TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
self-defense ከጭንቀት ለመዳን
_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1978 ዓ.ም ነበር የ 18 ዓመቷ ሳቫጅ ከትውልድ አገሯ ፈንሳይ ወደ እየሩሳሌም የተጓዘችው፡፡ እንግድነት እንዳይሰማት ያደረጋት ባለውለታዋን እንዳገኘት የተሰማትም ያኔ ነበር፤የ18 ዓመቱ የባስ ሹፌር ለ3 ተከታታይ ወራት አገሪቷን ሳይሰለች አስጎበኛት፡፡

"ቅን እና ትሁት ነገር ነበር" ትላለች ሳቫጅ እሱን ስትገልጸው ፤ በእንደዛ መልኩ አገሪቷን ካስጎበኘኝ በኋላ ወላጆቹ ጋር እንድተዋወቅ ወደ ቤቱ ሲጋብዘኝ ሳላንገራግር እሺ አልኩት ባለኝ ሰዐትም እዛ ተገኘሁ ለሰዓታት ስንስቅ እና ስንጫወት ከቆየን በኋላ ግን 6ኛው ህዋሴ አንዳች ነገር ሹክ አለኝ ጥሩ ነገር ሊፈጠር እንዳልሆነ ተረዳሁ ወዲያው በበሩ በኩል 4 ጎረምሶች ወደ ቤት ገቡና በሩን ከውስጥ ቆለፉት፤ ነገሩ እንዳበቃ ተረዳሁ እነዚህ ሰዎች ይህንን ነገር በተደጋጋሚ አርገውት እንደሆነም እርግጠኛ ሆንኩ፡፡

ሳቫጅ በዛኑ ዕለት ማታ ወደ አገሯ ፈረንሳይ ተመለሰች በተደጋጋሚ እራስ የማጥፋት ሙከራም አደረገች ይህ ሁኔታ ከባድ ወደ ሆነ ጭንቀት እና መረበሽ ስላመራትም የአዕምሮ ሃኪም ጋር እና የምክር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር መመላለስ ጀመረች፡፡ ይሁንና እንዲያረጋጓት ታስበው የተሰጧት መድሃኒቶች ሊጠቅሟት አልቻሉም ፡፡ ምንም እንኳን በሌሎች አማራጮችም እራሷን ለማከም ብትሞክርም የዛን ዕለት ክስተትን ወደ አዕምሮዋ እንዳይመጣ ማድረግ ግን አልቻለችም ሳቫጅየ post-traumatic stress disorder (PTSD) ክፉኛ ተጠቂ ሆነች፡፡

post-traumatic stress disorder ማለት ከአዲንት አደጋ በኋላ የሚከሰት ከባድ የሆነ የጭንቀት በሽታ ሲሆን በዚህ በሽታ በዓለማችን ውስጥ በየዓመቱ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ከዛ በላይ የሚሆኑ ደግሞ በበሽታው ይሰቃያሉ፡፡ በአሜሪካን 1.4ሚሊዮን ሰው በጥቃት ሳቢያ ጉዳት ደርሶበት ወደ ድንገተኛ ክፍል የሚገባ ሲሆን በ አውሮፓ ደግሞ 670,000 የሚሆን ያክሉ ሆስፒታል ይመጣል፡፡

በ1996 ሳቫጅ ተመልሳ ወደ እስራኤል አቀናች ምናልባትም ወደዛ በመቅረብ ችግሩን መጋፈጥ ትችል ከሆነም ብላ በወሲባዊ ጥቃት የተጎዱ ሰዎች የሚታከሙበት ተቋም ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ማገልገል ጀመረች ተጠቂዎች አድማጭ ያስፈልጋቸዋል አኔ ባለመናገሬ አልተሰማሁም አልተረዳሁምም ስትል ለሚጠይቋት ሁሉ መናገር ጀመረች፡፡

በ2006 አንዲት ጓደኛዋ ኢልሃቪቭ የተሰኛ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እራስ የመከላከል ብቃትን የሚያስተምር ተቋም ውስጥ እንድትሳተፍ ጠየቀቻት፡፡ ሳቫጅ ስትናገር እኔ ድብድብ ደግሞ ምን ሊያረግልኝ ብዬ ጥቆማዋን አጣጥዬ የነበር ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ተቀላቀልኩ ፤ ያኔ የኔ ህይወት ወደ ኋላ ላይመለስ ተቀየረ ትላለች፡፡
በሃርቫርድ የህክምና ትምህርት ቤት የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እራስ የመከላከልን ስልጠና እንደመስጠት የሚረዳ አንዳች ትምህርት የለም፡፡ ይህ ስልጠና ከፍርሃት ነፃ እንዲሆኑ ከመርዳቱም በላይ በዓይነ ህሊናቸው የሚስሉትን ክፉ አጋጣሚ በአካላቸው አፍርጠው እንዲጥሉት ስለሚረዳቸው ፈጣን በሆነ ሁኔታ ከዚህ እንዲያገግሙ ይረዳቸዋል፡፡

ምንም እነኳን ሳቫጅ በወቅቱ ስለዚህ ጥናት የምታውቀው ነገር ባይኖርም እዛ ውስጥ በፅናት በመቆየት እና በመስራት እራሷን ሙሉ ለሙሉ ለማከም የቻለች ሲሆን በኋላ ላይ IMPACT የተሰኘ ዓለም ዐቀፍ የሴቶች አቅም ማጎልበቻ እና የራስ መከላከል ብቃት ማሰልጠኛ ተቋም ሃላፊ በመሆን በስሯ ኢልሃቪቭ እና መሰል ተቋማትን አጠቃላ መምራት ጀመረች፡፡

ሳቫጅ የself-defense (እራስ የመከላከል ብቃት) ማስተር በመሆን ከዚህ በፊት ወንዳዊ ይዘት ነበረው የself-defense አርት አሁን ላይ ለሴት ልጆችም እንዲሆን አድርጋ ዳግም በመቅረፅ ለዓለም ትልቅ ነገር አበረከተች፡፡
ምንጭ፡- undark
የሀሳብ ልዩነት #በሳይንቲስቶች አለም : .....እንደ ትምህርት ለሀሳብ ልዩነት #በፖለቱከኞች አለም
***********************************
በ1930ዎቹ የታላቁ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ቲዮረቲካል ፊዚክስ ተማሪ የነበረው አልበርት አንስታይን ለኒውተን ስራዎች ትልቅ አድናቆት የነበረው ቢሆንም ኒውተን የስበት ንድፈሀሳቡ ላይ ፀሀይን ብናጠፋት 'ከመቅፅበት' ፕላኔቶች ምህዋራቸውን (orbit) ይስታሉ ያለው አልተዋጠለትም። 'ከመቅፅበት' የምትለዋ ቃል ናት ጥርጣሬ ያሳደረችበት። አንስታይን ይህን ሀሳብ መሰረት በማድረግ ለአስር አመታት ያህል አዲስ ንድፈሀሳብ ለማግኘት ጣረ። በመጨረሻም ዩኒቨርስን በሌላ አቅጣጫ እንድናይ የረዳንን የ ጀነራል ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብን (General relativity theory) አገኘ። በዚህ ንድፈሀሳብ መሰረት ከኒውተን ጋር ላልተስማማበት ሀሳብ መልስ አገኘ።

በአንስታይን ንድፈሀሳብ መሰረት ግዜ እና ቦታ አንድ ላይ የተሰፉ ምንጣፍ ናቸው። ግዜ ከቦታ ቦታ ከግዜ አይለዩም። ይህንን ስፔስ ታይም ፋብሪክ (Space-time fabric) ብሎ ጠራው። ክብደት ያላቸው ቁስ አካሎች በግዜ-ቦታ ድር ላይ ስርጉደት እንደሚያመጡም ይገልፃል። ምድራችን የምትዞርበት ምህዋር ፀሀያችን ድሩ ላይ በፈጠረችው ስርጉደት ውስጥ ነው ብሎ አመነ። ስለዚህ ፀሀያችንን ለአፍታ ማጥፋት ብንችል በፀሀያችን ክብደት ሰርጉዶ የነበረው ድር ወደቦታው ሲመለስ የሚፈጥረው ሞገድ ይኖራል። ልክ ወንዝ ውስጥ ድንጋይ ስንወረውር ጫፍ ድረስ እንደሚመጡት የውሀ ሞገዶች ሁሉ ይህም ሞገድ ከፀሀይ ተነስቶ መላው ስርአተ-ፀሀያችንን ያካልላል። ይህን ሞገድ የስበት ሞገድ (gravitational wave) ብሎ ጠራው። የሚጉዋዝበትም ፍጥነት በብርሀን ፍጥነት እንደሆነ በሂሳባዊ ስሌት አረጋገጠ። ስለዚህ ምድራችን ከምህዋሩዋ የምትወጣው 'ከመቅፅበት' ሳይሆን ይህ የስበት ሞገድ ከፀሀይ አቅጣጫ መጥቶ ምድራችንን ሲነካት እንደሆነ ተናገረ።

ከፀሀይ የመነጨ ብርሀን ምድራችን ለመድረስ 8 ደቂቃዎች ይፈጅበታል፤ የስበት ሞገድ ፍጥነት ከብርሀን ፍጥነት እኩል በመሆኑም ምድራችን ምህዋሩዋን ለመሳት 8 ደቂቃዎች ብቻ እንደሚያስፈልጓት አብራራ። አልበርት አንስታይን ይህንን ንድፈሀሳብ ጀነራል ሪላቲቪቲ ብሎ ጠራው። በዚህ ንድፈሀሳቡም ትልቅ ዝናን ተቀዳጀ። የኒውተንን የስበት ንድፈሀሳብም ከራሱ ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብ ጋር አዋሀደ።
ምንጭ፡ Airtable universe, Forbes እና E.A
፻ ሚሊዮን መንገደኞች
===============
በአይነቱ ልዩ የሆነው አየር ማረፊያ በቻይና ቤጂንግ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡ ቤጂንግ ዳሺንግ ተብሎ የተሰየመው ይህ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስምንት የአውሮፕላን መንደርደሪያዎች ሲኖሩት ሙሉ አቅሙን ሲጠቀምም በአመት መቶ ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል፡፡ ካሁኑም በርካታ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች መዳረሻቸውን ወደእርሱ ዘንድ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡፡
700,000 ሺህ ካሬ ወይም መቶ እግር ኳስ ሜዳዎችን ስፋት በሚስተካከል ቦታ ላይ ተንጣሎ ሲገነባ የኪነ ህንፃ ዲዛይኑን ስመ ጥሯ የኪነ ህንፃ ባለሙያ ዛሃ ሀዲድ አሽቀርቅራ ሰርታዋለች፡፡ ውስጣዊ ገፅታውም ቢሆን በኩርባ ቅርፆች የተንቆጠቆጠና ባሉት ክፍት ጣርያዎች አማካኝነት ብርሀንን እስከታችኛው ወለል እንዲያደርስ ሆኖ የተሰራ ነው፡፡ ከህንፃው ሰስርም አየር ማፊያውን ከመሀል ከተማ በ20 ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ እንዲያገናኝ ሆኖ ተሰራ የባቡር መስመር ተገንብቶለታል፡፡
ታድያ ይህ ሁሉ ልቀት በቀላልል ዋጋ አልተገኘም፡፡ የአየር ማረፊያው ግንባታ በአጠቃላይ 17.5 ቢሊዮን ዶላር ወይም 120 ቢሊዮን የቻይና ይኋን ወጪን ጠይቋል፡፡ ታድያ የባቡር መስመር ዝርጋታውን ያካተትን እንደሆነ ወጪው ወደ 400 ቢሊዮን ይኋን አሻቅቦ እናገኘዋለን፡፡
በአሁኑ ሰዓት ቤጂንግን እያገለገለ ያለው የቤጂንግ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን መንገደኞች በላይ በማስተናገድ በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡ ለዚህ ዋነኛው ምክንያት ቻይና ያላት የተትረፈረፈ የአየር ላይ ተጓዥ ነው፡፡ በፈጣን እድገት ላይ የሚገኘው ይህ የመንገደኞች ቁጥሯ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት አሜሪካንን በመቅደም የዓለማችን ቀዳሚው የአየር ትራንስፖርት ገበያ እንደሚያደርጋት ሲጠበቅ የመንገደኞቹ ቁጥርም ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረበት አንድ ቢሊዮን በ2037 ወደ 1.6 ቢሊዮን ያድጋል፡፡
ምንጭ፡ TechXplore
የበታችነት ኮምፕሌክስ
==============
የበታችነት ኮምፕሌክስ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ራስን ከሌላ ሰው ጋር በማወዳደር እንደሌሎች መሆን ባለመቻል የሚፈጠር ስነልቦናዊ ችግር ነው። የበታችነት በተፈጥሮ ሁሉም ሰው ላይ ይከሰታል። ህፃናት ወላጆቻቸውና ሌሎች ትልቅ ሰዎችን ሲመለከቱ በእውቀት፣ በጉልበት...ወዘተ ያነሱ እንደሆኑ ይሰማቸዋል።
ነገር ግን ይህን ሂደት ስለሚቀበሉት ወደ የበታችነት ኮምፕሌክስ አይመራም። አንዳንዳንድ ሰዎች አስተዳደግ ላይ የሚከሰቱ ነገሮች ይደማመሩበትና ህይወታቸውን ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ በማወዳደር ይጠመዳሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች በሚያድጉበት ጊዜ "እከሌን አታየውም?" እየተባሉ ከሌሎች ልጆች ወይም ከእህት/ወንድም ጋር እየተነፃፀሩ የሚያድጉ ከሆነ ወይም ያልተቀበሉት አካላዊ እክል ካለባቸው እድሜያቸው ከፍ ሲል የበታችነት ኮምፕሌክስ ሊፈጥርባቸው ይችላል።
'የበታችነት ኮምፕሌክስ' የሚለውን ሀረግ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠራው አልፍሬድ አድለር ነው። አድለር የበታችነት ኮምፕሌክስ የሚሰማቸው ሰዎች ሳይታወቃቸው ለማካካስ የሚደረግ ሀይለኝነት ወይም የበላይ ለመሆን የሚደረግ ከፍተኛ ጥረት ውስጥ እንደሚገቡ ይገልፃል። የበታችነት ኮምፕሌክስ ከፍ ሲል የበላይ መሆንን ለማረጋገጥ ሌሎችን የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ወደ ማድረግ ሊገፋፋ ይችላል።
የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ልዩ የሆነውን እምቅ ችሎታቸውን በማውጣት ላይ እንዲያተኩሩ ያግዛል።
ምንጭ፡ Mental wellness
የታላቁ ሳይንሳዊ እሳቤ መነሻ
***
ግዜው የ አስራሰባተኛው ክፍለዘመን ማገባደጃ አካባቢ ነበር። በግሪጎርያኑ አቆጣጠር 1687። የ 22 አመቱ የብሪታኒያ ተወላጁ አይዛክ ኒውተን በመኖሪያ ቤት ግቢው ከሚገኘው የአትክልት ስፍራ ውስጥ አንዱ የፖም ዛፍ ስር ተቀምጧል። እንደድንገት ከደረሱት ፖሞች ውስጥ አንዱዋ ከዛፉ ላይ ወድቃ የአይዛክ ኒውተን ራስ ላይ ታርፋለች። ያቺ ቅፅበት አሁን ላለንባት የፊዚክስ የላቀ ምጥቀት ምክንያት ሆነች።
አይዛክ ኒውተን ከተቀመጠበት ተነስቶ ማሰላሰል ጀመረ። 'ፍሬዋ እንዴት ልትወድቅ ቻለች?'፤ 'ወደመሬቱስ እንድትወድቅ ያደረጋት ምንድነው?' እነዚህ ጥያቄዎች አእምሮውን ይከነክኑት ጀመር። ከወራት ጥናት ቡሀላ ፍሬዋን እንድትወድቅ ያደረጋት የስበት ሀይል (Gravity) እንደሆነ አረጋገጠ።
ከጥቂት አስርት አመታት በፊት ታዋቂው ተወላጁ የጠፈር ተመራማሪ ጋሊሊዮ ጋሊሊ እንዲሁ ስለ ስበት ሀይል መኖር ሲያስተምር የነበር ቢሆንም የኒውተን ግን በሂሳባዊ ቀመር የተደገፈ እና የተብራራ በመሆኑ ተቀባይነትን አገኘ። የጣልያንኒውተን በዛው አመት 'ፕሪንሲፖ ማትማቲካ' የተባለ መጣጥፍ አሳተመ። በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ስለ ስበት ሀይል አብራርቶ ከሂሳባዊ ቀመር ጋር አስደግፎ ፅፎ ነበር።
ኒውተን የስበት ሀይልን ያየበት አቅጣጫ በግዜው የነበሩ ሌሎች ተመራማሪዎችን ያስደመመ ነበር። ፍሬዋን ከዛፉ ላይ እንድትወድቅ ያደረጋት ሀይል እና ምድራችን በፀሀያችን ዙሪያ እንድትዞር ያደረጋት ሀይል አንድ አይነት ናቸው ብሎ አሰበ፤ ይህ ሀይል የስበት ሀይል (Gravity) እንደሆነ አመነ። ፀሀይን ለአብንችልጥፋት ብንችል በቅፅበት ምድራችንም ሌሎች ፕላኔቶች ከምህዋራቸው ይወጣሉ ብሎ አሰበ። ይህ ንድፈሀሳብ ለ 250 አመታት ያክል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር።
ምንጭ፡ Airtable universe እና E.A
የኮምፒዩቲንግ ዘርፍ እና ምንነት
*******************************

ኮምፒዩቲንግ የተለያዩ ስልተ-ቀመሮች በመፍጠርና በመጠቀም አንድን አላማ ለማሳካት የሚከናወን ሂደት ነው። የተለያዩ ሶፍት ዌሮች ከማበልፀግና ሀርድዌሮች ከማምረት ጀምሮ፣ የተለያዩ መረጃዎችን በቀላሉ መቆጣጠርና ማደራጀት፣ ቅርፅ ማስያዝና ማስተዳደር፣ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በኮምፒዩተር መስራት እና የኮምፒተሮችን የማከናወን አቅም ማሳደግን ያጠቃልላል። በየጊዜው አቅሙን እያሳደገ በተለየዩ ፕላት-ፎርሞችና ዓይነቶች በመቅረብ ለተለያዩ የሳይንሳዊ ምርምሮች ቴክኖሎጂያዊ ድጋፍ በመስጠትም ላይ ይገኛል፤ ስለ ኮምፒውተሮችና የኮምፒውተር ሲስተሞች እንዴት እንደሚሰሩ፣ እንዴት እንደተገነቡ እና ፕሮግራም እንደተደረጉ በተለይም ደግሞ ከጀርባ ስላለዉ ስልተ ቀመር (አልጎሪዝም)፣ ንድፍ፣ ፕራይቬሲ እና ደህንነት የሚያጠና መስክ ነው።

ኮምፒዩቲንግ እና ኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ በተለያየ ደረጃ እየተቀያየሩ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላት ቢሆኑም አይ.ሲ.ቲ የሚያተኩረው ኮምፒውተርንና በውስጡ ያሉ አፕሊኬሽኖችን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ሲሆን ኮምፒዩቲንግ ደግሞ በአንፃሩ ንድፍና አፈፃፀማቸው (ኢምፕሊመንቴሽን) ላይ ነው።

ከ15ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ እየተስፋፋ የመጣው የኮምፒውቲንግ ፅንሰ ሀሳብና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የኮምፒውቲንግ ማሽን ስራ መጀመር የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ በዓለም እንዲንሰራፋ ምክንያት ሆኗል። የመጀመሪያው ኮምፒውቲንግ መሳሪያ ሒሳብ የሚሰራ ባለጥርስ ማሽን ነበር። ይህንን ለማሻሻል በተደረገ ያላሰለሰ ጥረት ቀስ በቀስ የኮምፒውቲንግ ስራዎችን በተቀላጠፈ መልኩ የሚያከናውኑ ማሽኖች ሊበለፅጉ ችለዋል። በተለይም ደግሞ የሰው ልጅ ለስራው በእነዚህ ማሽኖች ላይ መደገፍ በመጀመሩ የኮምፒውቲንግ ዘርፍ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ጎን ለጎንም የተለያዩ አይነት የኮምፒውቲንግ አፈፃፀሞች እድገታቸው ጨምሯል።

በዓለማችን ውስጥ ያለው የቴክኖሎጂ ምጥቀት ብዛት ያላቸው የኮምፒውቲንግ አይነቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል። ከብዙው በጥቂቱ እንደ ዩቲሊቲ ኮምፒዉቲንግ፣ ዲስትሪቢዩትድ ኮምፒዉቲንግ፣ ክላስተር ኮምፒዉቲንግ፣ ፓራሌል ኮምፒዉቲንግ፣ ግሪድ ኮምፒዉቲንግ፣ ሱፐር ኮምፒዉቲንግ፣ እንዲሁም ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህ የኮምፒውቲንግ አይነቶች ከተለምዶው የአንድ ኮምፒውተር ተግባር ወጣ ብለው ብዛት ባላቸው ፕሮሰሰሮች አማካኝነት ስራን የሚያቀላጥፉ ናቸው። ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮችን ከማገናኘት ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ፕሮሰሰሮችን አንድ ቦታ በማስቀመጥ ተፈላጊውን ስራ በፍጥነት ለማቅረብ ያስችላሉ። ከእነዚህ አሰራሮች መካከል ሱፐር ኮምፒውቲንግ በሀገር ደረጃ ትልቅ ቦታ እየተሰጠው ያለ የአገልግሎት ዘርፍ ሆኗል።
ምንጭ፡ tech viral እና si tech bufe
አርቴፊሻል ቆዳ ተሰራ
************

እንደ ማየት እና ማዳመጥም ሁሉ መዳሰስም ከሰዎች እና ከዓለማችን ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ የማይተካ ሚናን ይጫወታል፡፡የመዳደሰስ ህዋሳችንን መልሶ ሊገነባልን የሚችለው ቴክኖሎጂ haptic feedback በመባል ይወቃል፡፡

በጄሚ ፓይክ የሚመራው የReconfigurable Robotics Lab ሳይንቲስቶች ቡድን ስሜትን የሚለይ እና ለስሜት ምላሽ መስጠት የሚችል ቆዳን መስራት ችለዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ንዝረትን እና ግፊትን የሚለይ እና ለእነሱም ተገቢ ምላሽን የሚሰጥ ሲሆን ከዛ በተጨማሪም ማኛውም አደጋ ቢደርስበት እንደማንኛውም ቆዳ እራሱን የሚተካ እና የሚያክም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሳይቲስቶቹ እንዳሉት ከሆነ እንዲህ ያለ የተቀናጀ ስራን መስራት የሚችል አርቴፊሻል ቆዳ ሲሰራ የመጀመሪያው ከመሆኑም በላይ ጥቅመ ብዙ እና ታላቅ የህክምና አብዮትም ጭምር ነው ሲሉ አስረግጠዋል፡፡ በማከልም በተለይ በህክምና ወቅት ታማሚው እራሱን መግለጥ የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሲሆን የቆዳውን የግፊት እና የንዝረት ሁኔታ በመከታተል ተገቢውን ምላሽ እንድንሰጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡

አርቴፊሻል ቆዳው ከመጀመሪያ አቋሙ እስከ 4 እጥፍ ድረስ መለጥጥ የሚችል ነው ያሉ ሲሆን ይህ ለተጠቃሚው ምቾት እንዲሰጥ ይረዳል ብለዋል፡፡ ምንም እንኳ አሁን ላይ ጣት ላይ ሊጠለቅ የሚችል አርቴፊሻል ቆዳን የሰሩ ቢሆንም በቅርቡ መላ ሰውነት መሸፈን የሚችል የቆዳ ፕሮቶታይፕ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

ምንች፡- ScienceDaily
የኢትዮጵያን ሥነ-ህዝብ ፖሊሲ የሚፈትሽ አዲስ ጥናት ይፋ ሆነ
========================
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን የስነ-ህዝብ ሁናቴ የሚፈትሽ ጥናት ትናንት አመሻሽ ይፋ አድርጓል፡፡ የህዝብ ፖሊሲው ያለበትን ክፍተት ለመሸፈን ታስቦ የተሰራው ይህ ጥናት የሀገራችንን የሥነ-ህዝብ ፖሊሲ አፈፃፀም እንዲሁም የአፈፃፀም ሂደቱን ቅድመ እና ድህረ 2003 በማለት ከፍሎ በመቃኘት ምክረ ሃሳቦችን እንደለገሰ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በምልከታውም ከ2003 አስቀድሞ የነበረው የፖሊሲ አተገባበር መልካም እንደነበር አስቀምጧል፡፡ ሆኖም ከ2003 በኋላ በነበረው አፈፃፀም በርካታ ተግባራት ቢተተገበሩም ዝቅተኛ ውጤት የታየበት እንደነበር አመላክቷል፡፡ ለዚህም የፖለቲካዊ ድጋፍ መመንመን እና በስነ-ህዝብ ተቋማት ያለው ያልጠነከረ ተቋማዊ አደረጃጀትን ጨምሮ አምስት አባይት ምክንያቶች ተቀምጠውበታል፡፡
ሌላው በመድረኩ ይፋ የተደረገው የሥነ-ሕዝብ መዝገበ ቃላት ሲሆን በሀገራችን ያለውን የሥነ-ህዝብ ተኮር ውይቶችን እንዲያግዝ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በመዘዝገበ ቃላት ዝግጅቱም ከሥነ-ሕዝብና ከቋንቋ ዘርፍ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩበት፡፡
ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን በተደረገ የገንዘብና ቴክኒካዊ ድጋፍ የተሰሩት እነዚህ ስራዎች ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን ፈጅተዋል፡፡ በትናንትናው የምረቃ ስነስርዓቱ ማገባደጃም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ እና ወ/ሮ የምሰስራች በላይነህ (ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን) የመዝጊያና ምስጋና ንግግራቸውን አድርሰዋል፡፡

የ2019 3ቱ የፊዚክስ አዋርድ ተሸላሚዎችን አውቀዋቸዋል?
**********************************
የፕሪሴንትን ዩኒቨርስቲው ጀምስ ፒብል ፣ የጄኔቫ ዩኒቨርስቲው ማይክል ማየር እና የካምብሪጅ እና የጄኔቫ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነው ዲዲየር ክዌሎዝ የህዋን አዲስ ሚስጥር በማወቅ በሚል የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ ሁነዋል፡፡
የዘንድሮው የፊዚክስ ኖቤል ሽልማት በሁለት ዋና የአከፋፈል መንገድ ነበር የተሸለመው፡፡ የመጀመሪያው ግማሽ ሽልማት የስዊዲሽ 9 ሚሊዮን ክሮኖር ማለትም 9መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለፕሪሴንትን ዩኒቨርስቲው ጀምስ ፒብል የተሰጠ ሲሆን ይህም ለህዋ ሳይንስ አዲስ የአጠናን መንግድ በመቀየሱ እና አዳዲስ የምርምር አካሄዶችን በማሳየቱ ነው፡፡
ጥናቱ የፍጥረተዓለሙ የብራሀን ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያውን የፍጥረተ ዓለሙን ብርሃ ምንነት የመረመረ ነበር፡፡
ሁለተኛው የፊዚክስ ኖቤል ሽልማት ደግሞ ለጄኔቫ እና ለካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎቹ ለዲዲየር ክዌሎዝ እና ማይክል ማየር የተበረከተ ሲሆን ይህም ከሶላር ሲስተሙ ውጭ ያለ ፕላኔጊዜትን ለመጀመሪያ በማግኘታቸው ምክኒያት ለሳይቲስቶች ፈርቀዳጅ እና መንገድ ጠቋሚ የሆነ ግኝት ሆኗል በሚል ሳቢያ ነበር፡፡
ምንጭ፡- Science News
የወርክሾፕ ጥሪ
**************
October, 15 2019
Foundation of Big Data Analysis and Advanced Computing
# አዲስአበባ #ኢትዮጵያ
# AddisAbeba # Ethiopia
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከዜነሲስ ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር Foundation of Big Data Analysis and Advanced Computing በሚል የአንድ ቀን ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ ወርክሾፑ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ከከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባሉሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመሆኑም በዚህ ወርክሾፕ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ እንደምትችሉ ማሰወቅ እንወዳለን፡፡ ከአርባዎቹ እድለኛ ተሳታፊዎች መካከል ከሆኑም የ # UDEMY ስልጠናን በነፃ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ቀን፡- ጥቅምት 4 2012 (October 15 2019)
የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://docs.google.com/
forms/d/e/1FAIpQLSe6iJ-htk2LfOHQkRdxBXVc-
5UpG9Vsmj--jd2LwGs5LJ_gfg/viewform