ከባድ የሶላር ሱናሜ የአለምን ኢንተርኔት ሊያጠፋ ይችላል
===========================
ከፀሀይ የሚነሱ ሞቃት ነፋሳት የሚገድባቸው ነገር እስካላገኙ ድረስ ህዋ ውስጥ ይጉዋዛሉ። እነዚህን ነፋሳት ሊያቆሟቸው የሚችሉት ከሚጉዋዙበት ፍጥነት በበለጠ እና በተቃራኒ አቅጣጫ የሚነፍሱ ነፋሳት ብቻ ናቸው። የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ (magnetic field) ከፀሃይ ውስጠኛ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት የሚመጡትን ሞቃትማ ነፋሳት የሚያግድ ቢሆንም በጥለቁ የህዋ ክፍል የሚገኙ ሌሎች የበይነኮከባዊ ነፋሳት (Interstellar winds) ከፀሀያችን የሚወጡትን ሞቃታማ ነፋሳት የምድራችን ካባቢ አየር ጋር ከመድረሳቸው በፊት ፍጥነታቸውን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የብዙ ፕላኔቶች የመግነጢሳዊ መስክ መገኛ በሆነ የህዋ ክፍል የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ የበላይነት ይዞ የሚገኝበት እና በብዙ ሺ ኪሎሜትሮች ምድራችንን ሸፍኖ የሚገኘው ንጣፍ ማግኔቶስፌር (magnetosphere) ተብሎ ይጠራል፡፡
ከባህር ወለል በላይ ብዘ መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ በጥልቁ የህዋ ክፍል እስከ አስረሽ ሺ ኪሎ ሜትሮች ድረስ የሚዘረጋው የማግኔቶስፌር ንጣፍ የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ እና ከፀሀያችን የሚነሱ ፕላስማ የተሰኙ ፖርቲክሎች ከፍተኛ ግንኙነት የሚያድረጉበት የህዋ ክልል ነው፡፡ ምድርን ሸፍኖ የሚገኘው የማግኔቶስፌር ንጣፍ ወይም ሌየር ከፀሃይ የሚመጣውን ቻርጅድ ፓርቲክልስ የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ ቢሆንም አልፎ እልፎ በከፍተኛ መጠን የሚመጣው የሶላር ስቶርም ወይም በሳይንሳዊ አጣራሩ (geomagnetic storm) በምድራችን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ አደጋን ሊያስከትከል ይችላል፡፡
በፀሃይ የመግነጢሳዊ መስክ ዙሪያ በሚኖር አለመረጋጋት በከፍተኛ መጠን ወደ ህዋ ክፍል የሚሰራጨው በቢሊዮን ቶን የሚለካ ከፍተኛ ሙቀት ያለው ጋዝ ለምድራችን ስጋት ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት ተመራመሪዎች ይህም ከዚህ ቀድም በተለያዩ ጊዚያት ተከስቶ ለነበረው coronal mass ejection (CME) ዋና ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሚገኙትና በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ የምርምር ጽሁፍ ያሳተሙት ፕሮፌሰር አርቪንና ረዳቶቻቸው እንደሚሉት በተለያየ የጊዜ ኡደት ወደ ህዋ ክፍሎች የሚሰራጨው ከባድ የሶላር ሱናሜ የምድራችንን መግነጢሳዊ መስክ በማጥቃት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር የአለማችንን ኢንተርኔት ወይም በይነ-መረብ የማጥፋት አቅም አንዳለው ይናገራሉ፡፡ በተለይም በዓለምችን የበይነመረብ መሠረተ ልማት ውስጥ ወሳኝ አካል የሆኑት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች በሶላር ስቶርም የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስባቸው ከማቻሉ አንጻር የአለምን ኢንተርኔት በቀጥታ የመጥፋት እድል እንደሚኖረው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡
እንዲህ ያሉ ክስተቶች ቀድም ባሉት ጊዜያት አልፎ አልፎ የመከሰት እድል ቢኖራቸውም ኡሁን ባለው ደረጃ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በአለም ላይ ባለመስፋፋታቸው ጉዳቱን አነስተኛ አንዲሆን ማድረጉን የሚናገሩት ተመራማሪዎች የበይነ-መረብ ዝርጋታ ከመጀመሩ በፊት እንደአውሮፓውያኑ በ1989 የተከሰተው የ coronal mass ejection አደጋ ለብዙ ሰዓታት የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲቋረጥ ያደረገበት ሁኔታ እንደምሳሌ የሚጠቀስ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ አሁን ላይ ለበይነ-መረብ መስፋፋት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች (undersea internet cables) ዋና መሰረተ ልማት ከመሆናቸው አንጻር እነሱ ላይ በቀጥታ ሊደርስ የሚችል አደጋ የሰዎችን የበይነ-መረብ ግንኙነት በማቋረጥ ለአለማችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ትልቅ ጉዳትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በብዙ አመታት አንዴ ሊያጋጥም ይችላል የሚባለው ይህ ከባድ የሶላር ሱናሜ ምድራችንን በ1859፣ በ1921 እና በቅርቡ በ1989 እንዳጠቃት የሚናገሩት ተመራማሪዎች አሁን ካለው የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት መስፋፋፈት ጋር ተያይዞ አደጋው እጅግ የከፋ እንዳይሆን ተገቢውን ትከረት መስጠት እና ምርምሮች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈል ይናገራሉ፡፡
ምንጭ infomance
https://www.infomance.com/a-solar-tsunami-could-knock-out-global-internet-heres-what-that-means/

የኢኖቬሽን አምባሳደር ፕሮግራም የምረቃ በዓል
===============
ኢኖቬሽንን በሀገራችን ለማስፋፋት በማለም በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አማካኝነት ላለፉት ሦስት ወራት ሲካሄድ የቆየውን የመጀመሪያ ዙር የኢኖቬሽን አምባሳደር ፕሮግራምን የተከታተሉ ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ይመረቃሉ፡፡ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተውጣጥተው ፕሮግራሙን ሲከታተሉ የቆዩት ተማሪዎቹ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ደኤታው ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ እንዲሁም የስቴም ፓወር ኢትዮጵያ ፋብላብስ ማናጀሩ ዶ/ር ስሜነው ቀስቅስ በተገኙበት በኤሊያና ሆቴል የሚመረቁ ይሆናል፡፡
Innovation Ambassador Program graduation ceremony
The graduation ceremony of the first cohort of the Innovation Ambassador Program organized by the Technology and Innovation Institute (TECHIN) of Ethiopia will be held on September 21, 2021, at Eliana Hotel in Addis Ababa.
H.E. Prof. Afework Kassu, Sate Minister of Science and Higher Education, and Dr. Simenew Keskes, FabLabs Manager of STEM Power Ethiopia will make opening remarks on the occasion.

የሰው ሰራሽ ኩላሊት የተሳካ ሙከራ
*************************************
የኩላሊት ህመም ችግርን ለመቅረፍ የሚሰራው የኩላሊት ፕሮጀክት ሰው ሰራሽ ኩላሊትን የመጀመሪያ ምርት የተሳካ ሙከራ ማድረጉ ተሰማ፡፡ የኩላሊት ህመምተኞች ከኩላሊት እጥበት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጫናና ስቃይ ውጥ እንደሚገቡ ይታወቃል፡፡
ይህንን ችግር ያስተዋሉ ተመራማሪዎች የኩላሊት ህመምተኞችን ከዚህ ችግር ሊያላቅቅ የሚችል ከፍተኛ ምርምረን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ምርምሩም አድጎ የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ኩላሊት ተሰርቶ የተሳካ ሙከራ እንደተደረገበት መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ሰው ሰራሽ ኩላሊቱ 650 ሺህ የአሜሪካን ዶላረፍ እንደሚያወጣ የተነገረ ሲሆን ፕሮጀክቱም ኪድኒ ኤክስ በተሰኘ በአሜሪካ የጤናና የአገልግሎት ክፍል እና የአሜሪካ ኔፍሮሎጂ ማህበረሰብ ጥምረት የተሰራ ነው፡፡ ሰው ሰራሽ ኩላሊቱን ሰርቶ ያቀረበው የተመራማሪዎች ቡድን በዚህ ስራው በአለም ውስጥ በዘርፉ ሽልማትን ካገኙ ከስድስት ምርምሮች አንዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የምርምር ቡድኑ በቤት ውስጥ ደምን የሚያጣራ የኩላሊት ስራን ተክቶ ሊሰራ የሚችል መሳሪያን በማቅረብ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሰው ሰራሽ ኩላሊቱንም እነዚህን ሁለት ተግባራት መፈጸም በሚችል መልኩ ሰርቶ አቅርቧል፡፡ እንደ ምርምር ቡድኑ ሀሳብ ከሆነ ሰው ሰራሽ ኩላሊቱ ታካሚዎች በኩላሊት እጥበት ምክንያት ከሚመጣ የስነ-ልቦና ጫና ያላቅቃቸዋል፡፡
መሳሪያው በራሱ በታካሚው የደም ግፊት ብቻ ታግዞ የሚሰራ ሲሆን ምንም አይነት የደም ማቅተጠኛም ሆነ ሌላ መድሀኒት እንደማያስፈልገው ታውቋል፡፡
ለኩላሊት ታካሚዎች የሚሰጠው የኩላሊት እጥበትም ሆነ በበጎ ፈቃደኞች የሚለገሱ ኩላሊቶች ንቅለ ተከላ ከፍኛ የሆነ ተጓዳኝ ችግር የሚያስከትሉ በመሆኑ ይህኛው መንገድ የተሸለ የታካሚዎችን ጤና የመመለስ ብቃት እንዳለው ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ technology.org
ተጨማሪ ንባብ https://www.technology.org/2021/09/10/the-kidney-project-successfully-tests-a-prototype-bioartificial-kidney/?fbclid=IwAR36ufygumCzP0_x-K1NkXlBlzFjrSPSK2tB12yeeIDK170jih7ab7iKFJ4

Technology Org
The Kidney Project successfully tests a prototype bioartificial kidney
The Kidney Project’s implantable bioartificial kidney, one that promises to free kidney disease patients from dialysis machines and transplant waiting lists, took another big step toward becoming reality, earning a $650,000 prize from KidneyX for its first…
የ6 ዓመቱ ህጻን በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን በጊነስ የአለም ሪከርድ ተመዝግቧል
========================
አይቢኤም በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት የስልጠና ኔትወርክ ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጣናዎችን ለተከታታይ ወራት የወሰደው የ6 ዓመቱ ህጻን ካታሪያ ለትምህርቱ በነበረው ፈጣን አቀባበል እና በቤተሰቦቹ እገዛ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ የአይቢኤም ብሎግ ፖስት እንደዘገበው ታዳጊው ድርጅቱ በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት የስልጠና አምስት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን አጠናቆ በመማር ፓይተን በተባለው የኮምፒተር ፕሮግራም የሰርተፍኬት ዲግሪ ሊያገኝ ችሏል፡፡
በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ሊሚገኙና የኮምፒውተር ፕሮግራም ለመማር የሚፍለጉ ሰዎች በሚሰታፉበት በዚህ የአይቢኤም የትምህርት እድል ላይ የተሳተፈው ይህ ታዳጊ በተለይም የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የትምህርት ዘርፍ ላይ ለመስራት የሚያስችለውን የኮምፒውተር ፕሮግራም እንዳጠና የአይቢኤም ብሎግ ፖስት ዘግቧል፡፡ እንግሊዝ ውስጥ በምትገኝው ኖርዝሃምፕተን የተወለደው ካታሪያ ብዙ ወራትን ወሰዶ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን በጊነስ የአለም ሪከርድ ስሙ ሊመዘግብ ችሏል፡፡
ታዳጊው በቤተሰቦቹ የተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ እና የተሰጠው የትምህርት እድል ለዚህ አንዳበቃው የተናገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የኮዲንግ ትምህርትን እንደመዝናኛ በመውሰድ ስልጠናዎቹን ያለመሰልቸት መማሩ ለጥሩ ውጤት እንዳበቃው አስረድቷል፡፡ ሌሎች ታዳጊ ልጆች የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጠናዎችን በሚወስውዱበት ሰዓት ራሳቸውን እያዝናኑ ሊሚሩ እንደሚገባ የሚያስረዳው ታዳጊው ካታሪያ ወደፊትም በኮግኒቲቭ የኮምፒውቲንግ መስክ ላይ ትልልቅ ስራዎችን መስራት እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡
በአይቢኤም የሚያዘጋጀው የ Developer Skills Network ፕሮግራም የተለያዩ የኮምፒውተር ፕሮግራም ክህሎቶች ለተማሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈላጊዎች እና አነስተኛ ንግዶች ከመላው ዓለም ከሚገኙ መንግስታት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር በነጻ የኦንላይን ስልጠናዎችን ወይም ትምህርቶችን የሚሰጥ ሲሆን ፕሮግራሞችን ተከታትሎ ለጨረሰ ሰው የምስክር ወረቀቶች እና ወሳኝ የኮምፒውተር ክህሎቶችን እንዲያገኙ የሚግዝ ነው።
https://interestingengineering.com/6-year-old-becomes-the-youngest-ai-programmer-to-beat-covid-19-boredom

Interesting Engineering
6-Year-Old Becomes the Youngest AI Programmer to Beat COVID-19 Boredom
The young man's parents helped him on his path by providing educational resources, a laptop and an internet connection.
የሰው እንባ እና ሽንትን በመጠቀም ማርስ ላይ ቤት መስራት ይቻላል ተባለ
==============
የማንቼስተር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የማርስን አፈር ወደፊት በፕላኔቷ ላይ ሊሰሩ ለሚታሰቡ ህንፃዎች ብቁ ያደርግ ዘንድ የሰው ልጅ ደም፣ ሽንት፣ ላብ ብሎም እንባን ከማርስ ወይም ጨረቃ አቧራ ጋር ማዋሀድ እንደሚቻል ገለፁ፡፡ ውህዱ ልክ እንደ ተለምዶው አርማታ ሁሉ በ3ዲ ቴክኖሎጂ ወይም በሌላ አማካኝነት ለሚገነቡ ህንፃዎች ግብዓት የሚሆን ጠንካራ ማጣበቂያን ሊሰጥ እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡ ይህም በሌላ አነጋገር ወደ ስፍራው የሚያመሩ የህዋ ተመራማሪዎች ቤታቸውን በራሳቸው ደም፣ ሽንት፣ ላብ እና እንባ መገንባት አለባቸው እንደማለት ነው፡፡
ተመራማሪዎች እንከዛሬ ድረስ በማርስ ላይ አርማታ መሰል ነገርን መስጠት የሚችል ጠንካራ ቴክኖሎጂን ይዘው ለመምጣት ሲጥሩ መቆየታቸውን የሚያወሱት የጥናቱ ተሳታፊ አለድ ሮበርትስ መልሱ ከራሳችን ሰውነት ሊወጣ መቻሉን ግን ብዙም አስበነው እንደማናውቅ ይጠቅሳሉ፡፡ በጥናቱ ላይ እንደተቀመጠውም እንደ ኢን ቪኖ ባይንደር ያሉ በሰው ልጅ ደም ውስጥ የሚገኙትን ለየት ያሉ ፕሮቲኖችን በመጠቀም የማርስን አፈር ወደ አርማታነት መቀየር ይቻላል፡፡ ከሽንት የሚገኘው በናይትሮጅን የተሞላ ግብዓት በበኩሉ ይህን ቁስ ይበልጥ የሚያጠነክረው ይሆናል፡፡
ተመራማሪዎቹ “አስትሮክሪት” ብለው የሰየሙትን ይህን አርማታ በመጠቀም ህንፃውን በ3ዲ ህትመት አማካኝነት በማርስ ምድር ላይ መስራት እንደሚቻል ጠቅሰዋል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ አስትሮክሪት ከተለምዶው አርማታ የሚስተካከል ጫናን የመቋቋም ጥንካሬ ያለው ነው፡፡ ታድያ በስሌታቸው መሰረት 6 የህዋ ተመራማሪዎች በሁለት ዓመታት የማርስ ቆይታቸው ብቻ 500 ኪ.ግ የሚመዝን ግብዓትን መስጠት የሚችሉ ሲሆን ይህም ወደ ስፍራው ለሚያመሩ ተጨማሪ የህዋ ተመራማሪዎች መኖርያ ሊሆን የሚችል ቤትን ማቆም ይችላል፡፡
ተመራማሪዎች በማርስ ላይ ህንፃን ለመገንባት የሚያስችል ለየት ያለ ሀሳብ ይዘው ሲመጡ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ተመራማሪዎች ከምድር ውጪ ባሉት ስፍራዎች ላይ እንደ ሽንት እና እንጉዳይ ያሉ ግብዓቶችን ለግንባታ የመጠቀም ሀሳብን ሲያንሸራሽሩ ነበር፡፡
ደምን ለማጣበቂያነት መጠቀሙም ቢሆን አዲስ ግኝት አይደለም፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በመካከለኛው ዘመን የደም ፕሮቲኖች ባላቸው የማጣበቅ አቅም ሳብያ የሰው ልጆች የእንስሳትን ደም ለማጣበቂያነት ተጠቅመው ህንፃ ሲገነቡ ቆይተዋል፡፡
ምንጭ፤ ፊውቸሪዝም
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/mars-base-astronaut-blood

Futurism
Scientists Suggest Mixing "Astronaut Blood" With Mars Dust to Create Horrific Shelters
Scientists at The University of Manchester have come up with a macabre new way to turn Martian soil into a stronger material: human blood, sweat, and tears.
ከድምጽ ሞገድ የሚፈጥን ድሮን ማርስ ላይ
*****************************
የቻይና ተመራማሪዎች ከድምጽ ሞገድ በተሻለ ፍጥነት የሚበር ድሮን በመስራት ላይ መሆናቸው ተነገረ፡፡ ድሮኑ ከድምጽ ሞገድ 5 እጥፍ በሚበልጥ ፍጥነት መብረር የሚችል ነው ተብሏል፡፡ የመረጃ ምጫችን የደቡብ ቻይና ሞርኒንግ ፖስትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ድሮኑ 1,100 ፓውንድ ክብደት የሚኖረው ሲሆን በ5,000 ሜትር ከፍታ ላይ መብረር የሚችል ነው ተብሏል፡፡
ድሮኑን በመስራት ላይ ያለው የምርምር ቡድን ተመራማሪ የሆኑት የቤይሃንግ ዩኒቨርሲቲው ዡ ዡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በረራ (hypersonic flight) ማርስ ላይ ለማድረግ ቢያንስ 30 ዓመታት ይስፈልጋል ያሉ ሲሆን የድሮኑም ጉዳይ ተመሳሳይና ገና በጅማሮ ላይ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የሚሰሩት ድሮን ከድምጽ ሞገድ 5 እጥፍ በሆነ ፍጥነት መብረር የሚችለው ማርስ ላይ ወይም ምድር ላይ መሆኑን ማረጋገጫ መስጠት አልቻሉም፡፡ እንደሚታወቀው የድምጽ ሞገድ ምድራችን ላይ በሰዓት 1,223 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን ማርስ ላይ ደግሞ 869 ኪሎ ሜትር በሰዓት መጓዝ ይችላል፡፡
የሀይፐርሶኒክ ድሮኑ ዋና አላማም በማርስ ላይ ይሰፍራል ተብሎ ለሚጠበቀው ማህበረሰብ የመጓጓዣ አገልግሎት ለመስጠት ነው፡፡ በቀይዋ ፕላኔት ሰዎች በብዛት እና ሰፊ ቦታዎችን ሸፍነው መስፈር ሲጀምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ ለመንቀሳቀስ ድሮኑ ያግዛቸዋል፡፡ በተጨማሪም ድሮኑ ከናሳዋ ኢንጅኒዩቲ ድሮን የተሻለ የማርስ ላይ አሰሳ መስራት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ድሮኑ ተሰርቶ ሲያልቅ በማግኒዚየም አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ሲሆን ይህም የማርስ ከባቢ አየር 96 በመቶው በካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተሸፈነ በመሆኑና ማግኒዢየሙን በቀላሉ እንዲቀጣጠል የሚያደርገው በመሆኑ ነው፡፡ ቻይና ፈጣኑን ድሮን በ2045 ወደ ማርስ ለማምጠቅ አቅዳ እየሰራች እንደሆነም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ምንጭ futurism
ተጨማሪ ንባብ https://futurism.com/the-byte/china-mars-drone-faster-sound?fbclid=IwAR32IqBqVZCGp2mhOQKNP-vbVdnah2ip60QRlFA_y8yL7Ys3qWAKaVulKGc

Chinese Scientists Working on Mars Drone That Flies Faster Than Sound
A team of Chinese scientists have developed a concept for a Mars drone that weighs 1,100 pounds and could travel at five times the speed of sound.
ከጦርነት ቢሊዮኖችን የሚያተርፉት የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች
===================
ታላላቅ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ሀገሪቱ የመስከረም 11ዱን ሽብር ጥቃት ተከትሎ ከመጣውና አሜሪካን ሽብርተኝነትን የመዋጋት (War On Terror) ብላ ከሰየመችው ጦርነት በርካታ ቢሊዮኖን ዶላሮችን ማግኘታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ ሪፖርት አመላከተ፡፡ “ቢግ ቴክ ሴልስ ዋር” የተሰኘው ሪፖርቱ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አማዞን፣ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ማይክሮሶፍት እና ትዊተር በዋናነት በጦርነቱ ላይ ያተኮሩ ትላልቅ ኮንትራቶችን ከመንግስት ወስደው ሲሰሩ እንደነበር ገልጿል፡፡
የአሜሪካን ጦር ኃይል እና ስለላ ተቋማት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጉዜ ወደ ዲጂታል እየተለወጠ መምጣቱን ተከትሎ በክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ጂፒኤስ ሶፍትዌሮች ረገድ ፍላጎታቸውም እየጨመረ ቆይቷል፡፡ የመከላከያ ቢሮውን እንኳን ብናይ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባደረገው ስምምነት 43.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪን አውጥቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ ከሚያወጡት መካከል ከፊት የሚቀመጡት አምስቱ ተቋማት ሀገሪቱ ያወጀችው ይህን ዓለም አቀፍ ጦርነት ተከትለው የተመሰረቱ አልያም ከውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፡
በቅርቡ አማዞን እና ማይክሮሶፍት የነዚህ ስምምነቶች ቀዳሚ ተጠቃሚ ወደ መሆን የተሸጋገሩ ሲሆን ከ2015 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ አማዞን 5 ማይክሮሶፍት ደግሞ 8 ያህል ትላልቅ ኮንትራቶችን ከተቋማቱ ወስደዋል፡፡ ማይክሮሶፍት በተለይ በፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የሚያገኛቸው ከመከላከያ ጋር የተያያዙ መንግስታዊ ኮንትራቶች በይበልጥ አድገውለት ነበር፡፡ በሌላ መልኩ ግን ለወትሮ የጦር ኃይሉ ደንበኛ የነበሩት የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የኮንትራት ድርሻ በማሽቆልቆል ላይ ነው፡፡
መረጃው አሜሪካዊያን መንግስታቸው ውል የሚገባባቸው ኮንትራቶችን እንዲያጋልጡ በሚጠይቅ የበይነ መረብ መንገድ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ታድያ መረጃዎቹ እስካሁን ማግኘት የተቻለው መንግስት ለህዝብ ይፋ ያደረጋቸው ስምምነቶች ብቻ እንደመሆኑ እውነተኛው የኮንትራቶቹ መጠን ከተጠቀሰውም በላይ ላቅ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-big-tech-billions-war-terror.html

Tech Xplore
Big Tech made billions during 'war on terror': report
Tech giants made billions through contracts with the US military and other government agencies during the so-called "war on terror", according to a report released ahead of the 20th anniversary of 9/11.
የዋይ-ቴክ ስታርታፕ ጠቃሚ ፈጠራዎች
=================
ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ዲጂታል መፍትሄዎችንና አሰራሮችን በማቅረብ የሚሰራው ዋይ-ቴክ (Y-Tech) በኢትዮጵያውያን የአኗኗር ሂደት ህይወትን ቀላል የሚደርጉ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን እየሰራ የሚቀርብ በወጣቶች የተመሰረተ ጀማሪ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው፡፡ ስታረታፑ በሜካኒካልና በሶፍትዌር የአሰራር ሂደቶች በመታገዝ በጤና ዘርፉ፣ በቱሪዝም መስክ እና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማቅርብ ላይ ነው፡፡
በሰባት የስራ ክፍሎች ተከፋፍሎ የተለያዩ ጠቃሚ ፈጠራዎችን በማበልፀግ ላይ ያለው ይህ ስታርታፕ በዋናነት በውሃ ማጣሪያ የቴክኖሎጂ አይነቶች እና የቬንትሌተር መሳሪዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሰራቸው የፕሮታይፕ ፈጠራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ጥቅም ሊሰጥ የሚችለው ኢትዮ ሎኬት የተሰኘው የዲጂታል ፕላትፎረም ሌላው እጅግ ጠቃሚ ፈጠራ ነው፡፡
በተለይም ዋይ-ቴክ ስታርታፕ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ኢትዮ ሎኬት የተባለው የዲጂታል ፕላትፎረም በቀላል ሂደት ተጠቃሚዎች ቦታዎችን እና መረጃዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ እንዲያገኙ የሚያግዝ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም በመሆኑ ማንኛውም የንግድ ድርጅቶች እና ተቋማት አገልግሎታቸውን ወይም ምርቶቻቸውን በኦንላይን እንዲያስተዋውቁ እና ዲጂታል ፕሮፋይል እንዲኖራቸውም የሚያስችል ነው፡፡
ዝርዝሩን ከቪዲዮው ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=Bg4oQg5Cl14

YouTube
#ታዳጊ የፈጠራ ባለሙያዎች#
#የምንፈልገውን ነገር በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል የፈጠራ ውጤት ነው፡፡#
ሰሜን ዋልታ በከፍተኛ ፍጥነት አቅጣጫውን እየለወጠ ነው
==============
የምድራችን ዋልታዎች ብዙ እንስሳት ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ተፈጥሮአዊ እገዛን የሚሰጡና እንደ ቴሌቪዥን፣ የአየር ትንበያ እና ኮምዩኒኬሽን ላሉ የሰው ልጅ ቴክኖሎጂያዊ ግኝቶችም መሰረት ናቸው፡፡ ታድያ አሁን ላይ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የሰሜን ዋልታ አሁን ካለበት የካናዳ አርክቲክ ክፍል ወደ ሳይቤሪያ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነና ይህ እንቅስቃሴውም አስጊ በሆነ ሁኔታ ፍጥነቱን እየጨመረ መሆኑን አዲስ የወጣ ምርምር ይፋ አድርገኋል፡፡ በዚህም የሰሜን ዋልታ የሚንቀሳቀስበት ፍጥነት በዓመት ወደ 48 ኪ.ሜ አድጓል፡፡
የምድራችን ዋልታዎች መገኛቸውን ሲቀይሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ምድራችን ባለፉት 2.6 ሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ለ10 ጊዜያት የዋልታዎቿ መገኛ የተለወጠ ሲሆን የቅርብ የሚባለው ለውጥ የተከሰተውም የዛሬ 780 ሺህ ዓመታት ገደማ ነበር፡፡
እስካሁን እነዚህን ለውጦች በእርግጠኝነት ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን የዋልታዎች ለውጥ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ ተፅዕኖውን እንደሚያሳድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ ከነዚህ ተፅዕኖዎች መካከል ምድራችንን እራሷን ከፀሐይ እና ኮስሚክ ሬዮች ከሚመጡባት በቻርጅ የተሞሉ ቅንጣቶች (charged particles) እራሷን የምትጠብቅበትን ስርዓት ሊያዳክሙት ይችላሉ የሚለው ነው፡፡
በሌላ መልኩ አንዳንድ የስነ ምድር ምሁራን መሰል የዋልታ ለውጦችን ምድር ላይ ከተከሰቱ መጠነ ሰፊ የህይወት ድምሰሳዎች (mass extinctions) ጋር ሲያያይዟቸው ሌሎች በበኩላቸው ቅድመ የሰው ልጅ ዝርያዎች የተለያዩ የዋልታ ለውጦችን ቢያስተናግዱም ለውጡን ተቋቁመው መቆየታቸውን በመጥቀስ ይሞግታሉ፡፡ የሆነው ሆኖ የዋልታ ለውጦቹ የሚያመጡትን ተፅዕንዖ ሙሉ ለሙሉ መረዳት ባይቻልም ለውጦቹ የሚመጡበት ፍጥነት ግን ተፅዕኖዋቸውን እንደሚወስነው ይነገራል፡፡ ለአብነት ዋልታዎቹ አቅጣጫቸውን የሚለውጡት ዝግ ባለ ፍጥነት ከሆነ ተፈጥሮም ሆነ የሰው ልጆች ከለውጡ ጋር በተሻለ እራሳቸውን እያላመዱ መሄድ ይችላሉ፡፡
መንስኤያቸውን በተመለከተ የዋልታ ለውጦች ምናልባትም የዛሬ 4.5 ቢሊዮን ዓመት ከምድር ጋር በተጋጨችው ቴአ በተሰኘች ቀደምት ፕላኔት አማካኝነት የሚከሰቱ ሊሆኑ ይችላል የሚል ግምት በተመራማሪዎች ዘንድ አለ፡፡ የዚህች ጥንታዊ ፕላኔት ከምድር ጋር ስትጋጭ ስብርባሪዋ ለጨረቃ መፈጠር ምክንያትም ሆኗል፡፡ እስካሁን የዚህች ፕላኔት የተቀረው ክፍል የት እንዳለ ባይታወቅም አንዳንድ ተመራማሪዎች ግን ምድር ውስጥ ተቀብሮ ስለመቅረቱ ይናገራሉ፡፡
በቅርብ የወጡ የስነ-ምድር ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም የፕላኔቷ ቅሪት ምናልባትም ከዓለማችን በርዝመቱ ቀዳሚ ከሆነው የኤቨረስት ተራራ ሁለት እጥፍ የሚገዝፉ ሁለት አለቶች ሆነውና ከተቀረው የማንትል ክፍልም በይበልጥ ጠቅጠቅ እና ሞቅ ብለው መቀመጣቸውን ነው፡፡ እነዚህ አለቶች ታድያ የምድራችን ዋልታዎች መነሻ ላይ ጣልቃ በመግባት በደቡባዊ አትላንቲክ በኩል እያዳከሙት ሊሆን ይችላል፡፡
ምንጭ፤ ስፑቲኒክ
ለተጨማሪ፤ https://sputniknews.com/20210915/earths-magnetic-field-may-be-reversing-due-to-remains-of-ancient-planet-scientists-warn-1089094074.html

Sputnik International
Earth's Magnetic Field May Be Reversing Due to Remains of Ancient Planet, Scientists Warn
Our planet's magnetic field is something that naturally helps many animals to navigate, while also serving as a base for a huge amount of technological advances by humanity, such as television broadcasting, weather forecasting, and...
የአነስተኛ ካልኩሌተር ፈጣሪ ክላይቭ ሲንክላር በ81 ዓመታቸው አረፉ
==========================
ዘርፉ ብዙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ እና በመጀመሪያዎቹ የኮምፒውቲንግ ስራዎች ላይ ትልልቅ ግኝቶችን ያበረከቱት ሰር ክላይቭ ሲንክላር በ81 ዓመታቸው ማረፋቸው ተነግሯል፡፡ እኝህ የቴክኖሎጂ ሰው አሁን አለም በስፋት ለሚጠቀምባቸው የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች መሰረት የሆኑ የመጀመሪያዎቹን የቤት ወይም የግል ኮምፒውተሮች በማበልፀግ ስራ ላይ ትልቅ ሚና የነበራቸው ሲሆን በ1970ዎቹ ይበልጥ ዘምነው ወደተጠቃሚዎች መቅረብ በጀመሩት አነስተኛ ወይም ፖኬት የካልኩሌተር ፈጠራዎች ላይ ደግሞ ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
ሰር ክላይቭ ሲንክላር እንደአውሮፓውያኑ በ1980ዎቹ ZX80 የተባለውን የግል ኮምፒውተር መስራት በጀመሩበት አመታት የግል ኮምፒውተር ፈጠራዎች ብዙም ያልተስፋፉበት ዘመን ስለነበር የክላይቭ ሲንክላር ስራዎች ኋላ ላይ ይበልጥ እየጎለበቱ ለመጡት የላፕቶፕ ኮምፒውተር ፈጠራዎች ትልቅ መሰርት የጣሉ ሆነው አልፈዋል፡፡ ሰር ክላይቭ ሲንክላር በቋቋሙት ድርጀት ይበልጥ እየተሸሻለ ሲቀርብ የነበረው ZX ስፔክትረም ኮምፒውተር ለግል ኮምፒውተሮች ማደግ ከነበረው ሚና በተጨማሪ ለዘመናውያኑ የቪዲዮ ጌም ፈጠራዎች ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ ግኝት እንደነበር ይነገራል፡፡
እንደአውሮፓውያኑ በ1940 በእንግሊዝ ሃገር የተወለዱት ሰር ክላይቭ ሲንክላር እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ደረስ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን በተለይም ባለሶሰት እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈጠራዎች እና የቴሌቭዥን ምርት ላይ የነበራቸው ተሳትፎ በጉልህ የሚገለፅ ነው፡፡ ለብዙ አመታት ይዟቸው በነበረው ካንሰር የህክምና እገዛ ሲደረግላቸው ቆይተው በ81 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ሰር ክላይቭ ሲንክላር ዘርፉ ብዙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ እና በመጀመሪያዎቹ የኮምፒውቲንግ ስራዎች ላይ በነበራቸው ትልቅ አሻራ በትውልድ የሚታወሱ ይሆናል፡፡
https://www.independent.co.uk/news/uk/home-news/clive-sinclair-dead-spectrum-c5-b1921670.html

The Independent
Tech pioneer Sir Clive Sinclair dies aged 81
Technology pioneer Sir Clive Sinclair has died at the age of 81, his family have confirmed.
ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች
********************************************************************
በቻይና ታሪክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ ያደረጉትን የህዋ ላይ ቆይታ አጠናቀው ወደ ምድር መመለሳቸው ተነገረ፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች ቲያንጎንግ በተሰኘው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር ጣቢያ ለ90 ቀናት ያክል ቆይተው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ከሰሩ በኋላ በሙሉ ጤንነት ወደ ምድር ተመልሰዋል፡፡ በቆይታቸውም የህዋ ላይ እንቅስቃሴ (spacewalks) እና የተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን አካሂደዋል፡፡
12ቱም ተመራማሪዎች ወደቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት ለ2 ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ተቀምጠው ክትትል እንደሚደረግላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ተልዕኮ እያደገ የመጣው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር አካል ሲሆን ሀገሪቱ ማርስ ላይ የአሰሳ ሮቨር ማምጠቅና ወደ ጨረቃም የተለያዩ የምርምር ግብዓቶችን መላኳ በዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አመላካች ነው፡፡
ቲያንጎንግ ሰማያዊ ስፍራ ("heavenly palace") ማለት ሲሆን ለ10 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተሰራ የህዋ ላይ የምርምር ጣቢያ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ 3ቱም ከሀገሪቱ የመከላከያ ሀይል የተገኙ ሲሆኑ አንደኛው ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የህዋ ላይ ጉዞን በማድረግ ልምድ ያለው መሆኑ ተነግሯል፡፡
የቻይና ስፔስ ኤጀንሲ በቀጣዩ አመት ብቻ 11 የህዋ ላይ ጉዞ ያቀደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ተመራማሪዎችን ይዘው የሚጓዙ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም 70 ቶን የሚደርሱ ሁለት የቤተ ሙከራ መገንቢያ ቁሶችም እንደሚላኩ ታውቋል፡፡ ቻይና የህዋ ላይ ምርምሯን የመከላከያ ሀይሏን መሰረት ባደረገ መልኩ እያከናወነች ትገኛለች፡፡
ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-09-chinese-astronauts-earth-day-mission.html

phys.org
Chinese astronauts return to Earth after 90-day mission
Three Chinese astronauts returned to Earth Friday after completing the country's longest-ever crewed mission, the latest landmark in Beijing's drive to become a major space power.