ሙሉ በሙሉ በሮቦቶች ቁጥጥር ስር የወደቀው የኒሳን መኪና ፋብሪካ ስራ
===================
ከቶኪዮ ወጣ ብሎ የሚገኘውና ቶቺኚ ተብሎ የሚጠራው የኒሳን አስተዋይ የመኪና ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ሰዎች ብዙም አይታዩበትም፡፡ በፋብሪካው ሮቦቶች ይበይዳሉ፣ ይገጣጥማሉ፣ መኪናዎቹን ቀለም ይቀባሉ እንዲሁም የቀቡትን መልሰው የመገምገም ስራን ይሰራሉ፡፡ የኒሳን ምክትል ፕሬዘዳንት ሂዲዩኪ ሳካሞቶ እስከ አሁን ድረስ የምርት ማስተካከያዎች በልምድ ይሰሩ እንደነበር ገልፀው አሁን ግን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚታገዙት ሮቦቶቹ የሚሰበሰቡ ጥሬ ሀቆችን ጭምር መተንተን የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ይላሉ፡፡
በወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባ የሚነገርለት ፋብሪካው በኤሌክትሪክ፣ ነዳጅ እና በሁለቱ ቅልቅል (ሀይብሪድ) የሚሰሩ መኪኖችን በአንድ መስመር እንደሚገጣጥም ይጠበቃል፡፡ በፋብሪካው የሚገኙት ግዙፍ ሜካኒካዊ እጆች በተገጠመላቸው ብርሃን መርጫ እና ካሜራ አማካኝነት በተለያዩ አቅጣጫዎች ምልከታን በማድረግ ለማየት የምታዳግተው ትንሿን ችግር እንኳን ለይተው ያወጣሉ፡፡ በፋብሪካው የሚገኝ ማግኔትን ተክቶ በብረት ላይ ገመድን የሚጠመጥም አዲስ ስርዓትም በብዛት የማይገኙ ማዕድናትን ከመጠቀም እንደሚያድነውና በዚህም የምርት ወጪዎን እንደሚቀንስለት ኒሳን ይናገራል፡፡
እንደ ኒሳን ከሆነ በቶቺኚ ፋብሪካ የሚተገበሩ ኢኖቬሽኖች በመላው ዓለም በሚገኙት ሌሎች በእርሱና እህት ኩባንያው በሆነው የፈረንሳዩ ሬኖ ስር በሚገኙ መኪና አምራች ፋብሪካዎች የሚተገበሩ ይሆናል፡፡ የጉልበት ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ለሮቦቶቹ መሰጠታቸውን ተከትሎም በፋብሪካው የሚገኙ ሰራተኞች በሮቦቶቹ የሚሰበሰብ መረጃን መተንተን እና መሳሪያዎችን መጠገን በመሳሰሉ ሌሎች ክህሎትን በሚጠይቁ ስራዎች ላይ በይበልጥ የሚሰማሩ ይሆናል፡፡
ሙሉ በሙሉ በሮቦት መስራቱ ምን ያህል ወጪ እንደሚቆጥብለት ሂዲዩኪ ሳካሞቶ ባይናገሩም የምርት ስራዎች በኮቪድ 19 ሳብያ ከመጡ የሰራተኛ እጥረቶች እንዲሁም ከባቢ አየር ተስማሚነት ጋር የተላመዱ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
መቀመጫውን በጃፓን ያረገው ግዙፉ ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ኒሳን እ.አ.አ በ2050 ከካርበን የፀዳ የምርት ሂደትን ለመከተልና የምርት ግብዓቶቹንም ዳግም ጥቅም ላይ በማዋል ሂደት ለመጠቀም አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ በአልሙኒየም የሚሰራው የመኪናዎቹ አካልን እና ለወትሮ ለየት ባለ ቦታ በተለየ የሙቀት ደረጃ የሚቀቡት የፕላስቲክ መጋጫቸውን አንድ ላይ በመቀባት ብቻ የኃይል ፍጆታውን በ25 በመቶ መቀነስ እንደሚችል ይናገራል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከኒሳን በተጨማሪ ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ የመኪና አምራች ኩባንያዎች ገበያው ለሚጠይቀው ምላሽ መስጠት ያስችላቸው ዘንድ የሮቦት ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ፡፡
ምንጭ፤ አሶሼትድ ፕረስ
ምንጭ፤ https://apnews.com/article/technology-business-japan-84a67e7273b32a15a9e6ee1502b57d86

AP News
Smart robots do all the work at Nissan's 'intelligent' plant
Nissan’s “intelligent factory” hardly has any human workers. The robots do the work, including welding and mounting.
የማዕድን ቁፋሮ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ከብክለት መጠበቅ
*******************************
በአለማችን በኮፐር ምርቷ የምትታወቀው እና ካላትም ገቢ ውስጥ 15 በመቶውን በዚሁ ማዕድን የምትሸፍነው ችሊ በማዕድን ቁፋሮ አካባቢዎች ብክለት ላይ ለመስራት መዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡ በተለያዩ በብረት ቁርጥራጮች የተበከለን አካባቢ ብረትን በፍጥነት በመብላት በሚታወቅ ባክቴሪያ አማካኝነት ለማጽዳት መታሰቡ ተነግሯል፡፡
በዘርፉ ላይ ምርምር እያደረገች ያለችው ችሊያዊቷ ተመራማሪ ናዳክ ሪሌስ ከሳንቲያጎ ከተማ በስተ ሰሜን 1100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ከተማ በተገነባ ቤተ ሙከራ ውስጥ ምርምሯን እያካሄደች ነው፡፡ በሙከራውም ጊዜ ባክቴሪያው አንድን ሚስማር በሶስት ቀን ውስጥ በልቶ መጨረስ መቻሉ ተረጋግጧል፡፡
የ33 ዓመቷ የባዮ-ቴክኖሎጂ ተመራማሪ እንስት በአደገኛ አካባቢዎች የሚገኝን ደቂቅ ዘአካል በመጠቀም ነው ምርምሯን እያከናወነች ያለችው፡፡ ተመራማሪዋ የችሊን የኮፐር ምርት ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶችን እየደረገች በነበረበት ወቅት ይህ በብረት ቁርጥራጮች የሚፈጠር ብክለትን እንዴት መቀነስ ይቻላል የሚል ሀሳብ እንደመጣላት ትናገራለች፡፡
የብረት ቁርጥራጭን ሰብስቦ በማቅለጥ ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል አንደኛው መንገድ መሆኑ ቢታወቅም መሰብሰብ የማይችሉ በተቃራኒው ደግሞ የስራ አካባቢን የሚበክሉ ቁርጥራጮችን በዚህ መልክ ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተመራማሪዋ ታስገነዝባለች፡፡
አሁን ላይ ተመራማሪዋ የራሷን Rudanac Biotec የተሰኘ ድርጅት በማቋቋም ሌፕቶስፕሪሊየም የተሰኘ ብረት በል ባክቴሪያ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ነው፡፡ ይህ የባክቴሪያ ዝርያ በአሲዳማ መሬት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በመደበኛ አኗኗር አንድን ሚስማር ለመብላት ወደ ሁለት ወራት ያክል ይወስድበት ነበር፡፡ ተመራማሪዋ ባክቴሪያውን እንዲራብ በማድረግ ሚስማሩን በልቶ ለመጨረስ የሚጨርስበትን ጊዜ ወደ ሶስት ቀን ማሳነስ መቻሉን ተናግራለች፡፡
ውጋጅ ብረቶችን በባክቴሪ በማስበላት የሚገኘው ተረፈ ምርት በፈሳሽ መልክ የሚገኝ ሲሆን ይህ ፈሳሽ ምርት ሀይድሮሜታለርጂ በተሰኘ ሒደት የኮፐር ፍለጋውን ለማገዝ እንደሚጠቅም ተነግሯል፡፡ ይህም እንደ ተመራማሪዋ እምነት ከብክለት ነጻ የሆነ የማዕድን ፍለጋ ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ምዕራፍን የሚከፍት ግኝት ነው፡፡
ምንጭ phys
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-10-chilean-scientist-metal-bacteria.html

phys.org
Chilean scientist plans to clean up mining with 'metal eating' bacteria
Starving microorganisms capable of surviving in extreme conditions have already managed to "eat" a nail in just three days.
ልቡ ውስጥ ሲሚንቶ የተገኘበት ታካሚ
=============
አንድ የ56 ዓመት ጎልማሳ ከ10 ሴ.ሜ የሚልቅ ሲሚንቶ በደም ስሩ ውስጥ ተላልፎ ልቡ ውስጥ እንደተገኘበት ተዘገበ፡፡ ይህ ሰው ለሁለት ቀናት ያህል ያጋጠመውን የደረት ህመም እና ለመተንፈስ መቸገር ተከትሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል ካመራ በኋላ ነው ሲሚንቶው በውስጡ የተገኘበት፡፡
ህመሙ ከማጋጠሙ ከአንድ ሳምንት በፊት ቨርተብራል ኮምፕረሽን ፍራክቸር ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ ህመምን የሚፈጥርና በጥንካሬ ማጣት ሳብያ የጀርባ አጥንት ክፍል በራሱ ላይ በሚናድበት ወቅት የሚከሰት የጤና እክልን የሚያስተካክል ህክምናን አከናውኖ ነበር፡፡ ይህ ሰው ታድያ ከህመሙ ይድን ዘንድ ካይፎፕላስቲ ተብሎ የሚጠራውን ሀኪሞች በዓይነቱ የተለየ ሲሚንቶ ወደ አከርካሪዎቹ በማስገባት ወደ ትክክለኛ ቁመቱ የሚመልሱበት እና እንዳይናድ የሚያደርጉበት የህክምና ዓይነት ተከናውኖለታል፡፡
ህክምናው ደህነቱ የተጠበቀ ስለሆኑ ቢመሰከርለትም ህመሙ ከገጠማቸው ሰዎች ውስጥ ግን ሁለት በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ይህ ዓይነቱ ህክምና የሚደረግላቸው፡፡ ታድያ በዚህ የህክምና ስልት ላይ ሊፈጠሩ ከሚችሉት ችግሮች መካከል ሲሚንቶው ከአጥንቶቹ አፈትልኮ ወጥቶ ወደ ሌሎች የሰውነት አካባቢዎች በመሰራጨት የደም ስርን መዝጋት ነው፡፡ በዚህ ታማሚ ላይም የሆነው ይኸው ነው፤ ሲሚንቶው አፈትልኮ ወጥቶ ወደ ደም ስሮቹ ውስጥ የገባ ሲሆን በዚያም ከጠነከረና ከተቆራረጠ በኋላ ወደ ልቡ ሊጓዝ ችሏል፡፡
ታማሚው ድንገተኛ ክፍል ውስጥ በገባበት ወቅት የኤክስ-ሬይ እና ሲቲ ስካን ምልከታዎች ሲደረግለት ነው ባዕድ ነገር በሰውነቱ ውስጥ ስለመኖሩ የተደረሰበት፡፡ በማስከተል ድንገተኛ የልብ ቀዶ ህክምና ሲደረግለት ሀኪሞቹ ቀጭን እና ሹል የሆነ የሲሚንቶ ግግር በላይኛው የቀኝ ልብ ክፍሉ እና የቀኝ ሳንባው ውስጥ ሊያገኙ ችለዋል፡፡ ሀኪሞቹ ሲሚንቶውን ሲያወጡት 10.1 ሴ.ሜ የሚረዝም ሆኖ ሲያገኙት ካወጡት በኋላም ሲሚንቶው ልቡ ላይ የፈጠረው ስንጥቃት የሚጠግን ህክምና በሀኪሞቹ ተደርጎለታል፡፡
ታካሚው ይህን ቀዶ ክህምና ተከትሎ ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመውም፤ ከአንድ ወር ቆይታ በኋላም ሙሉ በሙሉ አገግሞ ወደ ቀድሞ ጤናው ስለመመለሱ ከሳምንት በፊት በኒው ኢንግላንድ የህክምና ጆርናል ላይ ታትሞ በወጣው ጥናታዊ ፅሁፍ ሪፖርት ተደርጓል፡፡
ምንጭ፤ ላይቭ ሳይንስ
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/cement-heart-spinal-procedure.html

livescience.com
How did cement end up in a man's heart?
A 4-inch piece of cement had pierced the man's heart and lung.
ጀርመን በዓለማችን የመጀመሪያውን አሽከርካሪ አልባ ባቡር ለአገልግሎት አበቃች
=================
የጀርመኑ ባቡር አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ዶቼ ባሀን ከሲመንስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር በዓለማችን የመጀመሪያው የሆነውን ያለ አሽከርካሪ የሚንቀሳቀስ ባቡርን ትናንት ይፋ አድርገዋል፡፡ በጀርመኗ ሀምቡርግ ከተማ ይፋ የተደረገው አሽከርካሪ አልባ ባቡሩ ከሌሎች ባቡሮች አንፃር በሰዓቱ የሚገኝና ኃይልን ቆጣቢ ስለመሆኑም ተነግሮለታል፡፡
ከዚህ ቀደም እንደ ፓሪስ ያሉ ጥቂት ከተሞች ያለ ሰው በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ፈጣን ባቡሮችን ይዘው መጥተዋል፤ የተለያዩ ኤርፖርቶችም እንዲሁ አሽከርካሪ አልባ ባቡሮች አሏቸው፡፡ ነገር ግን የሀምቡርጉን ባቡር የዓለማችን የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር ያሰኘው የተለየ መሰረተ ልማትን ሳይፈልግ ቀድሞ በተዘረጉት ሀዲዶች ላይ መንቀሳቀስ መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የፓሪሱም ሆነ የኤርፖርት ባቡሮቹ (Monorail) ለየት ተብሎ በተዘጋጀላቸው አንድ ነጠላ ሀዲድ ላይ ብቻ ነው መንቀሳቀስ የሚችሉት፡፡
የዚህ አሽከርካሪ አልባ ባቡር ዝርጋታ የሀምቡርግን ፈጣን የከተማ ባቡር ስርዓት የማዘመን ፕሮጀክት አካል ነው፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች አራት አሽከርካሪ አሽከርካሪ አልባ ባቡሮች የከተማዋ ሰሜናዊ ፈጣን ባቡር መስመርን የሚቀላቀሉ ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለውን የባቡር መሰረተ ልማት ተጠቅመውም በቀጣዩ ወር ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡
የሲመንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሮላንድ ቦች አዲሶቹ ባቡሮች በ30 በመቶ የበለጡ ተሳፋሪዎችን የሚያስተናግዱ፣ ሰዓታቸውን በተሻለ ጠብቀው የሚያጓጉዙና የኃይል ፍጆታቸውም በ30 በመቶ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባቡሮቹ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና ያለ አሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ ቢሆኑም ታድያ ተሳፋሪዎች ባሉበት ጊዜ ሁሉ ግን ጉዞውን የሚቆጣጠሩ አሽከርካሪዎች በውስጣቸው ይኖራቸዋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-10-germany-unveils-self-driving.html

Tech Xplore
Germany unveils first self-driving train
German rail operator Deutsche Bahn and industrial group Siemens on Monday unveiled the world's first automated, driverless train in the city of Hamburg, billing it as more punctual and energy efficient ...
ጎግል ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ ነው
==========================
በሳይበር ምህዳሩ ዘርፍ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በሃከሮች ዋና ኢላማ እየተደረጉ ከመምጣታቸው አንጻር ጎግል በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ለእነዚህ ተጠቃሚዎቹ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እና አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም (APP) የተባለውን የቅርብ ጊዜ የደህንነት ሲስተም እንዲተገብሩ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁንና በቅርብ ወራት ውስጥ ከፍተኛ ተከታይ ባላቸው የፖለቲካ መሪዎች፣ የሰብኣዊ መብት አክቲቪስቶች እና ሌሎች ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ባለባቸው አካላት ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የሳይበር ወንጀል፤ ሌሎች የደህንነት አሰራረሮችን ለመተግበር እያስገደደው እንደመጣ ያስታወቀው ጎግል አሁን ላይ 10ሺ ለሚጠጉ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው ተጠቃሚዎች አዲስ የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
በ2021 ብቻ ውስብስብ የሳይበር ጥቃት እየተፈፀማባቸው የሚገኙ እና የሃገር መንግስታት ድጋፍ የሚደርጉላቸው ሃከሮች የሚሞክሩትን የሳይበር ጥቃት ለማክሸፍ አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም የተባለውን የደህንነት ስርዓት ተጠቃሚዎች እንዲተግበሩ ጎግል ሲሳስብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ይህንን ሳያደርጉ የቆዩና በመስከረም ወር የማጣራት ሂደት ብቻ ከፍተኛ የሳይበር ሙከራ በተደረገባቸው 14 ሺ በላይ የጂሜል ተጠቃሚዎች የማስጠንቀቂያ መልክት መላኩን የተናገሩት በድርጅቱ ውስጥ የስጋት ትንተና ቡድን ሃላፊ የሆኑት ሚስተር ሃንትሊ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው አካላት የኦንላይን አጠቃቀማቸው ላይ የሚታየውን ተጋላጭነት በፍጥነት እንዲሞሉ ተዳጋገሚ ማሳሰቢያ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
ጎግል አሁን ላይ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የሚያቀርበው የደህንነት ቁልፍ በኮምፒውተራቸው ላይ በሚሰኩ የሃርድዌር ዩኤስቢ መሳሪዎች አማካኝነት የሚሰሩ ሲሆን በዋናነት የተጠቃሚዎችን አካውንት ለመጥለፍ የሚያስችሉ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በሚገባ ለመከላከል የሚግዝ ነው፡፡ ታይታን ብሎ የሰየመውን የድህንነት ቁልፉ ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት ጎግል ከብዙ የቴክኖሎጂ ድጅቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት ከከቀረቡት ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (two-factor authentication) አሰራሮች በተጨማሪ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የቀረበው ይህ የደህንነት ቁልፍ እየተባባሰ የመጠውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከል በእጅጉ እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
https://www.techradar.com/news/google-will-give-free-security-keys-to-high-risk-users

TechRadar
Google will give free security keys to 'high risk' users
Search giant plans to distribute 10,000 security keys throughout 2021
አዲስ ዓይነት የአውሮፕላን ነዳጅ ተሰራ
===============
ተመራማሪዎች የግብርና ተረፈ ምርትን በመጠቀም በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ሰሩ፡፡ ለተፈጥሮ በተሻለ ተስማሚ ነው የተባለለት አዲሱ ነዳጅ አሴቶን እና አልኮልን በማቀላቀል የተሰራ ነው፡፡
የተሻሻሉ ባዮፊውሎች ለከባቢ ተስማሚ ከሆነ ባዮማስ የሚመረቱና ከሌሎች ነዳጆች አንፃር አነስተኛ የበካይ ጋዝ ልቀት ያላቸው ነዳጆች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ረገድ አዲሱ ነዳጅ የተሻሻሉ ባዮፊውሎችን አስመልክቶ የተቀመጡ ደረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም ለደረጃዎቹ የቀረበና ጥቂት ስራዎች ከተሰሩበትም ተግባር ላይ መዋል የሚችል ነው፡፡
ከግብርና እና ምግብ የሚመነጩ ተረፈ ምርቶች አንዳንድ የተፈጥሮ ተስማሚነት መስፈርቶችን አሟልተው ከተገኙ ለተሻሻለ ባዮፊውል ምርት ግብዓት ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡ ይህ የባዮጀት ፊውል ፕሮጀክትም ከተፈጥሮ ግብዓቶች የሚመረት የአውሮፕላን ባዮፊውል ነዳጅ ዋጋ እና የምርት ሰንሰለትን በመመርመር ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ውጤት ታድያ ከፍተኛ ርጥበት ያላቸው የግብርና እና ምግብ ተረፈ ምርቶችን ወደተሻሻለ የአውሮፕላን ባዮፊውል ምርትነት በመውሰድ የገበያ ሰንሰለትን ለመዘርጋት ሊረዳ ይችላል ተብሎለታል፡፡
በጥናቱ ጥቅም ላይ የዋሉት ግብዓቶች ድንችን ከማቀነባበር ስራ የተገኙ ፈሳሽ ተረፈ ምርቶች ናቸው፡፡ ግብዓቶቹን በመጠቀም አሴቶን፣ ቡታኖል እና ኢታኖልን ወይም በሌላ አጠራር ኤቢኢ ፈርመንቴሽን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ፈሳሽ ውጋጆች ለኬሚካላዊ ለውጥ ወይም ፈርመንቴሽን የተመቹ ቢሆንም ያን ያህል ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ ናቸው፡፡
በዚህ ፕሮጀክት ላይ የነዚህ ሦስት ምርቶች ውህድ ከሃይድሮጅን ጋር ከተቀላቀሉ እና ኬሚካላዊ ንጠላ (Fractionation) ከተደረገባቸው በኋላ ወደ ሀይድሮ ካርበንነት ሊለወጡ ችለዋል፡፡ በጥናቱ ላይ በተደረጉ ሙከራዎች ነዳጁን በግብርና ተረፈ ምርት አማካኝነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ምርት ማስገባት እንደሚቻል የታየ ሲሆን በተፈጥሮ ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ተፅዕንዖ እንዲሁም ምጣኔ ሐብታዊ ሁናቴው ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡
በዚህ ጥናት ላይ ነዳጁን ለማምረት ጥቅም ላይ የዋለው የድንች ማቀነባበርያ ተረፈ ምርት ይሁን እንጂ ወደፊት ለገበያ የሚበቃ ነዳጅን ለማምረት ግን ከሌሎች የግብርና ምርቶችም የሚወጣ ተረፈ ምርትን በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-10-kerosene-bio-based-side-streams.html

Producing kerosene from bio-based side streams
Wageningen University & Research and its partners have developed a new type of aviation fuel that is produced using bio-based waste streams from the agriculture industry.
በክሊኒካዊ ሙከራው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው የካንሰር መድሃኒት
***********************************************
በተለምዶ አባ ጨጓሬ እያል ከምንጠራው የትል ዝርያ ከሚገኝ ፈንገስ የተለያዩ ሙከራዎችን አልፎ በተደረገለት ክሊኒካዊ ሙከራ ትልቅ ውጤት ያስመዘገበ የካንሰር መድሃኒት መገኘቱ ተነገረ፡፡ መድሃኒቱ በአባ ጨጓሬው ጥገኛ ሆኖ ከሚኖረው ሂማላያን የተሰኘ ፈንገስ የተዘጋጀ ሲሆን በተደረገው የደረጃ አንድ ክሊኒካዊ ሙከራ የካንሰር ህዋሳትን መግደል የሚችል መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም ውጤታማ የካንሰር መድሃኒት ለማዘጋጀት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ መሰረት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
መድሃኒቱ ኮርዲሴፒን ከተባለ በአባ ጨጓሬ ጥገኛ ሆኖ በሚኖረው ፈንገስ የሚመረት ውህድ የተሰራ መሆኑን ግኝቱ በተገለጸበት የክሊኒካል ካንሰር ምርምር መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡ አሁን ላይ ትልክ ተስፋ ከተጣለባቸው የካንሰር መድሃኒቶች መካከል የተካተተው በሌላ ስሙ 3'-dA በሚል የተሰየመው መድሃኒት ለዘመናት በቻይና ባህላዊ ህክምና ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ መድሃኒቶች ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያለው ነው፡፡
መድሃኒቱ በሙከራ ሂረት ውስጥ ካስመዘገበው ውጤት በተቃራኒው ጉድለቶችም ታይተውበታል፡፡ ከእነዚህም ዋነኛው በደም ስር ውስጥ በሚያደርገው ጉዞ የካንሰር ህዋሳትን እንዳያገኝ አዴኖሲን ዲያሜናስ (ADA) በተሰኘ ኢንዛይም ጥቃት የሚደርስበት መሆኑ ነው፡፡ በዚህም ጥቃት የተነሳ ራሱን ችሎ ወደካንሰር ህዋሳት መድረስ የማይችል በመሆኑ hENT1 የተሰኛ ድጋፍ ሰጭ ኒውክሎሳይድ ያስፈልገዋል፡፡
ይህንን ችግር ለመሻገርም ተመራማሪዎቹ ፕሮታይድ የተሰኘ ቴክኖሎጂን መጠቀም መርጠዋል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በድሃኒቱ በደም ስር ውስጥ ወደ ካንሰር ህዋሳት በሚያደርገው ጉዙ ከሚደርስበት ጥቃት የሚከላከል ጋሻ ነው፡፡ በማሻሻያውም የተገኘው መድሃኒት የአዴኖሲን ዲያሜናስ (ADA) ጥቃት መቋቋም የሚችል በመሆኑ NUC-7738 የሚል ስያሜ ተሰጥጾታል፡፡
መድሃኒቱ በዋናነት የካንሰር ህዋሳት በደም ውስጥ እንዳይራቡ የሚያደርግና ሞታቸውን የሚያፋጥን በመሆኑ ተመራጭነቱና ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎቹ የመድሃኒቱን ሁለተኛ ዙር ሙከራ ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/anticancer-drug-derived-from-caterpillar-fungus-shows-huge-potential-in-clinical-trial/?fbclid=IwAR3oQu8pimSLMVGaQK0Ke-35031d6UlbbA2bhlrozrLXdwfGzyCGDJPL84w

IFLScience
Anti-Cancer Drug Derived From "Caterpillar Fungus" Shows Huge Potential In Clinical Trial
A molecule found in a parasitic Himalayan fungus has been found to kill tumor cells in a Phase I clinical trial, raising hopes that it may provide a founda
ሁለት ጭንቅላት እና ስድስት እግሮች ያሏት ኤሊ ተወለደች
=================
ከሁለት ሳምንታት በፊት በአሜሪካኗ የማሳቹሴትስ ግዛት ሁለት አንገት እና ጭንቅላት ያላት ኤሊ ተወልዷለች፡፡ ይህች መገኛው በአሜሪካን እና ቤርሙባ ከሆነ የዳይመንድባክ ቴራፒን ዝርያ የሆነችው ኤሊ ከሁለት ጭንቃላት በተጨማሪ ስድስት እግሮች ያላት መሆኗ ይበልጥ ትኩረትን እንድትስብ አድርጓታል፡፡
የኤሊዋ ሁለት ጭንቅላቶች ለየብቻቸው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ሁለቱን የሰውነት ክፍሎቿን ይመግቡላት ዘንድም ሁለት የምግብ ስርዓቶችን (gastrointestinal) ይዛ ነው የተፈለፈለችው፡፡
በግዛቱ ውስጥ የመጥፋት አደጋ ላይ ናቸው ከሚባሉ እንስሳት መካከል ከሆነው የኤሊ ዝርያ የተገኘችው ኤሊዋ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትገኝና ትላትል እና ሌሎች የቀረቡላት ምግቦችን እየተመገበች ስለመሆኑ አሁን የምትገኝበት በርድዜይ ኬፕ ዱርጥበቃ ማዕከል ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
ኤሊዋ በቅድሚያ ከእንቁላሏ የተፈለፈለችበት ቦታ ለደህንነቷ መልካም የሚባል ባለመሆኑ ነው ወደ ማዕከሉ የተዛወረችው፡፡ የማዕከሉ እንስሳት ሀኪም ፒርላ ፓቴል ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ጤናዋን እየተከታተሏት ይገኛሉ፤ ኤሊዋንም በልጅነት ዕድሜያቸው እውቅናን አግኝተው በነበሩት መንትያ አሜሪካዊያን ተዋንያን ሜሪ ኬት እና አሽሊ ኦልሰን ስም ሰይመዋታል፡፡ ሀኪሞቹ በቀጣይም ስለ ኤሊዋ የደም ዝውውር ስርዓት የበለጠ ለመረዳት የሲቲ ስካን ምልከታን ለማድረግ አቅደዋል፡፡
ምንጭ፤ አሶሼትድ ፕረስ
ለተጨማሪ፤ https://apnews.com/article/oddities-massachusetts-turtles-wildlife-animals-3911b338a119295d443c3d909266dd96

2-headed baby turtle thrives at Massachusetts animal refuge
A rare two-headed diamondback terrapin turtle is alive and kicking — with all six of its legs — at the Birdsey Cape Wildlife Center in Massachusetts.
ሃብልን የሚተካው የስፔስ ቴሌስኮፕ የመጨረሻውን ሙከራ ሊያደርግ ነው
=====================
በሰው ልጆች የጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሃብል ቴሌስኮፕ ወደ ጠፈር የመጠቀው እ.ኤ.አ በ1990 ሲሆን ጋሊሊዮ ከሰራት የመጀመሪያዋ ቴሌስኮፕ ቀጥሎም ለጠፈር ሳይንስ ምጥቀት ትልቁን ድርሻ ያበረከተ ግኝት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ መረጃዎች እንደሚሳዩት ሀብልን በመጠቀም ብቻ እስከዛሬ ከ14,000 በላይ ሳይንሳዊ ጥናቶች በተለያየ ዘርፍ ተደርገውና ታትመው ለአንባቢዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ይህም በሳይንሱ ዓለም በየትኛውም ዘርፍ ለሚደረጉ ጥናቶች ትልቅ መረጃን በማቀበልና በተለይም ለህዋ ሳይንስ እድገት ትልቁን አበርክቶት በበዋወጣት በዘርፉ ከተፈጠሩ ቴክኖሎጀዎች ከፊት ለፊት እንዲቀመጥ ያደርገዋል፡
ለ31 ዓመታት ዩኒቨረስን በመቃኘትና በትንሹ 1.2 ሚልዩን የሚሆኑ የጠፈር እይታዎች (observations) በማድረግ ለህዋ ምርምሩ ትልቅ ሚና የተጫወተው ሃብል የስፔስ ቴሌስኮፕ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጋጠሙት ባሉ ቴክኒካል ችግሮች እና ዘመናዊው የህዋ ምርምር የሚፈልገውን ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ግብዓት ያካተተ ባለመሆኑ አሁን በመሰራት ላይ ካሉት እንደ ጀምስ ዌብ ካሉ ሱፐር ቴሌስኮፖች አነስተኛ አገልግሎት እንዲኖረው ደርጉታል፡፡ ሃብል እሱን ተክቶ እየመጣ ካለው ጀምስ ዌብ የስፔስ ቴሌስኮፕ አንጻር በብዙ ዘርፎች አነስተኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ቢችልም በየጊዜው በሚደረጉለት ጥገናዎችና ማሻሻያዎች ቀድሞ ሲሰራ የነበረውን በአነስተኛ ሞገድ የጠፈር እይታዎች የማካሄድ እና ልዩ ልዩ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራውን ሊቀጥል ይችላል፡፡
በ10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባተው ተጠናቆ ወደመጨረሻው ምዕራፍ የተሸጋገረው ጀምስ ዌብ ሱፐር ቴሌስኮፕ ሃብል ሲሰጠው የነበረውን አገልግሎት ከማቅረብ ባለፈ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የህዋ ምርምር ዘርፉንና አጠቃላይ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ይበልጥ የመሻሻል አቅም እንደሚኖረው ይነገርለታል፡፡ ወደምህዋር በገቡ የስፔስ ቴሌስኮፕች ታሪክ 6.5 ሜትር ርዝመት በመያዝ ግዙፍ የአስትሮኖሚካል ሚረር ወይም መስታዎት ካላቸው ቴሌስኮፕች ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፈው ይህ ቴሌስኮፕ በተለይም በረጅም የሞገድ ርዝመት እስከዛሬ ሊደረስባቸው ያልቻሉ የጠፈር እይታዎችን በማከናወን አዳዲስ እውነታዎችን ሊገልጥ መቻሉ ጀምስ ዌብን ለየት እንዲል ያደርገዋል፡፡
አሁን ላይ ይህ የስፔስ ቴሌስኮፕ በታህሳስ ወር ለሚያደርገው ወደ ህዋ የመወንጨፍ ፕሮግራም ደቡብ አሜሪካ በሚገኘው ፍሬንች ጊያና ማረፊውን ያደረገ ሲሆን ወደ ህዋ ከመጓዙ በፊት በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት የመጨረሻውን ፍተሻና አጠቀላይ የማጣራት ሂደት ኮርዋ ስፔስፖርት በተባለው የአውሮፓ ኩባንያ የሚደረግለት ይሆናል፡፡ በካናዳ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የስፔስ ኤጀንሲዎች ትብብር አጠቃላይ ስራው ሲከናወን ቆይቶ ወደመጨረሻው ምዕራፍ የተሸጋገረው ጀምስ ዌብ ሱፐር ቴሌስኮፕ ከሃብል የጠፈር እይታዎች ከ10 እስከ መቶ አጥፍ የላቀ ኦብዘርቬሽን በማድረግ ከ13 ቢሊዮን የብርሃን ዓመት ርቀት ላይ የሚታዩ ብርሃኖችን የመለየት አቅም አንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡
ቢቢሲ
https://www.bbc.com/news/science-environment-58888302

BBC News
James Webb super-telescope arrives at launch site
The successor to the Hubble Space Telescope reaches French Guiana to prepare for a December launch.