TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
መኖሪያም መጓጓዣም
መኖሪያም መጓጓዣም
**********************
የደቡብ ደች ከተማዋ ኢንድሆቨን ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፀሐይ ሐይል የሚንቀሳቀስና መኖሪያም መጓጓዣም የሚሆን መኪና ሰርተው መጠቀም መጀመራቸው ተነገረ፡፡ ቤትና መኪና በጣም አስፈላጊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በተለይ በዚህ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ባለበት ዘመን የብዙዎች ምኞት ከተቻለ ሁለቱም ካልሆነ አንዱ እንዲኖራቸው ነው፡፡

በኢድንሆቨን ቴክኒካ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች አንድ ቡድን አቋቁመው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው አይነት መፍትሔን ይዘው ቀርበዋል፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ የተለየ የሚያደርገው ቤትና መኪና አንድ ላይ መሂናቸው ሳይሆን በፀሐይ ሐይል የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡
የሙከራ ጉዞውን በያዝነው ሳምንት ያደረገው መኪናና ቤት በቅርፁ ለየት ያለ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

በመኪናው ጣሪያ ላይ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎች የተገጠሙለት ሲሆን ከዚህ የሚሰበሰበውም ሀይል ለመንቀሳቀስ እና ለመደበኛ የቤት ውስጥ የሐይል ፍጆታ እንደሚውል ተነግሯል፡፡ ቴክኖሎጂው በፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፉ አማካኝነት የሚሰበስበውን የሐይል መጠን የሚያሳውቅ በመሆኑ በቤት ውስጥ የምንጠቀማቸውን ሐይል ፈላጊ ስራዎች መወሰንና ባለን ልክ ማድረግ እንድንችል ያስችለናል ሲሉ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ ከሆነ ፈጠራው በፀሐያማ ቀን በሰዓት 120 ኪሎሜትሮችን እየተጓዘ 730 ኪሎሜትር ያክል ማካለል የሚችል ሲሆን በተገጠመለት ሐይል ማከማቻ ባለ 60 ኪሎዋት ባትሪ አማካኝነት በሌሊት 600 ኪሎሜትችን መጓዝ ይችላል፡፡

ይህ በፀሐይ ሐይል የሚሰራው ቤትም መኪናም የሆነው ቴክኖሎጂ በያዝነው ሳምንት በደቡባዊ ፈረንሳይ ለእይታ ቀርቦ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-van-life-dutch-students-road.html
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
***************************
በአለማችን ከተሰሩት ሰው ሰራሽ በራሪ ወይም ባለ ክንፍ ፈጠራዎች ውስጥ በትንሽነቱ ተስተካካይ የለውም የተባለ የኮምፒውተር ማይክሮ ቺፕ መሰራቱ ተነገረ፡፡ ይህ ማክሮ ቺፕ ለወደፊት የአየር ብክለት ቁጥጥርና የአየር ወለድ በሽታዎች ክትትልን የሚሰራ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህ ማይክሮፍላየር የተሰኘው ማይክሮ ቺፕ የሚንቀሳቀሰው በሞተር ወይም በኢንጅኖች አማካኝነት እንዳልሆነ ታውቋል፡፡

በራሪው ቺፕ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ከዛፍ ላይ እንደሚወድቁ የእጽዋት ብናኞች በነፋስ አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡ ተመራማሪዎቹ በነፋስ አማካኝነት የተበተኑ የዕጽዋት ዘሮችን እንቅስቃሴ በማጥናት እና በማክሮፍላይ ቺፑ አካባቢ አየር እንዴት እንደሚንቀሳቀስ በማጥናት ቺፑ በአየር ለይ መጠነኛ በሆነ ፍጥነት መብረር የሚያስችለውን ተስማሚ ቅርጽ እንዲይዝ አድርገውታል፡፡ ይህም ቅርጽ ማይክሮፍላየሩ በአየር ላይ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንዳሚያስችለውና ለታለመለት የከባቢ አየር ለውጥ ቅኝት እንዲውል እንደሚያደርገው ታውቋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የተለየዩ ቴክኖሎጂዎችን ከማይክሮ ቺፑ ጋር ለማዋሃድ ማሰባቸውም ታውቋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አየር ወለድ ቅንጣቶችን መለየት የሚችሉ ሰርኪዩቶች፣ የውሃ ጥራትን መቆጣተርና መከታተል የሚችሉ ሴንሰሮች፣ የፀሐይ ብርሃንን መለካት የሚያስችሉ የብርሃን ተከታታዮች፣ ከፀሐይ ብርሃን ሀይልን መሰብሰብ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች፣ ሲፒዩ እና ሚሞሪ እና መረጃን በገመድ አልባ መንገድ ማስተላለፍ የሚያስችል አንቴና ዋነኞቹ ናቸው፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ሀሳብ ከሆነ እነዚህ በራሪ ቺፖች አካባቢን ለመቃኘት እንዲችሉ ከአውሮፕላን ወይም ከትልልቅ ህንጻዎች ሊለቀቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎቹ የተለያዩ በነፋስ አማካኝነት ዘራቸውን የሚበትኑ እጽዋቶችን ሞዴል በማድረግ የተለያዩ ማይክሮፍላየሮችን እያበለጸጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ discover magazine
ተጨማሪ ንባብ https://www.discovermagazine.com/technology/engineers-make-flying-computer-chips-the-size-of-sand-grains?utm_source=dscfb&utm_medium=social&utm_campaign=dscfb&fbclid=IwAR2GhF13hWs7RUFOz7xkSfXXKaBS7NCVcZSqD1nr48_QXQRnosm2aJYMc8Y
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሞ የነበረ የኤሌክትሪክ መኪና ላይ ከፍተኛ ጥገና በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረክቧል፡፡
መኪናዋን የመሪ እና ኤሌክትሪክን ጨምሮ ውስጠ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ሲሆን ውጫዊ አካላቱም ጉዳት አጋጥሞት ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ በፅ/ቤቱ ጥያቄ መሰረትም የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በችግሩ ላይ ቅድሚያ ትንተናን በመስራት እና ጉዳት የደረሰባቸው ክፍሎችን በመለየት ማስተካከያ በማድረግ መኪናዋ ለፅ/ቤቱ አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስቴር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፣ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሣ/ማርያም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪው አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ምርምር እና ልማት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተመራማሪዎች ባሉበት ተከናውኗል፡፡
ኢትዮጵያዊው ምሁር ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፉ
=============
ኢትዮጵያዊው የጂኦፊዚክስ ምሁር ፕ/ር አታላይ አየለ የአሜሪካን ጂኦፊዚካል አሶሴሽን የ2021 ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ፕ/ር አየለ ሽልማቱን የተቀዳጁት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ባደረጉት አስተዋፅዖ እና በታዳጊ ሀገራት ዘንድ ሳይንስን ተጠቅመው ማህበረሰብን ለመጥቀም ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቀዋሴ ነው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን ፕሬዘዳንቷ ሱዛን ሎዜር እንዳስቀመጡት ፕ/ር አታላይ ሳይንስን ወደ አዲስ ከፍታ በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እና ስኬትን አስመዝግበዋል፡፡

ከምርምር ስራቸው በተጓዳኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ፕ/ር አታላይ ከወራት በፊት በጂኦፊዚክስ ዘርፍ ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራንን ባቀፈው የኢትዮጵያ ሳይንስ ውስጥ አካዳሚ አባል ናቸው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን (AGU) ለትርፍ ያልተቋቋማ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ማህበር ነው፡፡ ለማህበረሰብ የሚጠቅም የምድር እና ህዋ ሳይንስ አሰሳን ለማበረታታት አልሞ የሚንቀሳቀሰው ተቋሙ ከ100 ዓመታት በፊት በአውሮፓውያኑ 1919 ነበር የተመሰረተው፡፡ ተቋሙ ከሚሰጣቸው የተለያዩ ሽልማቶች አንዱ የሆነው ይህ ሽልማትም ከአውሮፓውያኑ 2007 አንስቶ ላለፉት 15 ዓመታት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ ምሁራን ሲበረከት ቆይቷል፡፡

ምንጭ፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ
የዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂ እድገት እና መሰረታዊ ሀሳቦች
=======================
የባዮቴክኖሎጂን የምርምር እድገት ከሰው ልጅ ዝግመታዊ እና ማሕበራዊ አመጣጥ ጋር የሚያይዙት ምሁራን ብዙ ናቸው፡፡ የምንመገበው ምግብ እና ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ እንስሳት ጭምር የዚህ ውጤት ናቸው ይላሉ እንደ ዴሊ ሮወላንድ ያሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡ ይህ ማለት የሰው ልጅ ለኑሮው ይጠቅመኛል ያለው የእህልና የጥራጥሬ ዘር እና እንስሳትን መርጦ ከራሱ እና ከአካባቢው ጋር አላምዶ ለተሻለ የህይወት አኗኗር ዘይቤ የሚሰራው ስራ ተጠቃሽ ይሆናል፡፡
በ1919 እ.አ.አ የስነ እርሻ ምሁሩ ካርል ኢረኪ እንደገለፀው ባዮ ቴክኖሎጂ ሰዎች ህይወት ባላቸው ነገሮች አማካይነት በሚያደርጉት ምርምር የተሻለ ምርት የማግኘት ሳይንስ ነው፡፡ በዘመናዊ ባዮ ቴክኖሎጂ ፅንሰ ሐሳብ ደግሞ ተመራማሪዎች ህይወት ያላቸው እፅዋትን፣ እንስሳትም ሆነ ሴሎች እና ፕሮቲኖችን ለሰው ልጅ ወደ ተሻለ ጥቅም የሚያስገኙበት ቅርፅ እና መጠን መቀየር ነው፡፡
በቀጣዩ ዘመንም ዲኤንኤዎችን ከነበራቸው ይዘት እና ቅርፅ በመቀየር እና በተሻለ መልኩ በማስተካከል የሴሎችን ሁለንተናዊ ምህዋር በመቆጣጠር አስደናቂ ምናልባትም አሁን የአለምን ህልውና እየተፈታተነ ያለው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ ሌሎች ለሰው ልጅ የአኗኗር ምቾት የሚቆረቁሩ ነገሮችን ማስወገድ እና መቆጣጥር የሚያስችሉ የተፈጥሮ ውጤቶችን እና መድሀኒቶችን ለማምረትም ያስችላል፡፡
በሌላ መልኩ ስናየው ደግሞ በዚህ ዘርፍ አማካኝነት የሰው ልጆች አመቺ አካባቢ እና ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ጥረት በሚደረግበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ እና ኃላፊነት ካልተደረገበት በተቃራኒው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለምሳሌ ያህል በሽታ የሚያመጡ ታህዋስያን፣ ነፍሳት እና ሌሎች ነገሮች ለማጥፋት በሚሰራበት ጊዜ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳራዊ ሚዛን ሊያዛባ እና የሞርፊ ህግ ሊቃረን ይችላል፡፡ ክትባት እና መድሀኒት ያልተገኘላቸው በሽታዎችን ለማጥፋት በዚህ ዘርፍ አማካኝነት እነኚህ በሽታዎችን የሚዋጉ ወይም ሊያጠፉ የሚችሉ ሌሎች የተሻለ ሐይል እና ጉልበት ያላቸው ቫይረሶች ወይም በክቴርያዎች ይፈጠራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እነሱ ራሳቸው ለሰው ልጅ በተለያየ መልኩ አደጋ የሚሆኑበት አጋጣሚ እንዳለ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡
ቴክኖሎጂ በነገሰበት በዚህ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ብዙ ሀገራት ልማት የባዮ-ቴክኖሎጂ ዘርፍ ወሳኝ ሚናዎችን የሚጫወት የሳይንስ ዘርፍ ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ደግሞ ሩቅ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይህ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ አቅም ግምባታ ላይ የጀርባ አጥንት ሆኖ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችል ወሳኝ ዘርፍ በሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ለረዥም ዘመናት ዝቅተኛ ትኩረት በመሰጠቱ ምክንያት ሳይሰራበት ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የተሸለ ማህበራዊ ግንዛቤ፣ አቅምና ተሳትፎ ለመፍጠር እንቅስቃሴዎች ተጀምረው በተለይ በግብርና ኢኮኖሚው ላይ ጉልህ አስተዋፅዖ እደረገ ከመምጣቱ አንጻር ወደፊት በዘርፉ ሊገኙ የሚችል ብዙ አድሎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
https://www.biotechnologynotes.com/.../risks-and.../10
ዩትዩብ 130 ሺህ ፀረ ኮቪድ 19 ክትባት ቪዲዮዎችን ማንሳቱን አስታወቀ
================
ዩትዩብ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ የኮቪድ 19 ክትባት ፖሊሲዬን ተላልፈው ተገኝተዋል ያላቸው 130 ሺህ ፀረ ክትባት ቪዲዮዎችን ከገፁ ማንሳቱን ትናንት ይፋ አደረገ፡፡ ኩባንያው ከአሁን በኋላም በታዋቂ ሰዎች የሚሰሩትን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ፍቃድ የተሰጣቸው የኮቪድ 19 ክትባቶችን የሚተቹ ቪዲዮዎችን ከገፁ እንደሚያነሳ ገልጿል፡፡

ዩትዩብ ከዚህ ቀደምም በኮቪድ 19 ህክምና ላይ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚያሰራጪ ቪዲዮዎችን ከልክሎ ቆይቷል፡፡ ሆኖም እንደ ድርጅቱ ከሆነ እነዚህ ሀሰተኛ ወሬዎች ከኮቪድ 19ኝም አልፈው በማንኛውም ክትባት ላይ ጭምር ሀሰተኛ ወሬን ወደመንዛት ተሸጋግሯል፡፡ ታድያ የኩባንያው ቃል አቀባይ እንደገለፁት ከአሁን በኋላ አንደዚህ ዓይነት ሀሰተኛ ፀረ ክትባት ወሬዎች የሚነዙባች ቻናሎችም ጭምር የሚታገዱ ይሆናል፡፡

ዬትዩብ እንዳስታወቀው እገዳው በዓለም ጤና ድርጅት እና የየሀገራቱ ጤና ቢሮዎች አማካኝነት ስለ ውጤታማነታቸውና ደህንነታቸው ፈቃድ የተሰጣቸው ክትባቶች ላይ ብቻ የሚሰነዘሩ አሉታዊ ቪዲዮዎችን የሚመለከት ነው፡፡ በተጨማሪም በሜዝልስ እና ሄፒታይተስ ቢ ላይ የሚሰራጩ ሀሰተኛ የህክምና ወሬዎችም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ክትባቱን ተከትበው ስለደረሰባቸው የጎንዮሽ ጉዳት አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች ክልከላው አይመለከታቸውም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ከግል ልምዳቸው አንፃር አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች የሚያሰራጯቸው ቪዲዮዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸውና ሰዎች ክትባትን እንዳይወስዱ የሚያበረታቱ ሆነው ከተገኙም እነርሱም ቢሆን የሚነሱ ይሆናል፡፡

ዩትዩብ ከሁለት ቀናት በፊትም የኮቪድ 19 ክትባትን አስመልክቶ ፖሊሲዬን የጣሱ ቪዲዮዎችን አሰራጭቷል ያለውን የሩስያው የዜና ማረሳጫ ተቋም አርቲ የጀርመንኛ ቻናልን ማገዱን አስታውቆ ነበር፡፡ እንደ ኩባንያው ከሆነ ቻናሉን ከመዝጋቱ አስቀድሞ ለሚዲያ ተቋሙ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲልክ ቆይቷል፡፡

ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-youtube-anti-vax-videos.html
ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለው iOS 15
ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለው iOS 15
*********************************
በአዲሲ የአፕል ምርት በሆነው አይፎን ስልክ ላ የተካተተው iOS 15 የተሰኘው ቴክኖሎጂ ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ወደፈለግነው ቦታ ማንቀሳቀስ እንድንችል የሚያደርግ ብቃት እንዳለው ታውቋል፡፡ ይህ የተለያዩ ብቃቶች እንዳሉት የተነገረለት ስርዓት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በአንድ ፎቶ ላይ ያሉ ይዘቶችን በመተንተን ተጠቃሚው የሚፈልገውን እንዲያደርግ (copy and paste) ያስችላዋል ተብሏል፡፡

ይህ ነገሮችን (ጽሁፎችን) አይቶ የመረዳት ስርዓት ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም እንደ አፕል ማብራሪያ ከሆነ የአሁኑ ቴክኖሎጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ ክላውድ ሰርቨር ላይ ያለ ሳሆን ስልኩ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ ተጠቃሚዎች አንድን ጽሁፍ ወይም ገጽ ፎቶ በማንሳት ካነሱት ፎቶ ላይ ያለውን ጽሁፍ በቀላሉ መገልበጥ (copy and paste) ማድረግ መቻሉ ዋነኛው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢዝነስ ካርድ ካሉ የመረጃ ወረቀቶች ላይ የተጻፉ ስልክ ቁጥሮችንና የኢሜል አድራሻዎችን በቀላሉ ፎቶ በማንሳት ስልክ መደወልም ሆነ ኢሜል መላክ ያስችላል፡፡

ሌላውና ይህ አዲሱ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የእጅ ጽሁፍን በፎቶ አማካኝነት ወደ ዲጂታል መቀየር የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡
ምንጭ CNBC Technology
ተጨማሪ ንባብ https://www.cnbc.com/2021/09/29/ios-15-live-text-how-to-copy-and-paste-text-from-a-photo.html?utm_content=Tech&utm_medium=Social&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR2ieGiSW7cBjJ5GKzPNkI5LEYJ0hgcCRLLTD2EBsbUoSbRYQkmoHaHfgp4#Echobox=1632951279
ትውስታን በመግነጢሳዊ የማነቃቃት ዘዴ
ትውስታን በመግነጢሳዊ የማነቃቃት ዘዴ
***************
መግነጢሳዊ የማነቃቃት ዘዴን በመጠቀም የአእምሮን የትውስታ አቅም ማሳደግ እንደሚቻል አንድ ጥናት አመላከተ፡፡ ጥናቱ በ2012 መከናወን የጀመረ ሲሆን በወቅቱ DLPFC የተሰኘው የጭንቅላት የግራ ክፍል ከመርሳት ጋር የተያያዙ ችግሮች የሚስተዋሉበት ክፍል እንደሆነ አረጋግጧል፡፡

አሁን ላይ በድጋሜ በተሰራው ጥናት ይህንን የጭንቅላት ክፍል ተመጣጣኝ መግነጢሳዊ ሀይል በመጠቀም ማነቃቃት ትውስታን መመለስ እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡

የዚህ ግኝት ሙከራ በግሎስጎው የኒቨርሲቲ የተሰራ ሲሆን የተገኘው ውጤትም አስደናቂ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ የሆኑት ሲሚን ሀንሰልማይር ተናግረዋል፡፡ በሙከራው 24 ጤነኛ ሰዎች እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን እያንዳንዳቸው 10 ቃላት ያሏቸው በሁለት ምድብ የተከፈሉ የቃላት ዝርዝሮችን አንብበው እንዲሸመድዱ ተደርጓል፡፡ ሁለቱ ዝርዝሮችም በተደጋጋሚ ተሳታፊዎቹ እንዲመለከቷቸው ተደርጓል፡፡

በመካከል ላይ ተሳታፊዎቹን ሌላ ስራ እንዲሰሩ በማድረግ ከቆይታ በኋላ የምርምሩ ተሳታፊዎች ከተመለከቷቸው ቃላት ውስጥ የሚችሉትን እንዲያስታውሱ ተደርገዋል፡፡

በዚህ ጊዜ ከተሳታፊዎቹ መካከል ግማሾቹ በጭንቅላታቸው የግራ ክፍል አካባቢ መጠነኛ መግነጢሳዊ ማነቃቂያ እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ተመሳሳይ መጠን ያለው መግነጢሳዊ ማነቃቂያ በላይኛው ጭንቅላታቸው ክፍል እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡

ከመግነጢሳዊ ማነቃቂየው በኋላ በጭንቅላታቸው የግራ ክፍል እገዛ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የተሻለ የማስታወስ ብቃት አስመዝግበዋል፡፡
ምንጭ science alert
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/a-certain-type-of-magnetic-stimulation-could-help-the-brain-remember?fbclid=IwAR0mFsmxU65PuQ6gwGQCyrRd6XqtXJEmS46da6XqqnZnRDJtzhMIF9hkO7Y
የዌቢናር ጥሪ
========
የኢትዮ-ጀርመን ኢንኪዩቤሽን እና ስታርታፕ ፕሮሞሽን ፕሮግራም በሚል የተዘጋጀው አዲሱ የዌቢናር መርሃ ግብር የፊታችን መስከረም 27 እና ጥቅምት 25 የሚከናወን ይሆናል፡፡ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከጀርመን የኢነርጂና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የበይነ-መረብ ሴሚናር ከዚህ ቀደም በኢንስቲትዩት የቅድመ ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም የተካፈሉ ጀማሪ ኢኖቬተሮች፣ በቴክኖሎጂ ስታርታፕ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና በዘርፉ እየተንቀሳቀሱ ላሉ የኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች ማህበር አባላት የልምድ ማግኛ መድረክ እንዲሆን በሚል የተዘጋጀ መርሃ-ግብር ነው፡፡

በዚህ ዌቢናር በስታርታፕ ፕሮሞሽን ዘርፉ ላይ የብዙ ዓመት ልምድ ያላቸው የጀርመን ስታርታፖች በቢዝነስ ሞዴል፣ የፋይናስ አቅም በመፍጠር እና በጀርመን ስላለው የኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም ድጋፍ ተሞክሮዎችን በማንሳት በዘርፉ ላይ እንዴት ስኬት ማምጣት እንደሚቻል ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን ከተሳታፊዎች የሚነሱ ሃሳቦችን በሰፊው ለመመልከትም የጥያቄና መልስ ክፍል በመርሃ-ግብሩ ተካቷል፡፡
You are all kindly invited to participate in the Ethio-German Incubation and Startups Program.
1. Start-up Split Tech Technologies GmbH, Frankfurt, Germany
• Speaker: Mr. Carsten Bock, CEO
• Date and Time: 07 October, 2021, 10:00 AM -12:00 PM (Nairobi Time)
2. Start-up Regiothek GmbH, Passau, Germany
• Speaker: Mr. Simon Nestmeier, CEO
• Date and Time: 04 November, 2021, 10:00 AM - 12:00 PM (Nairobi Time)

በሁለት የተለያዩ ቀናት በሚደረገው በዚህ ዌቢናር መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች ያሉትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ ትችላላቹ
1 https://us04web.zoom.us/j/75691666980?pwd=M2FFNElqZlV0aHlGdVFlNnN5RHhZUT09

2 https://us04web.zoom.us/j/75075017679?pwd=a1VHZWVSWEFBVG0xR1YxY1BqSTE0dz09
የቻይና ህዝብ ቁጥር በግማሽ ሊቀንስ ነው ተባለ