TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በቻይና የተገነባው የዓለማችን ትልቁ የስነ ፈለክ ሙዚየም
በቻይና የተገነባው የዓለማችን ትልቁ የስነ ፈለክ ሙዚየም
==================
በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት የሆነውና የቻይና የንግድ ከተማ በሆነችው ሻንጋይ ውስጥ የተገነባው አዲስና አስደናቂ ቤተ-መዘክር (ሙዚየም) በሆነ የህዋ ምርምር ሳይንስን ከውብ ኪነ-ህንፃ ጋር አዋዶ የተገነባ ነው፡፡ የሻንጋይ ስነ ፈለክ ቤተ-መዘክር የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አስደናቂ ህንፃ የኮስሞስን ጂኦሜትሪ እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ ተገንብቷል፡፡ በዚህም ምንም አይነት ቀጥተኛ መስመርም ሆነ 90 ዲግሪ ያለው ጥግ ጥቅም ላይ ያልዋሉበት ነው፡፡

39 ሺክ ካሬ ስፋት ያለው ቤተ-መዘክሩ የሻንጋይ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቤተ-መዘክር አካል ነው፡፡ በውስጡም የአወደ ርዕይ፣ ጠፈርን መመልከቻ (planetarium)፣ ኦብዘርቫቶሪ እና ወደ 24 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ፀሐይን መመልከቻ ቴሌስኮፕን ይዟል፡፡

የቤተ-መዘክሩ ንድፍ አውጪዎች እንደሚሉት ህንፃው ስነ-ፈለክን (ህዋ ምርምር) በኪነ-ህንፃ ለመግለፅ ያለመና ያለ ምንም ቀጥተኛ መስመሮች በክብ ቅርፅ ብቻ መገንባቱ በዩኒቨርስ ውስጥ ሁሉም ነገር በተለያዩ ኃይላት ቁጥጥር ስር ሆኖ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘቱን ለማሳየት የሚጥር ነው፡፡ በተጨማሪም “ስሪ ቦዲ ፕሮብሌም” ተብሎ በሚታወቀውና እስካሁንም ምላሽ ያላገኘው የሦስቱ አካላት ማለትም የከዋክብት፣ ፕላኔቶች እና ጨረቃዎች በስበት ላይ የተመሰረተ ሦስትዮሻዊ የጋራ እንቅስቃሴያቸውን ከሚመለከተው ሒሳባዊ ስሌትን መነሻ ሀሳብ ስለማገግኘታቸውም የኪነ-ህንፃ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡ ይህም ሙዚየሙ ላይ በሦስቱ የህንፃው አካላት ተገልጿል፡፡

በዚህም ጎብኚዎች ወደ ህንፃው ሲገቡ ሰዓቱ በተለዋወጠ ቁጥር ጊዜ እና ወቅትን በሚያመላክት መልኩ የሚሽከረከር የፀሐይ ብርሃንን በክብ ቅርፅ ወለሉ ላይ በሚያስተላልፈው ክፍል ይገባሉ (ምስል ሁለትን ይመልከቱ)፡፡ ከዚህ በመቀጠል ግዙፍና በኳስ ቅርፅ ተሰርቶ እየተንሳፈፈ ያለ የሚመስል መዋቅር ወዳለበት ክፍል ይገባሉ (ምስል ሦስትን ይመልከቱ)፡፡ በስተመጨረሻም ጎብኚዎች ከላይ ወደታች የተገለበጠ የመስታወት ጉልላት ወዳለበት ክፍል በመግባት በተለይ የምሽቱን ሰማይ ሽቅብ መመልከት ይችላሉ (ምስል ሦስትን ይመልከቱ)፡፡

የሙዚየሙን ንድፍ የሰራውና በቻይና እንዲሁም አሜሪካን ቢሮዎች ያሉት ኤናድ አርክቴክትስ ከዚህ ቀደም በኒው ዮርክ የሚገኘውን እውቁን ሮስ የመሬት እና ህዋ ማዕከልን (የአሜሪካን የተፈጥሮ ታሪክ ቤተ-መዘክር አካል) ንድፍ ከሌሎች ጋር በመሆን ሰርቷል፡፡

ምንጭ፤ ሲኤንኤን
ለተጨማሪ፤ https://edition.cnn.com/style/article/shanghai-astronomy-museum-ennead-architects-scn/index.html
በዓለም ዙርያ ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው ፌስቡክ
በዓለም ዙርያ ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው ፌስቡክ
==============
የዓለማችን ትልቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ፌስቡክ ለስድስት ሰዓታት ያህል ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ ትናንት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1 ሰዓት አንስቶ የጀመረው ይህ የአገልግሎት መቋረጥ ለስድስት ሰዓታት ከቆየ በኋላ ነው ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ የድርጅቱ አገልግሎቶች በሂደት መመለስ የጀመሩት፡፡ ታድያ ብልሽቱ ከፌስቡክ ባሻገር በኩባንያው ስር የሚገኙትን ኢንስታግራም እና ዋትሳፕንም ጭምር ያጠቃለለ ነበር፡፡

ፌስቡክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ችግሩ የአሰራር ስህተትን ለማስተካከል በተደረገ ጥረት አማካኝነት የመጣና ብልሽትን የማስተካከያ ውስጣዊ መንገዶቹን ጭምርም ከስራ ውጪ ያደረገ እንደነበር አስታውቋል፡፡ አክሎም አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው ሰዓታት የተጠቃሚዎቹ መረጃ ስጋት ውስጥ እንደነበር የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደሌለ ገልጿል፡፡ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከምበርግ በበኩሉ ለነበረው የአገልግሎት መቋረጥ ይቅርታውን አቅርቧል፡፡

ከሦስቱ የፌስቡክ ገፆች ባሻገር የኩባንያውን የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሄድሴት አገልግሎት አቅራቢ ኦኪውለስ እና ሌሎች እንደ ፖኪማንጎ ያሉት በፌስቡክ በኩል መግባትን የሚጠይቁ መተግበሪያዎችም አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው ሰዓታት ውስጥ እንዲሁ እክል አጋጥሟቸው ቆይተዋል፡፡

ፌስቡክ በተለያዩ ጊዜያት ቴክኒካዊ ችግሮች ሊያጋጥሙት ቢችልም ጉዳዮቹ ግን በፍጥነት የሚፈቱ ናቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር ችግሮቹ ሲከሰቱ በብዛት በአንድ አካባቢ ነው፤ ለምሳሌ ገፁ በአንድ ሀገር እየሰራ በሌላኛው ግን ይበላሻል፡፡ ነገር ግን የትናንቱ አገልግሎት መቋረጥ አንድን አካበባቢ ወይም ሀገር ብቻ የነካ ሳይሆን መላው ዓለምን የሸፈነ ነበር፡፡ ፌስቡክ መሰል ከፍተኛ የሆነና ለረጅም ሰዓታት የዘለቀ የአገልግሎት መቋረጥ ተደጋግሞ ሲገጥመው አይታይም፡፡ ኩባንያው በዚህ ልክ ከፍተኛ የአገልግሎት መቋረጥ ሲያጋጥመው የትናንትናው ከሁለት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ በአውሮፓውያኑ 2019 ያጋጠመው የያኔው የአገልግሎት መቋረጥ ፌስቡክ እና በስሩ የሚገኙ አብዛኛዎቹ መተግበሪያዎች ለ14 ሰዓታት ያህል አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ አስገድዷቸው ነበር፡፡

የድ-ገፆችን አገልግሎት መቆራረጥ በመከታተል የሚታወቀው ዳውንዲቴክተር የተባለው ገፅ ታድያ የአገልግሎት መቋረጡ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው ደረጃ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር ገልጿል፡፡

ፌስቡክ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ችግር ውስጥ ሲገባ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ የአገልግሎት መቋረጡ ተከስቶ ከነበረበት ከአንድ ቀን በፊት የቀድሞው ሰራተኛው ኩባንያው ከደህንነት በላይ ለእድገቱ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ሲቢኤስ ከተባለው የአሜሪካን መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ማሳወቋ በከፍተኛ ደረጃ ሲያወያይ ነበር፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ
ለተጨማሪ፤ https://www.bbc.com/news/technology-58793174
የዌቢናር ጥሪ
የዌቢናር ጥሪ
=======
የኢትዮ-ጀርመን ኢንኪዩቤሽን እና ስታርታፕ ፕሮሞሽን ፕሮግራም በሚል የተዘጋጀው አዲሱ የዌቢናር መርሃ ግብር የፊታችን ጥቅምት 3 እና ጥቅምት 18 የሚከናወን ይሆናል፡፡ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከጀርመን የኢነርጂና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የበይነ-መረብ ሴሚናር በዋናነት ለሁሉም የግል እና የመንግስት ኢንኪዩቤተሮች፣ በቴክኖሎጂ ስታርታፕ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና በዘርፉ እየተንቀሳቀሱ ላሉ የኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች ማህበር አባላት የልምድ ማግኛ መድረክ እንዲሆን በሚል የተዘጋጀ መርሃ-ግብር ነው፡፡

በዚህ ዌቢናር በኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም ዘርፉ ላይ የብዙ ዓመት ልምድ ያላቸው የጀርመን ኢንኪዩቤተሮች በቢዝነስ ሞዴል፣ የፋይናስ አቅም በመፍጠር፣ በጀርመን ስላለው የኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም ድጋፍ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተሞክሮዎችን በማንሳት በዘርፉ ላይ እንዴት ስኬት ማምጣት እንደሚቻል ሰፊ ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች የሚነሱ ሃሳቦችን በሰፊው ለመመልከትም የጥያቄና መልስ ክፍል በመርሃ-ግብሩ ተካቷል፡፡
All private and public incubators are cordially invited to participate in the Ethio-German Incubation and Startups Program
1. Incubator Untenrehmer TUM GmbH, Munich, Germany
• Speaker: Mr. Stefan Drüssler, CEO
• Date and Time: 13 October, 2021, 10:00-11:30 AM (Nairobi Time)
2. Incubator Digital HUB Logistics, Dortmund, Germany
• Speaker: Mr. Thorsten Hülsmann, Hub Manager
• Date and Time: 28 October, 2021, 10:00 AM -12:00 PM (Nairobi Time)

በሁለት የተለያዩ ቀናት በሚደረገው በዚህ ዌቢናር መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች ያሉትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ ትችላላቹ
1 https://us04web.zoom.us/j/71290108442?pwd=TWd1Qk5hSERzazE3NTYyNmhaa3dzZz09

2 https://us04web.zoom.us/j/74594426306?pwd=RFhYMWZoMnNjSHRVdVZodDBsK0F2Zz09
ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ተሳትፈውባት የነበረችው ሶፊያ ሮቦት በዚህ ዓመት በብዛት ልትመረት ነው
========================
መቀመጫውን በሆንኮግ ኮንግ ባደረገው እና ሀንሰን ሮቦቲክስ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በዋና መሪነት የተሰራችው ሶፍያ ሮቦት ከ50 የሚበልጡ የፊት ገለጻዎችን ማሳየት የምትችል መሆኗ ለየት ያደርጋታል። ሶፍያ ይህን ለማድረግ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (artificial intelligence) የሚባለውን ግሩም ቴክኖሎጂ ከማካተቷ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎች አሻራቻን ያሳረፉባት አስገራሚ የቴክኖሎጂ ግኝት ናት። ከአመታት በፊት አይኮግ ላብስ በተባለው ድርጅት የታቀፉ ኢትዮጵያውን ባለሙያዎች የሮቦቷን አካል ከሰራው ሀንሰን ሮቦቲክስ ኩባንያ ጋር በመተባባር ለሶፍያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቀመሮችን በማዘጋጀት ስራ ላይ በዋናነት ሲሰራ መቆዩታቸው የሚታወቅ ሲሆን ሮቦቷን ወደ ውጤት በማምጣት ሂደት ላይም የራሳቸውን ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

እንደአውሮፓውያኑ በ2016 ለአለም የተዋወቀችው ይህች ሮቦት የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከሚባሉት የምትመደብ ቢሆንም ከሷ በፊትና ከሷ በኋላ ከተሰሩት ማሽኖች እጅግ የሚለይ ባህሪዎችና ገፅታዎች የተላበሰች ሮቦት ናት፡፡ እስካሁን በዚህ ዘርፍ ከተሰሩት ማሽኖች ከሰዎች ጋር ባላት ግንኙነት እና እንደየሁኔታው በሚያጋጥሟት ክስተቶች እንደ መቆጣት፣ ማዘን እና መደሰት ያሉ ሰውኛ ባህሪዎችን ለመሳየት መቻሏ ሶፊያን ከሌሎች የማህበራዊ ሚና ካላቸው ሮቦቶች ለየት የሚደርጋት ነው፡፡ ሶፊያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያላት እና በማህበራዊ ሚና ላይ ለሰዎች ይበልጥ የቀረበች ሮቦት ብትሆንም በብዛት የመመረት እድል ስላልነበራት ወደብዙዎች መድረስ አለመቻሏን የሚያስረዱት የሀንሰን ሮቦቲክስ መስራች ዴቪድ ሃንሰን አሁን ላይ ከኮቪድ መምጣት ጋር ተያይዞ ሮቦቷን በብዛት አምርቶ ወደገበያ ለማቅርብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከወራት በፊት ይህን እቅድ በመሬት ላይ በማውረድ በብዙዎች የምትታወቀውን የሶፍያ ሮቦት እስከአመቱ መጨረሻ በሺዎች በመማረት ለገበያ ለማቅርብ እየሰራ መሆኑን የሚናገሩት ዴቪድ ሃንሰን አሁን ባለንበት አለም እንደሶፊያ ያሉ ማህበራዊ ሚና ያላቸው አውቶሜትድ ማሽኖች አቅመ ደካሞችን ያለመሰልቸት ለመርዳት እና የታመሙ ሰዎችንም ለማገዝ ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ያነሳሉ፡፡ አሁን ላይ ብዙ በሮቦቲክስ ዙሪያ የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶችን በብዛት በማምረት ላይ የሚገኙ ሲሆን እንደ ሃዩንዳይ ያሉ ትልልቅ ኩባንያዎች ሳይቀር በዘርፉ ላይ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ከዚህ በፊት የተሰሩ እንደ ሚሎ ያሉ የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከኦቲዝም ጋር የተያያዘ የጤና እክል ያለባቸው ህጻናትን ስሜቶቻቸውን አውጥተው አንዲናገሩ በማስቻል የተግባቦት አቅማቸውን ሊያስድጉ መቻላቸውን የሚናገሩት የዘርፉ ባለሙያዎች መሰል የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች በየቀኑ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን ያለመስለቸት በመስራት የታመሙ ሰዎች ለመርዳት እና አቅመ ደካሞችን ለማገዝ ጥሩ አማራጭ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰፊ እውቅና ያላት የሶፍያ ሮቦት እንዲህ ያሉ ማህበራዊ ተግባሮችን ለመከወን የሚስችል የስሜት ተለዋዋጭነት እና የበዛ የቋንቋ ክህሎት የታከለባት ሮቦት እንደመሆኗ መጠን ተቀባይነቷን እንደሚጨምረው የባለሙያዎች አስተያየት ነው፡፡
https://bigthink.com/technology-innovation/sophia-the-robot-hanson-robotics/
ሦስት ተመራማሪዎች የዘንድሮውን የፊዚክስ ዘርፍ ኖቤል ሽልማት አሸነፉ
ሦስት ተመራማሪዎች የዘንድሮውን የፊዚክስ ዘርፍ ኖቤል ሽልማት አሸነፉ
=================
ሸኩሮ ማናቤ፣ ክላውስ ሀስልማን እና ጆርጂኦ ፓሪሲ የተሰኙት ተመራማሪዎች የዘንድሮው የፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ትናንት ይፋ ተደርጓል፡፡ ከተመራማሪዎቹ መካከል ሸኩሮ ማናቤ እና ክላውስ ሀስልማን ለአሸናፊነት የበቁት የምድራችንን አየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተፅዕንዖ የሚያመላክት የኮምፒውተር ሞዴልን ባስገኘው ፈር ቀዳጅ ጥናታቸው አማካኝነት ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን የረጅም ጊዜ ባህርይ ለመተንበይ እጅግ አዳጋች የሚባል ተግባር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የበካይ ጋዞች ልቀት የሚያመጣውን ለውጥ የሚተነብዩ እና የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመረዳት ጥቅም ላይ የሚውሉ የኮምፒውተር ሞዴሎች እጅጉን አስፈላጊ ናቸው፡፡ በሁለቱ ተሸላሚዎች ጥናት ላይ ተመስርተው የተሰሩት የአየር ንብረት ለውጥን መመልከቻ የኮምፒውተር ሞዴሎች ታድያ የዓለም መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ስለማድረጋቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

የጃፓን ተወላጅ እና የ90 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት ሸኩሮ ማናቤ በአሜሪካን የፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ አንጋፋ ሚቲዮሮሎጂስት ሲሆኑ በጥናታቸውም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ በካይ ጋዝ በምድር ላይ የሚያስከትለውን የሙቀት መጨመር አሳይተዋል፡፡ በዚህም እ.አ.አ 1960ዎቹ የአየር ንብረት አካላዊ ሞዴል እንዲሰራ የመሪነት ሚናን ተጫውቷል፡፡

ከሸኩሮ ማናቤ ስራ አስር ዓመት በኋላ ደግሞ አሁን 89ኛ ዓመት ዕድሜያቸው ላይ የሚገኙት ክላውስ ሀስልማን አየር ፀባይ እና አየር ንብረትን ያስተሳሰረ የኮምፒውተር ሞዴል ይዘው መጥተዋል፡፡ ይህ ስራቸው ታድያ የአየር ንብረት ሞዴሎች የአየር ፀባዩ የሚለዋወጥ ቢሆን እንኳን ለምን እምነት የሚጣልባቸው እንደሆኑ አሳይቷል፡፡

የ73 ዓመቱ ተመራማሪ ጆርጂኦ ፓሪሲ ስራ በበኩሉ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ያለው ግንኙነት ያን ያህል ነው፡፡ ስራቸው ስፒን ግላስ የተሰኘ አተሞች ከኮፐር አተሞች መስመር ጋር የሚዋሀድበት የሜታል አሎይን ይመለከታል፡፡ ነገር ግን የኖቤል ኮሚቴው የጆርጂኦ ፓሪሲ ስራ ውስብስቡን የምድር አየር ንብረት ባህርይ በመረዳት ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘው ለሽልማቱ ተመርጠዋል፡፡ ጆርጂኦ ፓሪሲ በዚህ ስራቸው በጠጣር ቁሶች ዘፈቀዳዊ ባህርይ ላይ ተፅዕንዖ የሚያሳድሩ ድብቅ ሕጎችን ማግኘትና በሒሳባዊ ስሌትም ማብራራት ችለዋል፡፡

ለተመራማሪዎቹ ለሽልማት ከቀረበው ገንዘብ ውስጥ አስር ሚሊዮን የስዊድን ክሮና ወይም 842,611 ፓውንድ የሚሆነውን ሸኩሮ ማናቤ እና ክላውስ ሀስልማን የሚካፈሉት ሲሆን የተቀረው ለጆርጂኦ ፓሪሲ ይበረከታል፡፡

የኖቤል ሽልማት መሰጠት ከተጀመረበት ከአውሮፓውያኑ 1901 አንስቶ ባሉት 120 ዓመታት ውስጥ 218 ሰዎች በፊዚክስ ዘርፍ ያሸነፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ግን አራቱ ብቻ ሴቶች ናቸው፡፡ በሌላ መልኩ ጆን ባርደን በፊዚክስ ዘርፍ ኖቤልን ሁለት ጊዜ በማሸነፍ (በአውሮፓውያኑ 1956 እና 1972) እስካሁንም ብቸኛው ሰው ሆነው ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ
ለተጨማሪ፤ https://www.bbc.com/news/science-environment-58790160
ሕዋ ላይ ያተኮረ የሥዕል ውድድር፤ በኢትዮጵያ
===============
ሴቶች በሕዋ በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዚህን ዓመት የዓለም የሕዋ ሳምንትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የሥዕል እና ዲጂታል ምስል ውድድርን ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ተወዳዳሪዎች የሚያዘጋጇቸው ሥዕል እና ዲጂታል ምስሎች ሦስት አባይት ጉዳዮችን የተመለከቱ እንዲሆኑ ድርጅቱ ያስታወቀ ሲሆን እነዚህም፤
• ኢትዮጵያ፤
• ሴቶች፤
• ሕዋ ናቸው፡፡
በውድድሩ አንድ ሰው አንድ ስራ ብቻ እንዲልክ የሚፈቀድለት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ስራቸውን እስከ ቀጣይ ሳምንት ረቡህ ጥቅምት 3 2014 ዓ.ም ድረስ መላክ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ በዲጂታል መልኩ የሚልኩት ስራ ከ100 ሜጋባይት ያልበለጠና በJPEG ወይም PNG መልኩ የሚቀርብ መሆን አለበት፡፡
በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለመሆን እና ስለ ውድድሩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፤ https://forms.gle/i3gUASEFfytzzUQ7A
ምንጭ፤ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ
አመላካች ጥናቶች አተገባበር እና በኢኖቬሽን ዘርፉ ያላቸው ሚና
አመላካች ጥናቶች አተገባበር እና በኢኖቬሽን ዘርፉ ያላቸው ሚና
=================================
አሁን ባለንበት የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የኢኮኖሚ እድገትን የሚያንቀሳቅስ ዋነኛ ሞተር ሲሆን፤ አገራዊ የኢኖቬሽን ስርዓት (Innovation System) በተቀላጠፈ መልኩ መንቀሳቀስ ደግሞ ቀጣይነት ያለው እድገትና ልማትን ለማስመዝገብ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ሀገራት ይህንን ከግንዛቤ በማስገብት በአገር ደረጃ የተቀመጡ ስትራቴጂክ ግቦችን ከግብ ለማድረስ ስርዓቱን ለማጠናከር ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የተጠናከረ የኢኖቬሽን ስርዓት ለመገንባት በውስጡ ያሉ ዋና ዋና ተዋንያን መንግስት፤ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የንግድ ተቋማት፣ የሙያ ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በጋራ መስራት አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ነው። እነዚህም ተዋንያን ተሳስረው በመስራት አገሪቷ ከኢኖቬሽን ውጤቶች የገበያ ተደራሽነት ተጠቃሚ መሆን እንድትችል ጠንካራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የኢኖቬሽን ፖሊሲ ቀርፆ ለተግባራዊነቱ መስራት አስፈላጊ ነው።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ አመላካች ጥናት ውጤቶችን በግብዓትነት መጠቀም የፖሊሲውን ተፈፃሚነትና ስኬታማነት የሚወስኑ ወሳኝ ምክንያቶች ናቸው። የሳይንስና ቴክኖሎጂ አመላካች ጥናቶች አብዛኛውን ጊዜ የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትስስርና ልማት ድርጅት (Organisation for Economic Co-operation and Development) የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመከተል የሚሰሩ ሲሆኑ የተለያዩ አገራት ያሉበትን ደረጃ ለመለካትና ንፅፅሮችን ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣሉ።

ከሳይንስና ቴክኖሎጂ አመላካች ጥናቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የኢኖቬሽን አመላካች ጥናት በአንድ አገር በንግድ ተቋማት ተሰርተው ወደ ገበያ የገቡ ኢኖቬሽኖችን (በምርት፣ በምርት ሂደት፣ ተቋማዊ አወቃቀር እና የግብይት ስርዓት) ደረጃ ለመለካት፤ ከመንግስት ለንግድ ተቋማቱ የኢኖቬሽን እንቅስቃሴዎች የተበረከቱ የገንዘብ ድጋፎችን፤ በንግድ ተቋማት መካከል፣ በንግድ ተቋማትና በመንግስት መካከል እንዲሁም በንግድ ተቋማትና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ኢኖቬሽንን ከማሳደግ አንፃር አብሮ የመስራት ባህል ምን ደረጃ ላይ እንዳለ፤ በንግድ ተቋማቱ ያሉ ኢኖቬሽኖችን ለማበልፀግ አስፈላጊና ወሳኝ የነበሩ የመረጃ ምንጮችን፤ የንግድ ተቋማት የምርምርና ስርፀት የማካሄድ አቅምን እና በንግድ ተቋማቱ የኢኖቬሽን እንቅስቃሴዎች መሰናክል የሆኑ ጉዳዩችን በጥልቀት ይዳስሳል። በተጨማሪም ቁልፍና ጠቃሚ የሆኑ የፖሊሲ ግብዓቶችን በማካተት ለፓሊሲ አውጪ አካላት ጠቃሚ መረጃዎችን ያቀብላል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የሃገራችንን የኢኖቬሽን ትግበራ ሂደት በሁሉም ዘርፍ እየዋለ ያለበት ሁኔታ ለመገምገም እና በተለያዩ የማመላከች መነፅሮች ለይቶ ለማስቀመጥ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በየወቅቱ አሳትሞ የሚያወጣቸው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አመላካች ጥናቶች ትልቅ ጥቅም የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተለይም ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለውጭና ለሃገር ውስጥ ተመራማሪዎች ለጥናታቸው መነሻ የሚሆኑ ወሳኝ የመረጃ ግብዓቶችን በስፋት በማቅረብ የኢኖቬሽን ስርዓታችንን በሚገባ ለመገምገም እና የፖሊሲውን ተፈፃሚነትና ስኬታማነት ለመፈተሽ ትልቅ ሚና የሚኖራቸው ይሆናል፡፡
https://www.sciencedirect.com/.../pii/S016649721730140
ቻይናዊያን ተማሪዎች ለረጅም ሰዓት የምትበር ድሮን በመስራት ክብረ ወሰን ሰበሩ
ቻይናዊያን ተማሪዎች ለረጅም ሰዓት የምትበር ድሮን በመስራት ክብረ ወሰን ሰበሩ
==================
በቻይናዊያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች መሳርያ አልባ ድሮን ያለ እረፍት ለረጅም ሰዓት የበረረች ድሮን በመባል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች፡፡ ፌንግ አርዩ 3-100 የተሰኘችው ይህች በቤጂንግ የኤሮናቲክስ እና አስትሮናቲክስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች ድሮን ያለ ማቋረጥ ለ80 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ በመብረር ነው ቀድሞ በቦይንግ ስር በሚተዳደረው ኦሪዮን በተሰኘ ተቋም በ80 ሰዓት፣ ከ2 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ያሻሻለችው፡፡

የክንፍ ርዝማኔዋ 10 ሜትር የሆነው ድሮኗ በጋዝ ሞተር አማካኝነት የምትንቀሳቀስና ጠቅላላ ክብደቷም (የተሞላባትን ነዳጅ ጨምሮ) 60 ኪ.ግ ነው፡፡ ስያሜዋም የቻይና አቪዬሽን ኢንዱስትሪ አባት ከሚባሉት ከፌንግ ሩ የተወረሰ ነው፡፡

በረራው የተከናወነው ባሳለፍነው ግንቦት ወር በቻይና ሄናን ግዛት ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም ክብረ ወሰኑ ገና ባሳለፍነው እሁድ ነው በዓለም አቀፉ የኤሮናቲክስ ፌደሬሽን (FAI) እውቅና የተሰጠው፡፡ በበረራው ወቅት ድሮኗ በ300 ሜትር ከፍታ ላይ ስትጓዝ የነበረች ሲሆን በአየር ላይ እያለችም ምንም አይነት ተጨማሪ ነዳጅ እንዳይሞላላት ተከልክላ ነበር፡፡

እንደ ዩኒቨርሲቲው መረጃ ከሆነ ድሮኗን የሰራው የተማሪዎቹ ቡድን 25 ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ያቀፈ ነው፡፡ የተማሪዎቹ አማካኝ ዕድሜም ከ20 ዓመት በታች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፤ ሺኑዋ
ለተጨማሪ፤ http://www.news.cn/english/2021-10/05/c_1310227678.htm
የጎግል የ1 ቢሊዮን ዶላር እቅድ ለአፍሪካ ኢንተርኔት
የጎግል የ1 ቢሊዮን ዶላር እቅድ ለአፍሪካ ኢንተርኔት
****************************
ጎግል በአፍሪካ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግ የአንድ ቢሊዮን ዶላር እቅድ ማውጣጡን አሳወቀ፡፡ ጎግል ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው በአፍሪካ ያለው በወጣቶች የተሞላ የዘርፉ ገበያ እና እያደገ የመጣው ስማርት ስልክ የመጠቀም ልምድ በአህጉሪቱ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማሳደግ እንዳነሳሳው ያመለክታል፡፡

ይህ በአምስት አመታት ውስጥ ይፈጸማል የተባለው የጎግል እቅድ የተለያዩ ጉዳዮችን ለመተግበር የታሰበ ሲሆን ከእነዚህም ለአፍሪካውያን ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የባህር ውስጥ ገመድ ዝርጋታ ይገኝበታል፡፡ የጎግል የአፍሪካ ተወካይ የሆኑት ኒቲን ጋጅሪያ ይህ የጎግል ሀሳብ አለማችን ወጥ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖራትና ኢንተርኔት በአለማቀፍ ደረጃ ተደራሽና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል የታለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ተወካዩ አክለውም በአፍሪካ የሚገኘውን ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ሳናካትት አለማቀፍ ተደራሽነትን ማሰብ የማይቻል በመሆኑ ጎግል ይህን እቅድ ማውጣቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ አለም ባንክ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ ካሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከሶስቱ አንዱ አሁንም የብሮድባንድ መስመርን የሚጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ አህጉሪቷ ከሌሎች የአለማችን ክፍሎች የተሻለ የወጣት ሀይልና የገበያ አማራጭ እንዳላት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ 300 ሚሊዮን የሚደርሱ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሲሆን የጎግል እቅድ ተፈጻሚ በሚሆንባቸው በመጭዎቹ አምስት አመታት ውስጥ በእጥፍ አድጎ 600 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጎግል ኢኪዋኖ (Equiano) የተሰኘው የባህር ውስጥ የኢንተርኔት ገመድ አፍሪካን ከአውሮፓ ጋር በማገናኘት በ2022 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የገመድ ዝርጋታ ፕሮጀክቱ በ2019 ይፋ የተደረገ ሲሆን ስያሜውንም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበረውና ጸሐፊና የባሪያ ንግድን በመቃወም በሚታወቀው ኦላውዳህ ኢኪዋኖ ማስታወሻነት አግኝቷል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅም በአፍሪካ ያለውን የኢንተርኔት ዋጋ በ21 በመቶ እንደሚቀንሰውና ኔትወርኩም በቀጥታ በደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና በአትላንቲክ ደሴቷ ቅድስት ሄሌና ያልፋል ተብሏል፡፡

ምንጭ techxplore.
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-10-google-invest-bn-africa-internet.html
ሁለት ተመራማሪዎች በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሁለት ተመራማሪዎች በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
====================
ጀርመናዊው ቤንጃሚን ሊስት እና ብሪታንያዊው ዳቪድ ማክሚላን በኬሚስትሪ ዘርፍ የ2021 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ሽልማቱ ለተመራማሪዎቹ የተበረከተው የኬሚካል አፀግብሮትን ማከናወን የሚያስችል እና የኬሚካል ባለሙያዎችም የግራ እና የቀኝ ሞለኪውሎችን እንዲመርጡ የሚያስችለል አዲስ አይነት ካታሊስት ይዘው በመምጣታቸው ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ የተመራማሪዎቹ ስራ እንደ መድሃኒት ቅመማ ባሉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ከአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም በፊት የኬሚካል አፀግብሮቶችን ለማከናወን ሁለት ዓይነት ካታሊስቶችን ብቻ ነበር መጠቀም የሚቻለው፡፡ የመጀመሪያው በመቶ አልያም በሺዎች የሚቆጠሩ አሚኖ አሲዶችን አንድ ላይ በመደርደር የሚከናወነው የኢንዛይም ካታሊስት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የብረት ካታሊስቶች ናቸው፡፡

አሁን ላይ በአንድ የጀርመን የድንጋይ ከሰል ጥናት ተቋም ውስጥ የሚሰራው ቤንጃሚን ሊስት ታድያ አንድን አፀግብሮት ካታላይዝ ለማድረግ ሙሉ ኢንዛይምን ከማድረግ ይልቅ ፕሮላይን የተባለ አሚኖ አሲድን በመጠቀም ሙከራውን አድርጓል፤ በዚህም ስኬታማ ውጤትን ማግኘት ቻለ፡፡

ዳቪድ ማክሚላን በበኩሉ በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኮፐር አተምን በሚይዝ አነስተኛ ሞለኪውል መልኩ የብረት ካታሊስቶች ላይ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ሞለኪውል የተረጋጋ ባለመሆኑ የብረት አተሞችን ያልያዙና ካርበን ያለባቸው የተፈጥሮ ሞለኪውሎችን ለመጠቀም ወሰነ፤ በዚህም እንደ ቤንጃሚን ሁሉ እርሱም ስኬታማ ሊሆን ችሏል፡፡

የሁለቱ ተመራማሪዎች ስራ የተፈጥሮ ሞለኪውሎች እንደ ካታሊስት ሆነው ማገልገል እንደሚችሉ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳይቷል፡፡ በዋናነትም አነስተኛ የተፈጥሮ ካታሊስቶች ሞለኪውሎችን የግራ እና የቀኝ አድርጎ (Handedness) ለማግኘት አስችለዋቸል፡፡

ምንጭ፤ ኒው ሳይንቲስት
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2292772-chemistry-nobel-awarded-for-technique-to-produce-mirror-molecules/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1633565735
የፌስቡክ ለሰዓታት መቋረጥ ከ 70 ሚሊዮን በላይ አዲስ ተጠቃሚዎችን ያስገኘለት ቴሌግራም