TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሁዋዌ እና ኢትዮጵያ
=============
ግዙፉ የቻይና ቴክኖሎጂ ተቋም ሁዋዌ የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ድጋፍ እና የጋራ ስራዎችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ለአፍሪካ ሀገራት ከሚያደርጋቸው ድጋፎች መካከል የሆነው ይህ ትብብር በተለይም በትምህርት ዘርፉ የሚታይ አስተዋፅዖን እያደረገ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ከአውሮፓውያኑ 2018 አንስቶ የICT ውድድር በማዘጋጀት ከተለያዩ የኢትዮጵያ የኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ አንዱ የዚህ ትብብር ትሩፋት ነው፡፡ በዚህ ውድድር በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ዩነቨርሲቲዎች የተውጣጡ 2357 ተሳታፊዎችን ሲያወዳድር በቻይና ለሚደረገው የመቋጫ ውድድር ሁለት ተማሪዎች እና አንድ አስተማሪ ተመርጠው ይገኛሉ፡፡
በትምህርት ላይ ባተኮረው የክላውድ ስርዓት ዝርጋታው ከሁለት ዓመታት በፊት 25 ሺ የከላው ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን መገኛቸው በዘጠኑ የክልል እና ሁለት ከተማ አስተዳደር በሆኑ 310 ትምህርት ቤቶች ላይ ገጥሞ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ ቀድሞ የተዘረጉትን ስንጨምርበት በአጠቃላይ በዚህ ፕሮግራም 365 ትምህርት ቤቶች እና 10 ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራጩት 30000 ሺህ ኮምፒውተሮች ከ27 ሺህ በላይ ተማሪና መምህራንን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም በአስሩ ዩኒቨርሲቲዎች ዘመናዊ የዳታ ሴንተሮችን ብሎም የትስስር እና የክላውድ መሰረተ ልማቶችን ዘርግቷል፤ በ20 ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማትም ኮርሶችን በመስጠት ላይ ነው፡፡ በጠቅላላውም 300 ሺህ የኮሌጅ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ይናገራል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሁዋዌ ትብብርቸውን የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ ሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተለያ ወቅቶች ሲፈራረሙ ቆይተዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በ37 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን ለመገንባት በ2017 ስምምነት ላይ መደረሱ ነው፡፡ ባለፈው ዓመትም በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን በጋራ ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ ታድያ በቅርቡ የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ሀላፊው ዦው ቲያንቢንግ ከቻይናው የሚዲያ ተቋም ሺንዋ ጋር ባደረጉት ቆይታ በቀጣይም የኢትዮጵያን የአይ.ሲ.ቲ አቅም ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ድጋፎቹ በሶስት ማዕቀፎች ወደ መሬት ሲወርዱ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ የአይ.ሲ.ቲ ስነ-ምህዳር እርሾ እንደሚሆኑ እና ከታችኛው የትምህርት ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ በአስርት ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ዋና ሀላፊው ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ Xinhu
የአንድ ዓመት ጉዞ ማብሰሪያ
===================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባሳለፍነው ቅዳሜ በያያ ቪሌጅ በመገኘት ተከብሯል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች ሶሻል ኮሚቴ በሆነው “ላምባዲና” አማካኝነት የተሰናዳው ዝግጅቱ ልዩ ልዩ የመዝናኛና ሌሎች ክንውኖችን አቅፎ የያዘ ነበር፡፡ ሙሉ ሰራተኛውን አሳታፊ ባደረገ ስፖርታዊ ጨዋታ ጅማሬውን ያደረገው ክብረ በዓሉ ሁለት በሰራተኞች መካከል በተደጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች አስተናግዷል፡፡ ተቋሙን ለሚለቁ እንዲሁም የኃላፊነት ለውጥ ላደረጉ የተቋማችን ሰራተኞች የተደረጉ ስጦታና የምስክር ወረቀት አሰጣጥም የዝግጅቱ አንድ አካል ነበረ፡፡
ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ታስቦ ብዙ ስኬቶች መኖራቸውንና በራስም ሆነ ከአቅም በላይ በላይ በሆኑ ችግሮች ምክንያት ሳይሳኩ የቀሩ ስራዎች ቢኖሩም በአንጻራዊነት እንደ አዲስ ተቋም የተሸሉ ስራዎች መሰራታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ስኬቶቹ በተለይም እንደ አዲስ ተቋምነቱ መሰረት በመጣል እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት ረገድ መሆናቸውን በመናገር ለሚቀጥለው የተቋሙ ጉዞ ካለፈው መልካሙን በመውሰድ በአዲስ መንፈስ መስራት እንደሚገባ አሳስበው አልፈዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ወደ ኢንስቲትትነት ከመቀየሩ በፊት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል በነበረበት ወቅት ጭምር ይካሄዱ የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ አማካኝነት የተሰሩ ስራዎችን በአጭሩ የሚያስቃኝ አጭር ቪዲዩ የቀረበ ሲሆን በመድረኩም በባለ ተሰጥዖ የተቋመችን ቤተሰቦች አማካኝነት ግጥም እንዲሁም ዜማ ከታዳሚው ዘንድ ቀርበው አዝናንተው ነበር፡፡
TECHIN weekly seminar
===================
TECHIN weekly seminar will be held today in TECHIN hall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School).
Yodit molla and zebib getachew will lead today’s session
Issues for this week;
• Psychologists personal qualities as co-relates of their counseling effectiveness
•fligile based flight reservation system with service based approach
Don’t forget to join us
የስነ ልቦና ምክር በህይወታችን ላይ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም
==============================
በየሳምንቱ ሃሙስ የሚዘጋጀው የቴክኢን ሴሚናር በትላንትናው ዕለትም በስነ ልቦና ጉዳይ እና የአይቲ ዘርፍ ላይ ዋና ትኩረቱን አድርጎ ለታዳሚያን ቀርቧል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው የሴሚናር መርሃ ግብር በቅድሚያ በወይዘሪት ዮዲት ሞላ የቀረበው የስነ ልቦና ባለሙያዎች ግላዊ አቅም እና በማማከር ሂደት ውስጥ ያለው አወንታዊ ተፅዕኖ በሰፊው የተብራራ ሲሆን፤ ከሃገራችን የስነ ልቦና አረዳድ ጋር በማስተሳሰርም እጅግ ጠቃሚ ነጥቦች ለማንሳት የተሞከረበት ነው፡፡
ተመራማሪ ዮዲት በዚህ ጥናቷ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ከተለያዩ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ባገኘችው መረጃዎች እና እንደ ሞዴል በወሰደቻቸው መመዘኛዎች በመመርኮዝ ባደረገቸው ሰፊ ጥናት እንደ ቅንጦት የምናየው የስነ ልቦና ምክር በተሻለ ሁኔታ እንዲሰጥ ምን መደረግ አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳብ አቅርባለች፡፡ በዚህም በስነ ልቦና የትምህርት አሰጣጣችን ላይ ከሃልዮት ባለፈ በግለሰቦች ግላዊ እድገት ላይ በማተኮር የስነ ልቦና አማካሪዎችን ውጤታማነት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚቻል አንስታለች፡፡
በዕለቱ የሴሚናር መርሃ ግብር በተከታይነት ለታዳሚዎች የቀረበው ርዕሰ ጉዳይ በተመራማሪ ዘቢብ ጌታቸው የተከናወነው ከአይቲ ጋር የተያያዘው የፕሮጀክት ሃሳብ አንዱ ሲሆን፤ ይኸውም ሞባይልን መሰረት አድርጎ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች የተሰራው የበረራ ማስያዣ ስርዓት (flight reservation system) አንዱ ነበር፡፡ ተመራማሪ ዘቢብ በዚህ ፕሮጀክቷ ላይ አንደገለፀችው ዌብ ቤዝድ የሆነው ይህ ስርዓት ዲዛይን በሚደረገበት ጊዜ የአየር መንገዱ ሁኔታ ለሲስቱሙ ዝግጁ ባለመሆኑ ቀጥታ ወደ ስራ መግባት ባይቻልም ቀጥለው ለለተሰሩት የተለያዩ የበረራ ማስያዣ ስርዓቶች ጥሩ መነሻ እንደነበር ገልጻለች፡፡
በዕለቱ በነበረው ሴሚናር እንደሁልጊዜውም ሁሉ ከታዳሚያን የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፤ በአቅራቢዎች በኩልም መልስ ተሰጥቶባቸው አልፏል፡፡
ብሄራዊ የቢዝነስ ፖርታል ትናንት ይፋ ሆነ
=======================
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋራ በመሆን ያሰራውን ዘርፈ ብዙ የቢዝነስ ገፅ ወይም ፖርታል ይፋ አድርጓል፡፡ ትናንት ይፋ የተደረገው ገፁ ተለምዶአዊውን መንግስታዊ ተግባራትን በዲጂታል ስርዓት አማካኝነት በፍጥነት፣ ወጪ ቆጣቢና ጥራት ባለው መልኩ እንዲተገበር የሚያደርግ ነው፡፡ በተጨማሪም ተገልጋዮች አንዴ ያስገቡት መረጃ ለሁሉም የመንግስት ተቋማት እንዲያገለግላቸው እና ጉዳያቸው ምን ላይ እንደደረሰ ካሉበት ሆነው ለማወቅ ያስችላቸዋል፡፡ ይህም በተለይ ኢትዮጵያ ያላትን የስራ ምቹነት (ease of doing business) በእጅጉ ሲያሳድግ ዜጎችንም ከተንዛዛ አሰራር ይታደጋል፡፡
ሀገራችን ወደ ብልፅግና በምታደርገው ጉዞ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ተግባራት ውስጥ ለስራ ያላትን ምቹነት ማሳደግ አንዱ መሆኑን የገለፁት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ ገፁ በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጎ ሚናን እንደሚጫወት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡ አገልግሎቶችን ሁሉ በአንድ መስኮት እንዲሆኑ እንደሚያስችል እና ቀድሞ መረጃን ለማግኘት ይኬድበት የነበረውን ውጣ ውረድ እንደሚቀርፍ ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት 15 ሺህ ያህል ሰዎች ተመዝግበው እየተገለገሉበት የሚገኘው ይህ ፖርታል የክፍያ አገልግሎቶችን በቀለለ መልኩ እንዲያከናውን የሚያስችሉት ስራዎች እየተሰሩለት እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ እርስዎም ይህን ሊንክ ( www.business.gov.et ) በመጠቀም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
ቴክ ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዛሬ ይጀመራል
እነሆ ቀን ቆጥሮ ዝግጅቱንም አጠናቆ ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን ዛሬ ቅዳሜ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አንስቶ ወደ እርስዎ መድረሱን ይጀምራል፡፡ ከልዩ ልዩ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢኖቬሽንን የተመለከቱ ዜናዎች፣ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ትንታኔዎችቻችን ጋራ MOE TV ይጠብቁን፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=DoLHYKUYXCw
የሎጅስቲክስ ዘርፉን የሚያዘምን የኮምፒውተር ስርዓት ሊተገበር ነው
===============================
የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስ ዘርፍ የሚያዘምን የተቀናጀ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መካከል ተደረሰ፡፡ የኮምፒውተር ስርዓቱ ሐብት የት እንዳለ በአግባቡ ተረድቶ ለመጠቀም እና የክትትል ስራዎችን ለመስራት ጠቃሚ አንደሆነ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ያስረዱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ ዘርፉን በICT በማገዝ የትራንስፖርት ስራዎችን እንደሚያስተሳስር እና የሀገራችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እንደሚጠቅም ጠቁመው አልፈዋል፡፡
አዲሱ ስርዓት የሎጅስቲክስ ዘርፉን ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ ከማድረጉም በተጨማማሪ በተለይ ወደ ወደብ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚያሻሽል ይሆናል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ መረጃ አስተዳደር፣ የስራ ቅንጅት እና የጉዞ አስተዳደር ረገድ ማሻሻያዎችን እንደሚያመጣ ሲታመንበት ከዚህ በፊት በተተገበሩ ስርዓቶች ላይ ይስተዋል የነበረውን የቅንጅት ጉድለት እንደሚቀርፍ ስርዓቱን አስመልክቶ በቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህም ባለፈ ግን ይህ ብዙ ክፍተቶችን የሚሸፍን ስርዓት ባክኖ እንዳይቀር ዘላቂ ድጋፎች እንደሚያደረጉና ተቋማቸውም በከፍተኛ ኃላፊነት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል መሆኑን የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩትን ወክለው የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሳንዶካን ደበበ ተናግረዋል፡፡
በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ላይ የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር አብረሀም በላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የለውጥ አመራሩ የለያቸው የህብረተሰብ ጥያቄዎችን ከመመለስም ባሻገር የሎጅስቲክ ስርቱን እንደሚያዘምን ወሮ ዳግማዊት የገለጹ ሲሆን ዶ/ር አብረሀም በበኩላቸው ብዙ ባለድርሻዎች እንደሚሳተፉበት በማወቅ ስራዎች በጥራት እና ደህንነታቸው ተጠብቆ ይከናወኑ ዘንድ አሳስበዋል፡፡
እጅን መታጠብ ያድናል !!!

ተመራማሪዎች አሁንም ቢሆን የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገድን ለመረዳት በጥረት ላይ ናቸው፡፡ ቢሆንም ሁሉንም የሚያስማማ አንድ እውነታ አለ፤ እጅን መታጠብ እና ፊትን አለመነካካት በእጅጉ እንደሚጠቅመን፡፡ እጅን መታጠብ ለኮሮና ብቻም ሳይሆን አይነታቸው ለበዛ ሌሎች ቫይረሶችም ሁነኛ መከላከያ መፍትሄ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ታድያ አለኝታነቱ በበሽታው ላለመያዝ ለሚታትሩት ብቻ አይደለም፤ ተይዘው ከአልጋ ለዋሉትም እንጂ፡፡ በበሽታው የተጠቃን እንደሆነ እጃችንን በመታጠባችን ብቻ ከእኛ ወደ ሰዎች እንዲሁም ሰዎች ሊነኳቸው ወደሚችሏቸው ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ ማድረግ እንችላለን፡፡ ለ “20 ሴኮንድ” በሳሙና መታጠብ እራስን፣ ቤተሰብን እና ማህበረሰብነ ለመጠበቅ ቀዳሚው አማራጭ ነው፡፡
ኮሮናንም ሆነ ሌሎች በሽታዎችን የሚያመጡ ተህዋሲያን በዙርያችን እና አዘውትረን በምንነካቸው ቁሶች ላይ ሰፍረው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ የእጅ መታጠብ እነርሱን የመከላከል ኃይሉን እንዲያገኝ ያደረገው ተህዋሲያኑን ከእጃችን ማስለቀቅ በመቻሉ ነው፡፡ ይህም በምንታጠብበት ሰዓት ሳሙናው በእጃችን ላይ የተከማውን ዘይት እና ቆሻሻ አጥቦ ስለሚያወርዳቸውና ተህዋሲያኑም በዚህ እንቅስቃሴ ታጥበው ስለሚርዱ ነው፡፡ ስንታጠብ እጃችንን በምናሽበት ሰዓትም ዘይቱን ለማስለቀቅ የሚያበቃ ፍትጊያ እንፈጥራለን፡፡ በባዶ ውሃ መታጠብ በትንሹ ሊረዳን ይችላል፤ ካለመታጠብም የተሸለ ነው፡፡ ሆኖም ውጤታማነቱ በእጅጉ የወረደ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
እዚህ ላይ ግን ዋናው ችግር ከእኛ ዘንድ ያለው ግድ የለሽነት ነው፡፡ እጅን መታጠብ ያለው ኃይል ለመቶዎች አመታት ሲነገር ነበር፡፡ ብዙ ሃይማኖቶችም እጅ መታጠብን ሲያበረታቱ ቆይተዋል፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብቅ ያለው በጀርም ላይ የሚያውጠነጥን የበሽታ ትንተናን ተከትሎ በህክምናው ዓለምም ያለው ስፍራ ሊጨምር ችሏል፡፡ ሆኖም በጉዳዩ ዙርያ ዕውቀት መኖሩ እና የማንቂያ ስራዎች ለዓመታት መሰራታቸው ከመፀዳጃ ቤት መልስ እንኳን እጃችንን የምንታጠብ ሰዎች የዓለማችን ህዝብ ብዛት አንድ አምስተኛው እንኳን ሊያልፍ አልቻለም፡፡ ይታጠባሉ የሚባሉትም ቢሆን እንደነገሩ ከመታጠብ ባሻገር ሁሌም በስነ ስርዓት ለ20 እና 30 ሴኮንድ ሲታጠቡ አይስተዋልም፡፡
“እጃችንን በአግባቡ እንታጠብ” !!!
“ፊታችን ከመንካት እንቆጠብ” !!!
ምንጭ፡ Popular Science
TECHIN weekly seminar
For this week Wubishet Begashaw will discuss “design and develop digital traffic light system based on PICMICRO CONTROLLER” and “inventing user-centered technology: the case of BIRR ETHIOPIC” will be presented by Samuel Zeber.
As always we are delighted to have you here tomorrow.