርባ አንድትታየን ያደርጋል፤ ምንም እንኳን ልዩነቱን በባዶ አይን ለመመልከት አስቸጋሪ ቢሆንም፡፡ የዚህ ወር ሱፐርሙን ዛሬ ወይም ነገ መጋቢት 30 እንደሚከሰት ይጠበቃል፤ ይህችም በምዕራቡ ዓለም ሮዝ ጨረቃ ተበላ ስትጠራ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሌላ ስያሜ ትጠራለች፡፡
ይህ እንዴት ይፈጠራል?
ጨረቃ ምድርን የምትዞረው ፍፁም በተስተካከለ ክብ ምህዋር ላይ ሆና አይደለም (ሁለተኛውን ምስል ይመልከቱ)፡፡ ይልቁንም ከምድር የሚኖራት የ382,900 ኪ.ሜ አማካኝ ርቀት የጨረቃ ወራት (Lunar Month) መለዋወጥን ተከትሎ ሊያንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡ ለዚህ በዋነኝነት የሚቀመጠው ምክንያት ጨረቃን የሚስቡ እና ማዕበለኛ የሆኑ ብዙ ኃይሎች መኖር ነው፡፡ የፀሐይ፣ መሬት እና ሌሎች ፕላኔቶች የስበት ኃይል በጨረቃችን ምህዋር ላይ የራሳቸውን ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ እነዚህ የስበት ኃይሎች ጨረቃን በሚስቡበት እና በሚገፉበት ሰዓት ለእኛም ቀርባ አልያም ርቃ የምትታየን ይሆናል፡፡
ሱፐርሙን እንዲከሰት ታድያ ሁለት አባይት ነገሮች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ ዕለቱ ጨረቃ ምድርን በምትዞርባቸው 27 ቀናት ውስጥ በጣም የምትቀርብበት መሆን አለበት፡፡ በመቀጠልም ጨረቃ ሙሉ ገጿ መታየት መቻል አለባት፤ ይህም በየ 29.5 ቀናት ልዩነት የሚከሰት ነው፡፡ ምድር ፀሐይን በምትዞርበት ወቅት ጨረቃም ምድርን የምትዞርበት ምህዋር እየተቀያየረ በመምጣቱ ሳብያ ይህን ክስተት ሁሌ ማግኘት ያስቸግራል፤ በዓመት ለተወሰኑ ቀናት ብቻ እናየዋለን፡፡
በሱፐርሙን ወቅት ጨረቃ ብርሃኗ ከቀድሞው በ30 በመቶ ግዝፈቷ ደግሞ በ14 በመቶ ጨምራ ትታየናለች፡፡ ሁሌም ጨረቃን በአስተውሎት የማንመለከት ከሆነ ይህን ልዩነት በባዶ አይናችን ማስተዋል ይከብደናል፡፡ አንዳንዴ ግን ለአድማስ በጣም ከቀረበች ጨረቃዋ በተለየ ገዝፋ ልትታየን ትችላለች፡፡ አዕምሮአችንን ይህን ሁነት የሚገነዘብበት አኳሀን ግን የተለየ መልክ አለው፡፡ ጨረቃዋ ወደ አድማስ ስትጠጋ ለአይናችን ገዝፋ ትታያለች፤ ሁናቴው ጨረቃዊ ማስመሰል ወይም Moon Illusion ተብሎ ይጠራል፡፡ የሳይንሱ ዓለም ጠበብቶች ይህ የሚሆነው አዕምሮአችን ጨረቃን ከሚያያቸው ህንፃና ሌሎች ነገሮቸ ጋራ ለማነፃፀር ዕድል ስለሚያገኝ አልያም አዕምሮአችን በጎን በአድማስ በኩል ያሉ ነገሮችን በላይ በሰማይ ላይ ከሚታዩት በላቀ አግዝፎ እንዲያይ የሚያደርገው ትሰስርን ፈጥሮ ሊሆን በመቻሉ ነው ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሁነቱ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው ለብዙ አመታት ቆይቷል፤ በፅንሰ ሐሳባዊ መነሻውም ከህዋ ምርምር (Astronomy) ሳይሆን በህዋ ላይ ያሉ ነገሮችን እንቅስቃሴ በመመልከት ነገሮች ከሚተነበዩበት የከኮኮብ ቆጠራ (Astrology) ዘርፍ ነው፡፡ ከአውሮፓውያኑ 2004 ጀምሮ በተደረገ ምልከታ መሰረት እስከ 2011 ድረስ Supermoon ብለው ጎግል የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር እንብዛም ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር ሁነቱ በሁሉም ስፍራዎች እኩል ትኩረት አይሰጠውም፤ በአንዳንድ የዓለማችን ሀገራት በተለይም በሰሜን አሜሪካን እና ደደቡብ ምስራቅ እሲያ ይበልጥ ታዋቂ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ በ2016 ግን በከፍተኛ ሁኔታ ጉግል ይደረግ ጀመር፡፡ ለዚህ ዋነኛው ምክንያት የነበረው በዚያ ዓመት ከ69 ዓመታት በኋላ በመጠኑ የላቀ ሱፐርሙን በመታየቱ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጨረቃ ከምድር ያላትን ርቀት ወደ 356,508 ኪ.ሜ አጥብባ ነበር፡፡
ከዚህኛው ሱፐርሙን በተጨማሪ ሌሎች አስደናቂ ሱፐርሙኖችን ታዝበናል፡፡ ባለፈው ዓመት ወርሀ ጥር የፀሐይ ግርዶሽ እና ሱፐርሙን በአንድ ላይ ታይተው አልፈዋል፡፡ በዚህ ክስተት ወቅት ጨረቃ ቀይ ቡናማ ቀለምን ተላብሳ ነበር፡፡ ሌሎችም ከ2016ቱ ሱፐርሙን ከ100 ኪ.ሜ በላይ ጨረቃ ለመሬት የቀረበችበት የ1912ቱ ሱፐርሙን ሲጠቀስ ከ14 ዓመታተ በኋላ በ2034 የሚታየው ደግሞ ከሁለቱም የላቀ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ space.com

ሰበር ዜና
ቻይና የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዎቹን ሁለት የህመም ደረጃዎች ለማከም የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ከቻይና የባህል ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ጋር ቫይረሱን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡
ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትም በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ እና በሙያም እደግፋለሁ ብላለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ ሀገር ከተጀመሩ ስራዎች ጎንለጎን የቻይና ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል
==================
ትናንት የተፈራረሙት ስምምነት ማስተር ካርድ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዙርያ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችላቸው ነው፡፡ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት በተካሄደው ስነ-ስርዓቱ ላይ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ እና በኢትዮጵያ የማስተር ካርድ ተወካይ አቶ አለማየው ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ረገድ ማስተር ካርድ ከፍተኛ የሰው ኃይልና ቴክኒክ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህ ስምምነት ድጋፉ በትግበራ ረገድም እንዲቀጥል የሚያደርገው ይሆናል፡፡
ዲጂታሊዜሽን ስራው የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥ በመቀየር ለዜጎች የሚሰጣቸውን አገልግሎች ለማሻሻል እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከሚኖረው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ባሻገር በሚፈለገው መልኩ ከለማም ከፍተኛ የሆነ ሐብትና የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ክቡር ሚንስትር ደኤታው ገልፀዋል፡፡
አቶ አለማየሁ በበኩላቸው ተቋማቸው በአፍሪካ ለቀረፀው ፕሮጀክት ኢትዮጵያም ቁልፍ ተካፋይ መሆኗን ጠቅሰው በናሽናል ዲጂታሊዜሽን ፕላኑ ላይ ከተቀመጡት የትኩረት መስኮች ውስጥ የትኛውን ወደ ስራ ዕድል ምንጭነት መቀየር በሚቻልበት ሁኔታና ሊሎችም ስራዎች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋራ የጋራ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂው በአሁኑ ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ የማፀደቅና በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ተግባር ላይ ሲውልም የስራ ዕድሎችን በመፍጠር ለሀራችን ምጣኔ ሐብት ጉልህ ድርሻን እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

የኢትየጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ(COVID-19 Test) ለማድረግ የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቀቀ፡፡
====================
ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና ፕሮፈሰር ጣሰው ወልደሀና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከሌሎች የተቋሙ ክፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የቤተሙከራውን ሂደት የጎበኙ ሲሆን በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በመላው ሀገሪቱ ደረጃ የምርመራ ስራውን በስፋት ለማካሄድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ያደራጀው የኮሮና ቫይረስ መመርመርያ (COVID-19 Test) ላቦራቶሪ ክፍተኛ ሚና ይኖረዋል ፡፡
ይህንኑ ከግብ ለማድረስ ተቋሙ 2 ሪል ታይም ፒሲአር (Real Time-PCR) ማሽኖች በመጠቀም ለጊዜው በቀን ውስጥ እስከ 100 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ በሚችል መልኩ ተደራጅቷል፡፡
ይህ ኢንስቲትዩቱ የጀመረው ተግባር ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የተጀመረው ኮሮናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዋነኛ መንገድ በምርመራ የሚገኝ ውጤት በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ በስፋት በመመርመር ሂደት ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክትና የሚደረገውን የምርመራ ሥራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠናክረው ይሆናል።
የኮሮና ቫይረስ ምርመራውን ለማድረግ ስራውን ለሚሰሩት ለኢንስቲትዩቱ የቤተሙከራ ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ስልጠናዎች በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም የኢትዮጵያ ባዮቴክሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ወደ ተቋሙ የሚገቡ ሰራተኞችም ሆነ ማንኛውም እንግዳ ወደ ተቋሙ ሲገቡ የሰውነት ሙቀታቸው እያረጋገጠ እንዲገቡ የማድረግ ስራም እያከናወነ መሆኑንም ታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተቋሙ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በWHO የጥራት ደረጃ አዘጋጅተው ለተቋሙ ሰራተኞች እያከፋፈለ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ለአነስተኛና መካከለኛ እንተርፕራይዞች ስልጠና እና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም እጃችንን በውሀና በሳሙና በመታጠብ፤ ሰዎች ከሚበዙበት ቦታ በመራቅ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንከላከላለን እያለ ኢንስቲትዩቱ መዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት