TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከIBA ኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
****
ጀማሪ ፈጣሪ እና ቴክኖሎጂስቶችን በማብቃት ላይ የሚሰራው IBA ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የፊርማ ስነ ስርዓት አከሂደዋል፡፡ ስምምነቱን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የIBA ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አያሌው ግዛው የተፈራረሙ ሲሆን፤ በወናነትም በፈጠራ ስራ፣ ጀማሪ የንግድ ዘርፎች እና የስታር ታፕ ፕሮግራሞች በሚበለፅጉበት ሁኔታ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡
በአርባ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የኢኖቬሽን ማዕከላትን በማቋቋምና ያሉትንም በመጠናከር ዙሪያ እየሰራ የሚገኘው IBA ኢትዮጵያ በዚህ ስምምነትም ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ንግድ የሚገቡበትን፣ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ መዕከላት የሚስፋፉበትን እና በዘርፉ ላይ ያተኮሩ ወርክሾፕና ስልጠናዎች የሚደረጉበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንደሚሰሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
IBA ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂስቶች የሚሰሩ ልዩ ልዩ ፈጠራዎችን ወደ ገንዘብ ምንጭነት መቀየርን በዋና ግብነት ይዞ በሃገራችን እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን መቀመጫውን ካደረገበት ሃገረ ኖርዌይ ደግሞ በስፋት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ ከሰራቸው ስራዎቹ ውስጥም በኖርዌይ ያሉትን ስደተኞች በስራ ፈጠራ ማብቃት ይጠቀሳል፡፡ ወደ ሀገራችን ከመጣበትም ጊዜ አንስቶ ከተለያዩ አካላት ጋራ ግንኙነትን በመመስረተ የትምህርት ዘርፉን ዲጂታላይዝ በማድረግ እንዲሁም African innovation week የተሰኘውን የፈጠራና ቴክኖሎጂ መድረክ በማዘጋጀት ረገድ የሰራቸው ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከሜቴክ የተረከበውን የኳሊቲ ኢንጅነሪንግ ማዕከል በሙሉ አቅሙ ስራ ለማስጀመር ከምሁራን ጋር መከረ
========================
ምክክሩ የተካሄደው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትት የተውጣጡ ምሁራንና ተመራማሪዎች የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተረከበውን የኳሊቲ ኢንጅነሪንግ ማዕከል ባስጎበኘበት ወቅት ነበር፡፡
የጋዝና ሌሎች ፈሳሾችን ፍሰት ከሚለካ አንስቶ እስከ 3D ማሽን ግብዓቶች ድረስ ካሊብሬሽን እና ቴስቲንግ የሚያከናውኑ ማሽኖች የተጎበኙ ሲሆን ለእያንዳንዳቸው እስከ 40 ሚሊዮን ብር ወጪ ወጥቶባቸው ወደ ሀገር ቢገቡም ላለፉት አምስት ዓመታት ጥቅም ላይ ሳይውሉ ቆይተዋል፡፡
የማሽኖቹ ሐገራዊ ጥቅም የላቀ እንደሆነ ለመምህራን እና ተመራማሪዎቹ የገለፁት አቶ ሳንዶካን እነዚህን ወደ ስራ በማስገባት ረገድ ትልቅ ድርሻ ሊወስዱ እነደሚገባ ለምሁራኑ አሳስበዋል፡፡ ምሁራኑም በበኩላቸው ችገሩን ለመፍታተ የሚያስችል ምክረ ሐሳብ ይዘው ለመምጣት ቃል ገብተዋል፡፡
ስልሳ ስምንት ሺህ ካሬ ላይ ለምርምር ስራ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባው ማዕከሉ በውስጡ የኤሌክትሪካል ካሊብሬሽን እና ቴስቲንግ፣ የጂኦሜትሪካል ካሊብሬሽን እና ቴስቲንግ እንዲሁም የተርማል ካሊብሬሽን እና ቴስቲንግ ቤተ-ሙከራዎችን ይዟል፡፡
Crypto Currency
*****************************************
*****************
በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ግንኙነቶችን ሚስጥራዊ ለማድረግ ታስቦ የተፈጠረው ስነ-መሰውር (Cryptography) (ክሪፕቶግራፊ) የተሰኘው የመግባቢያ ቃል ኡሁን ባለንበት የዲጂታል ዓለም የሂሳብ ንድፈ ሃሳቦችን እና የኮምፒዊተር ሳይንስ መሰረታዊ ባህሪያትን ተላብሶ ግንኙነትን፣ መረጃን እና የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርን በደህንነት ቀጠና ውስጥ ለማስገባት የሚውል ልዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅንሰ ሃሳብ ሁኗል፡፡
ይህም ኢንተርኔትን ተጠቅሞ ተነባቢ መረጃዎችን (legible information) ወደ ማይነበቡና ሊደረስባቸው የማይችል የሚስጥር ኮዶች (uncrackable code) በመቀየር ዲጂታል ግብይቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ታዲያ cryptocurrency(ክሪፕቶ ከረንሲ) የሚለው ስያሜም ከዚህ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም እንደመገበያያ የሚያገልግል የዲጂታል ገንዘብ ወይም (virtual currency) ማለት ነው፡፡ ይህም በሌላ አገላለፅ ምናባዊ መገበያያ ማለት ሲሆን ሚስጥራዊ ስልቶችን (encryption techniques) ተጠቅሞ የሚፈፀሙ ግብይቶች ደህንነታቸው የተጠበቁ የሚያደርግ የዲጂታሉ ዓለም አማራጭ የክፍያ ስርዓት ነው፡፡
ልክ እንደሌሎች የገንዘብ ዓይነቶች ማለትም እንደ ዶላር፣ ፓውንድ ወይም ዩሮ በመንግስት አካል፣ በባንክ ወይም በሌላ ማዕከላዊ የፋይናንስ ተቋም የሚተዳደር ሳይሆን በኔትዎርክ ውስጥ ያለ ማንኛውም ተጠቀሚ የሚያስተዳድረው፣ በአንድ ኮምፒዩተር ወይም ሰርቨር ላይ የማይወሰን እና የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብንት ሳያስፈልገው ከአንድ አካል ወደ ሌላ አካል አቻ ለአቻ (Peer-to-Peer) በሆነ መንገድ የሚፈፀም የዲጂታል መገበያያ ነው፡፡ በክሪፕቶከረንሲ አሰራር ሁለት ሰዎች እርስ በዕርስ ሳይተዋወቁና እንደ ባንክ ያሉ ማዕከላዊ የገንዘብ ተቋማት ጣልቃ ሳይገቡ የገንዘብ ልውውጥ እና ግብይት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ነገር ግን በግብይቱ ወቅት ትምምኑ ሊፈጸም የሚችለው እያንዳንዱን የግብይት ሂዲት መዝግቦ በሚያስቀምጠው የዲጂታል የሂሳብ መዝገብ (digital ledger) አማካኝነት ነው፡፡ ይህን ደግሞ የሚዘረጋው በብሎክቼን ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ምንጭ፡ bitdegree.com
TECHIN weekly seminar
You are invited to join us today @TECHINhall
# TECHINtalk
# TECHIN #weeklyseminar
የተሳትፎ ጥሪ
=========
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ‘‘Digitizing Finance: Mobile Payment’’ በሚል ርዕስ ረቡህ ህዳር 24 2012 (Dec 4) የአንድ ቀን ወርክሾፕ በስብሰባ አዳራሻችን አዘጋጅቷል፡፡ ፡፡ በዚህ ወርክሾፕ መሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት እስከ ሰኞ ህዳር 22 ድረስ ብቻ መመዝገብ ትችላላችሁ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfYpO3jXQj8vTabRMdU0_sDcLk8-eanriLk0hJNR7y57VuKvA/viewform
ለተመራጭ ተሳታፊዎች ውጤቱን በኢሜይል የምናሳውቅ ሲሆን ተጨማሪ ጥያቄ ካልዎት በኢሜይል አድራሻችን conference@techin.gov.et ያድርሱን፡፡
ያለን ቦታ አነስተኛ ነውና ይፍጠኑ!!!
የመብረቅ ጥቃት መቼና የት እንደሚፈጠር መተንበይ ተቻለ
የመብረቅ ጥቃት መቼና የት እንደሚፈጠር በሰው ሰራሽ አስተውሎት መተንበይ ተቻለ!
ለመተንበየ ከሚያዳግቱ ተፈጥሯዊ ክስተቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው መብረቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ መብረቅ በየወቅቱ ሰዎችንና አንስሳቶችን ይገድላል፤ ቤቶችንና ደኖችን እሳት በማያያዝ ያወድማል እንዲሁም ብዙ መሰል ውድመቶችን ያስከትላል፡፡
የ EPFL’s School of Engineering ተመራማሪዎች በ 30 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ከ 10 እስከ 30 ደቂቃዎች በኋላ ሊፈጠር የሚችል የመብረቅ ጥቃትን ለመተንበይ የሚያስችል ቀላልና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አዲስ ዘዴ ፈጥረዋል፡፡ ዘዴው በአየር ንብረት ጣቢያዎች የሚገኙ መረጃዎችንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በጋራ በማጣመር ይጠቀማል፡፡
አሁን በስራ ላይ ያለው ዘዴ በጣም ውስብስብና ፍጥነት የሚጎድለው ሲሆን ከ ራዳር አና ከ ሳተላይት የሚገኙ መረጃዎችን መጠቀሙ ወጪውን ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡ አዲሱ ዘዴ በአንፃሩ በማንኛውም የአየር ንብረት ጣቢያ የሚገኝ መረጃን መጠቀሙ ከራዳርና ሳተላይት ውጪ የሆኑና የተግባቦት አውታሮች የሌሉባቸውን የገጠር አከባቢዎችን ለማካተት ያስችላል፡፡
በተጨማሪም ወቅታዊ መረጃን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ በፍጥነት ለመተንበይና አውሎነፋስ ወይም ማእበል ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ የማስጠንቀቂያ ደውል ለማበጀት ያስችላል፡፡
የመረጃው ምንጭ scitechdaily ሲሆን የምርምር ስራውም November 8, 2019 Climate and Atmospheric Science, a Nature Partner Journal ላይ መታተሙ ተገልጿል፡፡
ሐሴትን ከበጎነት !!!
*=*=*=*=*=*=*
የሰው ልጅ በምድር ሲመላለስ ታላቅ የመንፈስ እርካታን ከሚያጎናፅፉት ተግባራት መካከል አንዱ ለተቸገረ መድህን፤ ለወገንም አለኝታ መሆን ሲችል እንደሆነ ብዙዎቻችንን ያስማማል፡፡ ከነዚህ በጎ ተግባራት መካከልም ብዙዎችን ከህልፈት የሚታደገው የደም ልገሳ ተግባር ይጠቀሳል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በ፳፻፲፪ የመጀመሪያቸው የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይም የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ፲፰ የቤተሰብ አባላቶቻችን ተገኝተው ደማቸውን ለግሰዋል፡፡ ታድያ ለበጎ አድራጎት ተግባራት እንግዳ ያልሆኑት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች መሰል የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ሲያከናውኑ የዛሬው ለአስራ አንደኛ ጊዜ ነው፡፡
በቅርቡ ይህን መሰል የደም ልገሳዎች በሀገራችን ኢትዮጵያም ቀስ በቀስ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት አጋማሽ ሀገር ቀን ቆጥሮ ቀጠሮ ይዞ ካከናወነው የደም ልገሳ ዘመቻ በላይም ለዚህ ምስክር የሚሆነን አይገኝም፡፡ በዕለቱም በአርባ የሀገራችን ከተሞች ከአስራ አራት ሺህ በላይ ዜጎች ታላቁን ስጦታ ከአካላቸው ቀንሰው ለወገን አካፍለዋል፡፡