ከድምጽ ሞገድ የሚፈጥን ድሮን ማርስ ላይ
*****************************
የቻይና ተመራማሪዎች ከድምጽ ሞገድ በተሻለ ፍጥነት የሚበር ድሮን በመስራት ላይ መሆናቸው ተነገረ፡፡ ድሮኑ ከድምጽ ሞገድ 5 እጥፍ በሚበልጥ ፍጥነት መብረር የሚችል ነው ተብሏል፡፡ የመረጃ ምጫችን የደቡብ ቻይና ሞርኒንግ ፖስትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ድሮኑ 1,100 ፓውንድ ክብደት የሚኖረው ሲሆን በ5,000 ሜትር ከፍታ ላይ መብረር የሚችል ነው ተብሏል፡፡
ድሮኑን በመስራት ላይ ያለው የምርምር ቡድን ተመራማሪ የሆኑት የቤይሃንግ ዩኒቨርሲቲው ዡ ዡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በረራ (hypersonic flight) ማርስ ላይ ለማድረግ ቢያንስ 30 ዓመታት ይስፈልጋል ያሉ ሲሆን የድሮኑም ጉዳይ ተመሳሳይና ገና በጅማሮ ላይ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የሚሰሩት ድሮን ከድምጽ ሞገድ 5 እጥፍ በሆነ ፍጥነት መብረር የሚችለው ማርስ ላይ ወይም ምድር ላይ መሆኑን ማረጋገጫ መስጠት አልቻሉም፡፡ እንደሚታወቀው የድምጽ ሞገድ ምድራችን ላይ በሰዓት 1,223 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን ማርስ ላይ ደግሞ 869 ኪሎ ሜትር በሰዓት መጓዝ ይችላል፡፡
የሀይፐርሶኒክ ድሮኑ ዋና አላማም በማርስ ላይ ይሰፍራል ተብሎ ለሚጠበቀው ማህበረሰብ የመጓጓዣ አገልግሎት ለመስጠት ነው፡፡ በቀይዋ ፕላኔት ሰዎች በብዛት እና ሰፊ ቦታዎችን ሸፍነው መስፈር ሲጀምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ ለመንቀሳቀስ ድሮኑ ያግዛቸዋል፡፡ በተጨማሪም ድሮኑ ከናሳዋ ኢንጅኒዩቲ ድሮን የተሻለ የማርስ ላይ አሰሳ መስራት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ድሮኑ ተሰርቶ ሲያልቅ በማግኒዚየም አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ሲሆን ይህም የማርስ ከባቢ አየር 96 በመቶው በካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተሸፈነ በመሆኑና ማግኒዢየሙን በቀላሉ እንዲቀጣጠል የሚያደርገው በመሆኑ ነው፡፡ ቻይና ፈጣኑን ድሮን በ2045 ወደ ማርስ ለማምጠቅ አቅዳ እየሰራች እንደሆነም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ምንጭ futurism
ተጨማሪ ንባብ https://futurism.com/the-byte/china-mars-drone-faster-sound?fbclid=IwAR32IqBqVZCGp2mhOQKNP-vbVdnah2ip60QRlFA_y8yL7Ys3qWAKaVulKGc

Futurism
Chinese Scientists Working on Mars Drone That Flies Faster Than Sound
A team of Chinese scientists have developed a concept for a Mars drone that weighs 1,100 pounds and could travel at five times the speed of sound.
ከጦርነት ቢሊዮኖችን የሚያተርፉት የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች
===================
ታላላቅ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ሀገሪቱ የመስከረም 11ዱን ሽብር ጥቃት ተከትሎ ከመጣውና አሜሪካን ሽብርተኝነትን የመዋጋት (War On Terror) ብላ ከሰየመችው ጦርነት በርካታ ቢሊዮኖን ዶላሮችን ማግኘታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ ሪፖርት አመላከተ፡፡ “ቢግ ቴክ ሴልስ ዋር” የተሰኘው ሪፖርቱ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አማዞን፣ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ማይክሮሶፍት እና ትዊተር በዋናነት በጦርነቱ ላይ ያተኮሩ ትላልቅ ኮንትራቶችን ከመንግስት ወስደው ሲሰሩ እንደነበር ገልጿል፡፡
የአሜሪካን ጦር ኃይል እና ስለላ ተቋማት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጉዜ ወደ ዲጂታል እየተለወጠ መምጣቱን ተከትሎ በክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ጂፒኤስ ሶፍትዌሮች ረገድ ፍላጎታቸውም እየጨመረ ቆይቷል፡፡ የመከላከያ ቢሮውን እንኳን ብናይ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባደረገው ስምምነት 43.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪን አውጥቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ ከሚያወጡት መካከል ከፊት የሚቀመጡት አምስቱ ተቋማት ሀገሪቱ ያወጀችው ይህን ዓለም አቀፍ ጦርነት ተከትለው የተመሰረቱ አልያም ከውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፡
በቅርቡ አማዞን እና ማይክሮሶፍት የነዚህ ስምምነቶች ቀዳሚ ተጠቃሚ ወደ መሆን የተሸጋገሩ ሲሆን ከ2015 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ አማዞን 5 ማይክሮሶፍት ደግሞ 8 ያህል ትላልቅ ኮንትራቶችን ከተቋማቱ ወስደዋል፡፡ ማይክሮሶፍት በተለይ በፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የሚያገኛቸው ከመከላከያ ጋር የተያያዙ መንግስታዊ ኮንትራቶች በይበልጥ አድገውለት ነበር፡፡ በሌላ መልኩ ግን ለወትሮ የጦር ኃይሉ ደንበኛ የነበሩት የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የኮንትራት ድርሻ በማሽቆልቆል ላይ ነው፡፡
መረጃው አሜሪካዊያን መንግስታቸው ውል የሚገባባቸው ኮንትራቶችን እንዲያጋልጡ በሚጠይቅ የበይነ መረብ መንገድ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ታድያ መረጃዎቹ እስካሁን ማግኘት የተቻለው መንግስት ለህዝብ ይፋ ያደረጋቸው ስምምነቶች ብቻ እንደመሆኑ እውነተኛው የኮንትራቶቹ መጠን ከተጠቀሰውም በላይ ላቅ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-big-tech-billions-war-terror.html

Tech Xplore
Big Tech made billions during 'war on terror': report
Tech giants made billions through contracts with the US military and other government agencies during the so-called "war on terror", according to a report released ahead of the 20th anniversary of 9/11.
የዋይ-ቴክ ስታርታፕ ጠቃሚ ፈጠራዎች
=================
ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ዲጂታል መፍትሄዎችንና አሰራሮችን በማቅረብ የሚሰራው ዋይ-ቴክ (Y-Tech) በኢትዮጵያውያን የአኗኗር ሂደት ህይወትን ቀላል የሚደርጉ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን እየሰራ የሚቀርብ በወጣቶች የተመሰረተ ጀማሪ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው፡፡ ስታረታፑ በሜካኒካልና በሶፍትዌር የአሰራር ሂደቶች በመታገዝ በጤና ዘርፉ፣ በቱሪዝም መስክ እና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅርብ ላይ ነው፡፡
በሰባት የስራ ክፍሎች ተከፋፍሎ የተለያዩ ጠቃሚ ፈጠራዎችን በማበልፀግ ላይ ያለው ይህ ስታርታፕ በዋናነት በውሃ ማጣሪያ የቴክኖሎጂ አይነቶች እና የቬንትሌተር መሳሪዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሰራቸው የፕሮታይፕ ፈጠራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ጥቅም ሊሰጥ የሚችለው ኢትዮ ሎኬት የተሰኘው የዲጂታል ፕላትፎረም ሌላው እጅግ ጠቃሚ ፈጠራ ነው፡፡
በተለይም ዋይ-ቴክ ስታርታፕ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ኢትዮ ሎኬት የተባለው የዲጂታል ፕላትፎረም በቀላል ሂደት ተጠቃሚዎች ቦታዎችን እና መረጃዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ እንዲያገኙ የሚያግዝ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም በመሆኑ ማንኛውም የንግድ ድርጅቶች እና ተቋማት አገልግሎታቸውን ወይም ምርቶቻቸውን በኦንላይን እንዲያስተዋውቁ እና ዲጂታል ፕሮፋይል እንዲኖራቸውም የሚያስችል ነው፡፡
ዝርዝሩን ከቪዲዮው ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=Bg4oQg5Cl14

YouTube
#ታዳጊ የፈጠራ ባለሙያዎች#
#የምንፈልገውን ነገር በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል የፈጠራ ውጤት ነው፡፡#
ሰሜን ዋልታ በከፍተኛ ፍጥነት አቅጣጫውን እየለወጠ ነው
==============
የምድራችን ዋልታዎች ብዙ እንስሳት ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ተፈጥሮአዊ እገዛን የሚሰጡና እንደ ቴሌቪዥን፣ የአየር ትንበያ እና ኮምዩኒኬሽን ላሉ የሰው ልጅ ቴክኖሎጂያዊ ግኝቶችም መሰረት ናቸው፡፡ ታድያ አሁን ላይ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የሰሜን ዋልታ አሁን ካለበት የካናዳ አርክቲክ ክፍል ወደ ሳይቤሪያ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነና ይህ እንቅስቃሴውም አስጊ በሆነ ሁኔታ ፍጥነቱን እየጨመረ መሆኑን አዲስ የወጣ ምርምር ይፋ አድርገኋል፡፡ በዚህም የሰሜን ዋልታ የሚንቀሳቀስበት ፍጥነት በዓመት ወደ 48 ኪ.ሜ አድጓል፡፡
የምድራችን ዋልታዎች መገኛቸውን ሲቀይሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ምድራችን ባለፉት 2.6 ሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ለ10 ጊዜያት የዋልታዎቿ መገኛ የተለወጠ ሲሆን የቅርብ የሚባለው ለውጥ የተከሰተውም የዛሬ 780 ሺህ ዓመታት ገደማ ነበር፡፡
እስካሁን እነዚህን ለውጦች በእርግጠኝነት ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን የዋልታዎች ለውጥ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ ተፅዕኖውን እንደሚያሳድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ ከነዚህ ተፅዕኖዎች መካከል ምድራችንን እራሷን ከፀሐይ እና ኮስሚክ ሬዮች ከሚመጡባት በቻርጅ የተሞሉ ቅንጣቶች (charged particles) እራሷን የምትጠብቅበትን ስርዓት ሊያዳክሙት ይችላሉ የሚለው ነው፡፡
በሌላ መልኩ አንዳንድ የስነ ምድር ምሁራን መሰል የዋልታ ለውጦችን ምድር ላይ ከተከሰቱ መጠነ ሰፊ የህይወት ድምሰሳዎች (mass extinctions) ጋር ሲያያይዟቸው ሌሎች በበኩላቸው ቅድመ የሰው ልጅ ዝርያዎች የተለያዩ የዋልታ ለውጦችን ቢያስተናግዱም ለውጡን ተቋቁመው መቆየታቸውን በመጥቀስ ይሞግታሉ፡፡ የሆነው ሆኖ የዋልታ ለውጦቹ የሚያመጡትን ተፅዕንዖ ሙሉ ለሙሉ መረዳት ባይቻልም ለውጦቹ የሚመጡበት ፍጥነት ግን ተፅዕኖዋቸውን እንደሚወስነው ይነገራል፡፡ ለአብነት ዋልታዎቹ አቅጣጫቸውን የሚለውጡት ዝግ ባለ ፍጥነት ከሆነ ተፈጥሮም ሆነ የሰው ልጆች ከለውጡ ጋር በተሻለ እራሳቸውን እያላመዱ መሄድ ይችላሉ፡፡
መንስኤያቸውን በተመለከተ የዋልታ ለውጦች ምናልባትም የዛሬ 4.5 ቢሊዮን ዓመት ከምድር ጋር በተጋጨችው ቴአ በተሰኘች ቀደምት ፕላኔት አማካኝነት የሚከሰቱ ሊሆኑ ይችላል የሚል ግምት በተመራማሪዎች ዘንድ አለ፡፡ የዚህች ጥንታዊ ፕላኔት ከምድር ጋር ስትጋጭ ስብርባሪዋ ለጨረቃ መፈጠር ምክንያትም ሆኗል፡፡ እስካሁን የዚህች ፕላኔት የተቀረው ክፍል የት እንዳለ ባይታወቅም አንዳንድ ተመራማሪዎች ግን ምድር ውስጥ ተቀብሮ ስለመቅረቱ ይናገራሉ፡፡
በቅርብ የወጡ የስነ-ምድር ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም የፕላኔቷ ቅሪት ምናልባትም ከዓለማችን በርዝመቱ ቀዳሚ ከሆነው የኤቨረስት ተራራ ሁለት እጥፍ የሚገዝፉ ሁለት አለቶች ሆነውና ከተቀረው የማንትል ክፍልም በይበልጥ ጠቅጠቅ እና ሞቅ ብለው መቀመጣቸውን ነው፡፡ እነዚህ አለቶች ታድያ የምድራችን ዋልታዎች መነሻ ላይ ጣልቃ በመግባት በደቡባዊ አትላንቲክ በኩል እያዳከሙት ሊሆን ይችላል፡፡
ምንጭ፤ ስፑቲኒክ
ለተጨማሪ፤ https://sputniknews.com/20210915/earths-magnetic-field-may-be-reversing-due-to-remains-of-ancient-planet-scientists-warn-1089094074.html

Sputnik International
Earth's Magnetic Field May Be Reversing Due to Remains of Ancient Planet, Scientists Warn
Our planet's magnetic field is something that naturally helps many animals to navigate, while also serving as a base for a huge amount of technological advances by humanity, such as television broadcasting, weather forecasting, and...
የአነስተኛ ካልኩሌተር ፈጣሪ ክላይቭ ሲንክላር በ81 ዓመታቸው አረፉ
==========================
ዘርፉ ብዙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ እና በመጀመሪያዎቹ የኮምፒውቲንግ ስራዎች ላይ ትልልቅ ግኝቶችን ያበረከቱት ሰር ክላይቭ ሲንክላር በ81 ዓመታቸው ማረፋቸው ተነግሯል፡፡ እኝህ የቴክኖሎጂ ሰው አሁን አለም በስፋት ለሚጠቀምባቸው የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች መሰረት የሆኑ የመጀመሪያዎቹን የቤት ወይም የግል ኮምፒውተሮች በማበልፀግ ስራ ላይ ትልቅ ሚና የነበራቸው ሲሆን በ1970ዎቹ ይበልጥ ዘምነው ወደተጠቃሚዎች መቅረብ በጀመሩት አነስተኛ ወይም ፖኬት የካልኩሌተር ፈጠራዎች ላይ ደግሞ ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
ሰር ክላይቭ ሲንክላር እንደአውሮፓውያኑ በ1980ዎቹ ZX80 የተባለውን የግል ኮምፒውተር መስራት በጀመሩበት አመታት የግል ኮምፒውተር ፈጠራዎች ብዙም ያልተስፋፉበት ዘመን ስለነበር የክላይቭ ሲንክላር ስራዎች ኋላ ላይ ይበልጥ እየጎለበቱ ለመጡት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ፈጠራዎች ትልቅ መሰርት የጣሉ ሆነው አልፈዋል፡፡ ሰር ክላይቭ ሲንክላር በቋቋሙት ድርጀት ይበልጥ እየተሸሻለ ሲቀርብ የነበረው ZX ስፔክትረም ኮምፒውተር ለግል ኮምፒውተሮች ማደግ ከነበረው ሚና በተጨማሪ ለዘመናውያኑ የቪዲዮ ጌም ፈጠራዎች ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ ግኝት እንደነበር ይነገራል፡፡
እንደአውሮፓውያኑ በ1940 በእንግሊዝ ሃገር የተወለዱት ሰር ክላይቭ ሲንክላር እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ደረስ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን በተለይም ባለሶሰት እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈጠራዎች እና የቴሌቭዥን ምርት ላይ የነበራቸው ተሳትፎ በጉልህ የሚገለፅ ነው፡፡ ለብዙ አመታት ይዟቸው በነበረው ካንሰር የህክምና እገዛ ሲደረግላቸው ቆይተው በ81 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ሰር ክላይቭ ሲንክላር ዘርፉ ብዙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ እና በመጀመሪያዎቹ የኮምፒውቲንግ ስራዎች ላይ በነበራቸው ትልቅ አሻራ በትውልድ የሚታወሱ ይሆናል፡፡
https://www.independent.co.uk/news/uk/home-news/clive-sinclair-dead-spectrum-c5-b1921670.html

The Independent
Tech pioneer Sir Clive Sinclair dies aged 81
Technology pioneer Sir Clive Sinclair has died at the age of 81, his family have confirmed.
ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች
********************************************************************
በቻይና ታሪክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ ያደረጉትን የህዋ ላይ ቆይታ አጠናቀው ወደ ምድር መመለሳቸው ተነገረ፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች ቲያንጎንግ በተሰኘው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር ጣቢያ ለ90 ቀናት ያክል ቆይተው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ከሰሩ በኋላ በሙሉ ጤንነት ወደ ምድር ተመልሰዋል፡፡ በቆይታቸውም የህዋ ላይ እንቅስቃሴ (spacewalks) እና የተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን አካሂደዋል፡፡
12ቱም ተመራማሪዎች ወደቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት ለ2 ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ተቀምጠው ክትትል እንደሚደረግላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ተልዕኮ እያደገ የመጣው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር አካል ሲሆን ሀገሪቱ ማርስ ላይ የአሰሳ ሮቨር ማምጠቅና ወደ ጨረቃም የተለያዩ የምርምር ግብዓቶችን መላኳ በዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አመላካች ነው፡፡
ቲያንጎንግ ሰማያዊ ስፍራ ("heavenly palace") ማለት ሲሆን ለ10 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተሰራ የህዋ ላይ የምርምር ጣቢያ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ 3ቱም ከሀገሪቱ የመከላከያ ሀይል የተገኙ ሲሆኑ አንደኛው ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የህዋ ላይ ጉዞን በማድረግ ልምድ ያለው መሆኑ ተነግሯል፡፡
የቻይና ስፔስ ኤጀንሲ በቀጣዩ አመት ብቻ 11 የህዋ ላይ ጉዞ ያቀደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ተመራማሪዎችን ይዘው የሚጓዙ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም 70 ቶን የሚደርሱ ሁለት የቤተ ሙከራ መገንቢያ ቁሶችም እንደሚላኩ ታውቋል፡፡ ቻይና የህዋ ላይ ምርምሯን የመከላከያ ሀይሏን መሰረት ባደረገ መልኩ እያከናወነች ትገኛለች፡፡
ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-09-chinese-astronauts-earth-day-mission.html

phys.org
Chinese astronauts return to Earth after 90-day mission
Three Chinese astronauts returned to Earth Friday after completing the country's longest-ever crewed mission, the latest landmark in Beijing's drive to become a major space power.
የአይፎን ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በአስቸኳይ አፕዴት እንዲያደርጉ ተጠየቁ
=====================
እንደ ሌሎች የስልክ አምራቾች ሁሉ አፕልም በየጊዜው ለስልክ እና ሌሎች ምርቶቹ የሶፍትዌር ማሻሻያ ወይም አፕዴት ሲያቀርብ ቢቆይም ከሰሞኑ ግን ከጥቃት ተጋላጭነት ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ስልካቸውን አብዴት እንዲያደርጉ ተነግሯል፡፡ ገለልተኛ አጥኚዎች እንዳመላከቱት የአይፎን ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም በጋዜጠኞች ላይ ሲሰልል ከነበረ ሶፍትዌር ጋር በተያያዘ ለጥቃት ተጋላጭ ሆነዋል፡፡
የአፕል የደህንነት ምህንድስና ኃላፊ እንዳስታወቁት ሶፍትዌሩ የተወሰኑ ግለሰቦችን ብቻ ኢላማ የሚያደርግና ለአብዛኛው ተጠቃሚ ስጋት ያልሆነ ቢሆንም ተጠቃሚዎች ምንም አይነት አሳሳች ሊንኮችን ሳይጫኑ ጭምር ስልካቸው እንዲበረበር ወይም ሀክ እንዲደረግ በር የሚከፍት በመሆኑ አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም አይሜሴጅንግ በሚጠቀም በማንኛውም ሰው ላይ ተፅዕንዖ ሊኖረው ይችላል፡፡
በአዲሱ የሶፍትዌር አፕዴት ተጠቃሚዎች ስልካቸውን ወደ አይኦኤስ 14.8 በማሳደግ ሊሰነዘሩ ከሚችሉ ጥቃቶች ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ተጠቃሚዎች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሴቲንግ ከዚያም ጀነራል ወደሚለው ገብተው ሶፍትዌር አፕዴት የሚለውን በመንካት ብቻ ከዚህ ስጋት መጠበቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ ከእስራኤሉ ኩባንያ ኤን.ኤስ.ኦ ግሩፕ ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች አሳሳች ሊንኮችን ሳይነኩ ለጥቃት የሚጋለጡባቸው የ “ዜሮ ክሊክ” ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ኩባንያው አገልግሎቶቹን ሽብርተኝነት እና ወንጀልን ለሚከላከሉ የመንግስት አካላት ብቻ እንደሚያቀርብ ቢገልፅም በቅርብ የወጡ ጥናቶች እንዳመላከቱት ግን ሶፍትዌሩ በጋዜጠኞች እና እውቅ ፖለቲከኞች ላይ ስለላን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ታድያ እንዲህ አይነት ያለ ተጠቃሚው የአጠቃቀም ስህተት ወደ ስልክ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት ስልክን በየጊዜው አፕዴት የማድረግን ነገር እጅጉን አንገብጋቡ አድርገውታል፡፡
ምንጭ፤ ሲኤንኤን
ለተጨማሪ፤ https://edition.cnn.com/.../iphone-software.../index.html

ሸረሪቶችና ጥቅማቸው
************
ለመሆኑ ስነ-ምህዳር ወይም ኢኮሲስተም ማለት ምን ማለት ነው፤ የአንድ አካባቢ ስነ-ምህዳር ተፈጥሯዊ ይዘቱን እንደጠበቀ መቀጠል ከቻለ የአካባቢው ስነ ምህዳር የተጠበቀ ነው ይባላል፡፡ በአንድ ስነ-ምህዳር ውስጥ ፍጹም ጠቃሚ ፍጹም ጎጂ የሚባል ነገር የለም፡፡ የሁሉም መኖር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ ስለተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ አጭር መረጃን እናጋራችሁ፡፡
በቤታችን ውስጥ የቤታችን ግድግዳ እና አንዳንድ ጥጋጥጎች ቆሽሸዋል ከሚያስብላቸው ነገሮች መካከል አንደኛው የሸረሪት ከዚህም ከዚያም መገኘትና የሸረሪት ድር ተለጥፎ መመልከት ነው፡፡ ምንም እንኳን ለመቀበል አስቸጋሪ ቢመስልም ሳይንስ ከዚህ በኋላ በቤታችሁ የምታገኙትን ሸረሪት አትግደሉ ይለናል፡፡ ለመሆኑ ጥቅም ይኖራቸው ይሆን፡፡
እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ ሸረሪቶች በቤት ውስጥ እና በቤት ውጭ ላለው ስነ ምህዳር በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በብዙዎቻችን ሀሳብ ሸረሪቶች ከቤት ውጭ ወደ ውስጥ የሚመጡ ቢመስሉንም እውነታው ግን አንዳንዶቹ በተፈጥሯቸው በቤት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች በድንገት ወደቤት የገቡ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ጥቂት ጊዜያትን ለማሳለፍ በእንግድነት የሚመጡ ናቸው፡፡ ታዲያ በዚህ መልክ ወደቤታችን የሚገቡ ሸረሪቶች አብዛኘዎቹ ሰዎችን የማጥቃት ወይም የአደገኝነት መገለጫ የላቸውም፡፡
የመረጃ ምንጫችን በዚህ ዘርፍ የተደረገን አንድ ጥናት ዋቢ አድርጎ የሰራው ዘገባ በደቡብ ካሮሊና አንድ የጥናት ቡድን 50 ቤቶችን መሰረት ያደረገ ጥናት ማካሄዱን ይገልጽልናል፡፡ ሸረሪቶቹ የ50ወቹን ቤቶች ጣሪያዎች መኖሪያቸው አድርገው የተቀመጡ ናቸው፡፡ በብዛት በቤት ውስጥ ከሚኖሩ የሸረሪት ዝርያዎች ውስጥ ኮብዌብ እና ሴላር የሚባሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
እነዚህ ሸረሪቶች የሚያደሩት ድር ምግባቸውን ለማደን ይረዳቸዋል፡፡ በተለይ ሴላር የሚባሉት የሸረሪት ዝርያ አይነቶች ድራቸውን ሌሎች ሸረሪቶችን ለማጥመድ ይጠቀሙበታል፡፡ በሸረሪት ድር የመያዝ ስጋት ካለባቸው ነብሳት አብዛኘዎቹ ለሰዎች ጤና ጎጂ የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሸረሪቶች በቤት ውስጥ መኖራቸው ለበሽታ ምክነያት የሆኑ የተለያዩ ነገሮች ስነ ምህዳሩን ባልጎዳ መልኩ ሰዎችን እንዳይጎዱ የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ለሸረሪት ድሮች ዋነኛ ሲሳይ ከሆኑት ውስጥ በሽታ ተሸካሚ የሆኑ የተለያዩ በራሪ ነብሳት ሲሆኑ ከእነዚህም የወባ ትንኝ፣ ዝንብ እና ቢብቢ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሸረሪቶች በተፈጥሯቸው አስፈሪዎች ቢመስሉም የሚፈሩትን ያህል ጉዳት የሌላቸው እና ይልቁንም ከጉዳታቸው ጥቅማቸው እንደሚያመዝን የተሰራው ጥናት አመልክቷል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/plants-and-animals/why-you-should-never-kill-a-spider-in-your-home/?fbclid=IwAR3YrF4QITl2MIzIz3isQ4aQbnuZWV3uaxkfXRnvwDpoy6FuefZhS0a54Z4

IFLScience
Why You Should Never Kill A Spider In Your Home
I know it may be hard to convince you, but let me try: Don’t kill the next spider you see in your home. Why? Because spiders are an important part of natu
‘’የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት’’
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አመራሮችና መላው ሰራተኞች የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት በሚል የተዘጋጀውን ሀገራዊ ዘመቻ ተቀላቅለዋል፡፡
ስለሃገራችን የተዛቡ መራጃዎች እየተሰራጩ ባለበት በዚህ ጊዜ እወነታውን ለአለም አቀፍ ማህበረስብ ለማሳወቅ በተዘጋጀው በዚህ ሀገራዊ ዘመቻ ላይ የተሳተፉት የኢንስቲትዩት ሰራተኞች የመርሃግብሩ አስፈላጊነት ትልቅ እንደሆነ እና የዚህ አገራዊ ዘመቻው አካል በመሆናቸውም ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው አስረድተዋል፡፡
ስለ ሀገር ጉዳይ ላይ ለመሣተፍ ለደቂቃም ቢሆን አንዘገይም!!

በፈጣን ኢንተርኔት ዘገምተኛ አገልግሎት
*************************************
በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ በአሰልቺነታቸው ከሚታወቁ ችግሮች መካከል አንደኛው ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ አገልግሎት እየተጠቀምን እንኳን በተግባር ያለው ፍጥነቱ በጣም ዘገምተኛ መሆን ነው፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ ካሉ 8.2 ሚሊዮን የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ባሳለፍነው ነሀሴ 2021 የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው 77 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች በገመድ የሚተላለፍን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሲሆን ይህም በሴኮንድ 50 ሜጋ ባይት ማስጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
ይህም በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ የተለያዩ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጥነት የሚፈልጉ አገልግሎቶችን ለማግኘት በቂ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ኔትፍሊክስን ለመከታተል 12 ሜጋ ባይት የሚደርስ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡ ለቪዲዮ ኮንፍረንስ ደግሞ ከ2-3 ሜጋ ባይት በሴኮንድ ሲያስፈልገው ለተለያዩ ጌሞች ከ1 ሜጋ ባይት ያነሰ ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡
ይሁን እንጂ 50 ሜጋ ባይት ፍጥነት ያለውን የበይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀም ሰው የቪዲዮዎች መቆራረጥ፣ የምስሎች በፍጥነት አለመክፈት እና መረጃዎችን በፍጥነት የማስተላለፍ ችግር ይገጥመዋል፡፡ ይህ ችግር ማለትም ፈጣን ኢንተርኔት እያለ እንኳን የሚከሰት መቆራረጥ መሰረታዊ ችግሩ የሚመነጨው ከኢንተርኔት ፍጥነት ሳይሆን ከፍጥነት ጋር ከማይያያዙ latency እና loss ከተባሉ ችግሮች ነው፡፡
ሌተንሲ ወይም አንድ መረጃ ከመረጃ ቋት ወደ መገልገያ ቦታችን ለመድረስ የሚጨርስበት ጊዜ የሚመለከት ሲሆን አነስተኛ እና በአመዛኙ ተመጣጠኝ ወይም ወጥ የሆነ እንዲሆን በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከመረጃ ቋት ወደ ቤታችን ወይም ወደ መገልገያ ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን መረጃ ሲተላለፍ በጉዞ ሂደት የመጥፋት (loss) ወይም መንገድ ላይ የመቅረት ችግር ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው ሰዎች ለአገልግሎት ከከፈሉት የኢንተርኔት ፍጥነት ውስጥ በብዛት የሚጠቀሙት ከ6 በመቶ የማይበልጠውን ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በኦንላን ያለን ቆይታ ካለፈው አመት በ59 በመቶ መጨመሩ ተነግሯል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-09-internet-jumpy-high.html

Why does my internet connection feel slow and jumpy, even when my internet speed is high?
Of the 8.2 million homes and businesses active on Australia's National Broadband Network (NBN) in July 2021, 77% are now reported to be on a broadband plan that delivers speeds of at least 50 megabits ...