TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሃር እና ኢትዮጵያ
============
ከሀር እርሻ የሚገኘው ሃር ለሺዎች ዓመታት ያህል እንደ ቅንጦት እቃ ተቆጥሮ ኪስን ቆንጠጥ ከሚያደርግ ዋጋ ጋራ ለገበያ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ የቻይና ትርክቶች እንደሚያመላክቱን የሀር ምርት ግንዛቤ ከአራት ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት በፊት እንደሆነ ነው፡፡ በታሪኩም ሲ ሊንግ ሺ የተባለችው የቻይና ልዕልት (ንግስት) የሃር ትሎችን የየጊዜ እንቅስቃሴ እና እድገት ትከታተል ነበርና ቅርፊት ወይም ኮኮኖች በሚፈጠሩበት ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ታስቀምጣቸዋለች፡፡ በአንድ እለት ይህ ቅርፊት በምትጠጣው ሻይ ውስጥ ይወድቅና ቅርፊቱን የሞላው ቀጭን ገመድ ሲበታተን ታስተውላለች፡፡ በዚህም ሳቢያ ሃርን እንዴት ማውጣት እንደሚቻል መረዳት ቻለች፡፡
ምንም እንኳን የዚህን ትርክት እውነትነት ማረጋገጥ ባይችሉም ታሪክ ተፈፀመበት ከሚባልበት ወቅት አንስቶ ወይም ቀደም ብሎ የሃር ምርት በቻይና ይተገበር እንደነበረ የሚጠቁሙ ታሪካዊ ማረጋገጫዎች በተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ ታሪክ ባሻገር ግን ቻይናዊያን ይህን ምርት በመፍጠርም ሆነ ለሺዎች አመታት ያለተቀናቃኝ በማምረት ብቸኛዎቹ ነበሩ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ቻይናዊያኑ ለሺዎች አመታት የሃር እርሻን በሚስጥርነት በማቆየታቸው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን በዙሪያቸው ወደነበሩት ማህበረሰቦች በዋነኝነት ኮሪያ፣ ህንድና ጃፓን በመቀጠልም ወደ ምዕራቡ ዓለም በተለያዩ መንገዶች ሊተላለፍ ችሏል፡፡ ባለንበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ሐገራት ሃርን የሚያመርቱ ሲሆን ቻይናና ህንድ የዓለምን የሃር ምርት እንደተቆጣጠሩት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሃር እርሻ በዘመናዊ መልኩ ለኢትዮጵያ ከተዋወቀ ሁለት አስርት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ በቅድሚያ መልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል ስራው የተጀመረ ሲሆን ከአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም አንስቶ ግን ወደተለያዩ የሃገሪቱ ቦታዎች ስርጭቱን አድርጓል፡፡ በዚህም የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ምርቱን ወስዶ ወደ ክልሉ ገበሬዎች በማስፋፋት ቀዳሚ ነበር፡፡ ኋላ ላይ በሌሎች ባለ ድርሻ አካላት እና ግለሰቦች አማካኝነት ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር እና አዳማን ጨምሮ ወደ ሌሎች የሃገራችን ክፍሎች ሊስፋፋ ችሏል፡፡ በአንድ ሪፖርት ላይ እንደተቀመጠው በ2005 እንኳን የደረቁ ቅርፊቶች ምርት 3000 ኪ.ግ ደርሶ እንደነበረ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ 95 በመቶው ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ ተልከው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡
ይህ ሲባል ግን የሃር ምርት ሊኢትዮጵያ አዲስ ሁነት ነው ማለት አይደለም፡፡ ሃር በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ እና ሐይማኖታዊ የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ከዘመነ አክሱም አንስቶ ታሪካዊ ዳራውን አኑሯል፡፡ በጥንት ጊዜያት ከፍተኛ መጠን ያላቸው የሃር ምርቶች ከህንድ፣ አረቦች እና ችይና ጭምር ይገዛና በማዕከላዊው የሃገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዋሻዎች ይከማቹ እንደነበር ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ሀገራችን የተለያየ የአየር ንብረት፣ ዕፅዋት እና መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን በተላበሱ ስፍራዎች የተሞላች መሆኗ የተለያዩ አይነት የሃር ትሎችን በማራባት ልዩ ልዩ የምርት ዓይነቶችን እንድታመርት ዕድል ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ከዚህ የተፈጥሮ ፀጋ በሃር ምርት ረገድ ተጠቃሚ መሆን ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ኋላ ላይ በ1930ዎቹ ኢትዮጵያ ለሃር ምርት ያላትን ምቹነት ጣሊያኖች ሊገነዘቡ ችለው ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ግንዛቤ ወደ ተግባር ይለወጥ ዘንድ አስርት ዓመታት አስፈልገውታል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆነው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሃር ምርት በፍጥነት እያደገ ይገኛል፡፡ መረጃዎች እንደሚነግሩን የምርት መጠኑ ከ2014 በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት እንኳን በ200 በመቶ ጨምሯል፡፡ ሐገሪቱም የሃር ምርትን አምርተው ወደ ባህር ማዶ ከሚሸጡ ሐገራት ተርታ ለመሰለፍ በቅታለች፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ ሳባሃር የተሰኘው አነስተኛ የጨርቃጨርቅ አምራች የኢትዮጵያ ሃርን ተጠቅሞ ምርት በማምረት ወደ ውጭ የሚልክ ብቸኛው ኩባንያ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ ቁ.፲፮
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ሁዋዌ እና ኢትዮጵያ
=============
ግዙፉ የቻይና ቴክኖሎጂ ተቋም ሁዋዌ የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ድጋፍ እና የጋራ ስራዎችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ለአፍሪካ ሀገራት ከሚያደርጋቸው ድጋፎች መካከል የሆነው ይህ ትብብር በተለይም በትምህርት ዘርፉ የሚታይ አስተዋፅዖን እያደረገ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ከአውሮፓውያኑ 2018 አንስቶ የICT ውድድር በማዘጋጀት ከተለያዩ የኢትዮጵያ የኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ አንዱ የዚህ ትብብር ትሩፋት ነው፡፡ በዚህ ውድድር በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ዩነቨርሲቲዎች የተውጣጡ 2357 ተሳታፊዎችን ሲያወዳድር በቻይና ለሚደረገው የመቋጫ ውድድር ሁለት ተማሪዎች እና አንድ አስተማሪ ተመርጠው ይገኛሉ፡፡
በትምህርት ላይ ባተኮረው የክላውድ ስርዓት ዝርጋታው ከሁለት ዓመታት በፊት 25 ሺ የከላው ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን መገኛቸው በዘጠኑ የክልል እና ሁለት ከተማ አስተዳደር በሆኑ 310 ትምህርት ቤቶች ላይ ገጥሞ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ ቀድሞ የተዘረጉትን ስንጨምርበት በአጠቃላይ በዚህ ፕሮግራም 365 ትምህርት ቤቶች እና 10 ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራጩት 30000 ሺህ ኮምፒውተሮች ከ27 ሺህ በላይ ተማሪና መምህራንን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም በአስሩ ዩኒቨርሲቲዎች ዘመናዊ የዳታ ሴንተሮችን ብሎም የትስስር እና የክላውድ መሰረተ ልማቶችን ዘርግቷል፤ በ20 ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማትም ኮርሶችን በመስጠት ላይ ነው፡፡ በጠቅላላውም 300 ሺህ የኮሌጅ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ይናገራል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሁዋዌ ትብብርቸውን የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ ሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተለያ ወቅቶች ሲፈራረሙ ቆይተዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በ37 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን ለመገንባት በ2017 ስምምነት ላይ መደረሱ ነው፡፡ ባለፈው ዓመትም በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን በጋራ ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ ታድያ በቅርቡ የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ሀላፊው ዦው ቲያንቢንግ ከቻይናው የሚዲያ ተቋም ሺንዋ ጋር ባደረጉት ቆይታ በቀጣይም የኢትዮጵያን የአይ.ሲ.ቲ አቅም ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ድጋፎቹ በሶስት ማዕቀፎች ወደ መሬት ሲወርዱ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ የአይ.ሲ.ቲ ስነ-ምህዳር እርሾ እንደሚሆኑ እና ከታችኛው የትምህርት ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ በአስርት ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ዋና ሀላፊው ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ Xinhu
የአንድ ዓመት ጉዞ ማብሰሪያ
===================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባሳለፍነው ቅዳሜ በያያ ቪሌጅ በመገኘት ተከብሯል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች ሶሻል ኮሚቴ በሆነው “ላምባዲና” አማካኝነት የተሰናዳው ዝግጅቱ ልዩ ልዩ የመዝናኛና ሌሎች ክንውኖችን አቅፎ የያዘ ነበር፡፡ ሙሉ ሰራተኛውን አሳታፊ ባደረገ ስፖርታዊ ጨዋታ ጅማሬውን ያደረገው ክብረ በዓሉ ሁለት በሰራተኞች መካከል በተደጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች አስተናግዷል፡፡ ተቋሙን ለሚለቁ እንዲሁም የኃላፊነት ለውጥ ላደረጉ የተቋማችን ሰራተኞች የተደረጉ ስጦታና የምስክር ወረቀት አሰጣጥም የዝግጅቱ አንድ አካል ነበረ፡፡
ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ታስቦ ብዙ ስኬቶች መኖራቸውንና በራስም ሆነ ከአቅም በላይ በላይ በሆኑ ችግሮች ምክንያት ሳይሳኩ የቀሩ ስራዎች ቢኖሩም በአንጻራዊነት እንደ አዲስ ተቋም የተሸሉ ስራዎች መሰራታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ስኬቶቹ በተለይም እንደ አዲስ ተቋምነቱ መሰረት በመጣል እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት ረገድ መሆናቸውን በመናገር ለሚቀጥለው የተቋሙ ጉዞ ካለፈው መልካሙን በመውሰድ በአዲስ መንፈስ መስራት እንደሚገባ አሳስበው አልፈዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ወደ ኢንስቲትትነት ከመቀየሩ በፊት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል በነበረበት ወቅት ጭምር ይካሄዱ የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ አማካኝነት የተሰሩ ስራዎችን በአጭሩ የሚያስቃኝ አጭር ቪዲዩ የቀረበ ሲሆን በመድረኩም በባለ ተሰጥዖ የተቋመችን ቤተሰቦች አማካኝነት ግጥም እንዲሁም ዜማ ከታዳሚው ዘንድ ቀርበው አዝናንተው ነበር፡፡
TECHIN weekly seminar
===================
TECHIN weekly seminar will be held today in TECHIN hall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School).
Yodit molla and zebib getachew will lead today’s session
Issues for this week;
• Psychologists personal qualities as co-relates of their counseling effectiveness
•fligile based flight reservation system with service based approach
Don’t forget to join us
የስነ ልቦና ምክር በህይወታችን ላይ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም
==============================
በየሳምንቱ ሃሙስ የሚዘጋጀው የቴክኢን ሴሚናር በትላንትናው ዕለትም በስነ ልቦና ጉዳይ እና የአይቲ ዘርፍ ላይ ዋና ትኩረቱን አድርጎ ለታዳሚያን ቀርቧል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው የሴሚናር መርሃ ግብር በቅድሚያ በወይዘሪት ዮዲት ሞላ የቀረበው የስነ ልቦና ባለሙያዎች ግላዊ አቅም እና በማማከር ሂደት ውስጥ ያለው አወንታዊ ተፅዕኖ በሰፊው የተብራራ ሲሆን፤ ከሃገራችን የስነ ልቦና አረዳድ ጋር በማስተሳሰርም እጅግ ጠቃሚ ነጥቦች ለማንሳት የተሞከረበት ነው፡፡
ተመራማሪ ዮዲት በዚህ ጥናቷ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ከተለያዩ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ባገኘችው መረጃዎች እና እንደ ሞዴል በወሰደቻቸው መመዘኛዎች በመመርኮዝ ባደረገቸው ሰፊ ጥናት እንደ ቅንጦት የምናየው የስነ ልቦና ምክር በተሻለ ሁኔታ እንዲሰጥ ምን መደረግ አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳብ አቅርባለች፡፡ በዚህም በስነ ልቦና የትምህርት አሰጣጣችን ላይ ከሃልዮት ባለፈ በግለሰቦች ግላዊ እድገት ላይ በማተኮር የስነ ልቦና አማካሪዎችን ውጤታማነት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚቻል አንስታለች፡፡
በዕለቱ የሴሚናር መርሃ ግብር በተከታይነት ለታዳሚዎች የቀረበው ርዕሰ ጉዳይ በተመራማሪ ዘቢብ ጌታቸው የተከናወነው ከአይቲ ጋር የተያያዘው የፕሮጀክት ሃሳብ አንዱ ሲሆን፤ ይኸውም ሞባይልን መሰረት አድርጎ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች የተሰራው የበረራ ማስያዣ ስርዓት (flight reservation system) አንዱ ነበር፡፡ ተመራማሪ ዘቢብ በዚህ ፕሮጀክቷ ላይ አንደገለፀችው ዌብ ቤዝድ የሆነው ይህ ስርዓት ዲዛይን በሚደረገበት ጊዜ የአየር መንገዱ ሁኔታ ለሲስቱሙ ዝግጁ ባለመሆኑ ቀጥታ ወደ ስራ መግባት ባይቻልም ቀጥለው ለለተሰሩት የተለያዩ የበረራ ማስያዣ ስርዓቶች ጥሩ መነሻ እንደነበር ገልጻለች፡፡
በዕለቱ በነበረው ሴሚናር እንደሁልጊዜውም ሁሉ ከታዳሚያን የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፤ በአቅራቢዎች በኩልም መልስ ተሰጥቶባቸው አልፏል፡፡
ብሄራዊ የቢዝነስ ፖርታል ትናንት ይፋ ሆነ
=======================
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋራ በመሆን ያሰራውን ዘርፈ ብዙ የቢዝነስ ገፅ ወይም ፖርታል ይፋ አድርጓል፡፡ ትናንት ይፋ የተደረገው ገፁ ተለምዶአዊውን መንግስታዊ ተግባራትን በዲጂታል ስርዓት አማካኝነት በፍጥነት፣ ወጪ ቆጣቢና ጥራት ባለው መልኩ እንዲተገበር የሚያደርግ ነው፡፡ በተጨማሪም ተገልጋዮች አንዴ ያስገቡት መረጃ ለሁሉም የመንግስት ተቋማት እንዲያገለግላቸው እና ጉዳያቸው ምን ላይ እንደደረሰ ካሉበት ሆነው ለማወቅ ያስችላቸዋል፡፡ ይህም በተለይ ኢትዮጵያ ያላትን የስራ ምቹነት (ease of doing business) በእጅጉ ሲያሳድግ ዜጎችንም ከተንዛዛ አሰራር ይታደጋል፡፡
ሀገራችን ወደ ብልፅግና በምታደርገው ጉዞ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ተግባራት ውስጥ ለስራ ያላትን ምቹነት ማሳደግ አንዱ መሆኑን የገለፁት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ ገፁ በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጎ ሚናን እንደሚጫወት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡ አገልግሎቶችን ሁሉ በአንድ መስኮት እንዲሆኑ እንደሚያስችል እና ቀድሞ መረጃን ለማግኘት ይኬድበት የነበረውን ውጣ ውረድ እንደሚቀርፍ ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት 15 ሺህ ያህል ሰዎች ተመዝግበው እየተገለገሉበት የሚገኘው ይህ ፖርታል የክፍያ አገልግሎቶችን በቀለለ መልኩ እንዲያከናውን የሚያስችሉት ስራዎች እየተሰሩለት እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ እርስዎም ይህን ሊንክ ( www.business.gov.et ) በመጠቀም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
ቴክ ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዛሬ ይጀመራል
እነሆ ቀን ቆጥሮ ዝግጅቱንም አጠናቆ ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን ዛሬ ቅዳሜ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አንስቶ ወደ እርስዎ መድረሱን ይጀምራል፡፡ ከልዩ ልዩ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢኖቬሽንን የተመለከቱ ዜናዎች፣ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ትንታኔዎችቻችን ጋራ MOE TV ይጠብቁን፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=DoLHYKUYXCw
የሎጅስቲክስ ዘርፉን የሚያዘምን የኮምፒውተር ስርዓት ሊተገበር ነው
===============================
የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስ ዘርፍ የሚያዘምን የተቀናጀ የሎጅስቲክስ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መካከል ተደረሰ፡፡ የኮምፒውተር ስርዓቱ ሐብት የት እንዳለ በአግባቡ ተረድቶ ለመጠቀም እና የክትትል ስራዎችን ለመስራት ጠቃሚ አንደሆነ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ያስረዱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ ዘርፉን በICT በማገዝ የትራንስፖርት ስራዎችን እንደሚያስተሳስር እና የሀገራችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እንደሚጠቅም ጠቁመው አልፈዋል፡፡
አዲሱ ስርዓት የሎጅስቲክስ ዘርፉን ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ ከማድረጉም በተጨማማሪ በተለይ ወደ ወደብ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚያሻሽል ይሆናል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ መረጃ አስተዳደር፣ የስራ ቅንጅት እና የጉዞ አስተዳደር ረገድ ማሻሻያዎችን እንደሚያመጣ ሲታመንበት ከዚህ በፊት በተተገበሩ ስርዓቶች ላይ ይስተዋል የነበረውን የቅንጅት ጉድለት እንደሚቀርፍ ስርዓቱን አስመልክቶ በቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህም ባለፈ ግን ይህ ብዙ ክፍተቶችን የሚሸፍን ስርዓት ባክኖ እንዳይቀር ዘላቂ ድጋፎች እንደሚያደረጉና ተቋማቸውም በከፍተኛ ኃላፊነት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል መሆኑን የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩትን ወክለው የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሳንዶካን ደበበ ተናግረዋል፡፡
በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ላይ የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር አብረሀም በላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የለውጥ አመራሩ የለያቸው የህብረተሰብ ጥያቄዎችን ከመመለስም ባሻገር የሎጅስቲክ ስርቱን እንደሚያዘምን ወሮ ዳግማዊት የገለጹ ሲሆን ዶ/ር አብረሀም በበኩላቸው ብዙ ባለድርሻዎች እንደሚሳተፉበት በማወቅ ስራዎች በጥራት እና ደህንነታቸው ተጠብቆ ይከናወኑ ዘንድ አሳስበዋል፡፡