TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሳምንታዊው የቴኪኢን ሴሚናር ተካሄደ
****************************
የቴክኖሎጂ እና አኖቬሽን ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ ሃሙስ የሚዘጋጀው የቴኪኢን ሳምንታዊ ሴሚናር በዛሬው እለትም በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ሁለት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡ በዕለቱ በተከናወነው የሁለት ፕሮጀክቶች አቅርቦት በቅድሚያ አቶ አብዱላጢፍ ሃቢብ ያቀረቡት በህንድ እና ኢትዮጵያ ላይ ያተኮረው የቲውኒንግ (twinning) ፕሮግራም ግምገማ ለታዳሚዎች የቀረበ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ ሃገራት በሚገኙ የተመረጡ የኢንዱስትሪና የምርምር ተቋማት ውስጥ የቴክኖሎጂ እና የክህሎት ሽግግር ምን አይነት ገፅታና ውጤት አለው የሚለውን የሚቃኝ ነበር፡፡
በሴሚናሩ በተከታይነት ለታደሚዎች የቀረበው የምርምር ጥናት በአቶ ክንዴ አስማማው የተከናወነው በባዮማስ አመራረት ላይ ያተኮረ የፕሮጀክት ሃሳብ ሲሆን ይህም በአብዛኛው የሃገራችን ክፍሎች ለባዮማስ ኢነርጂ የሚውሉትን የኩበት እና የቻርኮል ግብዓቶች በተሻሻሉና ብዙ ቦታ በማይፈጁ ቀሳቁሶች በመተካት ለተሻለ ውጤት የሚውሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነበር፡፡ አቶ ክንዴ በዚህ ምርምራቸው ላይ አንደአማራጭ ያቀረቡት የግብዓት አይነት የሩዝ ገለባ እና የበቆሎ ቆሮቆንዳ ሲሆን በተደረገው ሰፊ የምርምር ሂደትም በእነዚህ ቁሳ ቁሶች አማካኝነት ለባዮማስ ኢነርጂ ግብዓት የሚሆን የተሻለ ብስባሽ ወይም (briquettes) ማግኘት እንደሚቻል ለማሳየት የተሞከረበት ነው፡፡
በዚህ ሳምንቱ ሴሚናር፤ እንደወትሮው ሁሉ ከተሳታፊዎች በኩል በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ ጥያቄና አስታያየቶች የቀረቡ ሲሆን በአቅራቢዎቹ ዘንድም ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው አልፈዋል፡፡ የቴክኢን ሴሚናር በየሳምንቱ ሐሙስ ከሰዓት የሚደረግ ሲሆን በተመራማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ ጥናት እና ምርምሮች የሚቀርቡበትና ለማንኛውም ሰው ክፍት የሆነ የእውቀት ማዕድ ነው፡፡
በአመጋገባችን ላይ የኢንዛይም አስፈላጊነት ምን ያህል ነው?
**************************************
ሠውነታችን ከሚያስፈልገው የኢንዛይም መጠን ውስጥ 5ዐ% ያህሉን ራሱ የሚያመርት ሲሆን ቀሪውን 5ዐ% ግን ከጥሬ ምግቦች (Raw Foods) እንድናቀርብለት ይፈልጋል፡፡ ኤንዛይሞች ከ450c በላይ የሆነን ሙቀት መቋቋም ስለማይችሉ ምግቡ ከዚህ መጠነ ሙቀት በላይ በሆነ እሳት ሲበስል ኢንዛይሞቹ ከጥቅም ውጪ ይሆናሉ/ይሞታሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን የ5ዐ% የኢንዛይም አቅርቦት ከጥሬ ምግቦች /አትክልት፣ ፍራፍሬ/ ለሠውነታችን ካላቀረብንለት ያለችውን 5ዐ% የኢንዛይም አቅርቦት አሟጦ ለመጠቀም ብቻ ይገደዳል፡፡ እድሜ እየጨመረ ሲሄድ የኤንዛይሞች ምርት በአንጻሩ እየቀነሰ ይሔዳል፡፡
ኢንዛይሞች በሠውነታችን ውስጥ ለሚከናወን ማንኛውም አይነት ኬሚካላዊ ኡደት (Chemical Reactions) አነሳሽ ሞተር ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ ምግብን ለመፍጨት፣ ልዩ ልዩ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ሰውነት በሚገባ እንዲጠቀም፣ ሰውነትን ራሱን በራሱ የመጠገን ሥራ ወዘተ በኬሚካላዊ ዑደት ወቅት ሳይቀየሩ ተሳትፎ በማድረግ ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣሉ፡፡
ኢንዛይም የተፈጥሮ የምግብ ስርአተ ልመት ስጦታ እንደመሆኑ መጠን ያለ ኢንዛይም ምንም አይነት የምግብ ስርአተ ልመት ወይም (digestion system) አይካሄድም፡፡ ሰውነታችን ውስጥ ያለው የኢንዛይም መጠን አነስተኛ ሲሆን የምግባችን የንጥረ ነገር ይዞታ በእጅጉ እንዲቀነሰ ከማድረጉም ባለፈ የሠውነታችን ሥራ በቀላሉ ሚዛኑን እንዲስት በማድረገም ከፍተኛ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ይህም ምግብ መፍጫ ንጥረ ነገሮችን በሠውነታችን ውስጥ የማሠራጨት ሥራ የሚሰሩ የሆድ ዕቃዎች ማለትም ጣፊያ፣ ቆሽት፣ ጨጓራ፣ ትንሹ አንጀትና ትልቁ አንጀት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡ ይህም በሂደት እንደ ጉበት ባሉ አካላት ላይ የሥራ ማስተጓጎል ያመጣል፡፡ ጉበት የዕለት ተዕለት ሥራው ሲስተጓጎል ደግሞ የሚከተሉት የጤና ችግሮች ይፈጠራሉ፡- ለምሰሌ የደም ቅምር ሚዛኑ ይዛባል (Blood Composition Imbalance)፣ የደም ዝውውር ሂደት ይስተጓጎላል፣ የኮሌስትሮል መጠን ይጨምራል፣ የደም ግፊት እንዲሁም የልብ ችግር ይከሰታል ሊከሰት ይችላል፡፡
በመሆኑም የኢንዛይም መጠናችንን በተገቢው ሁኔታ ለማመዛዘን ማንኛውም የሚዘጋጁ ምግቦች አጠቃላይ ይዘት እንዳይበላሽ እና ከጥቅማቸው ይልቅ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያስከትሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሰረታዊ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አትክልት እና ፍራፍሬ በብዛት አዘውትሮ መመገብ ሰውነታችን የሚፈልገው የኢንዛይም መጠን ሳይጓደል እንዲቀርብ ከማድረጉም ባለፈ ሌሎች ተጨማሪ ጥቅም እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ በተለይም ጥሬ አትክልት እና ፍራፍሬን መመገብ የሠውነታችን የአሲድ/አልካላይን ሚዛን (Acid/Alkaline Balance) እንዲጠበቅ ስለሚረዳ የሆድ ዕቃ ተግባር ወይም የሠውነት የአሠራር ስርዐት ሚዛን ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በምግብ፣ በመጠጥ፣ በአየር፣ እንዲሁም በመጽሐኒት አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የሚገቡ መርዛማ ነገሮች (Toxins) በአግባቡ ከሠውነታችን አንዲወገዱ (Detoxification) ይረዳል፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ ሠውነት በሽታ የመከላከል አቅሙ (Immune System) ይዳብራል፣ ቆዳ ይጠነክራል፣ ሰውነታችን በቂ ኃይል (Energy) ይኖረዋል፣ ሠውነታችንም በተስተካከለ አቋም ላይ ይገኛል፡፡
ምንጭ፡ ScienceDirect
ኮሮና በቻይና እየተረታ መስሏል፤ በተቀረው ዓለምስ?
======================
ከቻይና ውጪ በኮሮና ቫይረስ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር በቻይና ውስጥ እየተመዘገባ ካለው መብለጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ እንደ ድርጅቱ ከሆነ በትናንትናው ዕለት 427 አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች በ37 የዓለም ሀገራት ውስጥ ተገኝተዋል፡፡ ይህም በዕለቱ ቻይና ውስጥ ከተመዘገበው 411 አዳዲስ ተጠቂዎች አንፃር የቁጥጥር ብልጫውን የወሰደ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን እስከዛሬ ከተመዘገቡት የቫይረሱ ተጠቂዎች መካከል ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት በቻይና የተመዘገቡ ቢሆንም ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የወሰደቻቸው ጠንካራ እርምጃዎች በጎ ውጤት ማሳየት ችሏል፡፡ ቻይና መቀነስ የቻለችው የአዳዲስ ተጠቂዎችን ቁጥር ብቻም አይደለም የሟቾችም ቁጥር ወደ 52 ማውረድ ችላለች (በሦስት ሳምንታት ውስጥ የተመዘገበው አነስተኛ ቁጥር)፤ የመሽታው ዋና መነሾ ከነበረው ሁቤ ግዛት ውጪም ምንም ዓይነት ሞት ሳይከሰት ቀርቷል፡፡
ሆኖም ቫይረሱ በአውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች የእሲያ ክፍሎች በፍጥነት እተስፋፋ ይገኛል፡፡ በደቡብ ኮርያ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1700 ሲሻገር፤ ደቡብ አሜሪካንም ከጣሊያን በተመለሰ አንድ ብራዚላዊ አማካኝነት የመጀመሪያ የበሽታውን ተጠቂ አይታለች፡፡ በበሽታው ስርጭት ከአውሮፓ በቀዳሚነት በተቀመጠችው ጣሊያን የአጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 453 ሲደርስ 12 ሞትም ተመዝግቧል፡፡ ከዚህም ባለፈ በሽታው በጣሊያን አማካኝነት ወደ ጎረቤት የአውሮፓ ሀገራትም ጭምር እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህን ተከትሎ የጣሊያን መርማሪዎች በሽታውን ቀድሞ ማስቆም ይቻል የነበረ እንደሆን ምርመራ ከፍተዋል፡፡ ልክ እንደ ጣልያን ሁሉ ኢራንም በመካከለኛው ምስራቅ በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳችው ሀገር ናት፡፡ 26 ነዋሪዎቿን ስታጣ የሀገሪቱ ምክትል የጤና ሜኒስቴሩን ጨምሮ 245 ሰዎችም ሰለባ ሆነውባታል፡፡
እነዚህ ተደማምረው ቫይረሱ በዓለም አቀፍ ወረርሺኝነት እንዲፈረጅና እንቅስቃሴዎችም በዚያው ልክ እንዲሆኑ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሀሳብ እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡ ይህ ግን እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ዋና ሀላፊው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ከሆነ አላስፈላጊና ፈርሀት ውስጥ በመክተት ነገሮችን ሊያበለሻሽ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከዕውነታው በራቀ መልኩ በሽታውን መከላከልን አይቻልም የሚል አመለካከትን ይከስታል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
የግዙፍ ፕሮጀክቶች ውድቀት እና መፍትሄዎቹ
======================
እንደ ትላልቅ ግድብ፣ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የባቡር መስመር እና የፍጥነት መንገድ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሐብት ፈሰስ ይደረግባቸዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ፐሮጀክቶች በስኬት ሳይጠናቀቁ ማየት ለብዙዎቻችን ሩቅ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያም ለዚህ ተጠቃሽ የሚሆኑ ከበቂ በላይ ምሳሌዎችን ይዛለች፡፡
እንደ ለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ገለፃ እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ውስብስብነት ስላላቸው፣ እንዲሁም በማህበረሰብ፣ በአከባቢ እና በመንግስት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ የሚያሳድሩ መሆናቸው “ለማስተዳደር አስቸጋሪ” ያደርጋቸዋል። በፕሮጀክት ማኔጅመንት ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣ አንድ ጥናት በነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ለሚከሰተው ውድቀት መፍትሄ ሊሰጥባቸው ይገባል ያሏቸውን 18 ጉዳዮች አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ ፕሮጀክቶችን ከተያዘላቸው ጊዜና በጀት በላይ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ህልመኝነት፣ ደካማ አመራር፣ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋራ የተገናኘ የአደጋ ስጋት ይገኙበታል፡፡
ጥናቱ ከዳሰሳቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሆነው የእንግሊዝ ፈጣን ባቡር ግንባታ (HS2) በ15.9 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ ከሁለት ዓመት በፊት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ወጪው 18 ቢሊዮን ፓውንድን ተሻግሯል፤ እስካሁንም ስራው አልተጠናቀቀም፡፡ ከዚህ ባሻገር በዓለማችን በግዝፈቱ አቻ የሌለውን የቻይናው ዳሺንግ ኤርፖርት፣ ከዓለማችን በርዝመቱ ቀዳሚ የዋሻ ውስጥ ባቡር መስመር እንዲሁም በካሊፎርኒያ የሚገኘው የፈጣን ባቡር መስመር ያሉ ግንባታዎችንም በጥናቱ የተካተቱ ሲሆን 6000 ሌሎች ጥናቶችንም ተመልክቷል፡፡
ታድያ ችግሮችን በመጠቆም ብቻ ያላበቃው ጥናቱ ለችግሮቹ መልስ ይሆናሉ ያላቸውን የበዙ የመፍትሄ ሀሳቦችን አስቀምጧል፡፡ ባለፈው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ምን መሻሻል እንደሚገባው የሚዘረዝሩ ጥናቶችን ማከናወን፣ በስራው አላማ ላይ ያለ አሻሚነትን ማስወገድ እንዲሁም ነገሮችን በማቅለል ላይ ማተኮር ከነዚህ የመፍትሄ ሀሳቦች መካከል ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡
ምንጭ፡ E & T እና Daily Mail
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ሃር እና ኢትዮጵያ
============
ከሀር እርሻ የሚገኘው ሃር ለሺዎች ዓመታት ያህል እንደ ቅንጦት እቃ ተቆጥሮ ኪስን ቆንጠጥ ከሚያደርግ ዋጋ ጋራ ለገበያ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ የቻይና ትርክቶች እንደሚያመላክቱን የሀር ምርት ግንዛቤ ከአራት ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት በፊት እንደሆነ ነው፡፡ በታሪኩም ሲ ሊንግ ሺ የተባለችው የቻይና ልዕልት (ንግስት) የሃር ትሎችን የየጊዜ እንቅስቃሴ እና እድገት ትከታተል ነበርና ቅርፊት ወይም ኮኮኖች በሚፈጠሩበት ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ታስቀምጣቸዋለች፡፡ በአንድ እለት ይህ ቅርፊት በምትጠጣው ሻይ ውስጥ ይወድቅና ቅርፊቱን የሞላው ቀጭን ገመድ ሲበታተን ታስተውላለች፡፡ በዚህም ሳቢያ ሃርን እንዴት ማውጣት እንደሚቻል መረዳት ቻለች፡፡
ምንም እንኳን የዚህን ትርክት እውነትነት ማረጋገጥ ባይችሉም ታሪክ ተፈፀመበት ከሚባልበት ወቅት አንስቶ ወይም ቀደም ብሎ የሃር ምርት በቻይና ይተገበር እንደነበረ የሚጠቁሙ ታሪካዊ ማረጋገጫዎች በተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ ታሪክ ባሻገር ግን ቻይናዊያን ይህን ምርት በመፍጠርም ሆነ ለሺዎች አመታት ያለተቀናቃኝ በማምረት ብቸኛዎቹ ነበሩ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ቻይናዊያኑ ለሺዎች አመታት የሃር እርሻን በሚስጥርነት በማቆየታቸው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን በዙሪያቸው ወደነበሩት ማህበረሰቦች በዋነኝነት ኮሪያ፣ ህንድና ጃፓን በመቀጠልም ወደ ምዕራቡ ዓለም በተለያዩ መንገዶች ሊተላለፍ ችሏል፡፡ ባለንበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ሐገራት ሃርን የሚያመርቱ ሲሆን ቻይናና ህንድ የዓለምን የሃር ምርት እንደተቆጣጠሩት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሃር እርሻ በዘመናዊ መልኩ ለኢትዮጵያ ከተዋወቀ ሁለት አስርት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ በቅድሚያ መልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል ስራው የተጀመረ ሲሆን ከአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም አንስቶ ግን ወደተለያዩ የሃገሪቱ ቦታዎች ስርጭቱን አድርጓል፡፡ በዚህም የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ምርቱን ወስዶ ወደ ክልሉ ገበሬዎች በማስፋፋት ቀዳሚ ነበር፡፡ ኋላ ላይ በሌሎች ባለ ድርሻ አካላት እና ግለሰቦች አማካኝነት ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር እና አዳማን ጨምሮ ወደ ሌሎች የሃገራችን ክፍሎች ሊስፋፋ ችሏል፡፡ በአንድ ሪፖርት ላይ እንደተቀመጠው በ2005 እንኳን የደረቁ ቅርፊቶች ምርት 3000 ኪ.ግ ደርሶ እንደነበረ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ 95 በመቶው ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ ተልከው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡
ይህ ሲባል ግን የሃር ምርት ሊኢትዮጵያ አዲስ ሁነት ነው ማለት አይደለም፡፡ ሃር በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ እና ሐይማኖታዊ የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ከዘመነ አክሱም አንስቶ ታሪካዊ ዳራውን አኑሯል፡፡ በጥንት ጊዜያት ከፍተኛ መጠን ያላቸው የሃር ምርቶች ከህንድ፣ አረቦች እና ችይና ጭምር ይገዛና በማዕከላዊው የሃገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዋሻዎች ይከማቹ እንደነበር ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ሀገራችን የተለያየ የአየር ንብረት፣ ዕፅዋት እና መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን በተላበሱ ስፍራዎች የተሞላች መሆኗ የተለያዩ አይነት የሃር ትሎችን በማራባት ልዩ ልዩ የምርት ዓይነቶችን እንድታመርት ዕድል ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ከዚህ የተፈጥሮ ፀጋ በሃር ምርት ረገድ ተጠቃሚ መሆን ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ኋላ ላይ በ1930ዎቹ ኢትዮጵያ ለሃር ምርት ያላትን ምቹነት ጣሊያኖች ሊገነዘቡ ችለው ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ግንዛቤ ወደ ተግባር ይለወጥ ዘንድ አስርት ዓመታት አስፈልገውታል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆነው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሃር ምርት በፍጥነት እያደገ ይገኛል፡፡ መረጃዎች እንደሚነግሩን የምርት መጠኑ ከ2014 በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት እንኳን በ200 በመቶ ጨምሯል፡፡ ሐገሪቱም የሃር ምርትን አምርተው ወደ ባህር ማዶ ከሚሸጡ ሐገራት ተርታ ለመሰለፍ በቅታለች፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ ሳባሃር የተሰኘው አነስተኛ የጨርቃጨርቅ አምራች የኢትዮጵያ ሃርን ተጠቅሞ ምርት በማምረት ወደ ውጭ የሚልክ ብቸኛው ኩባንያ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ ቁ.፲፮
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ሁዋዌ እና ኢትዮጵያ
=============
ግዙፉ የቻይና ቴክኖሎጂ ተቋም ሁዋዌ የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ድጋፍ እና የጋራ ስራዎችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ለአፍሪካ ሀገራት ከሚያደርጋቸው ድጋፎች መካከል የሆነው ይህ ትብብር በተለይም በትምህርት ዘርፉ የሚታይ አስተዋፅዖን እያደረገ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ከአውሮፓውያኑ 2018 አንስቶ የICT ውድድር በማዘጋጀት ከተለያዩ የኢትዮጵያ የኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ አንዱ የዚህ ትብብር ትሩፋት ነው፡፡ በዚህ ውድድር በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ዩነቨርሲቲዎች የተውጣጡ 2357 ተሳታፊዎችን ሲያወዳድር በቻይና ለሚደረገው የመቋጫ ውድድር ሁለት ተማሪዎች እና አንድ አስተማሪ ተመርጠው ይገኛሉ፡፡
በትምህርት ላይ ባተኮረው የክላውድ ስርዓት ዝርጋታው ከሁለት ዓመታት በፊት 25 ሺ የከላው ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን መገኛቸው በዘጠኑ የክልል እና ሁለት ከተማ አስተዳደር በሆኑ 310 ትምህርት ቤቶች ላይ ገጥሞ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ ቀድሞ የተዘረጉትን ስንጨምርበት በአጠቃላይ በዚህ ፕሮግራም 365 ትምህርት ቤቶች እና 10 ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራጩት 30000 ሺህ ኮምፒውተሮች ከ27 ሺህ በላይ ተማሪና መምህራንን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም በአስሩ ዩኒቨርሲቲዎች ዘመናዊ የዳታ ሴንተሮችን ብሎም የትስስር እና የክላውድ መሰረተ ልማቶችን ዘርግቷል፤ በ20 ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማትም ኮርሶችን በመስጠት ላይ ነው፡፡ በጠቅላላውም 300 ሺህ የኮሌጅ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ይናገራል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሁዋዌ ትብብርቸውን የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ ሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተለያ ወቅቶች ሲፈራረሙ ቆይተዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በ37 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን ለመገንባት በ2017 ስምምነት ላይ መደረሱ ነው፡፡ ባለፈው ዓመትም በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይ.ሲ.ቲ አካዳሚዎችን በጋራ ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ ታድያ በቅርቡ የሁዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ሀላፊው ዦው ቲያንቢንግ ከቻይናው የሚዲያ ተቋም ሺንዋ ጋር ባደረጉት ቆይታ በቀጣይም የኢትዮጵያን የአይ.ሲ.ቲ አቅም ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ድጋፎቹ በሶስት ማዕቀፎች ወደ መሬት ሲወርዱ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ የአይ.ሲ.ቲ ስነ-ምህዳር እርሾ እንደሚሆኑ እና ከታችኛው የትምህርት ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ በአስርት ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ዋና ሀላፊው ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ Xinhu
የአንድ ዓመት ጉዞ ማብሰሪያ
===================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባሳለፍነው ቅዳሜ በያያ ቪሌጅ በመገኘት ተከብሯል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች ሶሻል ኮሚቴ በሆነው “ላምባዲና” አማካኝነት የተሰናዳው ዝግጅቱ ልዩ ልዩ የመዝናኛና ሌሎች ክንውኖችን አቅፎ የያዘ ነበር፡፡ ሙሉ ሰራተኛውን አሳታፊ ባደረገ ስፖርታዊ ጨዋታ ጅማሬውን ያደረገው ክብረ በዓሉ ሁለት በሰራተኞች መካከል በተደጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች አስተናግዷል፡፡ ተቋሙን ለሚለቁ እንዲሁም የኃላፊነት ለውጥ ላደረጉ የተቋማችን ሰራተኞች የተደረጉ ስጦታና የምስክር ወረቀት አሰጣጥም የዝግጅቱ አንድ አካል ነበረ፡፡
ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ታስቦ ብዙ ስኬቶች መኖራቸውንና በራስም ሆነ ከአቅም በላይ በላይ በሆኑ ችግሮች ምክንያት ሳይሳኩ የቀሩ ስራዎች ቢኖሩም በአንጻራዊነት እንደ አዲስ ተቋም የተሸሉ ስራዎች መሰራታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ስኬቶቹ በተለይም እንደ አዲስ ተቋምነቱ መሰረት በመጣል እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት ረገድ መሆናቸውን በመናገር ለሚቀጥለው የተቋሙ ጉዞ ካለፈው መልካሙን በመውሰድ በአዲስ መንፈስ መስራት እንደሚገባ አሳስበው አልፈዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ወደ ኢንስቲትትነት ከመቀየሩ በፊት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል በነበረበት ወቅት ጭምር ይካሄዱ የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ አማካኝነት የተሰሩ ስራዎችን በአጭሩ የሚያስቃኝ አጭር ቪዲዩ የቀረበ ሲሆን በመድረኩም በባለ ተሰጥዖ የተቋመችን ቤተሰቦች አማካኝነት ግጥም እንዲሁም ዜማ ከታዳሚው ዘንድ ቀርበው አዝናንተው ነበር፡፡
TECHIN weekly seminar
===================
TECHIN weekly seminar will be held today in TECHIN hall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School).
Yodit molla and zebib getachew will lead today’s session
Issues for this week;
• Psychologists personal qualities as co-relates of their counseling effectiveness
•fligile based flight reservation system with service based approach
Don’t forget to join us