ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የምርምር ውጤት ይፋ ሆነ
============================
የአገልግሎት መስጫ ጊዜያቸው ያበቃ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ዳግም ጥቅም እንዲሰጡ የሚያስችል አዲስ ስርዓት ማበልፀጋቸውን የአሜሪካን ተመራሪዎች ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኳን ባትሪዎቹ እንደቀድሞው መኪኖችን ማንቀሳቀስ ባይችሉም ርካሽ የኃይል ማከማቻ ሆነው ለአስር ዓመታት ያህል ማገልገል ይችላሉ፡፡ ይህም የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎች ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚያገኙትን ኃይል ከተጠቃሚው ፍላጎት ጋር አመጣጥኖ ለማሰራጨት ጠቃሚ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካን ብቻ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 የ18.7 ሚሊዮን ጭማሪ በማሳየት ከአጠቃላይ ተሽከርካሪዎች መጠን 7 በመቶውን እንደሚሸፍን ኤዲሰን ፋውንዴሽን ግምቱን አስቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል ከታዳሽ የኢነርጂ ምንጮች የሚገኘውን ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድ አዳዲስ የኢነርጂ ማከማቻ ቴክኖሎጂዎችን ማጎልበት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን፤ ይህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን እንደገና ጥቅም ላይ የሚያውል ስርዓትም የሚወገዱ ቆሻሻዎችን በመቀነስ ጤናማ ምጣኔ-ሐብትን እንደሚገነባ ታምኖበታል፡፡
ይህ በአሜሪካ የኢነርጂ ዲፓርትመንት የኢነርጂ ማከማቻ ፕሮግራም የሚደገፈው ፕሮጀክት በሰሜን ካሮሊና በ15 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ስርዓት ላይ የሙከራ ስራ የተሰራለት መሆኑን ማይክል ስታርኬ የተባለ ተመራማሪ ተናግሯል፡፡ በማይክል እና የስራ ባልደረቦች ዲዛይን የተደረገው ስርዓቱ ተጠቃሚዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት ከኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት የሚያገኙትን ኃይል በመተው ያከማቹትን ኃይል እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህም በነዚህ ሰዓታት ካለው ከፍተኛ የአገልግሎት ታሪፍ እንደታደጋቸው ማይክል ተናግሯል፡፡
ምንጭ፡ Techxplore

የግደል አዋጅ በአሜሪካ
===============
የአሜሪካኗ ፍሎሪዳ ግዛት ዘንዶዎችን በጅምላ የመግደል ስርዓትን ከአንድ ወር በኋላ ታዘጋጃለች፡፡ በዕለቱ የሚሳተፉ አዳኞች ተመልምለው እና ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ውድድሩ የሚገቡ ሲሆን ብዙ ዘንዶዎችን የገደለው አዳኝ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የ2000 ዶላር ሽልማትን ይቀበላል፡፡
ታድያ ዘንዶ ምን ባጠፋ?
ነገሩ እንዲህ ነው፤ የበርማ ዘንዶ ዝርያዎች (Python Bivittatus) በግዛቲቱ ረግረጋማ ስፍራዎች ችግር በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ ታድያ እነዚህ ዘንዶዎች ቀድሞ ለአካባቢው ነዋሪ የነበሩ ሳይሆን ምናልባትም ወደ ሀገሪቱ አስገብተው ያኖሩ ከነበሩ ባለቤቶቻቸው በመጥፋት ወደ ረግረግ ስፍራዎቹ ገብተው በፍጥነት የተራቡ ናቸው፡፡ ዘንዶዎቹ ስፍራው ላይ ቀድሞ የነበሩትን እንስሳት በማጥቃት እና በመብላት በስነ-ምህዳሩ ላይ ከፍተኛ ጥፋትን እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ እንደ ፍሎሪዳ አስተዳደር ከሆነ እስካሁን ድረስ 9,305 ዘንዶዎችን ከስነ ምህዳሩ ማስወገድ የተቻለ ቢሆንም ሴት ዘንዶዎቹ በአንዴ እስከ 100 እንቁላሎችን መጣላቸው ጨርሶ ለማጥፋት አዳጋች አድርጎታል፡፡
በቅርቡ አጥኚዎች በፍሎሪዳ ረግረጎች ኑሮዋቸውን ካደረጉት መካከል የተወሰኑት ከህንድ ዘንዶ ዝርያዎች (Python Molurus) ጋራ የተቀላቀለ ዘረ-መልን ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡ የዘር መዳቀሉ ዘንዶዎቹ ለገበያ በሚወሉበት ወቅት የተከወነ ሊሆን እንደሚችል ሲገመት የተለያየ አየር ንብረትን ለመልመድም ቀላል እንዳረገላቸው ይነገራል፡፡ እስከዛሬ የተያዙት ዘንዶዎች በአማካኝ ከሁለት ሜትር ብዙም ያልበለጠ ርዝመት አላቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2013 አንድ አዳኝ አግኝቶ የገደለው 5.6 ሜትር የሚረዝም ዘንዶ በክብረ ወሰኑ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
የዚህ ዓመት የዘንዶ አደን ከፈረንጆቹ ጥር 10 እስከ 19 ድረስ የሚቆይ ሲሆን አዳኞችም ከስድስት ሺህ ስኩዌር ኪ.ሜ በላይ ስፋት ባለው ስፍራ ላይ ሚከወን ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ሳይንስን በጥበብ የፈታችው ታዳጊ
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
ልጅቷ ቆፍጠን ባለው አኳኋኗ ጠንከር ባለው ንግግሯ ከብዙዎች ልብ ገብታለች፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ በኛ ሀገር ጭምር በተሰሩ የቴሌቪዥን ዘገባዎች ላይ ደጋግመን እንድናያትም ሆኗል፡፡ ግሪታ ተንበርግ መጠሪያ ስሟ የሆነው ይህች የ16 ዓመት ታዳጊ ስዊድናዊት የጥፋት አመፅ (Extinction Rebellion) ከተሰኘው እንቅስቃሴ ጋር በመሆን የብዙዎችን እይታ በመለወጥ ላይ ትገኛለች፤ ምስጋና ትኩረት ሰጥተው ትኩረት እንድንሰጣት ላደረጉን ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ይግባና፡፡ ተፅዕኖዋም ሀገር አቀፍ ምርጫዎችን እስከመወሰንም የደረሰ ነው፡፡ ሌላም ትኩረትን የሰበሰበላት አንድ ለየት ያለ ተግባር አከናውናለች፤ በስፔን ማድሪድ ለተከናወነው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለመሳተፍ ሶስት ሳምንታትን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በጀልባ ተጉዛለች፡፡ በቅርቡ የተባበሩት መንግስትታት ባዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተገኝታ ያደረገችው ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሁሉ የተለየ ነበር፡፡ አምስት መቶ ቃላትን ባልተሻገረ ምጥን ንግግሯ ብዙዎች እንባ እንዲያነቡ አስገድዳቸዋለች፡፡
ታድያ አንዲት ታዳጊ ይህን እንዴት ልታሳካ ቻለች፡፡ መልሱ ጥበብ እና ፈጠራ መሆኑ ይገለፃል፡፡ ብዙዎቻችን ስለ አየር ንብረት ሰምተናል ግን እርሷ ስታወራው ተለየብን፤ ብዙ ተመራማሪዎችም ለዓመታት ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውናል፤ ሆኖም የእርሷ ንግግር በለጠብን፡፡ ይህ ታድያ በሳይንስ ላይ ብቻ ትኩረቱን እየሰጠ ላለው የትምህርት ስርዓታችን ጥያቄን ይዞ መጥቷል፤ ጥበብን ለምን ረሳናት?
እንደ ዘጋርዲያን ትንተና ሳይንስ እና ጥበብ እርስ በእርስ የሚመጋገቡ ናቸው፡፡ የሂሳብ እና ሳይንስ ትምህርት ዘርፎች ለችግሮች መፍትሄ መስጠት ላይ ይሰራሉ፡፡ ታድያ ለችግሮች መፍትሄ ማቀበል ከተለምዷዊው መንገድ በመውጣት በጥበብ መጓዝን ይጠይቃል፡፡ በዓለም የሚከወኑትን ፊልም፣ ሙዚቃ ወዘተ.. የመሳሰሉ የጥበብ ዘርፎች ዳግም ማንሰራራት እና ከየትኛውም ጊዜ በላይ ጎልቶ መውጣትን በምሳሌነት በሚያጣቅሰው ይህ ዘገባ ሳይንስን ከጥበብ አዋህዶ ማስተማር በዓለም ምጣኔ-ሐብት ዕድገትም ሆነ ሁለንተናዊ ብልፅግና የማይተካ ሚናን እንደሚጫወት ይነግረናል፡፡
ለስንብት ከላይ ያነሳነውን ለመሪዎች እንዲደርስ የታለመ ንግግሯን ቀንጭበን እንደሚከተለው እናስነብባችሁ
“በባዶ ቃላቶቻችሁ ህልሜን እና ልጅነቴን ሰርቃችሁኛል፡፡ ሆኖም ከዕድለኞቹ መሃል ነኝ፡፡ ሰዎች እየተሰቃዩ ነው፤ ሰዎች በመሞት ላይ ናቸው፤ ጠቅላላው ስነ-ምህዳራችን በውድመት ላይ ይገኛል፤ በጅምላ ጥፋት ጅማሮ ላይ እንገኛለን፤ እናም የእናተ ንግግር ስለገንዘብ እና ማለቂያ ስለሌለው የምጣኔ-ሐብት ተረት ተረት ብቻ ነው፡፡ እንዴት ደፈራችሁ!!!”

ስልክዎን በመነካካት ሱሰ ተጠምደዋል፤ መፍትሄውን ጀባ እንበልዎ ***********************************
በስልክዎ ማለቂያ አልባ ይዘት (content) ተውጠው ያውቃሉ? በተደጋጋሚስ ስልኮትን ይነካካሉ? አንዳቸውም የእርስዎ ጥፋት አለመሆኑን ብንነግርዎስ፤ ይልቁንም ስልኮችዎ እንዲህ እንዲያደርግዎት ታስበው ነው የተሰሩት፡፡ በኪሶቻችን ውስጥ ስላሉት ስለእነዚህ ኃይለኛ መሣሪያዎች ንድፍ (አሰራር) የበለጠ ባወቅን መጠን በጤንነት፣ ግንኙነታችን እና በወደፊቱ ስኬታችን ላይ እንዴት ተፅእኖ እንደሚፈጥሩ ለመቆጣጠር የበለጠ እንረዳለን።
ስልካችን እንዴት ነው የተነደፈው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?
ስልኮቻችን የተሰሩት የእኛን ስነ-ልቦና በመከተል ስለሆነ ትኩረታችንን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በትክክል ያውቃሉ፡፡ ታድያ ስልኮቻችን ሱስ እንዲያስይዙን ተደርገው ነው የተሰሩት? ስልኮቻችንን መልሰን መቆጣጠር እንችላለን?
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስልኮቻችን እንዴት ጊዜያችንን ለመውሰድ እንደተፈጠሩና እኛም ማድረግ የምንችላቸውን ጥቂት ቀላል እርምጃዎችን እንማራለን፡፡
፩. ማሳወቂያዎች (notifications) እንዳይደርሱን ማድረግ፤
በህይወታችን አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች በስተቀረ ለሌሎቹ ምላሽ አይስጡ፡፡ ሁሉንም ዜናዎች በተከሰቱበት ቅፅበት ማወቅ ምን ያደርግልዎታል? ሁሉንም ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት በቀን የተወሰነ ጊዜ መመደብ ብቻ በቂ ነው፡፡
፪. የስልክዎን ብርሀን ያደብዝዙ፤
በእይታችን ውስጥ የገቡ ቀለም እና ምልክቶች ትኩረት እንድንሰጣቸው ያነሳሱናል፡፡ ስለሆነም ቀለማቱን ከሰወርን አዕምሮአችንን ወደ ስልከላችን የሚማርክ ምንም ነገር አይኖርም፡፡
፫. የመነሻ ገጽዎን (home screen) ያስተካክሉ፤
በዚህ ተግባር ውስጥ ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ጠቃሚ የሆኑትን መተግበሪያዎችን (የቀን መቁጠሪያ፣ አድራሻዎች፣ ካርታ፣ የባንክ አገልግሎት…) ብቻ በማቆየት ሌሎቹን ከመነሻ ገጽዎ ያንሷቸው፡፡ እነዚህ ያነሳችዋቸው የማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች መተግበሪያዎችን በመሰብሰብ በቀላሉ ሊያገኟቸው በማይችሉበት ቦታ ያስቀምጡ፡፡
፬. ስልክዎን በቀላሉ በማይደርሱበት ስፍራ ያስቀምጡ፤
ይህ ቀለል ያለ መፍትሄ ነው፤ ስልክ ከጎንዎ ከሌለ ጊዜዎትን ሊወስድ አይችልም።
፭. ሱስ የሚያስይዙትን እነዚህን ባህሪያትን ለበጎ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎችን ያውርዱ፤
ጤናማ ባህርያት ወይም ልምዶችን እንድናዳብር የሚያግዙን የሚያግዙ ብዙ መተግበሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህን አይነት መተግበሪያዎች ማህበራዊ ትስስርን የሚያበረታቱና ጤናማ አኳን እንዲኖረን የሚያደርጉ ናቸው፡፡
በመጨረሻም ቴክኖሎጂ አይቆጣጠርዎት እርሶ ይቆጣጠሩት እንጂ፤
ቴክኖሎጂ በጣም ጥሩ ነው በመሠረቱ በሕይወታችን ውስጥ የበለጠ እንድንሰራ ለማገዝ የተፈጠረ ነው:: የመጀመሪያው አላማው ጊዜያችንን ሙሉ በሙሉ ማባከን አልነበረም:: ግን የስልኮቻችን አሰራር በእኛ ላይ እንዴት ተጽዕንዎ እንደሚያሳድር ሁላችንም ብዙ እናውቃለን እናም ይህንን አውቀን ወደፊት ለመሄድ እና እድገትን እንዲያመጣልን ቴክኖሎጂን መልሰን ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡
ምንጭ- Ever Widening Circles

ህጻናት እና ስክሪን
“ኸረ ልጄ ዐይኑን ከስልኩ/ከኮምፒተር /ከቴሌቪዥን ላይ አልነቅልም ብሎኛል” እነዚህን እና መሰል ንግግሮች ልጆቻቸው በዲጂታል ገጽ(digital screen) ላይ ብዙ ሰዓታቸውን ማጥፋታቸው ባሳሳባቸው የወላጆች ላይ ይስተዋላል፡፡
ግን ለዚህ ልማድ ተጠያቂ እራሳቸው ወላጆች ወይም አሳዳጊዎቻቸው ቢሆኑስ?
በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ ላንጎን ሜዲካል ሴንተር በአልቢኒ እና በዩኒቨርሲቲው ብሔራዊ የጤና ተቋማት ተመራማሪዎች በተደረገው ጥናት መሠረት ቴሌቪዥን በመመልከት ወይም ኮምፒተርን ወይም ሞባይል በመጠቀም የሕፃናት አማካይ የዕለታዊ ጊዜ በ 12 ወራቸው 53 ደቂቃዎች ሲሆን እድሜቸው 3 አመት ሲሆን ወደ 150 ደቂቃ እና ከዚያ በላይ አድጓል ፡፡ 8 ዓመት ሲሆናቸው በተለይም በቤት ውስጥ ባሉ የሕፃናት መንከባከቢያ የሚቆዩ ወይም ለእናታቸው የመጀመሪያ ልጅ የሆኑ ልጆች ከፍተኛውን (ቴሌቪዥን ፣ ኮምፒተርን እና ሞባይል) የማያ ጊዜ ያስመዘግባሉ ተብሏል፡፡
የጥናቱ ዋና ደራሲና የ NICHD ተመራማሪ ኤዲዊና ይሁንግ (Edwina Yeung, Ph.D) እንደገለጹት “ የጥናት ውጤታችን የሚያሳየው የዲጂታል ገጽ (ቴሌቪዥን ፣ ኮምፒተርን እና ሞባይል) የማየት ልምዶች በልጅነት(early childhood) የሚጀምር መሆኑን ያሳያል” ብለዋል ፡፡ "ይህ ግኝት የሚያመለክተው የሰዎችን የዲጂታል ገጽ (digital screen) የማያ ጊዜን ለመቀነስ የሚረዱ መፍትሐዎችን በልጅነታቸው (early childhood) ቢተዋወቁ የተሻለ ውጤት ሊኖራቸው እንደሚችል ነው” ብለዋል ፡፡
የ NICHD ተመራማሪዎች እና የሥራ ባልደረቦች ከመሀንነት ህክምና በኋላ (infertility treatments) የተፀነሱና ከ 2008 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ በኒው ዮርክ ግዛት የተወለዱ ሕፃናትን እድገታቸውን ለመከታተል የተደረገውን የ Upstate Kids ጥናት መነሻ በማድረግ ወደ 4000 የሚጠጉ እናቶች ልጆቻቸው የ 12 ፣ 18 ፣ 24 ፣ 30 ፣ እና የ 36 ወር ዕድሜ ላይ እያሉ የሚዲያ ልምዶቻቸው በተመለከተ ለጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። እንዲሁም ልጆቹ ዕድሜያቸው 7 እና 8 ዓመት ሲሆናቸው ተመሳሳይ ለሆኑት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡
የጥናቱ ደራሲዎች እድሜያቸው ከ 1 እስከ 3 ዕድሜ በአማካይ ዕለታዊ ገጽ የማያ (screen time) ሰዓታቸው ምን ያህል እንደጨመረ በመመርኮዝ ልጆቹን በሁለት ቡድን ከፍለው ተመልክተዋቸዋል ፡፡ የመጀመሪያው ግሩፕ (73% ከአጠቃላይ) በቀን በ አማካኝ ከ 51 ደቂቃዎች ወደ አንድ ሰዓት እና ለ 47 ደቂቃዎች ያህል አነስተኛ የሆነ ጭማሪ አሳይተዋል። ሁለተኛው ቡድን ከአጠቃላይ 27% ሲሆኑ ፣ በአማካኝ በየቀኑ ከ 37 ደቂቃ ያህል ገጽ የማያ ሰዓት (screen time) በቀን እስከ 4 ሰዓታት ያህል ከፍተኛው ጭማሪ ነበረው ፡፡ ለዚህ ጭማሪ እንደ ምክንያት የ ተገለጹት የወላጅ ዝቅተኛ ትምህርትደረጃዎች ፣ የመጀመሪያ ልጅ መሆን እና ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በትንሹ የመቀነስ ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡
የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ ዕድሜያቸው ከ 18 ወር በታች የሆኑ ሕፃናት ለዲጂታል ሚዲያ መጋለጥ እንደሌለባቸው ፣ ከ 18 እስከ 24 ወር እድሜ ያላቸውን ሕፃናት ደግሞ ለሚዲያ ቀስ በቀስ ዕድልን መስጠት እና ከ 2 እስከ 5 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ገጽ የማያ ጊዜን (screen time) በቀን አንድ ሰዓት እንዲገድቡ ይመክራል ፡፡ አሁን ባለው ጥናት ተመራማሪዎቹ እንዳመለከቱት 87% የሚሆኑት ልጆች ከዚህ ምክረ ሃሳብ በተቃራኒው የበለጠ የእይታ ጊዜ አላቸው ፡፡
በ አገራችንም በአሁን ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማጫወትም ሆነ ምግብ ለማብላት ስልክን መስጠት ቴሌቪዥን መክፈት እና የመሳሰሉትን ዲጂታል ሚዲያዎችን መጠቀም ይስተዋላል ነገር ግን እነዚህ እጻናት እድሜያቸው ከፍ ሲል ረዥም ሰዓት የመጠቀም ልማድ ያዳብራሉ ይህም ለተለያዩ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል፡፡
ምንጭ: science daily

ትናንት ስለመጠቀችው የኢትዮጵያ ሳተላይት 10 አጫጭር መረጃዎችን ልናካፍላችሁ ወደድን
===================
ሙሉ ስም፡ Ethiopia Remote Sensing Satellite (ETRSS-1)
የአገልግሎት ቆይታ፡ 2.6 ዓመት
Resolution: 13ሜ
የዕይታ ስፋት (Swath)፡ >60 ኪ.ሜ
ክብደት 60+10 ኪ.ግ
የመንሳፈፊያ ከፍታ፡ 645.3 ኪ.ሜ
መረጃ የማከማቸት አቅም ≥256 Gbits
በስራው የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቁጥር፡ 20
አጠቃላይ ወጪ፡ 210 ሚሊዮን ብር (ከቻይና 6 ሚሊዮን ዶላር፣ ከመንግስት 20 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከተለያዩ አካላት 10 ሚሊዮን ብር)
የአገልግሎት መስኮች፡ የድንበር ምርመራ፣ የከተማ ፕላን፣ ካርታ ስራ፣ አካባቢ ጥበቃ….

በስራ ባህል እና ማይንድሴት ላይ ያተኮረ ሴሚናር በመካሄድ ላይ ነው
***********************************
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው የሁለት ቀን ሴሚናር ዋና ትኩረቱን የፕሮጀክት ማኔጅመንት አተገባበር፣ የስራ ባህል ፍልስፍናዎች እና የማይንድሴት እሳቤ ላይ በማድረግ በትናንትናው ዕለት ተጀምሯል፡፡ በሴሚናሩ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የተወጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በዋናነት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በሚመሩት የተለያዩ አቅርቦቶች እና የእርስ በእርስ ውይይቶች አማካኘነት መርሃ ግብሩ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
ሴሚናሩ በተከፈተበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በመጠቀም ተቋማትን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል እንደዚህ የሰዎችን አስተሳሰብ የሚቃኝ የስልጠና መርሃግብር መዘጋጀቱ ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም የቴክኖሎጂና የአይሲቲ እሳቤዎችን ለአመራሮች፣ ለሰራተኞች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በስፋት ከማስተዋወቅና ከማስረፅ አንጻር መሰል የማይንድሴት እና ውጤታማ የአሰራር ባህሎችን በትኩረት መዳሰስ አስፈላጊ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በሴሚናሩ የተለያዩ ገለፃዎችን ለተሳተፊው በማድረግ መድረኩን የመሩት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ውጤታማ የስራ ባህልን እና የአስተሳሰብ ለውጥን በትክክል ለማምጣት ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል እንደብዝሃነት፣ የአሰራር ስነ ምግባር፣ አካታችነት እና የምልዓት ወይም Integrity እሳቤዎችን በስፋት ያስረዱ ሲሆን፤ አክለውም በየተቋማቱ ሊኖር የሚገባውን የቢሮክራሲ ሁኔታና የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ከተሞክሯቸው አንፃር በጥልቀት ዳሰዋል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ በተለይም የፕሮጀክት ማኔጅመንት አተገበባር ላይ ባደረጉት ሰፊ ገለፃ የፕሮጀክት እቅድ ከማቅረብ አንስቶ በትግበራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ሪፖርት ምን መምሰል አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንተና ሰተዋል፡፡
በሴሚናር መርሃ ግብሩ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ ያደረጉት እና ተሞክሯቸውን ያካፈሉት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በጀርመን በሚገኘው ሜርሴዲስ ቤንዝ ኩባንያ ውስጥ የፕሮጀክት አስተዳደር ባለሙያ ሲሆኑ፤ ከዚህ በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ጁጂትሱ ፌዴሬሽን የስነ ምግባር ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የምስራቅ አፍሪካ ጁጂትሱ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ያሉ አትዮጵያዊም ናቸው፡፡

የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች የዘር መድሎ ያደርጋሉ ተባለ
*************************************
አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎች ነጭ የቆዳ ቀለም ካላቸው ሰዎች በላይ ሌላ የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች በትክክል ላይለዩ እና ሊያምታቱ እንደሚችሉ የአሜሪካ መንግስት ጥናት ያስታወቀ ሲሆን ይህም በህግ አስፈፃሚ አካላት በስፋት እየተተገበረ ያለውን የዚህን ቴክኖሎጂ ህፀፆች በማጉላት ቴክኖሎጂው ላይ ያሉ ጥርጣሬዎችን ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ጥናቱ የተከናወነባቸው አብዛኞቹ የፊት አሻራ መለያ አልጎሪዝሞች አፍሪካ-አሜሪካውያንን እና የኢሲያዊያን ፊቶች ከነጭ ካውኬዢያን ፊቶች ከ10 እስከ 100 ጊዜ በላይ በስህተት የለዩ ሲሆን ኔቲቭ አሜሪካውያንም በትክክል ካልተለዩት ውስጥ እንደሚገኙ ጥናቱን ያከናወነው የአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ገልጿል፡፡ ጥናቱ በወንጀል ምርመራዎች ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ለመለየት በብዛት የሚገለገለው የአልጎሪዝሙ የአንድ ለብዙ አቻ-መለያ በይበልጥ አፍሪካ-አሜሪካውያን ሴቶችን በትክክል እንዳለየ አሳይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ኩባንያዎች የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂዎቹ ቀደም ሲል የግለሰቦችን ፆታ በአግባቡ የመለየት ችግሮች እንዳሳዩ ሲያመለክቱ እንደነበር የታወሰ ሲሆን የጥናቱ ውጤትም የፊት አቻ-ልየታው በስነ-ህዝብ ልየታ መስክ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት ማረጋገጫ ሆኗል፡፡
የጥናቱ ውጤት በኤርፖርቶች፣ በፖሊስ ዲፓርትመንቶች እና በጠረፍ ፍተሻዎች እየተለመደ የመጣውን የዚህ የፊት አሻራ መለያ ቴክኖሎጂ አስመልክቶ በፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም በወንጀል ፍትህ አክቲቪስቶች ዘንድ ሲደረጉ የነበሩት የማንቂያ ደውል ማስጠንቀቂያዎች ላይ ተጨማሪ ማስረጃ ሆኗል፡፡ የመንግስት ሳይንቲስቶችም በቴክኖሎጂዎቹ ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች እየተጋሩ እንደሆነ በአሜሪካ የሲቪል ነፃነቶች ማህበር ከፍተኛ የፖሊሲ አናሊስት የሆኑት ጄይ ስታንሊ ተናግረዋል፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ አንድ የተሳሳተ የፊት-አቻ ሲያጋጥም በኤርፖርቶች የሰዎችን በረራ ሊያስተጓጉል፣ የተራዘመ ቃለመጠይቆችን ሊያስከትል እና በተጠርጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተትን ሊያመጣ ከመቻሉም በላይ፤ ለጠንካራ የፖሊሲ ምርመራዎች ሰዎች እንዲዳረጉ፣ በስህተት ወደእስር እንዲሄዱ እና ከዛም ለከፉ እርምጃዎች ሊዳርግ እንደሚችል አክለው ተናግረዋል፡፡
በዚህ በአሜሪካ ብሔራዊ የስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት የተከናወነው ጥናት ወደ 100 የሚጠጉ የቴክኖሎጂውን አቅራቢዎች እንደ ኢንቴል፣ ማይክሮሶፍት፣ ቶሺባን እንዲሁም ታዋቂ የቻይና ኩባንያዎች የተካተቱ ቢሆንም የፊት-መለያ ሶፍትዌሮችን ለፖሊስ ዲፓርትመንቶች በብዛት የሚያቀርበው የአማዞን ኩባንያ ግን በጥናቱ አልተሳተፈም፡፡
በጣት የሚቆጠሩ የአሜሪካን ከተሞች እንደ ሳን ፍራንሲስኮ፣ ኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ የመሳሰሉት የፊት-አሻራ መለያ እድገትን በቴክኖሎጂው ላይ የተለያዩ እገዳዎችን በማድረግ ሊቆጣጠሩት እየሞከሩ የሚገኙ ሲሆን እንደ ፖርትላንድ እና ኦሪጎን የመሳሰሉ ከተሞች ደግሞ ከዚያ ባለፈ የፊት-አሻራ መለያዎችን ሙሉ በሙሉ ከክልል መንግስት እና ከግል ኩባንያዎች የማስቀረት ሀሳብ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካን የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት የአሜሪካን ዜጎች እና ግሪን ካርድ ያላቸውን ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸውና ከመውጣታቸው በፊት የፊት-አሻራ መለያ ምርመራውን እንዲደረግ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን የሚዲያን ሪፖርቶች እንዲሁም ጠንካራ ህዝባዊ ተቃዎሞዎችን ተከትሎ እቅዱን ገተውታል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን እና ሮይተርስ

TECHIN weekly seminar
*********************
You are invited to join us today @TECHINhall
Issues for this week:
A Multistage Data Mining For Crime Prevention: The Case of Jimma Town Police Office
Dropout among Primary School Students: Reason, Experience and Mitigating Factors
Presenters:
Bikila Mezgebu and Biniam Wendmu
#TECHINtalk
#TECHIN #weeklyseminar