በ 10 ሰኮንድ ጥርስን የሚያፀዳው Y-Brush ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል
***********************
ባለፈው ዓመት Y-Brush የተባለው አምራች ድርጅት የተለመደውን የጥርስ ብሩሽ በግሩም ቴክኖሎጂ የሚተካ አዲስ ምርት እንደሚያመጣ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ድርጅት በቃሉ መሰረት ጥርስን በ 10 ሰከንዶች ውስጥ ብቻ ለማፅዳት የሚያስችል አስደናቂ ቴክኖሎጂ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
ቴክኖሎጂው በጥርስ ብሩሽ ምርቶች ዙሪያ እነ Oral-B እና Colgate ያላቀረቡትን አስገራሚ ይዘት እና ውጤታማነት በምርቶቹ ማካተቱ፤ አዲስ አብዮትን የፈጠረለት ሲሆን በማንኛውም የጥርስ ሳሙና በመጠቀምም ከመደበኛው ብሩሽ በበለጠ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት ሳያስከትል መገልገል እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የጥርስ ብሩሹ በተዘጋጀለት እጅግ አነስተኛ ሞተር አማካኘነት የትራፒዞይድ ቅርፅ ይዞ ያለውን የአፋችንን አምሳያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተርገበገበ የሚቦረሽ ሲሆን፤ በአጭር ሰኮንዶች ውስጥም በተመሳሳይ ጊዜ የጥርሳችንን የላይኛውንና የታችኛውን ክፍል በማፅዳት ሃጫ በረዶ እንደሚያስመስል ተነግሮለታል፡፡
ከዚህ በፊት እንደ Oral-B እና Colgate ያሉ አምራች ድርጅት ስማርት ቴክኖሎጂን የተላበሰ የጥርስ መቦረሻ ምርት ለገበያ ሲያቀርቡ ይዘው ከመጡት የምርት ይዘት አንጻር ከ100 እስከ 180 የአሜሪካን ዶላር የሚለጥፉበት ቢሆንም፤ አዲሱ Y-Brush ቴክኖሎጂ ግን ይዞት ከቀረበው አስገራሚ ገፅታ አኳያ የተቆረጠለት 125 ዶላር እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ቢቢሲ

ትችትን እንዴት እናስተናግድ
*****************
የበላያችን ወይም አለቃችን በስራችን ላይ አሉታዊ ነገር ተናግሮን ይቅርና ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደርግነው ፕሮፋይል ፒክቸር እንኳን ሁለት ላይክ ብቻ ሲያገኝ ጥሩ ስሜት አይስማንም፡፡ እንዴት እንዲሂ ሊሆን ይችላል ብለን ረሳችንን በመጠየቅ እንባዝናለን፡፡ ይሁንና በስራችንም ሆነ በግል ህይወታችን ስኬታማ የመሆን ትልቅ ጉጉት ካለን ትችትን በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ እና ሲቀጥልም በፀጋ መቀበል ያስፈልገናል፡፡
ትችት ምንድነው
ትችት ሰዎች ለሆነ ድርጊት ወይም ሁኔታ የሚሰጡት አስተያየት ሲሆን ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ትችት ሁሉም ቦታ አለ፡፡ በቤተሰ፣ በጓደኛ፣ በስራ ቦታ እና በፍቅረኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ትችት ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ ቤተሠብ ጓደኛ በቀና አስተሳሰብ የተሠማቸውን ለመግለፅ ወይም እንድንሻሻል በማሠብ አለቆች ሠራተኞች የበለጠ እንዲሰሩ ለማድረግ ትችትን ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቅናት፣ በጥላቻ፣ ስህተት ፈላጊ በመሆን እና የተሻሉ እንደሆኑ ለማሣየት ሲባል ትችት ያለቦታው ሊመጣ ይችላል፡፡
ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች ሰዎች ለራሣቸው የሚሰጡትን ግምት በመቀነስ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች መብሰልስል፣ ጭንቀት፣ ድብርት “ለምን እንደዚህ ተባልኩ?” እያሉ እንቅልፍ ማጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ትችትን በመፍራት አቅም እያላቸው መስራት የሚያቆሙም አይጠፉም፡፡ ትችት የማይቀር ነገር በመሆኑ ብዙ መጨነቅ አይገባንም፡፡ የሚሰነዘሩብንን ትችቶች በሚገባ ለማስተናገድ የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች እናንሳ፤
ማዳመጥ እና በተረጋጋ ሁኔታ መመለስ
ለትችት ምላሽ ከመስጠታችን በፊት ጠቃሚ ነው አይደለም የሚለውን መለየት አለብን፡፡ ጓደኛችን አብረን ከተዝናናን በኃላ ‘’ገንዘብ ታባክናህ’’ ቢለን ሊሠማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ያመለከተው ነገር ራሣችንን እንድንለውጥ የሚያግዘን ሊሆን ይችላል፡፡ ምላሽ ለመስጠት ከመፍጠናችን በፊት ማዳመጥና ምን ለማለት እንደሆነ መረዳት ጥሩ ነው፡፡ የተሰጠን ትችት ጠቃሚ ከሆነ በአክብሮት አመስግነን መቀበል፤ አሉታዊ ከሆነም በአክብሮት ምላሽ መስጠት ራሳችንን ለማጠንከር ትክከለኛው መንገድ ነው፡፡
በግል አለመውሰድ
ሰዎች የሚሰጡት ትችት ስለኛ ከሚናገረው ይበልጥ ስለእነሱ እንደሚናገር ማወቅ አለብን፡፡ በተጨማሪም አንድ ድርጊት ላይ ያለን ድክመት ስለማንነታችን እንደማይናገር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሂሣብ ላይ ቀሽም መሆናችን ቢነገረን ይህ የሚያሳየው ሂሳብ ላይ ቀሽም እንደሆንን እንጂ እኛ ቀሽም እንደሆንን አይደለም፡፡ አንዳንዴ ትችት ደካማ ጎን ላይ በማተኮር ራሣችንን እንድንጠራጠርና ያሉንን ብዙ ብቃቶች እንድንዘነጋ ያረገናል፡፡ በመሆኑም ትችትን በግል አለመውሰድ ለራሣችን ያለንን ግምት እንዳንቀነስ ይረዳናል፡፡
ጠንክሮ መቀጠል
ጠቃሚ ትችትን ተቀብሎ መቀጠል ራሣችንን እንድናሻሽል ይረዳል፡፡ አሉታዊ ትችት የአንድ ሰው አመለካከት ብቻ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ መድረስ ያሰብንበትን አላማ ላይ እንዳንደርስ አሉታዊ ትችቶች እንዲገድቡን መፍቀድ የለብንም፡፡ ትልልቅ ፈጠራ የሰሩ ሰዎች መጀመሪያ ሀሣባቸውን ሲናገሩ “ዋው የሚገርም ትልቅ ሀሣብ ነው” አልተባሉም፡፡ በተቃራኒው “ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡” እና “አትጃጃል ጊዜህን አታጥፋ፡፡” ነው የተባሉት፡፡ ስለዚህም ሼክስፒር እንዳለው የመስታወት ያህል ጥራት የበረዶ ያህል ንጣት ቢኖረንም ሰዎች ከሚሰነዝሩብን ትችት ማምለጥ ስለማንችል፤ የሚያደርሰውን ተፅእኖ መቋቋም እና ራሣችንን ለማሻሻል መጠቀም ትልቁ ነጥብ ነው፡፡
ምንጨ፡ mental wellness

የኤሌክትሪክ ኃይልን ሳይጠቀም ሰውነትን የሚያቀዘቅዘው መሳሪያ
******************
መሃንዲሶች የኤሌክትሪክ ኃይል ሳያስፈልጋቸው በቆዳ ላይ (on-skin) የሚደረጉ የኤሌክትሮኒክስ የግል አየር ማቀዝቀዣዎችን ወይም (air conditioners) ዲዛይን ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሚስሪ ዩኒቨርስቲ በሚገኙ መሐንዲሶች የተነደፈው ይህ “ተለባሽ አየር ማስተካከያ” (air conditioning) በተለይ ወታደሮች ይህን በቆዳ ላይ ያለ መሳሪያ በመጠቀም በጦር ሜዳ ሙቀትን ለመቀነስ እና ቅዝቃዜን ለመፈጠር እንደሚገለገሉበት የተናገሩ ሲሆን፤ ከዚያ ባለፈም የሙቀት ስትሮክ (heat stroke) ወይም ከፍተኛ ድካም እንዳይከሰትባቸው ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ መሣሪያው የደም ግፊትን፣ የልብን ኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እና የቆዳ ድርቀትን (skin hydration) ለመቆጣጠር የሚስችሉ በርካታ የጤና አጠባበቅ መተግበሪያዎች እንደተገጠሙለትም ተነግሯል።
በአሁን ጊዜ ጥቅም ላይ ከሚውሉት ተመሳሳይ ምርቶች ወይም ሌሎች ተዛማጅ ጽንሰ-ሀሳቦች በተቃራኒ ይህ መሳሪያ አየር እንዲገባ የሚያስችል እና በውሃ የማይበላሽ ሲሆን፤ በፓሲቭ ኩሊንግ (passive cooling) ሂደት ለሰውነት የግል አየር ማስተካከያ (air conditioning) አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ፓሲቭ ኩሊንግ (passive cooling) እንደ ፋን ወይም ፓምፕ የኤሌክትሪክ ኃይልን የማይጠቀም ስለሆነ ለተጠቃሚው ምቾትን የመስጠት ሁኔታው የተሻለ እንደሆነ መሀንዲሶቹ ይናገራሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ መሣሪያው አነስተኛ ገመድ ያለው ፓች (wired patch) ቢሆንም፤ ለወደፊቱ ግን ተመራማሪዎቹ የገመድ አልባ ሥሪትን ለመንደፍ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ይወስዳል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አንድ ቀን ይህን ቴክኖሎጂ በስማርት ልብስ ምርቶች ላይ የመተግበር ሃሳብ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ጊዜ መሳሪያው በተደረገበት ቦታ ብቻ የሚያቀዘቅዘው ውስን የሆነውን ችሎታ በማስቀረት የመሣሪያውን የማቀዝቀዝ አቅም በመላው አካል ላይ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል።
ይህ መሳሪያ በሙቀት ወቅት ሰዎች ለመቀዝቀዝ የሚጠቀሙትን የኤሌክትሪክ አጠቃቀምን ለመቀነስ ከመርዳቱም ባለፈ አንገብጋቢ በሆነው የዓለም ሙቀት መጨመር ላይ ትልቅ እገዛ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይታመናል።
ምንጭ፡ Techxplore.com

ዲጂታል ስለላ እስከምን?
******************
በአለማችን በኢኮኖሚ አቅማቸው እጅግ ደካማ ከሚባሉት አገሮች አንስቶ ፈርጣማ አቅማቸውን ተጠቅመው የረቀቁ ስልቶችን እስከሚጠቀሙት ድረስ ስለላ ለዘመናት በአገራት የኖረ አሁን ደግሞ እጅግ ውስብስብ ሆኖ የቀጠለ የደህንነት ማረጋገጫ አንድ ስልት ነው።
የቀድሞው ዘመን የስለላ መኮንኖች ረጅም ጊዜን የሚፈጁ የአካልና አዕምሮ ቅልጥፍናን በሚያጎናጽፉ የረቀቁ ስልጠናዎች አልፈው ወደ ስራ ይሰማራሉ። ሚስጥርን አነፍንፎ ለማግኘት ህይወታቸውን አደጋ ላይ እስከመጣል የሚደርስ መስዋዕትነትንም ይከፍላሉ። በታሪክ ተመዝግበው የሚገኙና ሰላዮች ድንበር እና ጥብቅ የደህንነት ስርዓቶችን ለማለፍ ሲሞክሩ የተያዙባቸው በእድሜ ልክ ጽኑ እስርና በሞት የተቀጡባቸው ታሪኮች በርካታ ናቸው። አንዳንዶቹም መያዛቸው እርግጥ መሆኑን ሲያውቁ ራሳቸውን ወዲያው የሚያጠፉባቸው ጊዜያት ብዙ ናቸው። አሁን ግን የስለላ መኮንኖች በአካል አገራትን እያቋረጡ ወሳኝ የደህንነት እና ውድድር መረጃዎችን ለማግኘት አደጋ የሚጋፈጡበት፣ ፋይሎችን በድብቅ ለማውጣት መከራ የሚያዩበት ዘመን የቀረ ይመስላል። ረቂቅ ቫይረሶችን ወደተለያዩ አገራት የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ስርዓት ውስጥ በማስረግ ቁልፍ መረጃዎችን ፈልፍሎ ማውጣት ተጀምሯል። ይህም ሰላዮችን ማዝመት የግድ ካልሆነ በቀር በአንዳንድ አገራት ስርዓቱ እየቀረ መምጣቱን የሚሳዩ ብዙ ትንታኔዎች ይወጣሉ። አገራት ይህን መሰል የእርስ በእርስ ስለላን ለአፋቸው ቢያወግዙም በተግባር ግን በተደጋጋሚ ይሳተፉበታል።
በተለይም ቫይረሶችንና የረቀቁ የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን ለስለላ መጠቀም ከቀድሞው ሰላዮችን የማሰማራት ዘዴ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ውጤታማ እና ሃላፊነትም ለመሸሽም ምቹ እንደሆነ ተንታኞቹ ይገልፃሉ። ወጪውም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ነገር ግን የረጅም ጊዜ ውጤቱ አስፈሪ ነው። እንደየትኛውም የቴክኖሎጂ ውጤት ቫይረሶቹ ሙሉ በመሉ መረጃ ለማነፍነፍ ብቻ ይውላሉ ብሎ መደምደምና መቶ በመቶ ስራቸውን በዚህ ገድቦ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ከመረጃው ባለፈ መሰረተ ልማቶችን ላለማጥቃታቸው መተማመኛን መስጠት አዳጋች ነው። አይበለውና ይህ መሰሉ በኔትወርኮች ውስጥ የተላከ ቫይረስ ሲስተሙ ላይ ጉዳት ቢያደርስ ሁሉ ነገር ዘመናዊ የሆነባቸው ከቀላል የስልክ ውይይት እስከረቂቅ የህክምና፣ ፋይናንስ እና የአገር ደህንነት ጉዳዮች ድረስ ድባቅ የሚመቱበት ዕድል ጥቂት አይደለም።
በዚህ ጊዜ ለጉዳዩ የቀላል መረጃ ፈላጊ ሁሉ የቫይረስ ጥቃት ብቻ ሳይሆን የሳይበር ጦርነት በድንገት ሊያነሳ ይችላል። ኔትወርካቸው ከስራ ውጪ የሆኑባቸው አገራት ደግሞ ለዚህ ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽን ለመስጠት ይገደዳሉ። በኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ የሆኑ አገራትም ቢሆኑ በቀላል የሚያልፉት ጉዳይ አይሆንም። የመረጃ እና ቢዝነስ ኔትወርኮችን በኮምፒውተር ቫይረሶች መሰለል አላማው ሁልጊዜ የአገር ደህንነት ብቻ አይደለም። የካፒታሊስት ስርዓት የአብዛኛው የአለም እውነታ እንደመሆኑ ኩባንያዎች ሁልጊዜ ውድድር ውስጥ ናቸው። ውድድሩን ለማሸነፍ የሚረዳቸውን የተቀናቃኞቻቸውን መረጃ በየትኛውም መልክ ቢሆን መሰብሰብ ይፈልጋሉ። ይህ ቫይረሶችን መጠቀምም ይጨምራል። ቫይረሶችን ወደተለያዩ አገራትና ኩባንያዎች መላክ ይፋ ይሁንታ የተሰጠው አይሁን እንጂ አሁንም አልቆመም። በርካታ ኩባንያዎች ለሚዲያዎች የደረሰባቸውን ጉዳት ገልፀው መፍትሄ ቢጠይቁም ጆሮ የሰጣቸው የለም። በርካታ የዘርፉ ተንታኞች እንደሚሉት ይህ መሰሉ ስለላ ስርዓት የሚይዝበት ስርዓት ካልተበጀ ቀጣዩ የአለም ጦርነት ከባድ ጥፋትን የሚያስከትለው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን መሰረተ ልማት ላይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ለዚህም ሁሉም አገራት የመረጃ ስርዓቶቻቸውን ደረጃ መፈተሽና ደህንነቱን ማረጋገጥ ለአፍታም ሊዘናጉበት የማይገባ ተግባር ይሆናል።
ምንጭ፡ Si Tech Bufe እና Live Technology

***TECHIN weekly seminar***
Don’t forget to join us for this week’s tech seminar will be held tomorrow in TECHINhall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School).
For this Week Bereket Abayineh and Bada Abdissa will take the stage
Issues to be discussed are;
• Does mind affect matter? (Mr. Bereket)
• Moisture sorption isotherm characteristics and shelf life prediction of Teff (Eraandstis Teff) seed and its flour (Mr. Bada)

አስተሳሰባችን መጪውን ይፈጥራል?
=========================
በትናንትናው የቴክ-ኢን ሴሚናር ከቀረቡት ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች መካከል በቀዳሚነት የቀረበው የሰው ልጆች አዕምሮ ሁናቴዎችን እንዴት መፍጠር እንደሚችል የተተነተነበት ነበር፡፡ “Does Mind Affect Matter?” በሚል ርዕስ ገለፃውን ያቀረበው አቶ በረከት በተለይም ከሳይንሱ ዓለም ጎራ በማለት የዕውኑ ዓለም እንዴት የእሳቤዎቻችን ውላጅ እንደሆኑ ያስረዳ ሲሆን ከዚህም በመነሳት እሳቤያችንን በማስተካከል መጪያችንን ብሩህ ማድረግ በመቻላችን ላይ አስረግጦ ተናግሯል፡፡
በቀጣይነት መድረኩን ተረክቦ ጥናታዊ ፅሁፉን ያቀረበው አቶ ባባ አብዲሳ ነበር፤ ጥናቱም ለኢትዮጵያዊያን የዕለት ተዕለት ምግባችን የሆነውን የጤፍ ዱቄት ያለብልሽት ማቆያ መንገድ ላይ ያውጠነጠነ ነበር፡፡ ምርምሩ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው የዱቄት ማስቀመጫችን ማዘመን ላይ እና በየትኛው ቁስ በምን ያህል የሙቀት ብሎም እርጥት መጠን ቢቀመጥ የቆይታው ጊዜ ይረዝማል በሚለው ላይ ነው፡፡ ነጭ ጤፍ ላይ ተመስርቶ የተሰራወ ይህ ምርምር ከተለያዩ ግብዓቶች ምጥን ቅንብር የሚሰራ ማሸጊያ ውስጥ ዱቄቱን በ27 ዲግሪ ሴሊሺየስ እና 65 በመቶ የወበቅ መጠን አሽገን ካስቀመጥነው በትንሹ 730 ቀናትን ያለ ብልሽት መቆየት እንደሚችል አሳይቷል፡፡
በዚህ ሳምንቱ ሴሚናር፤ እንደወትሮው ሁሉ ከተሳታፊዎች በኩል በርዕሰ ጥያቄና ላይ ጥያቄና አስታያየቶች የቀረቡ ሲሆን በአቅራቢዎቹ ዘንድም ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው አልፈዋል፡፡

ሊመለስ ነው!! ሊመለስ ነው!! ሊመለስ ነው!!
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
አዎ ቴክ-ሳይንስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከእርሰዎ ዘንድ ሊመለስ ነው፡፡ ቴክ-ሳይንስ የዕውቀት አድማስን የሚያሰፉ ስለ ሀገራችን እና የተቀረው ዓለም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁናቴ ብሎም ክንውኖች ዙሪያ ግንዛቤን ከሚያስጨብጡ ዝግጅቶቹ ጋራ በ MOE ቴሌቪዥን በቅርቡ ይመለሳል፡፡ ዕውቀትን እያዝናኑ ያስጨብጥልዎ ዘንድ ተጨንቀን በምናቀርባቸው የብላቴናት፣ የቴክ ታሪክ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ግለ ታሪክ መሰናዶዎቻችን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ይፈተሻል፤ ዜናና ጥቆማዎቻችንም ሳይረሱ፡፡

photo_2020-01-17_16-54-18.jpg
119.9 KB
የኢኖቬሽን ስታርታፕ እና ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ጥሪ
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለሚያካሂደው የቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን መቀበል መጀመሩን ያበስራል፡፡ ከአመልካቾች መካከል የተመረጡት ለስድስት ወራት ቆይታ ባለው በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በቆይታቸውም የስራ ቦታ፣ የምክር እና ስልጠና አገልግሎቶችን ከኢንስቲትዩቱ ሲቀርብላቸው ከአማካሪዎች፣ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ባለቤቶች እና የኢኖቬሽን ሀብ ጋርም ትሰስር የሚፈጠርላቸው ይሆናል፡፡
መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት እስከ መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
https://forms.gle/RHdfBrCJUNdR5oaY7
ዕድሉ እንዳያመልጥዎ፤ ይፍጠኑ!!!

ቢግ ዳታ እና የ4ተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ጅማሮ
************************
ዓለማችን ባሳለፈቻቸው የመጨረሻዎቹ አራት ምዕተ ዓመታት ውስጥ አራት የተለያዩ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን አሳልፋለች፤ በማሳለፍ ላይም ነች፡፡ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዮት እ.አ.አ በ1700 መጨረሻ እና በ1800 መጀመሪያ በእንግሊዝ ተጀምሮ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች የተሰራጨ ሁነት ነው። ታድያ በዚህ አብዮት ልዩ መገለጫነት የሚወሳው በእንፋሎት የሚሰሩ መሳሪያዎች መፈጠር ነው። በሁለተኛው ማለትም በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መካከል በነበረው የኢንዱስትሪ አብዮት ኤሌትሪክን በመጠቀም ምርቶችን በስፋት ማምረት ተጀምሯል። ሶስተኛውን እና አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮቶች ከመጀመሪያ ሁለቱ አብዮቶች በመለየት የኢንፎርሜሽን አብዮቶች ተብለው ይታወቃሉ። ሶስተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት (የመጀመሪያው የኢንፎርሜሽን አብዮት) በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የፈነዳ ሲሆን ኮምፕዩተር እና ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ እውቀቶች መምጣት የጀመሩበት ጊዜ ነበር። አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት (ሁለተኛው የኢንፎርሜሽን አብዮት) ከ21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እስከ አሁን ያለንበት ጊዜ የቀጠለ አብዮት ሲሆን በዚህ አብዮት ውስጥ እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ እንዲሁም ርእሳችን የሆነውም ግዙፍ ዳታ (big data) የዚህ አብዮት ፍሬዎች ናቸው።
ግዙፍ ዳታ ከበይነ መረብ፣ ከተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎች፣ ሴንሰሮች ወዘተ… የሚገኙ ያልተዋቀሩ እና በከፊል-የተደራጁ ዳታዎች ግዙፍ ስብስብ ነው። እነዚህ ዳታዎች የፔታባይት ወይም የኤክሳባይት ማካማቻ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ለመደበኛ ዳታቤዝ ይበዛሉ። ግዙፍ ዳታን ከመደበኛ ዳታ ጋር ስናነጻጽር የግዙፍ ዳታ መጠን ከፔታባይት(1015) እስከ ዜታባይት(1021) የሚደርስ ሲሆን የመደበኛ ዳታ መጠን ከጊጋባይት(109) እስከ ቴራባይት(1012) ነው። በሌላ ንፅፅር ግዙፍ ዳታ ያልተደራጁ የታጨቁበት ሲሆን መደበኛ ዳታ ከዚህ በተራኒ ተደራጅተው ተቀመጡበት ነው።
ግዙፍ ዳታ የሚገለጽባቸው አራት ባህሪያት አሉት። እነሱም መጠን(volume)፣ አይነት(variety)፣ ፍጥነት(velocity) እና ትክክለኛነት(veracity) ናቸው። አንድ ዳታ ግዙፍ ዳታ ለመባል ከፍ ያለ መጠን ያላቸው (ከፔታባይት እስከ ዜታባይት)፣ አይነታቸው የተለያየ (ምስሎች፣ ጽሁፎች፣ ተንቀሳቀሽ ምስሎች..)፣ በተለያየ ፍጥነት የገቡ እና ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ ዳታዎች ስብስብ መሆን ይኖርበታል።
ይህ ግዙፍ ዳታ የሚሰበሰበው ከሴንሰሮች፣ መተግበሪያዎች፣ ከሶፍትዌር ኤጀንቶች፣ ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች ሊሆን ይችላል። ይህን የተሰበሰበ ግዙፍ ዳታ ጥቅም ላይ ለማዋል ወይም ትርጉም እንዲሰጥ ለማድረግ የትንተና(analysis) ስራ መሰራት ይኖርበታል። የግዙፍ ዳታ ትንተና ለመስራት ከሚረዱ ሶፍትዌሮች መካከል ሃዱፕ(Hadoop) አንዱ ነው። ሶፍትዌሩ ከመምጣኔ-ሐብት፣ ፖለቲካ፣ ቢዝነስ እንዲሁም አየር ንብረት ጋራ የተያያዙ ትንበያዎችን ለመስራት ይረዳል። ድርጅቶች እንደ ፌስቡክ እና ትዊተርን ከመሰሉ የማህበራዊ መገናኛዎች ዳታዎችን በመሰብሰብ እና በመተንተን የደንበኞቻቸውን ፍላጎት ለማወቅ ይሞክራሉ። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም እ.ኤ.አ በ2012 የፕሬዝዳንትነት ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ሲያደርጉ የግዙፍ ዳታ ትንተናን ድምጽ ለማሰባሰብ ተጠቅመዋል።
ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገራችን ገና እየገባ ያለ ከመሆኑ አንጻር በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ደረጃ ጥቅም ላይ ሲውል ማየት አልተለመደም። ሆኖም እንደ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማት ቴክኖሎጂውን የማላመድ እና ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፡ The Conversation እና Enterprise Big Data Framework
ውድ ተከታታዮቻችን የዩትዩብ ቻናላችንን ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት በመቀላቀል አስተማሪ ምስሎችን በየጊዜው ያግኙ=> https://www.youtube.com/channel/
UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg

ቻይና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፒጃማ ለብሰው አደባባይ የሚወጡ ሰዎችን አሸማቀቀች
**
የቤት ውስጥ ልብስ (ፒጃማ) ቤት ውስጥ በምንሆንበት ሰዓት ምቾት የሚሰጠን ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ሰዎች ህዝብ በሚሰበሰብበት/አደባባይ ፒጃማ ለብሰው ሲወጡ ይስተዋላሉ፡፡ ይህንን ድርጊት የቻይና ከተማ የሆነችው የሱዡዋን ከተማ አስተዳደር ከህዝብ የወጣ/ከባህል ውጭ አንዳንዴም የስልጣኔ ጉድለት ሲሉ ይገልፁታል።
ይህን ህዝባዊ ያልሆነ ባህሪ ምንነት ኒዩ ወርክ ታይምስ ሲተረጉመው ሰዎች በህሊናቢስነት ከማህበረሰቡ የተለየ ባህሪ ሲያሳዩ ወይም ድርጊት ሲፈፅሙ ማለት ነው ብሎታል፡፡ አያይዞም ፒጃማ ለብሶ አደባባይ መውጣትን ብዙ ሰዎች እንደቀላልና ትኩረት የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ ሊሆን እንደማይገባው የተናገሩ ሲሆን አደባባዮች የሁሉም እንደመሆናቸው መጠን የህዝብ ክትትል የሌለባቸውና ከተፅዕኖ ነፃ የሆኑ ሊሆኑ እንደሚገባ እንደሚያምኑ ዘግቧል፡፡
ያም ሆነ ይህ የሱዡዋን ከተማ ማኔጅመንት ቢሮ ነዋሪዎቹ መሰል አለባበስን ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ፒጃማ በመልበስ ወደ አደባባይ የሚወጡ ነዋሪዎች እንዲሸማቀቁ ለማድረግና ድርጊቱን ለመቀነስ በሚል ሰኞ ዕለት የሰባት ሰዎችን ፎቶ ከነአለባበሳቸው እና ማንነታቸው በማህበራዊ ሚዲያ (ዊ-ቻት) ላይ በመልቅቀ እስከ ማክሰኞ ድረስ እንዳቆየው የቻይና ዘ-ፔፐር አሳታሚ ዘግቧል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንደገለፀው የሰዎቹ ፎቶ የሚወሰደው የሲሲቲቪ ካሜራዎችን በመጠቀም ሲሆን የተወሰደውን ፎቶ የፊት ገፅታ በመለየት ስማቸውን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚለይ እንደሆነ ዘግቧል፡፡
ምንጭ: cnet

ጭንቀት ጸጉር መሸበት ላይ አስተዋፅኦ እንዳለው በጥናት ተረጋገጠ፡፡
ለረጅም ጊዜ የጸጉር ሽበት ከጭንቀት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ይገመት ነበር፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ (Harvard University) ተመራማሪዎች ይህ ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር ሳይንሳዊ የሆነ ትንታኔ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡
ጭንቀት ሰውነታችን በ
ተመራማሪዎቹ የዚህን ጉዳይ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጥናታቸውን የጀመሩት የጭንቀት እና የጸጉር ሴሎች ምን አይነት ትስስር እንዳለቸው ለማወቅ በመሞከር ነበር ሆኖም ትስስሩን ማግኘት እንደሚታሰበው ቀላል አልነበረም፡፡ ይህም ጭንቀት የሁሉም የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያመጣው ችግር ስለሚኖር የትኛው የሰውነት ክፍልና የትኛው ሴል ከጸጉር መሸበት ጋር እንደሚያያዝ ለማወቅ የሰፋ ጥናት ጠይቋል፡፡
ይህንንም ችግር ለማወቅ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ሰውነታቸን ውስጥ የሚካሄዱ ሂደቶችን አጥንተዋል፡፡ አጥጋቢ የሆነውንም ውጤት ያገኙት በጸጉራችን ያሉ ጉበኖች(Follicles) ላይ ሲሆን በዚህ ውስጥ ያሉ ስቴም ሴሎች በውስጣቸው የጸጉር ቀለም ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፒግመንት (Pigments) ሴሎችን ይይዛሉ፡፡
ስለዚህም ከነርቮቻችን የሚለቀቁ ኬሚካሎች(Chemicals) በስቴም ሴል(Stem Cells) ውስጥ ያሉትን ፒግመንቶች(Pigments) ከመጠን በላይ እንዲመነጩ በማድረግ የስቴም ሴሎች (Stem Cells) እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሴሎቹ ራሳቸውን የሚተኩበትን አቅም ስለሚያሳጣ መመለስ በማይችሉበት መልኩ የጸጉር ቀለምን የሚያመነጩት ስቴም ሴሎች አቅማቸው እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡
ስለዚህም በተፈጥሮና በተለምዶ ለመኖራችን አስፈላጊ ተብሎ የሚነገረው የሰውነታችን ማምለጥ ወይም መጋፈጥ ምላሽ የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች ስቴም ሴሎች ላይ የሚያመጡት ዘላቂ የሆነ ጉዳት የጸጉር ቀለማችን ያለጊዜው እንዲቀይርና እንዲሸብት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ታይቷል፡፡
ጭንቀትን ከጸጉር መሸበት ጋር ለማያያዝ ተመራማሪዎቹ ከሙሉ የሰውነት ለውጦች ተነስተው ወደ ግለሰብ የሰውነት አካላት፣ ሴሎችና የተለያዩ ሂደቶችን በማጥናት በመጨረሻ የሚያገናኛቸውን ቦታ ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህንንም የጥናት መንገድ ጭንቀት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚያመጣውን ለውጦች ለማጥናት እንደሚጠቀሙበት ይናገራሉ፡፡
science daily
ለረጅም ጊዜ የጸጉር ሽበት ከጭንቀት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ይገመት ነበር፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ (Harvard University) ተመራማሪዎች ይህ ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር ሳይንሳዊ የሆነ ትንታኔ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡
ጭንቀት ሰውነታችን በ
ማምለጥ ወይም መጋፈጥ (Fight or Flight) ምላሽ የሚሰጠውን የነርቫችን ክፍል ስራውን እንዲጀምር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ በሰውነታችን ጸጉር የሚበቅልበት ክፍል ላይ የሚገኙ ሴሎችን(Cells) በማይመለስ መልኩ ለጉዳት ያጋልጣል፡፡ተመራማሪዎቹ የዚህን ጉዳይ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጥናታቸውን የጀመሩት የጭንቀት እና የጸጉር ሴሎች ምን አይነት ትስስር እንዳለቸው ለማወቅ በመሞከር ነበር ሆኖም ትስስሩን ማግኘት እንደሚታሰበው ቀላል አልነበረም፡፡ ይህም ጭንቀት የሁሉም የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያመጣው ችግር ስለሚኖር የትኛው የሰውነት ክፍልና የትኛው ሴል ከጸጉር መሸበት ጋር እንደሚያያዝ ለማወቅ የሰፋ ጥናት ጠይቋል፡፡
ይህንንም ችግር ለማወቅ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ሰውነታቸን ውስጥ የሚካሄዱ ሂደቶችን አጥንተዋል፡፡ አጥጋቢ የሆነውንም ውጤት ያገኙት በጸጉራችን ያሉ ጉበኖች(Follicles) ላይ ሲሆን በዚህ ውስጥ ያሉ ስቴም ሴሎች በውስጣቸው የጸጉር ቀለም ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፒግመንት (Pigments) ሴሎችን ይይዛሉ፡፡
ስለዚህም ከነርቮቻችን የሚለቀቁ ኬሚካሎች(Chemicals) በስቴም ሴል(Stem Cells) ውስጥ ያሉትን ፒግመንቶች(Pigments) ከመጠን በላይ እንዲመነጩ በማድረግ የስቴም ሴሎች (Stem Cells) እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሴሎቹ ራሳቸውን የሚተኩበትን አቅም ስለሚያሳጣ መመለስ በማይችሉበት መልኩ የጸጉር ቀለምን የሚያመነጩት ስቴም ሴሎች አቅማቸው እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡
ስለዚህም በተፈጥሮና በተለምዶ ለመኖራችን አስፈላጊ ተብሎ የሚነገረው የሰውነታችን ማምለጥ ወይም መጋፈጥ ምላሽ የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች ስቴም ሴሎች ላይ የሚያመጡት ዘላቂ የሆነ ጉዳት የጸጉር ቀለማችን ያለጊዜው እንዲቀይርና እንዲሸብት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ታይቷል፡፡
ጭንቀትን ከጸጉር መሸበት ጋር ለማያያዝ ተመራማሪዎቹ ከሙሉ የሰውነት ለውጦች ተነስተው ወደ ግለሰብ የሰውነት አካላት፣ ሴሎችና የተለያዩ ሂደቶችን በማጥናት በመጨረሻ የሚያገናኛቸውን ቦታ ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህንንም የጥናት መንገድ ጭንቀት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚያመጣውን ለውጦች ለማጥናት እንደሚጠቀሙበት ይናገራሉ፡፡
science daily
5ኛው የሚጥል ህመም ሳምንት በኢትዮጵያ
*****************************************
**********************
በህክምና ስሙ ኢፕለፕሲ በአገራችን ደግሞ በተለምዶ የሚጥል በሽታ እየተሰኘ የሚጠራው ይህ በሽታ በአገራችን ሊሰጠው የሚገባውን ያህል ትኩረት ያላገኘ በሽታ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ የተደረገው የአገራችን ጥናት እንደሚያመለክተው ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የበሽታው ተጠቂ ያሉ ሲሆን ከነሱ ውስጥ የህክምና እርዳታ እያገኙ ያሉት 5 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡
እንደ ባለሞያዎች ገለፃ ይህም የሆነበት ምክኒያት ማህበረሰቡ ስለበሽታው ባለው የተሳሳተ አመለካከት እና አናሳ ግንዛቤ ነው፡፡ ከዛም በተጨማሪ በአገራችን በህመሙ ዙሪያ ባለው ልማዳዊ አመለካከት የተነሳ ህመሙ ያለባቸው ሰዎች የሚገለሉ እና አድሎ የሚደርስባቸው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
ኢፒለፕሲ በማዕከላዊ የነርቭ ሲስተም ( central nervous system) መዛባት ምክኒያ የሚከሰት ኒውሮሎጂካል በሽታ ነው፡፡ በሽታው የመጣል፣ የማፈራገጥ፣ ያልተለመዱ በሃሪዎችን የማሳየት እና እራስን የማሳት ጠባይ እንዳለው ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
ኢፕለፕሲ ፆታ እና ዘር የማይለይ በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምልክቶች እንደየሁኔታው እና እንደየሰው ሊለያይ የሚችል ሲሆን አንዳንዱ ሰው ሲጥለው ለተወሰነ ጊዜ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሳያሳይ እራን ሊስት የሚችል ሲሆን አንዳንድ ሰው ላይ ደግሞ እጅና እና እግርን የማፈራገጥ ባህሪ ያሳያል፡፡
አንድ ሰው አንድ ግዜ ስለወደቀ እና እራሱን ስለሳተ በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ባይንም ከአንድ ጊዜ በላይ ምክኒያቱ ባልታወቀ መልኩ እራሱን ከሳተ ግን ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ሂዶ ምርመራ እንዲያደርግ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡
በሽታው በህክምና እርዳታ የሚድን ሲሆን የህክምናው ሁኔታ እንደ በሽታው ዓይነት እና ጥልቀት የሚለያይ መሆኑን ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ አብዘኃኛውን ግዜ በሽታውን በመድሃኒት ብቻ መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ በሽታው አንዳንድ ሰው ላይ የዕድሜ ልክ ሁኖ የሚቀጥል ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ ከእድሜ ጋር አብሮ የሚጠፋ ይሆናል፡፡
ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም በአገራችን እያደረሰ ያለውን የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ችግር ጥልቀት በመመልከት በህመሙ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል የህክምና እድሎችን የማመቻቸት ፣ስለህመሙ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማስተካከል እና በሽታው እንይከሰት ቀድሞ የመከላከል ግንዛቤን ለመፍጠር በሚል በጎ ዓለማ በ2008 ዓ.ም በወርሀ ጥቅምት ተመሰረተ፡፡
ይህ ተቋም ከዚህ በፊት ለ4ጊዜ ብሄራዊ የሚጥል ሀመም ሳምንት የተሰኘ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን ያዘጋጀ ሲሆን እነሆ ዘንድሮም ለ5ኛ ጊዚ ብሄራዊ የሚጥል ህመም ሳምንት ከየካቲት 2/2012- የካቲት 8/2012 ድረስ የሚቆይ እና የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ያሳተፈ የመድረክ ውይይት እና የእግር ጉዞ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ኢትዮጵያዊ እና ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ትስስር ያላቸውን አካላት ጋብዟል፡፡
ፕሮግራሙ የተለያዩ ውይይቶችን፣ጉብኝቶችን እና ስልጠናዎችን ያካተተ ሲሆን በስተመጨረሻም የካቲት 8/2012 በእግር ጉዞ ይጠናቀቃል፡፡የእግር ጉዞው መነሻ የሚሆነው ከ6ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው በር መግቢያ አካባቢ ሲሆን በ4ኪሎ አደባባይ ተደርጎ መልሶ መድረሻው እዛው 6ኪሎ እንደሚሆን አስታውቃዋል፡፡
እርሶም ተጋብዘዋል እንዳይቀሩ!