TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሶፍትዌርን ኤክስፖርት ለማድረግ እየሰራ ያለው ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ
==============
አዲስ ሶፍትዌር የተሰኘውና መቀመጫውን እዚሁ ኢትዮጵያ ያደረገ የሶፍትዌር ኩባንያ ደረጃውን የጠበቀ የሶፍትዌር ምርት በኢትዮጵያ መስራት እንደሚቻል ለዓለም አቀፉ ገበያ ለማሳየት እየሰራ ይገኛል፡፡ ኩባንያው ከድረ ገፅ ንድፍ እና ስራ አንስቶ እስከ ስልክ እና ዌብ መተግበሪያ ያሉ አገልግሎቶችን ባህር ማዶ ለሚገኙ ደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል፡፡ ከዚህ ስራው በተጨማሪም በሰርች ኢንጅን ኦፕቲማይዜሽን (SEO) እና ኮንቴንት ማኔጅመንት ሲስተም (CMS) ላይ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

አቤኔዘር ያቆብ እና እሌኒ ወርቁ በተባሉ ሁለት የሶፍትዌር ባለሙያዎች ጥምረት ምስረታውን ያገኘው አዲስ ሶፍትዌር መቀመጫውን ስዊድን ካደረገውና በአቤኔዘር ያቆብ እና ቶሜክ ፊካስ አማካኝነት ከተቋቋመው ስዊቶጲያ የተባለ አጋር ኩባንያ ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡ እሌኒ እንደምትለው ከሆነ ኩባንያው ለኢትዮጵያውያን ተጨማሪ የአይሲቲ ስራ ዕድሎችን ለማምጣትና ለተቀረው ዓለምም ኢትዮጵያ ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ ሶፍትዌር ሊሰራ እንደሚችል የማሳየት ሀሳብ ይዞ የተነሳ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ባንክስ ኢትየጵያ የተሰኘ ስለተለያዩ ኢትዮጵያዊያን ባንኮች በቀላሉ መረጃ የሚያቀርብ ፕሮጀክትንም ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ታድያ ኩባንያው በተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ማለፉን መስራቾቹ ይናገራሉ፡፡ እንደ እሌኒ ከሆነ ኩባንያውን ከማቋቋም አንስቶ ፕሮጀክቶችን የማግኘት እና ከፖሊሲ ብሎም በቂ ድጋፍ ከመንግስት ከማግኘት አንፃር ስጋት ነበረባቸው፡፡ ሌላኛው ተግዳሮት ደግሞ በቂ የሰው ኃይል ማግኘት ነበር፡፡ ምንም እንኳን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በዘርፉ ተመርቀው ገበያውን የሚቀላቀሉ ቢሆንም ለኩባንያው የስራ ባህል የሚስማሙ ተቀጣሪዎችን ማግኘቱ ግን አዳጋች እንደነበረባቸው ይናገራሉ፡፡

አሁን ላይ ኩባንያው ለ10 ሰዎች ስራ ዕድልን መፍጠር የቻለ ሲሆን በቀጣዮቹ 5 እና 10 ዓመታት ውስጥም ይህን የተቀጣሪዎቹን ቁጥር ከ50 በላ ለማድረስ አቅዷል፡፡

ምንጭ፤ ሸጋ
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/post/addis-software-building-high-end-products-for-international-market/
የአውሮፓ ህብረት የሁሉም ስልኮች ቻርጀር ተመሳሳይ እንዲሆን እያስገደደ ነው
====================
የአነስተኛ ኤሌክትሮኒክስ እና የስልክ አምራች ድርጅቶች በአለም አቅፍ ደረጃ ወጥነት ያላቸው ወይም ተመሳሳይ ቻርጀር ሊያስጠቅሙ የሚችሉ ምርቶችን እንዲያቀርቡ የአውሮፓ ህብረት በማስገደድ ላይ ነው፡፡ ለኤሌክትሮኒክስ ምርቶች የሚቀርቡ ብዛት ያላቸው የተለያዩ ቻርጀሮች በአካባቢ ብክለት ላይ የሚኖራቸውን ከፍተኛ ጫና ለመቀነስ ያለመው አዲሱ የአውሮፓ ህብረት ህግ ተጠቃሚዎች አዳዲስ ምርት በተጠቀሙ ቁጥር በቀደሞ ቻርጀራቸው እንዲገለጉ በማበረታታ ሊኖር የሚችለውን ከፍተኛ የኤሌክትሮኒክስ ውጋጅ ብክለት ለመቀነስ ያለመ ነው፡፡

አሁን ላይብዛኞቹ የስልክ አምራች ድርጅቶች እና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቻቸው የአንድሮይድ ሥርዓትን ጨምሮ እንደ ሳምሰንግ ያሉ አብዛኞቹ ስልኮች ዩኤስቢ ማይክሮ-ቢ (USB micro-B) የተሰኙትን ቻርጀር የሚጠቀሙ ሲሆን፤ የተወሰኑት ደግሞ ዩኤስቢ-ሲ (USB-C) የተሰኘውን ቻርጀር ይጠቀማሉ። በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽመነ ውሳኔ መሠረትም በዋናነት በአውሮፓ ውስጥ የሚሸጡ ስልኮች በሙሉ ዩኤስቢ-ሲ (USB-C) የተባለው የቻርጀር ገመድ እንዲኖራቸው የሚስገድድ ውሳኔ ቢሆንም በአውሮፓ ከፍተኛ የገበያ ተደራሽነት ያለው አፕል ኩባንያ እንዲህ ያለው ውሳኔ የፈጠራ ዘርፉን በእጅጉ ይጎዳል በሚል ውሳኔውን በመቃወም ላይ ይገኛል። እንደሚታወቀው አፕል የሚያመርታቸው የአይፎን ስልኮች Lightning የተባሉ ቻርጅ ማድረጊያ ኬብሎችን የሚጠቀሙ ሲሆን እንደድርጅቱ ተቃውሞ ከሆነ ድግሞ ይህ ውሳኔ በመላው ዓለም ያሉ የስልኩ ተጠቃሚዎችን በቀጥታ የሚጎዳ ነው ይላል።

በዚህ ውሳኔ መሰረት ሁሉም የአነስተኛ ኤሌክትሮኒክስ እና የስልክ አምራች ድርጅቶች ለገበያ የሚያቀርቡትን የቻርጀር ገመዶች ወጥነት ያላቸው ወይም ተመሳሳይ ጃርጀር የሚያደርጉ ከሆነ በየዓመቱ ከ11ሺህ በላይ ቶን የሚወገድን ቆሻሻ ማስቀርት ይቻላል የሚለው ህብረቱ ይህም ለተጠቃሚዎች የአጠቃቀም ቅለትን ከመፍጠሩ ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ላይ የማይናቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስታውቋል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት ለብዙ ዓመታት ትግበራ ላይ ለመዋል ሲጥር የነበረው ይህ ውሳኔ ከ2022 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም እንደ አፕል ካሉ ድርጅቶች የሚሰማው ተቃውሞ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስቸግር ሊሆን ይችላል፡፡
https://www.cnbc.com/2021/09/23/eu-plans-to-make-usb-c-mandatory-for-apple-iphones-and-other-devices.html
ጨረቃ ላይ ውሃ እንዳለ ተረጋገጠ
***********************
የፀሐይ ብርሃን የሚያገኙ የጨረቃ ክፍሎች ላይ ውሃ እንደሚገኝ ተመራማሪዎች አሳወቁ፡፡ ከዚህ በፊት በተሰሩ ምርምሮች ጨረቃ ላይ ውሃ ሊኖር እንደሚችል የሚያመላክቱ መረጃዎች ተገኝተው እንደነበር ያመለክታሉ፡፡ ይሄኛው ግኝት ደግሞ ሶፊያ በተባለችው ቴሌስኮፕ በመታገዝ የተሰራ ምርምር ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን ግምት እውነትነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

ይህ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የተገኘው የውሃ ሞሎኪዩል በቋሚነት በዚህ ስፍራ ብቻ የሚገኝ ላይሆን ስለሚችል ተጨማሪ ምርምሮችና ፍለጋዎች መሰራት አለባቸው ብለው እንደሚያምኑ የናሳው ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ግኝቱ ለወደፊት ወደ ጨረቃ ለሚሄዱ ተጓዦችና ተመራማሪዎች እንደ ግብዓት ሊጠቅም ይችላል የሚል ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሶፊያ (SOFIA) የተሰኘችው ቴሌስኮፕ በናሳ እና በጀርመን ኤሮስፔስ ማዕከል ጥቅም ላይ የምትውል ባለ 2.5 ሜትር እና በህዋ ላይ ግልጽ ምስሎችን ለመመልከት የምታስችል መሳሪያ ናት፡፡ ተመራማሪዎቹ በዚህች ቴሌስኮፕ በመታገዝ የተመለከቱት ምስል የውሃ ሞሎኪዩሎችን በፀሐይ ጨረሮች አማካኝነት ሲሆን ከዚህም በመነሳት ጨረቃ ላይ በተለያዩ ነገሮች ተሸፍኖ ውሃ እንዳለ መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ውሃም በጊዜ ሂደት ጨረቃ ላይ በፀሐይ ብርሃን አማካኝነት የተፈጠረ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ Science news
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencenews.org/article/water-moon-sun-sofia-telescope?fbclid=IwAR3m5KSxJGeLZqmDA1gNBwSByz2uvzHITn-M5ujCJQb5NSS_EUvEmHGiwQ0
የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ፩ ቢሊዮን አለፈ
የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ፩ ቢሊዮን አለፈ
==============
የዛሬ 4 ዓመት ገደማ ባይትዳንስ በተሰኘው የቻይና ኩባንያ ይፋ የተደረገው ቲክቶክ የወርሃዊ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን ማለፉን ትናንት አስታወቀ፡፡ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በሚሰራጩበት በፖፕ ሙዚቃ የታጀቡ የዳንስ እንቅስቃሴዎች የተነሳ ቀድሞውንም ከፍተኛ ዕውቅናን እያገኘ የነበረው ቲክቶክ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን መቀስቀስን እና ብዙዎችም እቤት ውስጥ መቀመጣቸውን ተከትሎ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ችሏል፡፡

በመጀመሪያ የ15 ሴኮንድ ቪዲዮዎችን ብቻ ለማሳየት ብሎ የጀመረው ቲክቶክ በሂደት ግን ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን ለማግኘት እና ከዩትዩብ ጋር ለመፎካከር እንዲያስችለው ይህን የጊዜ ገደብ ወደ ሦስት ደቂቃ ከፍ አድርጎታል፡፡ ታድያ የቲክቶክ ወርሀዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ1 ቢሊዮን ይለፍ እንጂ ወርሀዊ ተጠቃሚዎቹ 2.3 ቢሊዮን ከሆኑለት ዩትዩብ አንፃር ገና ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የቲክቶክ ከፍተኛ ተቀባይነትን የተመለከተው ዩትዩብ በበኩሉ ዩትዩብ-ሾርት የተሰኘ በተመሳሳይ አጫጭር ቪዲዮዎችን የሚያሰራጭ ገፅን ይፋ ያደረገ ሲሆን ገፁ ከ100 በላይ ሀገራት ውስጥም እየሰራ ይገኛል፡፡

ቲክቶክ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር እንዲህ መብዛቱን ተከትሎ ከዚህ ዕድል ይበልጥ ለመጠቀም እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት የማስታወቂያ ስራዎችን በይበልጥ መስራት የጀመረ ሲሆን ከወር በፊትም ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ ቪዲዮ በሚያሰራጩ ሰዎች አማካኝነት የሚቀርቡ ምርቶችን በቀጥታ ለመግዛት እንዲችሉ የሚያደርግ ስርዓትን ዘርግቷል፡፡

ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/.../2021-09-tiktok-billion-users.html
የሰዶም እሳት እና አዲሱ ሳይንሳዊ ግኝት
የሰዶም እሳት እና አዲሱ ሳይንሳዊ ግኝት
===========
በመፅሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 19 ላይ ከሰማይ በዘነበ እሳት አማካኝነት የሰዶም እና ገሞራ ከተሞች መጥፋታቸው ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ታድያ አዲስ የወጣ ጥናት ከሦስት እና አራት ሺህ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ሸለቆ ውስጥ ትገኝ የነበረች ጥንታዊቷ የታል ኤል-ሀማም ከተማ በ1,650 ዓመተ ዓለም ከህዋ የወረደ ኃይለኛ የሜትሮይቶች ስብስብ ባደረሰው ፍንዳታ (cosmic airburst) ተመታ መጥፋቷን አመላክቷል፡፡

ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ላይ እንዳስቀመጡት ክስተቱ እ.አ.አ በ1908 ከተከሰተውና ሂሮሺማ ላይ ከተጣለው ቦምብ 1ሺህ እጥፍ የላቀ ኃይልን ከለቀቀው የቱንጋስካ ፍንዳታም የላቀ ነበር፡፡ የጥናት ቡድኑ ባመላከተው መሰረት ጥንት ከተማዋ ትገኝበት በነበረበት ቦታ ላይ 1.5 ሜትር የሚወፍር የካርበን እና አመድ ድብልቅ የሆነ አጥፊ ሽፋን ለብሶ የተገኘ ሲሆን ሽፋኑ ምናልባትም ከታሪኩ መነሻ ወቅት ጋር ሊመሳሰል እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

በመፅሐፍ ቅዱስ በተቀመጠው ታሪክ ላይ የሚጠቀሱት ነገሮች የሜትሮይቶች ስብስብ ምደር ላይ ሲወርድ ጋር ከሚታየው ጋር የሚመሳሰሉ ሆነው ቢገኙም የጠፋችው ከተማ ግን በብሉይ ኪዳን ላይ የተቀሰችው የሰዶም ከተማ መሆኗን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳላገኙ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የታል ኤል-ሀማም በዚህ መልኩ መጥፋት ኋላ ላይ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ለሰፈረው ታሪክ መነሻ ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥጣሬያቸውን ይገልፃሉ፡፡

ምንጭ፤ ስፑትኒክ
ለተጨማሪ፤ https://sputniknews.com/20210922/biblical-story-of-sodom-likely-inspired-by-cosmic-airburst-bigger-than-tunguska-blast-study-says-1089298787.html
መኖሪያም መጓጓዣም
መኖሪያም መጓጓዣም
**********************
የደቡብ ደች ከተማዋ ኢንድሆቨን ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፀሐይ ሐይል የሚንቀሳቀስና መኖሪያም መጓጓዣም የሚሆን መኪና ሰርተው መጠቀም መጀመራቸው ተነገረ፡፡ ቤትና መኪና በጣም አስፈላጊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በተለይ በዚህ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ባለበት ዘመን የብዙዎች ምኞት ከተቻለ ሁለቱም ካልሆነ አንዱ እንዲኖራቸው ነው፡፡

በኢድንሆቨን ቴክኒካ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች አንድ ቡድን አቋቁመው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው አይነት መፍትሔን ይዘው ቀርበዋል፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ የተለየ የሚያደርገው ቤትና መኪና አንድ ላይ መሂናቸው ሳይሆን በፀሐይ ሐይል የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡
የሙከራ ጉዞውን በያዝነው ሳምንት ያደረገው መኪናና ቤት በቅርፁ ለየት ያለ እንደሆነም ተሰምቷል፡፡

በመኪናው ጣሪያ ላይ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎች የተገጠሙለት ሲሆን ከዚህ የሚሰበሰበውም ሀይል ለመንቀሳቀስ እና ለመደበኛ የቤት ውስጥ የሐይል ፍጆታ እንደሚውል ተነግሯል፡፡ ቴክኖሎጂው በፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፉ አማካኝነት የሚሰበስበውን የሐይል መጠን የሚያሳውቅ በመሆኑ በቤት ውስጥ የምንጠቀማቸውን ሐይል ፈላጊ ስራዎች መወሰንና ባለን ልክ ማድረግ እንድንችል ያስችለናል ሲሉ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ ከሆነ ፈጠራው በፀሐያማ ቀን በሰዓት 120 ኪሎሜትሮችን እየተጓዘ 730 ኪሎሜትር ያክል ማካለል የሚችል ሲሆን በተገጠመለት ሐይል ማከማቻ ባለ 60 ኪሎዋት ባትሪ አማካኝነት በሌሊት 600 ኪሎሜትችን መጓዝ ይችላል፡፡

ይህ በፀሐይ ሐይል የሚሰራው ቤትም መኪናም የሆነው ቴክኖሎጂ በያዝነው ሳምንት በደቡባዊ ፈረንሳይ ለእይታ ቀርቦ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-van-life-dutch-students-road.html
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
***************************
በአለማችን ከተሰሩት ሰው ሰራሽ በራሪ ወይም ባለ ክንፍ ፈጠራዎች ውስጥ በትንሽነቱ ተስተካካይ የለውም የተባለ የኮምፒውተር ማይክሮ ቺፕ መሰራቱ ተነገረ፡፡ ይህ ማክሮ ቺፕ ለወደፊት የአየር ብክለት ቁጥጥርና የአየር ወለድ በሽታዎች ክትትልን የሚሰራ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህ ማይክሮፍላየር የተሰኘው ማይክሮ ቺፕ የሚንቀሳቀሰው በሞተር ወይም በኢንጅኖች አማካኝነት እንዳልሆነ ታውቋል፡፡

በራሪው ቺፕ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ከዛፍ ላይ እንደሚወድቁ የእጽዋት ብናኞች በነፋስ አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡ ተመራማሪዎቹ በነፋስ አማካኝነት የተበተኑ የዕጽዋት ዘሮችን እንቅስቃሴ በማጥናት እና በማክሮፍላይ ቺፑ አካባቢ አየር እንዴት እንደሚንቀሳቀስ በማጥናት ቺፑ በአየር ለይ መጠነኛ በሆነ ፍጥነት መብረር የሚያስችለውን ተስማሚ ቅርጽ እንዲይዝ አድርገውታል፡፡ ይህም ቅርጽ ማይክሮፍላየሩ በአየር ላይ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንዳሚያስችለውና ለታለመለት የከባቢ አየር ለውጥ ቅኝት እንዲውል እንደሚያደርገው ታውቋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የተለየዩ ቴክኖሎጂዎችን ከማይክሮ ቺፑ ጋር ለማዋሃድ ማሰባቸውም ታውቋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አየር ወለድ ቅንጣቶችን መለየት የሚችሉ ሰርኪዩቶች፣ የውሃ ጥራትን መቆጣተርና መከታተል የሚችሉ ሴንሰሮች፣ የፀሐይ ብርሃንን መለካት የሚያስችሉ የብርሃን ተከታታዮች፣ ከፀሐይ ብርሃን ሀይልን መሰብሰብ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች፣ ሲፒዩ እና ሚሞሪ እና መረጃን በገመድ አልባ መንገድ ማስተላለፍ የሚያስችል አንቴና ዋነኞቹ ናቸው፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ሀሳብ ከሆነ እነዚህ በራሪ ቺፖች አካባቢን ለመቃኘት እንዲችሉ ከአውሮፕላን ወይም ከትልልቅ ህንጻዎች ሊለቀቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎቹ የተለያዩ በነፋስ አማካኝነት ዘራቸውን የሚበትኑ እጽዋቶችን ሞዴል በማድረግ የተለያዩ ማይክሮፍላየሮችን እያበለጸጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ discover magazine
ተጨማሪ ንባብ https://www.discovermagazine.com/technology/engineers-make-flying-computer-chips-the-size-of-sand-grains?utm_source=dscfb&utm_medium=social&utm_campaign=dscfb&fbclid=IwAR2GhF13hWs7RUFOz7xkSfXXKaBS7NCVcZSqD1nr48_QXQRnosm2aJYMc8Y
የአሸዋ ጠጠር መጠን ያለው በራሪ ማይክሮ ቺፕ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪክ መኪናን ማሻሻያ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረከበ
================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሞ የነበረ የኤሌክትሪክ መኪና ላይ ከፍተኛ ጥገና በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስረክቧል፡፡
መኪናዋን የመሪ እና ኤሌክትሪክን ጨምሮ ውስጠ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ሲሆን ውጫዊ አካላቱም ጉዳት አጋጥሞት ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ በፅ/ቤቱ ጥያቄ መሰረትም የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በችግሩ ላይ ቅድሚያ ትንተናን በመስራት እና ጉዳት የደረሰባቸው ክፍሎችን በመለየት ማስተካከያ በማድረግ መኪናዋ ለፅ/ቤቱ አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስቴር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፣ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሣ/ማርያም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪው አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ምርምር እና ልማት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተመራማሪዎች ባሉበት ተከናውኗል፡፡
ኢትዮጵያዊው ምሁር ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፉ
=============
ኢትዮጵያዊው የጂኦፊዚክስ ምሁር ፕ/ር አታላይ አየለ የአሜሪካን ጂኦፊዚካል አሶሴሽን የ2021 ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ፕ/ር አየለ ሽልማቱን የተቀዳጁት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ባደረጉት አስተዋፅዖ እና በታዳጊ ሀገራት ዘንድ ሳይንስን ተጠቅመው ማህበረሰብን ለመጥቀም ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቀዋሴ ነው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን ፕሬዘዳንቷ ሱዛን ሎዜር እንዳስቀመጡት ፕ/ር አታላይ ሳይንስን ወደ አዲስ ከፍታ በማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እና ስኬትን አስመዝግበዋል፡፡

ከምርምር ስራቸው በተጓዳኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ፕ/ር አታላይ ከወራት በፊት በጂኦፊዚክስ ዘርፍ ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራንን ባቀፈው የኢትዮጵያ ሳይንስ ውስጥ አካዳሚ አባል ናቸው፡፡

የአሜሪካን ጂፊዚካል ዩኒየን (AGU) ለትርፍ ያልተቋቋማ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ማህበር ነው፡፡ ለማህበረሰብ የሚጠቅም የምድር እና ህዋ ሳይንስ አሰሳን ለማበረታታት አልሞ የሚንቀሳቀሰው ተቋሙ ከ100 ዓመታት በፊት በአውሮፓውያኑ 1919 ነበር የተመሰረተው፡፡ ተቋሙ ከሚሰጣቸው የተለያዩ ሽልማቶች አንዱ የሆነው ይህ ሽልማትም ከአውሮፓውያኑ 2007 አንስቶ ላለፉት 15 ዓመታት በምድር እና ህዋ ሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ ምሁራን ሲበረከት ቆይቷል፡፡

ምንጭ፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ