የTECHIN ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል
****************************
ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ የቆየው የተቋማችን ቤተሰቦች የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በመርሀ ግብሩ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ስለ ተቋሙ ህጋዊ ቁመና፣ የተሰጡት ኃላፊነቶች እና ተቋማዊ መዋቅር ላይ ሰፊ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን በሰራተኛው በኩልም ሰፋ ያሉ ጥያቄዎች ተነስተው ለውይይት ቀርበዋል፡፡
በከሰዓቱ መርሀግብርም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዋና አማካሪ የሆኑት ዶክተር እሸቴ አበበ በፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዋናነትም የውጤት አሰጣጥ ሂደቶች ምን መምሰል እንደሚኖርባቸው እና የስትራቴጂክ ግቦች በምን መልኩ መቀረፅ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ እንዳሉትም የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በአዲስ ተስፋ ትልልቅ ሃገራዊ ትሩፋቶች ለማስመዝገብ እንዲችል ለስምንት ተከታታይ ቀናት የተደረጉት የማነቃቂያ ስልጠናዎች ትልቅ ዋጋ እንደነበራቸው ያነሱ ሲሆን እያንዳንዱ ሰራተኛም ጥንካሬ በተሞላበት መንፈስ፣ በእኔነት ስሜት እና የተሰጠውን ስራ በአግባቡ በመወጣት ለተቋሙ ስኬት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ታዳጊዎቹ የኢትዮጵያ ተስፉዎች የሮቦት ውድድር አድርገው ተሸለሙ
=================
ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ በሮቦቲክስ እና ፕሮግራሚንግ ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ አስመርቋል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉት እድሜያቸው ከ6-18 የሆኑ ታዳጊ ተማሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተከፍለው የተወዳደሩ ሲሆን ከአንድ እስከ ሦስት የወጡትም ከክብር እንግዳው እጅ የምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል፡፡
በክብር እንግድነት የተገኙት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ የትምህርት ስርዓታችን ችግር ፈቺ ተማሪዎችን ማውጣት አለመቻሉን ጠቅሰው መሰል ስልጠናዎች ተማሪዎች ወደፊት በምን መስክ መሰማራት እንዳለባቸው የሚለዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በተቋም ደረጃ የስታርታፕ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ያሉት አቶ ሳንዶካን ከኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ጋራም በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ታዳጊዎችን በሮቦቲክስ እና ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ በማሰልጠን ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ተማሪዎችን በመደበኛ እና የክረምት መርሃ ግብር ተቀብሎ በማተናገድ ላይ ነው፡፡ ስልጠናዎቹም ተማሪዎቹን በሮቦቲክስ ዙሪያ ዕውቀትን ከማስጨበጥ ባሻገር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ክህሎታቸውን እንደሚያዳብሩ ተደርገው እንደሚሰጡ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰናክሪም መኮንን (ሰናይ) ገልፀውልናል፡፡

መፅሐፍትን ተጋበዙልን
================
የቴክ ሳይንስ መፅሐፋችን አስራ ስድስተኛው ቅፅ ይህን ይመስላል፡፡ በውስጡ ከኢትዮጵያ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና አማራጭ ቴክኖሎጂዎች አንስቶ፣ የአረንጓዴ ከተማ ፅንሰ ሃሳብን፣ የባንክን ስራ ስለሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ሌሎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፋፊ ፅሁፎችን ከአጫጭሮች ጋር በማዋሃድ ወጥቷል፡፡ መፅሐፍቶቹን ከታች የተቀመጠውን የዲጂታል ቤተ መፅሐፍታችን ሊንክ በመጠቀም በሶፍት ኮፒ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በሌላ በኩል ህትመቱን በቅርቡ በሐበሻ፣ ጎልደን፣ ገዳ እና ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች፣ እንዲሁም በተለያዩ ቤተ መፅሀፍት እና የመንግስት ተቋማት በኩል ማግኘት ይችላሉ፡፡
http://library.techin.gov.et/web/dl-site/stic-resources/-/document_library/Y9QR0tiVPdYe/
view_file/4926068?_com_liferay_document_l
ibrary_web_portlet_DLPortlet_I
NSTANCE_Y9QR0tiVPdYe_redirect=http%3A%2F%2Flibrary.techin.gov.et%2Fweb%2Fdl-site%2Fstic-resources%2F-%2Fdocument_library
%2FY9QR0tiVPdYe%2Fview%2F67269
7%3F_com_liferay_document_library_web_portlet
_DLPortlet_INSTANCE_Y9QR0tiVPdYe_redirect%3Dhttp%253A%252F%252Flibrary.techin.gov.et%252Fweb%252Fdl-site%252Fstic-resources%253Fp_p_id%253Dcom_liferay_document_libra
ry_web_portlet_DLPortlet_INSTA
NCE_Y9QR0tiVPdYe%2526p_p_lifecycle%253D0%2526p_p_

የዓይን ምርመራ በማካሄድ ብቻ ለአልዛይመር በሽታ ተጋላጭ መሆን አለመሆንዎን ማረጋገጥ ተቻለ፡፡
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሳንዲያጎ የህክምና ት/ቤት በስብቴበር 9/2019 Neurobiology of Aging በተሰኘው የጥናት ዘርፍ ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ የግልሰቡን ብሌን በመመርመር እና ለመለጠጥ የሚወስድበትን ጊዜ በማየት ብቻ ግለሰቡ ለአልዛይመር እንደተጋለጠ ማወቅ ይቻላል ብለዋል፡፡
ይህ የብሌን በፍጥነት ያለመለጠጥ እና ያለመሰብሰብ ችግር የአልዛይመር በሽታ ያለበት ሰው የበሽታውን ምልክት ከሚያስይበት ከ 10 ዓመታት በፊት የሚታይ በመሆኑ ግለሰቡን ከበሽታው በቀላሉ መታደግ እና በቀላል ዋጋም ማከም እንዲቻል ይረዳል ብለዋል፡፡
ከመጠን በላይ በሆነ የፕሮቲን ክምችት ሳቢያ የሚከሰተው ይህ የአልዛይመር በሽታ የዓለም ህዝብን እያስጨነቀ ያለ እና ባለሞያዎችንም እረፍት እየነሳ ያለ ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም በአዕምሮ ውስጥ ያለው የፕሮቲን ክምችት በቅድሚያ የዓይን ብሌንን እንቅስቃሴ በመግታት የሚጀምር በመሆኑ ግለሰቡ ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት የዓይን ምርመራ በማድረግ እና የብሌኑን እንቅስቃሴ ብቻ በመለካት ሊደረስለት ይቻላል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily

የልጅነት ማብቂያ ዕድሜ ስንት ነው?
የ Murdoch Children’s Research Institute የጉርምስና ጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩት ፕሮፌሰር ሱዛን የዓለም የጤና ድርጅት ለጉርምስና ጤና ትኩረት አይሰጥም ሲሉ ተችተዋል፡፡
የልጅነት ማብቂያ ዕድሜ ስንት ነው? የሚለው ጥያቄ በዓለም የጤና ድርጅት በአግባቡ ባለመመለሱ ምክኒያት አገራት የራሳቸው የሆነ የእድሜ ክልል አበጅተው እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ፕሮፌሰሯ አክለውም የህፃናት ህክምና ላይ የሚሰለጥኑ ባለሞያዎችን በጉርምስና ህክምና ላይም ጨምረን ማሰልጠን ካልቻል በልጅነት ማብቂያ እና በጉርምስና መባቻ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ጤና መታደግ አይቻለንም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ምንም እንኳ የዓለም የጤና ድርጅት የጉርምስና እድሜ ክልል ከ 10 – 19 ዓመት ድረስ ያለው ነው ቢልም በህፃናት ህክምና ባለሞያዎች በአሁኑ ሰዓት እየታከሙ የሚገኙት ታካሚዎች ዕድሜ በወል የሚታወቅ ካለመሆኑ ጋር በጉዳዪ ላይም በቂ የሆኑ ጥናቶች እየተደረጉ አይደለም፡፡
የ Murdoch Children’s Research Institute ተመራማሪዎች የኦንላይን ሰርቬይ በመዘርጋትና በ115 አገራት የሚገኙ 1372 የህፃናት ህክምና ባለሞያዎችን (pediatricians) ያሳተፈ ጥናትን ያከናወኑ ሲሆን በስተመጨረሻም `The Age of Paediatrics' የሚል ጥናት ለህትመት አብቅተዋል፡፡
በጥናቱ ላይም አገራት ወጥ የሆነ የእድሜ ጣሪያ የሌላቸው እንደሆነ የተስተዋለ ሲሆን ለምሳሌ ያህል ደቡብ አፍሪካ ትንሹ የዕድሜ ጣርያ ያላት አገር በመባል የተመዘገበች ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የጉርምስና የእድሜ ጣሪያ 11.5 ዓመት ነው፤ በተቃራኒው አሜሪካን ደግሞ ትልቁ የእድሜ ጣሪያን ያስመዘገበች አገር ስትሆን የአሜሪካን የጉርምስና የዕድሜ ጣሪያ 19.5 ዓመት ነው፡፡
ተመራማሪዎች ከየአገራቱ የተገኙትን የጉርምስና

ትዊተር በሺዎች የሚቆጠሩ ሐሰተኛ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ
===================================
በመንግስት በመደገፍ ጭምር ሐሰተኛ መረጃን ሲያሰራጩ አጊኝቻቸዋለው ያላቸውን ብዙ ሺህ አካውንቶች በመላው ዓለም እንደዘጋ ባሳለፍነው ሳምንት መባቻ አስታውቋል፡፡ ከነዚህ ገፆች ውስጥ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ሳውዲ የሆኑ እንዲሁም በሆንግ ኮንግ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ አመፅ ለማላበስ እየሰሩ ናቸው ያላቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል፡፡
የመዘጋት እጣ ፈንታ ከደረሳቸው የመካከለኛው ምስራቅ አካውንቶች መካከከል በግብፅና አረብ ኢምሬቶች የሚንቀሳቀሰው DotDev የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከፍቶ የሚቆጣጠራቸው 273 አካውንቶች (ተገለባባጭ የመረጃ ስራን በማከናወን) እንዲሁም በአረብ ኢምሬቶች የሚገኙም 4,258 አካውንቶች ተመሳሳይ እጣ ደርሷቸዋል፡፡ ከሳውዲ መንግስትና በስሩ ካሉ ተቋማት ጋር በቅርበት የተቆራኙ በተለይም ከልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ጋር የተገናኙ አካውንቶችም በትዊተር ኢላማ ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ አፍቃሪ ሳውዲ አካውንቶች ሳውዲ አረቢያና አጋሮቿ በየመን ከሚያደርጉት ጦርነት አንስቶ ከኢራን እና ኳታር ጋራ ከገቡበት ማለቂያ የለሽ ትግል የሳውዲና አጋሮቿን ገፅታ ከመገንባትም ባለፈ የሳውዲን መንግስት መልዕክቶች ማስተላለፊያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡
በሆንግ ኮንግ ለወራት በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ ረገድ ትዊተር ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ያለውን እይታ ለመከፋፈል የሚጥሩ 4,302 አካውንቶችን የለየ ሲሆን ህዝባዊ መከፋፈሉን በማፋፋም ላይ የሚሰሩ ከ200,000 በላይ ሐሰተኛ አካውንቶችንም ማግኘት ችሏል (ሆንግ ኮንግም ሆነ ፌስቡክ በሰፊው/Mainland ቻይና መታገዱን ልብ ይሏል)፡፡ ትዊተር እነዚህን በቻይናዊያን የሚመሩ አካውንቶች በመዝጋት እና ፀጥ ማሰኘት ላይ የሰራው ስራ ታድያ በሰፊው/Mainland ቻይና አውንታዊ እይታ አልገጠመውም፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ ተግባር በታላላቆቹ የማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ዘንድ እየተለመደ ሲመጣ ፌስበኑክም ከጥቂት ወራት በፊት ተመሳሳይ ርምጃን የፕሮፖጋንዳ ስራን ሲሰሩ አግንቻቸዋለው ባላቸው መካከለኛው ምስራቅ እና ሆንግ ኮንግ በቀል አካውንቶች ላይ መውሰዱ ይታወሳል፡፡ ከቻይናና መካከለኛው ምስራቅ በተጨማሪም በኢኳዶር ከገዢውን ፓርቲ የተዛመዱ 1019 አካውንቶች የተዘጉ ሲሆን በሌሎች አንዳንድ ሐገራትም መሰል ቅጣት ተፈፅሟል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

self-defense ከጭንቀት ለመዳን
_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1978 ዓ.ም ነበር የ 18 ዓመቷ ሳቫጅ ከትውልድ አገሯ ፈንሳይ ወደ እየሩሳሌም የተጓዘችው፡፡ እንግድነት እንዳይሰማት ያደረጋት ባለውለታዋን እንዳገኘት የተሰማትም ያኔ ነበር፤የ18 ዓመቱ የባስ ሹፌር ለ3 ተከታታይ ወራት አገሪቷን ሳይሰለች አስጎበኛት፡፡
"ቅን እና ትሁት ነገር ነበር" ትላለች ሳቫጅ እሱን ስትገልጸው ፤ በእንደዛ መልኩ አገሪቷን ካስጎበኘኝ በኋላ ወላጆቹ ጋር እንድተዋወቅ ወደ ቤቱ ሲጋብዘኝ ሳላንገራግር እሺ አልኩት ባለኝ ሰዐትም እዛ ተገኘሁ ለሰዓታት ስንስቅ እና ስንጫወት ከቆየን በኋላ ግን 6ኛው ህዋሴ አንዳች ነገር ሹክ አለኝ ጥሩ ነገር ሊፈጠር እንዳልሆነ ተረዳሁ ወዲያው በበሩ በኩል 4 ጎረምሶች ወደ ቤት ገቡና በሩን ከውስጥ ቆለፉት፤ ነገሩ እንዳበቃ ተረዳሁ እነዚህ ሰዎች ይህንን ነገር በተደጋጋሚ አርገውት እንደሆነም እርግጠኛ ሆንኩ፡፡
ሳቫጅ በዛኑ ዕለት ማታ ወደ አገሯ ፈረንሳይ ተመለሰች በተደጋጋሚ እራስ የማጥፋት ሙከራም አደረገች ይህ ሁኔታ ከባድ ወደ ሆነ ጭንቀት እና መረበሽ ስላመራትም የአዕምሮ ሃኪም ጋር እና የምክር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር መመላለስ ጀመረች፡፡ ይሁንና እንዲያረጋጓት ታስበው የተሰጧት መድሃኒቶች ሊጠቅሟት አልቻሉም ፡፡ ምንም እንኳን በሌሎች አማራጮችም እራሷን ለማከም ብትሞክርም የዛን ዕለት ክስተትን ወደ አዕምሮዋ እንዳይመጣ ማድረግ ግን አልቻለችም ሳቫጅየ post-traumatic stress disorder (PTSD) ክፉኛ ተጠቂ ሆነች፡፡
post-traumatic stress disorder ማለት ከአዲንት አደጋ በኋላ የሚከሰት ከባድ የሆነ የጭንቀት በሽታ ሲሆን በዚህ በሽታ በዓለማችን ውስጥ በየዓመቱ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ከዛ በላይ የሚሆኑ ደግሞ በበሽታው ይሰቃያሉ፡፡ በአሜሪካን 1.4ሚሊዮን ሰው በጥቃት ሳቢያ ጉዳት ደርሶበት ወደ ድንገተኛ ክፍል የሚገባ ሲሆን በ አውሮፓ ደግሞ 670,000 የሚሆን ያክሉ ሆስፒታል ይመጣል፡፡
በ1996 ሳቫጅ ተመልሳ ወደ እስራኤል አቀናች ምናልባትም ወደዛ በመቅረብ ችግሩን መጋፈጥ ትችል ከሆነም ብላ በወሲባዊ ጥቃት የተጎዱ ሰዎች የሚታከሙበት ተቋም ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ማገልገል ጀመረች ተጠቂዎች አድማጭ ያስፈልጋቸዋል አኔ ባለመናገሬ አልተሰማሁም አልተረዳሁምም ስትል ለሚጠይቋት ሁሉ መናገር ጀመረች፡፡
በ2006 አንዲት ጓደኛዋ ኢልሃቪቭ የተሰኛ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እራስ የመከላከል ብቃትን የሚያስተምር ተቋም ውስጥ እንድትሳተፍ ጠየቀቻት፡፡ ሳቫጅ ስትናገር እኔ ድብድብ ደግሞ ምን ሊያረግልኝ ብዬ ጥቆማዋን አጣጥዬ የነበር ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ተቀላቀልኩ ፤ ያኔ የኔ ህይወት ወደ ኋላ ላይመለስ ተቀየረ ትላለች፡፡
በሃርቫርድ የህክምና ትምህርት ቤት የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እራስ የመከላከልን ስልጠና እንደመስጠት የሚረዳ አንዳች ትምህርት የለም፡፡ ይህ ስልጠና ከፍርሃት ነፃ እንዲሆኑ ከመርዳቱም በላይ በዓይነ ህሊናቸው የሚስሉትን ክፉ አጋጣሚ በአካላቸው አፍርጠው እንዲጥሉት ስለሚረዳቸው ፈጣን በሆነ ሁኔታ ከዚህ እንዲያገግሙ ይረዳቸዋል፡፡
ምንም እነኳን ሳቫጅ በወቅቱ ስለዚህ ጥናት የምታውቀው ነገር ባይኖርም እዛ ውስጥ በፅናት በመቆየት እና በመስራት እራሷን ሙሉ ለሙሉ ለማከም የቻለች ሲሆን በኋላ ላይ IMPACT የተሰኘ ዓለም ዐቀፍ የሴቶች አቅም ማጎልበቻ እና የራስ መከላከል ብቃት ማሰልጠኛ ተቋም ሃላፊ በመሆን በስሯ ኢልሃቪቭ እና መሰል ተቋማትን አጠቃላ መምራት ጀመረች፡፡
ሳቫጅ የself-defense (እራስ የመከላከል ብቃት) ማስተር በመሆን ከዚህ በፊት ወንዳዊ ይዘት ነበረው የself-defense አርት አሁን ላይ ለሴት ልጆችም እንዲሆን አድርጋ ዳግም በመቅረፅ ለዓለም ትልቅ ነገር አበረከተች፡፡
ምንጭ፡- undark

የሀሳብ ልዩነት #በሳይንቲስቶች አለም : .....እንደ ትምህርት ለሀሳብ ልዩነት #በፖለቱከኞች አለም
***********************************
በ1930ዎቹ የታላቁ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ቲዮረቲካል ፊዚክስ ተማሪ የነበረው አልበርት አንስታይን ለኒውተን ስራዎች ትልቅ አድናቆት የነበረው ቢሆንም ኒውተን የስበት ንድፈሀሳቡ ላይ ፀሀይን ብናጠፋት 'ከመቅፅበት' ፕላኔቶች ምህዋራቸውን (orbit) ይስታሉ ያለው አልተዋጠለትም። 'ከመቅፅበት' የምትለዋ ቃል ናት ጥርጣሬ ያሳደረችበት። አንስታይን ይህን ሀሳብ መሰረት በማድረግ ለአስር አመታት ያህል አዲስ ንድፈሀሳብ ለማግኘት ጣረ። በመጨረሻም ዩኒቨርስን በሌላ አቅጣጫ እንድናይ የረዳንን የ ጀነራል ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብን (General relativity theory) አገኘ። በዚህ ንድፈሀሳብ መሰረት ከኒውተን ጋር ላልተስማማበት ሀሳብ መልስ አገኘ።
በአንስታይን ንድፈሀሳብ መሰረት ግዜ እና ቦታ አንድ ላይ የተሰፉ ምንጣፍ ናቸው። ግዜ ከቦታ ቦታ ከግዜ አይለዩም። ይህንን ስፔስ ታይም ፋብሪክ (Space-time fabric) ብሎ ጠራው። ክብደት ያላቸው ቁስ አካሎች በግዜ-ቦታ ድር ላይ ስርጉደት እንደሚያመጡም ይገልፃል። ምድራችን የምትዞርበት ምህዋር ፀሀያችን ድሩ ላይ በፈጠረችው ስርጉደት ውስጥ ነው ብሎ አመነ። ስለዚህ ፀሀያችንን ለአፍታ ማጥፋት ብንችል በፀሀያችን ክብደት ሰርጉዶ የነበረው ድር ወደቦታው ሲመለስ የሚፈጥረው ሞገድ ይኖራል። ልክ ወንዝ ውስጥ ድንጋይ ስንወረውር ጫፍ ድረስ እንደሚመጡት የውሀ ሞገዶች ሁሉ ይህም ሞገድ ከፀሀይ ተነስቶ መላው ስርአተ-ፀሀያችንን ያካልላል። ይህን ሞገድ የስበት ሞገድ (gravitational wave) ብሎ ጠራው። የሚጉዋዝበትም ፍጥነት በብርሀን ፍጥነት እንደሆነ በሂሳባዊ ስሌት አረጋገጠ። ስለዚህ ምድራችን ከምህዋሩዋ የምትወጣው 'ከመቅፅበት' ሳይሆን ይህ የስበት ሞገድ ከፀሀይ አቅጣጫ መጥቶ ምድራችንን ሲነካት እንደሆነ ተናገረ።
ከፀሀይ የመነጨ ብርሀን ምድራችን ለመድረስ 8 ደቂቃዎች ይፈጅበታል፤ የስበት ሞገድ ፍጥነት ከብርሀን ፍጥነት እኩል በመሆኑም ምድራችን ምህዋሩዋን ለመሳት 8 ደቂቃዎች ብቻ እንደሚያስፈልጓት አብራራ። አልበርት አንስታይን ይህንን ንድፈሀሳብ ጀነራል ሪላቲቪቲ ብሎ ጠራው። በዚህ ንድፈሀሳቡም ትልቅ ዝናን ተቀዳጀ። የኒውተንን የስበት ንድፈሀሳብም ከራሱ ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብ ጋር አዋሀደ።
ምንጭ፡ Airtable universe, Forbes እና E.A