TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)
(“ሀኪም በሌለበት” ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ)

ኒሞኒያ(የሳንባ ምች) በጣም አጣዳፊ የሆነ የሳንባ ህመም ነው፡፡ ይህ ህመም አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው በመተንፈሻ አካል በሽታዎች ከተጠቃ በኋላ የሚከሰት ነው፡፡ ኩፍኝ፣ ትክትክ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ብሮንካይትስ፣ አስም ወይም ሌላ ከባድ ህመም ለሳንባ ምች በሽታ መንገድ ይጠርጋሉ፡፡ በሽታው በህፃናትና በሽማግሌዎች ላይ ይበረታል፡፡ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ያለበትም ሰው ተጋላጭነቱ ከፍ ይላል፡፡

መለያ ምልክቶች

• በድንገት ብርድ ብርድ ማለትና የትኩሳት ስሜት፡፡
• ከላይ ከላይ መተንፈስ፣ ማቃሰት፣ አንዳንዴም ፉጨት የመሰለ ድምፅ ይሰማል፡፡ የአፍንጫ ቀዳዳዎች ከአተነፋፈስ ጋር መርገብገብ፡፡
• ትኩሳት (አንዳንድ ጊዜ አራስ ልጆች፣ ሽማግሌዎችና ደካማ ሰዎች ትኩሳት ሳይኖራቸው የሳንባ ምች ሊይዛቸው ይችላል፡፡)
• ከሳሉ ጋር ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሽሮ የሚመስል ወይም ደም ለው አክታ ይወጣል፡፡
• የደረት ውጋት (አንዳንድ ጊዜ) ይኖራል፡፡
• የህመምተኛው ጉስቅልና ጎልቶ ይታያል፡፡
• ፊት ላይና ከንፈሮች አካባቢ ሽፍታ ይወጣል፡፡

ህክምና

በሽታው መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በሃኪሙ የታዘዘውን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ ይገባል፡፡ መድሃኒቱን ጨርሶ ባለመውሰድ የበሽታው ደረጃ ከፍ ሊል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

ሼር አድርጉት (Sharing is Happiness)
ስለጨጓራ ሕመም
===”===”

የገጻችን ቤተሰቦች… በመልዕክት መቀበያችን በደረስን ጥያቄ መሰረት ዛሬ ስለጨጓራ ህመም መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል፡፡ በቅድሚያ ሼር አድርጉት፡፡

► መንስኤዎች

የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶች ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

✔️ ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
✔️ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
✔️ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
✔️ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
✔️ ጭንቀት
✔️ ሲጋራ ማጤስ
✔️ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት

► የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡

✔️ የማቅለሽለሽ ስሜት
✔️ የሆድ መንፋት ስሜት
✔️ ማስመለስ
✔️ የምግብ አለመፈጨት
✔️ የማቃጠል ስሜት በተለይ ከምግብ በኋላ
✔️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔️ የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው

ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡

✔️ የማላብ ስሜት
✔️ የልብ ምት መጨመር
✔️ የትንፋሽ ማጠር
✔️ ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
✔️ ደም ማስመለስ
✔️ ደም የቀላቀለና ከወትሮው የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡

እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡

የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡
አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ9 ልምዶች
1- ልንተኛ ስንል መመገብ
(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡)
2- ያልተመጠነ እንቅልፍ
(ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡)
3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ
(በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ )
4- ጭንቀት እና ውጥረት
(አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡)
5- በፍጥነት መመገብ
(በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ )
6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት)
(የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ )
7- ቁርስን መዝለል
(የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡)
8- የበዛ ጨው መጠቀም
(ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ )
9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
(የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው።
ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን እንዴት መክፈት እንችላለን?

አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡

Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡

Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡

Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot). በትክክል ይሰራል…
TechIn2 pinned «ጠቃሚ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን እንዲሁም የጤና ምክሮችን በየቀኑ እናደርሳችኋለን። ወዳጅ ጓደጎቻችሁንም ወደዚህ ቻናል ይጋብዙ።»
የጨጓራ በሽታን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 3 የቤት ውስጥ ውህዶች

ሰሞኑ የበዓል ነው፡፡ አምሮት የሚቀሰቅሱ ቅባታማ እና በርበሬያማ ምግቦቻቻንን ባላየ ማለፍ የምንችልበት አቅም ያለን አይመስልም፡፡ ስለዚህ የልብ አድርሶ የመሸመበት ማደር ነው ብለን እጃችንን ሰብሰብ አድርገን የገባንበት ካለን እንግዲያውስ ለጨጓራችንም መላ እንፈላልግለት፡፡ እነዚህን በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የሚቻሉትን ውህዶች በመጠቀም እርፍ ማለት እንችላለን፡፡

1- የድንች ጭማቂ

(ድንቹን በ ጁስ መፍጫ ከፈጨነው በኋላ ውሃውን በቀን አንዴ 3 ወይንም 4 የሾርባ ማንኪያ መጠጣት ፡፡ ህመማችን ባስ ካለ በ ቀን ሁለቴ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ የጨጓራችንን የ ph መጠን የሚያረጋጋው ሲሆን የጋዝ ምርቱን እንዲቀንስ በማድረግም የማቃጠል ስሜትን ያጠፋል፡፡

2- የሩዝ ውሃ

(ሩዝ የተቀቀለበትን ውሃ ለተለያየ የህክምና ዓላማ መጠቀም አሁን አሁን ዓለማችን ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡ትንሽ ሩዝ በውሃ ከጣድን በኋላ ሩዙ እንደመብሰል ሲል የውሃው ቀለም ነጭ ይሆናል ያኔ ውሃውን አጥልሎ በመጠጣት የማቃጠልን ስሜት ማጥፋት ይቻላል፡፡ )

3- ማር

(2 የሾርባ ማኒኪያ ንፁህ ማርን ለብ ባለ ውሃ በጥበጥ አድርገን በመውሰድ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ልናገኝ እንችላለን፡፡ህመሙ ሊጀምረን አከባቢ ብናደርገውደግሞ የበለጠ ፍቱን እንደሆነ ይታመናል፡፡
መጽሀፍትን በነፃ
ኦንላይን በቀላሉ መጠቀም ለሚፈልጉ (በቅርቡ)

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል፣ ዲጂታል የሆነ ቤተ-መጽሀፍት የገነባ ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይደረጋል፡፡ እዚሁ በአገራችን የተገነባው ዲጂታል ላይብረሪው የሚከተሉትን የላይብረሪ አገልግሎቶችን ያገኙበታል፤ library.stic.et ብለው ይጎብኙ፤

• የመማሪያ መጽሀፍትን፣ በማህበራዊ ሳይንስም በተፈጥሮ ሳይንስም ዘርፍ

• ጥናታዊ ጽሁፎችን፣ ጆርናሎችን

• የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ህጎችን፣ ድንቦችንና መመሪያዎችን

• የሀገር ውስጥ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መረጃን

• አለም አቀፍ የፓተንት መረጃዎችን በአንድ ላይ ያገኙበታል

በዚህ አጋጣ ዌብሳይቱ_በይፋ_ስራ_የሚጀምረው_ጥር_15_እንደሆነ_ልንገልፅላችሁ_እንወዳለን፡፡

library.stic.et በመጎብኘት የዕውቀት አድማስዎን ያስፉ!!
—----------------------------------------------------------------------

• Educational Books For both Natural and Social sciences
• All kind Research papers
• Local and International Law books and Manuals
• Informations about Mega Projects in Ethiopia
• International patent informations
• Visit here: library.stic.et
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ

5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች

በኮምፒዩተር ሳይንስ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ትክክለኛ የድረገጽ ምንጭ ማወቅ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በየግዜው ዓለምን እያጥለቀለቀ ካለው አዳዲስ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤት ጋር እራስን እኩል ለማስኬድም ሆነ ተጨማሪ ክህሎቶችን ለማግኘት ትክክለኛ የኢንተርኔት ድረገጽ ማግኘት እጅጉን ወሳኝ ነው። ለዚህም ሲባል እነዚህን አምስት ምርጥ የኮምፒዩተር ሳይንስ ድረገጾችን እንሆ ብለናል።

1᎐ Stanford Engineering Everywhere(SEE)

ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ሲሆን ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

2᎐ MIT Open Courseware

የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

3᎐ GitHub.com

GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።

4᎐ W3 Schools

ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት የሚሰጥ ይሰጣል። በተጨማሪም በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

5᎐ Codecademy

አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
ምንጭ፡ The Best Master’s Degrees
መረጀውን ሼር ያድርጉ፡
የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎች

የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው አንዱ ፈተና ነዉ። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

ምንም እንኳ ኩባንያው ምርቶቹን እያሻሻለ ቢሆንም በአሜሪካ ብዙ ክሶች ተመስርተውበታል።

ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት በቶሎ የሚሞሉ ሊቲየም አየን ባትሪዎችን ሲሆን ዲዛይናቸውም ባትሪዎቹ ተጠጋግተው እንዲቀመጡ የሚያደርግ ነው።
የስማርት ስልኮች ግፅታና ዲዛይን ቶሎ ቶሎ መቀያየር ማሻሻያውን እንዳከበደውም እየተነገረ ነው። በርግጠኝነት ይህ ነው የሚባል ነገር ባይኖርም የስማርት ስልኮችን እድሜ ለማርዘም የሚረዱ አማራጭ መፍትሄዎች አሉ።

1.ደካማ በይነ መረብ

ስልኮዎ በየሄዱበት ጥሩ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) መስመርን ለማግኘት ይሞክራል። በተለይም ደካማ የበይነ-መረብ አገልግሎት ባለበት ወይም አንድ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች የገመድ አልባ ኢንተርኔትን (ዋይ ፋይ) ለመጠቀም ሲሞክሩ ስልክዎ ሙከራውን ያከረዋል።
ምርጥ የሚባል መፍትሄ ባይሆንም ስልክዎን ኤርፕሌን ሞድ ላይ ማድረግ ጥሩ ኢንተርኔት ለማግኘት እየታገለ ያለው ስልክዎ ባትሪ እንዳይጨርስ ይረዳዋል።

2. አንዳንድ መተግበሪያዎች (አፕልኬሽኖች)

አንዳንድ መተግበሪያዎች ባትሪ ይጨርሳሉ። ስለዚህ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎችን መዝጋት የባትሪን እድሜ ያረዝማል።በተጨማሪም ባትሪ የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ባትሪ እየጨረሰ ያለውን መተግበሪያ መለየት ያስፈልጋል።

3. ያሉበትን ቦታ አመልካች (ጂፒኤስ)

የቦታ አመልካችን (ጂፒኤስ) ማብራትም ባትሪ የሚጨርስ ነገር ነው። እንደ ትዊተር ያሉ አፕልኬሽኖች ደግሞ እርስዎ ሳያውቁት ሁሉ ያሉበትን ቦታ መዝግብው ይይዛሉ።ስለዚህ ያሉበትን ቦታ የሚመዘግቡ መተግበሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ የማይፈልጓቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል።

4.ከፍተኛ ሙቀት

ሊቲየም ባትሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጡ በደንብ አይሰሩም። ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው አየን ባትሪው ቶሎ ቶሎ ቻርጅ እንዲደርግ ያስገድዳልና።ስለዚህ ስልክዎ ለከፍተኛ ሙቀት ወይም ለከፍተኛ ቅዝቃዜ እንዳይጋለጥ ማድረግ ዓይነተኛ መፍትሄ ነው።

5. ትልልቅ ስክሪኖች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስልኮች ትልልቅ ስክሪኖች እንዲኖራቸው እየተደረገ ነው። ይህ ትልቅ ስክሪን ሲከፈትና ሲበራ ባትሪ ይጨርሳል። ስለዚህም የስክሪኑን የብርሃን መጠን መቀነስ ጠቃሚ ነው።ስክሪኑን ማጥፋትና ቶሎ ቶሎ ስልክዎን አለመመልከትም ሌላው መፍትሄ ነው።

6. ከፍተኛ ድምፅ

የመተግበሪያዎች ወይም የስልክ ጥሪዎች ድምፅ ከፍተኛ ከሆነ ባትሪ ይጨርሳል። አብዛኛውን ጊዜ የድምፅ ነገር ስልክዎ ባለው ስፒከር የሚወሰን ይሆናል።የጆሮ ማዳመጫ መጠቀምና በሚያዳምጡበት ወቅት የሌሎች መተግበሪያዎችን ድምፅ ማጥፋትም ጥሩ ነው።

7. ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ

በፊት በፊት ስልክዎ ባትሪ እስኪጨርስ ከተጠቀሙ በኋላ ቻርጅ ማድረግ ለስልኩ ባትሪ እድሜ ተመራጭ እንደሆነ ይነገር ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ሌላ መረጃ ብቅ ማለት ጀምሯል፡፡ ይህም ከስር ከስር ባትሪ ሳይጨርስ ስልክን ቻርጅ ማድረግ የባትሪን እድሜ ያረዝማል የሚል ነው፡፡ የባትሪዎ መጠን ከግማሽ በታች ዝቅ እንዳይል ቻርጅ ቢያደርጉ የባትሪዎን እድሜ እንደሚገዙ የሞባይል ስልኮች ባለሙያዎች ይመክራሉ።

እርግጠኛ መፍትሄዎች

ሁሉም የሞባይል አምራቾች የሚስማሙበት ዋነኛ መፍትሄ ስልክዎን ባትሪ ሃይል ቆጣቢ ሞድ ላይ ማድረግን ነው። ይህ ማለት ደግሞ የስልክዎ ስክሪን ብርሃን ይቀንሳል፣ ስልክዎ ንዝረት ያቆማል፣ ብዙ ማሳወቂያዎች (ኖቲፊኬሽን) አይደርስዎትም ማለት ነው። ያሉበትን ቦታ አመልካችም አገልግሎት አይሰጥም።ነገር ግን ባትሪዎ በአሁኑ ወቅት የደከመ ከሆነ እነዚህ ነገሮችን ማድረግ ብዙም ለውጥ አያመጣም፤ ያለው አማራጭ የስልክዎን ባትሪ መቀየር ብቻ ነው።

ምንጭ፡ ቢ.ቢ.ሲ አማርኛ
መረጃውን ለወዳጆ ያካፍሉ፡
የወንድ ልጅ መኃንነት … ምንነት፣ መንስኤና መፍትሄ

የወንድ ልጅ መኃንነት በተለያዩ ምክኒያቶች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ መንስዔዎች ግን የመራቢያ አካል በተገቢው መንገድ አለመነሳት፣ የወንዴ ዘር አረጫጨት ችግር እና የወንዴ ዘር ምርት ጤነኛ አለመሆን ናቸው፡፡ አያንዳንዳቸው ችግሮች የራሳቸው የሆነ ዘመናዊ የህክምና መንገድ የተበጀላቸው ሲሆን ለዘመናት በባህላዊ መንገድም ሲታከሙ ቆይተዋል፡፡ ስቲክ ኢትዮጲያም ዛሬ ለወንድ ልጅ መኃንነት የሁለት ሶስተኛውን ድርሻ የሚወስደውን የወንዴ ዘር አመራረት ችግርን ምንነት እና ከዘመናዊ ህክምና ጎን ለጎን በመሆን ሊያገለግሉ የሚችሉ ተፈጥሯዊ መፍትሄዎችን እንካችሁ ይላል፡፡
የወንዴ ዘር ምርት ችግር ሲባል የወንዴ ዘር ጥራት፣ መጠን እና እንቅስቃሴ ችግር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ጤነኛ እና በቂ የሆነ የወንዴ ዘር ምርትን ከሚያፋጥኑ ምግቦች መሀከል 5ቱን እንሆ ፡-
1- ቲማቲም፡-
ቲማቲም እንዲህ ያማረ ቀለም እንዲኖረው ምክኒያት የሆነው ላኮፒን የተሰኘው ንጥረ ነገር ከዛ ጎን ለጎን ለወንድ ልጅ ወላድነት ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ይህ ላኮፒን የተሰኘው ንጥረ ነገር እስከ ሰባ በመቶ ድረስ የወንዴ ዘር ምርትን ያሳድጋል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር የምርቱን መጠን ከማሳደጉም በላይ የወንዴ ዘርን እንቅስቃሴ እና የመዋኘት ዓቅም ይጨምራል፡፡

2- የዱባ ፍሬ
የዱባ ፍሬ በውስጡ ለወንዴ ዘር መጠን አስፈላጊ የሆነውን የዚንክ ንጥረ ነገር በርከት አድርጎ የያዘ በመሆኑ የወንዴ ዘር መጠንን ለማሳደግ ዓይነተኛ አማራጭ ነው፡፡ የዱባ ፍሬ አወሳሰድን በተመለከት ፍሬውን በቀጥታ ከመብላት በተጨማሪ ከሰላጣ ላይ በመበትን መጠቀም አልያም በመቁላት ከሌሎች ጥራጥሬዎች ጋር መውሰድ ይቻላል፡፡ ይህ ፍሬ በቀደምት ህንዳዊያን እና ቻይናዊያን የበሃል መድሃኒትነት ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የወንዴ ዘር መጠንን ከማሳደግ በተጨማሪ ለሌሎች የመራቢያ አከባቢ በሽታዎች እንደ መድሀኒትነትም ይጠቅማል፡፡

3- ሮማን
ሮማን በውስጡ የወንዴ ዘርን ለማጓጓዝ የሚጠቅመውን ፈሳሽ የሚጎዱ ፍሪ ራዲካል የተሰኙትን ጎጂ ውህዶች ለመዋጋት የሚያስችሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የያዘ በመሆኑ የወንድ ልጅን የመካንንት መጠን የመቀነስ ጉልበት አለው፡፡ የሮማን ጭማቂ በጥንታዊያን ግሪኮች እና ግብፆች ዘንደ የወላድ መሳሪያ ተብሎ ይጠራ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡

4- ነጭ ሽንኩርት
ነጭ ሽንኩት ለብዙ የጤና እክሎች እንደ መፍትሄ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ቪታሚን ቢ 6 እና ሲሊኒየም የተሰኙ ሁለት ቪታሚኖችን የያዘ ሲሆን እነኚህ ቫይታሚኖች ለ ጤናማ የ ወንዴ ዘር ምርት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ፡፡ ከዛ በተጨማሪም ነጭ ሽንኩርት የደም መተላለፊያ ቱቦዎችን የማጽዳት በሀሪ ስላለው ወደ መራቢያ አካል የደም ፍሰትን በመጨመር ጥሩ ለሆነ የስሜት ዝግጅት ይረዳል፡፡

5- ስፒናች
ስፒናች የተሰኘው ይህ የቆስጣ ዝርያ በውስጡ በቂ የሆነ የፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገር በመኖሩ ምክኒያት ጤናማ የሆነ ወንዴ ዘር ምርት እንዲኖር ይረዳል፡፡ይህ የፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገር በበቂ ሁኔታ ሰውነት ውስጥ የማይገኝ ከሆነ ጥራት ያለው የወንዴ ዘር ምርት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ማለትም በቂ የሆነ የወንዴ ዘር ብዛት ቢኖርም ከጥቅም አንፃር ሲታይ ግን የከሸፈ ነው፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ከስፒናች በተጨማሪ ብዙ ቅጠላማ አትክልቶች ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ አዘውትሮ መጠቀም ይመከራል፡፡
መረጃዉን ለወዳጆ ያካፍሉ፡፡

ምንጭ፡ healthista,healthline, babycenter
TechIn2 pinned «የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎች የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው አንዱ ፈተና ነዉ። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ምንም እንኳ ኩባንያው ምርቶቹን እያሻሻለ ቢሆንም በአሜሪካ ብዙ ክሶች ተመስርተውበታል። ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት…»
የእንግሊዘኛ ሰዋሰው(grammer) ለመረዳት እና ለመማር ሚጠቅሙ
4 ነፃ ድህረገፆች

1- EnglishGrammar.org
ይህ ድህረገፅ ለመማሪያነት የሚረዱ ቪድዎችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የእንግሊዘኛ እውቀት ላላቸው ሁሉ የሚሆኑ አጀንዳዎችን ይዳስሳል፡፡ በተጨማሪም እንግሊዘኛን በተመለከተ ያሏችሁን ጥያቄዎች ሁሉ በ ኮሜንት ባር ላይ መፃፍ የሚቻል ሲሆን በውስጥ መሰመርም መልዕክት መላክ ይቻላል፡፡

2- English Grammar Secretes
ይህ ከላይ የጠቀስነው ድህረገፅ የሌለወን ሁሉ ጨምሮ የያዘ ሲሆን ከእያንዳንዱ ትምህርት በኃላም የተማርነውን ምንለማመድበት መልመጃዎች አሉት፡፡

3- UsingEnglish.com
የተማሩትን መልሶ መለማመድ ከሚለው ሀሳብ ሳንወጣ ይህ ድህረገፅ ፕሪንት ተደርገው የሚወሰዱ በግል እራስን ማለማመጃ ጥቄዎችን ያዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር የሚማማሩበት መድረክ ያለው ሲሆን የቋንቋው ኤክስፐርቶችንም አግኝተው ጥያቄዎችን መጠየቅ የሚችሉበት አሰራር አመቻችቷል፡፡

4- Learn English by British Council
ብሪቲሽ ካውንስል በዓለም አቀፍ ደረጃ የእንግሊዘኛ እውቀትን ለማሳደግ ከሚሰሩ ተቋማት ውስጥ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ ተቋም ሰዋሰውን በ ደህረገፅ ከማስተማርም በተጨማሪ የተለያዩ ፎረሞችን እና ትምህርታዊ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት እና የእንግሊዘና ማህበረሰብ በመፍጠር እንግሊዘኛን በ ተግባር እንዲማሩ ይረዳል፡

ሼር በማድረግ ያወቁትን ያካፍሉ

ምንጭ ፡- my English Teacher.eu