የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች የዘር መድሎ ያደርጋሉ ተባለ
*************************************
አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች ነጭ የቆዳ ቀለም ካላቸው ሰዎች በላይ ሌላ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች በትክክል ላይለዩ እና ሊያምታቱ እንደሚችሉ የአሜሪካ መንግስት ጥናት ያስታወቀ ሲሆን ይህም በህግ አስፈፃሚ አካላት በስፋት እየተተገበረ ያለውን የዚህን ቴክኖሎጂ ህፀፆች በማጉላት ቴክኖሎጂው ላይ ያሉ ጥርጣሬዎችን ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ጥናቱ የተከናወነባቸው አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ አልጎሪዝሞች አፍሪካ-አሜሪካውያንን እና የኢሲያዊያን ፊቶች ከነጭ ካውኬዢያን ፊቶች ከ10 እስከ 100 ጊዜ በላይ በስህተት የለዩ ሲሆን ኔቲቭ አሜሪካውያንም በትክክል ካልተለዩት ውስጥ እንደሚገኙ ጥናቱን ያከናወነው የአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ገልጿል፡፡ ጥናቱ በወንጀል ምርመራዎች ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ለመለየት በብዛት የሚገለገለው የአልጎሪዝሙ የአንድ ለብዙ አቻ-መለያ በይበልጥ አፍሪካ-አሜሪካውያን ሴቶችን በትክክል እንዳለየ አሳይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ኩባንያዎች የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎቹ ቀደም ሲል የግለሰቦችን ፆታ በአግባቡ የመለየት ችግሮች እንዳሳዩ ሲያመለክቱ እንደነበር የታወሰ ሲሆን የጥናቱ ውጤትም የፊት አቻ-ልየታው በስነ-ህዝብ ልየታ መስክ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት ማረጋገጫ ሆኗል፡፡
የጥናቱ ውጤት በኤርፖርቶች፣ በፖሊስ ዲፓርትመንቶች እና በጠረፍ ፍተሻዎች እየተለመደ የመጣውን የዚህ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂ አስመልክቶ በፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም በወንጀል ፍትህ አክቲቪስቶች ዘንድ ሲደረጉ የነበሩት የማንቂያ ደውል ማስጠንቀቂያዎች ላይ ተጨማሪ ማስረጃ ሆኗል፡፡ የመንግስት ሳይንቲስቶችም በቴክኖሎጂዎቹ ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች እየተጋሩ እንደሆነ በአሜሪካ የሲቪል ነፃነቶች ማህበር ከፍተኛ የፖሊሲ አናሊስት የሆኑት ጄይ ስታንሊ ተናግረዋል፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ አንድ የተሳሳተ የፊት-አቻ ሲያጋጥም በኤርፖርቶች የሰዎችን በረራ ሊያስተጓጉል፣ የተራዘመ ቃለመጠይቆችን ሊያስከትል እና በተጠርጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተትን ሊያመጣ ከመቻሉም በላይ፤ ለጠንካራ የፖሊሲ ምርመራዎች ሰዎች እንዲዳረጉ፣ በስህተት ወደእስር እንዲሄዱ እና ከዛም ለከፉ እርምጃዎች ሊዳርግ እንደሚችል አክለው ተናግረዋል፡፡
በዚህ በአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት የተከናወነው ጥናት ወደ 100 የሚጠጉ የቴክኖሎጂውን አቅራቢዎች እንደ ኢንቴል፣ ማይክሮሶፍት፣ ቶሺባን እንዲሁም ታዋቂ የቻይና ኩባንያዎች የተካተቱ ቢሆንም የፊት-መለያ ሶፍትዌሮችን ለፖሊስ ዲፓርትመንቶች በብዛት የሚያቀርበው የአማዞን ኩባንያ ግን በጥናቱ አልተሳተፈም፡፡
በጣት የሚቆጠሩ የአሜሪካን ከተሞች እንደ ሳን ፍራንሲስኮ፣ ኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ የመሳሰሉት የፊት-አሻራ መለያ እድገትን በቴክኖሎጂው ላይ የተለያዩ እገዳዎችን በማድረግ ሊቆጣጠሩት እየሞከሩ የሚገኙ ሲሆን እንደ ፖርትላንድ እና ኦሪጎን የመሳሰሉ ከተሞች ደግሞ ከዚያ ባለፈ የፊት-አሻራ መለያዎችን ሙሉ በሙሉ ከክልል መንግስት እና ከግል ኩባንያዎች የማስቀረት ሀሳብ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካን የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት የአሜሪካን ዜጎች እና ግሪን ካርድ ያላቸውን ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸውና ከመውጣታቸው በፊት የፊት-አሻራ መለያ ምርመራውን እንዲደረግ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን የሚዲያን ሪፖርቶች እንዲሁም ጠንካራ ህዝባዊ ተቃዎሞዎችን ተከትሎ እቅዱን ገተውታል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን እና ሮይተርስ

TECHIN weekly seminar
*********************
You are invited to join us today @TECHINhall
Issues for this week:
A Multistage Data Mining For Crime Prevention: The Case of Jimma Town Police Office
Dropout among Primary School Students: Reason, Experience and Mitigating Factors
Presenters:
Bikila Mezgebu and Biniam Wendmu
#TECHINtalk
#TECHIN #weeklyseminar

የቴኪኢን ሳምንታዊ ሴሚናር ተካሂዷል
******************************************
የቴክኖሎጂ እና አኖቬሽን ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ ሃሙስ የሚዘጋጀው የቴኪኢን ሳምንታዊ ሴሚናር በትላንው እለትም በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ሁለት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው የሴሚናር መርሃ ግብር በቅድሚያ በተመራማሪ ቢቂላ መዝገቡ የተዘጋጀው A Multistage Data Mining For Crime Prevention: The Case of Jimma Town Police Office የተሰኘው የምርምር ውጤት ለታዳሚዎች የቀረበ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች እና ጠቃሚ አስተያየቶች መሰረትም ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል፡፡ ተመራማሪ ቢቂላ ያቀረበው ይህ የምርምር ውጤት በጅማ ከተማ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ለወንጀል መከላከል ታስቦ የተሰራውን የመረጃ ልየታ እና የዳታ ክላስተሪንግ ፕሮጀክት የሚያሳይ ሲሆን በሂደቱም በወንጀል ተከሰው የሚገኙ ግለሰቦችን የተለያየ መረጃ በመቀመርና በመመንጠር (Mining) እንዴት ለተሻለ ዉሳኔ እናውለዋለን የሚለውን ጉዳይ የሚያሳይ ነበር።
ከሱ በማስቀጠል የምርምር ውጤቱን ያቀረበው ተመራማሪ ቢኒያም ወንድሙ በቤንች ማጂ ዞን በሚገኝ ወረዳ የተደረገውን ፍሬያማ የምርምር ስራ ያስረዳ ሲሆን በዚህም እንዲሁ ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል። ተመራማሪው በዚህ ጥናት እንዳነሳው በተጠቀሰው ቦታ የሚኖሩ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደሌላ ነገር የሚሳቡበት ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ጥናቱን ለማድረግ እንዳነሳሳው ተናግሯል። በዚህም በተደረገው ሰፊ ጥናት ለችግሮቹ መከሰት ዋና መንስኤ የሆኑትን ጉዳዮች በመለየት እንዴት ከችግሩ መውጣት እንደሚቻል እና ማን ምን መሥራት አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ምክረ ሀሳብ የቀረበበት እንደሆነ ገልጿል።

የስኳር መጠንን ለመለካት የሚውለው መነፅር
******************************************
የብራዜል እና የዩኤስ ሳይንቲስቶች የሰውን እንባ በመጠቀም ደም ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን ለመለካት የሚያስችል መነፅር መስራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ተማራማሪዎቹ ይፋ ያረጉት ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት በመነጽሩ እጀታዎች ላይ በሚገጠም ባዮሴንሰር አማካኝነት ውጤቱን ወደ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ የሚልክ ቴክኖሎጂ ሲሆን፤ ለስኳር ህመምተኞች የምርመራ ጊዜን በማሳጠር እና እንግልትን በመቀነስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡
እንደሚታወቀው የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የግሉኮስ መጠናቸው ለማወቅ ዘወትር ክትትል ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በሽታ በአሜሪካ ውስጥ ብቻ 62 ሚሊዮን ሰዎችን ሲያጠቃ፣ በዓለም ዙሪያ ደግሞ 380 ሚሊዮን ሰዎች በዚህ ህመም ይጠቃሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ደግሞ በቅርብ አሥርት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ውስጥ የስኳር በሽታ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን በ2035 ወደ 580 ሚሊዮን ሰዎችን ሊያጠቃ እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
በበሽታው የተያዙ ብዙ ሰዎች የደም ናሙና ለመስጠት ጣታቸውን በመወጋት እንዲሁም የደም ግሉኮስ መጠናቸው ለመለካት ተንቀሳቃሽ የስኳር መለኪያን (glycosometer) ይጠቀማሉ። ይህ ሂደት በቀን ውስጥ ለብዙ ጊዜ ሊደጋገም የሚችል በመሆኑ በህመም እና በበሽታ (infection) የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡
ታዲያ ሳይንቲስቶች የፈጠሩት ይህ የባዮሴንሰር መነፅር ግሉኮስ ኦክሳይድ (glucose oxide) የሚባለውን ኢንዛይም መለየት ከመቻሉም ባላይ በሰውነታችን ውስጥ በፈሳሽ መልክ የሚገኙ ነፃ የሆኑ የግሉኮስ መጠኖችን ለማወቅ የሚያስችል ነው፡፡ ቴክኖሎጂው እንደቀደሙት መሳሪያዎች በየጊዜው ከጣት ላይ የሚወሰድ ደምን ከማስቀረቱም በተጨማሪ ስኳርን፣ ቫይታሚን እና የአልኮል መጠኖችን በአንድ ላይ መለካቱ ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
ባዮሴንሰሮቹ በእንባ አማካኝነት የስኳር መጠኑን መለካት ሲያስፈልጋቸው ላቺማል (lachrymal gland) የተሰኘውን ዕጢ እንባ እንዲመነጭ ማነሳሳት ያስፈልጋል፡፡ ታዲያ ይህ ከአይን የሚወጣው እንባ ከግሉኮስ ኦክሳይድ ጋር ሲገናኝ የኤሌክትሮኖችን ፍሰት በቀላሉ መለወጥ ስለሚችል፤ በዓይን መነፅሮች እጀታ ላይ በተጫነው ባዮሴንሰር ውስጥ የመጣውን መረጃ በመያዝ እና በመተንተን ውጤቱን ወደሚፈለገው ኮምፒውተር እና ስማርት ስልክ ለመላክ ያስችላል፡፡
ባዮሴንሰሮች በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት በተለይ በህክምናው ረገድ የሰው ልጅን ጤንነት ወደተሻለ ሁኔታ ከፍ ለማድረግ ላቅ ያለ ሚናን የሚጫወቱ ሲሆን ወደፊትም በምርምር ደረጃ እነዚህን ባዮሴንሰሮች በመጠቀም ለተለያዩ የህክምና ግልጋሎቶች ማዋል እንደሚቻል ሳይንቲስቶች ይጠቁማሉ፡፡
ምንጭ
https://www.scidev.net/…/brazilian-researchers-eye-biosenso…

SciDev.Net
Home
SciDev.Net: Bringing science & development together through news and analysis.
በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራችው እና በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሚትር በምትጓዘው መኪና ዙሪያ ከፈጠራው ባለቤት ጋራ ያደረግነውን አጭር ቆይታ በዩትዩብ ቻናላችን ይከታተሉት https://www.youtube.com/watch?v=xvaSA6T_N_Q
YouTube
የምስራች ለኢትዮጵያዊያን!!! በሊትር 40 ኪ.ሜ የምትጓዘዋ መኪና በኢትዮጵያዊዉ ታዳጊ
የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማ ፪
====================
በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና ገቢ ማመንጨት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የተሰሩ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ከሰራተኛው ዘንድ ዛሬ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከጠዋት አንስቶ በተከናወነው መርሀግብር 14 የተቋሙ ሰራተኞች ከተለያዩ ፕሮፖዛሎቻቸው ጋራ በመገኘት ገለፃ የተሰጡ ሲሆን ለአህዝቦተ ሳይንስ ግብዓት ከሚሆኑት አንስቶ ከመንገድ ላይ መፀዳዳት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የከተሞች የንፅና ጉድለት የሚፈቱ ሐሳቦች ለመድረኩ ቀርበዋል፡፡
የዛሬው መርሀ ግብር ለሁለተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን ከሳምንታት በፊትም መሰል 16 የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ቀርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቢሮ ውስጥ አቀማመጣችን ሁኔታ
======================
በቢሮዎ ውስጥ ያልዎት አቀማመጥ ምን ይመስላል? በስራ ቦታስ ምን ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያከናውናሉ? እነዚህ ሀሳቦች የተነሱት ጤናማ የሆነ ሰራተኛን እና የስራ ውጤታማነትን ለማሳደግ ያለመው የጤና ግንዛቤና የቢሮ አጠቃቀም ስልት (ergonomics) ስልጠና ዛሬ ለሰራተኞቻችን በተሰጠበት ወቅት ነበረ፡፡ ከአቀማመጥም ባሻገር ኮምፒውተና ሌሎች መሳሪያዎችን ስንጠቀም ልንወስዳቸው በሚገቡን ጥንቃቄዎች ዙሪያም በጥቁር አንበሳ ሰሆስፒታል የፊዚዮ ቴራፒ ሀኪሟ ዶ/ር ዊንታና መኮንን ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ከእርሳቸው በተጨማሪም በስኳር በሽታና መከላከለያ መንገዶቹ ላይ በኢትዮጵያ ስኳር ህመምተኞች ማህበር እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እያገለገሉ ባሉት ዶክተር ቴዎድሮስ አበራ አማካኝነት ስልጠና ሲሰጥ፤ የስኳር በሽታ ምንነት እንዲሁም በሀገር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተፅዕንዖ ተዳሶበታል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የስኳር ህመምተኞች ድርሻ እንደምትወስድ የገለፁት ዶክተር ቴዎድሮስ በሽታው የህይወት ዘይቤ ለውጥን ተከትሎ ከመምጣቱ አኳያ የአመጋገብ ስርዓትን በማስተካከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ እና በቅድመ ምርመራዎች መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሌላዋ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፊዚቴራፒ ሀኪም ዶ/ር ህይወት ዘላለም አማካኝነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አስመልክቶ የተሰጠ ስልጠናም የዛሬው ዝግጅት አካል ነበረ፡፡ በዚህኛው ክፍል ከተዳሰሱት ጉዳዮች መካከልም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረጋችን አስቀድመን ልናሟላቸው በሚገቡን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም ከስኳር በሽታ ጋራ ያለው ትስስር የገኙበታል፡፡ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዙሪያ ያሉ አጓጉል ልማድ እና አስተሳሰቦች አስወግዶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን በአጥንት ጤና፣ የደም ቧንቧዎች ብሎም ድብርትን ከማስወገድ አንፃር የሚያጎናፅፋቸው ጥቅሞቹ ተካፋይ መሆን እንደሚቻል ዶ/ር ህይወት አስረድተዋል፡፡
ከተሳታፊ ሰራተኞች በተወረወሩ ጥያቄዎች እና በአሳታፊ እንቅስቃሴዎች ታጅቦ በተከወነው በዚህ ዝግጅት ለሌሎች ስልጠናዎችም ቃል የተገባ ሲሆን፤ በተለይም በኒውትሬሽን ባለሙያ የታገዘ ትምህርት ለማቅረብ እንደሚሰራ የስፓይን ኦንሰልታንሲ ባለቤት እና ስራ አስኪያጁ አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡

ለኢትዮጵያዊያን የተዘጋጀ የስልጠና ዕድል፤ በቻይና
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
አሊባባ የኔትፕረነርሺፕ ስልጠና ፕሮግራም ለኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች እና የቢዝነስ አንቀሳቃሾች የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዴት በስራቸው ላይ መልካም ለውጥ ለማምጣት እና የከባቢያቸውን ምጣኔ ለመለወጥ እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ ስልጠና መስጠት ይፈልጋል፡፡ ስልጠናው የሚሰጠው የአሊባባ ዋና መስሪያቤት በሚገኝበት ሀንዦ፣ ቻይና ሲሆን ለ10 ሐብትቀናትም ይቆያል፡፡ በስልጠናው ላይ መሳተፊያ መስፈርቶች፤
• የግላቸውን ወይም በጋራ ቢዝነስ ያቋቋመ/ች ለሁለት ዓመታት የሰራ/ች
• እንግሊዘኛን አቀላጥፎ የሚናገር
• የስራ ፍቃድ ያለው
• ቢያንስ አንድ የማረጋገጫ ምስክር መጥቀስ የሚችሉ
• ዕድሜያቸው ከ45 በታች የሆነ (ሴቶች ይበረታታሉ)
ለምዝገባ እና ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት በዚህ ሊንክ ይጠቀሙ
https://activity.alibaba.com/supplier/alibaba-netpreneur-training-ethiopia.html

የተለገሰ የሰውነት አካልን ማቆያ ዘዴ
========================
የኩላሊት፣ ልብ እና ሌሎችም ንቅለ ተከላ ህክምናዎች በኛው ሀገር እንኳን ከጆሮዋችን ከተላመዱ ሰንበትበነት ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የኩላሊት ብቻ 21,000 ንቅለ ተከላዎች በየዓመቱ በማከናወን ዘርፉን ይመራል፡፡ ጉበት፣ ልብ እና ሳንባ ተከታዩን ስፍራ ይዘው እናገኛቸዋለን፡፡ ታድያ እዚህ ላይ ጥያቄን የሚፈጥረው እነዚህ የሰውነት አካላት ከለጋሹ ተወስደው ወደ ታካሚው እስከሚደርሱ ድረስ ያሉትን ሰዓታት እንዴት ያሳልፋሉ የሚለው ነው፡፡ በዛሬው ዓለም የንቅለ ተከላ ህክምና ውስጥ እነዚህን የሰውነት አካላት ለማቆየት በቀዳሚነት ጥቅም ላይ የሚውለው ስልት በቅዝቃዜ ውስጥ ማቆየት ነው፡፡ በመደበኛ ወቅት ህዋሶቻችን የሰውነት አካላቶቻችንን ከጉዳት ለመጠበቅ ኬሚካሎችን ያስወጣሉ ያስገባሉ፡፡ ሆኖም ህዋሶቻችን በሚቀዘቅዙበት ወቅት ይህን ተግባር ለማከናወን ስለሚቸገሩ ኬሚካሎቹ በዚያው በመቆየት ህዋሳቶችን ይጎዷቸዋል፡፡ ታድያ ይህን ለመከላከል በውስጣቸው ያለውን የሶዲየም እና ፖታሺየም መጠን በመቆጣጠር የሰውነት አካላቱ የሚገጥማቸውን ሙሉ በሙሉ የመበላሸት አደጋ በሰዓታት ለማዘግየት ታስቦ የሚሰጥ ነው፡፡
የንቅለ ተከላ ህክምና በብዛት ከሚከወንባቸው የሰውነት አካላት መካከል በቅዝቃዜ ውስጥ ሲቀመጥ ቶሎ በመበላሸት ልብ ቀዳሚ ነው፡፡ እንደ ባለሙያዎች ከሆነ ልብ በቀዝቃዛ ስፍራ ከ4 እስከ 6 ሰዓታት በላይ መቆየት አይችልም፡፡ በቅዝቃዜ ውስጥ አራት ሰዓት ከሞላው በኋላ በልብ ውስጥ ያሉት ህዋሳት ስራቸውን ማከናወን እያቃታቸው ይመጣል፤ ልቡም ወደ መክሸፍ ይሸጋገራል፡፡ ኩላሊት በአንጻራዊነት ከሌሎቹ በመላቅ ከ24 እስከ 36 ሰዓታት ሳይከሽፍ መቆየት ይችላል፡፡ ሳንባ ከ6 እስከ 8 ሰዓታት ጉበት ደግሞ እስከ 12 ሰዓታት ለሚዘልቅ ጊዜ ያለክሽፈት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡
አማራጭ ማቆያ ዘዴዎች?
እ.አ.አ ከ1960ዎቹ አንስቶ በህክምና ውስጥ የቆየው ለንቅለ ተከላ የተዘጋጁ የሰውነት አካላትን በቅዝቃዜ ውስጥ የማቆየት ስልት ከሰውነት ውጪ ያለውን የአካላቱን የቆይታ ጊዜ ከማሳጠሩም በላይ ቅዝቃዜ ስፍራ ውስጥ ተቀምጠው ባሉበት ሰዓታት ውስጥ መክሸፍ አለመክሸፋቸውን ለማረጋገጥ ምንም ዕድል አይሰጥም፡፡ ሆኖም ይህንን ማድረግ የሚያስችል አንድ ስልት በቅርብ ለህክምና ዓለም ቤተኛ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ፐርፊውዥን በመባል የሚታወቀው ይህ ስልት ከሰውነት የወጡት እነዚህን አካላት በማሽን አማካኝነት ልክ ልብ በሰውነታችን ውስጥ እንደሚያደርገው ሁሉ ኦክስጅን እና በንጥረ ነገሮች የበለፀገ ፈሳሽን ወደ እነርሱ ይረጫል፡፡ በማሽኑ ውስጥ ቆይታቸው ኬሚካላዊ አፀግብሮታቸውን የሚያከናወኑት እና ቆሻሻን የሚያመነጩት እነዚህ የሰውነት አካላት የስኳር ክምችታቸው ዳግም እንዲሞላ መርዛማ የአፀግብሮት ውጤቶቻቸውም እንዲወገድላቸው ይደረጋል፡፡ ግን ከዚህም ባሻገር ማሽኑ በአካላቱ ውስጥ ያለውን የላክቴት ሁኔታ በመገምገም በመስራት ወይም አለመስራት ላይ መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ ፐርፊውዥን የሰውነት አካላቱን በቅዝቃዜ ስፍራ ከማስቀመጥ የሚለየው በሚጠቀመው ስልት እና ሁኔታቸውን በማወቁ ብቻም አይደለም፤ የሰውነት አካላቱ ለንቅለ ተከላ ተብለው ከለጋሹ ሰው ከተለዩ በኋላ ያላቸውን የውጪ ዓለም ቆይታ በማሳደግና የሚደርስባቸው የጉዳት መጠንን በመቀነስ ጭምርም እንጂ፡፡ በአንድ ወቅት በተደረገ ጥናት ለንቅለ ተከላ ህክምና ከተለገሱት የሰውነት አካላት መካከል የህክምና ባለሙያዎች በብልሽት ምክንያት ከመለሷቸው መካከል በቅዝቃዜ ውስጥ የቆዩት በፐርፊውዥን ከቆዩት አንፃር ከእጥፍ ልቀው ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

የቴክኖሎጂ ወጪ ቱሩፋቶች
***********
አደጉ የሚባሉ አገራት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እጅግ ከፍተኛ ወጪን በመመደብ መስኩን ለመምራት በፉክክር ላይ ይገኛሉ። እርግጥ ነው ታዳጊ አገራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምጥቀት ተሳታፊነት ላይ ደካማ ቢሆኑም ወቅታዊ ሁኔታዎች ግን ወደ ዘርፉ እንዲያተኩሩ እያስገደዳቸው ይገኛል። ታዳጊ አገራት ባላቸው አቅም የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ከዘመኑ ጋር ለመራመድ የግዴታ ያህል ሆኖባቸዋል። ዘመኑ መጓዣው ቴክኖሎጂ፤ መራመጃው ሳይንስ ነውና መፃይ ዘመንን የተሻለ ለማድረግ በዘር ላይ ብርቱ ጥረት ማድረግ ይገባል።
አሁን በደረስንበት ዘመን በየትኛውም ዘርፍ አገራዊ አቅምን ለማጎልበት ዋንኛ መሳሪያ ሳይንስ መሆኑ አይካድም። አንዳንድ አገራት ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ማጠንከሪያ ዋንኛ የገቢ ምንጫቸውን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ አድርገዋል። ቀድመው በዚህ ዘመን ሳይንስ የማይተካ ሚና እንዳለው ተረድተዋልና ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማሳደግና ከቱርፋቱ በመጠቀም የኢኮኖሚ አቅማቸውን በማፈርጠም ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ በሰጠችው ልዩ ትኩረት የተለያዩ እምርታዎች በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች። ይሁንና በሳይንስና ቴክኖሎጂው መስክ ቀዳሚ ከሆኑ አገራት ጋር ስትነፃፀር እጅግ በራቀ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ይህ የሚያሳየው በቴክኖሎጂ አቅም ዳብሮና ተሻሽሎ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል እንደ አገር ብዙ ስራዎች ይጠበቃል።
በኢትዮጵያም የሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ መረጃና የኢኖቬሽን አጠቃላይ እንቅስቃሴና በዘርፉ ያሉ ጥናቶችና ምርምሮች አንዱ ተግባሩ የሆነው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሀገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ወጪ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ባጠናው ጥናት ለይቷል።
በጥናቱ ውጤትም የቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግ ስራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀቶችና ቁሶች አጠቃቀም ላይ መሰረት ያደረገ ነበር። በመሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን አቅም ባገናዘበ መልኩ ከጊዜ ወደ ጌዜ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በማሟላትና አገራዊ አገልግሎቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ከፍተኛ ወጪዎችን በማውጣት ዘርፉን በማዘመን ላይ መሆኑን አመላክቷል።
ጥናቱ 80 የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይና 41 ከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት ላይ ያተኮረ ሲሆን በአጠቃላይ 121 የመንግስት ተቋማት ላይ ትኩረት አድርጓል። መንግስት በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ የመንግስት ተቋማት ላይ የሚያወጣቸውን ውጪዎች መሰረት ያደረገው ጥናቱ ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ ትምህርታዊ ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም አገልግሎቶች ላይ የሚወጣው አገራዊ ወጪ የተመለከተ ነው።
ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም ወይም በፈረንጆች አቆጣጠር 2016/17 ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እስከ አምስት ቢሊዮን የሚደርስ ወጪ አውጥታለች። ውጤቱም ከቀደሙ ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ወጪዎች እያደገ ቢመጣም ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነፃፀር ግን አሁንም አነስተኛ ነው። አገራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገታቸው ለውጥ የሚለካው ለጉዳዩ ከሚሰጡት ትኩረትና እሱን ተከትሎ አጠቃላይ ሁኔታዎች ምቹ በማድረግ ለተግባራቱም አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ከዚያም የሚያስገኘውን ውጤት በመለካት ይሆናል።
ይህ ጥናት ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ በሁለተኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠና መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መንግስት በዘርፉ ያወጣው ወጪ በተመለከተ ያስቃኘና አሁን ላይ በአገሪቱ ያለውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች ያለበትን ደረጃ ለመለካት ያስቻለ ነው። ጥናቱ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ አጠቃላይ አገልግሎትና ጥናትና ምርምሮች በዘርፉ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ሁሉ የሚያቅፍ ወጪ ነው። ይህ ጥናት ያመላከታቸው ዋንኛ ጉዳዮች መሰረት በማድረግ በቀጣይ ለዘርፉ የሚመደበው በጀት ምን መልክ መያዝ እንዳለበትና ምን ላይ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ መነሻ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
አቶ ቃል ኪዳን ተሾመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመረጃ አደረጃጀትና ዕውቀት አስተዳደር ዳይሬክተር፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አገራዊ ወጪ ማውቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልፃሉ። ስለዚህም አገራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ወጪያቸውን ለይተውና የሚያወጡትን ወጪ ተግባራዊነቱን ለመገምገም ያስችላቸው ዘንድ የዘርፉን አጠቃላይ ወጪ በየጊዜው ያስጠናሉ።
አገሪቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ የምታወጣቸው ወጪዎች በጥናትነት መልክ መዳሰስና ያሉትን ገፅታ ማወቁ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያስገኘና ፋይዳውም የጎላ መሆኑን ያስረዳሉ። ዳይሬክተሩ፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አገራዊ የተሟላ መረጃ ለማግኘት ዋነኛ መነሻና የቴክኖሎጂ አጠቃላይ አቅምን ለመለካት እንደሚያስችልም ይናገራሉ።
መንግስታዊ ተቋማት በሳይንስና ቴክኖሎጂው ላይ ያወጡት ወጪ በዓይነት ሲመላከት ለውስጥ አገልግሎት የወጪውን 86 በመቶ ሲጠቀሙ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ለሰሩት የዘርፉ ተግባር 12 ነጥብ ሶስት በመቶ የሚሆነውን ወጪ አውጥተዋል። የመንግስት ተቋማት ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና የተሻለ አገልግሎት ማቅረብ እንዲያስችላቸው ተጠቅመውበታል።
አገራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አጠቃላይ ወጪና ተቋማት እየተጠቀሙ ያሉበት ሁኔታን የሚያመላክተው ጥናት የዘርፉ መነቃቃት መልካም ቢሆንም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንደ አገር ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራ አስፈላጊ መሆኑ አመላካች ነውና ትኩረት ይገባዋል እንላለን። አበቃን ቸር ይግጠመን።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 20/2012
ተገኝ ብሩ