የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከግሉ ዘርፍ ከተወጣጡ የቴክኖሎጂ አካላት ጋር በኤይሲቲ እና መሰል ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ
*****************************************
***************
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በግሉ ዘርፍ ተሰማርተው እንቅስቃሴያቸውን በኤይሲቲ እና መሰል የቴክኖሎጂ መስኮች ላይ ካደረጉ የተለያዩ ኩባንየዎች እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር በአይሲቲ ዘርፍ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ በተዘጋጃው የውይይት መድረክ ላይ እንደመነሻ ሃሳብ የሚሆኑ ጉዳዮች ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በመጡ ተወካዮች የቀረቡ ሲሆን፤ በዋናነትም በስራ ዕድል ፈጠራ እና በአይሲቲ እንቅስቀሴ ላይ የውይይት መነሻዎች ቀርበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ እጅግ ከፍተኛ ልምድ ካለቸው የዘርፉ አንቀሳቃሾች ጀምሮ እስከ ወጣት የሶፍተዌር አበልፃጊዎች ድረስ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አካላት ሲሳተፉ ሰፊ ማብራሪያ የሚስፈልጋቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም ከተሳታፊዎች ሊነሳ ችሏል፡፡ ውይይቱ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው አንኳር ሃሳቦች መካከልም የአይሲቲ ፓርክ ሁኔታ እና በአገር ደረጃ በተደጋጋሚ ሲስተዋል የነበረው የኢንተርኔት መዘጋት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በተጨማሪም የፖሊሲ ማሻሻያ የሚጠይቁ እና የአሰራር ለውጥ የሚያስፈልጋቸው የቢሮክራሲ ጉዳዮች ተነስተውበታል፡፡
በተሰጡ አስተያየቶች መሰርትም ከቡር ሚኒስቴሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ጨምሮ የአይሲቲ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት ዶክተር አህመዲን መሃመድ ለተነሱ ጥያቄዎችሲሉም ማብራሪያ ለመስጠት የሞከሩ ሲሆን ችግሮቹም እንደሃገር የምንጋራቸው ከመሆናቸው አኳያ ሁላችንም የመፍትሄው አካል ልንሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በወይይቱ መጨረሻ ላይ ከተሳታፊ አካላት የተወጣጡ 11 የኮሚቴ አባላት የግል ዘርፉን በመወከል የትብብር ስራዎችን ለመስራት የተሾሙ ሲሆን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋርም በጋራ በመሆን በፖሊሲ ግብዓቶች እና በማማከር ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ታውቋል፡፡

አዲሶቹ የኢቦላ መድኃኒቶች ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል
**********************************************
የኢቦላ በሽታ ለረዥም ዓመታት መድሃኒት ሳይገኝለት የቆየ እና በገዳይነቱም እጅግ ፈጣን ከሚባሉት የበሽታ አይነቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚሰለፍ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሽታው ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተስፋፍቶ የብዙ ምስኪኖችን ህይወት ሲያጠፋም እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በ2018 ሚያዚያ ወር ላይ ብቻ ተከስቶ ከ1,400 በላይ የሃገሪቱ ዜጎችን የቀጠፈበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡
በሽታው በእነዚህ አመታት ሁላ ከፍተኛ የመከላከል ሂደት ሲደረግበት እና የተለያዩ የምርምር ስራዎች ሲካሄዱበት የቆዩ ቢሆንም በስኬት ደረጃ ይህ ነው የሚባል ግኝት እንዳልነበረ በተደጋጋሚ የወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ ይሁንና በ2018 መጨረሻ ዓመት ላይ ክፍተኛ ምርምር ሲደረግባቸው ከነበሩት አራት የመከላከያ መድሃኒቶች ውስጥ ሁለቱ ትልቅ ተስፋ በማሳየታቸው ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጋቸውን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መቀመጨውን ያደረገ የምርምር ማዕከል ይፋ አድርጓል፡፡
እነዚህ ሁለት የመድሃኒት አይነቶች በዋናነት በደም ውስጥ በሚፈጠር የፀረ ባክቴሪያ ስሪት ወይም (antibodies) አማካኝነት የሚሰሩ የመከላከያ መድሃኒቶች ሲሆኑ Regeneron በሚባለው የመድሃኒት አምራች ድርጅት እና በሃገሪቱ በሚገኝ የብሄራዊ ጤና ኢኒስቲትዩት አማካኝነት መሰራታቸው ታውቋል፡፡
እንደሚታወቀው በኢቦላ ቫይረስ የተያዘ ሰው በፍጥነት ህክምና ካለተደረገለት 75 በመቶ ህይወቱን እንደሚያጣ በተደረጉ ምርምሮች ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ አኳያ እነዚህ ሁለት መድሃኒቶች በሽታው ብዙም ባልፀናበት ሰው ላይ ከ80 እስከ 90% በሽታውን ለመከላከል በመቻላቸው እስከዛሬ ከተሰሩት እንደ ZMapp ካሉ የመድሃኒት አይነቶች ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ነግር ግን ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃው ሰው መድሃኒቶቹን እየተጠቀመ እንኳን 30 በመቶ የመሞት እድል እንደሚኖረው የምርምሩ አካላት አስታውቋል፡፡
ይሁንና እስካሁን ከነበረው የመከላከል አቅም አንፃር ከፍተኛ ስኬት መታየቱን የተናገሩት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ የጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ጃኪዩስ ሙዬምቤ የብዙ ሺዎችን ህይወት የሚታደግ የኢቦላ መድሃኒት አግኝተናል ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ big think.com

የ8 ዓመቷ ህፃን በአስገራሚ ፈጠራዋ መነጋገሪያ ሆናለች
*****************************************
********
የሜክሲኮ ተወላጅ የሆነቸው የስምንት ዓመት ህፃን ሾቺየል ክሩዝ የሶላር ኢነርጂን በመጠቀም የሰራቸው የውሃ ማሞቂያ ቴክኖሎጂ አለምን እያነጋገረ ይገኛል፡፡ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ይህች ህፃን ገና ከአራት ዓመቷ ጀምሮ ለሳይንስ ያላት ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ በሃገሪቱ በሚገኝ ልዩ ችሎታ ያላቸው የህፃናት ማሳደጊያ እንድትገባ ተደርጋለች፡፡
ህፃኗ በዚህ የማሳደጊያ ፕሮግራም ከታቀፈች በኋላ ከሷ ሊጠበቁ የማይችሉ ፈጠራዎችን ስትሰራ የ የቆየች ሲሆን ለማበረታቻ የሚሆኑ የተለያዩ ሽልማቶችንም ከተቋሙ አግኝታለች፡፡ ሾቺየል ይህን የፈጠራ አቅሟን አሳድጋ በ8 ዓመቷ የሰራቸው የውሃ ማሞቂያ ቴክኖሎጂ ደግሞ ከማሳደጊያ ተቋሙ አልፎ በሀገሪቱ በሚገኝ የኒውክለር ሳይንስ ኢኒስቲትዩት ውስጥ ሽልማት እና አውቅናን አስገኘቶላታል፡፡
ቺያፓስ ተብሎ በሚጠራ በደቡባዊ ሜክሲኮ በሚገኝ ትንሽ የድሃ መንድር የምትኖረው ሾቺየል ቴክኖሎጂውን ለመስራት ምን አነሳሳሽ ተብላ ለቀረበላት ጥያቄ አንዳለቸው “በሰፈራችን የሚኖሩ ሰዎች የውሃ ማሞቂያ ቴክኖሎጂ ስለሌላቸው ብቻ ዛፎችን በመቁረጥ የከባቢ አየር ሁኔታን መጉዳታቸው ስለቴክኖሎጂው እንዳስብ አድርጎኛል ስትል ተደምጣለች፡፡” ቴክኖሎጂውን ለመስራት አባቴ ትልቅ ድጋፍ አድርጎልኛል ያለቸው ሾቺየል ለወደፊቱም ትልልቅ ፈጠራዎችን ለማበርከት እንደምትፈልግ ተናግራለች፡፡
በሶላር ሃይል የሚሰራው የውሃ ማሞቂያ ቴክኖሎጂ መልሶ መላልሶ ጥቅም ላይ በሚውል የተለያየ ቁስ ተዋቅሮ የተሰራ ሲሆን ለሙከራ እንዲሆን በማሰብም በቤታቸው ጣራ ላይ ተገጥሞ ቀዝቃዛ ውሃን ወደ ሙቅ ውሃ በመቀየር እየተገለገሉበት ይገኛል፡፡
ምንጭ፡ Truth Theory
እውቀቶን የሚያሳድግ፣ የሚያስተምር እና የሚያዝናና መሰል የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ ለማግኘት እንዲችሉ የዩቲዩብ እና የፌስቡክ አድራሻችንን ይጎብኙ
https://www.youtube.com/channel/
UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
https://m.facebook.com/TechinEthiopia/?ref=opera_speed_dial&_ft_=mf_story_key.2364169170357821%3Atop_level_post_id.2364169170357821%3Atl_objid.2364169170357821%3Acontent_owner_id_new.563821287059294%3Athrowback_story_fbid.2364169170357821%3Apage_id.563821287059294%3Aphoto_id.2364154333692638%3Astory_location.4%3Astory_attachment_style.photo%3Apage_insights.%7B%22563821287059294%22%3A%7B%22page_id%22%3A563821287059294%2C%22actor_id%22%3A563821287059294%2C%22dm%22%3A%7B%22isShare%22%3A0%2C%22originalPostOwnerID%22%3A0%7D%2C%22psn%22%3A%22EntStatusCreationStory%22%2C%22post_context%22%3A%7B%22object_fbtype%22%3A266%2C%22publish_time%22%3A1566461596%2C%22story_name%22%3A%22EntStatusCreationStory%22%2C%22story_fbid%22%3A%5B2364169170357821%5D%7D%2C%22role%22%3A1%2C%22sl%22%3A4%2C%22targets%22%3A%5B%7B%22actor_id%22%3A563821287059294%2C%22page_id%2C2%3A563821287059294%2C%22post_id%22%3A2364169170357821%2%22role%22%3A1%2C%22share_id%22%3A0%7D%5D%7D%7D%3Athid.563821287059294&__tn__=%2Cg

Facebook
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
Technology and Innovation Institute, Ethiopia, Addis Ababa, Ethiopia. 49,807 likes · 293 talking about this · 999 were here. TII is a go-to-place for anything scientific and technological information...
ቤተሰባዊ የክህሎት ግንባታ
==================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እንደ አዲስ መመስረቱን ተከትሎ ከተቀላቀሉትእና ነባር ባልደረቦቹ ጋር የእርስ በእርስ ትውውቅ እና ክህሎትን ለማዳበር ያለመ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ዛሬ ጅማሬውን አድርጎ ለተከታታይ ፲ ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ በተለያዩ ተቋማት እና ኃላፊነቶች እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን እና ባለ ታላቅ ስብዕና ግለሰቦች ልምዳቸውን ለተቋሙ ሰራተኞች እንደሚያካፍሉ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በተለያዩ መድረኮች በምትሰነዝራቸው አስተያየቶች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ስራዎቿ እውቅናን ያተረፈችው ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ፣ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ይጠቀሳሉ፡፡
በዛሬው መርሀግብር ላይ በemotional intelligence ዙሪያ የስነ ልቦና አማካሪ በሆኑት ወይዘሮ ሰብለ ኃይሉ አማካኝነት ለአንድ ቀን የቆየ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ምቀኞች ነን?
==================
በTECHIN ቤተሰቦች ሁለተኛ ቀን የክህሎት ግንባታ ውሎ በትናንትናው ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴን እና አንጋፋውን ምሁር ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን ባሳተፈው መድረክ ሰፊ ሀሳቦች ተንሸራሽረውበት አልፏል፡፡
መድረኩን በቅድሚያ ተረክበው የቆዩት ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ ስለ ቡድን ስራ ኃያልነት አስመልክተው ከታዳሚያኑ ጋር ጥልቅ ውይይት ሲያከናውኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን ምቀኞች አሊያም በጋራ መብላትን እንጂ መስራትን ያልታደልን መሆን አለመሆናችንን ጥያቄ ሰንዝረው ለሰፊ ውይይት ጋብዘው ነበር፡፡ በጉዳዩም ልዩ ልዩ ሐሳቦች ተንፀባርቀውበታል፡፡
ከእርሳቸው በማስከተል በሳይንስ፣ ሀገራዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከሰፊው የህይወት መንገዳቸው የተቀዱ እጅግ ጠቃሚ ልምድ እና ምሁራዊ እይታቸው አካፍለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በተለይም ሳይንስን ለሰፊው ሰህብረተሰብ በማዳረስ (አህዝቦተ ሳይንስ) ዙሪያ ባላቸው ተሞክሮ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

“እንደ እምነቱ የሚኖሩ አማኞች ጠፍተዋል”
=========================
“ትናንትን እያሰብን ዛሬን እየረሳን፤ ዛሬን እየረሳን ነገን እያጠፋን ነው”፣ “እንደ እምነቱ የሚኖሩ አማኞች ጠፍተዋል” እነዚህን ጠንካራ ቃላት የተናገሩት የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ናቸው፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባልደረቦች ክህሎት ግንባታ ላይ ተገኝተው የስብእና ግንባታ አስተምሮታቸውን በርእቱ አንደበት አዋዝተው ያቀረቡት መመህሩ በምድር ላይ እስካሉ ድረስ የእኔነትን ስሜት በማጥፋትና በእኛነት ስሜት በመታነፅ የየራሳቸውን አሻራ አስፍረው ሊያልፉ እንደሚገባም አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ከኡስታዝ አቡበከር በተጨማሪ በዛሬው መርሀ ግብር የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ (የህይወት ጉዞ /ከዳውሮ እስከ ኮሎራዶ)፣ የአይኮግ ላብስ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጌትነት አሰፋ (በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ) እንዲሁም ገበያ በተሰኘው ተቋም የቴክኖሎጂ ኩባንያ ውስጥ እያገለገሉ ያሉ ባለሙያዎች (በግንኙነት መንገዶች፣ ዲጂታል ገንዘብ...)ልምድና አስተምሮታቸውን ብሎም የተቋማቸውን ገፅታ ለቤተሰቦቻችን አካፍለዋል፡፡

፬ኛው ውሎ፤ ከአዕምሮ እስከ አዕምሮ ንብረት
======================
አራተኛ ቀኑን በያዘው የቴክኢን ቤተሰቦች የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠና ውሎ፤ በታዋቂው የህክምና ባለሙያ ዶክተር ብሩክ ላቢሶ "ሀ" ብሎ የጀመረው የዛሬው መርሀ ግብር ከህክምና እስከ አዕምሮአዊ ንብረት ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡ ዶ/ር ብሩክ በህክምና ረገድ ያሉትን ተቀዳሚ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በጥልቀት ያብራሩ ሲሆን ልዩና ውስብስብ ስለሆነው የሰው ልጆች ስነ አዕምሮአዊ አፈጣጠር ብሎም ማናቸውም የሰው ልጆች መፍጠር ስለሚችሉት ተፅዕንዖ (the power of one man the power of one woman) የዳሰሱበት ክፍል ቀልብን የሳበ ነበር፡፡ ለየት ባለው አቀራረባቸውም ተርታው ማህበረሰብ የተውጣጡ ግለሰቦች በምሳሌነት ተዳሰውበታል፡፡
ከእርሳቸው በማስከተል መድረኩን የተረከቡት የኢትዮጵያ አዕምሮ ንብረት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ የማነብርሀን ናቸው፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜም የአዕምሮአዊ ንብረት ምንነት፣ አይነቶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ተቃኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የአዕምሮ ንብረት እና ፈጠራ እንቀረስቃሴ ዝቅተኛ ግን ተስፋ ሰጪ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነቃቃቶች እንዳሉ አመላክተዋል፡፡

ሚዲያና ዕውነታ
===========
ሐሳብን ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ ለአንድ ስራ ቀና ውጤት ትልቁን ሚና ይወጣል፡፡ ለዚህ ይረዳ ዘንድ የዛሬውን የቴክ-ኢን ቤተሰቦች የክሆሎት ግንባታ ውሎ በሳይንስ ግንኙነት (science Communication) ላይ በማድረግ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ስልጠናን ሰጥተዋል፡፡ በሀገራችን የጋዜጠኝነት እና ግንኙነት አስተምሮት ሰፊ ልምድ ያላቸው ዶ/ር ጌታቸው በመሰረታዊ የግንኙነት ምንነት፣ መንገዶቹ፣ ታሪካዊ ዳራውን ብሎም በእይታዎቹ ዙሪያ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጥን አከናውነዋል፡፡ ካነሷቸው ሐሳቦች መካከል ግለሰቦች ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር ባላቸው የግንባር ግንኙነት እንዴት ጥሩ ተናጋሪ መሆን እንደሚችል ሲሆን ሃሳቦቹን በአዝናኝ አቀራረብና አስተማሪ ምሳሌዎች አዋዝተው አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ሚዲያው የህብረተሰብን አስተሳሰብ እና ድርጊት በማነፅ ደረጃ ያለውን ጉልበት እንዲሁም የአቀራረባቸውን እይታዊ እውነተኝነትና የዘገባ አድማስ ተዳሰውበታል፡፡
ሌላው በዛሬው መድረክ ስልጠኛ የተሰጠበት ደረጃዎችን (standard) እና አራተኛውን የኢንዱስትሪ አብዮት አስመልክቶ የተሰጠው ሲሆን ኢትዮጵያ ደረጃዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ እንዳለው መኮንን ነበሩ፡፡ ከደረጃዎች ምንነት አንስቶ በውስጡ ምን ይይዛል፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ መዳቢዎች ብሎም በኢትዮጵያ ያለው የደረጃዎች አሰጣጥ ሁኔታና የአሰጣጥ ሰንሰለት ምን ይመስላል የሚለው ተዳሷል፡፡