TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች
ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች
********************************************************************
በቻይና ታሪክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ ያደረጉትን የህዋ ላይ ቆይታ አጠናቀው ወደ ምድር መመለሳቸው ተነገረ፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች ቲያንጎንግ በተሰኘው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር ጣቢያ ለ90 ቀናት ያክል ቆይተው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ከሰሩ በኋላ በሙሉ ጤንነት ወደ ምድር ተመልሰዋል፡፡ በቆይታቸውም የህዋ ላይ እንቅስቃሴ (spacewalks) እና የተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን አካሂደዋል፡፡

12ቱም ተመራማሪዎች ወደቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት ለ2 ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ተቀምጠው ክትትል እንደሚደረግላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ተልዕኮ እያደገ የመጣው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር አካል ሲሆን ሀገሪቱ ማርስ ላይ የአሰሳ ሮቨር ማምጠቅና ወደ ጨረቃም የተለያዩ የምርምር ግብዓቶችን መላኳ በዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አመላካች ነው፡፡

ቲያንጎንግ ሰማያዊ ስፍራ ("heavenly palace") ማለት ሲሆን ለ10 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተሰራ የህዋ ላይ የምርምር ጣቢያ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ 3ቱም ከሀገሪቱ የመከላከያ ሀይል የተገኙ ሲሆኑ አንደኛው ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የህዋ ላይ ጉዞን በማድረግ ልምድ ያለው መሆኑ ተነግሯል፡፡

የቻይና ስፔስ ኤጀንሲ በቀጣዩ አመት ብቻ 11 የህዋ ላይ ጉዞ ያቀደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ተመራማሪዎችን ይዘው የሚጓዙ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም 70 ቶን የሚደርሱ ሁለት የቤተ ሙከራ መገንቢያ ቁሶችም እንደሚላኩ ታውቋል፡፡ ቻይና የህዋ ላይ ምርምሯን የመከላከያ ሀይሏን መሰረት ባደረገ መልኩ እያከናወነች ትገኛለች፡፡

ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-09-chinese-astronauts-earth-day-mission.html
የአይፎን ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በአስቸኳይ አፕዴት እንዲያደርጉ ተጠየቁ
የአይፎን ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በአስቸኳይ አፕዴት እንዲያደርጉ ተጠየቁ
=====================
እንደ ሌሎች የስልክ አምራቾች ሁሉ አፕልም በየጊዜው ለስልክ እና ሌሎች ምርቶቹ የሶፍትዌር ማሻሻያ ወይም አፕዴት ሲያቀርብ ቢቆይም ከሰሞኑ ግን ከጥቃት ተጋላጭነት ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ስልካቸውን አብዴት እንዲያደርጉ ተነግሯል፡፡ ገለልተኛ አጥኚዎች እንዳመላከቱት የአይፎን ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም በጋዜጠኞች ላይ ሲሰልል ከነበረ ሶፍትዌር ጋር በተያያዘ ለጥቃት ተጋላጭ ሆነዋል፡፡

የአፕል የደህንነት ምህንድስና ኃላፊ እንዳስታወቁት ሶፍትዌሩ የተወሰኑ ግለሰቦችን ብቻ ኢላማ የሚያደርግና ለአብዛኛው ተጠቃሚ ስጋት ያልሆነ ቢሆንም ተጠቃሚዎች ምንም አይነት አሳሳች ሊንኮችን ሳይጫኑ ጭምር ስልካቸው እንዲበረበር ወይም ሀክ እንዲደረግ በር የሚከፍት በመሆኑ አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም አይሜሴጅንግ በሚጠቀም በማንኛውም ሰው ላይ ተፅዕንዖ ሊኖረው ይችላል፡፡

በአዲሱ የሶፍትዌር አፕዴት ተጠቃሚዎች ስልካቸውን ወደ አይኦኤስ 14.8 በማሳደግ ሊሰነዘሩ ከሚችሉ ጥቃቶች ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ተጠቃሚዎች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሴቲንግ ከዚያም ጀነራል ወደሚለው ገብተው ሶፍትዌር አፕዴት የሚለውን በመንካት ብቻ ከዚህ ስጋት መጠበቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ከእስራኤሉ ኩባንያ ኤን.ኤስ.ኦ ግሩፕ ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች አሳሳች ሊንኮችን ሳይነኩ ለጥቃት የሚጋለጡባቸው የ “ዜሮ ክሊክ” ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ኩባንያው አገልግሎቶቹን ሽብርተኝነት እና ወንጀልን ለሚከላከሉ የመንግስት አካላት ብቻ እንደሚያቀርብ ቢገልፅም በቅርብ የወጡ ጥናቶች እንዳመላከቱት ግን ሶፍትዌሩ በጋዜጠኞች እና እውቅ ፖለቲከኞች ላይ ስለላን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ታድያ እንዲህ አይነት ያለ ተጠቃሚው የአጠቃቀም ስህተት ወደ ስልክ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት ስልክን በየጊዜው አፕዴት የማድረግን ነገር እጅጉን አንገብጋቡ አድርገውታል፡፡

ምንጭ፤ ሲኤንኤን
ለተጨማሪ፤ https://edition.cnn.com/.../iphone-software.../index.html
ሸረሪቶችና ጥቅማቸው
************
ለመሆኑ ስነ-ምህዳር ወይም ኢኮሲስተም ማለት ምን ማለት ነው፤ የአንድ አካባቢ ስነ-ምህዳር ተፈጥሯዊ ይዘቱን እንደጠበቀ መቀጠል ከቻለ የአካባቢው ስነ ምህዳር የተጠበቀ ነው ይባላል፡፡ በአንድ ስነ-ምህዳር ውስጥ ፍጹም ጠቃሚ ፍጹም ጎጂ የሚባል ነገር የለም፡፡ የሁሉም መኖር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ ስለተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ አጭር መረጃን እናጋራችሁ፡፡

በቤታችን ውስጥ የቤታችን ግድግዳ እና አንዳንድ ጥጋጥጎች ቆሽሸዋል ከሚያስብላቸው ነገሮች መካከል አንደኛው የሸረሪት ከዚህም ከዚያም መገኘትና የሸረሪት ድር ተለጥፎ መመልከት ነው፡፡ ምንም እንኳን ለመቀበል አስቸጋሪ ቢመስልም ሳይንስ ከዚህ በኋላ በቤታችሁ የምታገኙትን ሸረሪት አትግደሉ ይለናል፡፡ ለመሆኑ ጥቅም ይኖራቸው ይሆን፡፡

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ ሸረሪቶች በቤት ውስጥ እና በቤት ውጭ ላለው ስነ ምህዳር በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በብዙዎቻችን ሀሳብ ሸረሪቶች ከቤት ውጭ ወደ ውስጥ የሚመጡ ቢመስሉንም እውነታው ግን አንዳንዶቹ በተፈጥሯቸው በቤት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች በድንገት ወደቤት የገቡ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ጥቂት ጊዜያትን ለማሳለፍ በእንግድነት የሚመጡ ናቸው፡፡ ታዲያ በዚህ መልክ ወደቤታችን የሚገቡ ሸረሪቶች አብዛኘዎቹ ሰዎችን የማጥቃት ወይም የአደገኝነት መገለጫ የላቸውም፡፡

የመረጃ ምንጫችን በዚህ ዘርፍ የተደረገን አንድ ጥናት ዋቢ አድርጎ የሰራው ዘገባ በደቡብ ካሮሊና አንድ የጥናት ቡድን 50 ቤቶችን መሰረት ያደረገ ጥናት ማካሄዱን ይገልጽልናል፡፡ ሸረሪቶቹ የ50ወቹን ቤቶች ጣሪያዎች መኖሪያቸው አድርገው የተቀመጡ ናቸው፡፡ በብዛት በቤት ውስጥ ከሚኖሩ የሸረሪት ዝርያዎች ውስጥ ኮብዌብ እና ሴላር የሚባሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡

እነዚህ ሸረሪቶች የሚያደሩት ድር ምግባቸውን ለማደን ይረዳቸዋል፡፡ በተለይ ሴላር የሚባሉት የሸረሪት ዝርያ አይነቶች ድራቸውን ሌሎች ሸረሪቶችን ለማጥመድ ይጠቀሙበታል፡፡ በሸረሪት ድር የመያዝ ስጋት ካለባቸው ነብሳት አብዛኘዎቹ ለሰዎች ጤና ጎጂ የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሸረሪቶች በቤት ውስጥ መኖራቸው ለበሽታ ምክነያት የሆኑ የተለያዩ ነገሮች ስነ ምህዳሩን ባልጎዳ መልኩ ሰዎችን እንዳይጎዱ የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ለሸረሪት ድሮች ዋነኛ ሲሳይ ከሆኑት ውስጥ በሽታ ተሸካሚ የሆኑ የተለያዩ በራሪ ነብሳት ሲሆኑ ከእነዚህም የወባ ትንኝ፣ ዝንብ እና ቢብቢ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሸረሪቶች በተፈጥሯቸው አስፈሪዎች ቢመስሉም የሚፈሩትን ያህል ጉዳት የሌላቸው እና ይልቁንም ከጉዳታቸው ጥቅማቸው እንደሚያመዝን የተሰራው ጥናት አመልክቷል፡፡

ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/plants-and-animals/why-you-should-never-kill-a-spider-in-your-home/?fbclid=IwAR3YrF4QITl2MIzIz3isQ4aQbnuZWV3uaxkfXRnvwDpoy6FuefZhS0a54Z4
‘’የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት’’

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አመራሮችና መላው ሰራተኞች የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት በሚል የተዘጋጀውን ሀገራዊ ዘመቻ ተቀላቅለዋል፡፡

ስለሃገራችን የተዛቡ መራጃዎች እየተሰራጩ ባለበት በዚህ ጊዜ እወነታውን ለአለም አቀፍ ማህበረስብ ለማሳወቅ በተዘጋጀው በዚህ ሀገራዊ ዘመቻ ላይ የተሳተፉት የኢንስቲትዩት ሰራተኞች የመርሃግብሩ አስፈላጊነት ትልቅ እንደሆነ እና የዚህ አገራዊ ዘመቻው አካል በመሆናቸውም ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው አስረድተዋል፡፡
ስለ ሀገር ጉዳይ ላይ ለመሣተፍ ለደቂቃም ቢሆን አንዘገይም!!
በፈጣን ኢንተርኔት ዘገምተኛ አገልግሎት
*************************************
በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ በአሰልቺነታቸው ከሚታወቁ ችግሮች መካከል አንደኛው ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ አገልግሎት እየተጠቀምን እንኳን በተግባር ያለው ፍጥነቱ በጣም ዘገምተኛ መሆን ነው፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ ካሉ 8.2 ሚሊዮን የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ባሳለፍነው ነሀሴ 2021 የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው 77 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች በገመድ የሚተላለፍን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሲሆን ይህም በሴኮንድ 50 ሜጋ ባይት ማስጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

ይህም በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ የተለያዩ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጥነት የሚፈልጉ አገልግሎቶችን ለማግኘት በቂ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ኔትፍሊክስን ለመከታተል 12 ሜጋ ባይት የሚደርስ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡ ለቪዲዮ ኮንፍረንስ ደግሞ ከ2-3 ሜጋ ባይት በሴኮንድ ሲያስፈልገው ለተለያዩ ጌሞች ከ1 ሜጋ ባይት ያነሰ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡

ይሁን እንጂ 50 ሜጋ ባይት ፍጥነት ያለውን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀም ሰው የቪዲዮዎች መቆራረጥ፣ የምስሎች በፍጥነት አለመክፈት እና መረጃዎችን በፍጥነት የማስተላለፍ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ይህ ችግር ማለትም ፈጣን ኢንተርኔት እያለ እንኳን የሚከሰት መቆራረጥ መሰረታዊ ችግሩ የሚመነጨው ከኢንተርኔት ፍጥነት ሳይሆን ከፍጥነት ጋር ከማይያያዙ latency እና loss ከተባሉ ችግሮች ነው፡፡

ሌተንሲ ወይም አንድ መረጃ ከመረጃ ቋት ወደ መገልገያ ቦታችን ለመድረስ የሚጨርስበት ጊዜ የሚመለከት ሲሆን አነስተኛ እና በአመዛኙ ተመጣጠኝ ወይም ወጥ የሆነ እንዲሆን በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከመረጃ ቋት ወደ ቤታችን ወይም ወደ መገልገያ ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን መረጃ ሲተላለፍ በጉዞ ሂደት የመጥፋት (loss) ወይም መንገድ ላይ የመቅረት ችግር ነው፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው ሰዎች ለአገልግሎት ከከፈሉት የኢንተርኔት ፍጥነት ውስጥ በብዛት የሚጠቀሙት ከ6 በመቶ የማይበልጠውን ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በኦንላን ያለን ቆይታ ካለፈው አመት በ59 በመቶ መጨመሩ ተነግሯል፡፡

ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-internet-jumpy-high.html
ኮቪድ ያላቆመው የፈጠራ ስራ በአለማችን
***************************************
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአዕምሯዊ ንብረት ኤጀንሲ የፈጠራ ስራ ኮቪድ በተስፋፋበት ወቅት እንኳን እድገት እንዳስመዘገበ ገለጸ፡፡ ቴክኖሎጂ፣ የመድሃኒት ቅመማ እና የባዮ ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከፍተኛውን እድገት በማስመዝገብ ከአንዳንድ ዘርፎች በተቃራኒው የተለያዩ የማስፋፊያ ስራዎችን እንደሰሩ ታውቋል፡፡

ይህ የፈጠራ ባለሙያዎችን በማበረታታት፣ በማገዝና የፈጠራ ስራዎቻቸውን በመመዝገብና እውቅና በመስጠት የሚታወቀው የአለም የአእምሯዊ ንብረት ተቋም የፈጠራ ስራ እድገት እያስመዘገበ ቢሆንም አጠቃላይ የፈጠራ ስራ ስነ ምህዳር ግን የሚጠበቅበትን ያክል ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበ እንዳልሆነ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ሀገራት ከወረርሽኙ በኋላ ከዘርፉ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጥቅም በማሰብ መስራት እንዳለባቸው ምክሩን ለግሷል፡፡

በ2020 የፈጠራ ስራ ደረጃ መሰረት ሲውዘርላንድ፣ ስዊዲን፣ አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ መጠን ያለው ስራ ያስመዘገቡ ሲሆን ቻይናና ፈረንሳይ ደግሞ ደረጃቸውን በማሻሻል በእስያን፣ በአውሮፓንና በሰሜን አሜሪካ የበላይነት የተያዘውን የዘርፉ ግንባር ቀደምነት ተቀላቅለዋል፡፡

ኮቪድ 19 ብዙ የስራ ዘርፎችን ያቀዛቀዘ ሲሆን እንደ ኮሚኒኬሽን፣ ሀርድዌር፣ አይ.ሲ.ቲ፣ መድሃኒት ቅመማ እና ባዮ ቴክኖሎጂን የመሰሉ ዘርፎች በተቃራኒው ከፍተኛ መነቃቃት ታይቶባቸዋል፡፡

ይህ የ132 ሀገራትን የፈጠራ እንቅስቃሴ የመዘገበው መረጃ ከ2019 ይልቅ ዘርፉ ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበ እንደሆነና በመቶኛም 8.5 እድገት ማሳየቱን አመላክቷል፡፡ በአለማችን የሚገኙ እንደ አፕል፣ ማይክሮሶፍትና ሁዋዌ የመሰሉ የቴክሎጂ ካምፓኒዎች ካለፈው አመት በ10 በመቶ ከፍ ያለ የኢንቨስትመንት ስራ መስራታቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-agency-coronavirus-emerged.html
ወድቀው የማይሰበሩበት ምድር
************************
በአለማችን ላይ ከተለመደው ውጭ የሆነ የእሳተ ገሞራ ወይም ቅልጥ አለት ያለባት ሀገር ታንዛኒያ ናት፡፡ በአካባቢው ቋንቋ ‹ኦል ዶይንዮ ሌንጋዪ› ወይም የእግዚአብሔር ተራራ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በአካባቢው ያለው በጣም ዝቅተኛ ሀይል ወይም ንደት ያለው ፍንዳታ አለቶቹ ቢወድቁባቸው ጉዳት የማያደርሱ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

ቅልጥ አለቱ በአመዛኙ መጨመር በማያሳይ 520 ዲግሪ ሴልሺየስ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ባዛልት ከሚሰኘው በብዛት ከሚታወቀው የፍንዳታ አይነት ያነሰ ፍንዳታ ያለው ነው፡፡ ባዛልት የተሰኘው ቅልጥ አለት 1000 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚጠጋ መጠነ ሙቀት የሚፈነዳ የገሞራ አይነት ነው፡፡ በታንዛኒያ ያለው ይህ ገሞራ ከገሞራ ሙቀት አንጻር በጣም ቀዝቃዛ በመሆኑ ምንጊዜም አለቱ ጥቁር ሆኖ ይታያል፡፡ ይህም ማለት ፍህም እንደሚመስል የሚያስችለው ሙቀት የሌለው ነው ማለት ነው፡፡

በ2007 አንድ ሰው በዚህ ቅልጥ አለት ላይ ወድቆ በመጠነኛ ጉዳት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ለህይወት የሚያሰጋ ጉዳት እንዳልደረሰበት ተነግሯል፡፡ ከዚህ በጣም ዘገምተኛ ከሆነ ገሞራ የሚወጣው ቅልጥ አለት ‹ካርቦንታይት› የሚሰኝ ሲሆን ከአብዛኛው ቅልጥ አለቶች በተለየ የአልካሊ ውህድ የሆኑ ካልሺየምና ሶዲየም የያዘ ነው፡፡ ቅልጥ አለቶች በብዛት የሲልካ እና የኦክስጅን ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡

ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/environment/volcano-lava-cold-fall-survive/?fbclid=IwAR0_Y70OKo2zUzfUXC6OLdv2r_7atRA6Mm6Zudde1IL-qO8PH6XrwafhczA
ሁለገቡ የኮንቨርጀንስ ሳይንስ የምርምር እድገት
ሁለገቡ የኮንቨርጀንስ ሳይንስ የምርምር እድገት
======================
ኮንቨርጀንስ ሳይንስ (Convergence science) የሳይንቲፊክ ምርምር አሰራር ሰፊ አስተሳሰብ ሲሆን በአንድ ዘርፍ ላይ ከማተኮር ይልቅ የተቀናጀ የምርምር አሰራር ላይ ያተኩራል። ኮንቨርጀንስ ሳይንስ በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ስፔሻላይዝ ከማድረግ ወይም በአንድ ዘርፍ ላይ ከመብቃት ይልቅ ብዙ መስኮች ላይ ማተኮር የሚፈልግ ሳይንስ ነው። ይህም አንድ የህክምና ባለሙያ የአይሲቲ ባለሙያ፣ መሃንዲስ፣ የኤሌክትሮኔክስ ባለሙያ፣ የፊዚክስ ባለሙያ ወይም ሌላ የኬሚስትሪ ባለሙያ እንዲሆን የሚጠይቅ ዘርፍ ነው።

በርካታ ሰዎች ኮንቨርጀንስ ሳይንስ ለፈጠራ መሰረት ወይም ፈር ቀደጅ ነው ይሉታል። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ማቴሪያል ሳይንስ፣ ናኖ ቴክኖሎጂ፣ ኦፕቲክስ፣ ኳንተም ፊዚክስ፣ ኮምፒውቲንግ፣ ሲሙሌሽን እና ሞዴሊንግ የመሳሰሉ ዘርፎች በማደጋቸው የተነሳ ሙሉ ለሙሉ የፊዚካል ሳይንስን ሊቀይር ችሏል። ኮንቨርጀንስ ሳይንስ ቴክኒካዊ መሣሪያዎች፣ የተለያየ ሙያዊ ቅርጾች (ምህንድስና፣ ፊዚክስ) በህይወት ሳይንስ ጥናት ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ። የፊዚካል ሳይንስ የህይወት ሳይንስን እየቀየረ እንዳለ ሁላ በተቃራኒው የህይወት ሳይንሱ ፊዚካል ሳይንሱን በመቀየር ላይ ይገኛል። የባዮ ፊውል፣ ባዮ ማቴሪያል እና ቫይራል ሰልፍ አሴምብሊ ፊዚካል ሳይንስን በመቀየር ላይ የሚገኙ ጥቂት የህይወት ሳይንስ ምሳሌዎች ናቸው።

ከኮንቨርጀንስ ሳይንስ ጠቀሜታዎች መካከል ኮንቨርጀንስ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ወይም ለመፍጠር ነው። ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የተለያዩ ዘርፎች አንድ ላይ በመጣመር የሚሰሩ ተግባራት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው። ጥናትና ምርምር ደግሞ አዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ ነገሮችን ለመፍጠር ትልቅ ድርሻ እንዳለው እሙን ነው። የኮንቨርጀንስ ጥናትና ምርምርም ከተለያዩ ዘርፎች የተሰባጠሩ ሙያተኞች/ ምሁራንን በመያዝ ችግር ፈቺና አዲስ የሆኑ ስራዎችን ይሰራል። ኮንቨርጀንስ ጥናት በአንድ ዘርፍ ስፔሻላይዝ ባደረገ ሰው ብቻ መሰራት አይችልም። የኮንቨርጀንስ ጥናትና ምርምርን ለማከናወን ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ዘርፎች በአንድ ላይ መጣመር ግድ ይላል። በተለያዩ አለማት ዙሪያ ኮንቨርጀንስ ጥናትና ምርምር አሰራር በርካታ ተመራማሪዎች እየሰሩበት የሚገኝ ዘርፍ ነው።ይህም አለማችንን አዲስ ወደሆነ ምዕራፍ እያሸጋገራት የሚገኝ እና ትኩረት የሚሻ የጥናትና ምርምር አይነት ነው።
https://www.ncbi.nlm.nih.gov/pmc/articles/PMC5540327/#:~:text=Convergence%2C%20or%20transdisciplinary%20science%2C%20is,problem%2C%20topic%2C%20or%20theme.
ታዳጊ የኢኖቬሽን አምባሳደሮች ተመረቁ