ሐሴትን ከበጎነት !!!
*=*=*=*=*=*=*
የሰው ልጅ በምድር ሲመላለስ ታላቅ የመንፈስ እርካታን ከሚያጎናፅፉት ተግባራት መካከል አንዱ ለተቸገረ መድህን፤ ለወገንም አለኝታ መሆን ሲችል እንደሆነ ብዙዎቻችንን ያስማማል፡፡ ከነዚህ በጎ ተግባራት መካከልም ብዙዎችን ከህልፈት የሚታደገው የደም ልገሳ ተግባር ይጠቀሳል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በ፳፻፲፪ የመጀመሪያቸው የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይም የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ፲፰ የቤተሰብ አባላቶቻችን ተገኝተው ደማቸውን ለግሰዋል፡፡ ታድያ ለበጎ አድራጎት ተግባራት እንግዳ ያልሆኑት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች መሰል የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ሲያከናውኑ የዛሬው ለአስራ አንደኛ ጊዜ ነው፡፡
በቅርቡ ይህን መሰል የደም ልገሳዎች በሀገራችን ኢትዮጵያም ቀስ በቀስ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት አጋማሽ ሀገር ቀን ቆጥሮ ቀጠሮ ይዞ ካከናወነው የደም ልገሳ ዘመቻ በላይም ለዚህ ምስክር የሚሆነን አይገኝም፡፡ በዕለቱም በአርባ የሀገራችን ከተሞች ከአስራ አራት ሺህ በላይ ዜጎች ታላቁን ስጦታ ከአካላቸው ቀንሰው ለወገን አካፍለዋል፡፡

የዲጂታል ፋይናንስን ለማሳደግ የሁሉም ትብብር ወሳኝ አንደሚሆን ተገለፀ
***************************************
‘‘Digitizing Finance: Mobile Payment’’ በሚል የተሰናዳው ይህ የአንድ ቀን ወርክሾፕ አንደሃገር በዲጂታል ኢኮኖሚው ላይ ያለንበትን ደረጃ፤ ያሉ ችግሮች እና የሚታዩ መልካም እድሎች በማንሳት እንዴት እንምራው ወይም እናሳድገው በሚለው አጀንዳ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡
በወርክሾፑ የተለያዩ የባንክ ተቋማት፣ የዩኒቨርስቲ ሙሁራን እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሰማሩ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ በባለሙያዎች በቀረቡ ሰፊ ትንተናዎች እና የፓናል ውይይቶች ሰፊ ጊዜ በመስጠት ተካሂዷል፡፡ በመርሃግብሩ ጅማሬ ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የመድረኩ መዘጋጀት በዘርፉ ለሚንቀሳቀሱ ባለሙያዎችና ሌሎች የንግድ ተቋማት የሚፈጥረውን ወርቃማ እድል አንስተው የዲጂታል ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ የሁሉም ትብብር እጅግ መሰረታዊ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ የኬኒያን የዲጂታል ፋይናንስ እንቅስቀሴ እንደተሞክሮ በመጥቀስ ኢትዮጵያም ከዚህ ትልቅ ትምህርት መውሰድ እንደሚገባት እና ኢኒስቲትዩቱም እንዲህ ያሉ የውውይት መድረኮችን በማዘጋጀት የፕሮጀክት ሃሳቦች የሚያድጉበትንና የግንዛቤ ስራዎች የሚስፋፉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ወርክሾፕ ሰፊ ትንተና ካቀረቡ ባለሙያዎች መካከል ከደቡብ አፍሪካ የመጡት ወ/ሪት አንቶኒያ ኢሰር አንዷ ሲሆኑ የዲጂታል ፋይናንስና ቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ እየተራመዱ ያለበትን ሁኔታ እና ሃገራት በዚህ ዘርፍ ውጤት ለማምጣት እየሄዱበት ያለውን ርቀት በጥልቅት አስረድተዋል፡፡ ከሳቸው በማስቀጠል መድረኩን የተረከቡት የቴኪኢን የቀድሞ የስራ ባልደረባ አቶ ዮዳሂ ዘሚካኤል ነባሩ የፋይናንስ ስርዓት በፖሊሲና በመዋቅር ደረጃ በዲጂታል ዘርፉ ላይ የሚኖረውን ጫና በማስረዳት፤ መንግስት እየሄደባቸው ያሉትን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አብራርተዋል፡፡ አቶ ዮዳሂ በተለይም በመሰራት ላይ የሚገኘውን የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ በምሳሌ በማንሳት ሀገሪቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ሃብት ለመፍጠር የሚያስችል ጥሩ መሰራት እንደሚኖራት ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በማስቀጠል መድረኩን የያዙት የቤልካሽ ቴክኖሎጂ ዋና መስራች አቶ አብርሃም ጉልላት ከድርጅታቸው ተሞክሮ በመነሳት በዲጂታል ፋይናንስ እና የሞባይል ክፍያ ዙሪያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንና መልካም እድሎችን አብራርተዋል፡፡ የውርክሾፑ መርሃ ግብር ከእነዚህ አቅርቦቶች በተጨማሪ እጅግ ፍሬያማ በሆኑ የፓናል ወይይቶች የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊ በኩልም ገንቢ አስተያየቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ተንፀባርቀውበታል፡፡

የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማ
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና ገቢ ማመንጨት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የተሰሩ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ከሰራተኛው ዘንድ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በዕለቱ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች ይሆናል ይበጃል ያሏቸውን አስራ ስድስት(16)የፕሮጀክት ሀሳቦች ወደ መድረክ ያመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የእንቦጭን አረምን ወደ ገቢ ምንጭነት የሚለውጥ እና በአዲስ አበባ ላለው የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሄ የሚሰጡ ስርዓቶች ይገኙበታል፡፡
ቀሪ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች በሚቀጥሉት ቀናት ለውይይት እንደሚቀርቡ ሲጠበቅ ከነዚህ መካከልም የተመረጡት ስራ ላይ የሚውሉ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በጋራ እየሰሩ ነው
*********************************
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ ትኩረት ሰተው እየሰሩ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ራፋዬል ሞራቭ አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደሩ ሰሞኑን ከሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እና እስራኤል በአቮካዶ ምርት ለ13 አመታት ሲሰሩ እንደቆዩ እና በቅርብ ጊዜ ደግሞ የኤክስፖርት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ የአቮካዶ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለአቮካዶ ምርት እጅግ የተስማማ የአየር ፀባይ ያላት ከመሆኑ አኳያ ካለፉት አራት አመታት ጀምሮ የተሻሉ የአመራረት ስልቶችን በተለያዩ አካባቢዎች ለመተግበር መሞከሩን የጠቀሱት አምባሳደሩ በተካሄዱ አዋጭ መርሃግብሮችም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኘውን አርሶ አደር የተሻለ የአመራረት ዘዴን በማስለመድ ወደ መካከለኛ ደረጃ እንዲመጣ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ግብርናው ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተከተለ አዳዲስ መንገዶችን የሚሻ በመሆኑ በሃገራቸው የሚተገበሩትን ልዩ ልዩ የአመራረት ዘዴዎች በቴክኒካልም ይሁን በሌሎች መንገዶች ለማገዝ የመንግስታቸው ሙሉ ፍላጎት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ራፋዬል በተለይም ሃገራቸው አንደቅድ ይዛ እየተገበረች ያለውን፤ የስንዴን ምርት ከከፍተኛ ቦታዎች በተጨማሪ በዝቅተኛ ቦታዎች የማምረት ፕሮግራም በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሰፊው እየተሰራበት እንደሚገኝ የተናገሩ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ ሃገራት የንግድ ልውውጥ ላይ ተለዋጭ የምርት ውጤቶችን ከማምጣቱም ባለፈ ተጨማሪ እሴቶችን እንደሚያክል የሚጠበቅ ነው፡፡
መርሃግብሩ ዝቅተኛ በሆነው የእስራኤል መልካምድር የተሻሻለ የመስኖ ስርዓትን በመተግበር እጅግ ስኬታማ ከሆኑ የግብርና ልማት አይነቶች አንዱ ከመሆኑ አኳያ ለኢትዮጵያም የተሻለ ለውጥን ሊያመጣ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
The Ethiopian Herald

ድንበር አልባው የገንዘብ እንቅስቃሴና #የብሎክ - #ቼን ቴክኖሎጂ
****************************
የብሎክቼን ቴክኖሎጂ የማይለዋወጥ የዲጂታል መዝገብ በመሆኑና አብዛኛውን ጊዜ ግብይቶችን በዳታቤዝ መዝግቦ ከማስቀመጡ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰዎች ከፋይናንስ አሰራር ጋር ብቻ ሲያገናኙት ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ የብሎክቼን ቴክኖሎጂ ለፈይናንስ ጉዳይ በሚሰጠው ግልጋሎት ልክ ለተለያዩ ዘርፎች እና የኢንዱስተሪ አይነቶች ትልቅ አበርክቶት አንደሚኖረው ይታመናል፡፡ በተለይም በአንድ ማእከላዊ ሰርቨር ላይ ብቻ ይሰራ የነበረውን አሰራር ኢ-ማእከላዊ በማድረግ በኔትወርኩ ውስጥ ያለ ማንኛውም አካል እያንዳንዱን የሚደረግ እንቅስቃሴ በእጁ ላይ እንዲያገኝ ለማድረግ በመቻሉ ግለሰቦች፣ ኩባንያዎች አንዲሁም መንግስትን ጨምሮ በአሰራራቸው ላይ ደህንነት፣ ግለፀኝነት እና ፍጥነትን አንዲላበሱ ያስችላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ እነዚህ የተመረጡ የስራ ዘርፎች ከብሎክቼን ቴክኖሎጂ ወደፊት እንዴት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ማየት ይቻላል፡፡
ባንክና ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች
በብዙ ትሪሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮች የሚንቀሳቀስበት የድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ኢንዱስትሪ የባንኮችን የዕለት ተዕለት ፈጣን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ታዲያ አብዛኛውን አለም አቀፍ የገንዘብ ክፍያ እና እንቅስቃሴ በአግባቡ ለማሳለጥና ለማዘዋወር እንደ SWIFT ያለ የሶስተኛ ወገን አጋዥ አካል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ SWIFT እ.አ.አ በ1970 የተመሰረተ መቀመጫን በቤልጂየም ያደረገ አለምአቀፍ የገንዝብ አስተላላፊ ድርጅት ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ በተጠቃሚዎቹ ላይ በሚጥለው ውድ ክፍያና አዝጋሚ አሰራር በብዙዎች ይታማል፡፡ በመሆኑም በSWIFT እና በሌሎች የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ተመስርቶ የሚከናወነው የባንኮች የድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ጊዜ ለጥገኝነት የተጋለጠ ነው በሚል ይነሳል፡፡ በዚህ ረገድ ባንኮች የሶስተኛ ወገን አጋዥነት ሳያስፈልጋቸው አቻ ለአቻ (peer-to-peer) በሆነ መልኩ ቢዝነሳቸውን ለማከናወን አንዲስችላቸው የብሎክቼን ቴክኖሎጂ ትልቅ እድል ይፈጥራል፡፡ ቴከኖሎጂው ከዚህ በተጨማሪ ለግብይቱ መረጋገጥ ረዥም ጊዜ የማይፈጅ በመሆኑ እና በዝቅተኛ ወጪ ሊከወን በመቻሉ ቀድሞ ቀናቶችን ይወስድ ለነበረው አሰራር መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡፡ በአሁን ወቅት ከመቶ በላይ የሆኑ የተለያዩ ባንኮች “Ripple” በተሰኘው የብሎክቼን አይነት ላይ ይህን የድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ እንቅስቃሴ ለማከናወን እንዲስችላቸው ጠለቅ ያለ ምርምርና ሙኩራ እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ውስጥ ወደ ትግበራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሃይል አቅርቦት
ቀደም ባሉት ጊዚያት የሃይል ስርጭትም ሆነ አቅርቦት የሚተዳደረው ከአንድ ማዕከላዊ ምንጭ በሚዘረጋ አሰራር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም በበለፀጉ ሃገራት የታዳሽ የሃይል ምንጮችን በግለሰብ ደረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል “microgrids” የተሰኘ አዲስ የግሪድ ስርዓት በተግበራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የግሪድ ስርዓት ሶላር ፓኔል እና መሰል የሃይል አማራጭ ያላቸውን ሰዎች፤ ተገልግለው ከተረፋቸው የሃይል ክምችት ላይ ለሌላ አካል የሚሸጡበት አሰራር ሲሆን ይህም በሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት ወይም አከፋፋይነት ይከናወናል፡፡ በዚህ አሰራር ሁሉም የሃይል ባለቤቶች ለመሸጥ የሚፈልጉትን የሃይል ክምችት ለሌላ አካል ለማስተላለፍ እንዲችሉ የግድ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት መኖሩ የሚሸጡበትን ዋጋ ከማውረዱ በተጨማሪ በአከፋፋይነት ለሚሳተፉ አካለት እጅግ ከፍተኛ ትርፍ እንዲያጋብሱ ያስችላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በተመሳሳይ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ እንደ ስማርት ግሪድ ያሉ ሌሎች የሃይል አቅርቦት እና ማከፋፈያ አማረጮች ተመሳሳይ የሆነ ችግር የሚይስተዋልባቸው ሲሆን ይህን ክፍተት ለመሙላት እንዲስችላቸው እንደ ብሎክቼን ያለ ከሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የፀዳ አሰራር ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
የውልና የሰነድ ማረጋገጫ
የብሎክቼን ቴክኖሎጂ እንደ “smart contract” ያለ የሰነድ ማረጋገጫ እና አያያዝ ስርዓት የሚዘረጋ ሲሆን ይህም ጥብቅ የሆነ ስምምነትን የሚፈልግ የንብረት፣ የግዥ፣ የውል እንዲሁም የተለያየ አገልግሎት ልውውጥን ማካሄድ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ የህይወት መድህን ተቋም የደንበኛውን የህይወት ዋስትና ክፍያ ለሟች ቤተሰብ መላክ ቢፈለግ ክፍያውን ከመፈፀሙ በፊት ከተመረጠ የዶክተር ቢሮ የሟቹን የሞት ሰርተፍኬት የሚያረጋግጥ እና ዲጂታል ፊርማ የሰፈረበት ማስረጃ በብሎክቼይኑ ውስጥ በሶፍትዌር ኮድ አማካኝነት አውቶማቲካሊ ማረጋገጫ ማግኘት ሲችል ክፍያው ለሟች ቤተሰቦች ወዲያው መፈፀም የሚችልበት አሰራር ሊካሄድ ይችላል፡፡ ወይንም ደግሞ አንድ የአየር በረራ ጉዞ ቢዘገይ ወይንም ቢሰረዝ አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ቃል የገባውን የጉዞ ዋስትና ክፍያ አውቶማቲካሊ በ “smart contract” አማካኝነት ያለሰው ጣልቃ ገብነት ማከናወን ይቻላል፡፡
ለእርዳታ መላላኪያ
የብሎክቼን ቴክኖሎጂ ከዚህ በተለየ እርዳታ ለሚፈልጉ የዓለማችን ህዝቦች ትልቅ ጥቅም ሊኖረው ይችላል፡፡ “theguardian” የተሰኘው እውቁ የዜና ምንጭ በ2018 እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ለተለያዩ ታዳጊ ሃገራት በእርዳታ መልክ ከሚልከው አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው ከማጭበርበር እና ከሙስና ጋር ተያይዞ ለተረጂዎች እንደማይደርስ አስታውቋል፡፡ ይህ ደግሞ በአንድም በሌላ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የሚያመጣው መዘዝ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የማያስፈልገው እና አቻ ለአቻ በሆነ መንገድ የሚፈፀመው የብሎክቼን ቴክኖሎጂ ትልቅ ግልጋሎት ይኖረዋል፡፡ በተለይም በክሪፕቶከረንሲ አሰራር በመታገዝ ለተረጂዎች የተፈለገውን የገንዘብ ልክ ለማስተላለፍ የሚያስችል ስርዓት ቴክኖሎጂው በመዘርጋቱ ያለምንም በክነትና ሽርፍራፊ የታቀደውን እርዳታ ማከናወን ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ተራድኦ ድርጅት (Unicef) በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለተጎዱ ብዛት ያላቸው ህፃናት መቋቋሚያ እንዲሆን የሚሰጠውን እርዳታ “Ethereum” በተሰኘው የክሪፕቶከረንሲ አይነት ለመላክ ማቀዱ በብዙዎች ዘንድ እንደመልካም ጅምር ተወስዷል፡፡
ቴክ ሳይንስ ቅፅ ፻፶

የሌላው ዓለም ፍጡራንን አጥማጁ ቴሌስኮፕ
============================
በምዕፃረ ቃሉ ፋስት (Five-hundred-meter Aperture Spherical Telescope) የሚል ስያሜን ያገኘው ግዙፉ የቻይና ቴሌስኮፕ ከ2016 አንስቶ ሲያከናውን የቆየውን የሙከራ ሂደት አጠናቋል፡፡ ቻይናዊያን የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎችም በዓለም በግዝፈቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ይህን ቴሌስኮፕ የሌላው ዓለም ፍጡራንን ከማደን አንስቶ ብዙ ተግባራት ለማከናወን እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በእስካሁኑ የሙከራ ቆይታውም ግዙፉ ቴሌስኮፕ ቁጥራቸው 99 የሆኑና ፑልሳር በሚል ስያሜ የሚጠሩት በፍጥነት የሚዞሩ ከዋክብት መመዝገብ የቻለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 30 ያህሉ በላቀ ፍጥነት የሚሽከረከሩ ፑልሳሮች መሆናቸው ተዘግቧል፡፡
በፋስት ውስጥ የሳይንቲፊክ ኦብዘርቬሽን እና ዳታ ክፍል ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ እንዳሉት ዙሁ ሚንግ ከሆነ እስካሁን “ከሌላው ዓለም ፍጡራን የሚለቀቅን ሲግናል ለማግኘት በሚደረገው በዚህ ጥረት ውስጥ ከሰዎች አሊያም ከነዚህ ረቂቅ ፍጡራን የተነሱ ሊሆኑ የሚችሉ ልዩ ልዩ ሲግናሎች በቴሌስኮፑ አማካኝነት ቢገኝም 99 በመቶው የተለያዩ ድምፆች ሆነው ተገኝተዋል፡፡” ታድያ ከነዚህ ድምፆች ውስጥ ሲግናሎችን ለማግኘት ትልቅ ጥረት እና ጊዜ እንደሚጠይቅ የዳይሬክተሩ ንግግር ያሳያል፡፡
ይህ በደቡባዊ ቻይና ጉዌጆ ግዛት ውስጥ የተገነባው ግዙፍ ቴሌስኮፕ በሁለተኝነት ከሚከተለው ቴሌስኮፕ ነገሮችን በመገንዘብ ረገድ ሶስት እጥፍ የላቀ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ታድያ እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በሚደረግ ጥረት ብቻ የዕይታ ብቃቱ በ50 በመቶ እንደሚያድ እና ይበልጡን አስተማማኝ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ space.com

በቁፋሮ ስለተገኘችው ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ከተማ
=======================
የአራተኛው ክፍለ ዘመን የክርስትና ቅርሶችን በውስጧ እንደያዘች የተነገረላት ጥንታዊ ከተማ በኢትዮጵያ መገኘቱ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት በሚታተመው የአንቲኩኢቲ ጆርናል ይፋ ተደርጓል፡፡ ከክርስትና በተጨማሪ የሌሎች ሐይማኖት ቅርሶችንም እነደያዘች የተገመተችው ይህች ከተማ ታድያ ለጥንታዊው የአክሱም ስልጣኔ የተለየ ገፅታንም ሰጥታለች፡፡ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቤተ ሰማዕቲ በመባል የምትጠራው ከተማይቱ ከአራተኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ የተነገረለትና ባዛሊካ ለሚሰኘው የሮማዊያን የኪነ ህንፃ ስልት በቀረበ መልኩ የተገነባ ግዙፍ ቤተ-ክርስቲያን ይዛለች፡፡
ምንም እንኳን ዘመነ አክሱም በኢትዮጵያና አካባቢው የስልጣኔ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ድርሻ ከመውሰድም ባሻገር ከጊዜው ታላላቅ ስልጣኔዎች አንዷ ብትሆንም ከሌሎች አንፃር በአለም ህዝብ ዘንድ ያለው ዕውቅና አነስተኛ ነው፡፡ ይህን ለመለወጥ እየሰሩ መሆኑን ይህን ቁፋሮን ያደረገው የአኪዎሎጂስቶች ቡድን መሪ ሚካኤል ሀሮወር ገልጿል፡፡
ስፍራው በተለያዩ ምክንያቶች በሚገባው ልክ ያልተጠና መሆኑ ይነገርለታል፡፡ በጀርመኖች የተመራ የምርምር ስራ በአክሱም እና አካባቢው እ.አ.አ በ1906 መከናወን የተገመረ ቢሆንም በአካባቢው እና ሲሻገርም በኢትዮጵያ የነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጥናቶችን ለማድረግ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱ ይጠቀሳል፡፡
የምርምር ቡድኑ ጥንታዊያኑ ህንፃዎችን ወደ ውስጥ ቀብሮ የነበረውን ጠል የተባለን የአፈር ቁልል በማሰስ ነበር ከተማይቱን ያገኟት፡፡ በውጤቱ ቤተ ሰማዕቲ ውስጥ ከቅድመ አክሱም 750 እስከ 650 ዓ.ዓ አንስቶ እስከ 650 ዓ.ም ባሉት አንድ ሺህ ዓመታት በላይ ሰው የኖረባት እንደሆነችና ኋላም ባልታወቀ ምክንያት ልታሽቆለቁል መቻሏ ተረጋግጧል፡፡ ይህም ማለት ከተማይቱ ከቅድመ ክርስትና ጊዜያትም ጀምሮ ክርስትና እስከገባበትና እስልምናም በአካባቢው ሊገባ በተቃረበበት ወቅት ድረስ ህይወት ነበራት፡፡ የተገኘው ቤተ ክርስቲያንም አክሱም ወደ ክርስትና በመሸጋገሪያዋ ወቅት ላይ የተገነባ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ያስረዳሉ፡፡
እንደ አርኪዮሎጂስቶቹ ከሆነ መሰል በሮማዊ ስልት የገነቡ ቤተ ክርስቲያኖች መገኘት ቢችሉም ዕደሜያቸው በጣም የራቀ ከመሆኑም ባሻገር በውስጣቸው በዙም ቅርስ እና መረጃ የሌላቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ይህ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊ ቅርሶች፣ የነሀስ ሳንቲሞች፣ ቅርፃ ቅርፆች እንዲሁም ከውጪ የመጣውን ወይን አሊያም የወይራ ዘይትን ለማስቀመጥ ያገለገሉ እንስራዎች የያዘ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህም ቤተ-ክርስቲያኑን ይጠቀሙ የነበሩ ሰዎች ከባህር ማዶ ጥንታዊያን ስልጣኔዎች እና የንግድ መስመሮች የተሳሰሩ እንዲሁም በዚህ ሳቢያ ለቅንጦት ቁሳቁሶች ተደራሽነት ያላቸው መሆኑን እንደሚያሳብቅ ሀሮውል ይናገራል፡፡ በውስጡ የተገኙት የነሀስ ሳንቲሞችም ለቤተ ክርስቲያኑ ዕድሜ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡ ቀዳሚዎቹ ሳንቲሞቹ ንጉስ ኢዛና በደቡባዊ አረቢያው አማልክት አልማቃህ ምልክት በሆነው የግማሽ ጨረቃ ሲያሸበርቁ ንጉስ ኢዛና ወደ ክርስትና መለወጡን ተከትለው የመጡት ሳንቲሞች ግን በመስቀል ቅርፅ የተዋቡ ናቸው፡፡
ሌላው በቤተ ክርስትያኑ የተገኘ አስደናቂ ቅርስ ምናልባትም በቀሳውስቱ አንገት ይንጠለጠል አንደነበረ የተገመተ ቅዱስ የሚል የግዕዝ ፅሁፍ ያለበት እና በመስቀል ያጌጠ ቅርፅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅድመ ክርስትና ወቅት እንደተቀረፀ የተገመተ የበሬና ላም ጭንቅላት አምሳያ እንዲሁም በወርቅ እና የከበረ ድንጋይ ግብዓትነት የተሰራ ቀለበት ይገኙበታል፡፡
ሃሮወር አካባቢው ባለው የመሬት አቀማመጥ እና ታሪካዊነትም መሳባቸውን ገልፆ እርሱ እና ቡድኑ ለዳግም ቁፋሮ ወደ ቤተ-ሰማዕቲ ለማምራት እንዳቀዱ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፡ Live Science ውድ አንባቢያን ሙሉ የጥናት ውጤቱን ለማግኘት ከፈለጉ በዚህ ሊንክ አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ https://www.cambridge.org/core/services/aop-cambridge-core/content/view/643FA872A5B2F9B5E0E765D850C4A526/S0003598X1900084Xa.pdf/beta_samati_discovery_and_excavation_of_an_aksumite_town.pdf

ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የምርምር ውጤት ይፋ ሆነ
============================
የአገልግሎት መስጫ ጊዜያቸው ያበቃ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ዳግም ጥቅም እንዲሰጡ የሚያስችል አዲስ ስርዓት ማበልፀጋቸውን የአሜሪካን ተመራሪዎች ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኳን ባትሪዎቹ እንደቀድሞው መኪኖችን ማንቀሳቀስ ባይችሉም ርካሽ የኃይል ማከማቻ ሆነው ለአስር ዓመታት ያህል ማገልገል ይችላሉ፡፡ ይህም የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎች ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚያገኙትን ኃይል ከተጠቃሚው ፍላጎት ጋር አመጣጥኖ ለማሰራጨት ጠቃሚ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካን ብቻ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 የ18.7 ሚሊዮን ጭማሪ በማሳየት ከአጠቃላይ ተሽከርካሪዎች መጠን 7 በመቶውን እንደሚሸፍን ኤዲሰን ፋውንዴሽን ግምቱን አስቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል ከታዳሽ የኢነርጂ ምንጮች የሚገኘውን ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድ አዳዲስ የኢነርጂ ማከማቻ ቴክኖሎጂዎችን ማጎልበት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን፤ ይህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን እንደገና ጥቅም ላይ የሚያውል ስርዓትም የሚወገዱ ቆሻሻዎችን በመቀነስ ጤናማ ምጣኔ-ሐብትን እንደሚገነባ ታምኖበታል፡፡
ይህ በአሜሪካ የኢነርጂ ዲፓርትመንት የኢነርጂ ማከማቻ ፕሮግራም የሚደገፈው ፕሮጀክት በሰሜን ካሮሊና በ15 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ስርዓት ላይ የሙከራ ስራ የተሰራለት መሆኑን ማይክል ስታርኬ የተባለ ተመራማሪ ተናግሯል፡፡ በማይክል እና የስራ ባልደረቦች ዲዛይን የተደረገው ስርዓቱ ተጠቃሚዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት ከኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት የሚያገኙትን ኃይል በመተው ያከማቹትን ኃይል እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህም በነዚህ ሰዓታት ካለው ከፍተኛ የአገልግሎት ታሪፍ እንደታደጋቸው ማይክል ተናግሯል፡፡
ምንጭ፡ Techxplore