TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በዓይን የማይታየው ዓለም
********************

የሰው ልጅ በየዘመኑ በፈለሰፋቸው የቴክኖሎጂ አቅሞች በመታገዝ በዙሪያው የሚገኙትን በዓይን የሚታዩ ሕይወት ያላቸውንና የሌላቸውን አካላት አፈጣጠር፣ አኗኗርና ጠቀሜታ ሳይንሳዊ ትንታኔ በመስጠት ረገድ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከተለመደውና ከሚታወቀው ባሻገር ያለውን በዓይን መታየት የማይችለውን የደቂቅ አካላት ዓለም (microbial world) የማወቅ አቅም የፈጠረው ዘግይቶ ነው፡፡

ስለ ደቂቅ አካላት መኖር መነገር የጀመረው ከ5ኛው ክፍለ ዘመን (BC) ጀምሮ ቢሆንም በ17ኛው ክፍለ ዘመን የታዋቂዎቹ ሳይንቲስቶች የሮበርት ሁክና የአንቶኒዮ ቫን ሊቨንሆክ በማስረጃ የተደገፈ አዲስ ግኝት በዓይን የማይታዩ አካለት መኖራቸውን ያበሰረ ነበር፡፡ በ1663 ዓ.ም በሮበረት ሁክ በባለ አንድ ሌንስ ትንሽ ማይክሮስኮፕ በመታገዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙከር (Mucor) የተባለውን የፈንገስ ዘር በማግኘት የተጀመረው በዓይን የማይተየውን ዓለም የማወቅ ጅማሬ ከ1677-1678 ዓ.ም ባለው ጊዜ አንቶኒዮ ቫን ሊቨንሆክ ባሻሻለው ማይክሮስኮፕ “little animalcules” በመባል የተጠሩትን ባክቴሪያ ለማየት በመቻሉ የበለጠ ወደ መታወቅ የተሸጋገረበት ወቅት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል::

አሁን ላይ በተደረሰበት ሳይንሳዊ ውጤት መሰረት በዚህ በዓይን በማይታየው የፍጥረት ዓለም ውስጥ የተመደቡት በወል ስማቸው ደቂቅ አካላት1 (microorganisms/microbes) ተብለው የሚታወቁት ፍጥረቶች በየዘርፋቸው ሲዘረዘሩ አርኪያ (Archae)፣ ባክቴሪያ (bacteria)፣ ፈንገስ (Fungus)፣ ማይክሮአልጌ (Microalgae)፣ ፕሮቶዞዋ (Protozoa) እና ቫይረስ (virus) የተባሉት ናቸው፡፡

ደቂቅ አካላት ሕይወት ካላቸው የምድር ፍጥረታት ከ3.5 ቢሊዮን ዓመታት በፊት ቀድመው የተፈጠሩ የፍጥረት ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ በዓይን የማይታዩ የምድራችን ፍጥረታት ከነሱ በኋላ ለመጡት በሕይወት መቀጠል ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው እንደሆኑ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶች ያስረዳሉ፡፡ ዛሬም ቢሆን ካለነዚህ ደቂቅ ፍጥረታት አስተዋጽዖ ሌሎች በሕይወት መቀጠል እንደማይችሉ ሳይንቲስቶች ያምናሉ፡፡ በምድር ላይ ለ3.5 ቢሊዮን ዓመታት ባደረጉት ዝግመተ ለውጥና መላመድ በምድራችን በየትኛውም አካባቢ ለመኖር ችለዋል፡፡፡ በዚህም የተነሳ ሌሎች ፍጥረታት ሊኖሩ በማይችሉባቸው አስቸጋሪ ቦታዎች ምግብ ሳይቸግራቸውና በሕይወት ለመኖር ስጋት ሳይገባቸው ኖረዋል፣ እየኖሩም ነው፡፡ ለእነርሱ በሚኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ምግብ አለ፣ ሕይወት አለ፡፡

የደቂቅ አካላት ልከት (size) በጣም ትንሽ መሆን በዓይን እንዳይታዩ ያደረጋቸው ሲሆን፣ ዛሬም ቢሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂም እንኳን በመታገዝ መታየት የቻሉት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው፡፡ ያላቸው መጠንና የክብ አጋማሻቸውም ከሰው ህዋስ ጋር ሲነጻጸር በተዋረድ 1/8000ኛ እና 1/100ኛ እንደሆነ ነው የታወቀው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች በድምር ሊኖራቸው የሚችለው መጠን ሲገመትም የስፒል ጭንቅላት ያህል እንደሚሆን ነው፡፡ ብዛታቸውም በቁጥር ለመግለጽ ከሚቻለው በላይም እንደሆነ ነው፡፡ ለማሳያ ያህል በምድራችን ያሉ የባክቴሪያዎች ቁጥር ብቻ አምስት ኖኒሊዮን (5x1030) እንደሚደርስና የፕላኔታችን አብዛኛው ግዝፈ ሕይወት (biomass) የባክቴሪያ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያስረዳሉ፡፡ በጥቅል ሲታይ ደቂቅ አካላት በድምር መጠናቸው ከምድር ፍጥረታት አጠቃላይ መጠን የ2/3ኛውን ድርሻ የሚወስዱና 50% የሚሆነውን ፕሮቶፕላዝም የያዙ እንደሆኑ ይገመታል፡፡

በቅርብ ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ደቂቅ አካላት ከሰው ጋር ያላቸውን ቁርኝት ስንመለከት በሰው አካል ውስጥ ከሚገኘው ህዋስ 90%ቱን የሚሸፍኑት ባክቴሪያና ፈንገሶች እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ የሰው አንጀት ብቻ 40 ሺህ የባክቴሪያ ዝርያዎችን፣ 9 ሚሊዮን ልዩ የሆኑ የባክቴሪያ በራሂዎችን (genes) እና 100 ትሪሊዮን የደቂቅ አካላት ህዋሶችን (cells) እንደያዘም ተገምቷዋል፡፡ በአጠገባችን ያለ አንድ ግራም አፈር 40 ሚሊዮን እንዲሁም አንድ ሚሊ ሊትር ንጹህ ውኃ አንድ ሚሊዮን የባክቴሪያ ህዋሶችን እንደያዘ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው በዓይናችን ስለማናያቸው እንጂ ደቂቅ አካላት ከኛ ጋር እና በዙሪያችን በየትኛውም ስፍራና አካባቢ እንደሚገኙ ነው፡፡ ለምን? በአጭሩ ሊጠቅሙን!

ከፍጥረታት እጅግ ጉልበተኛውና ኃይለኛው ማነው የሚል ጥያቄ ቢነሳ የምድራችን ምላሽ ደቂቅ አካላ
የሰመር ካምፕ ተወዳዳሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው
****************************************************************
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ያዘጋጀው እና ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ሲካሄድ የቆየው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በእውቅና እና የሽልማት ስነ ስርዓቶች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ በዋናነት የመንግስት ተቋማት የአሰራር ስርዓትን የሚያዘምኑ የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች ማበልጸግ እና ማቅረብ በሚለው የትግበራ ዘርፍ ላይ አተኩሮ የተሰናደ ሲሆን፣ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ አመልካቾችም በመነሻነት መሳተፋቸውን በስነ ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በተዘጋጀው በዚህ የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የመክፈቻና የአንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የሰመር ካምፑ መዘጋጀት የሚኖረውን ከፍተኛ ጥቅም አንስተው ወደ ፊት ይበልጥ ተጠናከሮ እንደሚቀጥል እና ድጋፎችም በሰፊው እንደሚደረጉ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ በአዲስ የመዋቅር መስረታ እና የሽግግር ሂደት ላይ ከመሆኑ አኳያ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ እንደዚህ ያለ ፕሮግራምን በስኬት ማጠናቀቁ ጥሩ መነሻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

የሰመር ካምፕ ዝግጅቱን አጠቃላይ ሂደት እና የውድድር መስፈርት አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉት የኮምፒውቲንግ እና አናሊሲስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብሬ አላምነ በጥቅሉ ከሶስት መቶ በላይ ተማሪዎች ለውድድሩ ማመልከታቸውን ጠቅሰው በተዘጋጀው መስፈርትም 27 የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እና ፕሮጀክታቸውን እንዲያከናውኑ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በተዘጋጀው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ላይ ምንም እንኳን ጊዜን ጨምሮ የፋይናንስ እና የቁሳቁስ ችግሮች እንደነበሩ ያነሱት አቶ ገብሬ የሚቻለውን ድጋፍ ለተማሪዎቹ በማድረግ የመንግስት ተቋማትን የሚያዘምኑ ችግር ፈቺ ሶፍትዌሮች እንዲሰሩ መደረጋቸው በስኬት ደረጃ የሚታይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተዘጋጀው የመስፈርት ሁኔታ ሶስት ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሲሆኑ ፕሮጀክታቸውን በስኬት ያጠናቀቁ 14 ተማሪዎችም የእውቅና ሽልማት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በዚህም አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀው ፕሮጀክት በናትናኤል ዘነበ እና ሳምሶን ተከስተ የተሰራው Employe Attendance System የተሰኘው ፕሮጀክት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በአላዛር ደምሴ የተሰራው General Safty የተሰኘው ችግር ፈቺ ሶፍትዌር አሸናፊ ሆኗል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው ቢታኒያ ናስር እና ናትናኤል ሙሉጌታ የሰሩት Storage Management System የተሰኛው ፕሮጀክት ሲሆን ለሶስቱም አሸናፊች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ማጠናቀቂያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢንቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሳህለ ማሪያም በተማሪዎቹ የተሰራው ችግር ፈቺ ሶፍትዌር ብዙ የመንግስት ተቋማት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ጠቃሚ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ለወደፊቱም የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሶፍትዌሮቹ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል?
*****************************
የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲሆን የዲጂታል ዓለሙ የሚፈልገውን ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ያራመደ ቴክኖሎጂ ተደርጎም ይወሰዳል። የ 5G ቴክኖሎጂ የመረጃ መለዋወጫ ፍጥነትን አሁን ካለው የ4G ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 100 የተሻለ እጥፍ እንደሚልቅ ይገምታል። ይህም ማለት የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን እስከዛሬ ከነበረው የm/s ፍጥነት ወደ g/s ያሳድገዋል ማለት ነው።
ኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሃሪሽ ክሪሺናስዋሚ እንዳሉት “ የ 5G ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አሁን ባለው የኔትዎርክ ፍጥነት መተግበር ያልቻልናቸውን ከፊተኛ የሆነ የኔትዎርክ አቅምን የሚጠይቁ መተግበሪያዎችን እንዲንጠቀም ያስችለናል ለምሳሌ በ ጊጋ ባይት ደረጃ ያሉ ፊልሞችን በሰከንድ ከኢንተርኔት ማውረድ ያስችለናል እንድሁም እንደ ቨርችዋል ሪያሊቲ መተግበሪያና ሰው አልባ መኪኖችን ላይ ለፈጣን የመረጃ ዝውውር መጠቀም ያስችለናል”። በተጨማሪም ዘመኑ እየፈጠራቸው ያሉ ቴክኖሎጂዎች ማለትም እንደ አጉመንትድ ሪያሊቲ እና ሰው አልባ መኪኖች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ፍጥነትን ይሻሉ ስለሆነም የ5G ቴክኖሎጂ የመረጃ የመዘግየት ሂደንት ወደ 1 ሚሊ ሴኮንድ ዝቅ ማድረን አላማ አድርጎ ተነስቷል ይህ ማለት ተንቀሳቃች መሳሪያዎች መረጃን የ1 ሴኮንድ 1/1000 ባነሰ መለዋወጥ ያስችላቸዋል።
ባለፉት ትውልዶች ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙት የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረርን እንደ ሬድዮ ሞገድ ባሉ ቴክኖሎጂዎች በመሆኑ የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ በከፍተኛ ሁኔታ የኔትዎርክ መጨናነቅን ይፈጠርበታል፡፡ ስለሆነም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የራድዮ ሞገድ ከመጠየቁም በላይ በ ሴንቲሜትር የሚለካውን ወደ ሚሊሜትር ሞገድ ዝቅ ማድረግ አስፈልጓል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ቀድመን ከምናውቀው ትልልቅ የሆኑ የኔትዎርክ ምሰሶዎች በላይ በማይፈልጉ የህንጻዎች አናት እና በመብራት አስተላላፊ ምሰሶዎች ላይ ሊገጠሙ የሚችሉ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎቹ አዲስ የግንኙነት መንገድ የክፈቱ አስብሏቸዋል። ነገር ግን እነዚህ የሞገድ አይነቶች ሌሎች ተግዳሮቶች አጋጥሟቸዋል ከነዚህም መካከል ሞገዶቹ በዛፎችና በህንጻዎች ከመዋጥ አልዳኑም። ነገር ግን እነዚህ በመጠናቸው አንስተኛ የሆኑ የኔትዎክ አስተላላፊዎች ለአዳዲስ የምርምር ስራዎች መፈጠር ጉልህ አስተዋጾ ነበራቸው። የ አምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ የመፈጠር ምክንያትም ናቸው። የአምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ (5G) ቀድሞ በነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ በመጠን አነስተኛ የሆኑ አንቴናዎችን በመጨመር እንዲሁም የማስተላለፍ አቅማቸውን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መላላኪያ ፍጥነትን በመጨመር የተፈጠረ ሲሆን የመረጃ መዘግየትን በእጅጉ ቀንሷል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በተጨማሪም በፊት ከነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ያነሰ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀማቸውም ልዩ ያደርጋቸዋል።
ምንጭ:-Live science
የፔቲዲን (Pethidine) ሱስና ህክምናው
*********************
ፔቲዲን መካከለኛና ከፍተኛ ስቃይን ለማስታገስ በመርፌ የሚሰጥ መድሀኒት ሲሆን ህመም ከማስታገስ ባሻገር የደስታ ስሜት ስለሚፈጥር አንዳንድ ሰዎች ላይ ሱስ ሊሆን ይችላል። ፔቲዲን ሱስ ሲሆን ከአእምሮና ከሰውነት ጋር ስለሚለማመድ ህመምን ለመቀነስ ወይም ደስታን ለማግኘት ከፍ ያለ መጠን መውሰድ ይፈልጋል።
የፔቲዲን ሱስ ያለባቸው ሰዎች በተከታታይ የሚወጉት መድሀኒት እየጨመረ ስለሚመጣ በድንገት ብዙ መጠን ወስደው መንቀጥቀጥ ራስን መሳት እንዲሁም ሞት ሊያጋጥማቸው ይችላል። ብዙ መጠን ለረጅም ጊዜ የወሰዱ ሰዎች በድንገት ሲያቆሙ ከፍተኛ ጭንቀት፣ መቅበጥበጥ፣ እንባ መብዛት፣ ማቅለሽለሽ ...ወዘተ ይታይባቸዋል። በዚህ ምክኒያት በድንገት ማቆም አይመከርም።
የፔቲዲን ሱስ ያለባቸው ሰዎች ሀፍረት ስለሚሰማቸው ችግሩን መቀበል ያስቸግራቸዋል ከዛ ይልቅ ለመሸፋፈን ይሞክራሉ። አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ ጥናት ፔቲዲንን ጨምሮ በመርፌ የሚወሰዱ መድሀኒቶች ሱስ የሆነባቸው ከ አራት ሺህ በላይ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ብዙዎቹ ህክምና እንዳለው እና ህክምናው የት እንደሚሰጥ ባለማወቅ የህክምና እግዛ ሳያገኙ ይቀራሉ።
ዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኘው የአእምሮ ህክምና ክፍል ፔቲዲንን ደረጃ በደረጃ በመቀነስ እንዲያቆሙ የሚያግዝ ሲሆን የግልና የቡድን የንግግር ህክምናም ይሰጣል። የፔቲዲን ሱስ ለህክምና ተብሎ በተሰጠ መድሀኒት ተከትሎ የሚመጣ በመሆኑ Center for Disease Control የሚከተሉትን ነጥቦች ለባለሞያዎች እንደመርህ ያስቀምጣል።
*በተቻለ መጠን ፔቲዲን (ኦፒዮይድ) ከመጠቀም ሌሎች አማራጭ መድሀኒቶችን መጠቀም
*ፔቲዲን ማዘዝ አስፈላጊ ሲሆን የሚያስፈልገውን ትንሹን መጠን ለሚቻለው ትንሽ ጊዜ ብቻ ማዘዝ
*ፔቲዲን የሚወስዱ ሰዎች ላይ ሱስ መሆን አለመሆኑን በጥንቃቄ መመልከትና ሱስ ከሆነ የአእምሮ ህክምና እንዲያገኙ ማገዝ ናቸው።
ምንጭ፡ addiction hope እና mental wellness
የፀሃያችንን ድንበር አልፈው የሄዱት ሁለቱ መንኮራኩሮች
*********************
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ እንደግሪጎሪያኑ በ1977 በተለያየ ወር ልዩነት ያመጠቃቸው ቮዬጀር1 እና ቮዬጀር2 (Voyager 1&2) የተሰኙት አሳሽ መንኮራኩሮች ስለ ፕላኔት ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ዩራኑስ እና ኔፕቱን ስሪት አጥንተው እንደጨረሱ ወደ በይነኮከባዊ ህዋ (interstellar space) መላካቸው የሚታወቅ ነው። እነዚህ መንኮራኩሮች ከ37 አመታት የህዋ ውስጥ ጉዞ በኋላ በጁላይ 2012 አካባቢ ሴንሰሮቻቸው የፀሀይ ነፋሳት ፍጥነት ቀንሶ የበይነኮከባዊ ነፋሳት ፍጥነት እንደጨመረ ማረጋገጥ ችለዋል። በመሆኑም ስርአተፀሀያችንን ለቀው ወደ በይነኮከባዊ ህዋ ጉዟቸውን እንዳደረጉ እርግጥ ሆኗል።
ስለ ስርአተፀሀያችን ድንበሮች ያለንን እውቀት በሙሉ ያስጨበጡን ቮዬጀሮች በጥቂት ወራት ተለያይተው የተላኩ ቢሆንም ስርአተፀሀያችንን ከቦ የሚገኝውን እና ከድንኩዋ ፕላኔት ፕሉቶ ምህዋር በእጅጉ ርቆ የሚገኝውን ኢነባራዊ ድንበር ሂልዮስፌር (Heliosphere) አልፈው መሄዳቸው በታሪክ በሰው ልጅ ከተሰሩ አሳሽ መንኮራኩሮች ውስጥ ቀዳሚ ያደርጋቸዋል። መንትያዎቹ አሳሽ መንኮራኩሮች የሚጉዋዙበት አቅጣጫ እንዲሁ የተለያየ ቢሆንም ሁለቱም ግን ስርአተፀሀያችንን ለቀው ወጥተዋል። ቮዬጀር2 አሁን ላይ 'ሳጁታርየስ' ወደተሰኘው ህብረከዋክብት (Constallation) አቅጣጫ በሰኮንድ 16ኪ.ሜ እየገሰገሰች ጉዞዋን ቀጥላለች። በዚህ ፍጥነት ከቀጠለች ከ 296,000 አመታት በሁዋላ ሰማያችን ላይ ደምቃ ከምትታየው 'ሲረስ' ከተሰኘቸው ኮከብ ልትደርስ ትችላለች ተብሎ ይታሰባል።
ይሁንና ሁለቱም መንኮራኩሮች መንቀሳቀሻ ሀይላቸው የሆነው 'ፕሉቶኒየም ተርሞኤሌክትሪክ ጀነሬተር' የተሰኘው ባትሪያቸው ከ5 አመታት በሁዋላ በ 2025 ሙሉ ለሙሉ ተሟጦ የሚያልቅ በመሆኑ መረጃቸውን መላክ ያቆማሉ። ይህ ማለት ግን ጉዟቸውን ያቋርጣሉ ማለት አይደለም። ከሁለቱ መንኮራኩሮች በፊት እንደመጠቀችው ፓዮኔር 10 አሳሽ መንኩራኩር ሁላ መንትዮቹም በውስጣቸው ምድራችንን የሚገልፅ እና መገኛ አቅጣጫዋን የሚጠቁም ካርታ ይዘዋል። እነዚህ አሳሽ መንኮራኩሮች ማረፊያቸው በውል አይታወቅምና ምናልባት ከኛ ውጭ ህይወት ያላቸው ፍጡራን እነዚህን መንኮራኩሮች ቢያገኟቸው ከየት እንደመጡ እና ስለመጡበት ፕላኔት በደምብ የሚያስረዳ ካርታ እና ስእላዊ መግለጫን ይዘው ይጓዛሉ።
አሁን ላይ ከቮዬጀሮች የተላክ መልእክት ምድራችን ለመደረስ ከ16 ሰአታት በላይ የሚፈጅበት ሲሆን አሁን ከደረሱበት የinterstellar medium (ISM) አንፃር መልክቱን ለማድረስ የሚፈጅባቸው ጊዜ በመጠኑም ቢሆን ለውጥ ያመጣል፡፡ መንትዮቹ መንኮራኩሮች ከላይ እንሰተጠቀሰው በ2012 በላኳቸው መረጃዎች የፀሀይ ነፋሳት ፍጥነት ቀንሶ የበይነኮከባዊ ነፋሳት ፍጥነት መጨመር ተከትሎ interstellar medium ላይ መድረሳቸው የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡም በተለይም ቮዬጀር2 የተባለቸው ሞንኮራኩር የላከቸው ሲግናል ስለጥልቁ ህዋ ያላወቅናቸውን እና ስለበይነኮከባዊ ህዋ ሰፊ መረጃን ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡Science Focus እና theguardian
Presentation 2.jpg
1.3 MB
techin weekly seminar
venue: techin hall
date and time nov 14, from 4:30
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ፅህፈት ቤት ጋራ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
***************************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ የአዕምሮ ንብረት ድርጅት እና የአውሮፓ አዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት ጋራ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡ ኢንስቲትዩቱን ወክለው የመግባቢያ ስምምነቱነን የፈረሙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ሲሆኑ በኢትዮጵያ አዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት በኩል የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ የማነብርሀን ነበሩ፡፡
ስምምነቱን አስመልክተው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ባደረጉት ንግግር ስምምነቱ ከፊርማም ባለፈ በተቋማቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደላቀ ተቋማዊ ደረጃ እንደሚያሻግረውና ለወደፊት ስራዎችም መነሻ እንደሚሆናቸው ገልፀዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በበኩላቸው ስምምነቱ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከአውሮፓ የአዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት ጋራ እንዲሰራ እንደሚያደርገውና ፅህፈት ቤታቸውም በዚህ ትስስር የግንኙነት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ገልፀዋል፡፡ አክለውም ኢንስቲትዩቱ ፓተንቶችን ለህብረተሰቡ በማድረስ ረገድ የሄደባቸውን ርቀቶች አውስተው የአውሮፓ አዕምሮ ንብረት ቢሮ በዚህ እንቅስቃሴ ጉልህ እገዛ እንደሚያደርግ ያላቸውን ተስፋ አስረድተዋል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ተሳታፊ የነበሩት በአውሮፓ አዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት አቶ ኒኮላስ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋናን ችረው ስምምነቶቹን ወደ ተግባር የሚለውጡ የጋራ ስራዎችን ከኢንስቲትዩቱ ጋራ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡
በሂሳብ ትምህርት የሴቶች ውጤት ማሽቆልቆል ምክንያቱ ተፈጥሮ ወይስ…?
==========================
በ1992 ቲን ቶክ ባርቢ በሚባል የልጆች መጫወቻ አሻንጉሊት የተካተተ ቅንጭብ ድምፅ የሂሳብ ትምህርት ከባድ ነው የሚል ነበር፡፡ ሴቶች በተፈጥሯቸው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስኬታማ መሆን አይችሉም የሚል ሐሳብ ነገር ግን እውነትነቱ ያልተረጋገጠ አቋም በማስተላፉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ገጥሞት ነበር፡፡
ጄኔስ የተባለችው የኒዉሮ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር በካርኔጊ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ ስትመራው የነበረው የወጣት ወንዶችና ሴቶች ልጆችን የአንጎል እድገት በጥልቀት የሚመረምር ጥናት ታድያ በሂሳብ ችሎታ ውስጥ ምንም አይነት ጾታን መሰረት ያደረገ ልዩነት አለመኖሩን አመላክቷል፡፡ የምርምር ቡድኑ መሪ እንደተናገሩት፤ የምርምሩ ውጤት ወጣት ልጆች ጾታቸው ምንም ይሁን ምንም የአንጎል ተግባራቸው ተመሳሳይ በመሆኑ ህብረተሰቡ በሒሳብ ውጤታማነታቸው ያለውን አመለካከት እንደገና እንዲያስብበት ማድረግ ይቻላል ብላለች፡፡
ካንቶን እና የጥናቱ ቡድኗ የመጀመሪያዉን የኒዉሮኢሜጂንግ ጥናት በማካሄድና ቪድዮ እንዲሁም የተለያዩ የስታቲስቲክስ አነጻጻሪዎችን በመጠቀም ማረጋገጥ እንደቻሉት ከሆነ የአዕምሮአዊ ዕድገት ልዩነትን የሚያመላክት በወጣት ወንዶችና ሴቶች መካከል ምንም አይነት አዕምሯዊ የትግበራና እድገት ልዩነት አልተገኘም፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ከሆነ ለሴቶች ተማሪዎች የሒሳብ፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ውጤት መድቀቅ ዋነኛው ምክንያት ወደነዚህ የትምህርት መስኮች እንዳይቀላቀሉ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚደርስባቸው ተፅዕንዖ ነው፡፡ ቀድሞ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ቤተሰብ አብዛኛውን ትኩረት በወንድ ልጆቻቸው ላይ የሚያውሉ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ሃቅ ታዲያ በትምህርት ቤትም ቢሆን መገንዘብ ይቻላል፡፡ የውጤት ብልጫን እንደሚያመጡ በማሰብ የሂሳብ አስተማሪዎች ለወንድ ተማሪዎቻቸው ሰፊውን ትኩረት ይለግሳሉ፡፡
የተወሰኑ የሂሳብ መመዘኛዎችን በመጠቀም የታዳጊ ህፃናትን የዕድገት እምርታ ለመገምገም ታስቦ የተከናወነውን ይህን ጥናት ሌሎችን የሂሳብ ችሎታዎችንም ወደሚገመግም ጥናትነት ለማስፋት እንዳለሙ የጥናት ቡድኑ መሪ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፡ Science Daily
የእስራኤል ተመራማሪዎች አዲስ የስኳር በሽታ ህክምና ዘዴን አገኙ
==========================
የእስራኤል ተመራማሪዎች ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ጥናት የስኳር ሕመምን ለማከም የሚስችል አዲስ የሕክምና ዜዴ ማግኘታቸው አስታውቀዋል። እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ ታማሚዎችን በቋሚነት በተቀመጠ የሰዓታት ልዩነት በየቀኑ ሶስት ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ ብቻ የአይነት 2 ካንሰር ታማሚዎችን የኢንሱሊን ፍጆታ መቀነስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ይህ አዲስ የህክምና መንገድ የታማሚዎችን የክብደት መጠን ብሎም የምግብ ፍላጎት፣ ዕለታዊ የኢንሱሊን እና የሄሞግሎቢን A1C መጠንን እና በደማቸው ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መቆጣጠር ያስችላል።
በ12 ሳምንታት ቆይታ ሃያ ስምንት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ባለቸው የስኳር ሕመምተኞች ላይ በተካሄደ ሙከራ ታማሚዎቹ ከላይ የተገለጸውን የአመጋገብ ስርዓት በመከተላቸው ክብደታቸው በአማካይ በ5 ኪሎ ሲቀንስ የሄሞግሎቢን A1C መጠንም በ1.2 በመቶ ሊወርድ ችሏል፡፡ በተጨማሪም በነዚህ ሕመምተኞች ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን በጣም ቀንሶ ታይቷል፡፡ ይህም ከጠቅላላው የኢንሱሊን ፍጆታቸው በአማካኝ 26 ያህሉን መቀነስ አስችሏቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በነዚህ ሕመምተኞች ላይ የረሃብና ለጣፋጭ ምግቦች ያላቸው ስሜት ቀንሶ ተስተውሏል፡፡ በአንጻሩ በቀን ስድስት ጊዜ እንዲመገቡ የተደረጉ የስኳር ሕመምተኞች እነዚህ መሻሻሎች ሳይታይባቸው ቀርቷል፡፡
ከዚህ ጥናት ግኝቶች በመነሳት የስኳር ሕመምተኞችን አመጋገብ መቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት እየሰሩ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡
የስኳር ህመም የሚከሰተው ሰውነታችን ለኑሮም ሆነ ለእድገት የሚያስፈልገውን ስኳር በትክክል ለመጠቀም ሳይችል ሲቀር መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድ ሰው ለስኳር ሕመም ተጠቂ ነው የምንለው በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ ሲሆን፤ ይህም ሰውነታችን ኢንሱሊን የተሰኘውን ሆርሞን በበቂ ሁኔታ ወይም ጭራሹኑ እንዳያመነጭ ሲያደርገው ነው።
ምንጭ፡ Xinhua
ስትጠበቅ የቆየችው የኢትዮጵያ ሳተላይት በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ህዋ ታመራለች
==========================
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያዋ የሆነውን ሳተላይት የፊታችን ታህሳስ 7 ከጠዋቱ 12፡21 ወደ ህዋ እንደምታመጥቅ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ጀነራል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡ ከቻይና የጠፈር ምርምር ተቋም ጋራ በመተባበር የተሰራችው ይህች ሳተላይት ኢቲ.አር.ኤስ.ኤስ-1 (ERRSS-1) የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን ሳተላይቷን ለመቆጣጠር እና መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ጣቢያም በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል እንደተዘጋጀላት ተገልጿል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እንደገለፁት ይህች ሳተላይት በ80 ዲግሪ ላቲቲውድ ላይ በመሆን ኢትዮጵያን ብሎም የምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ አካባቢን ትሸፍናለች፡፡ በዚህም በግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድን ልማት እና አካባቢ ጥበቃ ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ ምልከታዎችን ለሀገራችን የምታቀርብ ይሆናል፡፡
ሳተላይት ማምጠቅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስ ሁለት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ሳተላይታቸውን በህዋ እያንሳፈፉ ሲሆን ኢትዮጵያም ዘጠነኛዋ በመሆን የምትቀላቀላቸው ይሆናል፡፡