የጎግል የ1 ቢሊዮን ዶላር እቅድ ለአፍሪካ ኢንተርኔት
****************************
ጎግል በአፍሪካ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግ የአንድ ቢሊዮን ዶላር እቅድ ማውጣጡን አሳወቀ፡፡ ጎግል ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው በአፍሪካ ያለው በወጣቶች የተሞላ የዘርፉ ገበያ እና እያደገ የመጣው ስማርት ስልክ የመጠቀም ልምድ በአህጉሪቱ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግ እንዳነሳሳው ያመለክታል፡፡
ይህ በአምስት አመታት ውስጥ ይፈጸማል የተባለው የጎግል እቅድ የተለያዩ ጉዳዮችን ለመተግበር የታሰበ ሲሆን ከእነዚህም ለአፍሪካውያን ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የባህር ውስጥ ገመድ ዝርጋታ ይገኝበታል፡፡ የጎግል የአፍሪካ ተወካይ የሆኑት ኒቲን ጋጅሪያ ይህ የጎግል ሀሳብ አለማችን ወጥ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖራትና ኢንተርኔት በአለማቀፍ ደረጃ ተደራሽና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል የታለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ተወካዩ አክለውም በአፍሪካ የሚገኘውን ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ሳናካትት አለማቀፍ ተደራሽነትን ማሰብ የማይቻል በመሆኑ ጎግል ይህን እቅድ ማውጣቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ አለም ባንክ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ ካሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከሶስቱ አንዱ አሁንም የብሮድባንድ መስመርን የሚጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ አህጉሪቷ ከሌሎች የአለማችን ክፍሎች የተሻለ የወጣት ሀይልና የገበያ አማራጭ እንዳላት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ 300 ሚሊዮን የሚደርሱ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሲሆን የጎግል እቅድ ተፈጻሚ በሚሆንባቸው በመጭዎቹ አምስት አመታት ውስጥ በእጥፍ አድጎ 600 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የጎግል ኢኪዋኖ (Equiano) የተሰኘው የባህር ውስጥ የኢንተርኔት ገመድ አፍሪካን ከአውሮፓ ጋር በማገናኘት በ2022 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የገመድ ዝርጋታ ፕሮጀክቱ በ2019 ይፋ የተደረገ ሲሆን ስያሜውንም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበረውና ጸሐፊና የባሪያ ንግድን በመቃወም በሚታወቀው ኦላውዳህ ኢኪዋኖ ማስታወሻነት አግኝቷል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅም በአፍሪካ ያለውን የኢንተርኔት ዋጋ በ21 በመቶ እንደሚቀንሰውና ኔትወርኩም በቀጥታ በደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና በአትላንቲክ ደሴቷ ቅድስት ሄሌና ያልፋል ተብሏል፡፡
ምንጭ techxplore.
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-10-google-invest-bn-africa-internet.html

Tech Xplore
Google to invest $1 bn to lift Africa internet access
Google announced Wednesday that it would invest $1 billion in boosting Africa's internet access and startup scene, as the tech giant eyes a youthful market increasingly armed with smartphones.
ሁለት ተመራማሪዎች በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
====================
ጀርመናዊው ቤንጃሚን ሊስት እና ብሪታንያዊው ዳቪድ ማክሚላን በኬሚስትሪ ዘርፍ የ2021 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ሽልማቱ ለተመራማሪዎቹ የተበረከተው የኬሚካል አፀግብሮትን ማከናወን የሚያስችል እና የኬሚካል ባለሙያዎችም የግራ እና የቀኝ ሞለኪውሎችን እንዲመርጡ የሚያስችለል አዲስ አይነት ካታሊስት ይዘው በመምጣታቸው ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ የተመራማሪዎቹ ስራ እንደ መድሃኒት ቅመማ ባሉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ከአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም በፊት የኬሚካል አፀግብሮቶችን ለማከናወን ሁለት ዓይነት ካታሊስቶችን ብቻ ነበር መጠቀም የሚቻለው፡፡ የመጀመሪያው በመቶ አልያም በሺዎች የሚቆጠሩ አሚኖ አሲዶችን አንድ ላይ በመደርደር የሚከናወነው የኢንዛይም ካታሊስት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የብረት ካታሊስቶች ናቸው፡፡
አሁን ላይ በአንድ የጀርመን የድንጋይ ከሰል ጥናት ተቋም ውስጥ የሚሰራው ቤንጃሚን ሊስት ታድያ አንድን አፀግብሮት ካታላይዝ ለማድረግ ሙሉ ኢንዛይምን ከማድረግ ይልቅ ፕሮላይን የተባለ አሚኖ አሲድን በመጠቀም ሙከራውን አድርጓል፤ በዚህም ስኬታማ ውጤትን ማግኘት ቻለ፡፡
ዳቪድ ማክሚላን በበኩሉ በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኮፐር አተምን በሚይዝ አነስተኛ ሞለኪውል መልኩ የብረት ካታሊስቶች ላይ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ሞለኪውል የተረጋጋ ባለመሆኑ የብረት አተሞችን ያልያዙና ካርበን ያለባቸው የተፈጥሮ ሞለኪውሎችን ለመጠቀም ወሰነ፤ በዚህም እንደ ቤንጃሚን ሁሉ እርሱም ስኬታማ ሊሆን ችሏል፡፡
የሁለቱ ተመራማሪዎች ስራ የተፈጥሮ ሞለኪውሎች እንደ ካታሊስት ሆነው ማገልገል እንደሚችሉ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳይቷል፡፡ በዋናነትም አነስተኛ የተፈጥሮ ካታሊስቶች ሞለኪውሎችን የግራ እና የቀኝ አድርጎ (Handedness) ለማግኘት አስችለዋቸል፡፡
ምንጭ፤ ኒው ሳይንቲስት
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2292772-chemistry-nobel-awarded-for-technique-to-produce-mirror-molecules/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1633565735

New Scientist
Chemistry Nobel awarded for technique to produce mirror molecules
The 2021 Nobel prize for chemistry has been awarded to Benjamin List and David MacMillan for developing catalysts that produce molecules of a desired left or right "handedness"
የፌስቡክ ለሰዓታት መቋረጥ ከ 70 ሚሊዮን በላይ አዲስ ተጠቃሚዎችን ያስገኘለት ቴሌግራም
=======================
የመልዕክት መላላኪያ አገልግሎት በማቅረብ የሚታወቀው የቴሌግራም መተግበሪያ ሰኞ ዕለት በአለም አቀፍ ደረጃ ፌስቡክን ጨምሮ ዋና ዋና የሚባሉት የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ለሰዓታት ከስራ ውጭ መቆየታቸውን ተከትሎ አምስት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዲስ ተጠቃሚዎች ሊያገኝ እንደቻለ ተገልጿል፡፡ የፕላትፎርሙ መስራች ፓቬል ዱሮቭ እንዳሉት በሁሉም የዓለም ክፍል ያሉ ሰዎች የመልዕክት መላላኪያ አገልግሎት የሚያገኙባቸው ፌስቡክ እና በሱ ስር ያሉት እንደ ዋትሳፕ፣ ኢንስታግራምና ሜሴንጀር ያሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለሰዓታት መቋረጥ ባልተለመደ ሁኔታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን ቁጥር በብዙ ሚሊዮን እንዲጨምር እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ ተቋርጦበት የነበረው ፌስቡክ በዕለቱ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች የመልዕክት መላላኪያ አገልግሎት ለማግኘት ሞክረው ሳይችሉ መቅረታቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የተቋረጠበት ሁኔታም የአሰራር ስህተትን ለማስተካከል በተደረገ ጥረት የመጣ ብልሽትን መሆኑንና የማስተካከያ ሂደቱም ውስጣዊ መንገዶቹን ጭምርም ከስራ ውጪ ያደረገ እንደነበር ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ ለሁሉም የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንደፌስቡክ ያለ የማህበራዊ ማገናኛ ሚዲያ ትልቅ ሚና ከመጫወቱ አንጻር በአገልግሎቱ ላይ የሚፈጠር የሰዓታት መቋረጥ ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንደዘርፉ ባለሙያዎች እምነት በሰዎች የኑሮ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ሚና እየኖረው የመጣው ፌስቡክ መስል ችግር ባጋጠመው ቁጥር በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳያስከትል በሱ ልክ አግልግሎት መስጥት የሚችሉ እና እንደአማራጭ የሚቀርቡ ሌሎች የመገናኛ ፕላትፎርሞች በበዛት ሊኖሩ እንደሚገባ ያስረዳሉ፡፡ እነኝህ ባለሙያዎች እንደሚሉት የፌስቡክና ሌሎች መሰል ፕላትፎርሞች ለሰዓታት ከስራ ውጭ መቆየት ተከትሎ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ቴሌግራም ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎች እንዲያገኝ ያስቻላው ይህ ክስተት ሌሎች ተፎካካሪ የመገናኛ ፕላትፎርሞች እጅግ እንደሚያስፈልጉ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡
እንደአውሮፓውያኑ በ2013 ኒኮላይ ዱሮቭ እና ፓቬል ዱሮቭ በተባሉ ሁለት ወንድማማቾች በሩሲያ የበለፀገውና ኋላም በጀርመኗ በርሊን ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው የቴሌግራም መተግበሪያ በቀላል አጠቃቀሙና በአነስተኛ ወጪው ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በብዙ የአለማችን ክፍል ብዙ ተጠቃሚዎችን እያፈራ የሚገኝ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፉም ሌላ አማራጭ ሆኖ የቀረበ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም ነው፡፡
https://www.reuters.com/technology/telegram-founder-says-over-70-mln-new-users-joined-during-facebook-outage-2021-10-05/

የኤሌክትሪክ ኃይልን ያለ ገመድ በአየር ላይ የሚያስተላልፈው ቴክኖሎጂ
================
ስዊድናዊው የቴሌኮምዩኒኬሽን ኩባንያ ኤሪክሰን ፖወርላይት ቴክኖሎጂስ ከተባለው የአሜሪካን ኩባንያ ጋር በመተባበር ለ5ጂ ጣብያዎቹ በብርሃን አማካኝነት ኃይልን በአየር ላይ አስተላልፎ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኤሌክትሪክን በአየር ላይ ማስተላለፍ ከዚህ ቀደም ያልታየ ቴክኖሎጂ አይደለም፤ አሁን ላይ ብዙዎች ገመድ አልባ የተንቀሳቃሽ ስልክ እና ሌሎችንም ቻርጅ ማድረጊያ መሳርያዎችን በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም በነዚህ መሳርያዎች ላይ ያለው በአየር ላይ ኃይልን ማስተላለፍያ ቴክኖሎጂ በአጭር እንጂ ረዘም ባለ ርቀት ላይ ለመስራት ይቸገራል፡፡ ታድያ ሁለቱ ኩባንያዎች ይህን ችግር ለመቅረፍ ኦፕቲካል ቢሚንግ የተባለውን ስርዓት በመጠቀም ኃይልን በሚለቀቅ ብርሃን አማካኝነት በማሰራጨትና ኃይሉን የሚቀበለው ጣብያም ይህን በአየር ላይ የሚላክለትን ከፍተኛ ብርሃን ተቀብሎ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል በመቀየር እንዲጠቀም የሚያደርጉት ይሆናል፡፡
ሁለቱ ኩባንያዎች ባከናወኑት ሙከራ ኃይልን ከአንድ ኃይል መላክያ ጣብያ 300 ሜትር ርቆ ወደሚገኝ የኤሪክሰን 5ጂ ራዲዮን ጣብያ በመላክ ቴክኖሎጂው ውጤታማ መሆን እንደሚችልም አሳይተዋል፡፡ በሙከራው ላይ 48 ዋት የሚሆን ኃይል የተላለፈ ቢሆንም ኤሪክሰን ግን በዚህ መንገድ የሚተላለፈውን ኃይል እስከ 1 ሺህ ዋት ማድረስ እንደሚቻል ጠቁሟል፡፡ እዚህ ላይ በመብራት አማካኝነት የሚተላለፈው ኃይል ለሰው ልጆችም ሆነ እንስሳት ጤና አስጊ እንዳይሆን በመስጋት ብርሃኑን አቋርጦ የሚያልፍ ሰው ወይም እንስሳ ሲመጣ መለየት የሚችሉ ሴንሰሮች ተካተውበታል፡፡ በዚህም ብርሃኑን አቋርጦ የሚተላለፈው ሰው አቋርጦ እስኪጨርስ ድረስ የሚተላለፈውን ብርሃን በመግታት ጣብያው ለጊዜው በባትሪ ኃይል ብቻ እንዲሰራ የሚያደርጉት ይሆናል፡፡
ፓወርላይት እንደሚለው ከሆነ ኃይል ተቀባዮቹ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ የሚችሉ በመሆናቸው ከ5ጂ ጣብያዎች ባሻገርም እንደ ሙዚቃ ኮንሰርት እና ሰው አልባ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች ባሉት ላይ የመዋል አቅም አላቸው፡፡ ሌሎች በበኩላቸው ቴክኖሎጂው የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ቻርግ ለሚያደርጉ ጣብያዎች ኃይል ለማቅረብ፣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የማስተካከል ስራን ቀለል ለማድረግ ወይም በተፈጥሮ አደጋና ጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች ላይ ኃይልን በቶሎ ለመመለስ እንደሚያስችል ይገልፃሉ፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-10-optical-power-portable-5g-base.html

Using optical beaming to power a portable 5G base station
Telecommunications company Ericsson has teamed up with a company called PowerLight Technologies to send power through the air to run a 5G base station. Both companies have posted the details on their ...
የራንሰምዌር ጥቃት መከሰቻ እና መከላከያ መንገዶች
===========================
በአሁኑ ወቅት የሳይበር ጥቃት በአይነትም፣ በመጠንም በዝቶ ተጠቃሚዎችን በከፍተኛ ስጋት ላይ በመጣል ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም እየተለመዱ ከመጡ የጥቃት አይነቶች መካከል ኢንፎርሜሽንን ማገት ወይም ራንሰምዌር የሚባለው ጥቃት ይጠቀሳል፡፡ ራንሰምዌሮች ባእድ የሆኑ አጥፊ ሶፍትዌሮች ሲሆኑ ሶፍትዌሮቹ ዲዛይን ሲደረጉ የኮምፒውተር ሲስተሞችን በመዝጋት ለተዘጋው ሲስተም ክፍያ እንዲፈጽሙ በማሰብ የተዘጋጁ አጥፊ ሶፍትዌሮች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የእነዚህ ራንሰምዌሮች ጥቃት እየረቀቀና እየሰፋ ብዙ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡
የራንሰምዌር ጥቃት ከማልዌር ቤተሰብ የሚመደብ ሲሆን ጠቃሚ ሶፍትዌር ወይም ፋይል እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልግ ማስጠንቀቂያ (Popup notification) በመምሰል ኮምፒዩተራችን ላይ ከጫንነው በኋላ የተወሰኑ ወሳኝ ፋይሎችን ወይም ኮምፒዩተሩን በአጠቃላይ በመመስጠር ወይም (Encrypt በማድረግ) ፋሎቹን መክፈት እንዳንችልና ተደራሽ እንዳይሆኑ የማድረግ ተግባር ይፈፅማል፡፡ ይህንን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ፋይሎቹን ወይም ኮምፒዩተሩን ተጠቃሚዎች መጠቀም ከፈለጉ በቢትኮይን እና በሌሎች የኦንላይን የመክፈያ ስርአቶች በመጠቀም እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና ተጠቃሚዎች ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ ገንዘቡ ከተከፈለም በኋላ ኮምፒውተሩ ወይም ሲስተሙ መለቀቁ ዋስትና አለመኖሩ ይህን የቫይረስ ጥቃት ለየት ያለ ያደርገዋል፡፡
ኮምፒውተር በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ የራንሰምዌር ማልዌር ጥቃት ሊጋለጥ የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል በኦፕሬቲንግ ሲስተም ዲዛይን ላይ በሚፈጠር ችግር፣ በአንድ ኔትወርክ ውስጥ ሁሉም ኮምፒውተሮች ተመሳሳይ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም ለተጠቃሚዎች በርካታ ፈቃዶችን የሚሰጥ ከሆነ በቀላሉ ለጥቃት ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ራንሰምዌር ከአጥፊ ሶፍትዌሮች መካከል አንዱ እና በአለማችን ትልቁ የሳይበር ምህዳር ስጋት እንደመሆኑ መጠን በየጊዜው በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ሁለንተናዊ ጉዳት በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም፡፡ በፈረንጆቹ 2019 ብቻ በራንሰምዌር አማካኝነት በተፈጸም የሳይበር ጥቃት 11.5 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ ኪሳራ ተመዝግቦ እንደነበር መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ይህ የሳይበር ስጋት ባለፉት ሁለት ዓመታትም ይበልጥ አየጨመረ ይገኛል፡፡
እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች የተጠቃሚውን መረጃ በመቆለፍ የመረጃው ባለቤት ያከማቸውን ዳታ መመልከት እንዳይችል በማድረግ የሚፈጸም የሳይበር ወንጀል በመሆኑ ብዙዎች ወሳኝ የሚሉትን መረጃ መልሰው ለማግኘት ለጥቃት አድራሹ ክፍያ ለመፈፀም ሊጋፋፉ ይችላሉ፡፡ ይሁንና ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው አንዴ ገንዘብ ተከፍሎ መረጃው ለባለቤቱ በአስተማማኝ ሁኔታ ይመለሳል የሚለው እና ከዚህ በኋላም ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ ለጥቃት አድራሾች ምንም አይነት ገንዘብ አለመክፈል በብዙዎች የሚመከረው ጉዳይ ነው፡፡
በዚህ የሳበር ጥቃት ዙሪያ የተሰሩ የቅርብ ጥናቶች እንደሚሳዩት የራንሰምዌር ቫይረስ የማኒዩፋክቸሪን ዝርፉን በዋናነት ኢላማ እያደረገ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዛ በተጨማሪም የፋይናንስ ዘርፉ፣ ትራንስፖርት፣ የጤና ተቀዋማት እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡ ሳይበር ክራይም የተባለ አለም አቀፍ ጋዜጥ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው የራንሰምዌር ጥቃት በአለማችን ዙሪያ በየአስራ አንድ ሰኮንዱ በአንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ላይ የሚደርስ ሲሆን እስከ 2021 አጋማሽ ብቻ 1,097 በሚሆኑ አነስተኛና ትላልቅ ተቋማት ሊደርስ ችሏል፡፡
ይህ የሳይበር ስጋት በየትኛውም ሁኔታና አጋጣሚ የግል ኮምፒውተራችንን አልያም የተቋም ሰርቨርና የኔትወርክ ደህንነትን አደጋ ውስት ሊከት በመቻሉ ሁልግዜም ወሳኝ የምንላቸውን የመረጃ ግልባጭ ወይም (Back up) መያዝና ማስቀመጥ እጅግ የሚመከር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ አደገኛ ሶፍትዌሮች በግል ኮምፒውተራችንን እና በተቋሞቻችን ሃብት ላይ ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ልንወስዳቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥንቃቄዎች መካከል ሁሉንም አይነት ሶፍትዌሮች፣ አፕሊኬሽኖችንና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን በየወቅቱ ማሻሻል፤ የታደሱ ፀረቫይረሶችን በመጠቀም በየጊዜው ኮምፒዩተራችንን ስካን ማድረግ፤ ተጋላጭነታችን ሊያሰፉ ከሚችሉ አጠራጣሪ ድረ-ገፅች፣ መተግበሪዎችና ፋይሎች ረሳችንን መጠበቅ፤ የማናውቃቸውን ኢሜይሎች አለመክፈትና የተላኩ አባሪዎችንም ዳውንሎድ አለማድረግ፤ በየጊዜው የሚመጡ ማስታወቂያዎችን ምላሽ ከመስጠታችን በፊት በጥንቃቄ መመልከት እና የራንሰምዌር ጥቃት እየደረሰ መሆኑ ከታወቀ ባለሙያ በማማከር ማልዌሩን በአፋጣኝ ማጥፋትና ቫይረሱ ወደሌሎች እንዳይሰደራጭ ጥቃት የደረሰበትን ኮምፒውተር ለይቶ ማስቀመጥ እጅግ ይመከራል፡፡
https://www.trendmicro.com/.../secu.../definition/ransomware

በህክምና ዘርፍ የዚህን ዓመት ኖቤል ያሸነፉት አሜሪካዊያን ተመራማሪዎች
=================
የ2021 በፊዚዮሎጂ እና ህክምና ዘርፍ የሰው ልጆች በንክኪ ጊዜ ከሚፈጠርባቸው ስሜት ጀርባ ያለውን ሚስጥር የፈቱት ዴቪድ ጁሊየስ እና አርደም ፓታፑሻን የተባሉ ሁለት አሜሪካዊያን ተመራማሪዎች የኖቤል ሽልማትን ማሸነፋቸው ከቀናት በፊት ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የሚያገለግሉት ዴቪድ ጁሊየስ ካፕሴያሲን የተባለ ከሚጥሚጣ የተሰራ ጠንካራ ቃና ያለውና የማቃጠል ስሜትን የሚፈጥር ውህድን በመጠቀም የቆዳ ነርቭ ጫፍ የሆነውንና ለሙቀት ምላሽ የሚሰጠውን ሴንሰር በመለየታቸው የሽልማቱን ግማሽ ሲወስዱ ከስክሪፕስ ጥናት ኢንስቲትዩት የሆኑት አርደም ፓታፑሻን በበኩላቸው ለግፊት ሴንሴቲቭ የሆኑ ሕዋሳትን በመጠቀም በቆዳ እና ውስጣዊ የሰውነት አካላት ውስጥ ለሚፈጠር ሜካኒካዊ ለውጥ (Stimuli) ምላሽ የሚሰጡ ሴንሰሮችን በማግኘታቸው ቀሪው የሽልማቱ ግማሽ ተበርክቶላቸዋል፡፡
የሁለቱ ተመራማሪዎች ግኝት ሙቀት፣ ቅዝቃዜ እና ሜካኒካዊ ኃይል የነርቭ ግፊትን እንዴት እንደሚቀሰቅሱ በማሳየት በዙርያችን ያለውን ዓለም እንድንረዳ እና እንድንላመድ ማስቻሉን የገለፀው የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ይህ ዕውቀት ለተለያዩ በሽታዎች ህክምናን በማፈላለግ ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ሽልማቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡
እ.አ.አ ከ1990ዎቹ አንስቶ ተመራማሪዎቹ እንዴት በቆዳ ላይ የሚፈጠር ሙቀት እና ግፊትን ወደ ነርቭ ተልኮ አንጎላችን እንደሚረዳው ለማወቅ ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ዴቪድ ጁሊየስ እና ባልደረቦቻቸው በሴንሰር ነርቮች ውስጥ ያሉ በራሒዎችን የያዙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዘረ-መል አካላትን በማሰባሰብ ነበር ስራቸውን የጀመሩት፡፡ በራሒዎችን በተለምዶው ለካፕሴያሲን ምላሽ የማይሰጡ ህዋሳት ውስጥ አንድ በአንድ እየጨመሩ በመሞከር ላይ ሳሉ በስተመጨረሻ ከካፕሴያሲን ጋር በተገናኘ የማቃጠል ስሜትን የሚፈጥረውን አንድ በራሒ ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህ ያገኙት በራሒ ሕዋሳት ቲአርፒቪ1 የተሰኙትንና ህመም የሚፈጥር ሙቀት ሲኖር የሚነቃቁትን ፕሮቲኖች እንዲገነቡ የሚያስችል ነው፡፡
ዴቪድ ጁሊየስም ሆነ አርደም ፓታፑሻን በየግላቸው ሜንቶልን በመጠቀም ቲፒአርኤም8 የተሰኘ በቅዝቃዜ ወቅት የሚነቃቃ አንድ ፕሮቲንን እንዲሁም በተለያዩ የሙቀት ደረጃዎች ውስጥ የሚነቃቁ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮቲኖችን ለማግኘት ችለዋል፡፡ በዚህ ስራ ላይ በመንተራስ አርደም ፓታፑሻን ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በሰሩት የምርምር ስራ አማካኝነት አንደኛው በራሒ ሕዋሳት በተቀሰቀሱ ቁጥር ትናንሽ የኤሌክትሪክ ሲግናሎችን እንዲያመነጩ እንደሚያደርግ መረዳት ቻሉ፡፡ ይህ ተመራማሪዎቹ ያገኙት ሪሴፕተር ታድያ ሜካኒካዊ ኃይላትን ሴንስ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ከመሆንም ባሻገር የደም ስሮችንም ደህንነት የሚጠብቅ እና የሰውነትን የደም ግፊትንም የሚያስተካክል ነው፡፡ የሰውነትን አቋም እና እንቅስቃሴ ሴንስ በማድረግ ረገድ ወሳኝ የሆነው ሌላኛውን የፕሮቲን ሪሴፕተር ካገኙ በኋላ ሁለቱን ሪሴፕተሮች ፒኤዞ 1 እና ፒኤዞ 2 ብለው ሰይመዋቸዋል፡፡
እነዚህ ግኝቶች እንደ ሙቀት እና ግፊት ያሉት ነገሮች እንዲሰሙን የሚያደርገንን ነገር ለማብራራት እንዲቻል ከማድረግም ባሻገር እንደ በሽታ ማስታገሻ መድሃኒት ያሉ አዳዲስ መድሃኒቶች እንዲፈጠሩ መንገዱን ጠርገዋል፡፡
ሁለቱ ተመራማሪዎች ለየዘርፉ አሸናፊዎች የሚበረከተውን 10 ሚሊዮን የስዊድን ክሮና ወይም 1.15 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ለሁለት የሚካፈሉት ይሆናል፡፡
ምንጭ፤ ላይቭ ሳይንስ
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/nobel-prize-in-medicine-won-by-us-scientists-who-unlocked-the-secrets-of-our-sense-of-touch

livescience.com
Nobel prize in medicine won by US scientists who unlocked the secrets of our sense of touch
The research gave us a mechanistic insight into two of our most fundamental sensory experiences.
አየርን ተጠቅሞ ውሃ የሚያመርተው ማሽን
============
መቀመጫውን ሀገረ አሜሪካን ካሊፎርኒያ ውስጥ ባደረገው ሱናሚ ፕሮዳክትስ የተባለ ኩባንያ አማካኝነት የተሰራው ማሽን ዝናብም ሆነ ወንዝ ሳያስፈልገው ከአየር ላይ ውሃን በመሰብሰብ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሰዎችም ገዝተው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ አየርን ወደ ውሃ የሚያሸጋግረው ማሽኑ ልክ እንደ አየር ማቀዝቀዣ ማሽን ሁሉ ኮይሎችን ተጠቅሞ አየሩን በማቀዝቀዝ የሚሰራ ሲሆን ከቀዘቀዘው አየርም የሚንጠባጠብ ውሃን በመሰብሰብ ለተጠቃሚዎቹ ያቀርባል፡፡
በኩባንያው ውስጥ ሆኖ የማሽኑን ንድፍ የሰራው ቴድ ቦውማን እንደሚለው ውሃን ከአየር ላይ መሰብሰቡ ምትሃት ሳይሆን የሚሰራ ሳይንስ ነው፡፡ እርሱ እንደሚያስረዳው በኩባንያ አማካኝነት የተሰራው ይህ ማሽን አየር ላይ ያለውን እርጥበት በመሰብሰብ የተጣራና ለመጠጥ የሚውል ውሃን ለቤት እና ቢሮ ጨምሮ የተለያዩ ቦታዎች ማቅረብን ያለመ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይ ጭጋጋማ በሆኑ አካባቢዎች በተሻለ መስራት የሚችል ሲሆን እንደ ማሽኑ መጠን ቢለያይም በቀን ከ900 እስከ 8,600 ሊትር ውሃ ማምረት ይችላል፡፡ ከጭጋጋማ አካባቢዎች ባለፈ ግን ማንኛውም አይነት ወበቅ ባለባቸው እንደ ባህር ዳርቻ ባሉ ቦታዎች ላይ መስራት ይችላል፡፡
ነገር ግን የማሽኑ ዋጋ የሚቀመስ አይደለም፤ እንደየ አይነቱ ቢለያይም ማሽኑ ከ30 ሺህ እስከ 200 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድረስ ያስወጣል፡፡ ቀረጥ እና ሌሎች ወጪዎችን ወደ ጎን ትተን ይህን ዋጋ አሁን ባለው የምንዛሬ ተመን ወደኛ ብንመልሰው ታድያ ከ1.4 እስከ 9.3 ሚሊዮን ብር እንደማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማሽኑ ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይልን ይጠቀማል፡፡ ሆኖም ይህ ከፍተኛ ዋጋ በከፍተኛ ድርቅ እና ውሃ እጥረት እየተመታ ባለው የካሊፎርኒያ ግዛት ያሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ማሽኑን ገዝተው ከመጠቀም አላገዳቸውም፡፡ አንዳንዶች በማሽኑ አማካኝነት የመጠጥ ውሃን ከማግኘትም ባሻገር ለአትክልት ማጠጫ ጭምር የሚተርፍ ውሃን እያገኙበት ናቸው፡፡
ማሽኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ውሃን ከወበቃማ አየር ለመሰብሰብ እየሰሩ ካሉ በርካታ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ምንጭ፤ አሶሼትድ ፕረስ
ለተጨማሪ፤ https://apnews.com/article/science-technology-lifestyle-business-california-bf3a376a4a23ab4ac88dfdb834613114

AP News
In dry California, some buy units that make water from air
Some residents in the drought-parched U.S. West are turning to pricey machines that developers say can produce hundreds of gallons of water a day, literally out of thin air.
ሙሉ በሙሉ በሮቦቶች ቁጥጥር ስር የወደቀው የኒሳን መኪና ፋብሪካ ስራ
===================
ከቶኪዮ ወጣ ብሎ የሚገኘውና ቶቺኚ ተብሎ የሚጠራው የኒሳን አስተዋይ የመኪና ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ሰዎች ብዙም አይታዩበትም፡፡ በፋብሪካው ሮቦቶች ይበይዳሉ፣ ይገጣጥማሉ፣ መኪናዎቹን ቀለም ይቀባሉ እንዲሁም የቀቡትን መልሰው የመገምገም ስራን ይሰራሉ፡፡ የኒሳን ምክትል ፕሬዘዳንት ሂዲዩኪ ሳካሞቶ እስከ አሁን ድረስ የምርት ማስተካከያዎች በልምድ ይሰሩ እንደነበር ገልፀው አሁን ግን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚታገዙት ሮቦቶቹ የሚሰበሰቡ ጥሬ ሀቆችን ጭምር መተንተን የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ይላሉ፡፡
በወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባ የሚነገርለት ፋብሪካው በኤሌክትሪክ፣ ነዳጅ እና በሁለቱ ቅልቅል (ሀይብሪድ) የሚሰሩ መኪኖችን በአንድ መስመር እንደሚገጣጥም ይጠበቃል፡፡ በፋብሪካው የሚገኙት ግዙፍ ሜካኒካዊ እጆች በተገጠመላቸው ብርሃን መርጫ እና ካሜራ አማካኝነት በተለያዩ አቅጣጫዎች ምልከታን በማድረግ ለማየት የምታዳግተው ትንሿን ችግር እንኳን ለይተው ያወጣሉ፡፡ በፋብሪካው የሚገኝ ማግኔትን ተክቶ በብረት ላይ ገመድን የሚጠመጥም አዲስ ስርዓትም በብዛት የማይገኙ ማዕድናትን ከመጠቀም እንደሚያድነውና በዚህም የምርት ወጪዎን እንደሚቀንስለት ኒሳን ይናገራል፡፡
እንደ ኒሳን ከሆነ በቶቺኚ ፋብሪካ የሚተገበሩ ኢኖቬሽኖች በመላው ዓለም በሚገኙት ሌሎች በእርሱና እህት ኩባንያው በሆነው የፈረንሳዩ ሬኖ ስር በሚገኙ መኪና አምራች ፋብሪካዎች የሚተገበሩ ይሆናል፡፡ የጉልበት ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ለሮቦቶቹ መሰጠታቸውን ተከትሎም በፋብሪካው የሚገኙ ሰራተኞች በሮቦቶቹ የሚሰበሰብ መረጃን መተንተን እና መሳሪያዎችን መጠገን በመሳሰሉ ሌሎች ክህሎትን በሚጠይቁ ስራዎች ላይ በይበልጥ የሚሰማሩ ይሆናል፡፡
ሙሉ በሙሉ በሮቦት መስራቱ ምን ያህል ወጪ እንደሚቆጥብለት ሂዲዩኪ ሳካሞቶ ባይናገሩም የምርት ስራዎች በኮቪድ 19 ሳብያ ከመጡ የሰራተኛ እጥረቶች እንዲሁም ከባቢ አየር ተስማሚነት ጋር የተላመዱ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
መቀመጫውን በጃፓን ያረገው ግዙፉ ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ ኒሳን እ.አ.አ በ2050 ከካርበን የፀዳ የምርት ሂደትን ለመከተልና የምርት ግብዓቶቹንም ዳግም ጥቅም ላይ በማዋል ሂደት ለመጠቀም አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ በአልሙኒየም የሚሰራው የመኪናዎቹ አካልን እና ለወትሮ ለየት ባለ ቦታ በተለየ የሙቀት ደረጃ የሚቀቡት የፕላስቲክ መጋጫቸውን አንድ ላይ በመቀባት ብቻ የኃይል ፍጆታውን በ25 በመቶ መቀነስ እንደሚችል ይናገራል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከኒሳን በተጨማሪ ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ የመኪና አምራች ኩባንያዎች ገበያው ለሚጠይቀው ምላሽ መስጠት ያስችላቸው ዘንድ የሮቦት ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ፡፡
ምንጭ፤ አሶሼትድ ፕረስ
ምንጭ፤ https://apnews.com/article/technology-business-japan-84a67e7273b32a15a9e6ee1502b57d86

Smart robots do all the work at Nissan's 'intelligent' plant
Nissan’s “intelligent factory” hardly has any human workers. The robots do the work, including welding and mounting.
የማዕድን ቁፋሮ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ከብክለት መጠበቅ
*******************************
በአለማችን በኮፐር ምርቷ የምትታወቀው እና ካላትም ገቢ ውስጥ 15 በመቶውን በዚሁ ማዕድን የምትሸፍነው ችሊ በማዕድን ቁፋሮ አካባቢዎች ብክለት ላይ ለመስራት መዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡ በተለያዩ በብረት ቁርጥራጮች የተበከለን አካባቢ ብረትን በፍጥነት በመብላት በሚታወቅ ባክቴሪያ አማካኝነት ለማጽዳት መታሰቡ ተነግሯል፡፡
በዘርፉ ላይ ምርምር እያደረገች ያለችው ችሊያዊቷ ተመራማሪ ናዳክ ሪሌስ ከሳንቲያጎ ከተማ በስተ ሰሜን 1100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ከተማ በተገነባ ቤተ ሙከራ ውስጥ ምርምሯን እያካሄደች ነው፡፡ በሙከራውም ጊዜ ባክቴሪያው አንድን ሚስማር በሶስት ቀን ውስጥ በልቶ መጨረስ መቻሉ ተረጋግጧል፡፡
የ33 ዓመቷ የባዮ-ቴክኖሎጂ ተመራማሪ እንስት በአደገኛ አካባቢዎች የሚገኝን ደቂቅ ዘአካል በመጠቀም ነው ምርምሯን እያከናወነች ያለችው፡፡ ተመራማሪዋ የችሊን የኮፐር ምርት ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶችን እየደረገች በነበረበት ወቅት ይህ በብረት ቁርጥራጮች የሚፈጠር ብክለትን እንዴት መቀነስ ይቻላል የሚል ሀሳብ እንደመጣላት ትናገራለች፡፡
የብረት ቁርጥራጭን ሰብስቦ በማቅለጥ ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል አንደኛው መንገድ መሆኑ ቢታወቅም መሰብሰብ የማይችሉ በተቃራኒው ደግሞ የስራ አካባቢን የሚበክሉ ቁርጥራጮችን በዚህ መልክ ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተመራማሪዋ ታስገነዝባለች፡፡
አሁን ላይ ተመራማሪዋ የራሷን Rudanac Biotec የተሰኘ ድርጅት በማቋቋም ሌፕቶስፕሪሊየም የተሰኘ ብረት በል ባክቴሪያ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ነው፡፡ ይህ የባክቴሪያ ዝርያ በአሲዳማ መሬት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በመደበኛ አኗኗር አንድን ሚስማር ለመብላት ወደ ሁለት ወራት ያክል ይወስድበት ነበር፡፡ ተመራማሪዋ ባክቴሪያውን እንዲራብ በማድረግ ሚስማሩን በልቶ ለመጨረስ የሚጨርስበትን ጊዜ ወደ ሶስት ቀን ማሳነስ መቻሉን ተናግራለች፡፡
ውጋጅ ብረቶችን በባክቴሪ በማስበላት የሚገኘው ተረፈ ምርት በፈሳሽ መልክ የሚገኝ ሲሆን ይህ ፈሳሽ ምርት ሀይድሮሜታለርጂ በተሰኘ ሒደት የኮፐር ፍለጋውን ለማገዝ እንደሚጠቅም ተነግሯል፡፡ ይህም እንደ ተመራማሪዋ እምነት ከብክለት ነጻ የሆነ የማዕድን ፍለጋ ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ምዕራፍን የሚከፍት ግኝት ነው፡፡
ምንጭ phys
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-10-chilean-scientist-metal-bacteria.html

phys.org
Chilean scientist plans to clean up mining with 'metal eating' bacteria
Starving microorganisms capable of surviving in extreme conditions have already managed to "eat" a nail in just three days.
ልቡ ውስጥ ሲሚንቶ የተገኘበት ታካሚ
=============
አንድ የ56 ዓመት ጎልማሳ ከ10 ሴ.ሜ የሚልቅ ሲሚንቶ በደም ስሩ ውስጥ ተላልፎ ልቡ ውስጥ እንደተገኘበት ተዘገበ፡፡ ይህ ሰው ለሁለት ቀናት ያህል ያጋጠመውን የደረት ህመም እና ለመተንፈስ መቸገር ተከትሎ ወደ ድንገተኛ ክፍል ካመራ በኋላ ነው ሲሚንቶው በውስጡ የተገኘበት፡፡
ህመሙ ከማጋጠሙ ከአንድ ሳምንት በፊት ቨርተብራል ኮምፕረሽን ፍራክቸር ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ ህመምን የሚፈጥርና በጥንካሬ ማጣት ሳብያ የጀርባ አጥንት ክፍል በራሱ ላይ በሚናድበት ወቅት የሚከሰት የጤና እክልን የሚያስተካክል ህክምናን አከናውኖ ነበር፡፡ ይህ ሰው ታድያ ከህመሙ ይድን ዘንድ ካይፎፕላስቲ ተብሎ የሚጠራውን ሀኪሞች በዓይነቱ የተለየ ሲሚንቶ ወደ አከርካሪዎቹ በማስገባት ወደ ትክክለኛ ቁመቱ የሚመልሱበት እና እንዳይናድ የሚያደርጉበት የህክምና ዓይነት ተከናውኖለታል፡፡
ህክምናው ደህነቱ የተጠበቀ ስለሆኑ ቢመሰከርለትም ህመሙ ከገጠማቸው ሰዎች ውስጥ ግን ሁለት በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ይህ ዓይነቱ ህክምና የሚደረግላቸው፡፡ ታድያ በዚህ የህክምና ስልት ላይ ሊፈጠሩ ከሚችሉት ችግሮች መካከል ሲሚንቶው ከአጥንቶቹ አፈትልኮ ወጥቶ ወደ ሌሎች የሰውነት አካባቢዎች በመሰራጨት የደም ስርን መዝጋት ነው፡፡ በዚህ ታማሚ ላይም የሆነው ይኸው ነው፤ ሲሚንቶው አፈትልኮ ወጥቶ ወደ ደም ስሮቹ ውስጥ የገባ ሲሆን በዚያም ከጠነከረና ከተቆራረጠ በኋላ ወደ ልቡ ሊጓዝ ችሏል፡፡
ታማሚው ድንገተኛ ክፍል ውስጥ በገባበት ወቅት የኤክስ-ሬይ እና ሲቲ ስካን ምልከታዎች ሲደረግለት ነው ባዕድ ነገር በሰውነቱ ውስጥ ስለመኖሩ የተደረሰበት፡፡ በማስከተል ድንገተኛ የልብ ቀዶ ህክምና ሲደረግለት ሀኪሞቹ ቀጭን እና ሹል የሆነ የሲሚንቶ ግግር በላይኛው የቀኝ ልብ ክፍሉ እና የቀኝ ሳንባው ውስጥ ሊያገኙ ችለዋል፡፡ ሀኪሞቹ ሲሚንቶውን ሲያወጡት 10.1 ሴ.ሜ የሚረዝም ሆኖ ሲያገኙት ካወጡት በኋላም ሲሚንቶው ልቡ ላይ የፈጠረው ስንጥቃት የሚጠግን ህክምና በሀኪሞቹ ተደርጎለታል፡፡
ታካሚው ይህን ቀዶ ክህምና ተከትሎ ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመውም፤ ከአንድ ወር ቆይታ በኋላም ሙሉ በሙሉ አገግሞ ወደ ቀድሞ ጤናው ስለመመለሱ ከሳምንት በፊት በኒው ኢንግላንድ የህክምና ጆርናል ላይ ታትሞ በወጣው ጥናታዊ ፅሁፍ ሪፖርት ተደርጓል፡፡
ምንጭ፤ ላይቭ ሳይንስ
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/cement-heart-spinal-procedure.html

How did cement end up in a man's heart?
A 4-inch piece of cement had pierced the man's heart and lung.