TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሳይንስን በስልካችን
በእጆቻችን ላይ የሚገኙ ስማርት ስልኮቻችን ብዙ ነገሮችን እንድንከውን በሚያስችሉን ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ ታድያ ስልካችንን ለፎቶ መነሳት እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ፍጆታ ከማዋል ባለፈ ተከታዮቹን መተግበሪያዎች ተጠቅመን ሳይንስን በተለየ መነፅር መመልከት እንችላለን፡፡
1. eBird
በስነ-አዕዋፍ (Ornithology) ጥናት ላይ በተሰማራ ቤተ-ሙከራ የሚተዳደረው ይህ መተግበሪያ የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንድናውቅና እንድንመረምር ከማስቻል ባለፈ ከዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር ጭምር መረጃውን እንድንለዋወጥ ያደርገናል፡፡ በመተግበሪያው አድራሻችንን በማስገባት በዙሪያችን ያሉ ዝርያዎችን ማየት ስንችል የወፍ መገኛ ስፍራዎች ላይ በአጋጣሚ ከተገኘንም ያሳውቀናል፡፡ ታድያ ከበይነ መረብ ውጪም ስለሚሰራ ገጠራማ ቦታዎች ላይ አንቸገርም፡፡
2. Star Walk
Star Walk በአመሻሹ ሰማይ ካሜራችንን ወደ ከዋክብት እንድናማትር በማድረግ ብቻ በእይታችን ስለገቡትን ከዋክብት እና ፕላኔቶች ገለፃ ያደርግልናል፡፡ ከማርስ የፀሐይ መውጫና መጥለቂያ ሰዓት አንስቶ እጅግ የበዙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ያቀብለናል፡፡
3. NASA Globe Observer
ይህ መተግበሪያ ከቀድሞዎቹ በተለየ ወደ ረጂነት ይለውጠናል፡፡ በዳመና ሽፋን፣ መሬት ሽፋን እና ወባ ትንኝ ዙሪያ መረጃን የሚሰበስብ ሲሆን እኛም ቢሆን የምንመለከተውን ዳመና ፎቶ በማንሳት ለናሳ እንድናደርስና የአየር ፀባይን በመረዳት ረገድ ሚና እንድንጫወት ያደርገናል፡፡
4. MyShake
ለምርምር ታስቦ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰራ ሲሆን በዙሪያችን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴዎችን ያሳውቀናል፤ እኛ ላይ ቢከሰቱ ምን ማድረግ እንዳለብንም ይነግረናል፡፡ ሌላኛው የዚህ መተግበሪያ ስራ ስልካችን ላይ ተፅዕንዖ ሳያደርስ ያለንበትን ስፍራ የመሬት መንቀጥቀጥ ሁናቴ በመገምገም ምሁራኑ ግምቶችን እንዲያስተካክሉና ህይወትን እነዲያድኑ መረጃ ያቀብላል፡፡
5. The Elements (በክፍያ)
iOS በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን Periodic Table ላይ የሚገኙትን ንጥረ-ነገሮች አካላዊ ቅርፅ ከመረጃ ደብሎ ያደርሰናል፡፡ ለምሳሌ እያንዳንዱን ንጥረ-ነገር ዙሪያውን ባሻን አቅጣጫ እንድንቃኝና ብሎም ስለ ይዘቱ፣ የግኝት ታሪኩ፣ ጥቅሙ፣ የገበያ ዋጋው ወዘተ… ጥልቅ ትንታኔ ይሰጠናል፡፡
6. Wolfram Alpha (በክፍያ)
በድረ-ገፁ አማካኝነት የምናገኘው ይህ መተግበሪያ የፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ቀመሮችን፣ የቁሶችን ይዘት፣ የምድራችን ንብርብሮችን መረጃ፣ የከዋክብት ካርታን እና ሌሎች መረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ የሂሳብ ኢኩዌዥኖችን የማስላትና የአየር ሁኔታንም የማሳወቅ ስራ ይሰራል፡፡
7. Science Journal
ይህ የጎግል ምርት በዙሪያችን ያሉ ሁቴዎችን እንድንመዘግብ ያደርገናል፡፡ ለምሳሌ፡- የስልካችንን ሴንሰሮች በመጠቀም ብርሃን፣ ድምፅ፣ ግፊት፣ እንቅስቃሴን ያነባል፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት ከሌሎች ማሳሪያዎች ጋር በመቀናጀትም ይሰራል፡፡ ውጤቶችን በፎቶና ፅሁፍ ሲያስቀርልን እነዚህን መረጃዎች ወደ ሌሎች መሳሪያዎች በማስተላለፍ መጠቀም እንድንችልም ያደርገናል፡፡
ምንጭ፡- popular science
ሜዲካል ቱሪዝም
***************
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከሐገራቸው በመውጣት የሕክምና አገልግሎትን እንዲገኙ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ሜዲካል ቱሪዝም በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ኢንዱስትሪ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየገዘፈና በጤናው ዘርፍ የተሸለ ደረጃ ላይ የደረሱት ሐገራትንም ከቀን ወደቀን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ቁጥራቸው የበዛ ሐገራት እና ፖሊሲ አውጪዎቻቸውም በዘርፉ ላይ አይናቸውን ከጣሉ ሰነባብተዋል፡፡

ሜዲካል ቱሪዝም ከረጅም ጊዜያት አንስቶ ሲተገበር የቆየ የህክምናው ኢንዱስትሪ አካል ነው፡፡ በተወሰኑ ሐገራት ያሉት ፈዋሽ ፍል ውሃዎች ቀዳሚዎቹ የሜዲካል ቱሪዝም አስጀማሪዎች ነበሩ፡፡ ታድያ ከጥቂት አስርት ዓመታት ወዲህ በተወሰኑ የህክምና አገልግሎቶች ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ የዘርፍ ዕድገትን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ለዚህ የቁጥጥር ስርዓቶች፣ የቴክኖሎጂ ዕድገት፣ የባለ ዝቅተኛ ታሪፍ አየር መንገዶች መስፋፋት፣ በባህል ዙሪያ እየተቀየረ ያለው አመለካከት እና ሌሎችም በገፊ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የደቡብ ምስርቅ እሲያ፣ አውሮፓ እና ላቲን አሜሪካ ሐገራት ቀዳሚዎቹ የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ በመሆን ገበያውን ይመራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ እንደ ህንድ፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ብራዚል፣ ኩባ፣ ሜክሲኮ እና ኮስታ ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ ክልሎች ወጣ ብለው በተቀመጡት ደቡብ አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶችም የሜዲካል ቱሪዝም እንቅስቃሴ ጎልቶ በመታየት ላይ ነው፡፡ ለነዚህ ሐገራት ጎልቶ መውጣት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አንፃራዊ የዋጋ ልዩነት፣ የሐገራቱ ትስስር፣ የህክምናው ዓይነት፣ መልከዓ ምድራዊ ቅርበት እንዲሁም የጤና መሰረተ ልማት፡፡ ከነዚህ መካከል በህክምው ዓይነት ላይ የተመሰረቱትን ያየን እንደሆን በላቲን አሜሪካን ያሉ ሐገራት በጥርስ፣ ውፍረት ቅነሳ፣ ውበት እና ፕላስቲክ ቀዶ ህክምናዎች የጠነከረ ስምን ለመገንባት ችለዋል፡፡ ህንድን ጨምሮ እነደ ማሌዢያ፣ ሲንጋፖር እና ታይላንድ ያሉ የደቡብ ምስራቅ እሲያ ሐገራት ደግሞ በልብ እንዲሁም አጥንትና ጡንቻ ህክምናዎች ዝናን አግኝተዋል፡፡ ሌላው በዋጋ ረገድ ሐገራት ያላቸው ተመራጭነት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የደቡብ ምስራቅ እሲያ ሐገራት ባላቸው አንፃራዊ የዋጋ ቅናሽ ከበለፀጉት ሐገራት ጭምር ታካሚዎችን ለመሳብ ችለዋል፡፡

ሆኖም እንደሌሎቹ ዘርፎች ሁሉ የሜዲካል ቱሪዝምም ከተግዳሮቶች አላመለጠም፡፡ በተለይ በህክምና እንዲሁም ስነ-ምግባር እና ሕግ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያሉ ስጋቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ ለዚህ ሐገራት ያላቸው የተለያየ የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ፣ አሰራር እና ሕግጋት እንዲሁም እነዚህን ተከትሎ የሚመጣው የህምና ተቋማት እና ባለሙያዎች ደረጃ መለያየት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡

ወደ ሐገራችን ስንመጣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታካሚዎችን ወደ ውጪ ሐገራት በመስደድ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህም ለሐገራችን ሌላ ምጣኔ-ሐብታዊና ማሕበራዊ ጫና ይዞልን መጥቷል፡፡ ይህን ሁናቴ የሚለውጡና ሐገራችንን ወደ ሌላ የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻነት ከፍ የሚያደርጉ እርምጃዎችን መውሰድ ከመንግስትም ሆነ የግል ባለሐብቶች ይጠበቃል፡፡ ታድያ ምንም እንኳን በዘርፉ መሪ ወደሆኑት ሀገራት ለመጠጋት ረጅም ጊዜን የሚፈጅ ቢሆንም ባለንበት አካባቢ እንኳን የስበት ማዕከል የሚያደርጉንን ስራዎች መስራት ይገባናል፡፡

ምንጭ፡- News Medical
3ኛው ዓለም ዓቀፍ የICT ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ
*************
ኢኖቬት ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት የሚከናወነው 3ኛው ዓለም አቀፍ የICT ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል፡፡
የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሐገራችን ለገባችበት የለውጥ ምህዋር ስኬት ሳይንስና ኢኖቬሽን ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም የተለያዩ ዘርፎቻችን በቴክኖሎጂ በማገዝ ማበልፀግና ሐገራችንንም አሁን ካለችበት የቴክኖሎጂ ኋላ ቀርናት ማላቀቅ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው ዘርፉ ላይ በሚሰሩት ሐገሀራዊ እንዲሁም ተቋማዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያተኮረ ንግር ለታዳሚያኑ አድርገዋል፡፡ በሐገራችን የ25 ሺህ ኪ.ሜ ፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ መሆኑንና ከወረዳ አንስቶ ባሉት ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሴኮንድ እስከ 1 ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው የፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎትም ዝርጋታ በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡
በኤክስፖው ላይ በሐገር ውስጥ እና ዊጪ ሐገራት መሰረታቸውን ያደረጉ በርካታ የግል እንዲሁም የመንግስት ተቋማት ተሳታፊ የሚሆኑበት ሲሆን ቁጥሩ ከፍ ያለ ህብረተሰብም እንደሚጎበኘው ይጠበቃል፡፡
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የዕፅዋት ተከላን አከናወኑ
******************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስትቲውት ሰተራተኞች በዛሬው እለት የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ በመገኘት ዕፅዋትን ተክለዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የክፍያ መንዶች ኢንተርፕራይዝ ጋራ በጋራ የተከወነው ይህ የዕፅዋት ተከላ በዓመቱ አራት ቢሊዮን ዕፅዋትን ለመትከል የተያዘው ሐገራዊ ዕቅድ አካል ነው፡፡
ይህን ተግባር በማስመልከት ቃለ መጠይቅ ያደረግንላቸው የኢንስትቲውታችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ መሰል ክንውኖች ለተቋሙ አዲስ ሁነት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም በተያዩ ጊዜያት ዕፅዋትን የመትከል ስነ ስራ እንደተሰራ ገልፀውልናል፡፡ አያይዘውም የተጀመረውን ሐገር ዓቀፍ እንቅስቃሴ በበጎ በመመልከት ሌሎች አካላትም እንዲሁ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በዓመት ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በአየር መበከል ምክንያት ለህልፈተ ህይወት ሲዳረግ 2.4 ሚሊዮን የሚሆኑትም ደግሞ የዓየር ንብረት መበከልን ተከትሎ በሚመጣ የልብ ህመም ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡
የICT ኤክስፖ ላይ በመገኘት ይጎብኙን
ኢኖቬት ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲከናወን የቆየው 3ኛው ዓለም አቀፍ የICT ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡ በዚህ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ አስመጪዎች፣ አገልግሎት ሰጪ አካላት እና ሌሎች ሐገራዊ እንዲሁም ግዙፍ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
ታድያ በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩትም እንደ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱ ይዘን ከቀረብናቸው ስራዎቻችን መካከል የዲጂታል ቤተ-መፅሐፍት (ከአጠቃቀም ገለፃ ጋር)፣ በወረቀት ላይ የሰፈሩ ፅሁፎችን ወደ ኮምፒውተራችን ገልብጠን ማስተካከል የሚያስችለንን ቴክኖሎጂ እነዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎቻችንን እናስዳስስዎታለን፡፡ በተጨማሪም ተቋማችን በየሶስት ወሩ የሚያሳትመውን የቴክ-ሳይንስ መፅሐፍት እና የሐገራችንን ጠሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽ ሁናቴ የሚቃኙ የዳሰሳ ጥናቶችን በነፃ ያገኛሉ፡፡
ይፍጠኑ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ በማምራት ይጎብኙን!!!
9ኛው ሐገር አቀፍ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሽልማት ተከናውኗል፡፡ በክብር እንግድነት ተገኝተው ሽልማቶችን ያበረከቱት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዓብይ አህመድ ተሸላሚዎቹ ስራዎቻቸው የረጅም ጉዞዋቸው ጅማሬ እንደሆኑና በሐገራችን ያለው የሐብትና ግብዓት እጥረት ሳይገታቸው ወደፊትም ለተሸለ ፈጠራ እንዲተጉ በማሳሰብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሐገራችን ፈጣሪ አዕምሮ ያላቸው ዜጎች እጥረት እንዳለባት ያመላከቱት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም እነዚህን ባለ ብሩክ ተስፋዎች ከመሸለም ባለፈ ከኢንዱስትሪዎች የማስተሳሰር ስራን ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሐገር ዓቀፉ የፈጠራ ሳምንት መዝጊያ ጭምር በነበረው በዚህ በስነ ስርዓት ላይ 177 ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪና መምህራን ብሎም በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ተሸላሚ እንደሆኑበት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ሚኒስትትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም ቴክኖሎጂን ያላማከሉ ማህበራዊም ሆነ ምጣኔ-ሐብታዊ እንቅስቃሴዎች ከስኬት ስለማይደርሱ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙትን ህፃናት ከቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የነገዎቹን ታላላቅ የፈጠራ ባለሙያዎች መፍጠር እንዳለብን አብራርተዋል፡፡
ከ2002 ዓ.ም አንስቶ ሲከናወን በቆየው በዚህ ሽልማት ከ1800 በላይ የፈጠራ ባለሙያዎች ተሸላሚ ሆነውበታል፡፡
የመጀመሪያው የክህሎት ውድድር ተጀመረ
************************************
የመጀመሪያው ሐገር ዓቀፍ የቴክኖሎጂ ክህሎት እና ተግባራዊ ምርምር ውድድር በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ታጅቦ ትናንት ተጀምሯል፡፡ በፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲና በፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስትቲውት በጋራ የሚዘጋጀው ይህ ውድድር “በክህሎትና ስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለሰላምና ልማታችን ዋስትና ናቸው” በሚል መሪ ቃል እስከ ሰኔ 11 የሚዘልቅ ይሆናል፡፡ በተሳታፊነትም የተለያዩ የቴክኒክ እና ሙያ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዝ ኦፕሬተሮች ተካፋይ ያደርጋል፡፡
የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሺዴ መንግስት ትምህርት እና ስልጠና ለሐገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት መሰረታዊ መሆኑን ተረድቶ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት መንቀሳቀሱን ገልፀዋል፡፡ ክቡር ሚንስትሩ “ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ዜጎችንም ያፈራል” ባሉት ቴክኒክ እና ሙያ ተቋም ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመለካከት ለማሻሻል የአተያይና የግንዛቤ ስራዎች መስራት እንደሚገባ አስቀምጠዋል፡፡ በመጨረሻም ዘርፉን ለማጎልበት እና የህብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ስራዎችን በጥናትና ምርምር መደገፍ እንደሚገባ በማሳሰብ በውድድሩ ለተሳተፉ ሰልጣኝ፣ አሰልጣኞች እና እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዝግጅቱ የእንኳን ደህና መጣችው ንግግሩን ያቀረቡት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታው ዶክተር አብዲዋሳ አብዱላሂ ትምህርት ለአንድን ሐገር የልማት መሳሪያና የእድገት ፍትሐዊነት ማረጋገጫ እንደሆነ ሲገልፁ፤ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናም የሰው ልጆችን ድህነትና ስራ አጥትን ለማስወገድ እንዲሁም ሰላምን ለማረገገጥ የቁልፎች ሁሉ ቁልፍ ነው ብለዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና አንዱ ተልዕኮ የቴክሎጂ አቅምን በመገንባት ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪ ማድረግ ቢሆንም ባለው የቅንጅት አሰራር፣ የማበረታቻ ስርዓት፣ የእይታ መድረኮች እና ኢንዱስትሪዎች ላይ መተግበሪያ መንገዶች አለመኖር ሳቢያ ይህ ሚናቸውን በብቃት መወጣት እንዳልቻሉ የተናገሩት ዶክተር አብዲዋሳ እነዚህን ተግዳሮቶች በመፍታት እና መሰል የቴክኖሎጂ ክህሎት እና ተግባራዊ ምርምር ውድድሮችን ከታች ከወረዳ አንስቶ እስከ ሐገር ዓቀፍ ድረስ ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
ውድድሩ የተወዳዳሪዎቹን ስራዎች በዓውደ ርዕይ መልክ በማሳየት እና የዘርፉን አቋም የሚገመግሙ የፓናል ውይይቶች በማካሄድ የሚቀጥል ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ላሳዩ 11 ተወዳዳሪዎችም የሚበረከትላቸው ይሆናል፡፡