TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ፩ ቢሊዮን አለፈ
==============
የዛሬ 4 ዓመት ገደማ ባይትዳንስ በተሰኘው የቻይና ኩባንያ ይፋ የተደረገው ቲክቶክ የወርሃዊ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን ማለፉን ትናንት አስታወቀ፡፡ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በሚሰራጩበት በፖፕ ሙዚቃ የታጀቡ የዳንስ እንቅስቃሴዎች የተነሳ ቀድሞውንም ከፍተኛ ዕውቅናን እያገኘ የነበረው ቲክቶክ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን መቀስቀስን እና ብዙዎችም እቤት ውስጥ መቀመጣቸውን ተከትሎ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ችሏል፡፡

በመጀመሪያ የ15 ሴኮንድ ቪዲዮዎችን ብቻ ለማሳየት ብሎ የጀመረው ቲክቶክ በሂደት ግን ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን ለማግኘት እና ከዩትዩብ ጋር ለመፎካከር እንዲያስችለው ይህን የጊዜ ገደብ ወደ ሦስት ደቂቃ ከፍ አድርጎታል፡፡ ታድያ የቲክቶክ ወርሀዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ1 ቢሊዮን ይለፍ እንጂ ወርሀዊ ተጠቃሚዎቹ 2.3 ቢሊዮን ከሆኑለት ዩትዩብ አንፃር ገና ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የቲክቶክ ከፍተኛ ተቀባይነትን የተመለከተው ዩትዩብ በበኩሉ ዩትዩብ-ሾርት የተሰኘ በተመሳሳይ አጫጭር ቪዲዮዎችን የሚያሰራጭ ገፅን ይፋ ያደረገ ሲሆን ገፁ ከ100 በላይ ሀገራት ውስጥም እየሰራ ይገኛል፡፡

ቲክቶክ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር እንዲህ መብዛቱን ተከትሎ ከዚህ ዕድል ይበልጥ ለመጠቀም እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት የማስታወቂያ ስራዎችን በይበልጥ መስራት የጀመረ ሲሆን ከወር በፊትም ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ ቪዲዮ በሚያሰራጩ ሰዎች አማካኝነት የሚቀርቡ ምርቶችን በቀጥታ ለመግዛት እንዲችሉ የሚያደርግ ስርዓትን ዘርግቷል፡፡

ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/.../2021-09-tiktok-billion-users.html
የሰዶም እሳት እና አዲሱ ሳይንሳዊ ግኝት
የሰዶም እሳት እና አዲሱ ሳይንሳዊ ግኝት
===========
በመፅሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 19 ላይ ከሰማይ በዘነበ እሳት አማካኝነት የሰዶም እና ገሞራ ከተሞች መጥፋታቸው ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ታድያ አዲስ የወጣ ጥናት ከሦስት እና አራት ሺህ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ሸለቆ ውስጥ ትገኝ የነበረች ጥንታዊቷ የታል ኤል-ሀማም ከተማ በ1,650 ዓመተ ዓለም ከህዋ የወረደ ኃይለኛ የሜትሮይቶች ስብስብ ባደረሰው ፍንዳታ (cosmic airburst) ተመታ መጥፋቷን አመላክቷል፡፡

ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ላይ እንዳስቀመጡት ክስተቱ እ.አ.አ በ1908 ከተከሰተውና ሂሮሺማ ላይ ከተጣለው ቦምብ 1ሺህ እጥፍ የላቀ ኃይልን ከለቀቀው የቱንጋስካ ፍንዳታም የላቀ ነበር፡፡ የጥናት ቡድኑ ባመላከተው መሰረት ጥንት ከተማዋ ትገኝበት በነበረበት ቦታ ላይ 1.5 ሜትር የሚወፍር የካርበን እና አመድ ድብልቅ የሆነ አጥፊ ሽፋን ለብሶ የተገኘ ሲሆን ሽፋኑ ምናልባትም ከታሪኩ መነሻ ወቅት ጋር ሊመሳሰል እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

በመፅሐፍ ቅዱስ በተቀመጠው ታሪክ ላይ የሚጠቀሱት ነገሮች የሜትሮይቶች ስብስብ ምደር ላይ ሲወርድ ጋር ከሚታየው ጋር የሚመሳሰሉ ሆነው ቢገኙም የጠፋችው ከተማ ግን በብሉይ ኪዳን ላይ የተቀሰችው የሰዶም ከተማ መሆኗን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳላገኙ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የታል ኤል-ሀማም በዚህ መልኩ መጥፋት ኋላ ላይ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ለሰፈረው ታሪክ መነሻ ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥጣሬያቸውን ይገልፃሉ፡፡

ምንጭ፤ ስፑትኒክ
ለተጨማሪ፤ https://sputniknews.com/20210922/biblical-story-of-sodom-likely-inspired-by-cosmic-airburst-bigger-than-tunguska-blast-study-says-1089298787.html
መኖሪያም መጓጓዣም
መኖሪያም መጓጓዣም
**********************
የደቡብ ደች ከተማዋ ኢንድሆቨን ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፀሐይ ሐይል የሚንቀሳቀስና መኖሪያም መጓጓዣም የሚሆን መኪና ሰርተው መጠቀም መጀመራቸው ተነገረ፡፡ ቤትና መኪና በጣም አስፈላጊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በተለይ በዚህ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ባለበት ዘመን የብዙዎች ምኞት ከተቻለ ሁለቱም ካልሆነ አንዱ እንዲኖራቸው ነው፡፡

በኢድንሆቨን ቴክኒካ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች አንድ ቡድን አቋቁመው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው አይነት መፍትሔን ይዘው ቀርበዋል፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ የተለየ የሚያደርገው ቤትና መኪና አንድ ላይ መሂናቸው ሳይሆን በፀሐይ ሐይል የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡
የሙከራ ጉዞውን በያዝነው ሳምንት ያደረገው መኪናና ቤት በቅርፁ ለየት ያለ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

በመኪናው ጣሪያ ላይ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎች የተገጠሙለት ሲሆን ከዚህ የሚሰበሰበውም ሀይል ለመንቀሳቀስ እና ለመደበኛ የቤት ውስጥ የሐይል ፍጆታ እንደሚውል ተነግሯል፡፡ ቴክኖሎጂው በፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፉ አማካኝነት የሚሰበስበውን የሐይል መጠን የሚያሳውቅ በመሆኑ በቤት ውስጥ የምንጠቀማቸውን ሐይል ፈላጊ ስራዎች መወሰንና ባለን ልክ ማድረግ እንድንችል ያስችለናል ሲሉ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ ከሆነ ፈጠራው በፀሐያማ ቀን በሰዓት 120 ኪሎሜትሮችን እየተጓዘ 730 ኪሎሜትር ያክል ማካለል የሚችል ሲሆን በተገጠመለት ሐይል ማከማቻ ባለ 60 ኪሎዋት ባትሪ አማካኝነት በሌሊት 600 ኪሎሜትችን መጓዝ ይችላል፡፡

ይህ በፀሐይ ሐይል የሚሰራው ቤትም መኪናም የሆነው ቴክኖሎጂ በያዝነው ሳምንት በደቡባዊ ፈረንሳይ ለእይታ ቀርቦ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-van-life-dutch-students-road.html
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
***************************
በአለማችን ከተሰሩት ሰው ሰራሽ በራሪ ወይም ባለ ክንፍ ፈጠራዎች ውስጥ በትንሽነቱ ተስተካካይ የለውም የተባለ የኮምፒውተር ማይክሮ ቺፕ መሰራቱ ተነገረ፡፡ ይህ ማክሮ ቺፕ ለወደፊት የአየር ብክለት ቁጥጥርና የአየር ወለድ በሽታዎች ክትትልን የሚሰራ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህ ማይክሮፍላየር የተሰኘው ማይክሮ ቺፕ የሚንቀሳቀሰው በሞተር ወይም በኢንጅኖች አማካኝነት እንዳልሆነ ታውቋል፡፡

በራሪው ቺፕ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ከዛፍ ላይ እንደሚወድቁ የእጽዋት ብናኞች በነፋስ አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡ ተመራማሪዎቹ በነፋስ አማካኝነት የተበተኑ የዕጽዋት ዘሮችን እንቅስቃሴ በማጥናት እና በማክሮፍላይ ቺፑ አካባቢ አየር እንዴት እንደሚንቀሳቀስ በማጥናት ቺፑ በአየር ለይ መጠነኛ በሆነ ፍጥነት መብረር የሚያስችለውን ተስማሚ ቅርጽ እንዲይዝ አድርገውታል፡፡ ይህም ቅርጽ ማይክሮፍላየሩ በአየር ላይ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንዳሚያስችለውና ለታለመለት የከባቢ አየር ለውጥ ቅኝት እንዲውል እንደሚያደርገው ታውቋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የተለየዩ ቴክኖሎጂዎችን ከማይክሮ ቺፑ ጋር ለማዋሃድ ማሰባቸውም ታውቋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አየር ወለድ ቅንጣቶችን መለየት የሚችሉ ሰርኪዩቶች፣ የውሃ ጥራትን መቆጣተርና መከታተል የሚችሉ ሴንሰሮች፣ የፀሐይ ብርሃንን መለካት የሚያስችሉ የብርሃን ተከታታዮች፣ ከፀሐይ ብርሃን ሀይልን መሰብሰብ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች፣ ሲፒዩ እና ሚሞሪ እና መረጃን በገመድ አልባ መንገድ ማስተላለፍ የሚያስችል አንቴና ዋነኞቹ ናቸው፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ሀሳብ ከሆነ እነዚህ በራሪ ቺፖች አካባቢን ለመቃኘት እንዲችሉ ከአውሮፕላን ወይም ከትልልቅ ህንጻዎች ሊለቀቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎቹ የተለያዩ በነፋስ አማካኝነት ዘራቸውን የሚበትኑ እጽዋቶችን ሞዴል በማድረግ የተለያዩ ማይክሮፍላየሮችን እያበለጸጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ discover magazine
ተጨማሪ ንባብ https://www.discovermagazine.com/technology/engineers-make-flying-computer-chips-the-size-of-sand-grains?utm_source=dscfb&utm_medium=social&utm_campaign=dscfb&fbclid=IwAR2GhF13hWs7RUFOz7xkSfXXKaBS7NCVcZSqD1nr48_QXQRnosm2aJYMc8Y
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሞ የነበረ የኤሌክትሪክ መኪና ላይ ከፍተኛ ጥገና በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረክቧል፡፡
መኪናዋን የመሪ እና ኤሌክትሪክን ጨምሮ ውስጠ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ሲሆን ውጫዊ አካላቱም ጉዳት አጋጥሞት ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ በፅ/ቤቱ ጥያቄ መሰረትም የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በችግሩ ላይ ቅድሚያ ትንተናን በመስራት እና ጉዳት የደረሰባቸው ክፍሎችን በመለየት ማስተካከያ በማድረግ መኪናዋ ለፅ/ቤቱ አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስቴር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፣ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሣ/ማርያም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪው አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ምርምር እና ልማት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተመራማሪዎች ባሉበት ተከናውኗል፡፡
ኢትዮጵያዊው ምሁር ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፉ
=============
ኢትዮጵያዊው የጂኦፊዚክስ ምሁር ፕ/ር አታላይ አየለ የአሜሪካን ጂኦፊዚካል አሶሴሽን የ2021 ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ፕ/ር አየለ ሽልማቱን የተቀዳጁት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ባደረጉት አስተዋፅዖ እና በታዳጊ ሀገራት ዘንድ ሳይንስን ተጠቅመው ማህበረሰብን ለመጥቀም ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቀዋሴ ነው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን ፕሬዘዳንቷ ሱዛን ሎዜር እንዳስቀመጡት ፕ/ር አታላይ ሳይንስን ወደ አዲስ ከፍታ በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እና ስኬትን አስመዝግበዋል፡፡

ከምርምር ስራቸው በተጓዳኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ፕ/ር አታላይ ከወራት በፊት በጂኦፊዚክስ ዘርፍ ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራንን ባቀፈው የኢትዮጵያ ሳይንስ ውስጥ አካዳሚ አባል ናቸው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን (AGU) ለትርፍ ያልተቋቋማ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ማህበር ነው፡፡ ለማህበረሰብ የሚጠቅም የምድር እና ህዋ ሳይንስ አሰሳን ለማበረታታት አልሞ የሚንቀሳቀሰው ተቋሙ ከ100 ዓመታት በፊት በአውሮፓውያኑ 1919 ነበር የተመሰረተው፡፡ ተቋሙ ከሚሰጣቸው የተለያዩ ሽልማቶች አንዱ የሆነው ይህ ሽልማትም ከአውሮፓውያኑ 2007 አንስቶ ላለፉት 15 ዓመታት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ ምሁራን ሲበረከት ቆይቷል፡፡

ምንጭ፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ
የዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂ እድገት እና መሰረታዊ ሀሳቦች
=======================
የባዮቴክኖሎጂን የምርምር እድገት ከሰው ልጅ ዝግመታዊ እና ማሕበራዊ አመጣጥ ጋር የሚያይዙት ምሁራን ብዙ ናቸው፡፡ የምንመገበው ምግብ እና ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ እንስሳት ጭምር የዚህ ውጤት ናቸው ይላሉ እንደ ዴሊ ሮወላንድ ያሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡ ይህ ማለት የሰው ልጅ ለኑሮው ይጠቅመኛል ያለው የእህልና የጥራጥሬ ዘር እና እንስሳትን መርጦ ከራሱ እና ከአካባቢው ጋር አላምዶ ለተሻለ የህይወት አኗኗር ዘይቤ የሚሰራው ስራ ተጠቃሽ ይሆናል፡፡
በ1919 እ.አ.አ የስነ እርሻ ምሁሩ ካርል ኢረኪ እንደገለፀው ባዮ ቴክኖሎጂ ሰዎች ህይወት ባላቸው ነገሮች አማካይነት በሚያደርጉት ምርምር የተሻለ ምርት የማግኘት ሳይንስ ነው፡፡ በዘመናዊ ባዮ ቴክኖሎጂ ፅንሰ ሐሳብ ደግሞ ተመራማሪዎች ህይወት ያላቸው እፅዋትን፣ እንስሳትም ሆነ ሴሎች እና ፕሮቲኖችን ለሰው ልጅ ወደ ተሻለ ጥቅም የሚያስገኙበት ቅርፅ እና መጠን መቀየር ነው፡፡
በቀጣዩ ዘመንም ዲኤንኤዎችን ከነበራቸው ይዘት እና ቅርፅ በመቀየር እና በተሻለ መልኩ በማስተካከል የሴሎችን ሁለንተናዊ ምህዋር በመቆጣጠር አስደናቂ ምናልባትም አሁን የአለምን ህልውና እየተፈታተነ ያለው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ ሌሎች ለሰው ልጅ የአኗኗር ምቾት የሚቆረቁሩ ነገሮችን ማስወገድ እና መቆጣጥር የሚያስችሉ የተፈጥሮ ውጤቶችን እና መድሀኒቶችን ለማምረትም ያስችላል፡፡
በሌላ መልኩ ስናየው ደግሞ በዚህ ዘርፍ አማካኝነት የሰው ልጆች አመቺ አካባቢ እና ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ጥረት በሚደረግበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ እና ኃላፊነት ካልተደረገበት በተቃራኒው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለምሳሌ ያህል በሽታ የሚያመጡ ታህዋስያን፣ ነፍሳት እና ሌሎች ነገሮች ለማጥፋት በሚሰራበት ጊዜ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳራዊ ሚዛን ሊያዛባ እና የሞርፊ ህግ ሊቃረን ይችላል፡፡ ክትባት እና መድሀኒት ያልተገኘላቸው በሽታዎችን ለማጥፋት በዚህ ዘርፍ አማካኝነት እነኚህ በሽታዎችን የሚዋጉ ወይም ሊያጠፉ የሚችሉ ሌሎች የተሻለ ሐይል እና ጉልበት ያላቸው ቫይረሶች ወይም በክቴርያዎች ይፈጠራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እነሱ ራሳቸው ለሰው ልጅ በተለያየ መልኩ አደጋ የሚሆኑበት አጋጣሚ እንዳለ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡
ቴክኖሎጂ በነገሰበት በዚህ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ብዙ ሀገራት ልማት የባዮ-ቴክኖሎጂ ዘርፍ ወሳኝ ሚናዎችን የሚጫወት የሳይንስ ዘርፍ ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ደግሞ ሩቅ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይህ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ አቅም ግምባታ ላይ የጀርባ አጥንት ሆኖ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችል ወሳኝ ዘርፍ በሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ለረዥም ዘመናት ዝቅተኛ ትኩረት በመሰጠቱ ምክንያት ሳይሰራበት ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የተሸለ ማህበራዊ ግንዛቤ፣ አቅምና ተሳትፎ ለመፍጠር እንቅስቃሴዎች ተጀምረው በተለይ በግብርና ኢኮኖሚው ላይ ጉልህ አስተዋፅዖ እደረገ ከመምጣቱ አንጻር ወደፊት በዘርፉ ሊገኙ የሚችል ብዙ አድሎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
https://www.biotechnologynotes.com/.../risks-and.../10
ዩትዩብ 130 ሺህ ፀረ ኮቪድ 19 ክትባት ቪዲዮዎችን ማንሳቱን አስታወቀ
================
ዩትዩብ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ የኮቪድ 19 ክትባት ፖሊሲዬን ተላልፈው ተገኝተዋል ያላቸው 130 ሺህ ፀረ ክትባት ቪዲዮዎችን ከገፁ ማንሳቱን ትናንት ይፋ አደረገ፡፡ ኩባንያው ከአሁን በኋላም በታዋቂ ሰዎች የሚሰሩትን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ፍቃድ የተሰጣቸው የኮቪድ 19 ክትባቶችን የሚተቹ ቪዲዮዎችን ከገፁ እንደሚያነሳ ገልጿል፡፡

ዩትዩብ ከዚህ ቀደምም በኮቪድ 19 ህክምና ላይ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚያሰራጪ ቪዲዮዎችን ከልክሎ ቆይቷል፡፡ ሆኖም እንደ ድርጅቱ ከሆነ እነዚህ ሀሰተኛ ወሬዎች ከኮቪድ 19ኝም አልፈው በማንኛውም ክትባት ላይ ጭምር ሀሰተኛ ወሬን ወደመንዛት ተሸጋግሯል፡፡ ታድያ የኩባንያው ቃል አቀባይ እንደገለፁት ከአሁን በኋላ አንደዚህ ዓይነት ሀሰተኛ ፀረ ክትባት ወሬዎች የሚነዙባች ቻናሎችም ጭምር የሚታገዱ ይሆናል፡፡

ዬትዩብ እንዳስታወቀው እገዳው በዓለም ጤና ድርጅት እና የየሀገራቱ ጤና ቢሮዎች አማካኝነት ስለ ውጤታማነታቸውና ደህንነታቸው ፈቃድ የተሰጣቸው ክትባቶች ላይ ብቻ የሚሰነዘሩ አሉታዊ ቪዲዮዎችን የሚመለከት ነው፡፡ በተጨማሪም በሜዝልስ እና ሄፒታይተስ ቢ ላይ የሚሰራጩ ሀሰተኛ የህክምና ወሬዎችም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ክትባቱን ተከትበው ስለደረሰባቸው የጎንዮሽ ጉዳት አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች ክልከላው አይመለከታቸውም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ከግል ልምዳቸው አንፃር አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች የሚያሰራጯቸው ቪዲዮዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸውና ሰዎች ክትባትን እንዳይወስዱ የሚያበረታቱ ሆነው ከተገኙም እነርሱም ቢሆን የሚነሱ ይሆናል፡፡

ዩትዩብ ከሁለት ቀናት በፊትም የኮቪድ 19 ክትባትን አስመልክቶ ፖሊሲዬን የጣሱ ቪዲዮዎችን አሰራጭቷል ያለውን የሩስያው የዜና ማረሳጫ ተቋም አርቲ የጀርመንኛ ቻናልን ማገዱን አስታውቆ ነበር፡፡ እንደ ኩባንያው ከሆነ ቻናሉን ከመዝጋቱ አስቀድሞ ለሚዲያ ተቋሙ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲልክ ቆይቷል፡፡

ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-youtube-anti-vax-videos.html
ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለው iOS 15
ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለው iOS 15
*********************************
በአዲሲ የአፕል ምርት በሆነው አይፎን ስልክ ላ የተካተተው iOS 15 የተሰኘው ቴክኖሎጂ ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ወደፈለግነው ቦታ ማንቀሳቀስ እንድንችል የሚያደርግ ብቃት እንዳለው ታውቋል፡፡ ይህ የተለያዩ ብቃቶች እንዳሉት የተነገረለት ስርዓት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በአንድ ፎቶ ላይ ያሉ ይዘቶችን በመተንተን ተጠቃሚው የሚፈልገውን እንዲያደርግ (copy and paste) ያስችላዋል ተብሏል፡፡

ይህ ነገሮችን (ጽሁፎችን) አይቶ የመረዳት ስርዓት ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም እንደ አፕል ማብራሪያ ከሆነ የአሁኑ ቴክኖሎጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ ክላውድ ሰርቨር ላይ ያለ ሳሆን ስልኩ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ ተጠቃሚዎች አንድን ጽሁፍ ወይም ገጽ ፎቶ በማንሳት ካነሱት ፎቶ ላይ ያለውን ጽሁፍ በቀላሉ መገልበጥ (copy and paste) ማድረግ መቻሉ ዋነኛው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢዝነስ ካርድ ካሉ የመረጃ ወረቀቶች ላይ የተጻፉ ስልክ ቁጥሮችንና የኢሜል አድራሻዎችን በቀላሉ ፎቶ በማንሳት ስልክ መደወልም ሆነ ኢሜል መላክ ያስችላል፡፡

ሌላውና ይህ አዲሱ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የእጅ ጽሁፍን በፎቶ አማካኝነት ወደ ዲጂታል መቀየር የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡
ምንጭ CNBC Technology
ተጨማሪ ንባብ https://www.cnbc.com/2021/09/29/ios-15-live-text-how-to-copy-and-paste-text-from-a-photo.html?utm_content=Tech&utm_medium=Social&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR2ieGiSW7cBjJ5GKzPNkI5LEYJ0hgcCRLLTD2EBsbUoSbRYQkmoHaHfgp4#Echobox=1632951279
ትውስታን በመግነጢሳዊ የማነቃቃት ዘዴ