TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?
*************************
ባዮሜትሪክስ የሚለው ቃሉ ቀጥታ ከግሪክ የተወሰደ ሲሆን “ባዮ” ማለት ህይወት፣ “ሜትሪክስ” ደግሞ መለካት ወይም ልኬት ማለት ነው። ሁለቱ ቃላት በአንድነት ሲነበቡ ደግሞ የህይወት መለኪያ/ልኬት የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ። ባዮሜትሪክስ የአንድን ነገር ተፈጥሯዊ ባህሪ ማለትም የዲ ኤን ኤ አደራደር፣ የዓይን ቀለምና ምጣኔ፣ የእጅ አሻራ፣ የድምፅ ሞገድ፣ የልብና ነርቭ መንገድ እንቅስቃሴ የሚያጠና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። ወይም ደግሞ ባዮሜትሪክስ የአንድን ሰው ማንነት በግልጥ በሰውነት ገፅታው ወይም በውስጣዊ ሥነ ህይወታዊ ባህሪው መረጃ ላይ በመመስረት ስለ ሰውየው አጠቃላይ ሁኔታ ማውራት የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። እነዚህ ባህሪያት በቀላሉ የማይረሱ፤ የማይጋሩና የማይሰረቁ መሆናቸው ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡
የባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ በጥንት ጊዜ ከክስቶስ ልደት በፊት ከ500BC ጀምሮ የባቢሎናውያን የንግድ ልውውጦች የጣት አሻራዎችን ሸክላ ላይ በማስቀመጥ ይጠቀሙ የነበረ ቢሆንም በትክክል በዘማናዊ ቴክኖሎጂ መልክ ይዞ ግን በስፋትና በረቀቀ መልኩ አገልግሎት መስጠት የተጀመረው እኤአ ከ1981 በኋላ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ በዚህም መሰረት ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ አሁን ካለንበት የቴክኖሎጂ ጣሪያ ላይ ደርሶ የረቀቁ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የሰዎችን ማንነት ለማወቅ የሚጠቅም የአሻራ ቴክኖሎጂ በመሆን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ባዮሜትሪክስ ትልቅ ፋይዳ ያለው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፤ አስፈላጊነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የዓለም የደህንነት ጥያቄ በመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በተለይም በትምህርት ተቋማት፣ ህክምና ተቋማት፣ በታላላቅ ኢንዱስትሪዎች፣ መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በደህንነት ተቋማት እና በሌሎችም ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂዎች መገለጫዎች
* ዩኒቨርሳሊቲ፡ በአለም ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ሊኖረው ይገባል
* ልዩነት፡ በአጠቃላይ ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት ባሕርይ የላቸውም ፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ የሆኑ መንትዮች ለመለየት ከባድ ናቸው ፡፡
* ዘላቂነት፡ የሰዎች የባዮሜትሪክስ ባህሪ ከጊዜ ጋር ልዩነት ሊኖራቸው አይገባም ለምሳሌ ፣ የአንድ ሰው ፊት ከእድሜ ጋር ሊለወጥ ቢችልም በቴክኖሎጂው የመለየት እድሉ ሰፊ ነው።
* ተቀባይነት፡ በሁሉም አለማት ላይ ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም የተቀበሉት መሆኑ
* አስቸጋሪነት፡ ይህም ማለት ሰዎች ለመሸወድ ወይም ለማጭበርብር የማይሞክሩት መሆኑ
ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል፡-
1. የጣት አሻራ ቴክኖሎጂ
2. የፊት ገፅታን የሚለይ ቴክኖሎጂ
3. የአይን እይታ ቴክኖሎጂ
4. የድምፅ ቴክኖሎጂ የሚሉት ከብዙዎች መካከል ጥቂቶች ናቸው፡፡
የባዮሜትሪክስ ጠቀሜታ
* የወንጀል ድርጊት ከመፈፀሙ በፊትና ከተፈፀመ በኋላ የሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ሰው የተለያዩ አለማትን በሚዞርበት ወይም በሚጎበኝበት ወቅት በሚዳረስባቸው ቦታዎች በሚገኙ የኢሚግሬሽን ጣቢያዎች ላይ የጣት አሻራ እንዲሰጥ ይጠየቃል ይህም በሀገር እና ግለሰብ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ወይም የወንጀል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡
* በበርካታ የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት እንደ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይጠቅማል
* የባዮሜትሪክ ሥርዓቶች ሰዎችን በፍጥነት፣ በቋሚነት እና በአስተማማኝ ሁኔታ በመለየት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ
ምንጭ፡ biometricupdate.com እና Si Tech Bufe
ስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia)
***************
ስኪዞፍሬኒያ ከሁለት የግሪክ ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ሲኾን በደምሳሳው “የተበታተነ አእምሮ” የሚል ትርጉምን የያዘ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን በሽታ በቅጡ አይረዱትም፡፡ ስኪዞፎርኒያ “እብደት” ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ስኮዞፎርኒያ በቤተሰብ እንክብካቤ ማጣት የሚመጣ ደዌ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ይህም ትክክል አይደለም፡፡
በሽታው በአንድ ሰው ሰነፍ ኾኖ መገኘት ወይም ደግሞ ስኬታማ ባለመኾኑ ምክንያት የሚመጣም አይደለም፡፡ ስኪዞፍሬኒያ አእምሮ በሚፈጥራቸው ባዕድ ምስሎች የመሰቃየት በሽታ ነው፡፡ ከፍ ሲልም በአእምሮ አስተካክሎ የማሰብ ችሎታ ባለመኖሩ ከውጭው ዓለም ጋር መግባባት መቸገር ማለት ነው፡፡
በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥር የሰደደ ሲሆን በተለይ በታዳጊ አገሮች በስፋት የሚስተዋል ነው፡፡ የአገራችንን ትተን እንደ ታላቋ ብሪታኒያ ባሉ ያደጉ አገሮች እንኳ ከ100 ሰዎች አንዱ በዚህ በሽታ የተጠቃ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህን ቁጥር ወደኛ ብንመነዝረው ስኪዞፎርኒያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እያሰቃየ የሚገኝ በሽታ እንደኾነ መገመት እንችላለን፡፡
ስኪዞፍሬኒያ የብቸኝነት ሕመም ከመሆኑም ባለፈ ከውጭው ዓለም ጋር የመግባባት አቅምን የሚያሳጣ ነው፡፡ በሽታው አስተሳሰባችንን ክፉኛ ስለሚበታትነው እውነታንና እውነት ያልኾነን ነገር የምንለካበትን ሚዛን ያስተናል፡፡ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ስኪዞፍሬኒያ “የመቀወስ” በሽታ ነው ብለው ለመደምደም ይገደዳሉ፡፡ በእርግጥ እስኪዞፎርኒያ የአእምሮ መታወክ አድርገን እንድንመለከተው የሚያደርገን ነገሮችን በጠራ መልኩ ለማየትና ለማገናዘብ መቸገርን ስለሚያስከትል ነው፡፡ ኾኖም በሐኪም እገዛና በቤተሰብ ክትትል በሂደት ማገገም የሚቻልበትና ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ መኾኑን መረዳት ያሻል፡፡
የስኪዞፍሬኒያ ተጠቂዎች ከሚታይባቸው ዋና ዋና ምልክቶች መካካል ሁሉም ሰዎች ሰለኔ እያወሩ ነው ብሎ ማሰብ፣ ራስን መጣል፣ ለነገሮች ምንም ግድ ማጣት፣ ለዓለም ችግሮችና ሰማያዊ ጥያቄዎች ለሁሉም መልስ ለመስጠት መሞከር፣ መንገድ ላይ ሰዎች ይጠቋቆሙብኛል ብሎ መስጋት እና ከቤተሰብና ከጓደኞች መገለል በሽታው የሚያሳያቸው ምልክቶች ናቸው፡፡
የስኪዞፍሬኒያ ምልክቶች ከሰው ሰው የተለያየ ባሕሪ ሊኖራቸው ቢችልም ታካሚው ምን ሁኔታ ላይ ሲኾን የተሻለ ስሜት እንደሚሰማው ለመረዳት መሞከር መልካም ተግባር ነው፡፡ በሽታው ከምንም በላይ የሰዎችን እንክብካቤ ስለሚሻ ከህክምና በተጨማሪ በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ ትልቅ እርዳታ ይኖረዋል፡፡
ምንጭ፡ www.alodokter.com
አውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ታማትር ይሆን?
======================
በአብዛሀው ሰው ሰራሽ የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለው የሚገኘውን ከባቢያዊ ጉዳቶች ለመገደብ ያለሙ እንቅስቃሴዎች በዓለም ሀገራት ዘንድ እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ከካርበን ልቀት የፀዳ ምጣኔ-ሐብትን በአውሮፓውያኑ 2050 ይፈጥር ዘንድ የአውሮፓ ህብረት ይዞት የመጣው “European Green Deal” የተሰኘ ዕቅድ አንዱ ነው፡፡ በተቀመጠው ዓመት ሰፊ የስራ መፍጠር እና የኑሮ ደረጃ ማሻሻልን ያካተተው ይህ የ1.1 ትሪሊዮን ዶላር ዕቅድ በአውሮፓ ብቻ የሚተገበር አይደለም ይልቁንም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት እንጂ፡፡
ለዚህ ድጋፍ በተለይ ኢትዮጵያ ተቀዳሚ ምርጫ ሆና እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡ ለዚህ መነሻው ኢትዮጵያ ለብዙ ጊዜያት ከዓለማችን ደሀ ሀገራት ትመደብ የነበረች ቢሆንም ላለፉት አመታት ግን ምጣኔ-ሐብታዊ ዕድገትን እያስመዘገበች እንድትቆይ መሆኗ ነው፡፡ ይህም የድህነት ምጣኔን በ40 በመቶ እንድትቀንስ ሲያስችላት የዜጎች የመኖሪያ የዕድሜ ጣሪያም በ8 ዓመታት በማደግ ወደ 66 ዓመታት ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡
ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ላይ ሰፊ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡ በቅርቡ እንኳን ባለ ራዕይ መሆናቸው የሚነገርላቸው የኖቤል አሸናፊው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 350 ሚሊዮን ችግኞችን እንዲተከሉ ያስደረጉበት ሁነትም ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ በኃይል ዘርፉም ቢሆን የአረንጓዴ ልማትን የሚያጠናክሩ የኃይል ምንጮችን በመገንባት ላይ ነች፡፡ በግንባታ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት የኮይሻና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቦች ሲጠናቀቁ በጋራ 20ሺ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይልን በየሰዓቱ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ይህም 21.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የካርበን ዳይ ኦክሳይድ ልቀትን ያድናሉ እንደማለት ነው፡፡ ሆኖም እነዚህን ስራዎች ለፍፃሜ የሚያበቃ የገንዘብ ምንጭን በማረጋገጥ ረገድ ክፍተቶች አሉ፤ ሁለቱ ፕሮጀክቶችም ከታለመላቸው ጊዜ ወደኋላ ቀርተዋል፡፡ የኮይሻ ግድብን ያየን እንደሆን የጣልያኑ SACE ባንክ ለግድቡ ግንባታ ይውል የነበረውን የ1.5 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አቁሟል፡፡ በውስጣዊ አቅም መስራት ደግሞ ቀላል የማይባል የምጣኔ-ሐብት መዛባትን ሊፈጥር እንደሚችል ይገመታል፡፡ ታድያ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በቅርቡ ለኢትዮጵያ የሰጠው ድጋፍ ለአውሮፓም ሆነ SACE ማረጋገጫ ሊሆናቸው እና ድጋፋቸውን በመቀጠል የተቋረጡት ስራዎች ዳግም እንዲጀመሩ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡- Project Syndicate
ቴክ-ሳይንስ
• ታዳጊ ፈጣሪዎቻችንን የሚያበረታቱ
• ቴክኖሎጂዎች የተጓዙባቸው የፈጠራ ጎዳናዎች መለስ ብለው የሚቃኙ
• ለኢትዮጵያም ሆነ መላው ዓለም ጉልህ አስተዋፅዖ ያደረጉ ግለሰቦችን የሚመለከቱ
• ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዮች የሚዳስሱ
• እንዲሁም ሌሎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዙርያ ከተጠናቀሩ ዝግጅቶቻችን ጋራ በቅርቡ በ #MOE #TV ይጠብቁን፡፡
ዩትዩብ youtube.com/channel/
UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ፌስቡክ facebook.com/TechinEthiopia/ ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ኮሮናቫይረስ እና ኤች.አይ.ቪን በስልክ አማካኝነት የሚመረምር መሳሪያ ተሰራ
=========================
ብዙ ጊዜ በሀኪም ቤቶች ውስጥ ካሉት አሰልቺ ነገሮች አንዱ የቤተ-ሙከራ ምርመራ ውጤትን መጠበቅ ነው፡፡ በሽታው ሳይታወቅ ስር የሰደደ ከሆነ ደግሞ የቤተ-ሙከራ ውጤትን በሚጠበቅ ወቅት በሽታው ምን እንደሆነ ገና ሳይታወቅ ለከፋ ችግር የሚዳረጉ ህመምተኞች ይኖራሉ፡፡
ይህን ችግር ሊቀርፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ግኝት ከቀናት በፊት ከወደ ሲንሲናቲ ዩኒቨርሲቲ ተሰምቷል፡፡ መሐንዲሶች ከሲንሲናቲ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን አነስ ያለች ተንቀሳቃሽ የስማርት ስልክ ቤተ-ሙከራ ፈጥረዋል፡፡ ይህች የኤ.ቲ.ኤም ካርድ መጠን ያላት መሳሪያ ስልኩ ላይ ተሰክታ የምትሰራ ናት፡፡ በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና ፕሮፌሰር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ቾንግ አህን ከምርምር ቡድናቸው ጋራ በመሆን የስማርት ስልክ መሣሪያዋን ለወባ በሽታ መመርመሪያነት የተጠቀሙባት ቢሆንም ሌሎች ስር የሰደዱ እና ተላላፊ በሽታዎችን ብሎም ከድብርት ጋራ የተያያዙ ሆርሞኖችን መመርመር እንደምትችል ተገልጿል፡፡ መሳሪያዋ መመርመር ከምችላቸው ከነዚህ በሽታዎች ውስጥ ኤች. አይ. ቪ እና አሳሳቢው የኮሮና ቫይረስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ምርመራውን ለማድረግ ታማሚው በቀላሉ የፕላስቲክ ከነዚህ ቺፑን ወደ አፉ በማስገባት የምራቅ ናሙና መውሰድና የወሰደውን ምራቅ ለፍተሻ መሳሪያዋ ላይ ወዳለው ማስገቢያ መክተት ይኖርበታል፡፡ የተወሰዱት ናሙናዎች መሳሪያዋ ላይ ካሉ ሁለት መተላለፊያዎች እንዲሰርጉ ይደረጋል፡፡ አንደኛው መተላለፊያ ናሙናውን ቀዝቅቀዘው ከደረቁ ተከላካይ ፀረ-እንግዳ አካላት (Antibodies) ጋራ ሲያቀላቅለው ሌላኛው ደግሞ የተለያዩት ናሙናዎች በሶስት ሴንሰሮች ላይ መልሰው በሚደባለቁበት ወቅት የሚያሳዩትን ውጤት የሚያነብ በቅዝቃዜ የደረቀ ሙቀት አልባ መብራትን (Luminescent) ይዟል፡፡ መሳሪያዋ በዚህ መልክ ምርመራውን ካከናወነች በኋላ ውጤቱን ለዚህ ተብሎ በተሰራ መተግበሪያ ወይም አፕሊኬሽን አማካኝነት ወደ ሀኪሙ እንዲደርስ ታደርጋለች፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ ከተለምዷዊው ቤተ-ሙከራ አንፃር ይህች መሳሪያ ተመሰሳሳይ ውጤትን የምትሰጥ ቢሆንም ከዋጋ እና አጠቃቀም ቅለት አንፃር ግን የተሻለች ናት፡፡ ከዚህ ባሻገር ግንየመሳሪያውትልቁ ግኝት ናሙናዎቹን ተፈጥሮአዊ መንገድን በመጠቀም በሁለቱ እጅግ ጠባባብ መተላለፊያዎች በማሳለፍ ከሴንሰሮቹ ማድረሷ ላይ መሆኑን የጥናቱ ዋና ፀሐፊ ስትሂቶድሂ ጎሆሽ ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኳን መሳሪያዋ የተሰራችው የተጠቀሱት አይነት በሽታዎችን ለመመርመር ቢሆንም ስማርት ስልኮች ጥቅም ላይ እየዋሉበት ባለው የአዕምሮ ጤና ህክምና ዘርፍ የማገልገል አቅም እንዳላት የተመራማሪዎቹ እምነት ነው፡፡
ምንጭ፡ SciTechDaily
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg
ፌስቡክ facebook.com/TechinEthiopia/
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ካሉበት ሆነው ዕውቀትን ይሸምቱ፤ የብሄራዊ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍትን ይጠቀሙ!!!
=======================
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍት በመገንባት ባለፉት ዓመታት ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍቱ የተለያዩና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን መረጃዎችን ሰብስቦ ያካተተና በሃገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት መስጠት በሚችል መልኩ የተገነባ ሲሆን፤ library.techin.et ብለው በመግባት በቀላሉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍቱ በይዘቱ ሁሉንም የዕድሜ ክፍል፣ የትምህርትና የዕውቀት ደረጃ ያማከለ መሆኑ እና ለአጠቃቀም ምቹ ሆኖ መሰናዳቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ተጠቃሚዎች እንዲጎበኝና አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡ እርስዎም በስራዎ፣ በትምህርትዎ፣ በልጆችዎ ውጤታማነት ላይ አስተዋፅኦ ለማድረግ የብሔራዊ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍትን ይጠቀሙ፤ ለሌሎችም ይጋብዙ!!!
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg
ፌስቡክ facebook.com/TechinEthiopia/
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ይቅርታ ወይስ በቀል፡ የትኛው ደስታን ይሰጥዎታል?
===============
ብዙዎቻችን ስለ ይቅርታ አስፈላጊነት ሲነገር ሰምተናል፤ እኛም ተናግረናል፡፡ በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ተሰርቶ የተሰራ አዲስ ጥናት ግን ሰዎች ከይቅርታ ይልቅ ለመጥፎ ስራ ቅጣት ሲሰጥ ማየት እንደሚስደስታቸው ያስረዳል፡፡
በጆርናል ኦፍ ኮምዩኒኬሽን ሪሰርች ላይ የወጣው ይህ ጥናት 184 የኮሌጀ ተማሪዎችን ማዕከል በማድረግ የተሰራ ነው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ለቴሌቪዥን ሊቀርብ እንደሚችል ተነግሮ 15 አጫጭር ታሪኮች እንዲያነቡ ሲሰጣቸው፤ ከነዚህ መካከል የመጀመሪያ አምስቱ ክፉ ሰው ከበደላቸው ሰዎች ዘንድ በቅንነት ሲስተናገድ፣ ሁለተኛዎቹ አምስት ታሪኮች በደለኛው ተመጣጣኝ ቅጣትን ሲቀበል፣ ሶስተኛዎቹ ደግሞ በደለኛው ላጠፋው ጥፋት ከሚገባው በላይ ቅጣትን ሲቀበል የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ከአጫጭር ታሪኮቹ ውስጥ በአንዱ የሆነ ሰው 50 ዶላርን ከስራ ባልደረባው እንደሰረቀ ይተርካል፡፡ ተሳታፊዎቹ ለዚህ ታሪክ ከተሰጠው ሶስት አይነት መቋጫ ውስጥ አንዱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡ በአንደኛው የታሪኩ መቋጫ ተበዳዩ ለሰራቂ ጓደኛው ይቅርታን ሰጥቶ ቡና እደሚጋብዘው ይተርካል፡፡ በሁለተኛው አፈፃፀም ተበዳዩ ከሰራቂው 50 ዶላር የሚያወጣ አንድ ጠርሙስ ውስኪ ሲወስድበት፤ ሶስተኛው ደግሞ ውስኪውንም ወስዶ የተሰረቀበትን ገንዘብ ሲያስመልስ ይተርካል፡፡
እነዚህን አጨራረሶች ካነበቡ በኋላ ተሳታፊዎቹ ታሪኩን መውደድ ወይ መጥላታቸውን እነዲገልፁ ይጠየቃሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ተበዳዩ ይቅርታን ከሰጠውም ሆነ ከሚገባው በላይ መልስ ከሰጠው በላቀ ተመጣጣኝ ቅጣት ለተሰጠበት ትረካ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ ባነበቧቸው 15 ታሪኮች ውስጥ ያለው የአዝናኝነት ደረጃ በሚገልፁበት ወቅት ደግሞ የይቅርታ ታሪኮቹ የመጨረሻውን ደረጃ ሲይዙ የልተመጣጠነ ቅጣት የሚሰጥባቸው ደግሞ ከሁሉም በበለጠ አዝናኝ ሆነው እንዳገኟቸው የሰጡት መልስ ያሳያል፡፡
ግን ምንም እንኳን ይቅርታ በበቀል ልክ ባያስደስታቸውም ይቅርታን ከበቀል በላይ ጥልቅና ስሜት የሚሰጥ እንደሆነ የተሳታፊዎቹ ዕምነት ነው፡፡ እንደ ግምገማ ከሆነ ሰዎች ላጠፉት ጥፋት ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ መታሰቡ የሰዎች ተፈጥሮአዊ እሳቤ ሲሆን የፍርድ መጓደልን መዳኘት ግን ለሁላችንም እኩል ያልተሰጠ ማመዛዘንን ይጠይቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ መውደድ አለመውደዳቸውን በሚያመነቡበት ኮምፒውተር ላይ የሚገልፁበት ፍጥነትም የተመዘገበ ሲሆን በዚህም መሰረት ጥናቱ ተሳታፊዎች ለተመጣጣኝ ቅጣቱ ትረካ የሚሰጡት ምላሽ ከከፍተኛ አፀፋም ሆነ የይቅርታ ትረካዎቹ የዘገየ ነበረ፡፡ እንደ ጥናቱ ዋና ፀሐፊ ፐሮፌሰር ማቲው ግሪዛርድ ከሆነ ሰዎች የበዳይ ተበዳይ ታሪክ በጠበቁት መልኩ ተጠናቆ ሲገኙት በፍጥነት ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቅጣቱ ወንጀሉን የማይመጥን ሆኖ ሲያገኙት ግን መውደድ መጥላታቸውን ለመግለፅ ረዘም ያለ ጊዜ ሲወስድባቸው ታይቷል፡፡ ሆኖም ፍጥነታቸው ታሪኩ በይቅርታ አሊያም በበዛ አፀፋ ከመጠናቀቁ ጋራ ተያይዞ የተለያየ ነው፡፡ ይህ ግን በሚቀጥሉ ጥናቶች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ Medical Xpress
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
የምድር በ habitable zone መገኘት
********************
ማንኛውም ኮከብ (ፀሀያችንን ጨምሮ) የራሱ የሆነ ሀቢቴብል ዞን (habitable zone) አለው። ሀቢቴብል ዞን ማለት ከኮከቡ በጣም ያልራቀ ወይንም ለኮከቡ በጣም ያልቀረበ የመኖሪያ ዞን ማለት ነው። ፀሀይ ወደ እኛ የተወሰነ የቀረበች ብትሆን ኖሮ ልክ እንደሜርኩሪ ሁሉ በመሬት ላይ ያለው ነገር በሙሉ በመድረቅ ይቃጠል ነበር፡፡ ከመሬት ትንሽ የራቀች ቢሆን ኖሮ ደግሞ ሁሉም ነገር በበረዶ ይሸፈን ነበር፡፡
በሁለቱም ሁኔታዎች መኖር አይቻልም፡፡ ከፀሀይ ጥቂት ሙቀትን የሚያገኙት የዋልታ አካባቢዎች ሁል ጊዜም በበረዶ የተሸፈኑ ሲሆኑ ከዛ የተሻለ ሙቀትን የሚያገኙት የምድር ወገብ አከባቢዎች ሁሌም ሞቃታማ ናቸው፡፡ በዋልታው እና በምድር ወገብ አካባቢ ያለው የሙቀት ልዩነት መሬት ላይ መጠነኛ ሙቀት እንዲኖር በማስቻል መሬት ለህይወት አመቺ እንድትሆን አድርጓታል፡፡
በዚህ ዞን የምትገኘው መሬት በምድር ወገብ ላይ 12,756 ኪሎሜትሮች የምትረዝም ቢሆንም በራሱዋ ዛቢያ ላይ የምትዞርበት ፍጥነት ግን ከግዜ ወደ ግዜ በጣም በዝግታ እየቀነሰ እንደሚገኝ የስነ ፈለክ ሊቃውንት ያስረዳሉ። ይሁንና እንደተመራማሪዎቹ ትንታኔ ከሆነ ይህ ብዙም የሚያሰጋ አይደለም ምክንያቱም በ 100 አመታት ውስጥ በ17 ሚሊ ሰኮንድ ብቻ ነው የሚቀንሰው። ይህም ማለት ከ 140 ሚሊየን አመታት በኋላ ምድር ላይ 25ኛ ሰአት ይጨመራል ማለት ነው።
ምድራችን ከ7 ትላልቅ አለቶች ተገጣጥማ ነው የተሰራችው። እነዚህን አለቶች ቴክቶኒክ ፕሌት (tectonic plates) እንላቸዋለን። ከሌሎች ፕላኔቶች በተለየ ለፀሃይ ብዙም ያልራቀች እና ያለቀረበችው መሬት በተመጣጠነ የህይወት ኡደቷ የእነዚህ አለቶች ተከፋፍሎ መቀመጥን በማስቻል፤ አንዱ ክፍለ መሬት ላይ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሌላኛው ላይ እንዳይሰማ ሆኗል። እዛው አለት ላይ ያሉ ሀገራት ብች ነው ሊሰማቸው የሚችለው። ምድር እንደሌሎቹ ከ 1 ወጥ አለት ተሰርታ ቢሆን ኖሮ ህንድ ላይ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ኢትዪጲያ ላይ ይሰማ ነበር።
ምድር በጠቅላላው በውስጡዋ 32.1%ብረት፣ 30.1% ኦክስጂን፣ 15.1% ሲልኮን እና 13.9% ማግኒዝየም ይዛለች። ከዚህ የምድር የተመጣጠነ የህይወት ኡደት ጀርባ ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ የጠፈር አካለት መካከል ጨረቃ ዋነኛዋ ስትሆን ከዛ ውጪ ደግሞ እንዲሁ ምድርን የሚዞሩ 2 አስትሮይዶች አሉ።
ምንጭ፡ Airtable universe እና E.A
የኮሮና ቫይረስ በአለማችን የደቀነው የኢኮኖሚ ፈተና
**********************************
በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የተለያዩ አደጋዎች ሲያንዣብቡ ቀጥሎ የሚመጣውን ነገር ለመመልከት ግዙፉ የፋይናንስ ማዕከል ዎል ስትሪት ብዙ ታሪኮችን ያገላብጣል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2003 በተከሰተው የሳርስ ወረርሽኝ የቻይና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በከባድ ሁኔታ የተመታ ቢሆንም ቶሎ ለማገገም ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም ነበር፡፡ አሁን የተከሰተው ኮቪድ-19 ከሳርስ የበለጠ የሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ቢሆንም ባለሀብቶች የኢኮኖሚ ተፅዕኖው በተመሳሳይ ሁኔታ ይስተካከላል የሚል እምነት አላቸው፡፡ በተለይም ወረርሽኙ በሁቤ ግዛት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እተስፋፋ ቢሆንም ከሁቤ ግዛት ውጭ ግን የመስፋፋት ፍጥነቱም እየቀነሰ በመምጣቱ አደጋው ብዙም እንደማይሆን ያነሳሉ፡፡ ታዲያ እነዚህን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ዎል ስተሪት እና ብዙ ኢኮኖሚስቶች ኮሮና ቫይረስ በአለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከተለው አሉታዊ ተጽእኖ ዘላቂና የከፋ እንደማይሆን ይተነብያሉ፡፡
ይሁንና በታዋቂው የኢኮኖሚስት መጽሄት ላይ የወጣው ዘገባ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአለም ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለውና የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽእኖ ቀለል እንደማይሆን ነው፡፡ ዘገባው እንደማሳያ ከሚያቀርባቸው ጉዳቶች መካካል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
የድንጋይ ከሰል ፍጆታ ከሌላ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር ከአማካዩ ከአንድ-ሦስተኛ በላይ በሆነ መጠን ቀንሷል፡፡ እንዲሁም የንብረት ሽያጮች ከ 90% በላይ ቀንሰዋል፡፡ እንደሚታወቀው ከቻይና የዘመን መለወጫ በዓል በኋላ ወደ 200 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከትውልድ ቀያቸው ወደ ስራ ይመለሳሉ፡፡ በዚህ ዓመት ግን ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከበአል ተመላሾችን የሚያጓጉዙት ባቡሮች ባዶ ሆነው ነበር፡፡ በዚህም እንግዶች ለ 14 ቀናት ተገልለው የመቆየት ሁኔታ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ከተሞች አስጠንቅቀዋል፡፡
የአሜሪካ ንግድ ምክር ቤት ባጠናው ጥናት መሰረት ከተመረመሩ አስር በሻንጋይ ከሚገኙ ኩባንያዎች ውስጥ ዘጠኝ የሚሆኑት በቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች አሏቸው። ፖስተኞችና መልእክት አመላላሾች አሁንም በኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌታቸው ላይ በጎዳናዎች በብዛት ይታያሉ፤ ነገር ግን ሰዎች በሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ውስጥ በማያውቋቸው ሰዎች የተዘጋጁ ምግቦችን ለመብላት ይፈራሉ፤ ምክንያቱም አዘጋጆቹ በበሽታው ተጠቅተው ሊሆን ይችላል በሚል፡፡ ማኪያቶ፣ ቡና ወዘት መጠጣት በጣም አደገኛ ነው። በዚህም የተነሳ ታዋቂው የቡና ንግድ ኩባንያ ስታርባክስ እንኳን በቻይና ውስጥ ካሉት ከ4,000 በላይ ካፌዎች ግማሹን ለመዝጋት ተገዷል፡፡
ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ደግሞ የኮሮናን ተጽእኖ በሳርስ መነጸር ማየት ይቻላል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ቻይና አሁን 16% የዓለም አቀፍ ገቢ ትሸፍናለች፤ የሳርስ ወረርሽኝ በተነሰበት ጊዜ ግን ይሄ ድርሻ 4% ብቻ ነበር፡፡ በአሁን ጊዜ ቻይና የአለም ሁለተኛዋ ትልቅ አስመጪ (የሌላ አገር ምርት ገዥ) ናት፣ ስለሆነም ማንኛውም በቻይና ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጠር ድክመት ጊዜያዊ ቢሆንም እንኳን በሌሎች ሀገሮች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ አንዳንድ የቻይና ኩባንያዎች ከውጭ ለማስገባት የተዋዋሉትን መዳብ እና የተፈጥሮ ጋዝ ለመሰረዝ እየሞከሩ ነው፡፡ ከ250 ቢሊዮን ዶላር በለይ ወጭ የሚያወጡ ቱሪስቶችም እቤት ውስጥ ዉለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቻይና ኩባንያዎች በአለም የምርት ሰንሰለት ውስጥ በእጅጉ የሚሳተፉ በመሆናቸው፤ የእነሱ ስራ መስተጓጎል በምርት ስንሰለት ውስጥ የሚሳተፉትን በመለው አለም የሚገኙ የሌሎች ኩባንያዎችን ስራ ማስተጓጎሉ እንደማይቀር ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ዎል ስትሪት እና ኢኮኖሚስቶች የሚያቀርቡት የሳርስ ማነፃፀሪያ ብዙም አሳማኝ እንደማይሆን የሚያመለክት ነው፡፡
ዘ ኢኮኖሚስት
cut, copy and paste የሚሉትን የኮምፒውተር መከወኛዎች የፈለሰፈው ሳይንቲስት በ74 ዓመቱ አልፏል
***********************
አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ማዕከል በሆነቸው የሳን ፍራንሲኮዋ ሲልከን ቫሊ ስራውን የጀመረው ላሪ ቴስለር በኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ ላይ ትልቅ አሻራ ያኖረለትን የ cut copy and paste ትዕዛዞችን በኮምፒውቲንግ ስርዓት ውስጥ ያስተዋወቀ ትልቅ ባለሙያ ነው፡፡ ሳይንቲስቱ በ1960ዎቹ አካባቢ አነዚህ ስራዎችን ለመስራት ሲነሳ የኮምፒውተር እንቅስቃሴ እንዳሁኑ ምንም ያልተስፋፋ በመሆኑ የራሱን ከፍተኛ ጥረት ያሳየበት እንደሆነ ይነገራል፡፡
ኒው ዮርክ ውስጥ በምትገኝ ብሮንክስ በተባለች ስፍራ በ1945 የተወለደው ቴስለር ካሊፎርኒያ በሚገኘው ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፤ ከዛም በኋላ የተጠቃሚ በይነገፅ ዲዛይን (user interface design) በሚለው የትምህርት ዘርፍ ላይ በይበልጥ በመስራት የኮምፒውተር ሲስተምን ከሰዎች ጋር ለማቀራረብ በትኩረት እንደሰራ ይነገርለታል፡፡ በረዥም የስራ ህይወቱ ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትልልቅ ስራዎችን የሰራው ላሪ ቴስለር፤ አብዛኛውን የህይወቱን ክፍል ካሳለፈበት እና ታወቂ ስራውን ከሰራበት ዜሮክስ የምርምር ማዕከል በተጨማሪ ስቲቭ ጆብስ በመሰረተው አፕል ኩባንያ ውስጥ ለ17 ዓመት በቺፍ ሳይንቲስትነት የሰራበት ሁኔታ ከሰፊው የስራ ህይወቱ በዋናነት የሚጠቀሱለት ናቸው፡፡
ሳይንቲስቱ የታወቀበት ይህ የ cut copy and paste ፈጠራ ቀድም ባለው ጊዜ ታትሞ የወጣ ፅሁፍን በአካል በማውጣት እና በማጣበቂያ ወይም በሌሎች ቁሶች በመቀየር የሚከናውን ቢሆንም ከፈጠራው በኋላ ግን ብዙ ለውጦች መታየታቸውን በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በተለይም በሲልከን ቫሊ የሚገኘው የኮምፒውተር ታሪክ ሙዚየም ስለሳይንቲስቱ ታላቅ ስራ ህያው ምስክሩን ሲያስቀምጥ የኮምፒውተር ሳይንስ ስልጠናን ከነባሩ አሰራር ጋር አጣምሮ ኮምፒውተርን ለሁለም እንዲሆን ያደረገ የፈጠራ ሰው ሲል ይገልፀዋል፡፡
ቢቢሲ